ተሳተፍ!
ይህ ሥዕላዊ አነስተኛ መጽሐፍ ቅዱስ በሁሉም የዓለም ቋንቋዎች እንዲገኝ ለማድረግ እንፈልጋለን፣ አንተም መርዳት ትችላለህ! ይህ የማይቻል አይደለም፤ መላው የክርስቶስ አካል ይህን ጽሑፍ ለመተርጐምና ለማሠራጨት አብሮ ሊሠራ ይችላል ብለን እናስባለን፡፡
በነጻ ለሌሎች አካፍል
በተቻለ መጠን ያለ ገደብ የዚህን መጽሐፍ ብዙ ቅጂዎች እንደፈለግኸው ስጥ፡፡ በቊጥር የሚሠሩ /ዲጂታል/ እትሞች ሁሉ በዓምደ መረብ /ኢንተርኔት/ በነጻ ይገኛሉ፣ እየተጠቀምንበት ባለው ግልጽ ፈቃድ ምክንያትም ያለ አበል ክፍያ በማንኛውም የዓለም ክፍል በንግድ መስክ ግልጽ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን ዳግም ማሳተም እንኳ ትችላለህ! በተጨማሪ በ http://openbiblestories.com ፈልግ፡፡
አስፋፋ!
ግልጽ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን በቪዲዮና በሞባይል ስልክ አጠቃቀም በhttp://openbiblestories.com በሌሎች ቋንቋዎች አግኝ፡፡ በድረ ገጽ፣ ግለጽ የመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮችን ወደ ቋንቋህ ለመተርጐም እርዳታ ማግኘት ደግሞ ትችላለህ፡፡