አማርኛ: Unlocked Dynamic Bible

Updated ? hours ago # views See on DCS

ዮሐንስ

ምዕራፍ 1

1 2 3 በመጀመሪያ ቃል ነበር፡፡ ቃልም ከእግዚአብሔር ጋር ነበረ፣ ቃልም እግዚአብሔር ነበር፡፡ 2አንዳች ነገር መፍጠር ከመጀመሩ አስቀድሞ እርሱ ከእግዚአብሔር ጋር ነበር፡፡ 3ሁሉንም ነገር ለመፍጠር የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ ያከናወነው እርሱ ነው፡፡ አዎን፣ የተሰራው ነገር ፍጹም አንዳች ሳይቀር የሰራው በእርሱ ነው! 4 5 ህይወት ሁሉ በቃል ውስጥ ነው፣ ስለዚህ እርሱ ለሁሉም ነገር እና ለእያንዳንዱ ህይወት መስጠት ይችላል፡፡ ቃሉ በእያንዳንዱ ላይና በሁሉም ስፍራ የሚያበራ የእግዚአብሔር ብርሃን ነበር፡፡ 5ይህ ብርሃን በጨለማ ሲያበራ ጨለማው ሊያስወግደው ሞከረ ነገር ግን አልቻለም፡፡ 6 7 8 እግዚአብሔር ስሙ ዮሐንስ የተባለ ሰው ላከ፡፡ 7እርሱ ስለ ብርሃን ለሰዎች ሊመሰክር መጣ፡፡ የተናገረው እውነት ነበር፣ እያንዳንዱ ያምን ዘንድ እርሱ ያንን መልዕክት አወጀ፡፡ 8ዮሐንስ ራሱ ያን ብርሃን አልነበረም፣ ነገር ግን ስለዚያ ብርሃን ለሰዎች ለመናገር መጣ፡፡ 9 በእያንዳንዱ ላይ የሚያበራ እውነተኛ ብርሃን ይህ ነበር፣ እናም ያብርሃን ወደ ዓለም እየመጣ ነበር፡፡ 10 11 ቃል በዓለም ውስጥ ነበር፣ እርሱ ዓለምን ቢሰራም እንኳን፣ እርሱ ማን እንደነበር ከዓለም ህዝብ ማንም አላወቀም፡፡ 11የእርሱ ወደ ሆነ ዓለምና፣ ወደ ራሱ ሰዎች ወደ አይሁዶች ቢመጣም እንኳን አልተቀበሉትም፡፡ 12 13 ነገር ግን እርሱን ወደ ህይወታቸው በተቀበሉና በእርሱ ላመኑ ሁሉ፣ ለእነርሱ የእግዚአብሔር ልጆች የመሆን መብት ሰጣቸው፡፡ 13እነዚህ ከእግዚአብሔር የተወለዱ ልጆች ናቸው፡፡ በተለመደው የሰው አወላለድ ወይም ከሰው ፍላጎት ወይም ምርጫ በመነሳት ወይም ከባል አባት የመሆን ፍላጎት ምክንያት የተወለዱ አይደሉም፡፡ 14 15 አሁን ቃል ተጨባጭ ሰው ሆኖ እኛ ለጊዜው በምንኖርበት በዚህ ኖረ፡፡ እግዚአብሔር እኛን በታማኝነት መወደዱንና ስለ እርሱ እውነት ያስተማረንን አንድና ብቸኛ የአብ ልጅ ባህሪ የሆነውን ድንቅና አስገራሚ ባህሪውን ሲገልጽ አየነው፡፡ 15አንድ ቀን አጥማቂው ዮሐንስ ስለ ቃል ለሰዎች ይናገር ነበር፣ በዚያን ሰዓት ኢየሱስ ወደ እርሱ መጣ፡፡ ዮሐንስ በዙሪያው ለነበሩ ሰዎች ጮህ ብሎ እንዲህ በማለት ተናገረ፣ “ከእኔ በኋላ ከእኔ ይልቅ እጅግ ጠቃሚ የሆነ አንድ ሰው ይመጣል በማለት ነግሬያችሁ ነበር፡፡ ከእኔ እጅግ አስቀድሞ ነበረ፣ በዘላለም ዘመናት፣ እኔ ከመወለዴ አስቀድሞ ነበረ፡፡ ይህ ሰው እነሆ በዚህ! ስለ እርሱ ስናገርለት የነበረው ሰው ይህ ነው!” 16 17 18 እኛ ሁላችንም እርሱ ከሰራው ብዙ ተጠቅመናል፡፡ እርሱ ደግሞ ደጋግሞ በጣም በደግነት ለእኛ ሰርቷልና፡፡ 17ሙሴ የእግዚአብሔርን ህጎች ለአይሁድ ህዝብ አውጇል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ስለ እግዚአብሔር እውነቱን በቸርነት አስተምሮናል፡፡ 18ማንም እግዚአብሔርን አይቶት አያውቅም፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔር አንዲያ ልጅ፣ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁለጊዜ ለአብ ቅርብ የሆነው እርሱ እግዚአብሔርን እንድናውቀው አድርጓል፡፡ 19 20 21 ዮሐንስ የሰጠው ምስክርነት ይህ ነው፡፡ አይሁዶች ከኢየሩሳሌም ካህናትንና ሌዋዊያንን ላኩ፤ ዮሐንስን “አንተ ማን ነህ?” ብለው ለመጠየቅ መጡ፡፡ 20ስለዚህም ዮሐንስ ለእነርሱ ምስክርነቱን እንዲህ ሲል ሰጠ፣ “እኔ ክርስቶስ አይደለሁም!” 21ከዚያ እነርሱ እንዲህ ብለው ጠየቁት፣ “ስለ ራስህ ምን ትላለህ? ኤሊያስ ነህን?” እርሱ “አይደለሁም” አለ፡፡ እነርሱ እንደገና ጠየቁት፣ “ነቢያት ይመጣል ያሉት ነቢዩ ነህ?” ዮሐንስ፣ “አይደለም” ሲል መለሰ፡፡ 22 23 ስለዚህ አንድ ጊዜ በተጨማሪ ጠየቁት፣ “ታዲያ ማን ነኝ ትላለህ? ወደ ላኩን ተመልሰን ሄደን መመለስ እንድንችል ንገረን፡፡ ስለ ራስህ ምን ትላለህ?” 23እርሱ እንዲህ ሲል መለሰ፣ “ነቢዩ ኢሳይያስ ‘ወደ እኛ እንዲመጣ ለጌታ መንገዱን አቅኑ፡፡’ ሲል እንደጻፈው እኔ በበረሃ የሚጮኸው ነኝ፡፡” 24 25 ከእነዚህ ሰዎች አንዳንዶቹ ከፈሪሳውያን ዘንድ ወደ ዮሐንስ መጡ፡፡ 25እንዲህ ብለውም ጠየቁት፣ “አንተ ክርስቶስ ወይም ኤሊያስን ወይም ነቢዩን አለመሆንህን እስከተናገርክ ድረስ ታዲያ ለምን ታጠምቃለህ?” 26 27 28 ዮሐንስ እንዲህ ሲል መለሰ፣ “እኔ ሰዎችን በውሃ አጠምቃለሁ፣ ነገር ግን አሁን እናንተ የማታውቁት በመካከላችሁ የቆመ አንድ ሰው አለ፡፡ 27እርሱ ከእኔ በኋላ ይመጣል፣ ነገር ግን እኔ የእርሱን የጫማ መሳሪያዎች ለመፍታት የምበቃ አይደለሁም፡፡ 28እነዚህ ነገሮች የሆኑት ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተምስራቅ በኩል በቢታኒያ መንደር ነው፡፡ ዮሐንስ ያጠምቅ የነበረው በዚያ ስፍራ ነው፡፡ 29 30 31 ዮሐንስ በማግስቱ ኢየሱስ ወደ እርሱ ሲመጣ አየ፡፡ እርሱም ለህዝቡ እንዲህ አለ “ተመልከቱ! የዓለምን ሀጢአት ለማስወገድ የራሱን ህይወት መስዋዕት አድርጎ የሚሰጥ የእግዚአብሔር በግ፡፡ 30‘ከእኔ ይበልጥ አስፈላጊ የሆነ ከእኔ በኋላ የሚመጣ፣ ምክንያቱም ከእኔ በፊት እጅግ ቀድሞ የነበረ፣ ዘላለማዊ፣ እኔ ከመወለዴ በፊት የነበረ ነው፡፡’ ያልኩት እርሱ ነው፡፡ 31በመጀመሪያ አላውቀውም ነበር፣ ነገር ግን አሁን እርሱ ማን እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ የእኔ ስራ የተፀፀቱትንና ከሀጢአታቸው የተመለሱትን መጥቼ በውሃ ማጥመቅ ነበር፡፡ እኔ እርሱ ማን እንደሆነ የእስራኤል ሰዎች እንዲያውቁ እፈልጋለሁ፡፡ 32 33 34 ምን እንደተመለከተ ለእኛ መናገር ይህ የዮሐንስ ሥራ ነበር፡፡ እሱ እንዲህ ተናገረ፣ “የእግዚአብሔር መንፈስ በእርግብ መልክ ከሰማይ ሲወርድ አየሁ፡፡ መንፈሱ ወደ ታች መጥቶ በኢየሱስ ላይ ኖረ፡፡ 33በመጀመሪያ እኔ ራሴ አላወኩትም፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ከሀጢአተኝነት መንገዳቸው መመለስ እንፈልጋለን የሚሉ ሰዎችን በውሃ እንዳጠምቅ ላከኝ፡፡ እግዚአብሔር እንዲህ ብሎ ነገረኝ፣ ‘መንፈሴ ሲወርድበትና በእርሱ ላይ ሲኖርበት የምታይበት ሰው እርሱ ሁላችሁንም በመንፈስ ቅዱስ የሚያጠምቀው ይሆናል፡፡’ 34እኔ አይቻለሁ እሱ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ለእናንተ በእርግጠኝነት እመሰክራለሁ፡፡” 35 36 አጥማቂው ዮሐንስ በቀጣዩ ቀን እንደገና ከሁለቱ ደቀመዛሙርቱ ጋር በተመሳሳይ ቦታ ነበር፡፡ 36ኢየሱስ ሲያልፍ ተመልክቶ እንዲህ አለ፣ “ተመልከቱ! እነሆ የእግዚአብሔር በግ፣ እግዚአብሔር የእሱን ሕይወት አሳልፎ እንዲሰጥ የላከው ሰው፣ በእስራኤላውያን ሰዎች ስለ ሀጢአታቸው ክፍያ እንደ ጠቦት ይታረዳል! 37 38 39 ሁለቱ የዮሐንስ ደቀ መዛሙርት፣ ዮሐንስን በሰሙት ጊዜ፣ ዮሐንስን ትተው እርሱን ተከተሉት፤ 38ኢየሱስ ወደ ኋላ ዞር አለና እርሱን ሲከተሉት አያቸው፣ እናም እንዲህ ብሎ ጠየቃቸው፣ “ምን እየተመለከታችሁ ነው?’ እነርሱም እንዲህ አሉት፣ “ረቢ (‘መምህር’ ማለት ነው) የት እንደምትኖር ንገረን?” 39እርሱ ሲመልስ፣ “ከእኔ ጋር ኑና ታያላችሁ!” አላቸው፡፡ ስለዚህም መጥተው ኢየሱስ የት እንደሚኖር አዩ፣ እናም በዚያ ቀን ከእርሱ ጋር ቆዩ፣ እየመሸ ነበር፡፡ (ከረፋዱ 10 ሰዓት ነበር፡፡) 40 41 42 ከተከተሉት ሁለት ደቀመዛሙርት የአንዱ ስም እንድርያስ ነበር፤ እርሱ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም ነበር፡፡ 41በመጀመሪያ እንድርያስ ወንድሙን ስምዖንን ሊፈልግ ሄደ፡፡ ሲያገኘው እንዲህ አለ፣ “መሲሁን (‘ክርስቶስ’ ማለት ነው) አገኘነው!” 42እንድርያስ ስምዖንን ወደ ኢየሱስ ወሰደው፡፡ ኢየሱስ በጉጉት ዐይን ወደ ጴጥሮስ እየተመለከተ እንዲህ አለ፣ “አንተ ስምዖን ነህ፡፡ የአባትህ ስም ዮሐንስ ነው፡፡ ኬፋ የሚባል ስም ይሰጥሃል፡፡” ኬፋ የአረማይክ ስም ነው፡፡ ትርጉሙም ‘ጠንካራ አለት’ ማለት ነው፡፡ (በግሪክ ጴጥሮስ ማለት ተመሳሳይ ትርጉም አለው፡፡) 43 44 45 በቀጣዩ ቀን ኢየሱስ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝን ሸለቆ ለመሄድ ወሰነ፡፡ በገሊላ ዙሪያ ወደሚገኝ አካባቢ ሄደና ፊልጶስ የተባለ አንድ ሰው አገኘ፡፡ ኢየሱስ እርሱን እንዲህ አለው፣ “ከእኔ ጋር ና” 44ፊሊጶስ፣ እንድርያስ እና ጴጥሮስ ሁሉም ከቤተሳይዳ (ገሊላ ውስጥ ትገኛለች) ከተማ ነበሩ፡፡ 45ከዚያ ፊሊጶስ ጓደኛውን ናትናኤልን ለመፈለግ ሄደ፡፡ ወደ እርሱ ሲመጣ እንዲህ አለው “ሙሴ ስለ እርሱ የጻፈለትን፣ ክርስቶስን እኛ አግኝተነዋል፡፡ ነቢያት እርሱ እንደሚመጣ ተንብየዋል፡፡ የምንጠብቀው ክርስቶስ እርሱ ኢየሱስ ነው፡፡ እርሱ ከናዝሬት ከተማ ነው የአባቱ ስም ዮሴፍ ነው፡፡ 46 47 48 ናትናኤል እንዲህ ሲል መለሰ፣ “ከናዝሬት? ከናዝሬት መልካም ነገር ይገኛልን?” ፊሊጶስ እንዲህ ሲል መለሰ፣ “ና እና ታያለህ!” 47ኢየሱስ ወደ እርሱ ናትናኤል ሲቃረብ አይቶ፣ እርሱን ከመገናኘቱ አስቀድሞ ናትናኤልን እንዲህ ሲል ገለጸው፣ “ቅን እና መልካም የሆነው እስራኤላዊ ይሄውና! እርሱ ፍፁም ማንንም አታሎ አያውቅም!” 48ናትናኤል እንዲህ ሲል ጠየቀው፣ “እኔ ምን አይት ሰው እንደሆንኩ እንዴት ታውቃለህ? አንተ እኔን አታውቀኝም፡፡” ኢየሱስ፣ “ብቻህን ከበለስ ዛፍ ስር ተቀምጠህ ሳለህ፣ ፊሊጶስ አንተን ከመጥራቱ አስቀድሞ አየሁህ” ሲል መለሰለት፡፡ 49 50 51 ከዚያ ናትናኤል፣ “ረቢ፣ አንተ የእግዚአብሔር ልጅ መሆን አለብህ! አንተ ስንጠብቅህ የቆየነው የእስራኤል ንጉስ ነህ!” በማለት ማመኑን በግልጽ ተናገረ፡፡ 50ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰለት፣ “ከበለስ ዛፍ ስር አየሁህ ስላልህ ብቻ በእኔ አመንክን? ከዚያ እጅግ የሚበልጥ ነገሮችን ስሰራ ታየኛለህ!” 51ከዚያ ኢየሱስ እንዲህ አለው፣ “እኔ እውቱን እየነገርኩህ ነው፡ ከረጅም ዘመን በፊት አባትህ ያዕቆብ እንዳየው አይነት ራዕይ ታያለህ፤ አንድ ቀን ሰማይ ሲከፈት እናም የእግዚአብሔር መላዕክት በእኔ በሰው ልጅ ላይ ሲወጡና ሲወርዱ ታያለህ፡፡”

ምዕራፍ 2

1 2 በሶስተኛው ቀን በገሊላ አካባቢ ቃና ውስጥ የሰርግ ድግስ ነበረ፡፡ የኢየሱስ እናት በዚያ ነበረች፡፡ 2ደጋሾቹ ኢየሱስንና ደቀመዛሙርቱን ጭምር ወደ ሰርጉ ጋብዘው ነበር፡፡ 3 4 5 በሰርጉ ላይ ለተገኙ ወይን አቅርበውላቸው የነበራቸውን ወይን በሙሉ እንግዶቹ ጠጥተውት አልቆ ነበር፡፡ የኢየሱስ እናት ለእርሱ እንዲህ አለችው “ወይን ጠጁ አልቆባቸዋል፡፡” 4ኢየሱስ እንዲህ አላትት “አንቺ ሴት፣ ይህ ከእኔ ጋር ምን የሚያይዘው ነገር አለ? የእኔ በጣም አስፈላጊው ስራ የሚጀምርበት የተመረጠው ጊዜ ገና አልደረሰም፡፡” 5የኢየሱስ እናት ወደ አገልጋዮቹ ዘወር ብላ እንዲህ አለች፤ “እርሱ የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ፡፡” 6 7 8 በዚያ ስፍራ ስድስት ባዶ የድንጋይ ጋኖች ነበሩ፡፡ እንግዶቹና አገልጋዮቹ እጆቸውንና እግሮቻቸውን እንዲታጠቡባቸው፣ እንዲሁም ሌሎች የአይሁድ የመንጻት ሀይማኖታዊ ስርዓትን ለማከናወን ጋኖቹ ውሃ ይዘው ነበር፡፡ እያንዳንዱ ጋን ከ75 እስ 115 ሊትሮች መያዝ ይችላል፡፡ 7ኢየሱስ አገልጋዮቹን እንዲህ አላቸው፣ “ጋኖቹን ውሃ ሙሏቸው!” ስለዚህም ጋኖቹን እስከ አፋቸው ሞሏቸው፡፡ 8ከዚያ እንዲህ አላቸው፣ “አሁን ከአንዱ ጋን ጥቂት ውሃ ቅዱና ወደ ድግሱ ኃላፊ ውሰዱ፡፡” ስለዚህም አገልጋዮቹ ያንን አደረጉ፡፡ 9 10 የድግሱ ኃላፊ ወደ ወይንነት የተቀየረውን ውሃ ቀመሰ፡፡ አገልጋዮቹ የሚያውቁ ቢሆንም እንኳን እርሱ ግን ወይኑ ከየት እንደመጣ አላወቀም፡፡ ስለዚህ ሙሽራውን ወደ ራሱ ጠራውና እንዲህ አለው፡፡ 10“ሁሉም ሰው መጀመሪያ ምርጡን ወይን ያቀርባ፣ ከዚያ በኋላ እንግዶች ብዙ ሲጠጡና ምርጡ ሲያቅ ርካሹን ወይን ያቀርባ፡፡ አንተ ግን ምርጡን ወይን እስከ አሁን አቆይተሃል፡፡” 11 ስለ ኢየሱስ እውነቱን አጉልቶ የሚያሳይ የመጀመሪያው ኢየሱስ የሰራው ተአምራት ያ ነበረ፡፡ ይህን ያደረገው በቃና መንደር በገሊላ አካባቢ ነው፡፡ በዚያ አስደናቂ ነገሮችን ማድረግ እንደሚችል አሳየ፡፡ ስለዚህም ደቀመዛርቱ በእርሱ ላይ እምነት አደረባቸው፡፡ 12 ከዚህ በኋላ ኢየሱስና እናቱ እንዲሁም ወንድሞቹ፣ ከእርሱ ደቀመዛሙርቱ ጋር ወደ ቅፍርናሆም ከተማ ሄደው በዚያ ጥቂት ቀናት ቆዩ፡፡ 13 14 አሁን የአይሁድ ፋሲካ በዓል ተቃርቦ ነበር፡፡ ኢየሱስና የእርሱ ደቀመዛሙርት ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ፡፡14በዚያ በመቅደሱ ቅጽር ግቢ ሰዎች ከብቶችን፣ በጎችን እና እርግቦችን ሲሸጡ አየ፡፡ እንስሳቱ ይሸጡ የነበረው በመቅደስ መስዋዕትን ለሚያቀርቡ ነበር፡፡ እንዲሁም ሰዎች በመቅደስ ተቀምጠው ገንዘብ ሲመነዝሩ አየ፡፡ 15 16 ስለዚህም ኢየሱስ መግረፊያ ከቆዳ ጅራፍ አበጅቶ ከመቅደስ በጎችንና ከብቶችን ለማስወጣት ተጠቀመበት፡፡ የገንዘብ መንዛሪዎችን ጠረጴዛዎች ገለበጠ እንዲሁም ሳንቲሞቻቸውን በመሬት ላይ በተነ፡፡ 16እርግቦችን ይሸጡ የነበሩትን፣ “እነዚህን እርግቦች ከዚህ አውጡ! የአባቴን ቤት የገበያ ስፍራ አታድርጉ!” በማለት አዘዛቸው፡፡ 17 18 19 ይህ በመጽሐፍ አንዱ ደቀመዛሙርቱን ከዘመናት አስቀድሞ፣ “እኔ የአንተን ቤት በጣም እወዳለሁ፣ ኦ ኦምላኬ፣ ለቤትህ እሞታሁ” በማለት የጻፈውን አስታወሳቸው፡፡ 18የአይሁድ መሪዎች፣ “እያደረግህ ያለኸውን ለማድረግ ከእግዚአብሔር ዘንድ የተፈቀደልህ መሆኑን ለማረጋገጥ ለእኛ ምን ተአምር ማሳየት የትችላለህ?” በማለት ጠየቁት፡፡ 19ኢየሱስ፣ “ይህን ቤተመቅደስ አፍርሱት፣ እኔ በሶስት ቀናት መልሼ እገነባዋለሁ፡፡” ብሎ መለሰላቸው፡፡ 20 21 22 “ይህን ቤተመቅደስ በሶስት ቀናት ብቻ ዳግም እገነባዋለሁ እያልክ ነው?” ሲሉ ጠየቁት፡፡ “ይህን ቤተ መቅደስ ለመገንባት አርባ ስድስት አመታት ፈጅቷል፡፡” 21የሆነ ሆኖ፣ ኢየሱስ ቤተ መቅደስ ሲል የራሱን አካል ማለቱ ነበር፣ የቤተ መቅደሱን ግንብ ማለቱ አልነበረም፡፡ 22ኢየሱስ ከሞተና እግዚአብሔር ከሞት ካስነሳው በኋላ፣ ደቀመዛርቱ እርሱ ስለ ቤተመቅደስ የተናገረውን አስታውሱ፡፡ መጽሐፍ የተናገረውንና ኢየሱስ ራሱ የተናገረውንም አመኑ፡፡ 23 24 25 በፋሲካ በአል ኢየሱስ በኢየሩሳሌም በነበረበት ወቅትት ስለ ኢየሱስ ዕውቱን አጉልቶ የሚያሳዩ ተአምራቶችን በማየታቸው ምክንያት ብዙ ሰዎች በእርሱ ላይ እምነት አደረባቸው፡፡ 24የሆነ ሆኖ፣ ኢየሱስ ሰዎች ምን አይነት እንደሆኑ ስለሚያውቅ፣ እንዲሁም እነሱን በሚገባ ስለሚያውቃቸው በእነርሱ ላይ እምነት አልነበረውም፡፡ 25ምን አይት ሰዎች እንደሆኑ ማንም ሰው እንዲነግረው አይፈልግም ነበር፡፡ ስለ እነርሱ ሁሉንም ነገር ያውቃል፡፡

ምዕራፍ 3

1 2 ኒቆዲሞስ የሚባል አንድ ሰው ነበር፡፡ እርሱ በዘመኑ በአይሁድ እምነት ውስጥ እጅግ ወግ አጥባቂ ቡድን የነበረው የፈሪሳውያኑ አባል ነበር፡፡የአይሁዳዊያን ከፍተኛው አስተዳደር መማክርት አባል የሆነ የተከበረ ሰው ነበር፡፡ 2በምሽት ወደ ኢየሱስ ሄደ፡፡ ኢየሱስን ረቢ፣ “ረቢ፣ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣህ አስተማሪ መሆንህን እናውቃለን፡፡ ይህን እናውቃለን ምክንያቱም እግዚአብሔር ካልረዳው በስተቀር አንተ የምታደርጋቸውን ተአምራቶች ማንም ማድረግ አይችልም፡፡” 3 4 ኢየሱስ ኒቆዲሞስ ለተናገረው እንዲህ ሲል ምላሽ ሰጠ፣ “እኔ እውነቱን እነግርሃለሁ፣ ማንም ዳግም ካልተወለደ በስተቅር የእግዚአብሔርን መንግስት መውረስ አይችልም፡፡” 4ከዚያ ኒቆዲሞስ ለእርሱ እንዲህ አለው፣ “አንድ ሰው ሽማግሌ ሆኖ እንዴት ዳግም መወለድ ይችላል? ማንም ወደ እናቱ ማህጸን መግባትና ለሁለተኛ ጊዜ መወለድ አይችልም!” 5 6 ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰ፣ “እኔ ይህም ደግሞ እውነት መሆኑነ አረጋግጣለሁ፣ ማንም ከውሃና ከመንፈስ ከሁለቱም ካልተወለደ በስተቀር ወደ እግዚአብሔር መንግስት መግባት አይችልም፡፡ 6አንድ ሰው ከአንድ ሰው ቢወለድ፣ ያ ሰው ሰው ነው፡፡ ነገር ግን በእግዚአብሔር መንፈስ ስራ ዳግም የተወለዱ እነርሱ እግዚአብሔር በእነርሱ ውስጥ የሰራው አዲስ መንፈሳዊ ባህሪይ አላቸው፡፡ 7 8 ዳግም መወለድ አለብህ በማለት ስነግርህ አትደነቅ፡፡ 8ነገሩ እንደዚህ ነው ነፋስ ወደ ፈለገው ይነፍሳል፡፡ የነፋሱን ድምጽ ትሰማለህ፣ ነገር ግን ከየት እንደመጣ ወይም ወዴት እንደሚሄድ አታውወቀም፡፡ በመንፈስ ህያው የሚሆን ሁሉ ልክ እንደዚሁ ነው መንፈስ ለማንኛውም እሱ ለወደደው ሰው አዲስ ልደት ይሰጠዋል፡፡ 9 10 11 ኒቆዲሞስ እንዲህ ሲል መለሰለት፣ “ይህ እንዴት እውት ሊሆን ይችላል?” 10ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰለት፣ “አንተ በእስራኤል ትልቅ አስተማሪ ነህ፣ ሆኖም ግን የምናገረውን አሁንም አትረዳም 11እኔ እውነቱን እየነገርኩህ ነው፣ እኛ እውነት መሆኑን የምናውቀውን ነገር እንናገራለን፣ እኛ ያየነውን እየነገርናችሁ ነው፣ እነዚህን ነገሮች ከምንናገራችሁ ከእናንተ አንዳችሁም እኛ የምንናገረውን አታምኑም፡፡ 12 13 ስለዚህ ምድር ነገሮ ስነግራችሁ የተናገርኩትን ካላመናችሁ፣ ስለ ሰማያዊ ነገሮች ስነግራችሁ የተናገርኩትን እንዴት ማመን ትችላላችሁ 13እኔ፣ የሰው ልጅ፣ ወደ ሰማይ የሄድኩ እኔ ብቻ ነኝ፣ ደግሞም ወደዚህ ወደምድር የመጣሁት እኔ ብቻ ነኝ፡፡ 14 15 ከዘመናት በፊት ሙሴ፣ እስራኤላውያን ከግብፅ ሲወጡ በበረሃ በነበረበት ጊዜ በአንድ ምሰሶ ላይ አንድ መርዛማ እባብ ከፍ አድርጎ ሰቀለ፡፡ ወደዚያ ቀና ብለው የተመለከቱ ሁሉ ይድኑ ነበር፡፡ በተመሳሳይ መንገድ የሰው ልጅ ወደ ላይ ከፍ መደረግ አለበት፡፡ 15ስለዚህም ማንኛውም ቀና ብሎ እርሱን የተመለከተና በእርሱ ያመነ የዘለዓም ህይወት ይኖረዋል፡፡ 16 17 18 እግዚአብሔር በዚህ መንገድ ዓለምን ወዷል፡ እሱ አንድያ ልጁን ስለ ሰጠ በእርሱ የሚያምን ማንኛውም ሰው የዘላለም ህይወት ይኖረዋል እንጂ አይሞትም፡፡ 17እግዚአብሔር ልጁን ወደ ዓለም የላከው በዓለም ሊፈርድበት ሳይሆን ሊያድናት ነው፡፡ 18በልጁ የሚያምን እያንዳንዱን ሰው፣ እግዚአብሔር በፍጹም አይፈርድበትም፡፡ ነገር ግን እያንዳንደን በእርሱ የማያምነውን እግዚአብሔር አሁን ከእርሱ ፍርድ በታች አድርጎል፣ ምክንያቱ አንድያ በሆነው በእግዚአብሔር ልጅ ስም እምነታቸውን አላደረጉምና ነው፡፡ 19 20 21 እግዚአብሔር ሁሉም ይመለከተው ዘንድ ፍርዱን ለሀጢአተኛ ሰዎች ግልጽ አድርጓል፡ የእርሱ ብርን ወደዚህ ዓለም መጥቷል፣ የዚህ ዓለም ሰዎች ግን ጨለማቸውን ወደዱ ደግሞም ከብርሃን ተደበቁ፡፡ ጨለማውን የወደዱበት ምክንያት ይሰሩ የነበሩት ደስ የማያሰኝና ክፉ ስለነበር ነው፡፡ 20እያንዳንዱ ክፉ ነገር የሚያደርግ ብርሃንን ይጠላል፣ እነርሱ በፍጹም ወደ ብርሃን አይመጡም ምክንያቱም ብርሃኑ የሰሩትን ይገልጣል እንዲሁም ምን ያህል ክፉዎች እንደሆኑ ይገልጣል፡፡ 21ነገር ግን መልካምና እውነት የሆነውን የሚያደርጉ ወደ ብርሃን ይመጣሉ፣ ስለዚህም የሰሩት በሁሉም ሊታይና ሁሉም እነርሱ እነዚህን ነገሮች ሲያደርጉ እግዚአብሔርን ይታዘዙ እንደነበር ሊያውቁ ይችላሉ፡፡ 22 23 24 እነዚያ ነገሮች ከሆኑ በኋላ ኢየሱስና ደቀመዛርቱ ወደ ይሁዳ አካባቢ ሄዱ፡፡ እርሱ በእዚያ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ለጥቂት ጊዜ ቆየ ደግሞም ብዙ ሰዎችን አጠመቀ፡፡ 23አጥማቂው ዮሐንስም በሄኖን መንደር አቅራቢያ በሳሌም አጠገብ በሰማርያ ግዛት ሰዎችን ያጠምቅ ነበር፡፡ በዚያ ስፍራ ብዙ ውሃ ነበር፣ በጣም ብዙ ሰዎች ወደ ዮሐንስ ያለማቋረጥ ይመጡ ነበር፡፡ 24ይህ የሆነው የዮሐንስ ጠላቶች እሱን እስር ቤት ሳያስገቡት አስቀድሞ ነው፡፡ 25 26 በዮሐንስ አንዳንድ ደቀመዛሙርትና በአንድ አይሁዳዊ መሀል በእግዚአብሔር ዘንድ ተቀባይነት ለማግኘት አንድ ሰው ስለሚያደርገው የመንጻት ስርዓት ክርክር ተነሳ፡፡ 26ይከራከሩ የነበሩት ወደ ዮሐንስ መጥተው እንዲህ አሉ፣ “ረቢ፣ በዮርዳኖስ ወንዝ ማዶ ሰዎችን ታጠምቅ በነበረበት ጊዜ ከአንተ ጋር አብሮህ የነበረ ሰው ነበር፡፡ እርሱ ማን እንደሆነ ለእኛ ነግረኸን ነበር፡፡ አሁን እርሱ በይሁዳ አካባቢ እያጠመቀ ነው፤ ብዙ ሰዎችም ወደ እርሱ እየሄዱ ነው፡፡” 27 28 ዮሐንስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፣ “እግዚአብሔር ካልሰጠው በስተቀር ሰው አንድ ነገር እንኳን መቀበል አይችልም፡፡ 28እንዲህ ብዬ ስነግራችሁ እውነቱን እየነገርኳችሁ እንደነበር ታውቃላችሁ፣ “እኔ መሲሁ አይደለሁም፣ ነገር ግን ከእርሱ በፊት ለእርሱ መምጣት መንገዱን መልካም ለማድረግ የተላክሁ ነኝ፡፡” 29 30 እኔ እንደ ሙሽራው ጓደኛ ነኝ፡፡ ሙሽራው እስኪመጣ በዚያ ቆሜ እጠብቃለሁ፡፡ የሙሽራው ጓደኛ በመጨረሻ ሙሽራው ደርሶ ድምጹን ሲሰማ በጣም ደስ ይለዋል፡፡ ስለዚህ፣ ይህ ሁሉ በመሆኑ ምክንያት ደስታዬ ሞልቶ ይፈሳል፡፡ ምክንያቱም እርሱ መጥቷል፡፡ 30በጊዜ ሂደት በማዕረግና በአስፈላጊነት እርሱ ከፍ ሲል እኔ እያነስኩና አስፈላጊነቴ እየቀነሰ ይመጣል፡፡ 31 32 33 ኢየሱስ የመጣው ከሰማይ ነው፣ እናም ከሌላ ከማንም ይልቅ እርሱ በማዕረግ ከፍ ያለ ነው፡፡ እኛ በምድር ቤት አለን፣ እናም የምድር የሆኑ ነገሮችን ብቻ መናገር እንችላለን፡፡ ከሰማይ የማጣው በምድር ላይና በዚያ ካለው እያንዳንዱ ነገር በላይ ነው፡፡ 32አሁን ላየውና ለሰማው ምስክርነቱን የሚሰጥ አንድ ጀግና አለ፣ ነገር ግን እርሱ የሚናገረውን ማንም አይቀበልም ወይም እውነት ነው ብሎ አያምንም፡፡ 33የሆነ ሆኖ፣ እርሱ የተናገረውን ያመኑ፣ እግዚአብሔር የእነውት ሁሉ መገኛ፣ እና እርሱ ብቻ እውነት የሆነ ነገር ሁሉ መለኪያና ደረጃ እንደሆነ ይመሰክራሉ፡፡ 34 35 36 እግዚአብሔር የእርሱን መልዕክተኛ ልኳል እናም እርሱ የተናገረው እውነት ነው፣ እርሱ የእግዚአብሔርን ቃላት ይናገራልና፡፡ እርሱ መንፈሱን ሳይሰፍር ይሰጣል፡፡ 35አባት ልጁን ይወዳል እርሱ ሁሉንም ነገር ከእርሱ ሀይል በታች አድርጎታል፡፡ 36በእግዚአብሔር ልጅ የሚያምን ሁሉ ዘላለማዊ ህይወት አለው፡፡ የእግዚአብሔርን ልጅ የማይታዘዝ ሁሉ የዘለዓለም ህይወት ሊኖረው አይችልም፣ ደግሞም ያ ሰው ለሰራው እያንዳንዱ ሀጢአት የእግዚአብሔር ጻድቅ ፍርድ በእርሱ ላይ ለዘለዓለም ይኖራል፡፡

ምዕራፍ 4

1 2 3 ኢየሱስ ስለ ፈሪሳዊያን ወሬ ደረሰው፡፡ ኢየሱስ ከዮሐንስ መጥመቁ የበለጠ ተከታዮችን እያገኘና ከዮሐንስ ይልቅ ብዙ ሰዎችን እያጠመቀ መሆኑን እነርሱ ሰሙ፡፡ 2ነገር ግን ኢየሱስ ራሱ የማጥመቅን ሥራ እየሰራ አልነበረም፤ የእርሱ ደቀመዛሙርት ነበሩ ያንን ይሰሩ የነበረው፡፡ 3ስለዚህ ኢየሱስና ደቀመዛሙርቱ የይሁዳን አካባቢ ትተው እንደገና አንዴ ወደ ገሊላ ተመለሱ፡፡ 4 5 4በዚህ ጊዜ በሰማርያ በኩል ማለፍ ነበረባቸው፡፡ 5ስለዚህ በሰማርያ አካባቢ ወደሚገኝ ሲካር ወደሚባል ከተማ ደረሱ፡፡ ሴካር ያዕቆብ ለልጁ ዮሴፍ ከረጅም ዘመን በፊት በሰጠው ትንሽ መሬት አጠገብ ይገኛል፡፡ 6 7 8 ከሴካር ከተማ ወጣ ብሎ የያዕቆብ ጉድጓድ ነበር፡፡ ኢየሱስ ረጅም መንገድ በመጓዙ ምክንያት በጣም ደክሞ ነበር፣ እናም አረፍ ለማለት ከጉድጓዱ አጠገብ ተቀመጠ፡፡ ጊዜው እኩለ ቀን ላይ ነበር፡፡ 7ከሰማርያ አንዲት ሴት ውሃ ለመቅዳት ወደ ጉድጓድ መጣች፡፡ ኢየሱስስ “ውሃ አጠጪኝ” አላት፡፡ 8በዚህ ጊዜ ደቀመዛሙቱ ምግብ ለመግዛት ብቻውን ትተዉት ወደ ከተማ ሄደው ነበር፡፡ 9 10 ሴቲቱ እሱን፣ “አንተ አይሁዳዊ ሆነህ እኔ ከሰማርያ የሆንኩትን ሴት የሚጠጣ መጠየቅህ አስደንቆኛል” አለችው፡፡ 10ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላት፣ “እግዚአብሔር ለአንቺ ሊሰጥሽ የፈለገውን ስጦታ አውቀሽ ቢሆንና የሚጠጣ የጠየቀሽ ማን እንደሆነ አውቀሽ ቢሆን፣ አንቺ ትጠይቂኝ ነበር እኔም የህይወትን ውሃ እሰጥሽ ነበር፡፡” 11 12 “ጌታዬ፣ ከጉድጓዱ ውሃ የምታወጣበት ባልዲ ወይም ገመድ የለህም ይህ ጉድጓድ ደግሞ ጥልቅ ነው፡፡ ይህን የህይወት ውሃ ከየት ታገኛለህ? 12አንተ ከአባታችን ከያዕቆብ ልትበልጥ አትችልም፡፡ እርሱ ዛሬ የምንጠቀምበትን ጉድጓድ ቆፈረ፣ እርሱ ራሱ ልጆቹና እንስሳቱ ከዚህ ጠጡ፡፡ 13 14 ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላት፣ “ከዚህ ጉድጓድ የሚጠጣ ሁሉ እንደገና ይጠማል፣ 14እኔ የምሰጣቸውን ውሃ የሚጠጡ ግን በፍጹም ዳግመኛ አይጠሙም፡፡ እኔ የምሰጠው ውሃ እነርሱን የሚያረካና የዘላለም ህይወት የሚሰጣቸው የህይወት ውሃ ምንጭ ይሆናል፡፡” 15 16 ሴትየዋ እንዲህ አለችው፣ “ጌታዬ፣ ይህን ውሃ ስጠኝ፣ ይህ ከሆነ ወደፊት በፍጹም አልጠማም ወይም ውሃ ለመቅዳት ደግሜ ወደዚህ መምጣት አያስፈልገኝም፡፡” 16ኢየሱስ እርሱ እየተናገረ የሚገኘውን ነገር እንዳልተረዳች አውቋል፣ ስለዚህም እንዲህ አላት፣ “አንቺ ሴት ሄደሽ ባልሽን ጥሪና እርሱንም እዚህ አምጭው፡፡” 17 18 ሴትየዋ እንዲህ ስትል መለሰችለት፣ “ባል የለኝም፡፡” ኢየሱስ እንዲህ አላት፣ “ባል የለኝም በማለትሽ ትክክል ነሽ 18ምክንያቱም አንድ ባል ብቻ አልነበረሽም፣ ነገር ግን አምስት ባሎች ነበሩሽ እናም አሁን አብረሽው እየኖርሽው ያለሽው ሰው ባልሽ አይደለም ባል እንደሌለሽ የተናገርሽው እውነት ነው፡፡” 19 20 ሴትየዋ እንዲህ አላቸው፣ “ጌታዬ፣ አንተ ነቢይ እንደሆንክ አያለሁ፡፡ 20አባቶቻችን በዚህ ስፍራ በዚህ ተራራ ላይ እግዚአብሔርን አምልከዋል፣ እናንተ አይሁዶች እግዚአብሔርን ማምለክ ያለብን በኢየሩሳሌም ነው ትላላችሁ፡፡ ማነው ትክክለኛው? 21 22 ኢየሱስ እንዲህ አላትት፣ “አንቺ ሴት፣ እዚህ በዚህ ተራራ ላይ ወይም በኢየሩሳሌም ሰዎች አብን የማያመልኩበት ጊዜ እየመጣ ነው ብዬ ስናገር እመኚኝ፡፡ 22እናንተ በሰማርያ ያላችሁ ሰዎች የማታውቁትን ታመልካላችሁ የአይሁድ አምላኪዎች እኛ የምናመልከውን እናውቃለን ምክንያቱም ደህንነት ከአይሁዶች ይመጣል፡፡” 23 24 እግዚአብሔር በእውነት የሚያመልኩት አብን በመንፈሳዊነት እና በእውት የሚያመልኩበት ጊዜ እየመጣ ነው ይህም አሁንም ደርሷል፡፡ በዚህ አይነት መንገድ ያመልኩት ዘንድ አብ እንዲህ ያሉ ሰዎችን ይፈልጋል፡፡ 24እግዚአብሔር መንፈስ ነው፣ እርሱን የሚያመልኩት በመንፈሳዊነት ሊያመልኩት ይገባል፣ እናም በአምልኮ እውነቱ ሊመራቸው ይገባል፡፡ 25 26 ሴትየዋ እንዲህ አለችው፣ “መሲሁ፣ ክርስቶስ ሊመጣ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ እርሱ ሲመጣ፣ መስማት የሚገባንን ሁሉንም ነገር ይነግረናል፡፡” 26ኢየሱስ እንዲህ አላትት፣ “እኔ፣ ከአንቺ ጋር የምንነግረው እኔ እሱ ነኝ!” 27 ከዚያ ወዲያውኑ ደቀመዛሙርቱ ከከተማ ተመለሱ፡፡ ኢየሱስ ከእርሱ ቤተሰብ ጋር ዝምድና ከሌላት ሴት ጋር እየተነጋገረ ስለነበር ተገረሙ፡፡ (ይህ ከአይሁዶች ልማድ ጋር የማይስማማ ነገር ነበር) የሆነ ሆኖ “ብቻህን ለምን ከሴት ጋር ተነጋገርክ?” ወይም “ ለምን ከእርሷ ጋር ተነጋገርክ?” ብሎ ስጠይቀው የደፈረ አልነበረም፡፡ 28 29 30 ሴትየዋ የውሃ እንስራዋን እዚያው ትታ ወደ ከተማ ሄደች፡፡ ለከተማው ሰው እንዲህ እያለች ተናገረች፣ 29“ያደረግሁትን ነገር ሁሉ የነገረኝን ሰው መጥታችሁ ተመልከቱ! እርሱ ክርስቶስ ሊሆን አይችልም ይሆንን ወይስ እርሱ ይሆንን?” 30ብዙ ሰዎች ከከተማ እየወጡ ኢየሱስ ወዳለበት ስፍራ ሄዱ፡፡ 31 32 33 ምግብ ይዘው የተመለሱት ደቀመዛሙርቱ አጥብቀው እንዲህ አሉት፣ “ረቢ፣ ጥቂት ነገር ቅመስ” 32ኢየሱስ፣ “እናንተ ስለዚያ ምንም የማታውቁት እኔ የምበላው ምግብ አለኝ!” አላቸው፡፡ 33ስለዚህም አንዳቸው ለሌላቸው፣ “ሌላ ምግብ ሊያመጣለት የሚችል የለም፣ አለን?” ተባባሉ፡፡ 34 35 36 ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ "እጅግ የተራብኩበትን እነግራችኋለሁ ይህም የላከኝ አባቴ እንዳደርገው የሚፈልገውን ማድረግና የእርሱን ሥራ መፈፀም ነው፡፡ 35በአመቱ ውስጥ በዚህ ወቅት ብዙውን ጊዜ እንዲህ ትላላች ‘አራት ወራት ቀሩ፣ ከዚያ በኋላ አዝመራችንን እንሰበስባለን፡፡’ እስቲ ዙሪያችሁን ተመልከቱ! እርሻዎቹ በዚህን ሰዓት ለአጨዳ ተዘጋጅተዋል፡፡ አሁን አይሁዳዊ ያልሆኑ እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ እንዲገዛ እየፈለጉ ነው፤ እነርሱ ለመታጨድ እንደተዘጋጀ ማሳ ናቸው፡፡ 36ይህን የሚያምንና በእንዲህ አይነቱ ምርት ለመስራት የተዘጋጀ ክፍያውን ከወዲሁ እየተቀበለና ለዘለዓለም ህይወት ብዙ ፍሬ እየሰበሰበ ነው፡፡ ዘር የዘሩና ምርቱን የሚያጭዱ በአንድነት ደስ ይላቸዋል፡፡ 37 38 ይህ አባባል እውነት ነው አንድ ሰው ዘር ይተክላል እናም ሌላው ሰው አዝመራ ይሰበስባል፡፡ 38እኔ ያልተከላችሁትን አዝመራ እንድትሰበስቡ ላኳችሁ፡፡ ሌሎች በጣም ደክመው ሰሩ ነገር ግን አሁን እናንተ በእነርሱ ስራ ተቀላቀላችሁ፡፡” 39 40 በሲካር ከተማ የሚኖሩ ብዙ ሳምራዊያን ከሴትየው ስለ እርሱ ከሰሙት የተነሳ በኢየሱስ ላይ እምነታቸውን አደረጉ፡፡ እርሷ፣ “ያደረኩትን ሁሉንም ነገር ነገረኝ” ብላቸው ነበር፡፡ 40ሳምራዊያኑ ወደ ኢየሱስ ሲመጡ፣ ከእነርሱ ጋር ረጅም ጊዜ እንዲቆይ አጥብቀው ጠየቁት ስለዚህም ተጨማሪ ሁለት ቀናት በዚያ ቆየ፡፡ 41 42 እርሱ ከነገራቸው የተነሳ በተጨማሪ ብዙዎቹ በኢየሱስ አመኑ፡፡ 42እነርሱም ሴትየዋን እንዲህ አሏት፣ “አሁን እኛ በኢየሱስ አምነናል፣ ይህም አንቺ ስለ እርሱ በነገርሽኝ ብቻ ሳይሆን ነገር ግን እኛ ራሳችንም የእርሱን መልዕክት ሰምተናል፡፡ እኛ አሁን ይህ ሰው በእውነት የዓለም አዳኝ እንደሆነ እናውቃለን፡፡” 43 44 45 ከእነዚያ ሁለት ቀናት በኋላ ኢየሱስና ደቀመዛሙርቱ ሰማርያን ለቀው ወደ ገሊላ አካባቢ ሄዱ፡፡ 44(ኢየሱስ ራሱ አንድ ነቢይ በብዙ ቦታዎች ክብር ያገኛል ነገር ግን በፍጹም ባደገበት ስፍራ አይደለም የሚለውን አረጋግጧል፡፡) 45ሆኖም፣ ገሊላ ሊደርስ በዚያ የነበሩ ብዙ ሰዎች ጥሩ አቀባበል አደረጉለት፡፡ እርሱ ማን እንደሆነ ያውቁ ነበር፡፡ ምክንያቱም በቅርቡ ኢየሩሳሌም ውስጥ በተካሄደ የፋሲካ በዓል ያደረጋቸውን ነገሮች ሁሉ አይተዋል፡፡ 46 47 ኢየሱስ ተመልሶ ገሊላ ውስጥ ወደሚገኘው ቃና ሄደ፡፡ (ውሃውን ወደ ወይን የቀየረው በዚያ ነበር፡፡) ሃያ ሰባት ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኘው በቅፍርናሆም የሚኖር፣ ልጁ የታመመበት አንድ የንጉሱ መኮንን ነበረ፡፡ 47ያሰው ኢየሱስ ከይሁዳ ተመልሶ ወደ ገሊላ መምጣቱን ሲሰማ፣ ቃና ወደሚገኘው ወደ ኢየሱስ ሄዶ “ወደ ቅፍርናሆም ወርደህ ልጄን ፈውስልኝ፡፡ እርሱ ሊሞትብኝ ነው!” በማለት ለመነው፡፡ 48 49 50 ኢየሱስ እንዲህ አለው፣ “እኔ ማን እንድሆን የሚያረጋግጥ ተአምራቶችን ስሰራ ካላያችሁ በስተቀር በእኔ አታምኑም!” 49መኮንኑ አሁንም እንዲህ አለው፣ “ጌታዬ፣ እባክህ ልጄ ከመሞቱ አስቀድሞ ወደ ቤቴ ውረድ!” 50ኢየሱስ፣ “ሂድ፣ ልጅህ በህይወት ይኖራል” አለው፡፡ ሰውዬው ኢየሱስ ያለውን አምኖ ወደ ቤቱ መመለስ ጀመረ፡፡ 51 52 ወደ ቤቱ እየተጓዘ ሳለ፣ አገልጋዮቹ በመንገድ ላይ ተገናኙት፡፡ እንዲህ ብለውም ነገሩት፣ “ልጅህ ድኗል፡፡” 52“ልጄ ጤናው የተሸሻለው በምን ሰዓት ነበር?” ሲል ጠየቃቸው፡፡ እነርሱም እንዲህ አሉት፣ “ትናንትና ከሰዓት በኋላ በሰባት ሰዓት ትኩሳቱ ለቀቀው፡፡” 53 54 ከዚያ የልጁ አባት ይህ ሰዓት “ልጅህ በህይወት አለ” ብሎ ኢየሱስ ለእርሱ የተናገረበት ሰዓት እንደሆነ አስተዋለ፡፡ ስለዚህም እርሱና ቤተሰቡ ሁሉ በኢየሱስ አመኑ፡፡ 54ኢየሱስ እርሱ ማን እንደሆነ ለሰዎች ለማረጋገጥ ሁለተኛ ጊዜ የሰራው ነገር ያ ነበረ፡፡ ይህን ያደረገው ከይሁዳ ተነስቶ ወደ ገሊላ አካባቢ በመጣበት ወቅት ነበረ፡፡

ምዕራፍ 5

1 2 3 4 ሌላ የአይሁድ በአል ጊዜ ደረሰ፣ ኢየሱስም ለበአሉ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደ፡፡ 2በኢየሩሳሌም ወደ ከተማው ከሚወስደው መግቢያ በአንዱ አጠገብ፣ የበጎች በር የሚባል ቦታ አለ፡፡ በዚያ መግቢያ ቤተሳይዳ (በአረማይካ እንደሚጠራው) የሚባል መጥመቂያ አለ፡፡ ከመጥመቂያው አጠገብ አምስት ጣራ ያላቸው በረንዳዎች ወይም መጠለያዎች ነበሩ፡፡ 3-4በዚያም የታመሙ፣ ዐይነ-ስውራን፣ እና መራመድ የማይችሉ በጣም ብዙ ቁጥር የነበራቸው ሰዎች ነበሩ፡፡ መራመድ የማይችሉ ብዙ ሰዎች በመጠለያው ተኝተው ነበር፡፡ 5 6 አንድ መራመድ የማይችል ሰው ለስላሳ ስምንት አመታት በዚያ ነበር፡፡ 6ኢየሱስ ሰውዬው በዚያ ተኝቶ አየውና ለረጅም ጊዜ በዚህ ሁኔታ ውስጥ እንደነበረ አወቀ፡፡ እርሱ ሰውዬውን፣ “ጤናማና ጠንካራ መሆን ትፈልጋለህ?” አለው፡፡ 7 8 ሰውዬው እርሱን፣ “ጌታዬ፣ ውሃው ሲናወጥ ወደ መጥመቂያው ውስጥ እንድገባ የሚረዳኝ ሰው በዚህ የለኝም፡፡ እኔ ወደ መጥመቂያው ለመግባት እየሞከርኩ እያለሁ፣ ሁልጊዜም ሌላ ሰው ከፊቴ ቀድሞ ይገባል፡፡” ሲል መለሰለት፡፡ 8ኢየሱስ፣ “ተነስ! አልጋህን ተሸከምና ሂድ!” አለው፡፡ 9 ሰውዬው ወዲያውኑ ተፈወሰና አልጋውን ተሸክሞ ተራመደ፡፡ ያ ቀን ሰንበት ነበር፣ የእረፍት ቀን፡፡ 10 11 የተፈወሰውን ሰው የአይሁድ መሪዎች እንዲህ አሉት፣ “ቀኑ ሰንበት ነው፣ በዚህ የዕረፍት ቀን ምንጣፍህን መሸከምህ ከህጋችን ጋር እንደሚቃረን ታውቃለህ፡፡” 11የተፈወሰው ሰው፣ “ነገር ግን የፈወሰኝ ሰው አልጋህን አንሳና ሂድ! አለኝ” አላቸው፡፡ 12 13 እነርሱም እንደዚህ ብለው ጠየቁት፣ “ያሰው ማን ነበር?” 13 ምንም እንኳን ኢየሱስ ሰውዬውን ቢፈውሰውም፣ ሰውዬው ስሙን አያውቅም ነበር፡፡ ኢየሱስ ከፈወሰው በኋላ ሰውዬውን ትቶ ወደ ህዝቡ መሀል ተመልሶ ገብቶ ነበር፡፡ 14 15 ቆይቶ፣ ኢዩሱስ ሰውየውን ቤተመቅደስ ውስጥ አግኝቶት እንዲህ አለው፣ “ልብ በል፣ አሁን ጤናማ ነህ፡፡ ከዚህ በኋላ ሀጢአት አትስራ እንዲህ ከሆነ ምንም የከፋ ነገር አይደርስብህም፡፡” 15ሰውዬው ሄዶ ለአይሁድ መሪዎች የፈወሰው ሰው ኢየሱስ እንደነበረ ተናገረ፡፡ 16 17 18 16ስለዚህ አይሁዶች ኢየሱስን ለማስቆም ጥረት ማድረግ ጀመሩ ምክንያቱም ብዙውን ጊዜ እሱ እነዚያን ስራዎች በሰንበት ቀን ይሠራ ነበር፡፡ 17ኢየሱስ ይህን መልስ ሰጣቸው፣ “አባቴ አሁንም እንኳን እየሰራ ነው፣ እና እኔም ደግሞ እየሰራሁ ነው፡፡” 18አይሁዶች ኢየሱስን ለመግደል አብዝተው ይሞክሩ የነበሩት የሰንበትን ቀን ስለሻረ ብቻ ሳይሆን፣ ነገር ግን እራሱን ከእግዚአብሔር ጋር እኩል አድርጎ እግዚአብሔርን የእራሱ አባት ብሎ ስለ ጠራ ነው፡፡ 19 20 ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፣ “እኔ የሰው ልጅ፣ እውነቱን እየነገርኳችሁ ነው፡፡ በእራሴ ስልጣን ምንም ነገር ማድረግ አልችልም፡፡ መስራት የምችለው አብ ሲሰራ ያየሁትን ብቻ ነው፡፡ ልጁ የሚሰራው ማናቸውንም አብ የሰራውን ነው፡፡ 20አብልጅን ይወደኛል እናም የሚሰራውን ሁሉ ያሳየኛል፡፡ ምን መስራት እንደምችል እንድታዩና እንድትደነቁ አብ ከእነዚህ የበለጡ ስራዎችን እንኳን ያሳየኛል፣ 21 22 23 አብ የሞቱትን አስነስቶ ዳግም ሕይወት እንደሚሰጣቸው፣ እንዲሁ እኔ፣ የሰው ልጅ፣ ለምፈልገው ለማንኛውም ህይወት እሰጣለሁ፡፡ 22አብ በማንም ላይ አይፈርድም፣ ነገር ግን ሁሉንም ፍርድ ለእኔ አሳልፎ ሰጥቶኛል፣ 23ስለዚህም ሁሉም ሰዎች እኔን የሰው ልጅን፣ አብን በሚያከብሩበት በተመሳሳይ መንገድ ያከብሩኛል ማንም እኔን የማያከብር አብን ማክበር አይችልም፡፡ 24 እኔ እውነቱን እየነገርኳችሁ ነው ማንም የእኔን መልእክት ሰምቶ እግዚአብሔር እንደላከኝ የሚያምን የዘላአለም ህይወት አለው፡፡ እርሱ ወደ እግዚአብሔር ፍርድ አይመጣም፡፡ ነገር ግን ሙት ከመሆን ህያው ወደመሆን ይሸጋገራል፡፡ 25 እኔ እውነቱን እየነገርኳችሁ ነው፡ ሙታን የነበሩ ድምጼን የሚሰሙበት ጊዜ እየደረሰ ነው፣ እኔን የእግዚአብሔር ልጅን የሚሰሙኝ በህይወት ይኖራሉ፡፡ 26 27 አብ ሰዎች እንዲኖሩ ምክንያት እንደሚሆን በተመሳሳይ መንገድ እኔ ልጅ ለሆንኩት እነርሱ በህይወት እንዲኖሩ ምክንያት ለመሆን ሀይልን ሰትቶኛል፡፡ 27አብ እርሱ ትክክል ነው የሚለውን ሁሉ ለማድረግ ለእኔ ስልጣን ሰጥቶኛል፣ ምክንያቱም እኔ የሰው ልጅ ነኝ፡፡ 28 29 በዚህ አትደነቁ ምክንያቱም ሞተው የነበሩ ሰዎች ሁሉ ስጣራ ድምጼን የሚሰሙበት ጊዜ ይመጣል፣ 29እናም ከመቃብራቸው ይወጣሉ፡፡ እግዚአብሔር ጥሩ የሰሩትን ለዘለዓለም ህይወት ያስነሳቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ክፉ ያደረጉትንም ያስነሳቸዋል፣ ነገር ግን ሊኮንናቸውና ለዘለዓለም ሊቀጣቸው ያስነሳቸዋል፡፡ 30 31 32 እኔ በራሴ ምንም ማድረግ አልችልም፡፡ ከአብ የሰማሁትን ማናቸውንም፣ እንደዚያው እንደሰማሁ ነው የምፈርደው፣ ደግሞም እኔ በትክክለኛ ሁኔታ እፈርዳለሁ፡፡ እኔ በትክክል እፈርዳለሁ ምክንያቱም እኔ የምፈልገውን ለማድረግ አልሞክርም፣ ነገር ግን ወደዚህ የላከኝ አብ የሚፈልገውን አደርጋለሁ፡፡ 31ስለራሴ የምመሰክረው እኔ ብቻ ከሆንኩ፣ ማንም የእኔን ምስክርነት እውነት ነው ብሎ አያምንም ወይም አይቀበለውም፡፡ 32የሆነ ሆኖ፣ ስለ እኔ ምስክርነት የሚሰጥ አለ፣ እርሱ ስለ እኔ የሚሰጠው ምስክርነት እውት እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ 33 34 35 እናንተ ወደ መጥመቁ ዮሐንስ መልዕክተኛ ላካችሁ፣ እርሱም ስለ እኔ እውነቱን ነገራችሁ፡፡ 34በእርግጥ እኔ እርሱም ሆነ ሌላ ማናቸውም ሰው ስለ እኔ ምስክር እንዲሆን አልፈልግም፣ ነገር ግን እነዚህን ነገሮች የምናገረው እግዚአብሔር እናንተን ማዳን እንዲችል ነው፡፡ 35አጥማቂው ዮሐንስ የሚነድና የሚያንፀባርቅ ብርሃን ነበር፣ ለአጭር ጊዜ በእርሱ ብርሃን ደስ ልትሰኙ ወደዳችሁ፡፡ 36 37 38 የሆነ ሆኖ ስለራሴ የሰጠሁት ምስክርነት ዮሐንስ ለእኔ ከሰጠው ምስክርነት እንኳን ይበልጣል፡፡ አብ እኔ እንዳደርጋቸው የፈቀደልኝን ነገሮች ሁሉ እኔ ማን እንደሆንኩ በሚገባ ናገራሉ፡፡ እኔ እነዚያን ነገሮች በየዕለቱ አደረኩ፣ እናንተም ሳደርጋቸው አያችሁ፡፡ ስራዎቼ የመጣሁበትን አላማ የሚገልፁና አብ እኔን ለመላኩ ማረጋገጫዎች ናቸው፡፡ 37የላከኝ አባቴ ስለ እኔ ምስክርነት ሰጥቷል፡፡ እናንተ ፈጽሞ ድምፁን አልሰማችሁም እንዲሁም በፍፁም በአካል አላያችሁትም፡፡ 38በእንተ ውስጥ የሚኖር የእርሱ ቃል የሌላችሁ መሆኑ ማረጋገጫው እርሱ የላከኝን እኔን አለማመናችሁ ነው፡፡ 39 40 እናንተ መጽሀፍትን በጥንቃቄ ታጠናላች ምክንያቱም እነርሱን በማጥናት የዘለዓለም ህይወት እንደምታገኙ ታስባላችሁ፣ መጽሐፍት ስለ እኔ ይናገራሉ፡፡ 40እንዲያም ሆኖ ከእኔ የዘለዓለም ህይወትን ለመቀበል ወደ እኔ መምጣትን አትፈልጉም፡፡ 41 42 ሰዎች ቢያመሰግኑኝ ወይም ቢያደንቁኝ እኔ አልቀበላቸውም፡፡ 42እኔ ስለእናንተ ይህን አውቃለሁ፣ እናንተ እግዚአብሔርን አትወዱም፡፡ 43 44 እኔ በአባቴ ስልጣን መጥቻለሁ ነገር ግን እስከ አሁን አልተቀበላችሁኝም ወይም አላመናችሁኝም፡፡ ሌላው ግን በራሱ ስልጣን ቢመጣ እናንተ ትሰሙታላችሁ፡፡ 44በመካከላችሁ ሌሎች ክብር እንዲሰጧችሁ እጅግ እየደከማችሁ እንዴት በእኔ ልታምኑ ትችላላችሁ፡፡ ነገር ግን ሁሌም አንድ እና አንድ ብቻ ከሆነው እግዚአብሔር የሆነውን እውነተኛ ክብር ትቃወማላችሁ፡፡ 45 46 47 በአባቴ ፊት የምከሳችሁ እኔ እንደምሆን አታስቡ፡፡ ሙሴ እናንተን እንደሚደግፍ ታስባላችሁ፣ ስለዚህም ተስፋችሁን በእርሱ ላይ ታደርጋላች ሆኖም፣ የሚከሳች ሙሴ ነው፡፡ 46ሙሴ የተናገረውን ተቀብላችሁ ቢሆን ኖሮ፣ እኔ የነገርኳችሁን እውነት ትቀበሉ ነበር፡፡ 47ሙሴ የጻፈውን እንኳን እስካላመናችሁ ድረስ እኔ የነገርኳችሁን እንዴት ልታምኑ ትችላላችሁ!”

ምዕራፍ 6

1 2 3 ኢየሱስ ሀይቁን አቋርጦ ወደ ሌላው ዳርቻ ሄደ፡፡ አንዳንዶች የሀይቁን ስም “የገሊላ ባህር” ሲሉት “የጥብርያዶስ ባህር” ብለውም ይጠሩታል፡፡ 2በጣም ታመው የነበሩ ሰዎችን በመፈወስ የሰራውን ድንቆች ተመልክተው ስነበር በዚህ ምክንያት ብዙ ህዝብ ተከተለው፡፡ 3ኢየሱስ ቀን ያለውን የኮረብታ ደረት ወጥቶ ከደቀመዛሙቱ ጋር ተቀመጠ፡፡ 4 5 6 ወቅቱ የአይሁዶች ልዩ የአመቱ የፋሲካ ክብረ በአል የሚከበርበት ነበር፡፡ 5ኢየሱስ አሻግሮ ሲመለከት ወደ እርሱ የሚመጣ በርካታ ህዝብ አየ፡፡ ኢየሱስ ፊሊጶስን እንዲህ አለው፣ “እነዚህ ሁሉ ሰዎች የሚበሉት እንዲያገኙ እንጀራ ከየት እንገዛለን?” 6እርሱ ይህንን ጥያቄ ፊሊጶስን የጠቀው ምን ዐይነት መልስ እንደሚሰጥ ሊፈትነው ነበር፡፡ ሆኖም፣ ኢየሱስ ይህን ችግር ለመፍታት ምን እንደሚያደርግ ያውቅ ነበር፡፡ 7 8 9 ፊሊጶስ እንደህ ሲል መለሰለት፣ “አንድ ሰው በሁለት መቶ ቀናት ውስጥ ሰርቶ የሚያገኘው ገንዘብ ቢኖረን እንኳን ለዚህ እጅግ ብዙ ህዝብ ለእያንዳንዱ ሰው ትንሽ ትንሽ ለማቃመስ የሚሆነ እንጀራ ለመግዛት በቂ ገንዘብ አይሆንም፡፡” 8እንድርያስ የተባለው ሌላኛው ደቀመዝሙር፣ የስምዖን ጴጥሮስ ወንድም፣ ኢየሱስን እንዲህ አለው፣ 9“እዚህ አምስት ትናንሽ የገብስ እንጀራና ሁለት ትናንሽ አሣ ያለው ልጅ አለ፡፡ ሆኖም፣ ይህ በጣም ጥቂት ምግብ እንዴት እጅግ ብዙ ሰዎችን መመገብ ይችላል?” 10 11 12 ሰዎች ሁሉ በአንድነት የተሰበሰቡበት ስፍራ ብዘ ሳር ነበረበት፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ “ሰዎቹ እንዲቀመጡ ንግሯቸው፡፡” ስዚህም ሁሉም ሰዎች ተቀመጡ፤ ከዚያም ደቀመዛሙርቱ የተሰበሰበውን ህዝብ ከቆጠሩ በኋላ፣ ወደ አምስት ሺህ የሚጠጋ ሆኖ አገኙት፡፡ 11ከዚያ ኢየሱስ ጥቂቱን እንጀራ እና አሳ ወሰደና እግዚአብሔርን አመሰገነ፡፡ ከዚያ እንጀራውንና አሳውን በተቀመጡት መሀል ዐደለ፡፡ ሰዎቹ ሁሉ የፈለጉትን ያህል አሳና እንጀራ ተመገቡ፡፡ 12እያንዳንዱ ተመግቦ ሲጨርስ፣ ደቀመዛሙርቱነ እንዲህ አላቸው፣ “ሰዎቹ ያልተመገቡትን ትናንሽ የገብስ ዳቦ በሙሉ ሰብስቡ፡፡ ምንም ነገር እንዲባክን አታድርጉ፡፡” 13 14 15 ስለዚህም ከአምስቱ የገብስ እንጀራዎች ከተራረፈው አስራ ሁለት ትላልቅ መሶብ ሙሉ ሰበሰቡ፡፡ 14ሰዎቹ ኢየሱስ በፊታቸው ያደረገውን ተአምራት ከተመለከቱ በኋላ፣ እንዲህ አሉ፣ “በእርግጥ እግዚአብሔር ወደ ዓለም የሚልከው ነቢይ ይህ ነው!” 15ኢየሱስ ሰዎቹ ምን እያቀዱ እንደነበር አውቋል፤ ሊመጡና ንጉሳቸው እንዲሆን ግድ ሊሉት ነበር፡፡ ስለዚህ ትቷቸው ብቻውን ለመሆን ወደ ተራራ ሄደ፡፡ 16 17 18 ምሽት ሲሆን፣ ደቀመዛሙርቱ ወደ ገሊላ ባህር ሄዱ፣ 17ወደ ጀልባ ገበተው ባህሩን አቋርጠው ወደ ቅፍርናሆም ከተማ እየቀዘፉ መጓዝ ጀመሩ፡፡ አሁን ጊዜው ጨልሞ ነበር፣ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር አልነበረም፡፡ 18ሀይለኛ ነፋስ መንፈስ ጀመረ፣ የባህሩ ማዕበልም በጣም የከፋ ሆነ፡፡ 19 20 21 ወደ አምስት ወይም ስደስት ኪሎሜትሮች ከቀዘፉ በኋላላ ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስ በውሃ ላይ ሲራመድና ወደ ጀልባው ሲመጡ አዩ፡፡ ደንግጠው ነበር! 20ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ “እኔ ነኝ! አትፍሩ!” 21እርሱን ወደ ጀልባው ለማስገባት በጣም ደስተኞች ነበሩ፡፡ ወዲያው እርሱ አብሯቸው ጀልባቸው ወደሚሄድበት ስፍራ ደረሰ፡፡ 22 23 በማግስቱ ከሀይቁ በሌላኛው ዳርቻ የነበረው የህዝብ ስብስብ ከአንድ ቀን ቀደም ብሎ በዚያ አንድ ጀልባ ብቻ እንደነበረ አወቁ፡፡ ኢየሱስ በጀልባ ከደቀመዛሙርቱ ጋር አብሮ እንዳልሄደም ጭምር አውቁ፡፡ 23አንዳንድ ሰዎች ከጥብርያዶስ ከተማ በነበሯቸው ሌሎች ጀልባዎች ሐይቁን አቋርጠው መጡ፡፡ ጀልባዎቻቸውን ጌታ እግዚአብሔርን አመስግኖ እንጀራ በበሉበት ስፍራ አጠገብ አደረጉ፡፡ 24 25 ሰዎቹ ኢየሱስ ወይም ደቀመዛሙርቱ በዚያ እንደሌሉ ሲያውቁ፣ አንዳንዶቹ ወደእነዚያ ጀልባዎች ገብተው ኢየሱስን ለመፈለግ ወደ ቅፍርናሆም ተጓዙ፡፡ 25 ከገሊላ ባህር በሌላው ዳርቻ በቅፍርናሆም ኢየሱስን ፈልገው አገኙት፡፡ እንዲህ ብለውም ጠየቁት፣ “መምህር፣ መቼ ወደዚህ መጣህ?” 26 27 ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፣ “እኔ እውነቱን እየነገርኳችሁ ነው፣ የምትፈልጉኝ እኔ ማን እንደሆንኩ የሚያሳይ ተአምራቶች ሳደርግ ስያችሁ አይደለም፡፡ የመትፈልጉኝ እስክትጠግቡ ድረስ እንጀራ ስለበላችሁ ነው፡፡ 27በቶሎ ለሚጠፋ ምግብ መስራትን አቁሙ! ይልቁንም የዘለዓለም ህይወት ለሚሰጣችሁ ምግብ ስሩ! እኔ የሰው ልጅ የእግዚአብሔር ምርጥ የሆንኩ የምሰጣችሁእንጀራ ያ ነው፡፡ እግዚአብር አብ በእያንዳንዱ መንገድ ስለ እኔ አረጋግጧል፡፡ 28 29 ከዚያ ሰዎቹ እንዲህ ብለው ጠየቁት፣ “እገዚአብሔርን ለማስደሰት ምን ስራዎችንና አገልግሎት መስራት አለብን?” 29ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፣ “እግዚአብሔር እናንተ እንድትሰሩት የሚፈልገው ይህ ነው፤ እርሱ በላከው በእኔ እመኑ፡፡” 30 31 ስለዚህም እንዲህ አሉት፣ “ማን እንደሆንክ ለማረጋገጥ ሌላ ተአምር አድርግ፣ ይህ ከሆነ አይተን ከእግዚአብሔር መምጣትህን እናምናለን፡፡ ለእኛ ምን ታደርጋለህ 31አባቶቻችን መና በሉ ልክ መጽሐፍ እንደሚል ‘እግዚአብሔር ይበሉ ዘንድ ከሰማይ እንጀራ ሰጣቸው፡፡” 32 33 34 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ “እኔ እውነቱን እየነገርኳችሁ ነው፡ ለሙሴ ያንን እንጀራ ለአባቶቻችሁ የሰጠው ሙሴ አልነበረም፡፡ አይ አልነበረም፣ ከሰማይ እውነተኛውን እንጀራ እየሰጣችሁ የሚገኘው አባቴ ነው፡፡ 33በዓለም የሚገኝ እያንዳንዱ በእውነት መኖር እንዲችል ከሰማይ የወረደ የእግዚአብሔር እውነተኛ እንጀራ እኔ ነኝ፡፡ 34እነርሱ እንዲህ አሉት፣ “ጌታችን፣ ሁልጊዜ ይህን እንጀራ ስጠን፡፡” 35 36 37 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ “በህይወት የማኖራችሁ እንጀራ እኔ ነኝ፡፡ ማንም ወደ እኔ የሚመጣ በፍጹም አይራብም፡፡ ማንም በእኔ የሚያምን በፍጹም አይጠማም፡፡ 36የሆነ ሆኖ፣ እኔ ነግሬያችኋለሁ፣ ምንም እንኳን ብታዩኝም እስከአሁን በእኔ አላመናችም፡፡37አባቴ ለእኔ የሰጠኝ ሰዎች ሁሉ ወደ እኔ ይመጣሉ፣ እኔም ወደ እኔ የመጣውን ማንንም ወደ ውጭ አላወጣውም፡፡ 38 39 40 ከሰማይ ወርጄ የመጣሁት እኔ የምፈልገውን ለማድረግ አይደለም፣ ነገር ግን የላከኝን የእርሱን ፈቃድ ለማድረግ ነው፡፡ 39የላከኝ የሚፈልገው ይህንን ነው፣ እሱ ከሰጠኝ አንዱንም እንዳላጠፋ ደግሞም በመጨረሻው ቀን እነርሱን ሁሉ እንዳስነሳ ነው፡፡ 40አባቴ የሚፈልገው ይህንን ነው፣ በእምነት ልጁ የሆነኩትን እኔን የሚመለከት እያንዳንዱ፣ እና በእኔ የሚያምን የዘለዓለም ህይወት ይኖረዋል፡፡ እኔ በመጨረሻው ቀን አስነሳቸዋለሁ፡፡” 41 42 እርሱ፣ “ከሰማይ የወረደ እንጀራ እኔ ነኝ” ስላለ አይሁድ ስለ ኢየሱስ ማጉረምረም ጀመሩ፡፡ 42እንዲህም አሉ፣ “ይህ አባቱ ዮሴፍ የሆነው ኢየሱስ አይደለምን? እኛ አባቱንና እናቱን አናውቅምን? በምን እውነት፣ “እኔ ከሰማይ መጥቻለሁ ማለት ይችላል?” 43 44 45 ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፣ “እርስ በእርሳችሁ ማጉረምረም አቁሙ፡፡ 44የላከኝ አብ ወደ እኔ ካልሳበው ማንም ወደ እኔ መምጣት አይችልም፡፡ ወደ እኔ የመጣውን፣ እርሱን በመጨረሻው ቀን እኔ አስነሳዋለሁ፡፡ 45በነቢያት እንዲህ ተጽፎአል፣ ‘እግዚአብሔር እነርሱን ሁሉንም ያስተምራል፡፡’ እያንዳንዱ ከአብ የሰማና የተማረ ወደ እኔ ይመጣል፡፡ 46 47 ከእግዚአብሔር ከመጣሁት ከእኔ በቀር ማንም አብን አላየም፡፡ እኔ ብቻ አብን አይቻለሁ፡፡ 47እኔ እውነቱን እየነገርኳችሁ ነው፡፡ ማንም በእኔ የሚያምን የዘለዓለም ሕይወት አለው፡፡ 48 49 እውነተኛ ሕይወት የምሰጥ እንጀራ እኔ ነኝ፡፡ 49አባቶቻችሁ በበረሃ መና በሉ፣ ይሁን እንጂ ሞቱ፡፡ 50 51 የሆኖ ሆኖ፣ እኔ የምናገርለት እንጀራ ከሰማይ የወረደ እንጀራ ነው፣ እርሱን የበላ በፍጹም አይሞትም፡፡ 51እኔ ሰዎች በእውነት እንዲኖሩ የማደርግ እንጀራ ነኝ፣ ከሰማይ የወረደ እንጀራ እኔ ነኝ፡፡ ማንም ይህን እንጀራ ቢበላ፣ እርሱ ለዘለዓለም ይኖራል፡፡ ለዓለም ሕይወት እንዲሆነ እኔ የምሰጠው እንጀራ የአካላዊ ስጋዬ መሞት ነው፡፡” 52 53 አሁን ኢየሱስን የሰሙ አይሁዶች በመካከላቸው በቁጣ ተከራከሩ፡፡ ማንም ቢሆን የራሱን ሥጋ ሌሎች እንደሚበሉ ቃል ሊገባ እንደሚችል ሊገባቸው አልቻለም፡፡ 53ስለዚህ ኢየሱስ በከባድ ቃላት ፊት ለፊት ተጋፈጣቸው፡፡ “እኔ እውነቱን እየነገርኳችሁ ነው የእኔን፣ የሰው ልጅ፣ ስጋ ካልበላችሁ በስተቀር እና የእኔነ ደም ካልጠጣች በፍጹም ለዘለዓለም አትኖሩም፡፡ 54 55 56 የእኔን ስጋ የሚበሉና ደሜን የሚጠጡ ለዘለዓለም ይኖራሉ፣ በመጨረሻውም ቀን እንደገና ህያው አደርጋቸዋለሁ 55ምክንያቱም ስጋዬ እውነተኛ መብል ደሜ እውነተኛ መጠጥ ነው፡፡ 56ማንም ስጋዬን የበላ እና ደሜን የጠጣ ከእኔ ጋር አንድ ይሆናል እኔም ከእርሱ ጋር አንድ እሆናሁ፡፡ 57 58 59 እያንዳንዱን ህያው የሚያደርገው አባቴ እኔን ልኮኛል፣ እናም እኔ እኖራለሁ ምክንያቱም አባቴ ህያው መሆን እንድችል አድርጎኛል፡፡ በተመሳሳይ መንገድ፣ ከእኔ የተመገቡ እኔ ለእነርሱ ካደረግሁት የተነሳ ለዘለዓለም ይኖራሉ፡፡ 58ከሰማይ የመጣ እውነተኛ እንጀራ እኔ ነኝ፡፡ ማንም እኔን የሚበላ፣ ይህን እንጀራ የሚበላ፣ በፍፁም አይሞትም፤ ነገር ግን ለዘለዓም ይኖራል! እኔ የማደርገው በአባቶቻችሁ እንደሆነው አይደለም ምክንያቱም እነርሱ መናውን በልተው ከዚያ ሞቱ፡፡” 59ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች በቅፍርናሆም ከተማ በምኩራብ ሲያስተምር ተናገረ፡፡ 60 61 ብዙዎቹ ደቀመዛሙርቱ እንዲህ አሉ፣ “የሚያስተምረውን ለመረዳት ከባድ ነው፡፡ የሚናገረውን ማን ሊቀበለው ይችላል” 61ኢየሱስ አንዳዶቹ ደቀመዛሙርቱ ቅሬታ እያሰሙ መሆኑን ያውቅ ነበር፣ ስለዚህም እንዲህ አላቸው፣ “የማስተምረው ያሰናክላችኋልን?” 62 63 የሰው ልጅ፣ ወደ ሰማይ ተመልሼ ስሄድ ብታዩኝ ምን ትላላችሁ 63መንፈስ የሚሰጠው ብቻ ማንም ለዘለዓም እንዲኖር ማድረግ ይችላል፡፡ የሰው ባህሪ በዚህ ጉዳይ ምንም አይረዳም፡፡ እኔ ያስተማርኳችሁ ቃላት መንፈስ ናቸው፣ እናም ሰዎች ለዘለዓም እንዲኖሩ ያደርጋሉ፡፡ 64 65 እኔ እያስተማርኳችሁ ያለሁትን ገና ያላመናችሁ አንዳንዶች አላችሁ፡፡ “ኢየሱስ ይህን ያለበት ምክንያት ከሥራው መጀመሪያ አንስቶ በእርሱ የማያምነው ማን እንደሆነ ያውቅ ስለነበረና የሚክደውንም ሰው ስለሚያውቅ ነው፡፡ 65ከዚያ እንዲህ አለ፣ “አብ ወደ እኔ እንዲመጣ ካላስቻለው በስተቀር ማንም ወደ እኔ ሊመጣና ለዘለዓለም ሊኖር አይችልም ብዬ የነገርኳችሁ ለዚህ ነው፡፡” 66 67 68 69 ከዚያ ጊዜ አንስቶ፣ ብዙዎቹ የኢየሱስ ደቀመዛሙርት እርሱን ከመከተል ወደኋላ ተመለሱ፡፡ 67ስለዚህም ለአስራ ሁለቱ እንዲህ አላቸው፣ “እናንተ ደግሞ እኔን መተው ትፈልጋላችሁን?” 68ስምኦን ጴጥሮስ፣ “ጌታ ሆይ፣ እኛ ወደ ማን እንሄዳለን አንተ ብቻ ለዘለዓለም ለመኖር የሚፈቅድልን መልዕክት አለህ! 69እኛ በአንተ እናምናለን፣ አንተ ቅዱሱ እግዚአብሔር የላከህ መሆንህን በእርግጠኝነት እናውቃለን!” አለ፡፡ 70 71 ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፣ “አስራ ሁለታችሁን ደቀመዛሙርት የመረጥኳችሁ እኔ አይደለሁምን ሆኖም ከእናንተ አንዱ ሰይጣን ነው!” 71ስለ ይሁዳ፣ የስምዖን አስቆሮቶስ ልጅ ስለሆነው፣ እየተናገረ ነበር፡፡ ይሁዳ ከአስራ ሁለቱ አንዱ ቢሆንም እንኳን በኋላ ኢየሱስን የሚክደው እርሱ ነበር፡፡

ምዕራፍ 7

1 2 ከዚህ በኋላላ ኢየሱስ በገሊላ አውራጃ ወደ ሌላ ስፍራዎች ሄደ፡፡ ወደ ይሁዳ መሄዱን ተወ ምክንያቱም የአይሁድ ባለስልጣናት እርሱን በወንጀል የሚከሱበትንና የሚገድሉበትን መንገድ ይፈልጉ ነበር፡፡ 2አሁን ጊዜው የአይሁድ የዳስ በዓል ነበር፡፡ ይህ ጊዜ የአይሁድ ህዝቦች ከረጅም ዘመናት በፊት በመውጣት ወቅት በድንኳኖች የኖሩበትን የሚያስታውሱበት ነው፡፡ 3 4 የኢየሱስ ወንድሞች እንዲህ አሉት፣ “ይህን አካባቢ ትተህ ወደ ይሁዳ ሂድ ይህን ካደረግህ ሌሎች ተከታዮችህ ማድረግ የምትችለውን ሀይል ያለው ስራ ማየት ይችላሉ፡፡ 4ሰዎች ምን አይነት ሰው እንደሆነ እንዲያውቁ ከፈለገ ማንም ሰው ስራውን አይደብቅም፡፡ ራስህን ለዓለም ግለጽ!” 5 6 7 የራሱ ወንድሞች እንኳን በእርሱ አላመኑበትም ወይም እውነቱን እየተናገረ እንደሆነ አላሰቡም፡፡ 6ስለዚህም ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ “ስራዬን የማበቃበት ጊዜ ገና አልደረሰም፡፡ እናንተ ግን የወደዳችሁትን በማንኛውም ጊዜ ለማድረግ መምረጥ ትችላላችሁ፡፡ 7ለራሳቸው የሚኖሩና የዚህን ዓለም ነገሮ የሚወዱ ሰዎች እናንተን ሊጠሉ አይችሉም፣ እኔን ግን ይጠሉኛል፡፡ በህይወታቸው የሚያደርጉት ክፉ መሆኑን የምነግራቸው እኔ ነኝ፡፡ 8 9 እናንተ ወደ በዓሉ ሂዱ፡፡ እኔ አሁን አልወጣም፤ ለእኔ ትክክለኛው ጊዜ አይደለም፡፡” 9ኢየሱስ ያንን ከተናገረ በኋላላ በገሊላ ትንሽ ጊዜ ቆየ፡፡ 10 11 የሆነ ሆኖ፣ ወንድሞቹ ወደ በዓሉ ከሄዱ ከጥቂት ቀናት በኋላ፣ እርሱም ደግሞ ሄደ፣ ነገር ግን እንደሚመጣ ለማንም አልነገረም ነበር፡፡ 11አይሁዳውያን ተቃዋሚዎቹ በበዓሉ እንደሚያገኙት ተስፋ በማድረግ እርሱን ይፈልጉት ነበር፡፡ “ኢየሱስ የት ነው? በዚህ አለን?” እያሉ ሰዎችን ይጠይቁ ነበር፡፡ 12 13 ከህዝቡ መካከል ብዙዎቹ ሰዎች ስለ ኢየሱስ እርስ በርሳቸው በጣም ይነጋገሩ ነበር፡፡ አንዳዶቹ “እሱ መልካም ሰው ነው!” ሲሉ ሌሎቹ “አይ ህዝቡን ያስታል ደግሞም በተሳሳተ መንገድ ይመራል!” አሉ 13አይሁዳዊ የሆኑ ጠላቶቹን በመፍራት ማንም ህዝብ በተሰበሰበበት ስለ እርሱ ሌሎች እየሰሙት የሚያወራ አልነበረም፡፡ 14 15 16 የዳስ በአሉ በከፊል ሲጠናቀቅ፣ ኢየሱስ ወደ ቤተመቅደስ አደባባይ ሄዶ በዚያ ማስተማር ጀመረ፡፡ 15አይሁዶች እርሱ በሚናገረው ተደንቀው ነበር፡፡ “ይህ ሰው እውቅና ባለው አስተማሪ አስተምህሯችንን በፍፁም አላጠናም፣ በትምህርት ቤታችን ገብቶ አልተማረም! እንዴት ይህን ያህል ብዙ ማወቅ ቻለ?” አሉ፡፡ 16ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፣ “እኔ የማስተምረው ትምህርት ከራሴ የሚመጣ አይደለም፡፡ እኔ የማስተምረው ትምህርት የሚመጣው ከላከኝ ነው፡፡ 17 18 ማንም እግዚአብሔር የሚፈልገውን ለመስራት ከመረጠ፣ እኔ የማስተምረው ትምህርት ከእግዚአብሔር ይምጣ ወይም እኔ በራሴ ስልጣን ብቻ ልናገር ማወቅ ይችላል፡፡ 18ማንም በራሱ ስልጣን የሚናገር ሌሎች እርሱን ብቻ እንዲያከብሩት ይናገራል፡፡ ሆኖም፣ አገልጋይ የላከውን ለማክበር ጠንክሮ ከሰራ፣ እንደ ታማኝ ሰው ለላከው ጥሩ ዝና ለማትረፍ ይሰራል በዚያ አይነቱ አገልጋይ ምንም ጥፋት የለም፡፡ 19 20 ሙሴ ህጉን አልሰጣችሁምን? ሆኖም አንዳችሁም ህጉ የሚጠይቀውን አላደረጋችም፡፡ አሁን እኔን ለመግደል የምታሴሩት እናንተ ናችሁ! 20ከህዝቡ መሃል አንዱ እንዲህ ሲል ተናገረ፣ “አንተ ሰይጣን አለብህ! አንተን ለመግደል የሚፈልግን ሰው ስም ጥራ!” 21 22 ኢየሱስ ለተሰበሰቡት ሰዎች እንዲህ ሲል መለሰላቸው፣ “እናንተ እንድታዩ አንድ የሀይል ስራ ስሰራ እናንተ ሁላችሁ በዚያ ትደነቃላችሁ፡፡ 22ሙሴ ህግ ሰጣችሁ፣ ያ ህግ ወንድ ልጆቻችሁን መግረዝ አለባችሁ ይላል ይህንንም ልጁ ከተወለደ በትክክል በሰባተኛው ቀን ማድረግ አለባችሁ፡፡ (በጣም ትክክል ለመሆን፣ ይህ ስርዓት ከቀደሙት አባቶቻችሁ ከአብርሃም፣ ይስሐቅና ያዕቆብ እንጂ ስለዚህ ተግባር የጻፈላችሁ ሙሴ አይደለም) በህጉ በመጠየቁ ምክንያት፣ አንዳንድ ጊዜ አንድን ህጻን በሰንበት ቀን ትገርዛላችሁ፣ እናም ያ ደግሞ ስራ መስራት ነው! 23 24 እናንተ አንዳንድ ጊዜ ወንዶች ልጆችን በሰንበት ስትገርዙ የሙሴን ህግ እንዳፈረሳችሁ አትቆጥሩም፡፡ በሰንበት ሰውን ስፈውስ እኔን በሰንበት ሰራህ በማለት ለምን ትቆጣላችሁ፡፡ አንድን ሰው መፈወስ አንድን ልጅ ከመገረዝ የበለጠ አስደናቂ ስራ ነው! 24የእግዚአብሔርን ህግ በተሳሳተ አንጻር በማየትና ሚዛናዊ ባለመሆን! ይህን ሰው መፈወስ ልክ ነው! ወይም ስህተት ነው ማለትን አቁሙ፡፡ ይልቁንም፣ በሰው ዕይታ ሳይሆን ከእግዚአብሔር አንጻር ትክክልና ፍትሃዊ የሆነውን በማየት አንድ ሰው ማድረግ ያለበትንና እንዴት ሊፈርድበት እንደሚገባ ወስኑ፡፡” 25 26 27 ከኢየሩሳሌም የመጡ አንዳንድ ሰዎች እንዲህ ይሉ ነበር፣ “ሊገድሉት የሚፈልጉት ሰው ይህ አይደለምን 26እሱ እነዚህን ነገሮች በህዝብ መሀል ይናገራል፣ ነገር ግን ባለስልጣናት እሱን ለመቃወም ምንም ነገር እየተናገሩ አይደለም፡፡ እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ እነሱ ስላወቁ ነውን? 27ነገር ግን ይህ ክርስቶስ ሊሆን አይችልም ምክንያቱም ይህ ሰው ከየት እንደመጣ እኛ እናውቃለን፡፡ክርስቶስ ሲመጣ፣ ማንም እርሱ ከየት እንደሆነ አያውቅም፡፡” 28 29 ስለዚህ ኢየሱስ በቤተ መቅደስ አደባባይ ሲያስተምር ሳለ፣ ድምጹን ከፍ አድርጎ እንዲህ አለ፣ “አዎን፣ እናንተ እኔን እናውቅሃለን ትላላችሁ፣ እኔ ከየት እንደሆንኩ የምታውቁ ይመስላችኋል፡፡ ነገር ግን እኔ ወደዚህ የመጣሁት ራሴን ሾሜ አይደለም ይልቁንም፣ የላከኝ እውነቱን ስለ እኔ ይመሰክራል፣ እናንተ እሱን አታውቁም፡፡ 29እኔ አውቀዋለሁ ምክንያቱም እኔ የመጣሁት ከእርሱ ነው፡፡ የላከኝ እርሱ ነው፡፡” 30 31 32 ከዚያ እጃቸውን በእርሱ ላይ ሊጭኑ ሞከሩ፣ ነገር ግን ማንም ሊያስረው አልቻለም፡፡ ምክንያቱም ስራውን ለመጨረስ ጊዜው ገና አልደረሰም ነበር፤ ህይወቱም ሊያበቃ ገና ነበር፡፡ 31ከህዝቡ መሀል ብዙዎች ከሰሙት እና ስራዎቹን ካዩ በኋላ በእርሱ ላይ እምነት አደረባቸው፡፡ እንደዚህም አሉ፣ “ክርስቶስ ሲመጣ ይህ ሰው ካደረገው በላይ ተአምራቶችንና ምልክቶችን ማድረግ ይችል ይሆን?” 32ሰዎች አብዝተው ስለ ኢየሱስ እንደነዚህ አይነት ነገሮችን ሲናገሩ ፈሪሳውያን አደመጡ፡፡ ስለዚህም ሊቀ ካህናቱና ፈሪሳውያኑ በአንድነት እርሱን እንዲያስሩ መኮንኖችን ላኩ፡፡ 33 34 ከዚያ ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ “እኔ ለትንሽ ጊዜ ብቻ ከእናንተ ጋር እሆናለሁ ከዚያ ወደላከኝ ተመልሼ እሄዳለሁ፡፡ 34እናንተ እኔን ትፈልጉኛላችሁ፣ ነገር ግን አታገኙኝም፡፡ እኔ ወደምሄድበት እናንተ ልትመጡ አትችሉም፡፡ 35 36 ስለዚህ የእርሱ ጠላቶች የነበሩ አይሁዳዊ ሰዎችን ራሳቸውን እንዲህ ብለው ጠየቁ፣ “ይህ ሰው እኛ ልናገኘው ወደማንችለው ወዴት ሊሄድ ነው? አይሁዳዊያን በተበተኑበት በግሪክ አለም ዙሪያ ሊሄድና በዚያ ያሉ ሰዎችን እዚህን አዲስ ነገሮች ሊያስተምር አቅዷል? 36‘እናንተ እኔን ትፈልጉኛላችሁ፣ ነገር ግን ልታገኙኝ አትችሉም’ ሲል ምን ማለቱ ነው? እንዲሁም፣ ‘እኔ ወደምሄድበት፣ እናንተ ልትመጡ አትችሉም’ ሲል ምን ማለቱ ነው?” 37 38 ስለዚህ በበዓሉ በመጨረሻ ቀን፣ በታላቁ ቀን፣ ኢየሱስ ተነስቶ በታላቅ ድምጽ እንዲህ ብሎ ጮኸ፣ “ማንም ተጠምቶ ቢሆን፣ ወደ እኔ ይምጣና ይጠጣ፡፡” 38ማንም በእኔ የሚያምን፣ መጽሐፍ እንደሚል፣ ‘ከልቡ የህይወት ውሃ ወንዞች ይፈሳል፡፡’” 39 እርሱ ይህን በእርሱ ለሚያምኑ አብ ሊሰጠው ስላለው መንፈስ ተናገረ፡፡ እግዚአብሔር መንፈሱን በእርሱ በሚያምኑት ውስጥ እንዲኖር ገና አልላከም ነበር፡፡ ምክንያቱም ኢየሱስ በሞቱ በኩል ሰዎችን በማዳን ለእግዚአብሔር ትልቅ ክብር የሚያመጣውን ስራውን ገና አልጨረሰም ነበር፡፡ 40 41 42 ከህዝቡ አንዳንዶቹ እነዚያን ቃላት ሲሰሙ፣ እንዲህ አሉ፣ “ይህ በእውነት የምንጠብቀው ነቢይ ነው፡፡” 41ሌሎች ደግሞ እንዲህ አሉ፣ “ክርስቶስ ከገሊላ ሊመጣ አይችልም፡፡ 42መጽሐፍት ክርስቶስ ከዳዊት ዘር መምጣትና ደግሞም እርሱ የዳዊት ቤት በሆነችው መንደር በቤተልሔም መወለድ አለበት ይሉ የለምን?” 43 44 ስለዚህ ስለ ኢየሱስ የአስተያየት ልዩነት ነበር፡፡ 44አንዳንዶቹ ሰዎች ሊያስሩት ፈለጉ፡፡ ሆኖም ማንም እጁን አልጫነበትም፡፡ 45 46 ስለዚህ መኮንኖቹ ወደ ሊቀ ካህናቱና ፈሪሳውያኑ ተመለሱ፡፡ እነዚህ መሪዎች ኢየሱስን እንዲያስሩ የላኳቸው መኮንኖች ነበሩ፡፡ ፈሪሳውያኑ መኮንኖቹን እንዲህ አሏቸው፣ “ለምን እርሱን አልያዛችሁትምና ወደዚህ አላመጣችሁትም?” 46መኮንኖቹ እንዲህ ብለው መለሱ፣ “እንደዚህ ሰው ከቶ ማንም ተናግሮ አያውቀም፡፡” 47 48 49 ከዚያ ፈሪሳውያኑ፣ “እናንተም ደግሞ ተታለላችሁን? 48ከአይሁድ ባለስልጣናት ወይም ከፈሪሳውያን አንድም ኢየሱስን አላመነም፡፡ 49የህጋችንን ትምህርት የማያውቁ ይህ የሰዎች ክምችት፣ እነርሱ የተረገሙ ይሁኑ!” 50 51 52 ከዚያ ኒቆዲሞስ ተናገረ፡፡ እርሱ ኢየሱስን ለማየት የሄደውና በምሽት ከእርሱ ጋር የተነጋገረው ነበር፡፡ ከፈሪሳውያን አንዱ ነበር፣ ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ 51“በእኛ በአይሁዶች ህግ አንድን ሰው ሳንሰማው መኮነን የተፈቀደ አይደለም፡፡ በመጀመሪያ፣ እንዲናገር እድል እንሰጠዋለን፣ እናም የሰራውን ማወቅ አለብን፡፡” 52እንዲህ ብለው መለሱለት፣ “አንተም ደግሞ ከገሊላ ነህን በጥንቃቄ መርምር ደግሞም በመጽሐፍት የተፃፈውን አንብብ! አንድም ነቢይ ከገሊላ እንዳልመጣ ታገኛለህ፡፡” 53 ከዚያ ሁሉም ትተው ወደየቤቶቻቸው ሄዱ፡፡

ምዕራፍ 8

1 2 3 ኢየሱስ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ወደ ደብረ ዘይት ተራራ ሄዶ ምሽቱን በዚያ አካባቢ ቆዩ፡፡ 2በማግስቱ ማልደው ወደ ቤተ መቅደስ ቅጽር ግቢ ተመለሱ፡፡ ብዙ ሰዎች በኢየሱስ ዙሪያ ተሰብስበው እርሱ ሊያስተምራቸው ተቀመጠ፡፡ 3ከዚያ የአይሁድ ህግን የሚያስተምሩ ሰዎችና ጥቂት ፈሪሳውያን አንዲት ሴት ወደ እርሱ አመጡ፡፡ እርሷ በዝሙት ድርጊት ተይዛ ነበር ማለትም የራሷ ባል ካልሆነ ሰው ጋር ተኝታ ነበር፡፡ በዚህ ቡድን ፊት ሊጠይቋት አቆሟት፡፡ 4 5 6 ኢየሱስን እንዲህ አሉት፣ “መምህር፣ ይህቺ ሴት ባሏ ካልሆነ አንድ ወንድ ጋር ዝመት ስትፈጽም ተይዛለች፣ 5ሙሴ በህግ እንዲህ ያለችውን ሴት በድንጋይ ወግረን እንድንገድላት አዞናል፡፡ ሆኖም ግን፣ እኛ ምን ማድረግ አለብን ትላለህ?” 6ይህን ጥያቄ የጠየቁት አንዳች የተሳሳተ ነገር ተናገረ በሚል መክሰስ እንዲችሉ እንደ ወጥመድ ነበር፡፡ ልትገድሏት አትችሉም ብሎ ቢናገር፣ የሙሴን ህግ አቃለለ ብለው ሊናገሩ ይችላሉ፡፡ ልትገድሏት ትችላላችሁ ብሎ ቢናገር፣ ለገዥዎች የተተወውን ሰዎችን የመግደል ስልጣን በመተላለፍ የሮማዊያንን ህግ ይጥሳል፡፡ ሆኖም ኢየሱስ ጎንበስ ብሎ በጣቶቹ መሬት ላይ አንዳች ነገር ጻፈ፡፡ 7 8 እርሱን መጠየቃቸውን ሲቀጥሉ፣ እርሱ ተነስቶ ቆሞ እንዲህ አላቸው፣ “ከእናንተ ማንናቸውም ሀጢአት ሰርቶ የማያውቅ እርሱ እርሷን ለመቅጣት ሌሎችን መምራት አለበት፡፡ ያ ሰው የመጀመሪያውን ድንጋይ ይወርውር!” 8ከዚያ ጎንበስ ብሎ ሌላ ተጨማሪ ነገር መሬት ላይ ጻፈ፡፡ 9 10 11 እሱ የተናገረውን ከሰሙ በኋላ ይጠይቁት የነበሩት በመጀመሪያ ትላልቆቹ ከዚያም ወጣቶቹ አንድ በአንድ እያሉ ትተው መሄድ ጀመሩ፡፡ ሁሉም ሀጢአተኞች እንደሆኑ አወቁ፡፡ በመጨረሻ ኢየሱስ ብቻ ከሴትየዋ ጋር በዚያ ነበሩ፡፡ 10ኢየሱስ ተነሳና እንዲህ ሲል ጠየቃት፣ “አንቺ ሴት፣ እነዚያ የከሰሱሽ የት ናቸው? መቀጣት እንዳለብሽ ክስ ያቀረበብሽ ማንም የለም?” 11እንዲህ ስትል መለሰች፣ “አይ፣ ጌታዬ፣ አንድም የለም፡፡” ከዚያ ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ “እኔም አልፈርድብሽም አሁን ወደ ቤትሽ ሂጂ፣ ከአሁን በኋላ እንደዚህ ደግመሽ ሀጢአት አትስሪ!) [1] የተሻሉት የቀደሙት ጥቅልል መጽሐፍት ዮሐንስ 7:35- 8:11 የላቸውም፡፡ 12 13 ኢየሱስ ለሰዎች ደግሞ ተናገረ፡፡ እንዲህም አለ፣ “እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፡፡ ማንም እኔን የሚከተል ህይወት የሚሰጥ ብርሃን ይኖረዋል፣ እርሱ ዳግም በጨለማ አይመላለስም፡፡ 13ስለዚህ ፈሪሳዊያን እንዲህ አሉት፣ “ስለ ራስህ አብዝተህ በመናገር አንተን እንድናምንህ እኛን ለማሳመን የምትሞክር ይመስላል! ስለ ራስህ የምትናገረው አንዳች ነገር አያረጋግጥም!” 14 15 16 ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰ፣ “ስለ ራሴ እነዚህን ነገሮች የምናገረው እኔ ራሴ ብቻ ብሆንም እንኳን፣ የምናገረው እውነት ነው ምክንያቱም ከየት እንደመጣሁ አውቃለሁ፡፡ ደግሞም ወዴት እንደምሄድ አውቃለሁ፡፡ ሆኖም ግን፣ እናንተ ከየት እንደመጣሁ አታውቁም ደግሞም ወዴት እንደምሄድ አታውቁም፡፡ 15እናንተ ሰዎችን በሰው ደረጃዎችና በሰዎች ህጎች መሠረት ትፈርዳላችሁ፡፡ በዚህን ጊዜ የመጣሁት በማንም ላይ ለመፍረድ አይደለም፡፡ 16በምፈርድበት ጊዜ፣ ፍርዴ ትክክልና ልክ ይሆናል ምክንያቱም ፍትሁን የምሰጠው ብቻዬን አይደለም እኔና የላከኝ አብ ፍትህን አብረን እንፈጽማለን፡፡ 17 18 በህጋችሁ አንድ ጉዳይ መፍትሄ የሚደረግለት ቢያንስ ማስረጃ የሚሰጡ ሁለት ምስክሮች ሲኖሩ ብቻ እንደሆነ ተጽፏል፡፡ 18ስለራሴ ለእናንተ ማስረጃ እያቀረብኩ ነው፣ ደግሞም የላከኝ አባቴ ስለ እኔ ማስረጃ እየሰጠ ነው፡፡ ስለዚህ እኛ የምንነግራችሁ እውነት እንደሆነ ማመን አለባችሁ፡፡ 19 20 ከዚያ እንዲህ ብለው ጠየቁት፣ “አባትህ የት ነው?” ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፣ “እናንተ እኔን አታውቁኝም፣ አባቴንም አታውቁትም፡፡ እኔን ብታውቁኝ ኖሮ፣ አባቴንም ታውቁት ነበር፡፡” 20እነዚህን ነገሮች የተናገረው በመቅደስ ቅጽር ግቢ ውስጥ ሰዎች ስጦታዎቻቸውን በሚያመጡበት ስፍራ ግምጃ ቤት አጠገብ በነበረበት ጊዜ ነበር፡፡ ሆኖም ማንም ሰው አልያዘውም ምክንያቱም የሚገደልበት ጊዜ አልደረሰም ነበር፡፡ 21 22 ኢየሱስ እንደዚህም ደግሞ አላቸው፣ “እኔ እሄዳለሁ፣ እናንተ ትፈልጉኛላችሁ፣ ነገር ግን በሀጢአታችሁ በእርግጥ ትሞታላችሁ፡፡ እኔ ወደምሄድበት፣ እናንተ መምጣት አትችሉም፡፡” 22አይሁዳዊ ተቃዋሚዎቹ እርስ በእርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፣ “ራሱን ሊገድል ነውን? ‘እኔ ወደምሄድበት፣ እናንተ መምጣት አትችሉም ሲል ያንን ማለቱ ነውን?’” 23 24 ኢየሱስ ለእነርሱ እንዲህ እያለ ቀጠለ፣ “እናንተ ከታች ከዚህ ምድር ናችሁ፣ ነገር ግን እኔ ከላይ ከሰማይ ነኝ፡፡ እናንተ የዚህ ዓለም ናችሁ፡፡ እኔ የዚህ ዓለም አይደለሁም፡፡ 24እኔ ትሞታላችሁ ብዬ ነግሬያችኋለሁ ደግሞም እግዚአብሔር በኃጢአቶቻችሁ ይኮንናችኋል፡፡ እኔ እኔ ነኝ ብዬ እንደተናገርኩ፣ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ ካላመናችሁ በስተቀር በእርግጥ በኃጢአቶቻችሁ እግዚአብሔር ይኮንናችኋል፡፡” 25 26 27 “አንተ ማን ነህ?” ብለው ጠየቁት፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ “ከመጀመሪያው አንስቶ፣ ስነግራችሁ ነበር! 26ልፈርድባችሁና በብዙ ነገሮች ጥፋተኞች ናችሁ ማለት እችላለሁ፡፡ ከዚህ ይልቅ፣ ይህን ብቻ እላችኋለሁ፤ እኔን የላከኝ እውነት ይናገራል፣ እኔም በዚህ ዓለም ላሉ ሰዎች ከእርሱ የሰማሁትን ብቻ እናገራለሁ፡፡” 27ስለ አብ እየተናገረ እንደነበረ አልገባቸውም፡፡ 28 29 30 ስለዚህም ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ “እኔን በመስቀል ላይ ከፍ ባደረጋችሁ ጊዜ እኔ፣ የሰውልጅ፣ እኔ እግዚአብሔር እንደሆንኩ ታውቀላችሁ፤ ደግሞም በራሴ ስልጣን ምንም ነገር እንደማላደርግ ታውቃላችሁ፡፡ ይልቁንም፣ እኔ የምናገረው አባቴ እንድናገር፣ ያስተማረኝን ብቻ ነው፡፡ 29የላከኝ እርሱ ከእኔ ጋር ነው፣ እሱ ብቻዬን አልተወኝም ምክንያቱም እኔ እርሱ ደስ የሚያሰኘውን ብቻ አደርጋሁ፡፡” 30ኢየሱስ እነዚህ ነገሮች ሲናገር ብዙ ሰዎች በተጨማሪ በእርሱ አመኑ፡፡ 31 32 33 ከዚያ ኢየሱስ አሁን በእርሱ ማመናቸውን ለተናገሩ አይሁዶች እንዲህ አለ፣ “ያስተማርኳችሁን ሁሉ ከሰማችሁና በምታደርጉት ነገር ሁሉ በትምህርቴ ከኖራችሁ፣ እናንተ እውነተኛ የእኔ ደቀመዛሙርት ናችሁ፡፡ 32እናንተ እውነቱን ታውቃላችሁ፣ እውነቱ የራሱ ባሪያ ካደረጋችሁ ማንኛውም ነገር ነፃ እንድትሆኑ ይመራችኋል፡፡” 33እነርሱ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፣ “እኛ የአብርሃም ዘሮች ነን ደግሞም የማንም ባሪያዎች ሆነን አናውቅም፡፡ ለምን እኛን ነጻ መሆን ያስፈልጋችኋል ትለናህ?” 34 35 36 ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፣ “እኔ እውነቱን እየነገርኳችሁ ነው፤ ባሪያ ጌታውን ለመታዘዝ እንደሚገደድ ሀጢአትን የሚያደርጉ ሁሉ የኃጢአተኝነት ፍላጎታቸውን ይታዘዛሉ፡፡ 35ባሪያዎች የአንድ ቤተሰብ ዋና አባል ሆነው አይቀሩም፡፡ ነገር ግን ወደ ቤት ለመመለስ ነጻ ይሆናሉ ወይም ይሸጣሉ፡፡ ሆኖም ግን፣ አንድ ልጅ ለሁልጊዜውም የአንድ ቤተሰብ አባል ነው፡፡ 36ስለዚህ ልጁ ነፃ ካወጣችሁ፣ ፍጹም ነፃ ትሆናላችሁ፡፡ 37 38 በአብርሃም ቤተሰብ ውስጥ እንደሆናችሁ አውቃለሁ፣ እናንተ የእርሱ ዘር ሀረግ ናችሁ፡፡ ሆኖም፣ የእናንተ ሰዎች እኔን ለመግደል እየሞከሩ ነው፡፡ እኔ የተናገርኩትን፣ ምንም ነገር አታምኑም፡፡ 38አባቴ ስላሳየኝ አስደናቂ ነገሮችና ጥበብ ሁሉንም ነገርኳችሁ፣ ነገር ግን እናንተ አባታችሁ እንድታደርጉት የነገራችሁን ብቻ እያደረጋችሁ ነው፡፡” 39 40 41 እነርሱ እንዲህ ብለው መለሱለት፣ “አብርሃም አባታችን ነው፡፡” ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ “እናንተ የአብርሃም ልጆች ብትሆኑ ኖሮ እርሱ ያደረጋቸውን ነገሮች ታደርጉ ነበር፡፡ 40ከእግዚአብሔር የሰማሁትን እውነት ስነግራችሁ ነበር፣ ነገር ግን እናንተ ልትገድሉኝ እየሞካራችሁ ነው፡፡ አብርሃም እንደዚህ የመሰሉ ነገሮችን አላደረገም፡፡ 41አይ! እናንተ እያደረጋችሁት የምትገኙት እርግጠኛ አባታችሁ ያደረገውን ነው፡፡” እነርሱ እንዲህ አሉት፣ “እኛ ስለ አንተ አናውቅም፣ ነገር ግን እኛ ህጋዊ ያልሆኑ ልጆች አይደለንም፡፡ እኛ አንድ አባት ብቻ አለን፣ እርሱም እግዚአብሔር ነው፡፡” 42 43 44 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ “እግዚአብሔር አባታችሁ ቢሆን ኖሮ፣ እናንተ እኔን ትወዱኝ ነበር ምክንያቱም እኔ ከእግዚአብሔር መጥቻለሁ እናም አሁን ወደዚህ ዓለም መጣሁ፡፡ እኔ ራሴ ለመምጣት ወስኜ አልመጣሁም ነገር ግን እርሱ ስለላከኝ መጥቻለሁ፡፡ 43የምናገረው ለምን እንደማይገባችሁ እነግራችኋለሁ፡፡መልእክቴን ወይም ትምህርቶቼን ስላልተቀበላችሁ ነው፡፡ 44እናንተ የአባታችሁ ናችሁ፣ የሰይጣን ናችሁ፣ እርሱ የሚፈልገውን ማድረግ ትፈልጋላችሁ፡፡ እርሱ ሰዎች በመጀመሪያ ኃጢአት ከሰሩበት ጊዜ አንስቶ ነብሰ ገዳይ ነበር፡፡ እርሱ የእግዚአብሔርን እውነት ጥሏል፣ በእርሱ ውስጥ የእግዚአብሔር እውነት የለም፡፡ በሚዋሽበት ጊዜ ሁሉ፣ እንደ ባህርይው እየተናገረ ነው ምክንያቱም እርሱ ውሸታም ነው፤ የሚዋሽ ሁሉ ሰይጣን እንዲሰራ የሚፈልገውን እየሰራ ነው፡፡ 45 46 47 እኔ እውነት ስለነገርኳችሁ፣ እናንተ እኔን አታምኑም! 46ከእናንተ በኃጢአት ጥፋተኛ ሆኜ ያገኘኝ ማንኛችሁ ናችሁ? እውነት እስከ ነገርኳችሁ ደረስ፣ እኔን ላለማመን ምን ምክንያት ትሰጣላችሁ? 47የእግዚአብሔር የሆኑ እነርሱ እርሱ የሚነግራቸውን ይሰማሉ ይታዘዙማል፡፡ የእርሱን መልዕክት የማትሰሙበትና የማትታዘዙበት ምክንያት የእግዚአብሔር ስላልሆናች ነው፡፡” 48 49 አይሁዳዊ ጠላቶቹ እንዲህ ሲሉ መለሱለት፣ “አንተ ሳምራዊ ነህ በማለታችን በእርግጥም ትክክለኞች ነን አንተ በእርግጥ ፈጽሞውኑ እውነተኛ አይሁድ አይደለህም፡ - በአንተ ውስጥ ሰይጣን ይኖራል!” 49ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰ፣ “ሰይጣን በእኔ ውስጥ አይኖርም! እኔ አባቴን አከብረዋለሁ፣ እና እናንተ እኔን ታዋርዱኛላችሁ!” 50 51 ሰዎች እኔን እንዲያመሰግኑኝ ለማግባባት አልሞክርም፡፡ የሚገባኝን ሊሰጠን የሚፈልግ ሌላ አለ፣ እኔ የምለውንና የማደርገውን ሁሉንም ነገር የሚፈርደው እሱ ነው፡፡ 51እኔ እውነቱን እየነገርኳችሁ ነው፤ ማንም ቃሉን አጥብቆ ቢጠብቅና እኔ እንደተናገርኩ በቃሌ ቢያምን ያ ሰው በፍጹም አይሞትም!” 52 53 ከዚያ አይሁዳዊ ጠላቶቹ እንዲህ አሉት፣ “አሁን ሰይጣን በአንተ ውስጥ እንደሚኖር እርግጠኞች ነን! አብርሃምና ነቢያት ከረጅም ዘመን በፊቱ ሞቱ! ሆኖም አንተ ያስተማርከውን አጥብቆ የያዘ ማንም ቢሆን አይሞትም ብህ ትናገራለህ! 53አንተ ከአባታችን ከአብርሃም የምትበልጥ አይደለህም፡፡ እርሱ ሞተ እንዲሁም ሁሉም ነቢያት እርሱን ጨምሮ ሞቱ፡፡ ስለዚህ አንተ ማን ነኝ ብለህ ታስባለህ?” 54 55 56 ኢየሱስ እንዲህ ሲል ምላሽ ሰጠ፣ “እኔ ሰዎች እንዲያመሰግኑኝ ለማድረግ ብሞክር ያ ምንም ጥቅም የሌለው ይሆናል፡፡ የእኔ ባህርይና መልካምነት የሚያመሰግን አባቴ ነው፣ እንዲያም ሆኖ እርሱ እናንተ ‘የእኛ አምላክ’ የምትሉት ነው፡፡ 55ምንም እንኳን እርሱን ባታውቁትም፣ እኔ አውቀዋለሁ፡፡ እኔ አላውቀውም ብዬ ብናገር እንደ እናንተ ውሸተኛ እሆናለሁ፡፡ እኔ አውቀዋለሁ ሁልጊዜም እርሱ የሚለውን እታዘዛለሁ፡፡ 56አባታችሁ አብርሃም እንደ ነቢይነቱ አሻግሮ አይቶ እኔ ማድረግ የምችለውን ተመልክቶ ደስ ተሰኝቶ ነበር፡፡ 57 58 59 ከዚያ የአይሁድ መሪዎች እንዲህ አሉት፣ “ገና ሃምሳ አመት አልሞላህም! አንተ አብርሃምን አይተሃልን?” 58ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ “እኔ እውነቱን እየነገርኳችሁ ነው፤ ከአብርሃም በፊት እኔ ነበርኩ፡፡” 59ስለዚህ ሊወግሩትና ሊገድሉት ድንጋይ አነሱ፡፡ ሆኖም ኢየሱስ ራሱን ሸሸገ፣ ቤተመቅደሱን ትቶ ወጣ እናም ወደ ሌላ ስፍራ ሄደ፡፡

ምዕራፍ 9

1 2 ኢየሱስ ሲያልፍ፣ በህይወት ዘመኑ ሁሉ ከተወለደበት ጊዜ አንስቶ አይነ ስውር የነበረ አንድ ሰው አየ፡፡ 2ደቀመዛሙርቱ፣ “መምህር፣ ይህ ሰው ዐይነ ስውር ሆኖ እንዲወለድ ምክንያት የሆነው የማን ኃጢአት ነው? ይህ ሰው ራሱ ነበር ኃጢአት ያደረገው ወይንስ የእርሱ ወላጆች ነበሩ?” ብለው ጠየቁት፡፡ 3 4 5 ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰ፣ “እርሱ ወይም ደግሞ የእርሱ ወላጆች ኃጢአት ስለ ሰሩ አልነበረም፡፡ እውር ሆኖ የተወለደው ዛሬ ሰዎች እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የሚሠራውን ታላቅ ሥራ ማየት እንዲችሉ ነው፡፡ 4ገና ቀን እያለ የላከኝን ስራዎች እኛ መስራት አለብን፡፡ ምሽቱ እየደረሰ ነው ምሽቱ ሲመጣ ማንም መስራት አይችልም፡፡ 5በዓለም ላይ እስካለሁ ድረስ፣ እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ፡፡ 6 7 ይህን ተናግሮ፣ በምድር ላይ እንትፍ አለ፡፡ በምራቁ ጭቃ አበጀና በሰውዬው ዐይኖች ላይ እንደ መድሃኒት ቀባው፡፡ 7ከዚያም ኢየሱስ እንዲህ አለው፣ “ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ!” (የመጠመቂያው ስም ‘የተላከ’ ማለት ነው)፡፡ ስለዚህም ሰውዬው ሄዶ በመጠመቂያው ውስጥ ታጠበ፡፡ ሲመለስ ማየት ችሎ ነበር፡፡ 8 9 ሲለምን ያዩት የነበሩ የሰውየው ጎረቤቶቹና ሌሎች ሰዎች እንዲህ አሉ፣ “እዚህ ተቀምጦ ሲለምን የነበረው ሰው አይደለምን? 9አንዳንዶቹ፣ “እርሱ ነው” አሉ፡፡ ሌሎች፣ “አይደለም፣ ነገር ግን ያንን ሰው ይመስላል” አሉ፡፡ ሆኖም፣ ሰውየው ራሱ እንዲህ አለ፣ “አዎን፣ ያ ሰው እኔ ነኝ!”፡፡ 10 11 12 ስለዚህም እነርሱ እንዲህ አሉት፣ “አሁን ማየት የቻልከው እንዴት ነው?” 11እርሱም እንዲህ ሲል መለሰ፣ “ኢየሱስ የተባለው ሰው ጥቂት ጭቃ አበጀና እንደ መድሃኒት ተጠቅሞበት በዐይኖቼ ላይ አደረገው፡፡ ከዚያ ወደ ሰሊሆም መጠመቂያ ሄጄ እንድታጠብ ነገረኝ፡፡ ስለዚህም ወደዚያ ሄጄ ታጠብኩ፣ እና ከዚያ ለመጀመሪያ ጊዜ ማየት ቻልኩ፡፡” 12እነርሱ እንዲህ አሉት፣ “ያ ሰው የት አለ?” እርሱ “እኔ አላውቅም” አለ፡፡ 13 14 15 በዚያ የነበሩ አንዳንድ ሰዎች ሰውየውን ወደ ፈሪሳውያን ስብሰባ ወሰዱት፡፡ 14ኢየሱስ ይህን ተአምራት ያደረገው በሰንበት ቀን ነበር፡፡ 15ስለዚህ ፈሪሳዊያኑ ሰውየውን አሁን እንዴት ማየት እንደቻለ እንደገና ጠየቁት፡፡ እርሱ እንደዚህ አላቸው፣ “ሰውየው በአይኖቼ ላይ ጭቃ አደረገና እኔ ታጠብኩት፣ እና አሁን አያለሁ፡፡” 16 17 18 አንዳንዶቹ ፈሪሳውያን እንዲህ አሉ፣ “እኛ ይህ ኢየሱስ የሚባል ሰው ከእግዚአብሔር እንዳልሆነ እናውቃለን ምክንያቱም የሰንበትን ቀን አይጠብቅም፡፡” ከዚያ ቡድን ሌሎች እንዲህ ብለው ጠየቁ፣ “እርሱ ሀጢአተኛ ቢሆን ኖሮ፣ ሁሉም ሰው የሚያየው እንዲህ ያለ የሀይል ስራዎችን መስራት ይችላልን?” ስለዚህም በፈሪሳውያን መሀል የአስተያየት ልዩነት ነበር፡፡ 17ዐይነ ስውር የነበረውን ሰው ደግመው እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፣ “እርሱ እይታህን የመለሰልህ እስከሆነ ድረስ ስለ እርሱ ምን ትላለህ?” ሰውየው እንዲህ አለ፣ “እሱ ነቢይ ነው፡፡” 18ኢየሱስን የሚቃወሙት አይሁዶች ሰውየው እውር እንደነበረና ከዚያ ማየት እንደቻለ አላመኑም፡፡ ስለዚህ አንድ ሰው የሰውየውን ወላጆች እንዲያመጣ ላኩ ይህን ያደረጉት ወላጆቹም እንዲጠየቁ ነው፡፡ 19 20 21 ወላጆቹን እንዲህ ብለው ጠየቋቸው፣ “ይህ የእናንተ ልጅ ነው? ከተወለደበት ቀን አንስቶ አይነ ስውር ነበርን? ከሆነ እንዴት አሁን ማየት ቻለ?” 20ወላጆቹ፣ “እኛ ይህ የእኛ ልጅ መሆኑን እናውቃለን፡፡ ሲወለድ ዕውር እንደነበረም እናውቃለን፡፡ 21ሆኖም ግን አሁን እንዴት ማየት እንደቻለ እኛ አናውቅም፡፡ ማን ዐይኖቹን እንደፈወሰም እኛ አናውቅም፡፡ እርሱን ጠይቁት፣ እሱ ስለራሱ መናገር የሚችል ትልቅ ሰው ነው” በማለት ምላሽ ሰጡ፡፡ 22 23 ኢየሱስን ይቃወም የነበሩ አይሁዶች ቀደም ሲል ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ እንደሆነ የሚናገርን ሰው ከምኩራባቸው እንደሚያባርሩ ተስማምተው ነበር፡፡ 23ወላጆቹ፣ “እርሱን ጠይቀት፣ እርሱ ስለራሱ መናገር የሚችል ትልቅ ሰው ነው” ያሉት በዚህ ምክንያት ነበር፡፡ 24 25 ስለዚህም ዐይነ ስውር የነበረውን ሰው ጠርተው፣ ለሁለተኛ ጊዜ በፊታቸው እንዲቀርብ ጠየቁት፡፡ በዚያ ሲደርስ፣ እንዲህ ብለው ተናገሩት፣ “እውነቱን ብቻ እንደምትናገር ለእግዚአብሔር ማል! ይህ የፈወሰህ ሰው ኃጢአተኛ እንደሆነ እኛ እናውቃለን፤ ደግሞም ሙሴ ለእኛ የሰጠንን ህግ አይጠብቅም፡፡” 25 እንዲህ ሲል መለሰላቸው፣ “እርሱ ኃጢአተኛ ይሆን አይሁን፣ እኔ አላውቅም፡፡ እኔ የማውቀው አንድ ነገር ዕውር እንደነበርኩ፣ ነገር ግን አሁን እንደማይ ይህንን አውቃለሁ፡፡” 26 27 28 29 ስለዚህም እንደዚህ አሉት፣ “እርሱ ለአንተ ምን አደረገ አሁን ማየት እንድትችል እንዴት ፈወሰህ?” 27እንዲህ ሲል መለሰላቸው፣ “እኔ ያንን አስቀድሜ ነገርኳችሁ፣ ነገር ግን እኔን አላመናችሁም፡፡ ለምን እንደገና እንድነግራችሁ ፈለጋችሁ? እናንተም ደግሞ በእርግጥ የእርሱ ደቀመዛሙርት ለመሆን ፈለጋችሁን? 28ከዚያ በጣም ተቆጡና ሰደቡት፤ “አንተ የሰውየው ደቀመዝሙር ነህን? ነገር ግን እኛ የሙሴ ደቀመዛሙርት ነን! 29እኛ እግዚአብሔር ሙሴን እንደተናገረው እናውቃለን፣ ስለዚህ ሰው ግን፣ እርሱ ከየት እንደመጣ እንኳን አናውቅም፡፡” 28 29 ከዚያም ተቆጡና ሰደቡት፡ አንተ የሰው ደቀመዝሙር ነህ፤ እኛ ግን የሙሴ ደቀመዝሙር ነን! 29 እግዚአብሔር ሙሴን እንደተናገረው እናውቃለን፤ ነገር ግን ይህንን ሰው በተመለከተ ከዬት እንደመጣ እንካ አናውቅም 30 31 ሰውየው እንዲህ ሲል መለሰ፣ “ይህ በጣም አስደናቂ ነው! እናንተ እርሱ ከየት እንደመጣ አታውቁም፣ ነገር ግን ማየት እንድችል ዐይኖቼን የከፈተው እሱ ነው! 31እግዚአብሔር ህጉን ቸል የሚሉትን የኃጢአተኞችን ጸሎት እንደማይሰማ እኛ እናውቃለን፣ ነገር ግን እርሱ የሚሰማው የሚያመልኩትን እርሱ የሚፈልገውን የሚያደርጉትን ነው፡፡ 32 33 34 ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ አንስቶ በየትም ስፍራ አንድ ሰው ከተወለደበት ጊዜ አንስቶ አይነ ስውር የነበረን ሰው አይኖች መክፈት መቻሉ ተሰምቶ አያውቅም! 33ይህ ሰው ከእግዚአብሔር ባይመጣ ኖሮ፣ እንደዚያ ያለ ምንም ነገር መስራት አይችልም ነበር!” 34እነርሱ እንዲህ ሲል መለሱለት፣ “አንተ በኃጢአት ተወለድክ መላውን ህይወትህን በኃጢአት ውስጥ ኖርክ! እኛን ለማስተማር የምትበቃ እንደሆንክ ታስባለህ?” ከዚያ ከምኩራብ አገዱት፡፡ 35 36 37 38 ኢየሱስ ፈሪሳውያኑ እርሱ በፈወሰው ሰው ላይ ያደረጉትንና እንዴት ከምኩራብ እንዳስወጡት ሰማ፡፡ ስለዚህም ሄዶ ሰውየውን ፈለገው፡፡ ባገኘው ጊዜ፣ እንዲህ አለው “የሰው ልጅ በሆንኩት በእኔ ታምናለህን?” 36ሰውየው እንዲህ አለ፣ “ጌታዬ እርሱ ማን ነው? በእርሱ አምንበት ዘንድ፣ ንገረኝ፡፡” 37ኢየሱስ እንዲህ አለው፣ “አይተኸዋል፡፡ እርሱ አሁን ከአንተ ጋር በመነጋገር ላይ የሚገኘው ነው፡፡” 38ሰውዬው እንዲህ አለ፣ “ጌታ ሆይ፣ እኔ አምናለሁ፡፡” ከዚያ በጉልበቱ ተንበረከከና አመለከው፡፡ 39 40 41 ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ “የማያዩ እንዲያዩ እና የሚያዩ እንዲታወሩ በዓለም ለመፍረድ ስለዚህ ወደዚህ ዓም መጥቻሁ፡፡” 40ከእርሱ ጋር የነበሩ ይህንን ሲናገር የሰሙ አንዳንድ ፈሪሳዊያን ኢየሱስን እንዲህ ሲሉ ጠየቁት፣ “እኛም ደግሞ ዕውሮች ነን?” 41ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ “ዕውሮች ብትሆኑ ኖሮ፣ ኃጢአት አይኖባችሁም ነበር፡፡ ሆኖም፣ ‘እናያለን’ እያላችሁ ራሳችሁን ስለምትከላከሉ ኃጢአታችሁ ከእናንተ ጋር ይኖራል፡፡”

ምዕራፍ 10

1 2 “እኔ እውነቱን እየነገርኳችሁ ነው፤ ወደ በጎቹ ጉረኖ የሚገባ፣ በበሩ በኩል መግባት አለበት፡፡ በሌላ በማንኛውም መንገድ ቢንጠላጠል፣ እርሱ ስለ በጎቹ ግድ የሚለው አይደለም፣ ነገር ግን በጎቹን የሚሰርቅ ሌባና ወንጀለኛ ነው፡፡ 2በበሩ በኩል ወደ ጉረኖ የሚገባ ሰው ለበጎቹ ጥንቃቄ ስለሚያደርግ እሱ እውነተኛ እረኛ ነው፡፡ 3 4 እረኛው ሩቅ በሆነ ጊዜ በሮችን የሚጠብቀው ቅጥረኛ ሰው እረኛው በመጣ ጊዜ ለእርሱ በሩን ይከፍታል፡፡ ሆኖም በጎቹ የእረኛውን ድምጽ ብቻ ያውቃሉ፣ እናም በስም በጠራቸው ጊዜ ብቻ ለይተው እርሱን ያውቃሉ፡፡ ከዚያ ከጉረኖ ውጭ ሊመግባቸውና ውሃ ሊሰጣቸው ይመራቸዋል፡፡ 4የራሱን በጎች ሁሉ ካወጣ በኋላ ከፊታቸው ይሄዳል፡፡ በጎቹ እርሱን ለመከተል ይጓጓሉ ምክንያቱም የእርሱን ድምጽ ያውቃሉ፡፡ 5 6 እንግዳ የሆነውን የሚጠራቸውን ፈጽሞ አይከተሉትም፡፡ ከእርሱ ይሸሻሉ ምክንያቱም የእንግዳውን ድምጽ እውቅና አይሰጡትም፡፡” 6ኢየሱስ ከእረኞች ሥራ ይህን ማብራሪያ ተጠቀመ፡፡ ሆኖም ግን፣ ደቀመዛሙርቱ ምን እየነገራቸው እንደሆነ አልተረዱም፡፡ 7 8 ስለዚህ ኢየሱስ እንደገና ለእነርሱ ተናገረ፣ “እኔ እውነቱን እየነገርኳችሁ ነው፤ እኔ በጎቹ ወደ ጉረኖ ሁሉ የሚገቡበት በር ነኝ፡፡ 8ከእኔ በፊት የመጡ ሁሉ፣ በጎችን የሰረቁ ሌቦችና ወንጀለኞች ነበሩ፤ ነገር ግን በጎቹ እነርሱን አልሰሟቸውም እናም አይከተሏቸውም፡፡ 9 10 እኔ ራሴ እንደዚያ በር ነኝ፡፡ ማንም በበሩ ቢገባ በጎቹ ወደሌሉበት ወደ ጉረኖው ቢሄድ የተጠበቀ ይሆናል፣ ደግሞም ወደ ውጪ ይሄድና መልካም መሰማሪያ ያገኛ፡፡ እኔ ወደዚያ ወደ ለመለመ መሰማርያ እመራዋለሁ፡፡ 10ሌባው ሊሰርቅ፣ ሊገድል፣ ሊያጠፋ ብቻ ይመጣል፣ እኔ ሕይወት እንዲኖራቸውና አንዳች ነገር ያልጎደለው ህይወት እንዲኖራቸው ስለዚህ መጥቻለሁ፡፡ 11 12 13 እኔ እንደ መልካም እረኛ ነኝ፡፡ መልካም እረኛ በጎቹን ለመጠበቅና ለማዳን ሕይወቱን ይሰጣል፣ 12አንድ ሰው ለተቀጣሪ ሰው በጎቹን እንዲመለከት ገንዘብ ይከፍላል፡፡ ያ ሰው በጎቹ የእርሱ እንደሆኑ አድርጎ አይንከባከባቸውም፤ እርሱ ልክ አንድን ስራ እንደሚሰራ ተቀጣሪ ነው፡፡ ስለዚህ አንድ ተኩላ በጎቹን ለመግደል መምጣቱን ሲመከት፣ ሕይወቱን ለአደጋ አያጋልጥም፡፡ በጎቹን ትቶ ይሸሻል፡፡ በመሆኑም ተኩላው በበጎቹ ላይ አደጋ መጣል፣ አንዳንዶቹን መያዝና ሌሎቹን መበተን ይችላል፡፡ 13ቅጥረኛው ሰራተኛ ይሸሻል ምክንያቱም እሱ የሚሰራው ገንዘብ ለማግኘት ሲል ብቻ ነው፡፡ በበጎቹ ላይ ስለሚደርሰው ነገር ግድ የለውም፡፡ 14 15 16 እኔ ራሴ መልካሙ እረኛ ነኝ፡፡ 15ልክ እኔ አባቴን እንደማውቀው፣ እና አባቴ እኔን እንደሚያውቀኝ እኔ የራሴን በጎች አውቃለሁ፣ የራሴ በጎችም እኔን ያውቁኛል፡፡ በዚህም ምክንያት እኔ ለበጎቼ ለመሞት ፈቃደኛ ነኝ፡፡ 16እናንተ ከምትገኙበት ከዚሁ ቡድን ውስጥ ያልሆኑ ሌሎች በጎች አሉኝ፡፡ እነርሱም እኔን እንዲሰሙኝ አደርጋለሁ፡፡ እነርሱ ብቸኛውን እረኛ ይሰሙኛል፣ ስለዚህም በመጨረሻ በእኔ ስር አንድ የበጎች መንጋ ብቻ ይኖራል፡፡ 17 18 አባቴ እኔን የሚወድበት ምክንያት ህይወቴን መስዋዕት አድርጌ ስለምሰጥ ነው፡፡ እኔ ሕይወቴን እሰጣለሁ፣ እናም መልሼ ወደ ሕይወት አመጣታለሁ፡፡ 18ማንም ሕይወቴን እንድጥል ሊያደርገኝ አይችልም፡፡ እኔ ሕይወቴን መስዋዕት ለማድረግ መርጫለሁ፡፡ ሕይወቴን አሳልፌ ለመስጠት ስልጣን አለኝ እናም መልሼ ልወስዳትና ዳግም ለመኖር ስልጣን አለኝ፡፡ ይህ ሥራ ከአባቴ ነው፣ ይህን እንድሰራ እርሱ አዞኛል፡፡” 19 20 21 ኢየሱስ የተናገራቸውን እነዚህን ቃላት ከሰሙ በኋላ፣ አይሁዳዊያኑ ስለ እርሱ ባላቸው አስተያየት ተከፋፈሉ፡፡ 20ከእነርሱ ብዙዎቹ እንዲህ አሉ፣ “ሰይጣን እየተቆጣጠረው ነው እናም እያሳበደው ነው፡፡ እርሱን በመስማት ጊዜ አታባክኑ!”፡፡ 21ሌሎች ደግሞ፣ “የሚናገረው በሰይጣን ተፅዕኖ ስር ያለ ሰው መቼም ቢሆን ሊናገረው የሚችለው አይደለም፡፡ የቱም ሰይጣን የአንድን ዐይነ ስውር አይኖች ሊከፍት አይችልም!” አሉ፡፡ 22 23 24 የአይሁድ ህዝቦች አባቶቻቸው በኢየሩሳሌም ያለውን ቤተመቅደስ አንጽተው ዳግም ለእግዚአብሔር ያደረጉበት የቤተ መቅደስ መታደስ በዓል የተባለው ጊዜ ደረሰ፡፡ ጊዜውም ክረምት ነበር፡፡ 23ኢየሱስ በቤተ መቅደስ ቅጽር ግቢ የሰለሞን ሰገነት በተባለው ስፍራ ያልፍ ነበር፡፡ 24የኢየሱስ ተቃዋሚ የሆኑት አይሁዶች በዙሪያው ከበዉት እንዲህ አሉ፣ “እስከ መቼ ማን እንደሆንክ እያስደነቅከን ትቆያህ አንተ ክርስቶስ ከሆንክ እናውቅ ዘንድ በግልጽ ንገረን፡፡” 25 26 ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፣ “ነገርኳችሁ፣ ነገር ግን እናንተ አታምኑኝም፡፡ በአባቴ ስምና በእርሱ ስልጣን በሰራኋቸው ተአምራቶችና ሌሎች ነገሮች ምክንያት እኔ ማን እንደሆንኩ ታውቃላችሁ፡፡ እነዚያ ነገሮች ስለ እኔ ማወቅ የሚያስፈልጋችሁን ሁሉ ይነግሯችኋል፡፡ 26እናንተ በእኔ አታምኑም ምክንያቱም የእኔ አይደላችሁም፡፡ እናንተ የሌላው እረኛ በጎች ናችሁ፡፡ 27 28 የእኔ በጎች ድምጼን ይሰማሉ፡፡ እያንዳንዳቸውን በስማቸው አውቃቸዋለሁ፤ እነርሱ ይከተሉኛል ይታዘዙኝማል፡፡ 28እኔ ዘለዓለማዊ ሕይወት እሰጣቸዋለሁ፡፡ ማንም መቼም ሊያጠፋቸው አይችልም፣ ደግሞም ማንም መቼም ከእኔ ሰርቆ ሊወስዳቸው አይችልም፡፡ 29 30 31 እነርሱን ለእኔ የሰጠኝ አባቴ ነው፤ እርሱ ከማንም ይበልጣል፣ ስለዚህ ማንም ከእርሱ ሰርቆ ሊወስዳቸው አይችልም፡፡ 30እኔና አብ አንድ ነን፡፡” 31የኢየሱስ ጠላቶች እንደገና ሊወግሩትና ሊገድሉት ድንጋይ አነሱ፡፡ 32 33 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ “አባቴ እንድሰራቸው የነገረኝን፣ ብዙ መልካም ስራዎችን ስሰራ አይታችሁኛል፡፡ ከእነዚህ ስለ የትኛዎቹ ትወግረኛላችሁ?” 33ተቃዋሚዎቹ አይሁዶች እንዲህ ሲሉ መለሱ፣ “እኛ ሕይወትህን ልንወስድ የምንፈልገው ማንኛውንም መልካም ስራ ስለሰራህ ሳይሆን፣ ነገር ግን አንተ አንድ ሰው ብቻ ሆነህ ሳለ ራስህን አምላክ እያደረግህ! እግዚአብሔርን ትሳደባለህ፡፡” 34 35 36 ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፣ “በመጽሐፍ እርሱ ስለ ሾማቸቸው መሪዎች እግዚአብሔር የተናገረው እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፤ ‘እኔ እናንተ እንደ አማልክት ናችሁ ብዬ ተናግሬአለሁ (በታላቅ ክብርና በብዙዎች ላይ በሀይል)፡፡’ 35እግዚአብሔር በሾማቸው ጊዜ ለነዚያ መሪዎች ይህን ተናግሯል፡፡ ማንም ይህን አይቃወምም፣ በመጽሐፍ ውስጥ ከሚገኘው ውስጥ ምንም ነገር ሀሰት ተብሎ ሊታይ አይቸልም፡፡ 36አባቴ የለየኝና የራሱ ያደረገኝ እኔ ነኝ፡፡ ወደዚህ ዓለም የላከኝ እርሱ ነው፡፡ ስለዚህ ‘እኔ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ’ ብዬ ስናገር ከእግዚአብሔር ጋር እኩል መሆኔን በመናገሬ ለምን በእኔ ላይ ትቆጣላችሁ? 37 38 39 አባቴ እንድሰራው የነገረኝን ሥራ ሳልሰራ ቀርቼ ቢሆን ኖሮ፣ በእኔ እንድታምኑ አልጠበቅባችሁም ነበር፡፡ 38ሆኖም ግን፣ እኔ እነዚህን ስራዎች እየሰራሁ በመሆኑ፣ የተናገርኩትን ባታምኑ እንኳን እነዚህ ሥራዎች ስለ እኔ በሚነግሯችሁ እምነት ይኑራችሁ፡፡ ያንን ብታደርጉ፣ ከዚያ አባቴ በእኔ ውስጥ እንዳለ እኔ በአባቴ እንዳሁ ታውቃላችሁ ትረዱማላችሁ፡፡” 39ያንን ከሰሙ በኋላ፣ እንደገና ኢየሱስን ሊይዙት ሞከሩ፣ ነገር ግን እንደገና ከእነርሱ አመለጠ፡፡ 40 41 42 ከዚያ ኢየሱስ ወደ ዮርዳኖስ ወንዝ ምስራቅ ተመልሶ ሄደ፡፡ አጥማቂው ዮሐንስ በአገልግሎቱ መጀመሪያ ብዙ ሰዎችን ወዳጠመቀበት ስፍራ ሄደ፡፡ ኢየሱስ በዚያ ለብዙ ቀናት ቆየ፡፡ 41ብዙ ሰዎች ወደ እርሱ መጡ፡፡ እነርሱም እንዲህ ይሉ ነበር፡፡ “አጥማቂው ዮሐንስ አንድም ተአምር አላደረገም ነገር ግን ይህ ሰው ብዙ ተአምራቶችን አድርጓል! ዮሐንስ ስለዚህ ሰው የተናገረው ሁሉ እውት ነው!” 42ብዙ ሰዎች እየመጡ በእርሱ አመኑ፤ እርሱ ማን እንደሆነና ለእነርሱ ባደረገው አመኑ፡፡

ምዕራፍ 11

1 2 አንድ አልዓዛር የሚባል ሰው በጣም ታመመ፡፡ እርሱ ማርያምና ማርታ በሚኖሩበት በቢታኒያ መንደር ይኖር ነበር፡፡ 2ይህች ማርያም ለጌታ ያላትን ፍቅሯንና ለእርሱ ያላትን ክብር በላዩ ላይ ሽቶ በማፍሰስና እግሮቹን በፀጉሯ በማበስ የገለጸችው ናት፡፡ የታመመው ወንድሟ አልዓዛር ነበር፡፡ 3 4 ስለዚህ ሁለቱ እህትማማቾች ስለ አልዓዛር እንዲነግሩት ወደ ኢየሱስ “ጌታ ሆይ የምትወደው ታሟል” ብለው ሰው ላኩበት፡፤ 4ኢየሱስ የአልዓዛርን መታመም በሰማ ጊዜ እንዲህ አለ፣ “ይህ ህመም በአልዓዛር መሞት አይጠናቀቅም፡፡ የዚህ ህመም ዓላማ ሰዎች እግዚአብሔር አስደናቂ ነገሮችን ሲያደርግ እንዲያዩና እንዴት ታላቅ እንደሆነ እንዲያውቁ ደግሞም እኔ፣ የሰው ልጅ የእርሱን ታላቅ ሀይል እንድንገልጽ ነው፡፡” 5 6 7 ኢየሱስ ማርያምን፣ እህቷን ማርታንና አልዓዛርን ይወዳቸው ነበር፡፡ 6የሆነ ሆኖ፣ ኢየሱስ የአልዓዛርን መታመም በሰማ ጊዜ፣ እርሱን ለማየት ከመሄድ ዘገየ፡፡ በነበረበት ስፍራ ለሁለት ተጨማሪ ቀናት ቆየ፡፡ 7ከዚያ ለደቀመዛሙርቱ እንዲህ አለ፣ “ወደ ይሁዳ ተመልሰን እንሂድ፡፡” 8 9 ደቀመዛሙርቱ እንዲህ አሉ፣ “መምህር፣ ከጥቂት ጊዜ በፊት የሚቃወሙህ አይሁዶች በድንጋይ ወግረው ሊገድሉህ ይፈልጉ ነበር፣ አሁን ወደዚያ ተመልሰህ መሄድ ትፈልጋለህ!” 9ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላቸው፣ “በአንድ ቀን ውስጥ አስራ ሁለት ብርሃን የሚሆንባቸው ሰዓቶች አሉ፣ ይህ እውነት አይደለምን? በቀን የሚራመድ በሰላም ይራመዳል ምክንያቱም በመንገድ ላይ ያለውን ማየት ይችላል፡፡ 10 11 ሆኖም ግን፣ አንድ ሰው በምሽት ሲራመድ በቀላሉ ይደነቃቀፋል ምክንያቱም ማየት አይችልም፡፡ 11እነዚህን ነገሮች ከተናገረ በኋላ፣ ለእነርሱ እንዲህ አላቸው፣ “ወዳጃችን አልዓዛር ተኝቷል፣ እኔ ግን ከተኛበት ልቀሰቅሰው ወደዚያ እሄዳለሁ፡፡” 12 13 14 ደቀመዛሙርቱ እንዲህ አሉት፣ “ጌታ ሆይ፣ እንቅልፍ ተኝቶ ከሆነ በደህና ይነሳል፡፡” 13ኢየሱስ ግን በእርግጥ ስለ አልዓዛር ሞት እየተናገረ ነበር፣ ደቀመዛሙርቱ እረፍት ለማግኘት ስለሆነው መኝታ የሚናገር መስሏቸው ነበር፡፡ 14ከዚያ በግልጽ ነገራቸው፣ “አልዓዛር ሞቷል፤ 15 16 ነገር ግን ስለ እናንተ፣ እርሱ ሲሞት በዚያ ባለመሆኔ ደስ ይለኛል፤ ስለዚህም እናንተ በእኔ ለምን ማመን እንዳለባችሁ ታውቃላችሁ፡፡ አሁን ሰዓቱ ደርሷል፣ ወደ እርሱ እንሂድ፡፡” 16ከዚያ ‘መንትያው’ ተብሎ የሚጠራው ቶማስ፣ ለተቀሩት ሐዋርያት እንዲህ አላቸው፣ “ከእርሱ ጋር እንሞት ዘንድ እኛም ደግሞ ከኢየሱስ ጋር እንሂድ፡፡” 17 18 19 20 ኢየሱስ ቢታኒያ ሲደርስስ አልዓዛር ሞቶና ለአራት ቀናት በመቃብር ውስጥ ቆይቶ ደረሰ፡፡ 18ኢየሩሳሌም ከቢታኒያ ሶስት ኪሎሜትሮች ያህል ብቻ ትርቅ ነበር፡፡ 19ብዙ አይሁዶች አልዓዛርንና ቤተሰቡን ያውቁ ስለነበር ማርታንና ማርያምን የወንድማቸውን ሞት ሊያጽናኑ ከኢየሩሳሌም መጡ፡፡ 20ማርታ አንድ ሰው ኢየሱስ በቅርበት እንደሚገኝ ሲናገር ስትሰማ እርሱን ለማግኘት ወደ መንገድ ወጣች፡፡ ማርያም ግን አልተነሳችም ነገር ግን በቤት ውስጥ ቆየች፡፡ 21 22 23 ማርታ ኢየሱስን ስታይ እንዲሀ አለች፣ “ጌታ ሆይ፣ አንተ በዚህ ብትኖር ኖሮ፣ ወንድሜ አይሞትም ነበር፡፡ 22ሆኖም፣ አሁንም ቢሆን እግዚአብሔር አንተ የጠየቅከውን ሁሉ እንደሚሰጥህ አውቃለሁ፡፡” 23ኢየሱስ እንዲህ አላት፣ “ወንድምሽ እንደገና ይነሳል፡፡” 24 25 26 24ማርታ እንዲሀ አለችው፣ “እግዚአብሔር በመጨረሻው ቀን ሙታንን ሁሉ ሲያስነሳ በዚያን ቀን እንደገና ህያው እንደሚሆን አውቃለሁ፡፡” 25ኢየሱስ እንዲህ አላት፣ “ሰዎችን ከሞት የማስነሳ እኔ ነኝ፤ ለእነርሱ ህይወት የምሰጠው እኔ ነኝ፡፡ ማንም በእኔ የሚያምን፣ ቢሞትም እንኳን፣ እንደገና በህይወት ይኖራል፡፡ 26ህይወት የተቀበሉ ሁሉ ከእኔ ጋር ይሆናሉ ደግሞም በእኔ የሚያምኑ በፍጹም አይሞቱም፡፡ እኔን ታምኛለሽ?” 27 28 29 እንዲህ አለችው፣ “አዎን፣ ጌታ ሆይ! አንተ የተናገርከውን አምናለሁ፣ ደግሞም አንተ ማን እንደሆንክ፣ አንተ ክርስቶስ የእግዚአብሔር ልጅ፣ እግዚአብሔር ወደዚህ ዓም ይመጣል ብሎ ቃል የገባው እንደሆንክ አምናለሁ፡፡ 28ይህን ከተናገረች በኋላ ወደ ቤት ተመልሳ እህቷን ማርያምን ለብቻዋ ወደ ጎን ወስዳ እንዲህ አለቻት፣ “መምህሩ በዚህ አለ፣ እርሱ እየጠራሽ ነው፡፡” 29ማርያም ይህንን ስትሰማ፣ በፍጥነት ተነስታ ወደ ውጭ ወደ እርሱ ሄደች፡፡ 30 31 32 በዚህ ጊዜ ኢየሱስ ገና ወደ መንደር አልመጣም ነበር፤ እስከዚያ ጊዜ ድረስ ማርታ እርሱን ባገኘችው ስፍራ ላይ ነበር፡፡ 31እህትማማቾቹን ለማጽናናት ወደ ቤታቸው የመጡ ሰዎች ማርያም በፍጥነት ተነስታ ወደ ውጭ ስትወጣ አዩ፡፡ ስለዚህም አልዓዛር ወደ ተቀበረበት ወደ መቃብሩ ስፍራ ሄዳ ለወንድሟ ልታለቅስ መስሏቸው ተከተሏት፡፡ 32ማርያም ኢየሱስ ወደነበረበት ስፍራ መጣች፤ ስታየው፣ በእግሮቹ ስር ወድቃ ተንበረከከችና እንዲህ አለች፣ “ጌታ ሆይ፣ አንተ በዚህ ኖረህ ቢሆን ወንድሜ አይሞትም ነበር፡፡” 33 34 35 ኢየሱስ ስታዝንና ስታለቅስ ሲመለከታት እንዲሁም ከእርሷ ጋር የመጡ ሀዘንተኞች ጭምር ሲያለቅሱ፣ እርሱ በመንፈሱ ታውኮ አለቀሰ በጣም ተጨንቆ ነበር፡፡ 34እንዲህ አለ፣ “አስከሬኑን የት አሳረፋችሁት?” እነርሱም፣ “ጌታ ሆይ፣ መጥተህ እይ” አሉት፡፡ 35ኢየሱስ አለቀሰ፡፡ 36 37 ስለዚህ አይሁዶቹ እንዲህ አሉ፣ “እዩ አልዓዛርን እንዴት ይወደው እንደነበር!” 37ሆኖም፣ ሌሎቹ ደግሞ እንዲህ አሉ፣ “የዐይነ ስውሩን ዐይኖች የከፈተ ይህን ሰው ደግሞ ከመሞት ለማዳን ስለምን አይቻለውም ነበር?” 38 39 40 ኢየሱስ ወደ መቃብሩ ሲደርስ አካሉ ይርገፈፍና ስሜቱ ይታወክ ነበር፡፡ መቃብሩ ዋሻ ነበር፣ መግቢያው በትልቅ ድንጋይ ተዘግቶ ነበር፡፡ 39ኢየሱስ በዚያ ቆመው ለነበሩ እንዲህ ሲል ትዕዛዝ ሰጠ፣ “ድንጋዩን አንሱ፡፡” ሆኖም ማርታ፣ “ጌታ ሆይ፣ በዚህ ጊዜ መጥፎ ሽታ ይኖራል፣ ከሞተ አራት ቀን ሆኖታል” ስትል ተቃወመች፡፡ 40ኢየሱስ እንዲህ አላት፣ “እኔን ብታምኚኝ እግዚአብሔር ማን እንደሆነ ታያለሽ፣ ደግሞም እግዚአብሔር ምን ማድረግ እንደሚችል ታውቂያለሽ ብዬ በነገርኩሽ ጊዜ እውቱን አልነገርኩሽምን?” 41 42 ስለዚህ ድንጋዩን ከስፍራው አነሱ፡፡ ኢየሱስ ወደ ሰማይ ቀና ብሎ ተመልክቶ እንዲህ አለ፣ “አባት ሆይ፣ ስለሰማኸኝ አመሰግንሀላለሁ፡፡ 42ሁልጊዜም እንደምትሰማኝ አውቃለሁ፡፡ ይህንን በዚህ የቆሙ ሰዎች በአንተ ላይ እምነታቸውን ያደርጉ ዘንድና አንተ እኔን እንደላከኝ እርግጠኝት ይኖራቸው ዘንድ እናገራለሁ፡፡” 43 44 ይህን ከተናገረ በኋላ፣ ከፍ ባለ ድምጽ እንዲህ ብሎ ጮኸ፣ “አልዓዛርር ና ውጣ!” 44የሞተው ሰው ወጥቶ መጣ! እጆቹ እንደተጠቀሰለሉ ነበር፤ እግሮቹም በላይነን ቁርጥራጭ ጨርቆች ታስረው ነበር፤ እንደዚሁም ፊቱ በጨርቅ ተሸፍኖ ነበር፡፡ ኢየሱስ እዲህ አላቸው፣ “የታሰረበትን ቁርጥራጭ ጨርቆቹ አንሱለትና ፍቱት፡ ነጻ ሆኖ ይሂድ፡፡” 45 46 በውጤቱም፣ ማርያምን ለማየት የመጡና ኢየሱስ ሲያደርግ የተመለከቱ ብዙ አይሁዶቹ በእርሱ አመኑ፡፡ 46ሆኖም ሌሎች ጥቂቶች ደግሞ ወደ ፈሪሳውያን ሄደው ኢየሱስ ያደረገውን ነገሯቸው፡፡ 47 48 ስለዚህም ሊቀ ካህናቱና ፈሪሳውያኑ የአይሁድ መማክርት አባላትን በሙሉ ሰበሰቡ፡፡ እርስ በእርቸው እንዲህ ይባባሉ ነበር “ምን ማድረግ እንችላለን? ይህ ሰው ብዙ ተአምራቶችን እያደረገ ነው፡፡ 48እነዚህን ማድረጉን እንዲቀጥል ከፈቀድን፣ ሁሉም በእርሱ ያምናል ደግሞም በሮም አገዛዝ ላይ ያምጻሉ፡፡ ከዚያ የሮም ሰራዊት መጥቶ ቤተ መቅደሳችንን አገራችንን ያጠፋል!” 49 50 ከምክር ቤቱ አባላት አንዱ ቀያፋ ነበር፣ እርሱም በዚያ አመት ሊቀ ካህን ነበር፡፡ እንደዚህም አላቸው፣ “እናንተ ሁላችሁም ምንም አታውቁም! 50መላው አገር ከሚጠፋ አንድ ሰው ቢሞት እንደሚሻል ይህን አታስውሉም፡፡” 51 52 53 ይህን የተናገረው፣ ከራሱ አስቦት አልነበረም፡፡ ይልቁንም፣ በዚያ አመት ሊቀ ካህን ስለነበር ኢየሱሰ ለአይሁድ ህዝብ እንደሚሞት ትንቢት እየተናገረ ነበር፡፡ 52ኢየሱስ የሚሞተው ለአይሁድ ህዝብ ብቻ እንዳልሆነ ጨምሮ ትንቢት እየተናገረ ነበር፤ እርሱ በሌላ ምድር በየስፍራው የሚኖሩትን የእግዚአብሔር ልጆች ወደ አንድ አገር እንደሚሰበስብም ትንቢት እየተናገረ ነበር፡፡ 53ስለዚህ ከዚያን ቀን ወዲህ፣ መማክርቱ ኢየሱስን ለመያዝና ለመግደል መንገድ መፈለግ ጀመረ፡፡ 54 55 በዚህም ምክንያት ኢየሱስ በተቃዋዎቹ አይሁዶች መሀል በግልጽ ህዝብ ባለበት አልተንቀሳቀሰም፡፡ በምትኩ፣ ኢየሩሳሌምን ትቶ፣ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ሰው በማይኖርበትና በበረሃ አካባቢ ወደሚገኘው ኤፍሬም ወደሚባል አንድ ከተማ ሄደ፡፡ በዚያ ለአጭር ጊዜ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ቆየ፡፡ 55ጊዜው የአይሁድ የፋሲካ በዓል የደረሰበት ወቅት ነበር፣ ብዙ አምልኮ የሚፈጽሙ ሰዎች ከገጠሮችና ከመንደሮች ወደ ኢየሩሳሌም ሄዱ፡፡ እንደ አይዶች ህግ በመታጠብ ራሳቸውን ያነፁና ያፋሲካውን በዓል ለማክበር የተዘጋጁ ይሆኑ ነበር፡፡ 56 57 ለፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ለአምልኮ የመጡ ሰዎች ኢየሱስን ይፈልጉት ነበር፡፡ መጥተው በመቅደስ ሲቆሙ፣ እርስ በእርሳቸው እንዲህ ይባባሉ ነበር፣ “ምን ታስባላችሁ ወደ ፋሲካ በዓሉ አይመጣም፣ ይመጣ ይሆን?” 57የአይሁድ ሊቀ ካህናትና ፈሪሳውያኑ ማንም ኢየሱስ የት እንደሆነ ካወቀ ማሰር ይችሉ ዘንድ ለእነርሱ መናገር እንዳለበት ትዕዛዝ አውጥተው ነበር፡፡

ምዕራፍ 12

1 2 3 ኢየሱስ የፋሲካ በአል ከመጀመሩ ስድስ ቀናት አስቀድሞ ቢታኒያ ደረሰ፡፡ ቢታኒያ፣ ኢየሱስ ዳግም ወደ ህይወት የመለሰው ሰው አልዓዛር ይኖርበት የነበረው መንደር ነው፡፡ 2በቢታኒያ፣ ኢየሱስን ለማክበር እራት አዘጋጁለት ማርታ የእራት ዝግጅት አደረገች፣ አልዓዛር በዚያ በአንድነት ተቀምጠው ከሚመገቡት መሃል ነበር፡፡ 3ከዚያ ማርያም ውድ የሆነ የሽቶ ጠርሙስ ወሰደችና (ናርዶስ የተባለ ሽቱ) ኢየሱስን ለማክበር እግሩ ላይ አፈሰሰችው፡፡ ከዚያ እግሮቹን በፀጉሯ ጠረገች፡፡ የሽቱው መዓዛ መላ ክፍሉን ሞላው፡፡ 4 5 6 ሆኖም ከደቀመዛሙቱ አንዱ የአስቆሮቱ ይሁዳ፣ (እርሱ ኢየሱስ በእርሱ ላይ የነበረውን እምነት ያፈረሰና በቶሎም ኢየሱስን ለጠላቶቹ አሳልፎ የሚሰጠው ነበር) ተቃውሞ እንዲህ አለ፣ 5“ይህንን ሽቶ ለሶስት መቶ ቀናት የጉልበት ክፍያ በሚሆን ዋጋ ልንሸጠውና ገንዘቡን ለድሆች ልንሰጥ ይገባ፡፡” 6እርሱ ይህን የተናገረው፤ ለድሃ ሰዎች ግድ ስለሚለው አልነበረም፣ ነገር ግን ሌባ ስለነበረ ነው፡፡ የገንዘብ ቦርሳቸውን ለመያዝ ሀላፊነቱን የወሰደው እርሱ ነበር፣ ነገር ግን በፈለገ ጊዜ ሁሉ ለራሱ ጥቅም ገንዘብ ይወስድ ነበር፡፡ 7 8 ከዚያ ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ “ተዋት አታስቸግሯት! ይህን ሽቱ ለምሞትበት ቀን አምጥታዋለች እነርሱ እኔን ይቀብሩኛል፡፡ 8እናንተ ሁልጊዜም ድሆችን ታገኛላችሁ፣ እኔን ግን ሁልጊዜ አታገኙኝም፡፡ 9 10 11 በኢየሩሳሌም ያሉ ብዙ አይሁዶች ኢየሱስ ቢታያ ውስጥ መሆኑን ሰሙ፣ ስለዚህም ወደዚያ ሄዱ፡፡ የመጡት ኢየሱስ በዚያ ስለነበረ ብቻ አልነበረም፣ ነገር ግን ኢየሱስ ከሞት ያስነሳውን አልዓዛርን ለማየት ጭምር ነበር፡፡10ከዚያ ሊቀ ካህናቱ አልዓዛርን ጭምር መግደል አስፈላጊ እንደሆነ ወሰኑ፣ 11ለዚህም ምክንቱ ብዙዎቹ አይሁዶች ሊካህናቱ የሚያስተምሩትን ማመን እየተዉ በምትኩ እየሱስን ማመን የጀመሩት በእርሱ ምክንያት ስነበረ ነው፡፡ 12 13 በማግስቱ ለፋሲካ በአል የመጡ ብዙ ሰዎች ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም እየመጣ እንደሆነ ሰሙ፡፡ 13ስለዚህ ከዘንባባ ዛፍ ቅርንጫፎችን እየቆረጡ ይዘው በመውጣት እርሱ ወደ ከተማ ሲገባ አቀባበል አደረጉለት፡፡ ሰዎች እንዲህ እያሉ ይጮሁ ነበር፣ “ሆሳዕና! እግዚአብሔር ይመስገን! በጌታ ስም የሚመጣውን እግዚአብሔር ይባርከዋል! የእስራኤል ንጉስ፣ እንኳን ደህና መጣህ!” 14 15 ኢየሱስ ወደ ኢየሩሳሌም ሲቃረብ፣ አንድ አህያ ውርንጭላ አገኘና ተቀመጠበት፣ እየጋለበበት ወደ ከተማ ገባ፡፡ ይህን በማድረግ፣ በመጽሐፍ እንዲህ ተብሎ የተጻፈውን አሟላ 15 “እናንተ በኢየሩሳሌም የምትኖሩ፣ አትፍሩ፡፡ተመልከቱ! ንጉሳችሁ በአህያ ውርንጭላ ላይ ተቀምጦ እየመጣ ነው! 16 ይህ ሲሆን፣ ደቀመዛሙርቱ የትንቢት ፍጻሜ መሆኑን አልተረዱም፡፡ ሆኖም ግን፣ ኢየሱስ ሥራውን ከጨረሰ በኋላና እንደ እግዚአብሔር እንደገና ሙሉ ሀይሉን ሲቀበል ነቢያት ስለ እርሱ የጻፉትንና ሰዎች በእርሱ ላይ ያደረጉትን ዘወር ብለው አይተው አስታወሱ፡፡ 17 18 19 ኢየሱስን ይከተሉ የነበሩ ብዙ ሰዎች ያዩትን ለሌሎች መናገራቸውን ቀጠሉ፤ ይኸውም ኢየሱስ አልዓዛርን ከመቃብር ጠርቶ ማስነሳቱንና ለእርሱ ዳግም ሕይወት መስጠቱን ይናገሩ ነበር፡፡ 18ኢየሱስን ለማግኘት ከከተማው ውጭ የሄደው ሌላው የህዝብ ክምችት ይህን ያደረገው፣ የእርሱን ሀይል ለማሳየት ታላላቅ ነገሮችን እንደሰራ ስለሰሙ ነበር፡፡19ስለዚህም ፈሪሳውያኑ እርስ በርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፣ “እዩ! በዚህ ምንም ጥቅም አላገኘንም፡፡ ተመልከቱ! መላው ዓለም እርሱን እየተከተለው ነው!” 20 21 22 በፋሲካ በዓል ወደ ኢየሩሳሌም ከሄዱት መካከል ግሪኮች ይገኙበታል፡፡ 21በገሊላ አውራጃ ውስጥ በምትገኘው ከቤተሳይዳ ወደ ሆነው ሰው ወደ ፊልጶስ መጡ፡፡ እርሱን የሚጠይቁት ነገር ነበራቸው፤ እንዲህ አሉት፣ “ከኢየሱስ ጋር ልታስተዋውቀን ትችላለህ?” 22ስለዚህም ፊሊጶስ ይህንን ለእንድርያስ ነገረው፣ እናም ሁለቱም ወደ ኢየሱስ ሄደው ነገሩት፡፡ 23 24 ኢየሱስ ለፊልጶስና እንድርያስ እንዲህ ሲል መለሰ፣ “አሁን ጊዜው እግዚአብሔር እኔ፣ የሰው ልጅ ለሰዎች ያደረኩትንና የተናገርኩትን ነገር ሁሉ የሚያሳይበት ነው፡፡ 24እኔ እውነቱን እየነገርኳችሁ ነው፤ የስንዴ ቅንጣት በመሬት ውስጥ እስካልተዘራችና እስካልሞተች ድረስ፣ ዘር ብቻ ሆና ትቀራለች፤ ነገር ግን በመሬት ውስጥ ከሞተች በኋላ፣ ከዚያ ታድግና ብዙ ፍሬዎችን ታፈራለች፡፡ 25 26 ራሱን ደስ ለማሰኘት ለመኖር የሚሞክር ሁሉ ሕይወትን ያጣል፣ ነገር ግን ራሱን ለማስደሰት የማይኖር ሕይወቱን ለዘለዓለም ይጠብቃል፡፡ 26ማንም እኔን ለማገልገል ቢፈልግ፣ እኔን መከተልም ይኖርበታል ምክንያቱም የእኔ አገልጋይ እኔ ባለሁበት መገኘት አለበት፡፡ አብ እኔን የሚያገለግሉትን ሁሉ ያከብራል፡፡ 27 28 29 አሁን ነብሴ እጅግ ተጨንቃለች፡፡ “አባት ሆይ ከምጨነቅበትና ከምሞትበት ከዚህ ጊዜ አድነኝ!” ማለት ይኖርብኛል? አይ አይኖርብኝም፣ ወደዚህ ዓም የመጣሁበት ዋነኛው ምክንያት ይህ ነው፡፡ 28አባቴ፣ በተናገርው ሁሉ፣ ባደረከው ሁሉና በማንንት ሁሉ እንዴት ሀያል እንደሆንክ አሳይ!” ከዚያ እግዚአብሔር ከሰማይ እንዲህ ብሎ ተናገረ፣ “እኔ ባህርዬን ቃላቶቼንና ስራዎቼን ቀድሜ ገልጫለሁ፤ ደግሞም እንደገና ይህን አደርጋሁ!” 29በዚያ የነበሩ ሰዎች የእግዚአብሔርን ድምጽ ሰሙ፡፡ ነገር ግን አንዳንዶቹ ይህ መብረቅ ነው አሉ፡፡ ሌሎች መልአክ ከኢየሱስ ጋር ተናገረ አሉ፡፡ 30 31 ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፣ “ሲናገር የሰማችሁት ድምጽ የእግዚአብሔር ድምጽ ነበር ሆኖም ግን፣ እርሱ የተናገረው ለእኔ ጥቅም አይደለም፣ ነገር ግን ለእናንተ እንጂ! 31አሁን እግዚአብሔር በዓለም ላይ የሚፈርድበት ጊዜ ነው፡፡ አሁን እርሱ ይህን ዓለም የሚገዛውን ሰይጣንን የሚያባርርበት ጊዜ ነው፡፡ 32 33 እኔን በሚመለከት፣ ሰዎች እኔን በመስቀል ላይ ከፍ በሚያደርጉበት ጊዜ፣ እያንዳንዱን ወደ ራሴ እስባለሁ፡፡” 33ይህን የተናገረው እንዴት እንደሚሞት ሰዎች እንዲያውቁ ነው፡፡ 34 35 36 ከህዝቡ መሃል አንድ ሰው እንዲህ ሲል ተናገረ፣ “ከመጽሐፍት ይህን ተረድተናል መሲሁ ለዘለዓለም ይኖራል፡፡ ታዲያ አንተ ለምን የሰው ልጅ ይሞታል ትላለህ? ይህ ‘የሰው ልጅ’ ማን ነው?” 35ኢየሱስ እንደህ ብሎ መለሰ፣ “የእኔ ብርሃን ለጥቂት ጊዜ በእናተ ላይ ያበራል፡፡ የእኔ ብርሃን ሳለላችሁ በብርሃን ተመላለሱ፣ አለበለዚያ ጨለማው ይወርሳችኋል፡፡ በጨለማ የሚመላለሱ ወዴት እንደሚሄዱ ማየት አይችሉም! 36ብርሃኑ ሳላችሁ በዚያ ብርሃን እመኑ፤ እንዲህ ከሆነ የዚያ ብርሃን ትሆናላችሁ፡፡” እነዚያን ነገሮች ከተናገረ በኋላ ኢየሱስ ትቷቸው ሄደና ከእነርሱ ተሰወረ፡፡ 37 38 ኢየሱስ ብዙ ተአምራቶችን ቢሰራም እንኳን፣ ብዙዎቹ ሰዎች እርሱ የነገራቸውን አላመኑም፡፡ 38ይህ የሆነው ነቢዩ ኢሳይያስ ከረጅም ጊዜ አስቀድሞ የፃፈው እንዲፈጸም ነበር፤ “ጌታ ሆይ፣ ከእኛ የሰሙትን የትኛውንም ነገር ማን አመነ ጌታ እንዴት በሀይል እንደሚያድነን አሳይቶናል! 39 40 ሆኖም፣ ኢሳይያስ እንደፃፈው በእርሱ ሊያምኑ አልቻሉም፡፡ 40“ጌታ ማየት እንዳይችሉ አድርጓል፣ እናም ደንዳና አድርጓቸዋል፤ እነርሱ በዐይኖቸው ማየት እንኳን አይችሉም፣ ቢችሉ ኖሮ፣ ይረዱ ነበር፤ ይቅር እንድለቸው ንስሃ ይገቡና ወደ እኔ ይጸልዩ ነበር፡፡ በዚህ ምክንያት ልፈውሳቸው አልቻልኩም! 41 42 43 ኢሳይያስ እነዚያን ቃላት ከረጅም ጊዜ አስቀድሞ የጻፈበት ምክንያት ክርስቶስ እግዚአብሔርን በሀይል እንደሚያገለግል ስለተረዳ ነበር፡፡ 42ይህ እውነት ቢሆንም እንኳን ብዙዎቹ የአይሁድ ህዝብ መሪዎች በኢየሱስ አምነዋል፡፡ የሆነ ሆኖ፣ ፈሪሳውያን ከምኩራባቸው ስለሚያግዷቸው በጣም ፈርተው ነበር፤ ስለዚህም በኢየሱስ ስለማመናቸው በግልጽ አልተናገሩም፡፡ 43ከእግዚአብሔር ምስጋና ከማግኘት ሌሎች ሰዎች የሚሰጧቸውን ምስጋናና ክብር መርጠዋል፡፡ 44 45 ኢየሱስ ለተሰበሰበው ህዝብ ጮክ ብሎ ተናገረ፣ “በእኔ የሚያም በእኔ ማመናቸው ብቻ አይደለም ነገር ግን በላከኝ በአብ ማመናቸውም ነው፡፡ 45እኔን በምታዩበት ጊዜ፣ የላከኝንም ታያላችሁ፡፡ 46 47 ወደ ዓለም የዓለም ብርሃን ሆኜ መጥቻለሁ፤ ማንም በእኔ የሚያምን በጨለማ ውስጥ አይቀርም፡፡ 47እኔ ቃሌን በሚሰሙት ላይ አልፈርድም፡፡ ነገር ግን ሰምተው በማይታዘዙት ላይ እፈርዳለሁ፡፡ ዓለምን ለመኮንን ወደ ዓለም አልመጣሁም፡፡ 48 49 50 ሆኖም፣ እኔን በማይቀበሉና መልዕክቴን የማይከተሉትን የሚኮንን ነገር አለ፡፡ ለእነርሱ በተናገርኩት መልዕክት ይኮነናሉ፡፡ 49እኔ ስለ እግዚአብሔር ሳስተምር የማስተምረውን እየተናገርኩ ብቻ አይደለም፡፡ የላከኝ አብ ምን ማለት እንዳለብኝና እንዴትስ ያንን ማለት እንዳለብኝ ግልጽ መመሪያ ሰጥቶኛል፡፡ 50የአብ በጣም አስፈላጊዎቹ መመሪያዎች ሰዎች እንዴት ለዘለዓለም እንደሚኖሩ የሚያስተምሩት ናቸው፣ እኔም አባቴ የነገረኝን በትክክል ተናግሬያለሁ፡፡”

ምዕራፍ 13

1 2 የፋሲካ በዓል ከመጀመሩ አስቀድሞ የነበረ ቀን ነበር፡፡ ኢየሱስ ይህን ዓለም ትቶ ወደ አባቱ የሚመለስበት ወቅት እንደሆነ አውቋል፡፡ እዚህ በዘህ ዓለም ከእርሱ ጋር ያሉትን ምን ያህል እንደ ወደዳቸው አሳይቷቸው፣ እስከ ህይወቱ መጨረሻ ድረስ ወደዳቸው፡፡ 2ኢየሱስና ደቀ መዛሙርቱ እራት ከመብላታቸው አስቀድሞ ሰይጣን ኢየሱስን አሳልፎ ለጠላቶቹ በሚሰጠው በስምዖን ልጅ በአስቆሮቱ ይሁዳ አይምሮ አሳብ አስገብቶ ነበር፡፡ 3 4 5 ሆኖም ኢየሱስ አባቱ በሁሉም ነገር ላይ ሙሉ ሀይልና ስልጣን እንደሰጠው ያውቃል፡፡ እሱ ራሱ ከእግዚአብሔር እንደመጣና ወደ እግዚአብሔር በቶሎ እንደሚመለስ ጭምር ያውቃል፡፡ 4ኢየሱስ ከእራት ላይ ተነሳ፣ የደረበውን ልብስ አወለቀና በወገቡ ዙሪያ ፎጣ አደረገ፡፡ 5በማስታጠቢያ ሰሃኑ ውስጥ ውሃ ጨምሮ የደቀመዛሙርቱን እግር ማጠብና በፎጣ ማድረቅ ጀመረ፡፡ 6 7 8 9 እንዲህ ብሎ ወደተናገረው ስምዖን ጴጥሮስ መጣ፣ “ጌታሆይ፣ አንተ የእኔን እግር ልታጥብ ነውን?” 7ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰለት፣ “እኔ አሁን ለአንተ የማደርገውን አትረዳም ነገር ግነ በኋላ ትረዳዋለህ፡፡” 8ጴጥሮስ እንዲህ አለ፣ “አንተ ፈጽሞ የእኔን እግር አታጥብም!” ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰለት፣ “እኔ ካላጠብኩህ፣ ከእ ጋር አንዳች የምታደርገው የለህም፡፡” 9ስለዚህም ስምኦን ጴጥሮስ እንዲህ አለው፣ “ጌታ ሆይ፣ እግሬን ብቻ አትጠብ! እጆቼንና ራሴን ጭምር እጠብ!” 10 11 ኢየሱስ እንዲህ አለው፣ “ገላውን የታጠበ ሰው እግሮቹን ብቻ መታጠብ ያስፈልገዋል፡፡ ሌላው የሰውነቱ ክፍል አስቀድሞ ንጹህ ነው፡፡ እናንተ ንጹህ ናችሁ ነገር ግን ሁላችም አይደላችሁም፡፡” 11አሳልፎ የሚሰጠው ማን እንደሆነ ያውቃል፡፡ “ሁላችሁም ንጹህ አይደላችሁም” ያለበት ምክንያት ይህ ነው፡፡ 12 13 14 15 እግራቸውን አጥቦ ከጨረሰ በኋላ ያወለቀውን መደረቢየ መልሶ አደረገ፡፡ ከዚያ ወደ ቦታው ተመልሶ ተቀመጠና እንዲህ አለ፣ “ለእናንተ ያደረግኩት ምን እንደሆነ ትረዳላችሁ? 13‘መምህር’ እና ‘ጌታ’ ብላችሁ ትጠሩኛላችሁ፡፡ እኔ እንደዚያው ስለሆንኩ ይህን ማለታችሁ ትክክል ነው፡፡ 14እኔ መምህራችሁና ጌታችሁ የሆንኩት እግራችሁን ካጠብኩ፣ እናንተም ደግሞ አንዳችሁ የሌላችሁን እግር ማጠብ ይኖርባችኋል፡፡ 15እኔ ለእናንተ እንዳደረኩት እናንተም ማድረግ ስለሚኖርባች የምትተሉትን ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁ፡፡ 16 17 18 እውነቱን እየነገርኳችሁ ነው፤ አንድ አገልጋይ ከጌታው እንደማይበልጥ፣ የተላከም ከላከው አይበልጥም፡፡ 17እነዚህን ነገሮች ብታውቁና ብታደርጓቸው እንዴት መልካም በሆነላችሁ፡፡ 18ይህን ስለሁላችሁም እየተናገርኩ አይደለም፡፡ እኔ የመረጥኳቸውን አውቃለሁ፡፡ ሆኖም፣ በመጽሐፍ እንዲህ ተብሎ የተፃፈው መፈጸም አለበት፤ ‘እንደ አንድ ጓደኛ ከገበታዬ የበላ፣ በእኔ ላይ ተነሳብኝ ደግሞም እንደ ጠላት ሆነብኝ፡፡’ 19 20 እርሱ አሳልፎ ሳይሰጠኝ በፊት አሁን ይህን እነግራችኋለሁ ስለዚህም ነገሩ በሆነ ጊዜ እኔ መሆኔን እግዚአብሔር መሆኔን ልታምኑ ትችላላች፡፡ 20እኔ እውነቱን እየነገርኳችሁ ነው፤ እኔ ለእናንተ የላኩትን ብትቀበሉ፣ እኔንም መቀበላችሁ ነው፤ እኔን የተቀበለ ደግሞ የላከኝን አባቴንም እየተቀበለ ነው፡፡ 21 22 ኢየሱስ ይህን ከተናገረ በኋላ፣ በውስጡ ታወከ፡፡ ዝግ ብሎ እንዲህ ተናገረ፣ “እውነቱን እየነገርኳችሁ ነው፤ ከእናንተ አንዱ ለጠላቶቼ አሳልፎ ይሰጠኛል፡፡” 22ደቀመዛሙርቱ እርስ በእርሳቸው ተያዩ፡፡ ስለማንኛቸው እንደሚናገር ግራ ተጋብተው ነበር፡፡ 23 24 25 ኢየሱስ በልዩ ሁኔታ የሚወደው ከደቀመዛሙርቱ መሃል አንዱ የሆነው ዮሐንስ በገበታ ከኢየሱስ አጠገብ ተቀምጦ ነበር፡፡ 24ኢየሱስ ስለ የትኛው ደቀመዝሙር እየተናገረ እንደሆነ እንዲጠይቀው ስምዖን ጴጥሮስ ለዮሐንስ አሳብ አቀረበለት፡፤ 25ስለዚህ ዮሐንስ ወደ ኢየሱስ ዘንበል ብሎ በፀጥታ፣ “ጌታ ሆይ፣ እሱ ማን ነው?” ብሎ ጠየቀው፡፡ 26 27 ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰ፣ “ይህን ቁራሽ እንጀራ አጥቅሼ የምሰጠው እርሱ ነው፡፡” ከዚያ እንጀራውን አጥቅሶ ለስምዖን አስቆሮቱ ልጅ ለይሁዳ ሰጠው፡፡ 27ይሁዳ ቁራሹን እንጀራ እንደተቀበለ ወዲያውኑ፣ ሰይጣን ገባበትና ተቆጣጠረው፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አለው ማድረግ የምትፈልገውን በቶሎ አድርግ፡፡” 28 29 30 በማዕድ ከተቀመጡት ኢየሱስ ለምን እንዲህ እንዳለው ያወቀ ሌላ ማንም አልነበረም፡፡ 29አንዳንዶቹ ይሁዳ የገንዘብ ቦርሳ ይይዝ ስነበር ኢየሱስ ለፋሲካ በአል አንዳች ነገር እዲገዛ እየነገረው መስሏቸው ነበር፡፡ ሌሎች ኢየሱስ ለድሆች አንዳች ነገር እንዲሰጥ ለይሁዳ እየነገረው መሰሏቸው ነበር፡፡ 30ይሁዳ እንጀራውን ከተቀበለ በኋላ ወዲያውኑ ወጥቶ ሄደ፡፡ ጊዜውም ምሽት ነበር፡፡ 31 32 33 ይሁዳ ከሄደ በኋላ ኢየሱስ እንዲህ አለ፣ “አሁን እግዚአብሔር፣ እኔ የሰው ልጅ፣ ምን እንደማደርግ ሰዎች እንዲያውቁ ያደርጋል፡፡ እኔ፣ የሰው ልጅ፣ እግዚአብሔርም ምን እንደሚያደርግ ሰዎች እንዲያውቁ አደርጋለሁ፣ እናም ሰዎች ስለዚያ እርሱን ያመሰግናሉ፡፡ 32እኔ የሰው ልጅ፣ ሰዎች እግዚአብሔርን እንዲያውቁ እስካደረግኩና እኔ እርሱን እስካከበርኩ ድረስ፣ እግዚአብሔርም እኔን ያከብረኛል፡፡ እግዚአብሔር ይህን ወዲያውኑ ያደርገዋል፡፡ 33ልጆቼ ሆይ ለጥቂት ጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ፡፡ እናንተ ትፈልጉኛላችሁ፤ ነገር ግን፣ ለአይሁዶች እንደነገርኳቸው አሁን ለእናንተ እንዲህ እላችኋለሁ፡፡ እኔ ወደምሄድበት፣ እናንተ ልትመጡ አትችሉም፡፡ 34 35 ይህን አዲስ ትዕዛዝ እሰጣችኋለሁ፤ ልክ እኔ እንደወደድኳችሁ እርስ በርሳችሁ መዋደድ አለባችሁ፡፡ 35እርስ በእርሳችሁ ብትዋደዱ፣ ሁሉም ሰዎች እናንተ የእኔ ደቀመዛሙርት እንደሆናች ያውቃሉ፡፡” 36 37 38 ስምዖን ጴጥሮስ እንዲህ አለው፣ “ጌታ ሆይ፣ ወዴት ልትሄድ ነው?” ኢየሱስ መለሰ፣ “እኔ ወደምሄድበት፣ አሁን ከእኔ ጋር መምጣት አትችልም፤ ነገር ግን በኋላ ትመጣለህ፡፡” 37ጴጥሮስ እንዲህ አለ፣ “ጌታ ሆይ፣ አሁን ከአንተ ጋር መምጣት የማልችለው ለምንድን ነው? ለአንተ ሕይወቴን አሳልፌ እሰጣለሁ!” 38ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰ፣ “ጴጥሮስ፣ በእርግጥ ሕይወትህን ለእኔ አሳልፈህ ትሰጣለህ? እኔ እውነቱን እየነገርኩህ ነው፤ አንተ እኔን ሶስት ጊዜ አላውቀውም እስከምትል ድረስ አውራ ዶሮ በማለዳ አይጮህም!”

ምዕራፍ 14

1 2 3 “አትታወኩ ወይም አትጨነቁ፡፡ እናንተ በእግዚአብር ታምናላችሁ፤ በእኔመ ደግሞ እመኑ፡፡ 2አባቴ በሚኖርበት ብዙ የመኖሪያ ቦታዎች አሉ፡፡ ይህ እውነት ባይሆን ኖሮ፣ እኔ እነግራችሁ ነበር፡፡ ለእናን ቦታ ለመዘጋጀት ወደዚያ እሄዳለሁ፡፡ 3ለእናንተ ቦታ ለማዘጋጀት ወደዚያ የምሄድ ከሆነ ተመልሼ እመጣና ከእኔ ጋር እንድትሆን እወስዳችኋለሁ፣ ስለዚህም እኔ በምሆንበት፣ እናንተም ከእኔ ጋር በዚያ ትሆናላችሁ፡፡ 4 5 6 7 ወዴት እንደምሄድ እናንተ ታውቃላችሁ፣ ደግሞም መንገዱን ታውቃላችሁ፡፡ 5ቶማስእንዲህ አለው፣ “ጌታ ሆይ፣ አንተ ወዴት እንደምትሄድ እኛ አናውቅም፡፡ መንገዱን እንዴት ልናውቅ እንችላለን?” 6ኢየሱስ እንዲህ አለው፣ “መንገዱ እኔ ነኝ፣ ዕውነቱ እኔ ነኝ፣ እኔ ህይወት ነኝ፡፡ በእኔ በኩል ካልመጣ በስተቀር ማንም ወደ አብ ሊመጣና ከእርሱ ጋር ሊኖር አይችልም፡፡ 7እኔን ብታውቁኝ አባቴንም ደግሞ ታውቁታላችሁ፡፡ ከአሁን በኋላ እሱን ታውቁታላችሁ ደግሞም አይታችሁታል፡፡ 8 9 ፊሊጶስ ኢየሱስን እንዲህ አለው፣ “ጌታ ሆይ፣ አብን አሳየን፣ የምንፈልገው ይህንን ብቻ ነው!” 9ኢየሱስ እንዲህ አለው፣ “ፊሊጶስ፣ ለረጅም ጊዜ ከአንተ ጋር ነበርኩ እና እስከ አሁን እኔን አታውቀኝም፡፡ እኔን ያዩ፣ አባቴን አይተዋል፡፡ ስለዚህ ለምን ‘አብን አሳየን’ ትላለህ? 10 11 እኔ ከአባቴ ጋር መሆኔን አታምንም? ደግሞስ አባቴ ከእኔ ጋር አንድ መሆኑን አታምንም? እኔ የነገርኩህን እነዚህን ነገሮች ከራሴ አልተናገርኳቸውም፤ ይልቁንም እነዚህን ነገሮች ሁሉ እንድነግራችሁ የላከኝ አባቴ ነው፤ አባቴ ከእኔ ጋር አንድ ነው እናም በእኔ በኩል ይሰራል፡፡ 11በእኔ እመኑ ምክንያቱም እኔ ከአባቴ ጋር አንድ መሆኔን ነግሬያችኋለሁ እንዲሁም አብ ከእኔ ጋር አንድ ነው፣ ይህ ካልሆነም ስሰራቸው ስላያችኋቸው ምልክቶችና ታላላቅ ድርጊቶች በእኔ እመኑ፡፡ 12 13 14 እኔ እውነቱን እየነገርኳችሁ ነው፣ ማንም በእኔ የሚያምን እኔ ያደረኳቸውን ነገሮች ያደርጋል፡፡ የበለጠ ስራዎችንም እንኳን ማድረግ ይችላል፣ ምክንያቱም እኔ ከአብ ጋር ለመሆን እሄዳለሁ፡፡ 13በስሜ የጠየቃችሁትን ሁሉ፣ ያንን እኔ አደርገዋለሁ እኔ፣ የእርሱ ልጅ፣ ባደረግኳቸው ነገሮች ምክንያት እያንዳንዱ አብን ያከብር ዘንድ እና አብን ያውቁ ዘንድ ይህን አደርጋለሁ፡፡ 14የእኔ በመሆናች ምክንያት አብን ማናቸውንም ነገር ብትጠይቁ እኔ አደርገዋለሁ፡፡ 15 16 17 እኔን የምትወዱኝ ከሆነ፣ ባስተማርኳችሁ መሰረት ትኖራላችሁ፡፡ 16ከዚያ እኔ አብን ሌላ ስጦታ እንዲሰጣችሁ እጠይቃሁ፣ እርሱም ወደ እናንተ መጥቶ ከእናንተ ጋር ለዘለዓለም የሚኖር ሌላ ረዳት ይልክላችኋል፡፡ 17እርሱ ስለ እግዚአብሔር እውነተኛ የሆነውን የሚናገር መንፈስ ነው፡፡ በዚህ ዓለም የሚኖሩ የማያምኑ ሰዎች እርሱን በፍጹም በእሽታ አይቀበሉትም፡፡ ዓለም እርሱን ሊያየው ወይም ሊያውቀው አይችልም፡፡ እናንተ እርሱን ታውቁታላችሁ ምክንያቱም በእናንተ ውስጥ ይኖራል፣ ከእናንተ ጋር አንድ ይሆናል፡፡ 18 19 20 ስለ እናንተ ግድ የሚለው ማንም ሳይኖር እኔ አልተዋችሁም፤ እኔ ወደ እናንተ እመጣለሁ፡፡ 19ከቅርብ ጊዜ በኋላ ዓለም አያየኝም፣ ነገር ግን እናንተ ታዩኛላችሁ፡፡ ከእኔ የተነሣ እናንተ ህያዋን ናችሁ፡፡ 20ዳግም ስታዩኝ፣ እኔ ከአብ ጋር አንድ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ ደግሞም እናንተ ከእኔ ጋር አንድ እንደሆናችሁ እኔም ከእናንተ ጋር አንድ እንደሆንኩ ታውቃላችሁ፡፡ 21 22 ትዕዛዞቼን የሚሰሙና የሚያደርጉ፣ እነርሱ የሚወዱኝ ናቸው፡፡ እኔን የሚወዱኝን፣ አባቴም ይወዳቸዋል፤ እኔም እወዳቸዋለሁ፣ ለእነርሱ ራሴን እገልጻለሁ፡፡› 22ከዚያ ይሁዳ (የአስቆሮቱ ይሁዳ ሳይሆን፣ ተመሳሳይ ስም ያለው ሌላኛው ደቀመዝሙር) ኢየሱስን እንዲህ አለው፣ “ጌታ ሆይ፣ ለዓለም ሁሉ ሳይሆን ለእኛ ራስህን የምትገልጸው እንዴት ነው?” 23 24 ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰለት፣ “ሰዎች እኔን መውደዳቸውን ማወቅ የምትችለው በዚህ ነው፤ እኔ እንድታደርጉ የነገርኳችሁን በማድረግ ነው፡፡ እንደነዚህ ያሉትን አባቴ ይወዳቸዋል፡፡ እኔና እርሱ ወደ እነርሱ መጥተን ከእነርሱ ጋር እንኖራለን፡፡ 24እኔን የማይወዱኝ ግን፣ እንዲያደርጉ የነገርኳቸውን አያደርጉም፡፡ የነገርኳችሁ ነገሮች እኔ ከራሴ ልናገርኳቸው የወሰንኳቸው ነገሮች አይደሉም፤ ይልቁንም አባቴ እንድነግራችሁ የነገረኝ ነገሮች ናቸው፡፡ 25 26 27 እኔ ገና እዚህ ከእናንተ ጋር እያለሁ እነዚህን ነገሮች ለእናንተ ተናግሬያለሁ፡፡ 26ከእናንተ ጋር አብሯችሁ ለመሆን የሚመጣውን ረዳት አባቴ በስሜ ይልከዋል፡፡ ማወቅ የሚያስፈልጋችሁን ነገር ሁሉ እርሱ ያስተምራችኋል፡፡ እንደዚሁም እኔ የነገርኳችሁን ነገሮች ሁሉ እንድታስታውሱ ምክንያት ይሆናችኋል፡፡ 27የእኔን ሰላም እንደተውኩላችሁ፣ የምሰጣችሁ የእኔ ሰላም ነው፡፡ እኔ የምሰጣችሁ ሰላም ማንም እና የትኛውም የዚህ ዓለም ነገር ሊሰጣችሁ የማይችለው ዐይነት ሰላም ነው፡፡ ስለዚህ አትታወኩ ወይም አትጨነቁ፤ አትፍሩም፡፡ 28 29 30 31 እኔ መሄዴ ነው በኋላ ወደ እናንተ ተመልሼ እመጣለሁ ብዬ ለእናንተ ስናገር ሰምታችኋል፡፡ የምትወዱኝ ከሆነ፣ ወደ አብ ተመልሼ በመሄዴ ደስ ሊላችሁ ይገባል ምክንያቱም አብ ከእኔ ይበልጣል፡፡ 29እኔ እነዚህን ነገሮች ከመሆነቸው አስቀድሞ ነገርኳችሁ ስለሆነም በሚሆኑበት ጊዜ በእኔ ማመናችሁን ትቀጥላላችሁ፡፡ 30ከእናንተ ጋር ከዚህ በላይ ብዙ መነጋገር አልችልም ምክንያቱም የዚህ ዓለም ገዢ እየመጣ ነው፡፡ ሆኖም፣ እሱ በእኔ ላይ ምንም ሀይል የለውም፣ 31እኔ አባቴ እንዳደርግ ያዘዘኝን አደርጋለሁ፡፡ ይህም ማለት ዓለም እኔ አብን እንደምወድ ለዘለዓም እንዲያውቅ ነው፡፡ ኑ፣ ከዚህ እንሂድ፡፡”

ምዕራፍ 15

1 2 እኔ እውነተኛ ወይን ነኝ፣ አትክልተኛው አባቴ ነው፡፡ 2በእኔ ያለውን እያንዳንዱን ፍሬ የማያፈራውን ቅርንጫፍ አባቴ ይቆርጠዋል ያስወግደውማል፡፡ መልካም ፍሬ የሚሰጠውን እያንዳንዱን ቅርንጫፍ፣ የበለጠ ፍሬ እንዲያፈራ በመግረዝ ንጹህ ያደርገዋል፡፡ 3 4 ከነገርኳችሁ መልዕክት የተነሳ አሁንም እንኳን እናንተ ንጹህ ናችሁ፡፡ 4ከእኔ ጋር አንድ ሆናች ብትቀሩ እኔም ከእናንተ ጋር አንድ ሆኜ እቀራለሁ፤ ቅርንጫፍ በራሱ ፍሬ መስጠት እንደማይችል፣ ከእኔ ጋር እንድ ሆናችሁ ካልኖራችሁና ለሁሉም ነገር በእኔ ላይ ጥገኛ ካልሆናችሁ እናንተም ፍሬ ማፍራት አትችሉም፡፡ 5 6 7 እኔ ወይኑ ነኝ፤ እናንተ ቅርንጫፎቹ ናችሁ፡፡ በእኔ ላይ ተጋጥማችሁ ብትኖሩና እኔ ከአባቴ ጋር ተጣብቄ ብኖር እናንተ ብዙ ፍሬ ታፈራላችሁ፣ ከእኔ ተለይታችሁ ምንም ማድረግ አትችሉም፡፡ 6ከእኔ ጋር አንድ ሆኖ የማይኖርና ከእኔ ሕይወቱን የማያገኝ ሁሉ እንደ ደረቀ ቅርንጫፍ ወደ ውጭ ይጣላል፡፡ እነዚያ ቅርንጫፎች በአንድነት ይሰበሰቡና ወደ እሳት ተጥለው ይቃጠላሉ፡፡ 7ከእኔ ጋር አንድ ሆናች ብትቆዩና በመልዕክቶቼ ብትኖሩ፣ ማንኛውንም ነገር እግዚአብሔርን መጠየቅ ትችላላችሁ፣ እርሱም ያደርገዋል፡፡ 8 9 እናንተ ብዙ ፍሬ ስታፈሩ ይህ ሰዎች አብን እንዲያከብሩ ምክንያት ይሆናል፡፡ ከዚያ እናንተ የእኔ ደቀመዛሙርት ትባላላችሁ፡፡ 9አባቴ እኔን እንደወደደኝ፣ እኔም እናንተን ወደድኳችሁ እናንተን መውደዴ እንዲቀጥል አድርጉ፡፡ 10 11 እንድታደርጉ የነርኳችሁን ብትታዘዙ፣ እኔ እናንተን መውደዴ እንዲቀጥል ታደርጋላችሁ፡፡ በዚህ መንገድ እንደ እኔ ትመስላላችሁ፡ እኔ አባቴ እንዳደርገው የሚጠይቀውን አድረጌያለሁ፣ ከመታዘዜም የተነሳ፣ በፍቅሩ ኖሬያለሁ፡፡ ይህ ስለ እናንተም እውነት ይሆናል፡፡ 11የእኔ ደስታ በእናንተ ውስጥ እንዲሆን እነዚህን ነገሮች ነግሬያችኋለሁ፣ ስለዚህም ሙሉ ደስታ ይሆናለችኋል፡፡ 12 13 እንድታደርጉት የምሰጣችሁ ትዕዛዝ ይህ ነው፡ እኔ በወደድኳችሁ መንገድ እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ፡፡ 13ለወዳጆቻችሁ ህይወታችሁን ከመስጠት የሚበልጥ ፍቅር ሊኖራችሁ አይችልም፡፡ 14 15 ወዳጆቼ የምትሆኑት ትዕዛዛቶቼና በመስማት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን በእነርሱ በመኖር ጭምር ነው፡፡ 15ከዚህ በኋላ አገልጋዮቼ ብዬ አልጠራችሁም፣ አገልጋይ ጌታቸው የሚያደርገውን አይረዳምና፡፡ እኔ አሁን ወዳጆቼ ብዬ እጠራችኋለሁ፣ ከአባቴ የሰማሁትን ነገር ሁሉ እናንተ እንድታውቁ አድርጌያለሁ፡፡ ስለዚህም እናንተም ይህን መረዳት ትችላላችሁ፡፡ 16 17 እናንተ እኔን አልመረጣችሁኝም፣ ነገር ግን እኔ በምክንያት መረጥኳችሁ ይህም ምክንያት ሄዳችሁ ብዙ ፍሬ እንድታፈሩና ፍሬያችሁ እንዲኖር ነው፡፡ በውጤቱ፣ በስሜ አብ የምትጠይቁትን ነገር ሁሉ ያደርግላችኋል፡፡ 17እንድታደርጉት የምሰጣችሁ ትእዛዝይህ ነው፤ እርስ በእርሳችሁ ተዋደዱ፡፡ 18 19 ዓለም ቢንቃችሁ፣ በመጀመሪያና እኔን እንደጠላኝ ማወቅ አለባችሁ፡፡ 19በዚህ ዓለም ከሚያምኑ ሰዎች ብትሆኑ፣ ዓለም ይወዳችሁ ነበር፣ እናንተም እነርሱ የሚወዱትን ትወዱና የሚያደርጉትን ታደርጉ ነበር፡፡ ነገር ግን የእነርሱ አይደላችሁም፤ ይልቁንም፣ ከመሀላቸው እንድትወጡ እኔ መረጥኳች፡፡ የማያምኑ ሰዎች በዚህ ዓለም የሚንቋችሁ ከዚህ የተነሳ ነው፡፡ 20 21 22 እንዲህ ብዬ ያስተማርኳችሁን አስታውሱ፤ ‘አገልጋይ ከጌታው አይበልጥም፡፡’ እነርሱ እኔን እስካሰቃዩኝ ድረስ፣ እናንተም ደግሞ እንደሚያሰቃይዋችሁ እርግጠኛ መሆን ትችላላች፡፡ ከእነርሱ ማናቸውም የእኔን ትምህርቶች ተቀብለው ተከትለዋቸው ከሆነ፣ እናንተ የምታስተምሯቸውንም ይከተላሉ፡፡ 21በዚህ ዓለም የማያምኑ በእናንተ ላይ አስከፊ ነገሮችን ያደርጋሉ ምክንያቱም እናንተ እኔን ትወክላላችሁ ደግሞም እነሱ የላከኝን አባቴን አያውቁም፡፡ 22መጥቼ የእግዚአብሔርን መልዕክት ባልነግራቸው ኖሮ፣ እኔንና መልዕክቴን ባለመቀበላቸው ጥፋተኛ አይሆኑም ነበር፡፡ ሆኖም፣ አሁን እኔ መጥቼ የእግዚአብሔርን መልዕክት ነግሬያቸዋለሁ እናም ለኃጢአታቸው ምክንያት የላቸውም፡፡ 23 24 25 እኔን የሚጠላ ሁሉ አባቴን ይጠላል፡፡ 24በመሀላቸው እነዚያን ነገሮች ባላደርግ ፣ እነዚያን ሀይሌን ያሳየሁባቸው ነገሮች ባላደርግ፣ ሌላ ማንም አድርጓቸው የማያውቁ ነገሮችን ባላደርግ፣ በኃጢአት ጥፋተኛ ባልሆኑ ነበር፡፡ አሁን ግን እነርሱ እኔን አይተዋል፣ እኔን ጠልተዋ አባቴንም ደግሞ ጠልተዋል፡፡ 25በህጋቸው ውስጥ “ያለ ምክንያት ጠሉኝ” ተብሎ የተፃፉት እነዚህ ቃላት አሁን ተፈጽመዋል፡፡ 26 27 ረዳት የሆነው ሲመጣ፣ እርሱ ከአብ የሚመጣና እናንተን የሚያጽና ነው፡፡ ስለ እግዚአብሔርና ስለ እኔ እውነቱን የሚናገር መንፈስ ነው፡፡ እኔ ማን እንደሆንኩ ለእያንዳንዱ ይናገራል፣ ደግሞም እኔ ያደረኩት ሁሉ ለእያንዳዱ ያሳያል፡፡ 27እናንተም ደግሞ ስለ እኔ የምታውቁትን ለሁሉም መናገር አለባችሁ ምክንያቱም ሰዎችን ማስተማርና ተአምራቶችን ማድረግ ከጀመርኩበት ከመጀመሪያው ቀን አንስቶ ሁልገዜም ከእኔ ጋር ነበራችሁ፡፡”

ምዕራፍ 16

1 2 እነዚህን ነገሮች የነገርኳችሁ በሚያጋጥማችሁ ችግሮች እንዳትናወጡ ወይም በእኔ ማመናችሁን እንዳትተዉ ነው፡፡ 2ከፊት አስቸጋሪ ቀኖች አሉ፡፡ ጠላቶቻችሁ በምኩራብ እንዳታመልኩ ይከለክሏችኋል፡፡ ሆኖም፣ ከዚህ የባሰ ነገርም ይሆናል፡፡ ሰዎች እናንተን ገድለው እግዚአብሔርን ደስ እንዳሰኙ የሚያስቡበት ቀናት እየመጡ ነው፡፡ 3 4 ይህን የሚያደርጉት አብን ወይም እኔን ስላላወቁ ነው፡፡ 4እነዚህን ነገሮች የነገኳችሁ እነዚህ መከራዎች በመጡ ጊዜ እንዳስጠናቀቅኳችሁ ታስታውሳላችሁ፡፡ እነዚህን ነገሮች በመጀመሪያ አልነገርኳችሁም ምክንያቱም በዚያን ጊዜ እኔ ከእናንተ ጋር ነበርኩ፡፡ 5 6 7 “አሁን ተመልሼ ወደ አብ እሄዳለሁ፡፡ የላከኝ እርሱ ነው፡፡ ከእናንተ ማንም ደፍሮ ‘ወዴት ትሄዳለህ?’ የሚለኝ የለም፡፡6እነዚህን ነገሮች ስለነገርኳችሁ፣ አሁን ልባችሁን ሀዘን ሞልቶታል፡፡7እኔ እውነቱን ነግሬያችኋለሁ፣ መሄዴ ለእናንተ መልካም ነው፡፡ እኔ ካልሄድኩ፣ እናንተን የሚያጽናናው ረዳት አይመጣም፡፡ እኔ ብሄድ ግን፣ እኔ እርሱን ወደ እናንተ እልካለሁ፡፡ 8 9 10 11 ረዳት የሆነው ሲመጣ፣ በሰሩት ሀጢአት ይወቅሳቸዋል፤ የእግዚአብሔርን መልካምነት በህይወታቸው እንዳልገለጹ ያሳያቸዋል፤ እግዚአብሔር እንዲያደርጉት የሚጠብቅባቸውን ባለማድረጋቸው እግዚአብሔር እንደሚፈርድባቸው ያሳስባቸዋል፡፡ 9በኃጢአታቸው ጥፋተኝነት የሚሰማቸው በእኔ ማመን ባለመቻላቸው ነው፡፡ 10የእግዚአብሔርን መልካምነት በህይወታቸው አለማሳየታቸው እኔ ወደ አባቴ በመመለሴ ምክንያት ይረጋገጣል፣ ከዚህ በኋላ አታዩኝም፡፡ 11እግዚአብሔር በኃጢአታቸው ምክንያት በእነርሱ ላይ ቅጣት ሲያመጣ የመጨረሻቸው ይሆናል፡፡ ይህ የሚታየው የዚህ አለም ገዥ ሰይጣን እግዚአብሔርን በመዋጋቱ ቅጣቱን ሲቀበል ነው፡፡ 12 13 14 ሌላ ልነግራችሁ የምፈልገው ብዙ ነገር አለኝ፡፡ ሆኖም፣ አሁን ብነግራችሁ፣ እነዚህን ነገሮች አውቃችሁ በደህና ለመኖር ልትሸከሙት አትችሉም፡፡ 13የእውነነት መንፈስ ሲመጣ፣ ማወቅ ወዲያስፈልጋችሁ እውነት ሁሉ ይመራችኋል፡፡ እርሱ በራሱ ስልጣን አይናገርም፣ ነገር ግን የሰማውን ይነግራችኋል፣ ደግሞም ስለሚሆኑ ነገሮች አስቀድሞ ይነግራችኋል፡፡ 14መንፈሱ እኔ ማን እንደሆንኩ ለእናንተ በመናገርና የሰራሁትን ለእናንተ በማሳየት ያከብረኛል፡፡ እርሱ ከእኔ የሰማውን ሁሉ ለእናንተ ይገልጻል፡፡ 15 16 አባቴ ያለው ነገር ነገር ሁሌ የእኔ ነው፡፡ ስለዚህም ነው መንፈሱ ከእኔ የተቀበለውን ሁሉ ወስዶ ለእናንተ ያብራራል ብዬ የተናገርኩት፡፡ 16ከጥቂት ጊዜ በኋላ እኔን አታዩኝም፡፡ ከዚያ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እንደገና ታዩኛላችሁ፡፡ 17 18 ስለዚህ አንዳዶቹ ደቀመዛሙርቱ እርሱ በእርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፣ ‘ኢየሱስ ለእኛ እንዲህ ሲል ምን ማለቱ ነው፣ ‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ እኔን አታዩኝም፣’ ደግሞም ‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ እኔን እንደገና ታዩኛላችሁ’ ሲል ምን ማለቱ ነው? ደግሞም ‘ምክንያቱም እኔ ተመልሼ ወደ አባቴ እሄዳሁ’ ሲል ምን ማለቱ ነው? ተባባሉ፡፡ 18እንዲህ እያሉ መጠያየቃቸውን ቀጠሉ፣ ‘ከጥቂት ጊዜ በኋላ’ ሲል ምን ማለቱ ነው? ምን እየተናገረ እንደሆነ እኛ አልገባንም፡፡” 19 20 21 ብዙ ጥያቄዎችን ሊጠይቁት እንደፈለጉ አወቀ፡፡ ስለዚህ ለደቀመዛሙርቱ እንዲህ አላቸው፣ ‘ምን ማለቴ እንደሆነ ለምን እርስ በእርሳችሁ ትጠያየቃላችሁ? እኔ ለጥቂት ጊዜ አታዩኝም፣ ከዚያ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እንደገና ታዩኛላችሁ ብዬ ተናግሬያለሁ፡፡ 20እኔ እውነቱን እየነገርኳችሁ ነው፤ እናንተ ታላቅሳላችሁ ታዝኑማላችሁ የዚህ ዓለም የሆኑት ግን ይደሰታሉ፡፡ እናንተ በታላቅ ሀዘን ውስጥ ታልፋላችሁ፣ ነገር ግን ሀዘናችሁ ወደ ከፍተኛ ደስታ ይለወጣል፡፡ 21ይህ ልክ አንዲት ሴት ለመውለድ ስታምጥ እንደሚሰማት ጭንቀት አይነት ነው፡፡ ህጻኑ ከተወለደ በኋላ ወደዚህ ዓለም ልጇ በመወለዱ ምክንያት በምታገኘው ከፍተኛ ደስታ ስቃይዋን ትረሳዋለች፡፡ 22 23 24 እናንተ፣ እንደ እርሷ አሁን አዝናችኋል ነገር ግን እንደገና አያችኋለሁ ደግሞም እግዚአብሔር ከእናንተ ማንም ሊወስድባችሁ የማይችለውን ታላቅ ደስታ ይሰጣችኋል፡፡23በዚያን ቀን፣ እኔን የምትጠይቁት ተጨማሪ ጥያቄ አይኖራችሁም፡፡ እኔ እውነቱን እየነገርኳችሁ ነው፤ አብን የምትጠይቁትን ሁሉ በጠየቃችሁ ጊዜ እርሱ ለእናንተ ይሰጣል ምክንያቱም እናንተ ከእኔ ጋር አንድ ሆናችኋል፡፡ 24እስከ አሁን ድረስ፣ እንደዚያ ያለ ነገር አልጠየቃችሁም፡፡ ጠይቁ የጠየቃችሁትን ያንን ትቀበላላችሁ፤ እግዚአብሔር ሁሉንም ነገር የሚሞላ እንደዚህ ያለ ከፍ ያለ ደስታ ይሰጣችኋል፡፡ 25 እነዚህ ነገሮች ምሳሌዎችንና እንቆቅልሾችን በመጠቀም ስናገር ቆይቻሁ፡፡ ነገር ግን እንደዚያ ዐይነት ቋንቋ የማልጠቀምበት ጊዜ በቶሎ ይመጣል፡፡ ይልቁንም ስለ አባቴ በግልጽ በሚገባችሁ ቋንቋ እነግራችኋለሁ፡፡ 26 27 28 በዚያን ጊዜ እንደ እግዚአብሔር ሀሳብ በስሜ ጥያቄዎቻችሁን ለእግዚአብሔር ታቀርባላችሁ፡፡ ፍላጎቶቻችሁን እንዲያሟላ እኔ አብን መጠየቅ አይኖርብኝም፣ 27እናንተ እኔን ስለወደዳችሁ እና በእኔ ስላመናችሁ እንዲሁም እኔ ከእግዚአብሔር እንደመጣሁ ስላወቃችሁ አብ ራሱ እናንተን ይወዳል፡፡ 28እኔ ከአብ መጥቻለሁ፣ እናም ወደዚህ ዓለም ገብቻለሁ፡፡ አሁን ይህን ዓለም እተዋለሁ፣ እናም ወደ አብ ተመልሼ እሄዳለሁ፡፡ 29 30 31 ከዚያ ደቀመዛሙርቱ እንዲህ አሉ፣ “በመጨረሻ! አሁን በግልጽ ትናገራለህ ምሳሌያዊ ቋንቋዎችን አትጠቀምም፡፡ 30አሁን አንተ ሁሉንም ነገር እንደምታውቅ ተረድተናል፡፡ አንተን ጥያቄዎችን መጠየቅ አስፈላጊ አይደለም፡፡ አንተን ያመነው ለዚህ ነው፣ እናም በእርግጠኝነት ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደመጣህ አውቀናል፡፡” 31ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰላለቸው፣ “አሁን በመጨረሻ በእኔአ መናችሁን? 32 33 ልብ በሉ! በየስፍራ የምትበተኑበት ጊዜ እየመጣ ነው! እያንዳንዱ ወደየቤቱ ይሄዳል፣ እናንተም እኔን ትተዉኛላችሁ፡፡ ሆኖም እኔ ብቻዬን አልሆንም ምክንያቱም አብ ሁልጊዜም ከእኔ ጋር ነው፡፡ 33በእኔ ሰላም እንዲኖራችሁ እነዚህን ነገሮች ነገርኳችሁ በዓለም ውስጥ ፈተናና ሀዘን አለባችሁ፡፡ ነገር ግን ብርቱ ሁኑ! እኔ ዓለምን አሸንፌአለሁ!”

ምዕራፍ 17

1 2 ኢየሱስ እዚህን ነገሮች ከተናገረ በኋላ፣ ወደ ሰማይ ቀና ብሎ እንዲህ አለ፣ “አባት ሆይ ለእያንዳንዱ የሰራሁትን ሁሉ የምታሳይበትና የምታውጅበት እንዲሁም እኔ የአንተ ልጅ ማን እንደሆንኩ ለእነርሱ የምትናገርበት ጊዜው አሁን ነው፡፡ እኔ፣ የአንተ ልጅ ሁሉን ማድረግ የምትችውን ታላቅ ንጉስ የሆንከውን አንተን ማን እንደሆንክ ለእያንዳንዱ እገልጽ ዘንድ ይህን አድርግ፡፡ 2ለልጅህ፣ በሁሉም ሰዎች ላይ መግዛት አንደፈቀድክልኝ ሁሉ ይህን አድርግ፡፡ አባት ሆይ፣ ለእኔ የሰጠኸኝን ሁሉ ለዘለዓም እንዲኖሩ ማድረግ እችል ዘንድ ይህን አድርገሃል፡፡ 3 4 5 አባት ሆይ ብቸኛ እውነተኛ አምላክ የሆንከውን አንተንና ወደዚህ ዓለም የላከውን እኔን ኢየሱስ ክርስቶስን ማወቅ ይህ የዘለዓም ህይወት ነው፡፡ 4ስለ አንተ ሁሉንም ለማሳየት ሁሉንም አይነት ሰዎች ወደ አንተ አምጥቻለሁ፡፡ የሰጠኸኝን ሥራ በመጨረስ ይህን አድርጌያለሁ፡፡ 5አባት ሆይ፣ ዓምን ከመፍጠራችን በፊት እንነበርነው እኔን ወደ ራስህ መገኘት በማምጣት አክብረኝ፡፡ 6 7 8 የእኔ እንዲሆኑ በዚህ ዓለም ከእያንዳንዱ አንተ የመረጥካቸውን አንተ በእርግጥ ማን እንደሆንክ እና ምን ዐይነት እንደሆንክ አስተምሬያቸዋለሁ፡፡ እነርሱ የአንተ ናቸው እናም አንተ እነርሱን ለእኔ ሰጥተኸኛል፡፡ አንተ ለእኔ የነገርከኝን እነርሱ አምነዋል፣ እናም ያንን ታዘዋል፡፡ 7እነርሱ አሁን አንተ የሰጠኸኝ ነገር ሁሉ ከአንተ እንደመጣ አውቀዋል፡፡ 8የሰጠኸኝን መልእክት ሰጥቻቸዋለሁ፡፡ እነርሱም ተቀብውታል፣ እኔ ከአንተ እንደመጣሁ እነርሱ አሁን በእርግጥ አውቀዋል፣ ደግሞም እንተ እንደላከኝ አምነዋል፡፡ 9 10 11 እኔ ለእነርሱ እጸልያለሁ፡፡ የዚህ ዓም ለሆኑት አንተን መቃወማቸውን ለሚቀጥሉ አልጸልይም፡፡ አንተ ለእኔ ለሰጠኸኝ ለእነርሱ እጸልያለሁ ምክንያቱም እነርሱ የአንተ ናቸው፡፡ 10እኔ ያለኝ ሁሉ የአንተ ነው፣ አንተ ያለህ ሁሉ የእኔ ነው፡፡ እነርሱ እኔ ማን እንደሆንኩ ያውቃሉ፣ እኔ ማን እንደሆንኩ እውነቱን በታማኝነት ይናገራሉ፡፡ 11ከዚህ በኋላ በዓለም አልቆይም፡፡ ሆኖም እነርሱ በዓለም ውስጥ ይቆያሉ፡፡ እኔ ወደ አንተ እየመጣሁ ነው፡፡ ቅዱስ አባት ሆይ፣ በሰላም ጠብቃቸው፤ ልክ እኛ እንደሆነው በአንድነት ይሆኑ ዘንድ አንተ ለእኔ በሰጠኸው በዚያው ዐይነት ሀይል የራስህ አድርገህ ጠብቃቸው፡፡ 12 13 14 ከእነርሱ ጋር በነበርኩበት ጊዜ፣ በአንተ በራስህ ሀይል በሰላም ጠብቅኳቸው ከለልኳቸውም፡፡ መጽሐፍት ከዘመናት አስቀድሞ እንደተናገሩት፣ አንተ ለጥፋት ከወሰንከው ከአንዱ በስተቀር ከእነርሱ አንዱም አልጠፉም፡፡ 13አባት ሆይ፣ አሁን ወደ አንተ እየመጣሁ ነው፡፡ ሙሉ ደስታዬን እሰጣቸው ዘንድ እነዚህን ነገሮች እዚህ በዓለም እያለሁ ተናግሬያለሁ፡፡ 14እኔ የአንተን መልዕክት ለእነርሱ ተናግሬያለሁ፣ የዚህ ዓለም የሆኑት የአንተን ሰዎች ይጠላሉ ምክንያቱም የአንተ የሆኑ የዚህ ዓለም አይደሉም፡፡ 15 16 17 ከዚህ ዓለም እንድታወጣቸው አልጠይቅህም፣ ነገር ግን ይልቁንም ክፉው ሊያደርግባቸው ከሚችለው ጉዳት እንድትጠብቃቸው እጠይቅሃለሁ፡፡ 16ልክ እኔ የዚህ ዓለም እንዳልሆንኩት ሁሉ እነርሱም የዚህ ዓለም አይደሉም፡፡ 17ስለራስህ እውነቱን በማስተማር ለራስህ ለያቸው፡፡ መልዕክቶችህ ሙሉ ለሙሉ እውነት ናቸውና እነርሱን ትለያቸው ዘንድ ማወቅ የሚያስፈልጋቸውን አስተምራቸው፡፡ 18 19 እኔን ወደ ዓለም እንደላከኝ፣ እኔም እነርሱን ወደ ዓለም እልካቸዋለሁ፡፡ 19በእውነት ራሳቸውን ለአንተ መስጠት ይችሉ ዘንድ እኔ ስለ እነርሱ ራሴን ለአንተ ሙሉ ለሙሉ ሰጥቻለሁ፡፡ 20 21 “ስለ እነዚህ ብቻ አልጸልይም፣ ነገር ግን የእነርሱን መልዕክት ሲሰሙ በእኔ ስለሚያምኑ ጭምር እጸልያለሁ፡፡ 21ልክ አንተ እና እኔ አንድ እንደሆንን እነርሱ ሁሉ አንድ እንዲሆኑ እጸልያለሁ፡፡ አባት ሆይ፣ አንተ ከእኔ ጋር አንድ ነህ፣ እኔም ከአንተ ጋር እነርሱም ከእኛ ጋር አንድ ይሁኑ፡፡ ዓለም አንተ እንደላከኝ ያውቅ ዘንድ ይህን አድርግ፡፡ 22 23 እኔ ማን እንደሆንኩ ገልጬላቸዋለሁ፣ እነርሱም ያደረግኩትን አይተዋል፡፡ አንተ እና እኔ አንድ እንደሆንን እነርሱ አንድ ይሆኑ ዘንድ ይህን አስተምሬያቸዋለሁ፡፡ 23እኔ ከእነርሱ ጋር አንድ ሆኛለሁ፡፡ አንተም ከእኔ ጋር አንድ ሆነሀል፡፡ በእኔ የሚያምኑ ፍጹም አንድ ይሆኑ ዘንድና የማያምኑ አንተ እንደላከኝ ያውቁና ልክ አንተ እኔን እንደወደድከኝ በእኔ የሚያምኑትን እንደምትወዳቸውያውቁ ዘንድ ይህንን አድርጌያለሁ፡፡ 24 “አባት ሆይ፣ እኔ ከአንተ ጋር ስሆን የምትሰጠኝን ውበትና ግርማ ማየት ይችሉ ዘንድ እነዚህ የሰጠኸኝ ሁልጊዜም እኔ ባለሁበት ከእኔ ጋር እንዲሆኑ እፈልጋለሁ፡፡ እኛ ዓለምን ከመፍጠራችን አስቀድሞ አንተ እኔን ስለወደድከኝ ይህን አድርግ፡፡ 25 26 ጻድቅ አባት ሆይ ዓለም አንተን አላወቀህም፣ ነገር ግን እኔ አውቅሃለሁ፤ እነዚህ አሁን ከእኔ ጋር ያሉት ወደ እነርሱ እንደላከኝ ያውቃሉ፡፡ 26አንተ ማን እንደሆንክ እንዲያውቁ አድርጌያለሁ፡፡ አንተ እኔን እንደወደድከኝ እነርሱንም እንድትወዳቸው ይህን ማድረግ እቀጥላለህ ስለዚህም ደግሞ ከእነርሱ ጋር አንድ እሆናለሁ፡፡”

ምዕራፍ 18

1 2 3 ኢየሱስ ጸሎቱን ሲጨርስ፣ ከደቀመዛሙርቱ ጋር የቄድሮንን ሸለቆ አቋርጦ ሄደ፡፡ ከማዶ የወይራ ዛፎች እርሻ ነበር እነርሱም እዚያ ውስጥ ገቡ፡፡ 2ኢየሱስን ለጠላቶቹ አሳልፎ ሊሰጠው የተዘጋጀው ይሁዳ፣ ቦታው የት እንደነበር ያውቃል፤ ምክንያቱም ኢየሱስ ብዙ ጊዜ ከደቀመዛሙርቱ ጋር ወደዚያ ይሄድ ነበር፡፡ 3ሊቀካህናቱና ፈሪሳውያን ከይሁዳ ጋር ጥቂት ወታደሮችና መኮንኖች ወደዚያ እንዲሄዱ ትዕዛዝ ሰጥተው ነበር፡፡ ስለዚህም ወደ አትክልት ሥራ ፋኖሶች፣ ችቦዎች እና መሳሪያዎች ይዘው ሄዱ፡፡ 4 5 ኢየሱስ ምን እንደሚደርስበት ያውቅ ነበር፣ ስለዚህም ወደፊት ቀረብ ብሎ እንዲህ ሲል ጠየቃቸው፣ “ማንን እየፈለጋችሁ ነው?” 5እንዲህ ብለው መለሱለት፣ “የናዝሬቱን ኢየሱስን፡፡” ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ “እኔ ያ ሰው ነኝ፡፡” (አሁን ይሁዳ፣ አሳልፎ የሚሰጠው፣ ከእነርሱ ጋር ቆሞ ነበር፡፡) 6 7 ኢየሱስ፣ “እኔ ያ ሰው ነኝ፣” ባላቸው ጊዜ “በፍጥነት ወደኋላ አፈግፍገው ምድር ላይ ወደቁ፡፡ 7ስለዚህም ዳግም ጠየቃቸው፣ “ማንን እየፈለጋችሁ ነው?” እንዲህ ብለው መለሱለት፣ “የናዝሬቱን ኢየሱስን፡፡” 8 9 ኢየሱስ እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፣ “ያ ሰው እኔ ነኝ ብዬ ነገርኳችሁ፡፡ የምትፈልጉት እኔን እስከሆነ ድረስ፣ እነዚህ ሌሎች ሰዎች ይሂዱ ተዉአቸው፡፡ 9ይህ የሆነው ለአባቱ ሲጸልይ፣ ፣ከሰጠኸኝ ከእነርሱ ውስጥ አንዱ እንኳን አልጠፋብኝም” ብሎ የተናገራቸው ቃላት እንዲፈፀም ነው፡፡ 10 11 ከዚያ ስምዖን ጴጥሮስ አጠር ያለ ሰይፍ አወጣና የሊቀ ካህኑን አገልጋይ መታው፣ የሰውየው ስም ማልኮስ ነበር፣ ቀኝ ጆሮውን ቆረጠው፡፡ 11ኢየሱስ ጴጥሮስን እንዲህ አለው፣ “ሰይፍህን ወደ አፎቱ መልስ! አባቴ እኔ እንዳደርገው ባቀደው መሠረት መከራን በእርግጥ እቀበላለሁ፡፡” 12 13 14 ከዚያ የወታደሮች ቡድን ከአዛዣቸው እና ከጥቂት የቤተ መቅደስ ጠባቀዎች ጋር ኢየሱስን ይዘው እንዳያመልጥ ለመከላከል አሰሩት፡፡ 13ከዚያ የቀያፋ አማት ወደሆነው ወደ ሐና ወሰዱት በዚያ አመት ሊቀካህን ነበር፡፡ 14ሌሎች መሪዎችን ሁሉም ሰው ከሚጠፋ ለህዝቡ ሲባል አንድ ሰው ሲሞት ይሻላል ብሎ የመከራቸው ቀያፋ ነበር፡፡ 15 16 ስምዖን ጴጥሮስ ኢየሱስን ተከተለው እንዲሁም ሌላ አንድ ደቀመዝሙር ኢየሱስን ተከተለው፡፡ ሌላኛው ደቀመዝሙር በሊቀ ካህኑ ይታወቅ ነበር፣ ስለዚህም ወታደሮቹ ኢየሱስን ሲወስዱት ይህ ደቀመዝሙር ወደ ሊቀካህኑ ግቢ ለመግባት ተፈቀደለት፡፡ 16ጴጥሮስ ግን ከውጭ በር ላይ ቀረ፡፡ ስለዚህ ሌላኛው ደቀመዝሙር እንደገና ወደ ውጭ ወጣና በሩን ትጠብቅ ከነበረች አገልጋይ ልጃገረድ ጋር ተነጋገረ እርሷም ጴጥሮስ እንዲገባ ፈቀደችለት፡፡ 17 18 አገልጋይዋ ልጃገረድ ጴጥሮስን እንዲህ አለችው፣ “እነርሱ ያሰሩት ሰው ደቀመዝሙር ነህ፣ አይደለህምን?” እርሱ እንዲህ አለ፣ “አይይ እኔ አይደለሁም፡፡” 18ብርድ ነበርና ስለዚህም የሊቀ ካህኑ አገልጋዮችና የቤተመቅደስ ጠባቂዎች ከሰል አንድደው በእሳቱ ዙሪያ ቆመው ይሞቁ ነበር፡፡ ጴጥሮስም ደግሞ በዚያ ከእነርሱ ጋር ነበር፤ ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር፡፡ 19 20 21 ሊቀ ካህኑ ኢየሱስን ስለ ደቀመዛሙርቱና እነርሱን ምን ያስተምራቸው እንደነበር ጠየቀው፡፡ 20ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰ፣ “ለእያንዳንዱ በግልጽ ተናገርኩ፡፡ በምኩራቦች እና በቤተ መቅደስ፣ ህዝባችን በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች ሁልጊዜም አስተማርኩ፡፡ ምንም ነገር በሚስጥር አልተናገርኩም፡፡ 21ስለዚህ እነዚህን ጥያቄዎች ለምን ትጠይቀኛለህ? ትምህርቴን ያደመጡ ሰዎችን ጠይቅ፡፡ እነርሱ ምን እንደተናገርኩ ያውቃሉ፡፡ 22 23 24 ኢየሱስ እነዚህን ነገሮች ሲናገር፣ ከአጠገቡ ከቆሙ የቤተመቅደስ ጠባቀዎች አንዱ በሀይል በእጁ መታው፡፡ እርሱም እንዲህ አለ፣ “ለሊቀ ካህኑ መልስ የምትሰጥበት ትክለኛ መንገድ ይህ አይደለም፡፡” 23ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰለት፣ “ስህተት የሆነ ነገር ተናግሬ ከሆነ፣ ምን እንደነበረ ንገረኝ፡፡ ሆኖም፣ የተናገርኩት ትክክል ከነበረ፣ በጥፊ ልትመታኝ አይገባም!” 24ከዚያ ሐና ኢየሱስን እንደታሰረ ወደ ሊቀካህኑ ወደ ቀያፋ ላከው፡፡ 25 26 27 ስምዖን ጴጥሮስ እስከ አሁንም ድረስ ቆሞ እሳት ይሞቅ ነበር፡፡ ሌላ ሰው ደግሞ እንዲህ አለው፣ “እነርሱ ካሰሩት ሰው ደቀመዛሙርት መሀል አንዱ አንተ ነህ፣ አይደለህምን? እርሱም እንዲህ አለ፣ “አይ፣ እኔ አይደለሁም፣” 26ጴጥሮስ ጆሮውን የቆረጠው አገልጋይ ዘመድ የሆነ ከሊቀ ካህናቱ አገልጋዮች አንዱ፣ እንዲህ አለው፣ “እነርሱ ካሰሩት ሰው ጋር በወይራ ዛፍ እርሻ ስፍራ በእርግጥ እኔ አይቼሃለሁ፣ አላየሁህምን?” 27ጴጥሮስ ዳግም ይህንንም ካደ እናም ወዲያውኑ አንድ አውራ ዶሮ ጮኸ፡፡ 28 29 30 ከዚያ ወታደሮች ኢየሱስን ከቀያፋ ቤት ወደ ሮማዊው ገዥ ጲላጦስ ግቢ ወሰዱት፡፡ ጊዜው ገና ማለዳ ነበር፡፡ ጲላጦስ አይሁዳዊ አልነበረም፣ ስለዚህም የኢየሱስ ከሳሾች ወደ ጲላጦስ ግቢ ቢገቡ ራሳቸውን እንደሚያረክሱና የፋሲካ በዓልን ማክበር እንደማይችሉ አሰቡ፡፡ ስለዚህም ወደ ውስጥ አልገቡም፡፡ 29ስለዚህ ጲላጦስ ከእነርሱ ጋር ለመነጋገር ከግቢው ወደ ውጭ ወጣ፡፡ እንዲህም አለ፣ “ይህን ሰው የምትከሱት በምንድን ነው?” 30እነርሱ፣ ይህ ሰው ወንጀለኛ ካልሆነ ወደ አንተ አናመጣውም ነበር!” ሲሉ መለሱ፡፡ 31 32 ከዚያ ጲላጦስ እንደዚህ አላቸው፣ “እናንተ ራሳችሁ ይዛችሁት ሂዱና በራሳችሁ ህግ ፍረዱበት፡፡” ከዚያ የአይሁድ መሪዎች እንዲህ አሉ፣ “እኛ ልንገድለው እንፈልጋለን፣ ነገር ግን የእናንተ የሮማውያን ህግ ይህን እንዳናደርግ ይከለክለናል፡፡” 32እነርሱ ይህን የተናገሩት ኢየሱስ በምን ዐይነት ሞት እንደሚሞት የተናገረው ይፈፀም ዘንድ ነው፡፡” 33 34 35 ከዚያ ጲላጦስ ወደ ግቢው ተመልሶ ገባ፡፡ ኢየሱስን አስጠርቶ እንዲህ አለው፣ “አንተ የአይሁድ ንጉስ ነህ?” 34ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰ፣ “ይህን የምትጠይቀው አንተ ራስህ ማወቅ ፈልገህ ነው፣ ወይንስ ሌሎች ይህን ጥያቄ እንድትጠይቀኝ ነግረውህ ነው?” 35ጲላጦስ እንዲህ ሲል መለሰ፣ “እኔ አይሁዳዊ አይደለሁም! የአንተ የራስህ ህዝቦችና ሊቀ ካህናት አንተን ለእኔ አሳልፈው ሰጡ፡፡ ምን ስህተት ፈጽመሃል?” 36 37 ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰ፣ “የእኔ መንግስት ከዚህ ዓለም አይደለም፡፡ የእኔ መንግስት ከዚህ ዓለም ቢሆን ኖሮ፣ አገልጋዮቼ ለአይሁድ ተቃዋሚዎች ታልፌ እንዳልሰጥ እኔን ለመጠበቅ ይዋጉ ነበር፣ ነገር ግን የእኔ መንግስት ከዚህ ዓለም አይደለም፡፡ 37ከዚያ ጲላጦስ እንዲህ አለው፣ “ስለዚህ አንተ ንጉስ ነህ?” ኢየሱስ እዲህ ሲል መለሰ፣ “አዎን፡፡ የተወለድኩበትና ወደዚህ ዓም የመጣሁበት ምክንያት ስለ እግዚአብሔር ለሰዎች ለመናገር ነው፡፡ እውነትን የሚወድ ሁሉ እኔን ይሰማል፡፡” 38 39 40 ጲላጦስ እንዲህ ሲል ጠየቀው፣ “እውነት ምንድን ነው?” ጲላጦስ ያንን ጥያቄ ከጠየቀ በኋላ፣ ወደ ውጭ ወጥቶ እንደገና ከአይሁድ መሪዎች ጋር ተነጋገረ፡፡ እንደዚህም አላቸው፣ “ምንም ህግ እንዳላፈረሰ ደርሼበታለሁ፡፡ 39ሆኖም፣ እናተ አይዶች በየአመቱ በፋሲካ በኣል አንድ ልማድ አላችሁ፣ በእስር ቤት ያለ አንድ ሰው እንድፈታ ትጠይቁኛላችሁ፡፡ ስለዚህ የአይሁድን ንጉስ እንድፈታላችሁ ትፈልጋላችሁን? 40እንደገና እንዲህ እያሉ ጮሁ፣ “አይ! ይህን ሰው አትፍታው ነገር ግን በርባንን ፍታው!” ባርባን አመፀኛ ነበር፡፡

ምዕራፍ 19

1 2 3 ከዚያ ጲላጦስ ኢየሱስን ላከው፡፡ ወታደሮቹ በአለንጋ ክፉኛ ገረፉት፡፡ 2እንደዚሁም ወታደሮቹ የሾህ አክሊል አበጅተው በራሱ ላይ አደረጉ፡፡ እንዲሁም ሀምራዊ ልብስ አለበሱት፡፡ 3እያፌዙበት እንዲህ አሉ፣ “የአይሁድ ንጉስ፣ ሠላም ላንተ ይሁን!” ደግሞም እየደጋገሙ መቱት፡፡ 4 5 6 ጲላጦስ እንደገና ወደ ውጭ መጥቶ ለህዝቡ እንዲህ አለ፣ “ተመልከቱ፣ እርሱን ለመቅጣት ምንም ምክንያት እንዳላገኘሁበት ታውቁ ዘንድ ወደ እናንተ አምጥቼዋለሁ፡፡” 5ስለዚህም ኢየሱስ የሾህ አክሊል ደፍቶና ሀምራዊ ልብስ ለብሶ ወደ ውጭ ወጣ፡፡ ጲላጦስ እንደዚህ አላቸው፣ “ተመልከቱ ሰውየው እነሆ!” 6ሊቀ ካህናቱና የመቅደስ ጠባቂዎቹ እርሱን ሲመለከቱ እንዲህ እያሉ ጮሁ፣ “ስቀለው! ስቀለው!” ጲላጦስ እንዲህ አላቸው “እናንተ ራሳችሁ ውሰዱትና ስቀሉት! በእኔ በኩል እርሱን ለመቅጣት ምንም ምክንያት አላገኘሁም፡፡” 7 8 9 የአይሁድ መሪዎች ለጲላጦስ እዲህ ብለው መለሱለት፣ “እኛ ህግ አለን፣ ራሱን የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ስላ መሞት ይገባዋ፡፡” 8ጲላጦስ ይህንን ሲሰማ፣ ይበልጥ ፈራ 9እንደገና መልሶ ወደ ግቢው ገባና ኢየሱስን መልሰው ወደ ውስጥ እንዲያስገቡት ወታደሮችን ጠራ፡፡ ከዚያ ኢየሱስን እንዲህ አለው፣ “የመጣኸው ከየት ነው?” ሆኖም ኢየሱስ ምንም መልስ አልሰጠውም፡፡ 10 11 ስለዚህም ጲላጦስ እንዲህ አለው፣ “መልስ አትሰጠኝምን? ልፈታህ ስልጣን እንዳለኝ ደግሞም ልለቅህ ስልጣን እንዳለኝ አታውቅምን?” 11ኢየሱስ እንዲህ ሲል መለሰለት፣ “እግዚአብሔር ይህን ባይሰጥህ ኖሮ፣ በእኔ ላይ ምንም ስልጣን አይኖርህም ነበር፡፡ ለአንተ አሳልፎ የሰጠኝ በባሰ ኃጢአት ጥፋተኛ ነው፡፡” 12 13 ከዚያ ሰዓት አንስቶ ጲላጦስ ኢየሱስን ለመፍታት ጥረት አደረገ፡፡ ሆኖም የአይሁድ መሪዎች እንዲህ እያሉ ጮሁ፣ “ይህንን ሰው ከፈታኸው፣ አንተ የቄሳር ወዳጅ አይደለህም! ማንም ራሱን ንጉስ የሚያደርግ የቄሳር ተቃዋሚ ሆኖ ይቆማል፡፡” 13ጲላጦስ ይህን ሲሰማ፣ ኢየሱስን ወደ ውጭ አወጣው፡፡ ከዚያ ጲላጦስ ከእርሱ ፊት ብዙውን ጊዜ ውሳኔ በሚሰጥበት ስፍራ በፍርድ ወንበር ላይ ተቀመጠ፡፡ ይህ ስፍራ “የድንጋይ ንጣፍ” ተብሎ ሲጠራ፤ በአረማይክ “ገበታ” ይባላል፡፡ 14 15 16 አሁን ከፋሲካ በዓል አንድ ቀን ቀደም ብሎ የዝግጅት ቀን የሚባለው ነበር፡፡ ሰዓቱ እኩለ ቀን ላይ ነበረ፣ ጲላጦስ ለአይሁዶች፣ “እዩ፣ ንጉሳችሁ ይኸውና!” አላቸው፡፡ 15እነርሱ ግን፣ “አስወግደው! አስወግደው! ስቀለው!” ብለው ጮሁ፡፡ ጲላጦስ እንዲህ አላቸው፣ “ንጉሳችሁን ልስቀለውን?” ሊቀካህናቱ፣ “እኛ ከቄሳር ሌላ ንጉስ የለንም!” ሲሉ መለሱ፡፡ 16ስለዚህም ጲላጦስ ኢየሱስን አሳልፎ ለእነርሱ ሰጣቸው፣ እነርሱም ይዘዉት ሄዱ፡፡ 17 18 የራሱን መስቀል ተሸክሞ “የራስ ቅል” ተብሎ ወደሚጠራ ስፍራ ሄደ፤ ይህ ስፍራ በአረማይክ “ጉልጎታ” ይባላለ፡፡ 18በዚያ ስፍራ እርሱን ሰቀሉት፣ እናም ደግሞ በዚያው ሰዓት ሁለት ወንጀለኞችን አንዱን በዚህኛው አንዱን በዚያኛው ጎን ኢየሱስን ከመሀል አድርገው በየመስቀሎቸው ላይ ሰቀሏቸው፡፡ 19 20 እንደዚሁም ጲላጦስ አንድ ሰው በሰሌዳ ላይ ማስታወሻ እንዲጽፍ ተናግሮ በኢየሱስ መስቀል ላይ ጽህፈቱን አንጠለጠለ፡፡ ጽህቱ እንዲህ ይነበባል “የአይሁዶች ንጉስ፣ የናዝሬቱ ኢየሱስ” ይላል፡፡ 20ኢየሱስ የተሰቀለበት ስፍራ ከተማው አጠገብ ስለነበርና ደግሞም በሶስት ቋንቋዎች፤ በአረማይክ፣ ላቲንና ግሪክ ተጽፎ ስነበር ብዙ አይሁዶች ይህን ምልክት አነበቡ፡፡ 21 22 ሊቀካህናቱ ወደ ጲላጦስ ተመልሰው ሄደው፣ “‘የአይሁዶች ንጉስ’ ብለህ መፃፍ አልነበረብህም፣ ነገር ግን ‘ይህ ሰው፣ እኔ የአይሁዶች ንጉስ ነኝ!’ ብሏል ብለህ መፃፍ ነበረብህ” አሉት፡፡ 22ጲላጦስ፣ “ምልክቱን ልክ እኔ እንደፃፍኩት መተው አለባችሁ፡፡” ሲል መለሰ፡፡ 23 24 ወታደሮቹ ኢየሱስን በመስቀል ላይ ከሰቀሉ በኋላላ ልብሱን ወሰዱና በአራት ክፍል ከፋፈሉት ለእያንዳንዱ ወታደር አንድ ክፍል፡፡ ሆኖም፣ እጀ ጠባቡን ለይተው አስቀመጡ፡፡ እጀ ጠባቡ የተሰራው ከላይ እስከ ታች ከአንድ ጨርቅ ነበር፡፡ 24ስለዚህም እርስ በእርሳቸው እንዲህ ተባባሉ፣ “ይህን አንቅደደው ይልቁንም፣ እጣ በመጣል ማን እንደሚወስደው እንወስን የደረሰው ሳይቀደድ ይውሰደው፡፡” ይህ የሆነው በመጽሐፍ እንዲህ ተብሎ የተጻፈው ይፈፀም ዘንድ ነው፣ “በመሀላቸው ልብሴን ተከፋፈሉት፡፡ በእጀ ጠባቤ ላይ ዕጣ ተጣጣሉ፡፡” 25 26 27 የኢየሱሰ እናት፣ የእናቱ እህት የቀልዮጳ ሚስት ማርያም እና ማርያም መቅደላዊት ሁሉም ከእርሱ መስቀል አጠገብ ቆመው ነበር፡፡ 26ኢየሱስ እናቱ በዚያ ቆማ ሲመለከትና በልዩ ሁኔታ ይወደው የነበረው ደቀመዝሙር ዮሐንስ በዚያ ቆሞ ሲመለከት፣ እናቱን እንዲህ አላት፣ “እናቴ፣ ለአንቺ እንደ ልጅሽ የሆነው ይኸው” 27ለደቀመዝሙሩ ደግሞ እንዲህ አለው፣ “እናትህ በዚህ ናት!” ስሊሊህም ከዚያች ሰዓት አንስቶ፣ ያ ደቀመዝሙር በእርሱ ቤት ለመኖር ወሰዳት፡፡ 28 29 30 ከጥቂት ጊዜ በኋላ፣ እግዚአብሔር እርሱ እንዲሰራው የላከው ሥራ ሁሉ እንደሚጠናቀቅ ኢየሱስ ያውቅ ነበር፤ በመጽሐፍ የተነገረው አንድ የመጨረሻ ነገር እንዲፈጸም ‘ተጠማሁ!’ አለ፡፡ 29በዚያ ስፍራ አንድ የሆመጠጠ ወይን የያዘ ዕቃ ነበር፣ ከሂሶጵ ተክል አጭር ቅርንጫፍ ወስደው በላዩ ስፖንጅ አደረጉበት፣ ከዚያ በሆመጠጠው ወይን ውስጥ ነክረው ወደ ኢየሱስ አፍ አቀረቡለት፡፡ 30ኢየሱስ የሆመጠጠውን ወይን ከጠጣ በኋላ ‘ተፈጸመ’ አለና ራሱን አዘንብሎ ሞተ፡፡ 31 32 33 ቀኑ ለፋሲካ ዝግጅት የሚደረግበት ነበር እናም በማግስቱ ሰንበት ነበር፡፡ በሰንበት የሞተ አካልን በመስቀል ላይ ማቆየት በህጉ ያልተፈቀደ ነበር፣ ስዚህም ወደ ጲላጦስ ሄደው ሰዎቹ በቶሎ እንዲሞቱና አካላቸው ከመስቀል እንዲወርድ የሶስቱን ሰዎች እግሮች ለመስበር ጠየቁት፡፡ 32ስለዚህም ወታደሮቹ መጥተው ከኢየሱስ ጋር ተሰቅለው ከነበሩት ሁለት ሰዎች የመጀመሪያውን ሰው እግር ሰበሩ፣ ከዚያም የሌላኛውን እግር ሰበሩ፡፡ 33ወደ ኢየሱስ ሲመጡ፣ ቀድሞውኑ ሞቶ አዩት፡፡ ስለዚህ የእርሱን እግር አልሰበሩም፡፡ 34 35 በምትኩ፣ ከወታደሮቹ አንዱ የኢየሱስን ጎን በጦር ወጋው፣ እናም ወዲያውኑ ደምና ውሃ ከሰውነቱ ወጣ፡፡ 35ይህን የተመለከተ ምስክርነቱን ሰጥቷል ምስክርነቱ እውነት ነው፤ እርሱ እውነቱን እየተናገረ እንደሆነ ያውቃል ይህም እናንተ በኢየሱስ እንድታምኑ ነው፡፡ 36 37 እነዚህ ነገሮች የሆኑት በመጽሐፍ “ማንም ከእርሱ አጥንቶች የትኛውንም አይሰብርም” ተብሎ የተጻፈው እንዲፈጸም ነው፡፡ 37እንደዚሁም በሌላው የመጽሐፍ ክፍል፤ ‹የወጉትን ያዩታል› ተብሎ የተፃፈውን ያሟላሉ፡፡ 38 39 ከእነዚህ ነገሮች በኋላ፣ አይሁዶችን በመፍራት በድብቅ የኢየሱስ ደቀመዝሙር የነበረው የአርማትያሱ ዮሴፍ ወደ ጲላጦስ ሄዶ የኢየሱስን በድን ለመውሰድ ጠየቀው፡፡ ጲላጦስ ለዮሴፍ ፈቀደለት፣ ስለዚህም መጥቶ የኢየሱስን በድን ወሰደ፡፡ 39በአንድ ወቀት በምሽት ወደ ኢየሱስ መጥቶ የነበረው ኒቆዲሞስ የኢየሱስን በድን ለቀብር ለማዘጋጀት የከርቤ ድብልቅና የእሬት ቅመሞች ይዞ መጣ፡፡ ቅመማ ቅመሞቹ ሰላሳ አራት ኪሎ ግራም ይመዝናሉ፡፡ 40 41 42 የኢየሱስን በድን ወስደው በላይ ነን ጨርቅ ጠቀለሉት፣ ደግሞም መገነዣዎቹን ሁሉ ምን አይነት ቅመሞች በስፋት አደረጉባቸው፡፡ 41ኢየሱስ የተሰቀለበት ስፍራ የአትክልት ስፍራ ነበር፣ በአትክልት ቦታው አንድ ጥግ ማንም ያልተቀበረበት አዲስ የመቃብር ስፍራ ነበር፡፡ 42በዚያ ምሽት የፋሲካ በዓል የሚከበርበት ጊዜ ተቃርቦ ነበር፣ ይህን መቃብር የመረጡት ቅርብ ስለሆነና ኢየሱስን በቶሎ ለመቅበር ነበር፡፡ ስለዚህም ኢየሱስን በዚያ ቀበሩት፡፡

ምዕራፍ 20

1 2 በሳምንቱ በመጀመሪያ ቀን፣ ማርያም መቅደላዊት በጣም በጠዋት ገና ሳይነጋ ወደ መቃብሩ መጣች፡፡ ድንጋዩ ከመቃብሩ ተነስቶ አየች፡፡ 2ስለዚህ ስምዖን ጴጥሮስና ኢየሱስ ይወደው የነበረው ሌላ ደቀመዝሙር ወደሚገኙበት ወደ ኢየሩሳሌም በሩጫ ተመልሳ እንዲህ ብላ ነገረቻቸው፣ “ጌታን ከመቃብሩ አውጥተው ወስደውታል፣ የት እንዳደረጉት እኛ አናውቅም!” 3 4 5 ይህንን ሲሰሙ፣ ጴጥሮስና ሌላው ደቀመዝሙር ወደ መቃብሩ ፈጥነው ሄዱ፡፡ 4ሁለቱም ይሮጡ ነበር፣ ሌላው ደቀመዝሙር ግን ከጴጥሮስ ፈጣን ነበር ስለዚህም ቀድሞ ወደ መቃብሩ ደረሰ፡፡ 5ጎንበስ ብሎ የመቃብሩን ውስጥ ተመለከተ፤ በዚያ የላይነን ቁርጥራቾች ጨርቆችን ተመለከተ፣ ነገር ግን ወደ ውስጥ ለመግባት አቅማማ፡፡ 6 7 ከዚያ ከኋላው ሲሮጥ የነበረው ስምዖን ጴጥሮስ ቦታው ደረሰ፣ እርሱ ግን ወደ መቃብሩ ውስጥ ገባ፡፡ እርሱም ደግሞ የላይነን ቁርጥራጭ ጨርቆቹን አየ፣ 7ደግሞም በኢየሱስ ራስ ላይ የነበረውን የጨርቅ መሸፈኛ ተጣጥፎና በአንድ ጥግ ከላይነን ቁርጥራጭ ተለይቶ ተመለከተ፡፡ 8 9 10 ከዚያ ሌላውም ደቀመዝሙር ወደ ውስጥ ገባ፤ እነዚህን ነገሮች ተመልክቶ ኢየሱስ ከሞት መነሳቱን ማመን ጀመረ፡፡ 9እስከ አሁን ድረስ መጽሐፍ ኢየሱስ ከሞት ይነሳል የሚለው አልገባቸውም፡፡ 10ስለዚህ ደቀመዛሙርቱ ወደየቤቶቻቸው ተመለሱ፡፡ 11 12 13 ማርያም ከመቃብሩ ውጭ ቆማ እያለቀሰች ነበረች፡፡ እያለቀሰች ጎንበስ ብላ ወደ መቃብሩ ውስጥ ተመለከተች፡፡ 12ሁለት መልእክት ነጭ ልብስ ለብሰው የኢየሱስ አስከሬን በነበረበት ስፍራ አንዱ በራስጌ ሌላው በግርጌው ተቀምጠው አየች፡፤ 13እነርሱ እንዲህ አሏት፣ “አንቺ ሴት፣ ለምን ታለቅሻለሽ?” እርሷ እንዲህ አለቻቸው “ጌታዬን ወስደውታል፣ የት እንዳደረጉት እኔ አላውቅም!” 14 15 ይህን ከተናገረች በኋላ ዞር ብላ ኢየሱስ በዚያ ቆሞ አየችው፣ ነገር ግን እርሱ እንደሆነ አላወቀችም፡፡ 15እርሱ እንዲህ አላት፣ “አንቺ ሴት ለምን ታለቅሻለሽ? ማንን እየፈለግሽ ነው?” ከእርሷ ጋር የሚነጋገረው ሰው አትክክልተኛው መስሏት እንዲህ አለችው፣ “ጌታዬ፣ አንተ ወስደኸው ከሆነ የት እንዳደረግከው ንገረኝ፣ እኔ እወስደዋለሁ፡፡” 16 17 18 ኢየሱስ፣ “ማርያ” አላት፡፡ ዘወር ብላ በአረማይክ ቋንቋ “ረቡኒ!” አለች (ትርጉሙ “መምህር” ማለት ነው)፡፡ 17ኢየሱስ እንዲህ አላት፣ “እንዳትነኪኝ፣ ከአባቴ ጋር ለመሆን ገና ወደ መንግስተ ሰማይ አልሄድኩም፡፡ ወደ ደቀመዛሙርት ሄደሽ እንዲህ በያቸው፣ ‘ከአባቴና ከአባታችሁ ጋርለመሆን፣ የእኔ አምላክ የእናንተ አምላክ ወደሆነው ተመልሼ ሄጄ ከእርሱ ጋር ለመሆን ወደ መንግስተ ሰማይ ልመለስ ጊዜው ደርሷል፡፡’” 18ማርያም መቅደላዊት ወደ ደቀመዛሙርቱ ሄዳ እዲህ ብላ ተናገረች፣ “ጌታን አየሁት” ኢየሱስ የተናገራትንም ተናገረች፡፡ 19 20 በዚያን ቀን ምሽት፣ በሳምንቱ በመጀመሪያ ቀን፣ በሮች ተዘግተው ደቀመዛሙርት የአይሁድ ባለስልጣናት እንዳያስሯቸው ፈርተው ቤት ውስጥ ነበሩ፡፡ ኢየሱስ በድንገት መጥቶ በተሰበሰቡት መሀል ቆመ፤ እንዲህም አላቸው፣ “የእግዚአብሔር ሠላም ከእናንተ ጋር ይን፡፡” 20ይህን ከተናገረ በኋላላ እጆቹንና ጎኑን አሳያቸው፡፡ ደቀመዛሙርት ጌታን ሲያዩ እጅግ ደስ አላቸው! 21 22 23 ኢየሱስ እንደገና እንዲህ አላቸው፣ “ሠላም ለእናንተ ይሁን፡፡ አብ እኔን እንደላከኝ፣ አሁን እኔ እንተን እልካችኋለሁ፡፡” 22ይህን ከተናገረ በኋላ፣ እፍ አለባቸውና እንዲህ አላቸው፣ “መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ፡፡ 23የሰዎችን ኃጢአት ይቅር ብትሉ፣ እግዚአብሔር ይቅር ይላቸዋል፡፡ የሌሎችን ኃጢአት ይቅር ባትሉ፣ ደይቅር አይባልላቸውም፡፡” 24 25 ከአስራ ሁለቱ አንዱ የሆነው ቶማስ “መንትያው” ተብሎ የሚጠራው ኢየሱስ ወደ እነርሱ ሲመጣ ከሌሎች ደቀመዛሙርት ጋር አልበረም፡፡ 25ሌላው ደቀመዝሙር እዲህ ብሎ ነገረው፣ “ጌታን አየነው፡፡” ሆኖም፣ እርሱ እንዲህ አላቸው “በእጆቹ ላይ የምስማሮቹን ምልክቶ ካላየሁ በስተቀር እና በምስማሮቹ በተፈጠሩት ቀዳዳዎች ውስጥ ጣቶቼን ካልጨመርኩ፣ እንዲሁም በጎኑ የቁስሉ ቀዳዳ እጆቼን ካላደረግኩ በስተቀር በፍጹም አላምንም፡፡” 26 27 ከስምንት ቀናት በኋላ ደቀመዛሙርቱ እንደገና በቤት ውስጥ ነበሩ፣ በዚህ ጊዜ ቶማስ ከእነርሱ ጋር ነበር፡፡ በሮች እንደተዘጉ ቢሆንም፣ ኢየሱስ መጥቶ በመሀላቸው ቆሞ እንዲህ አላቸው፣ “ሰላም ለእናንተ ይሁን፡፡” 27ከዚያም ቶማስን እንዲህ አለው “ጣቶችህን እዚህ አድርግ እጆቼን ተመልከት እጆችህን ዘርጋና በጎኔ ላይ አድርግ! እኔ መሆኔን መጠራጠር አቁም፤ በእኔ እመን፡፡” 28 29 ቶማስ እንደህ ብሎ መለሰለት፣ “ጌታዬና አምላኬ!” 29ኢየሱስ እንዲህ አለው፣ “አሁን ስላየህ ከሞት መነሳቴን አመንክ፡፡ እግዚአብሔር ሳያዩኝ ለሚያም ታላቅ ደስታ ይሰጣቸዋል፡፡” 30 31 ኢየሱስ እርሱ ማን እንደሆነ የሚያረጋግጡ ሌሎች ብዙ የሀይል ስራዎችንና ታምራቶችን አድርጓል፡፡ ደቀመዛሙርቱ ያዩትን መስከረዋል፣ ነገር ግን በጣም በርካታ በመሆናቸው በዚህ መጽሐፍ ሁሉንም የሀይል ስራዎቹንና ተአምራቶቹን አልጻፍኩም፡፡ 31የሆነ ሆኖ፣ ኢየሱስ እርሱ ክርስቶስ፣ የእግዚአብሔር ልጅ መሆኑን ሙሉ እርግጠኝነት እንዲኖራቸው እነዚህ ጽፌያለሁ፤ እናም ደግሞ እርሱን በማመን በስሙ የዘለዓለም ሕይወት ይኖራችኋል፡፡

ምዕራፍ 21

1 2 3 ከዚያ በኋላ ኢየሱስ በጥብርያዶስ (የገሊላ ባህር ተብሎም ይታወቃል) ሐይቅ ለደቀመዛሙርቱ ታየ፡፡ ራሱን የገለጠው በዚህ መንገድ ነበር፤ 2ስምዖን ጴጥሮስ፣ ቶማስ (መንትያው ተብሎ የሚጠራው)፣ ገሊላ ውስጥ ከምትገኘው ከቃና የሆነው ናትናኤል፣ የዘብዴዎስ ልጆች (ያዕቆብና ዮሐንስ)፣ እና ሌሎች ሁለት ደቀመዛሙርት አብረው ነበሩ፡፡ 3ስምዖን ጴጥሮስ ለተቀሩት እንዲህ አላቸው፣ “አሳ ላጠምድ መሄዴ ነው፡፡” እነርሱም እዲህ አሉ፣ “እኛም ከአንተ ጋር እንሄዳን፡፡” እነርሱም ወጥተው ወደ ጀልባቸው ሄዱ፣ ነገር ግን በዚያ ምሽት ምንም አላጠመዱም፡፡ 4 5 6 በጠዋት ገና ቀኑ ሲነጋ፣ ኢየሱስ ውሃው ዳርቻ ቆመ፣ ነገር ግን ደቀመዛሙርቱ ኢየሱስ እንደሆነ አላወቁም ነበር፡፡ 5ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ “ወዳጆቼ፣ አሳ አላችሁን?” እነርሱም “የለንም” ብለው መለሱለት፡፡ 6እርሱ እንዲህ አላቸው፣ “መረባችሁን ከጀልባው በስተቀኝ በኩል ጣሉ ጥቂት ታገኛላች” እነርሱም እርሱ እንደነገራቸው መረባቸውን ጣሉ፣ መረባቸውን ወደ ጀልባዋ መሳብ እስከማይችሉ ድረስ በጣም ብዙ አሳዎች ያዙ! 7 8 9 ዮሐንስ፣ በተለየ ሁኔታ ኢየሱስ ይወደው የነበረው ደቀመዝሙር፣ ጴጥሮስን እንዲህ አለው፣ “ጌታ እኮ ነው!” ስምዖን ጴጥሮስ ይህንን ሲናገር ሲሰማ፣ ከላይ በሚለብሰው አካሉን ሸፈን አደረገና (እየሰራ ሳለ ከሞላ ጎደል እርቃኑን ነበር) ዘሎ ወደ ውሃ ውስጥ ገባ፡፡ 8ሌሎቹ ደቀመዛሙርት በጀልባዋ ውስጥ ሆነው በአሳ የተሞላውን መረብ እየጎተቱ ወደ ዳርቻ መጡ፡፡ ከዳርቻው አስራ ዘጠኝ ሜትር ያህል ብቻ ርቀት ላይ ስለነበሩ ከዳርቻው ሩቅ አልነበሩም፡፡ 9ወደ ባህሩ ዳርቻ ሲደርሱ፣ የተዘጋጀና የተቀጣጠለ ከሰል ተመለከቱ፣ በላዩ ላይ አሳ እየበሰለበት ሲሆን ጥቂት እንጀራም ነበር፡፡ 10 11 ኢየሱስ እዲህ አላቸው፣ “አሁን ከያዛችሁት አሳ ጥቂት አምጡ!” 11ስምዖን ጴጥሮስ ወደ ጀልባዋ ተመልሶ በትልልቅ አሳዎች የተሞላውን መረብ ወደ ዳርቻ ሳበ፡፡ 153 አሳዎች ነበሩ፡፡ እንዲያም ሆኖ መረቡ አልተቀደደም፡፡ 12 13 14 ኢየሱስ እንዲህ አላቸው፣ “ኑና ቁርስ በሉ!” ከደቀመዛሙርት ማንም፣ “አንተ ማን ነህ?” ብሎ ሊጠይቀው የደፈረ አልነበረም፡፡ ጌታ እንደሆነ አውቀው ነበር፡፡ 13ኢየሱስ መጥቶ እንጀራውን ተቀብሎ ሰጣቸው፡፡ ከአሳውም እንዲሁ አደረገ፡፡ 14እግዚአብሔር ከሙታን ካስነሳው በኋላ ለደቀመዛሙርት ሲታይ ይህ ለሶስተኛ ጊዜ ነበር፡፡ 15 16 ቁርስ በልተው ሲጨርሱ ኢየሱስ ስምኦን ጴጥሮስን እንዲህ አለው፣ “የዮና ልጅ ስምኦን እነዚህ ሌሎች ከሚወዱኝ ይልቅ ይበልጥ ትወደኛህን?” ጴጥሮስ እንዲህ አለው፤ “አዎን ጌታ እደምወድህ አንተ ታውቃህ፡፡” ኢየሱስ እዲህ አለው፣ “ጠቦቶቼን መግብ፡፡” 16ኢየሱስ ለሁለተኛ ጊዜ እንዲህ አለው፣ “የዮና ልጅ ስምኦን ትወደኛለህ?” እርሱ እንዲህ ሲል መለሰ፣ “አዎን፣ ጌታ፣ እንደምወድህ አንተ ታውቃለህ፡፡” ኢየሱስ እንዲህ አለው፣ “የበጎቼ እረኛ ሁን፡፡ 17 18 ኢየሱስ ለሶስተኛ ጊዜ እንዲህ አለው፣ “የዮና ልጅ ስምኦን ትወደኛለህን?” ለሶስተኛ ጊዜ ኢየሱስ ሶስት ጊዜ ትወደኛለህን?” ብሎ ስለጠየቀው ጴጥሮስ አዘነ፡፡ ጴጥሮስ፣ “ጌታ አንተ ሁሉንም ነገር ታውቃለህ፡፡ እንደምወድህ ታውቃለህ” አለ፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አለው፣ “በጎቼን መግብ፡፡” 18እኔ እውነቱን እየነገርኩህ ነው፤ “ወጣት ሆነህ፣ ልብስህን ራስህ ትለብሳለህ ደግሞም መሄድ ወደምትፈልግብት ስፍራ ሁሉ ትሄዳለህ፡፡ ሆኖም፣ በምታረጅበት ጊዜ አንተ እጆችህን ትዘረጋለህ፣ እናም ሌላ ሰው ያለብስሃል ደግሞም መሄድ ወደማትፈልግበት ይመራሃል፡፡” 19 ኢየሱስ ይህን የተናገረው ጴጥሮስ እግዚአብሔርን ለማክበር ሲል እንዴት እንደሚሞት ለማመልከት ነው፡፡ ከዚያ ኢየሱስ እንዲህ አለው፣ “ተከተለኝ፡፡” 20 21 ጴጥሮስ ወደኋላ ዞር ብሎ፣ ዮሐንስ፣ ኢየሱስ በተለየ ሁኔታ የሚወደው ደቀዝሙር ሲከተላቸው አየ፡፡ ይህ ደቀመዝሙር እራት ላይ ወደ ኢየሱስ ጠጋ ብሎ፣ “ጌታ፣ ለጠላቶችህ አሳልፎ የሚሰጥህ ማን ነው?” ብሎ የጠየቀው ነበር፡፡ 21ጴጥሮስ እርሱን ሲመለከተው፣ ኢየሱስን እዲህ አለው፣ “ጌታ ሆይ በዚህ ሰው ላይ ምን ሊደርስ ነው?” 22 23 ኢየሱስ እንዲሀ አለው፣ “እስክመለስ ድረስ በህይወት እንዲቆይ ብፈልግ፣ ያ የአንተ ጉዳይ አይደለም! አንተ እኔን ተከተለኝ፡፡” 23ይህ ወሬ በክርስቶስ ወንድማማቾች በሆኑ መሀል፣ ይህ ደቀመዝሙር አይሞትም በሚል ወሬው ተሰራጨ፤ ሆኖም ግን ኢየሱስ እርሱ አይሞትም አላም ነበር፡፡ “እስክመለስ ድረስ በህይወት እንዲቆይ ብፈልግ ያ የአንተ ጉዳይ አይደለም!” ብቻ ነበር ያለው፡፡ 24 25 እኔ፣ ዮሐንስ፣ ስለ እነዚህ ነገሮች ሁሉ ምስክርነት የሰጠሁ ደቀመዝሙር ነኝ፣ እናም እነዚያን ጽፌያለሁ፡፡ የእርሱ ምስክርነት እውነት እንደሆነ እኛ እናውቃን፡፡ 25ኢየሱስ ሌሎች ብዙ ነገሮችን አድርጓል ሁሉም ቢጻፉ ከብዛታቸው የተነሳ የሚፃፉትን መጽሐፍት መላው ዓለም ሊይዛቸው የሚችል አይመስለኝም፡፡