አማርኛ: tn

Updated ? hours ago # views See on DCS

Job

Job 1

Job 1:1-3

በዖጽ ምድር

ይህ ስፍራ ሊገኝ የሚችለው 1) በአሁኗ ዮርዳኖስ፣ ከዮርዳኖስ ወንዝ በስተ ምስራቅ ጥንት ኤዶም በምትባል ስፍራ ወይም 2) በአሁኗ ኢራን ከኤፍራጥስ ወንዝ በስተ ምስራቅ ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ነቀፋ የሌለበት እና ትክክለኛ

"ነቀፋ የሌለበት" እና "ትክክለኛ" የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ ደግሞም ቃላቱ ኢዮብ ጻድቅ ሰው መሆኑን ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ "በእግዚአንሔር ፊት ትክክል የሆነውን የሚያደርግ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔርን የሚፈራ

"እግዚአብሔርን የሚያከብር"

ከክፉ የራቀ

እዚህ ስፍራ ክፉ የተገለጸው ሰው ወደዚያ ስፍራ ሄዶ ክፉ ከማድረግ ይልቅ ወደዚያ ከመሄድ ራሱን እንደሚያቅብበት ስፍራ ተደርጎ ነው፡፡ "ክፉ ማድረግን አሻፈረኝ ማለት/ከክፋት የራቀ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሰባት ወንዶች ልጆች እና ሶስት ሴቶች ልጆች

"7 ወንዶች ልጆች እና 3 ሴቶች ልጆች" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ሰባት ሺህ በጎች ነበሩት

"7,000 በጎች ነበሩት" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ሶስት ሺህ ግመሎች

"3,000 ግመሎች" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

አምስት መቶ ጥማድ/ጥንድ በሬዎች

"500 ጥማድ/ጥንድ በሬዎች" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

እጅግ ታላቅ

"ከሁሉም ባለጸጋ"

በምስራቅ የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ

ከከነዓን በስተ ምስራቅ የሚገኝን ስፍራ ያመለክታል፡፡ "ከከነዓን በስተ ምስራቅ በሚገኝ ምድር የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ" (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 1:4-5

በእያንዳንዱ ልጅ ተራ፣ እርሱ ያቀርብ ነበር

"ቀን" የሚለው ቃል ምናልባት የአንዱን ልጅ ልደት የሚያከብሩበት ቀን ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ቢያንስ ልጆቹ በየተራ ድግስ እንደሚያደርጉ ያመለክታል፡፡ "በእያንዳንዱ ልጅ የልደት ቀን፣ ልጁ ያቀርብ ነበር" ወይም "እያንዳንዱ ልጅ በተራው ያቀርብ ነበር"

እርሱ ያቀርብ ነበር… እነርሱ ልከው… ይጠሩ ነበር… ኢዮብ ይልክ ነበር… እርሱ ይሳል ነበር… በጥዋት ማልዶ ተነስቶ መስዋዕት ያቀርብ ነበር... እንዲህ ይል ነበር

"ሁሌም ያቀርብ ነበር…እነርሱ ሁሌም… ልከው ይጠሩ ነበር… ኢዮብ ሁሌም ይልክ… ሁሌም ይሳል… እርሱ ሁሌም ማልዶ ይነሳ እና ይሰዋ… እርሱ ሁሌም እንዲህ ይል ነበር"

ከእነርሱ ጋር

"እነርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሰባቱን ወንዶች ልጆች እና ሶስቱን ሴት ልጆች ሲሆን ኢዮብን ግን አይጨምርም፡፡

የድግሱ ዕለት ሲያልፍ

"ድግሱ ሲጠናቀቅ" ወይም "ከድግሱ በኋላ"

ኢዮብ ወደ እነርሱ ይልክና

"ኢዮብ ዘወትር እነርሱ ወደ እርሱ እንዲመጡ አንድ ሰው ይልክ ነበር"

እነርሱን ያነጻ ነበር

እዚህ ስፍራ "ማንጻት" ማለት የኢዮብ ልጆች በደስታ በአንድነት ተሰብስበው ግብዣ ሲያደርጉ የፈጸሙት የምልኮ ነቀፊታ ቢኖር ጥፋት እንዳይደርስባቸው እግዚአብሔርን ይቅርታ መለመን ማለት ነው፡፡ ኢዮብ ስለ እነርሱ መስዋዕት በማቅረብ ይህን ያደርግ ነበር፡፡

በልባቸው እግዚአብሔርን ረግመው ቢሆን

"በልባቸው" የሚለው የሚወክለው ሃሳባቸውን ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ እንዲህ ያሉ ሃሳቦች አንድ ሰው ነገሩን ሊያስበው ሳይፈልግ ከፈቃዱ ውጭ ሊመጡ ይችላሉ፡፡ "በሃሳባቸው እግዚአብሔርን ረግመው ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 1:6-8

ከዚያም … የሚደረግበት ቀን ነበር

"በ…በሚሆንበት ጊዜ" ወይም "አንድ ዕለት... በ…ጊዜ፡፡" ይህ በአንድ የተለየ ቀን ብቻ የተደረገ አይደለም፣ ይልቁንም ስብሰባው ብዙውን ጊዜ እንደሚደረግ ግልጽ ነው፡፡

የእግዚአብሔር ልጆች

ይህ ሰማያዊ ፍጥረታትን፣ መላዕክትን ያመለክታል፡፡

ራሳቸውን በያህዌ ፊት ለማቅረብ

"ያደርጉት ዘንድ እርሱ እንዳዘዛቸው በያህዌ ፊት በአንድነት ለመቆም"

ያህዌ

ይህ እግዚአብሔር በብሉይ ኪዳን ራሱን ለህዝቡ የገለጸበት ስም ነው፡፡ ስለ ያህዌ ይህ እንዴት እንደሚተረጎም የቃል ትርጉም ገጽን ይመልከቱ፡፡

በምድር ከመዞር፣ በላይዋ ከመመላለስ

"መዞር" እና "መመላለስ" የሚሉት ሀረጋት በምድር ሁሉ የመጓዝን ድርጊት በሙላት ለማጉላት የዋለ ነው፡፡ "በምድር ላይ በሁሉም ስፍራ መዞር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ጽንፍ የሚሉትን ይመልከቱ)

ባሪያዬን ኢዮብን አይተኸዋልን?

"ስለ ባሪያዬ ኢዮብ አውቀሃልን?" እዚህ ስፍራ እግዚአብሔር ስለ ኢዮብ ከሰይጣን ጋር መነጋገር ይጀምራል፡፡ "ባሪያዬን ኢዮብን አይተኸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ነቀፋ የሌለበት እና ቅን ሰው

"ነቀፋ የሌለበት" እና "ቅን" የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉሞችን ሲይዙ ኢዮብ ጻድቅ ሰው መሆኑን አጉልተው ያሳያሉ፡፡ ይህ በኢዮብ 1፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነውን የሚያደርግ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔርን የሚፈራ

"እግዚአብሔርን የሚያከብር፡፡" ይህ በኢዮብ 1፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

Job 1:9-12

ኢዮብ እግዚአብሔርን የሚፈራው ያለ ምክንያት ነውን?

"ኢዮብ እግዚአብሔርን የሚያከብረው ያለ ምክንያት ነውን?" ሰይጣን ለእግዚአብሔር ጥያቄ አቅርቦ ራሱ መልስ ይሰጣል፡፡ ኢዮብ እግዚአብሔርን የሚታዘዘው እግዚአብሔር ስለባረከው ብቻ ነው ይላል፡፡ "ኢዮብ እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ምክንያት አለው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

በዙሪያው፣ በቤቱ ዙሪያ እና ባለው ነገር ሁሉ ዙሪያ ቅጥር አላኖርክለትምን?

ሰይጣን ክርክሩን ለማጠናከር የሚረዱትን መረጃዎች ሁሉ ይናገራል፡፡ "አንተ እርሱን፣ ቤተሰቡን እና ያለውን ነገር ሁሉ ጠብቀሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

በዙሪያው፣ በቤቱ ዙሪያ እና ባለው ነገር ሁሉ ዙሪያ ቅጥር አድርገህለታል

እንደ ግርግዳ ወይም አጥር ያለ መከላከያ የአንድን ሰው ይዞታ ዙሪያውን እንደሚከብ እና እንደሚጠብቅ፣ እግዚአብሔር ኢዮብን በጥበቃው ከቦታል፡፡ "እርሱን እና ቤቱን እንዲሁም የእርሱ የሆነውን ሁሉ ጠብቀሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የእጆቹን ስራዎች

"የሚሰራውን ነገር ሁሉ"

በምድር ላይ ከብቱ በዝቶለታል

"በምድር ላይ ከብቱ ተትረፍርፏል"

ነገር ግን አሁን እጅህን ዘርግተህ ያለውን ሁሉ ንካበት፣ በዚያን ጊዜ ፊት ለፊት እንደማይረግምህ ታያለህ

ሰይጣን ይህንን ማለቱ እግዚአብሔር ኢዮብን ቢነካው፣ የኢዮብ ምላሽ ምን እንደሚሆን ይመለከታል ማለቱ ነው፡፡ "ነገር ግን አሁን፣ እጅህን ብትዘረጋ እና ያለውን ሁሉ ብትነካ ፊት ለፊት እንደሚረግምህ ታያለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ነገር ግን አሁን፣ እጅህን ዘረጋ

እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚወክለው የእግዚአብሔርን የማድረግ አቅም ነው፡፡ "ነገር ግን አሁን ሀይልህን ተጠቀም" (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ያለውን ሁሉ ንካ

እዚህ ስፍራ "መንካት" የሚወክለው ጉዳት የማድረስ ወይም የማጥፋት ድርጊትን ነው፡፡ "ያለውን ሁሉ አጥፋ" ወይም "ያለውን ሁሉ ደምስስ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በፊትህ

"እየሰማኸው፡፡" ይህ የሚያመለክተው እግዚአብሔር ትኩረት የሚሰጥበትን ጊዜ ነው፡፡

እነሆ

"እነሆ" ወይም "የምናገረውን ትኩረት ሰጥተህ ብትሰማኝ"

እርሱ ያለው ሁሉ በእጅህ ነው

እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚወክለው አንድ ሰው አንድን ነገር ለመቆጣጠር ያለውን አቅም/ሀይል ነው፡፡ "እርሱ ባለው ነገር ላይ ሁሉ አቅም ተሰጥቶሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በእርሱ በራሱ ላይ

"በህይወቱ ላይ"

ያህዌ ከሚገኝበት ወጥቶ ሄደ

"ከያህዌ ፊት ወጥቶ ሄደ" ወይም "ያህዌ ካለበት ለቆ ሄደ"

Job 1:13-15

ሳባውያን

ይህ በዛሬ ዘመን በየመን አካባቢ የሚኖሩ ሰዎችን ያመለክታል፡፡ እዚህ ስፍራ ይህ የሚወክለው የፈረሰኞችን ቡድን ወይም ሽፍቶችን ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ እና ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

በእነርሱ ላይ ወደቁባቸው

እዚህ ስፍራ "መውደቅ" የሚለው የሚገልጸው ማጥቃትን ነው፡፡ "እነርሱን አጠቋቸው/አደጋ ጣሉባቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

መቷቸው

እዚህ ስፍራ ማጥቃት የሚለው የሚገልጸው መግደልን ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የሰይፍ ስለት

እዚህ ስፍራ "የሰይፍ ስለት" የሚለው የሚወክለው ሰው ለመግደያነት የሚውለውን የሰይፉን ክፍል ነው፤ ይህም ማለት አንድም የሰይፉን ጫፍ ወይም የተሳለውን ጠርዝ ማለት ነው፡፡ እንደዚሁም ደግሞ፣ የሳባውያን ሰይፎች ሁሉ እንደ አንድ ሰይፍ ብቻ ተደርጎ ተገጽዋል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና የስማዊ ሀረጋት ክፍል የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 1:16-17

እርሱ ገና እየተናገረ ሳለ

"እርሱ" የሚለው የሚያመለክተው የመጀመሪያውን መልዕክተኛ ነው፡፡

ሌላው ደግሞ መጣ

ይህ የሚያመለክተው ሌላውን መልዕክተኛ ነው፡፡ "ሌላው መልዕክተኛ ደግሞ መጣ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተዘለለ/የተተወ የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ ብቻዬን አመልሁ፤ ልነግረህም መጣሁ

ይህ በኢዮብ 1፡15 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

አገልጋዮችህንም በሰይፍ ስለት መቷቸው፡፡ እኔ ብቻ ልነግርህ አመለጥሁ

እዚህ ስፍራ "የሰይፍ ስለት" የሚለው የሚወክለው ሰው ለመግደያነት የሚውለውን የሰይፉን ክፍል ነው፤ ይህም ማለት አንድም የሰይፉን ጫፍ ወይም የተሳለውን ጠርዝ ማለት ነው፡፡ እንደዚሁም ደግሞ፣ የከለዳውያን ሰይፎች ሁሉ እንደ አንድ ሰይፍ ብቻ ተደርጎ ተገጽዋል፡፡ ይህ በኢዮብ 1፡15 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና የስማዊ ሀረጋት ክፍል የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 1:18-19

ወንዶች እና ሴቶች ልጆችህ በታላቅ ወንድማቸው ቤት ይበሉና ወይን ይጠጡ ነበር

ይህ በኢዮብ 1፡13 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

አውሎ ነፋስ

"አውራቂስ/ቶርኔዶ" ወይም "የበረሃ ማዕበል"

የቤቱ አራት ማዕዘኖች

"ቤቱን ያቆመው መዋቅር/ቤቱ የተዋቀረበት ድጋፍ"

በወጣቶቹ ላይ ወደቀ

"ቤቱ በወንዶች እና ሴቶች ልጆችህ ላይ ወደቀ"

እኔ ብቻዬን አመልሁ፤ ልነግረህም መጣሁ

ይህ በኢዮብ 1፡15 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

Job 1:20-22

ልብሱን ቀደደ፣ ራሱን ተላጨ

እነዚህ ሀዘንን የመግለጫ ስርዓቶች ነበሩ፤ ጥልቅ ሀዘንን መድረሱን ያመለክታሉ፡፡ (ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊቶች የሚለውን ይመልከቱ)

ከእኔቴ ማህጸን ስወጣ እርቃኔን ነበር፣ ደግሞም እርቃኔን እመለሳለሁ

"ስወለድ፣ ወደዚህ ዓለም አንዳች ይዤ አልመጣሁም፤ ስሞትም ምንም ሳልይዝ ወደ ምድር እመለሳሉ"

በዚህ ሁሉ ነገር

"በሆነው ነገር ሁሉ"

እግዚአብሔርን አጥፍተሃል ብለህ ክሰስ

"እግዚአብሔርን ተሳስተሃል በለው"

Job 2

Job 2:1-2

አጠቃላይ መረጃ፡

እነዚህ ሀረጋት በኢዮብ 1፡1-6 ውስጥ ካለው ጋር ፍጹም ተመሳሳይ ናቸው፤ እናም ምናልባትም በተመሳሳይ መንገድ ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡

ከዚያም ዕለቱ ያ ነበር

ይህ በኢዮብ 1፡6 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ

አንድ ዕለት

ይህ አንድ ውሱን ቀን አይደለም፡፡ መሰባሰቡ ብዙ ጊዜ ይደረጋል፡፡ "በ…ጊዜ" ወይም "በ…አንድ ዕለት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

የእግዚአብሔር ልጆች

ይህ በኢዮብ 1፡6 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ

ራሳቸውን በያህዌ ፊት አቀረቡ/በእግዚአብሔር ፊት መጡ

ይህ በኢዮብ 1፡6 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ

በምድር ላይ ከመዞር፣ በላይዋ ወዲያና ወዲህ ከመመላለስ

ይህ በኢዮብ 1፡7 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ

Job 2:3

አጠቃላይ መረጃ፡

ይህ ሀረግ "አንተ ያለ ምክንያት እንዳጠፋው በእርሱ ላይ ብታነሳሳኝም እርሱ ታማኝነቱን እንዳጸና ነው" የሚለው ከመጨመሩ በስተቀር ከኢዮብ 1፡8 ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡

አገልጋዬን ኢዮብን ተመለከትከውን?

ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ በእርግጥ ዐረፍተ ነገርን ይመሰርታል፡፡ ይህ በኢዮብ 1፡8 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "አገልጋዬን ኢዮብን ተመለከትከው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ነቀፋ የሌለበት እና ቅን ሰው

"ነቀፋ የሌለበት" እና "ቅን" የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉሞችን ሲይዙ ኢዮብ ጻድቅ ሰው መሆኑን አጉልተው ያሳያሉ፡፡ ይህ በኢዮብ 1፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "በእግዚአብሔር ፊት መልካም የሆነውን የሚያደርግ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔርን የሚፈራ እና ከክፋት የራቀ

ይህ በኢዮብ 1፡1 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

እስከ አሁን ታማኝነቱን ጠብቋል

"መልካም እና ትክክል የሆነውን ለማድረግ እስከ አሁን ሙሉ ለሙሉ ራሱን ሰጥቷል"

በእርሱ ላይ በክፉ ብትገፋፋኝም

"ያለ ምክንያት እርሱን እንዳጠፋው ብትገፋፋኝም"

እርሱን እንዳጠፋው

እዚህ ስፍራ "ማጥፋት" የሚለው የሚገልጸው "ማደህየት" የሚለውን ነው፡፡ "ደሃ ሰው እንዳደርገው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

Job 2:4-6

በእርግጥ ቆዳ ስለ ቆዳ ነው

እዚህ ስፍራ "ቆዳ" የሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ የሚገልጸው የኢዮብን ህይወት ነው፡፡ "ሰው ህይወቱን ለማዳን ሀብቱን እና የሚወዳቸውን ሰዎች ማጣትን መቀበልን ጨምሮ ማናቸውንም ዐይነት ነገር ያደርጋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ነገር ግን አሁን እጅህን ዘርግተህ አጥንት እና ስጋውን ብትነካ፣ በፊትህ በእርግጥ የማይራገም ስለመሆኑ እስኪ ተመልኩት

ሰይጣን ይህን ማለቱ፣ እግዚአብሔር ኢዮብን ቢጎዳው ኢዮብ እንዴት ምላሽ እንደሚሰጥ ይመለከታል ማለቱ ነው፡፡ "ነገር ግን አሁን፣ እጅህን ብትዘረጋ እና አጥንቱን እና ስጋውን ብትነካ በፊትህ እንደሚረግምህ ትመለከታለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

እጅህን ዘርጋ

እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚያመለክተው የእግዚአብሔርን የማድረግ ሀይል ነው፡፡ "ነገር ግን አሁን ሀይልህን ተጠቀም" ይህ በኢዮብ 1፡11 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

መንካት

እዚህ ስፍራ "መንካት" የሚያመለክተው መጉዳትን ነው፡፡ "አጥቃው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

አጥንቱ እና ስጋው

ይህ አገላለጽ የሚወክለው የኦዮብን አካል ነው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

በፊትህ ይረግምሃል

ይህ በኢዮብ 1፡11 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

በፊትህ

ይህ የሚያመለክተው እግዚአብሔር በትኩረት ነገሩን የሚመለከትበትን ጊዜ ነው፡፡ "እየሰማህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 2:7-8

ከዚያም ሰይጣን ከእግዚአብሔር ፊት ወጥቶ ሄደ

ይህ በኢዮብ 1፡12 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

እርሱ ኢዮብን በቁስል መታው

"በከባድ ቁስል አሰቃየው"

የስቃይ ቁስል

ትልቅ፣ የሚያሳክክ እና ስቃይ የሞላበት የቆዳ ቁስል

ገላውን የሚያክበት ገል/የሸክላ ስባሪ

ማከኪያው ስቃዩን ለመቀነስ ቆዳውን የሚያክበት ነው

በአመድ መሃል ተቀመጠ

ይህ ምናልባት አመድና ቆሻሻ ተጥሎ የሚቃጠልበትን ስፍራ ሊያመለክት ይችላል፡፡ እንዲህ ባለው ስፍራ መቀመጥ ጥልቅ ሀዘን መድረሱን የሚያመለክት ነበር፡፡ "በቆሻሻ ክምር ላይ ተቀመጠ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዩፊሚዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት እና ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊቶች የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 2:9-10

እስከ አሁን ታማኝነትህን ጠብቀሃል?

ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ ዐረፍተ ነገርን ይገልጻል፡፡ "እሰከ አሁን ታማኝነትህን መጠበቅ አልነበረብህም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔርን ተራገም

"እግዚአብሔርን ተው"

አንቺ እንደ ሞኝ ሴት ተናገርሽ

"የማይረቡ ሴቶች እንደሚናገሩት ተናገርሽ"

መልካሙን ከእግዚአብሔር ዘንድ እንደ ተቀበልን ክፉውንስ አንቀበልምን?

ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ ዐረፍተ ነበርን ይገልጻል፡፡ "መልካሙን ከእግዚአብሔር እንደተቀበልን ሁሉ ክፉውንም በእርግጥ መቀበል ይገባናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

መልካሙን መቀበል

"መልካም ከሆኑ ነገሮች ሁሉ ተጠቃሚ መሆን"

መልካም የሆነው

ይህ የሚወክለው እግዚአብሔር የሰጠንን መልካም ነገሮች ሁሉ ነው፡፡ (የስማዊ ሀረጋት ክፍሎች)

ክፉ የሆነውን መቀበል

"ሳያማርሩ ክፉ የሆነውን ሁሉ መቀበል"

ክፉ የሆነው

ይህ የሚወክለው እግዚአብሔር እንድናልፍበት የፈቀደቀውን ወይም ያደረገውን ክፉ ነገሮች ሁሉ ነው፡፡ (የስማዊ ሀረጋት ክፍሎች)

ከከንፈሮቹ በደል

እዚህ ስፍራ "ከንፈሮች" የሚወክለው የንግግርን ነው፡፡ "በንግግር እግዚአብሔርን መበደል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 2:11

ቴማናዊው ኤልፋዝ፣ ሹሐዊው በልዶስ፣ እና ናዕማታዊው ሶፋር

ኤልፋዝ፣ በልዶስ እና ሶፋር የወንድ ስሞች ናቸው፡፡ ቴማን በኤዶም ውስጥ የምትገኝ ከተማ ናት፡፡ ሹሐዊያን የአብርሃም እና የኬጡራ ትውልዶች ናቸው፡፡ ናዕማ በከነዓን ውስጥ የምትገኝ ከተማ ናት፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ጊዜ ወሰኑ

"በጊዜው ላይ ስምምነት ላይ ደረሱ)

ከእርሱ ጋር ለማልቀስ እና እርሱን ለማጽናናት

እዚህ ስፍራ "አብሮ ለማልቀስ" እና "ለማጽናናት" የሚሉት ቃላት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ወዳጆቹ ኢዮብን ለማጽናናት የሞከሩት ከእርሱ ጋር በማዘን ነው፡፡ "መከራውን እንዲረሳ" ከኢዮብ ጋር አዘኑ በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

Job 2:12-13

ዐይኖቻቸውን አነሱ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን ትርጉሙም "በትኩረት ተመለከቱ" ወይም "በጥንቃቄ አዩ" ማለት ነው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አላወቁትም

ይህ ምናልባት የኢዮብ ጠያቂዎች ከሩቅ ሲመለከቱት በመጀመሪያ በቶሎ አላወቁትም ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ ኢዮብ ከሀዘኑ እና ገላውን ከወረሰው ህመም የተነሳ ከወትሮው በጣም የተለየ ሆኖ ይታይ ነበር፡፡ "ለይተው ሊያውቁት አልቻሉም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ድምጻቸውን አንስተው አለቀሱ

እዚህ ስፍራ "ድምጻቸውን አንስተው" የሚለው ጮኸው ለሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "ጮኸው አለቀሱ" ወይም "ድምጻቸውን ከፍ አድርገው አለቀሱ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ልብሱን ቀደደ

ይህ የሀዘን ምልክት ነው፡፡ (ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

ትቢያ ወደ ላይ እየበተነ እና በራሱ ላይ እየነሰነሰ

እነዚህ የሀዘን መግለጫዎች ነበሩ፡፡ (ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 3

Job 3:1-3

አፉን ከፈተ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ንግግርን መጀመር ማለት ነው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የተወለድኩባት ቀን እና ምሽት ይጥፉ/መታሰቢያ ይጡ

ኢዮብ ስለዚያ ቀን እና ምሽት የሚናገረው ሰዎች እንደሆኑ አድርጎ ነው፡፡ "ምነው ባልተወለድኩ ኖሮ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

‘ወንድ ልጅ ተጸነሰ' የተባለበት ምሽት

ይህ አገላለጽ የኢዮብን ሀዘን ከተወለደበት እስከ ተጸነሰበት ቀን ድረስ ወደ ኋላ በመመለስ አጠንክሮ ይገልጻል፡፡ ‘ወንድ ልጅ ተጸነሰ የተባለበት ዕለት ይጥፋ' በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተዘለለ/የተተወ የሚለውን ይመልከቱ)

የተባለበት ምሽት

እዚህ ስፍራ ምሽት የተገለጸው መናገር የሚችል ሰው ተደርጎ ነው፡፡ ሆኖም ተርጎሚው ከዚህ ዝቅ ባለ ዘይቤያዊ አገላለጽ ሊተረጉመው ይችላል፡፡ "ሰዎች … ያሉበት ምሽት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ወንድ ልጅ ተጸንሷል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እናቱ ወንድ ልጅ ጸንሳለች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

Job 3:4-5

አጠቃላይ መረጃ፡

በዚህነዚህ ሀረጋት ውስጥ የሚገኙት አገላለጾች ኢዮብ የተወለደበት ቀን ከእንግዲህ እንዳይኖር ያለን ምኞች የሚገልጹ ናቸው፡፡ ይህ ምናልባት የቀደመው ቀን በአንድ መንገድ የሚቀጥል መሆኑን የሚጠቁም ሊሆን ይችላል፡፡ ዩዲቢ ቀኑ ምን ይመስል እንደነበር የሀዘን መግለጫ አድርጎ ይተረጉማቸዋል፡፡

ያ ቀን ጨለማ ይሁን… ፀሐይም አይውጣበት፡፡

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ኢዮብን ጸጸት በመደጋገም የተወለደበትን ቀን ጨለማነቱ ይገልጻሉ፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ያ ቀን ጨለማ ይሁን

ይህ ያዚያችን ቀን ከእንገዲህ ያለመኖር የሚገልጽ ምኞት ነው፡፡ "ያቺ እለት ትጥፋ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ ( ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ጨለማ እና የሞት ጥላ እርሱን ይውረሱት

እዚህ ስፍራ ጨለማ እና የሞት ጥላ የተገለጹት አንድን ሰው ወይም አንድን ነገር የራሱ እንደሚያደርግ ሰው ተደርገው ነው፡፡ "እርሱን" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የኢዮብን የልደት ቀን ነው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የሞት ጥላ

እዚህ ስፍራ ጥላ የሚወክለው ሞትን ነው፡፡ "ሞት እንደ ጥላ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ደመና በላዩ ይኑር

እዚህ ስፍራ ደመና የተገለጸው በኢዮብ የልደት ቀን ላይ መኖር እንደሚችል ሰው ተደርጎ ነው፡፡ "ማንም ሊመለከተው እንዳይችል ደመና ይሸፍነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ቀኑን ጨለማ የሚያደርግ ነገር ሁሉ

ይህ የሚያመለክተው የፀሐይን ብርሃን የሚጋርድን እና መለማ የሚፈጥርን ነገር ሁሉ ነው፡፡ እዚህ ስፍራ "ጥቁር" የሚወክለው ጨለማን ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ያስፈራሩት

"ያንን ቀን ያስፈራሩት፡፡" ቀኑ የተገለጸው በጨለማ ፍርሃት እንደሚውጠው ሰው ተደርጎ ነው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 3:6-7

ድቅድቅ ጨለማ ይያዘው

ይህ ጨለማ የተገለጸው ምሽቱን እንደሚይዝና እንደሚጨብጥ አንድ ሰው ተደርጎ ነው፡፡ "ከባድ ጨለማ ጨርሶ ያጥፋው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጥቅጥቅ ጨለማ

"ጥልቅ ጨለማ" ወይም "ድፍን ጨለማ"

እርሱን ደስ አይበለው

"እርሱን" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ኢዮብ የተወለደበትን ወይም የተጸነሰበትን ምሽት ነው፡፡ ኢዮብ የተጸነሰበት ምሽት የተገለጸው ደስታ ማግኘት እንደማይገባው ሰው ተደርጎ ነው፡፡ "ያ ምሽት ከቀኖች መሀል ተለይቶ ይጥፋ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አይቆጠር/ወደ ቁጥር አይምጣ

ምሽቱ የተገለጸው መራመድ የሚችል ሰው ተደርጎ ነው፡፡ "ማንም በቁጥር ውስጥ አስገብቶ አይቁጠረው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ያ ቀን መሃን ይሁን

ኢዮብ የተወለደበት ምሽት አንዲት ሴት ሆኖ ተገልጽዋል፡፡ "በዚያ ምሽት አንድም ልጅ አይወለድ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የደስታ ድምጽ ወደ እርሱ አይምጣ/አይሰማበት

እዚህ ስፍራ ኢዮብ የተወለደበት ምሽት የተገለጸው በዚያ ዕለት ወንድ ልጅ በመወለዱ ደስ የተሰኘ ሰው እንደነበር ተደርጎ ነው፡፡ "ወንድ ልጅ ሲወለድ የተሰማውን የደስታ ጩኸት ድምጽ/እልልታ ማንም አይስማው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የደስታ ጩኸት ደረሰ

እዚህ ስፍራ ድምጽ የሚለው ሚገልጸው ደስተኛ የሆነን ሰው ነው፡፡ "በእርሱ ማንም ደስተኛ አይሁን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 3:8-10

ሌዋታንን መቀስቀስ የሚችሉ

እዚህ ስፍራ ኢዮብ ጥፋትን በማስፋፋት ሌዋታንን ሳይቀር ለመቀስቀስ ይችሉ ይሆናል የሚላቸውን ጠንቆዮችን እና አስማተኞችን እያመላከተ ሊሆን ይችላል፡፡ ሌዋታን ሁሉንም አይነት ጥፋት፣ ስርአት ማጣትና ምስቅልቅል ያደርሳል ተብሎ የሚታሰብ በቅርብ ምስራቅ አገራት አፈታሪክ ውስጥ የሚታወቅ እንስሳ ነበር፡፡

የዚያን ዕለት የንጋት ከዋከወበት ይጨልሙ

ይህ የሚያመለክተው ብዙውን ጊዜ ንጋት ላይ የሚታዩትን ፕላኔቶች ነው፡፡ "ከዚያን ቀን ከሚፈነጥቀው ብርሃን አስቀድሞ የሚታዩ ከዋክብት ይጨልሙ"

ያ ቀን ብርሃን ቢፈልግን አንዳች አያግኝ

የኢዮብ ልደት ቀን የተገለጸው አንዳች ነገር እንደሚፈልግ ሰው ተደርጎ ነው፡፡ "ያ ቀን ብሃንን ተስፋ ቢያደርግም፣ ነገር ግን አንዳች አያግኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የንጋት ሽፋሽፍቶች አይመልከቱ

ንጋቱ የተገለጸው እንደ ሰው ሁሉ ሽፋሽፍቶች እንዳሉት ተደርጎ ነው፡፡ "የንጋቱን የብርሃን ፍንጣቂ አይመልከት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ምክንያቱም የእናቴን ማህጸን አልዘጋምና

ማህጸን የተገለጸው በሮች እንዳሉት መያዣ ተደርጎ ነው፡፡ "ምክንያቱም ያ ቀን የእናቴን ማህጸን አልዘጋምና" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ምክንያቱም ከዐይኖቼ ችግርን አላራቀምና

እዚህ ስፍራ የኢዮብ ልደት ቀን የተገለጸው አንድን ነገር ሊደብቅ እንደሚችል ሰው ተደርጎ ነው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከዐይኖቼ

እዚህ ስፍራ "ዐይኖች" የሚለው የሚወክለው የሚመለከትባቸውን ሰው ነው፡፡ "ከእኔ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 3:11-12

አጠቃላይ መረጃ፡

ይህ የንባብ ክፍል ኢዮብ የተለያዩ ተከታታይ ሃሳቦችን ለማቅረብ የሚጠይቃቸውን አራት ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄዎችን ይይዛል

ከማህጸን ሳልወጣ ሞቼ በቀረሁ?

"ለምን በምወለድበት ጊዜ ሳልሞት ቀረሁ?" ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የሚያቀርበው የተወለደበትን ቀን ለመርገን እና ጭንቀቱን ለመግለጽ ነው፡፡ "ምነው በተወለድኩበት ቀን በሞትኩ ኖሮ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ምነው እናቴ በወለደችኝ ቀን ነፍሴን ሳልሰጥ ቀረሁ?

ኢዮብ ይህንን የሚለው በህይወት መወለድ አልነበረብኝም ለማለት ነው፡፡ "ምነው ከማህጸን በመጣሁበት ሰአት በሞትኩ ኖሮ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ነፍሴን ብሰጥ

ይህ ሞትን ያመለክታል፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ለምን ጉልበቶቿ ታቀፉኝ

ይህ ምናልባት የኢዮብን እናት ጭኖች ሊያመለክት ይችላል፡፡ የእናቱ ጉልበቶች የተገለጹት አዲስ የተወለደን ህጻን እንደሚቀበሉ ሰዎች ተደርጎ ነው፡፡ "እኔን የሚታቀፉ የእናት ጭኖች/ጉልበቶች ባይኖሩ በመደድኩ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ሰውኛ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

እጠባቸው ዘንድ ስለምን የእናቴ ጡቶች ተቀበሉኝ?

የኢዮብ እናት ጡቶች የተገለጹት አዲስ የተወለደን ህጻን እንደሚቀበሉ ሰዎች ተደርጎ ነው፡፡ "የምጠባቸው ጡቶች ባይኖሩ በወደድኩ " በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ሰውኛ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 3:13-14

አሁን በጸጥታ ባረፍኩ ነበር፡፡ በዚህን ጊዜ ተኝቼ በእረፍት ላይ በሆንኩ ነበር፡፡

ኢዮብ ሁለቱን ዐረፍተ ነገሮች የተጠቀመው ከነጭርሱ ሳይወለድ ቢቀር ኖሮ ወይም በሚወለድበት ሰአት ሞቶ ቢሆን ኖሮ ምን ይሆን እንደነበር ለማሰብ ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ዩፊሚዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት/ የሚሉትን ይመልከቱ)

በሰላም አንቀላፋ ነበር

ኢዮብ ከላይ እንደተጠቀሰው ሳይሆን ስለቀረው ነገር ግን ባለፈው ዘመን ሊሆን ይችል ስለነበረው ነገር ያሰላስላል፡፡ "በፀጥታ በተኛሁ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

በፀጥታ መተኛት

"መተኛት፣ ማረፍ፣ በሰላም"

በዕረፍት መሆን

እዚህ ስፍራ "ዕረፍት" ማለት በሰላም መተኛት ማለት ሲሆን ነገር ግን ኢዮብ የገጠመውን ስቃይ አይኖረውም ነበር ማለት ነው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከምድር ነገሥታት እና አማካሪዎች ጋር

"ከነገሥታት እና አማካሪዎቻቸው ጋር"

Job 3:15-16

አጠቃላይ መረጃ

ኢዮብ ከመወለዱ አስቀደሞ ስለመሞቱ ያለውን ሀሳብ ይቀጥላል፡፡

ወይ እተኛ ነበር…ብርሃን በፍጹም እንዳላየ

ይህ ሊሆን የሚችል ነገር ግን ያልሆነ ነገርን ይገልጻልለለ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ከልዑላን ጋር አርፍ ነበር

" ከልዑላን ጋር አርፍ ነበር" በዚህ ሀረግ፣ "መተኛት" እና "ማረፍ" የሚሉት ቃላት በትሁት/በተሻለ አገላለጽ "ከዚያ ወዲያ በህይወት አለመኖር" የሚሉ ናቸው፡፡ (ዩፊሚዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚለውን ይመልከቱ)

በአንድ ወቅት ወርቅ የነበራቸው፣ ቤቶቻቸውንም በብር የሞሉ

ኢዮብ ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤን የተጠቀመው እየተናገረ የሚገኘውን ነገር ለማጉላት ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ወይም ምናልባት ብርሃን ፈጽሞ አይቶ እንደማያውቅ፣ ሞቶ የተወለደ ጭንጋፍ እሆን ነበር

ኢዮብ ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤን የተጠቀመው እየተናገረ የሚገኘውን ነገር ለማጉላት ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሞቼ በተወለድሁ

"በእናቴ ማህጸን ሳለሁ በሞትኩ"

ብርሃን ፈጽሞ እንዳላየ ጨቅላ

"እንዳልተወለዱ ህጻናት"

ጨቅላ ህጻናት

"ህጻናት" ወይም "በጣም ትንንሽ ልጆች"

Job 3:17-19

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ ንግግሩን ከሞት ወደ ከሞት በኋላ ያለ ህይወት ይለውጠዋል፡፡

በዚያ ክፉዎች ማስቸገር ያቆማሉ፤ በዚያ የደከሙ በዕረፍተ ላይ ይሆናሉ፡፡

ኢዮብ ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የተጠቀመው የተጨቆኑ ከመከራ እንደሚያርፉ አጉልቶ ለማሳየት ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በዚያ የክፉዎች ማወክ ያበቃል

ኢዮብ እየተናገረ የሚገኘው ሰዎች በምድር መኖር ካቆሙ በኋላ ስለሚሄዱበት ስፍራ ነው፡፡ "ክፉ ሰዎች ችግር ማድረሳቸው በሚያበቃበት በዚያ ስፍራ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የባሪያ አሳዳሪዎች/ገዢዎች ድምጽ

እዚህ ስፍራ "ድምጽ" የሚለው የባሪያ ጌቶች በባሪያዎቻቸው ላይ ያላቸውን ሀይል የሚገልጽ ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "ከእንግዲህ ወዲያ በባሪያ ገዢዎች ቁጥጥር ስር አይሆኑም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ታናናሾች እና ታላላቆች

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን "ሁሉም ሰው፣ ደሃውም ሆነ ባለጸጋው" የሚል ትርጉም አለው፡፡ (ጽንፍ የሚለውን ይመልከቱ)

አገልጋይ ከጌታው ነጻ ነው

ከዚያ በኋላ አንድ አገልጋይ ጌታውን ለማገልግል አይገደድም

Job 3:20-22

በመከራ ውስጥ የሚኖር ለምን ብርሃን ያያል? ነፍሱ የተመረረች ለምን ህይወት ይሰጠዋል?

ሁለቱ የኢዮብ ጥያቄዎች በመሰረቱ አንድ አይነት ናቸው፡፡ በመከራ ውስጥ የሚገኙ ለምን በህይወት እንደሚቀጥሉ ይገረማል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በመከራ ውስጥ የሚኖር ለምን ብርሃን ይሰጠዋል?

እዚህ ስፍራ ኢዮብ ሰዎች ለምን በህይወት ቆይተው እንደሚሰቃዩ በመገረም ይጠይቃል፡፡ "እግዚአብሔር ስለምን በመከራ ውስጥ ለሚኖረው ህይወት እንደሚሰጠው ሊገባኝ አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ብርሃን

እዚህ ስፍራ ብርሃን የሚወክለው ህይወትን ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የተደበቀ ሀብት….በነፍሱ ለተመረረ ለምን ህይወት ይሰጠዋል የተደበቀ ሀብት?

"እግዚአብሔር ለመከረኛው ሰው ለምን ህይወት ይሰጠዋል?" "እግዚአብሔር እጅግ ሀዘንተኛ ለሆነ ሰው ለምን ህይወት እንደሚሰጠው አይገባኝም… የተደበቀ ሀብት…" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ሞትን እየተመኘ ለማያገኘው ሰው

እዚህ ስፍራ ሞት የተገለጸው ወደ አንድ ሰው እየመጣ እንሚገኝ ቁስ ነው፡፡ "ለመኖር ለማይፈልግ ሰው፣ ነገር ግን አሁንም በህይወት ለሚገኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የከበረ ሀብትን በቁፋሮ ከሚፈልግ ሰው ይልቅ ሞትን ለሚፈልግ ሰው

ሞትን ተስፋ የሚያደርግ ሰው የተገለጸው የተቀበረ ውድ ሀብትን ለማግኘት እንደሚቆፍር ሰው ተደርጎ ነው፡፡ "የተደበቀ ውድ ሀብትን ከሚፈልግ ሰው ይልቅ መሞትን በብርቱ የሚፈልግ ሰው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡(ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

መቃብርን ሲያገኝ እጅግ ደስ ለሚሰኝ ለምን ብርሃን ይሰጠዋል

እዚህ ስፍራ ኢዮብ ጥያቄ የሚጠይቀው ዐረፍተ ነገር ለማበጀት ነው፡፡ "ሰውየው ሞቶ መቀበር እጅግ ደስ የሚያሰኘው ከሆነ እግዚአብሔር ለዚያ ሰው መኖርን ለምን እንደሚፈቅድ አይገባኝም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

በጣም ደስ የሚሰኝ እና ደስተኛ የሆነ

"በጣም ደስ የሚሰኝ" የሚለው ሀረግ "ደስተኛ የሆነ" ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ሁለቱ አገላለጾች በአንድነት ሆነው የደስተኝነትን መጠን ያጎላሉ፡፡ "እጅግ ደስ የተሰኘ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

መቃብርን ሲያገኝ

ይህ ሞትን ሻል ባለ መንገድ መግለጫ ነው፡፡ "በሚሞትበት እና ሊቀበር በሚችልበት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዩፊሚዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚለውን ይመልከቱ)

መቃብር

እዚህ ስፍራ መቃብር የሚወክለው ሞትን ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 3:23-24

መንገዱ ለተደበቀችበት እግዚአብሔር ላጠረበት ሰው፣ ለምን ብርሃን ተሰጠው?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው ዐረፍተ ነገር ለማበጀት ነው፡፡ "እግዚአብሔር ለሰው ህይወት ከሰጠው በኋላ የወደፊቱን ነጥቆ ሊያጥርበት አይገባም" በሚለው ወስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ለሰው ለምን ብርሃን ተሰጠው

እዚህ ስፍራ ብርሃን የሚወክለው ህይወትን ነው፡፡ "እግዚአብሔር ለምን አንድን ሰው በህይወት ያኖረዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

መንገዱ ለተደበቀችበት

እዚህ ስፍራ ኢዮብ አስቀድሞ ስለማያውቀው ስለ ወደፊቱ እግዚአብሔር እንደሰወረበት አድርጎ ይናገራል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር መንገዱን ያጠረበት

እዚህ ስፍራ በችግር ውስጥ መሆን እና አደጋዎች የተገለጹት በጠባብ ስፍራ እንደመወሰን ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ትካዜ ምግብ ሆኖኛል፣ የስቃይ ጩኸቴ/መቃተቴ እንደ ውሃ ይፈሳል

ኢዮብ ጭንቀቱን በሁለት መንገዶች ይገልጻል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ትካዜ ምግብ ሆኖኛል

"ከመመገብ ይልቅ፣ ሀዘንተኛ ሆኛለሁ"

የስቃይ ጩኸቴ/መቃተቴ እንደ ውሃ ይፈሳል

እንደ ሀዘን የመሰሉ የስነምግባር ባህሪያት እና ስሜቶች ብዙውን ጊዜ በውሃ ይገለጻሉ፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 3:25-26

የፈራኋቸው ነገሮች በላዬ መጡብኝ፣ የፈራሁት ደረሰብኝ

እነዚህ ሁለት ሀረጋት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ "በጣም ሰግቻለሁ" ወይም "እጅግ የፈራሁት ነገር ደረሰ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ተዘልዬ የተቀመጥኩ አይደለሁም፣ አላረፍኩም፣ ደግሞም እረፍት የለኝም

ኢዮብ ጭንቀቱን በሶስት የተለያዩ ሀረጋት ይገልጻል፡፡ "በጣም ሰግቻለሁ" ወይም "በስሜትም በአካልም ተሰቃይቻለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 4

Job 4:1-3

ኤልፋዝ

ኤልፋዝ የወንድ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ቴማናዊ

ቴማናዊ ከተምና ነገድ የሆነ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ትታገሳለህን?

ኤልፋዝ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው በዐረፍተ ነገር ሃሳቡን ለመግለጽ ነው፡፡ "በእርግጥ ልትታገስ ይገባል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ትታገሳለህን?

"ይህ ነገር ያስከፋሃልን?"

ነገር ግን ማን ከመናገር ራሱን ሊገታ ይችላል?

ኤልፋዝ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው የወዳጁን መጨነቅ እየተመለከተ ማንም ዝም ማለት አይችልም ለማለት ነው፡፡ "ወዳጁ አንተ በምትገኝበት ሁኔታ ሆኖ ማንም ከመናገር ራሱን መግታት አይችልም" ወይም "አንተ በጭንቀት ውስጥ ሆነህ እኔ ከመናገር ዝም ማለት አልችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ ብዙዎቹን አስተምረሃል፣ የላሉ እጆችን አጽንተሃል

ይህ ስንኝ አንድን ሃሳብ በሁለት የተለያዩ መንገዶች ይገልጻል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ የላሉ እጆችን አጽንተሃል

እዚህ ስፍራ "የላሉ/ደካማ እጆች" የሚለው የሚወክለው እርዳታ የሚፈልጉ ሰዎችን ነው፡፡ "ሌሎች እርዳታ በሚፈልጉ ጊዜ አንተ ረድተሃቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 4:4-6

አጠቃላይ መረጃ፡

ጸሐፊው ሁለት ሃሳቦችን በመጠቀም አንድ ሃሳብ ለመመስረት ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤን በእያንዳንዱ ሀረግ ውስጥ የሚጠቀመው 1) በቀደመው ጊዜ ኢዮብ ለሌሎች የሰጠውን ድጋፍ፣ 2) በአሁኑ ችግሩ ላይ ያሳደረውን ተጽዕኖ፣ እና 3) በእግዚአብሔር ፊት የእርሱን ንጽህና ለማጉላት ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ትደግፍ

የተበረታታ አንድ ሰው የተገለጸው ወደ ታች ከመውደቅ እንደተጠበቀ ተደርጎ ነው

መውደቅ

እዚህ ስፍራ ተስፋ መቁረጥ የተገለጸው ወደ ታች መውደቅ ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የተብረከረኩ ጉልበታችን ታጠነክር ነበር

እዚህ ስፍራ ተስፋ መቁረጥ የተገለጸው ደካማ ጉልበቱ ተሸክሞ ሊያቆመው እንዳልቻለ አንድ ሰው ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አሁን ግን መከራ ወደ አንተ መጥቷል

እዚህ ስፍራ መከራ የተገለጸው ወደ አንድ ሰው እንደሚመጣ ቁስ ተደርጎ ነው፡፡ "ነገር ግን አንተ አሁን ከውድቀት የተነሳ ትጨነቃለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ ዝለሃል

"አንተ ተስፋ ቆርጠሃል"

የምትፈራው

"አንተ እግዚአብሔርን ማክበርህ"

ፍርሃትህ ልበ ሙሉነትህ አይደለምን፣ ደግሞስ የመንገዶችህ ጽናት ተስፋህ አይደለምን?

ኤልፋዝ እነዚህን ጥያቄዎች የሚጠይቀው ኢዮብን የምትሰቃየው ከኃጢአትህ የተነሳ ነው ሊለው ፈልጎ ነው፡፡ "ሁሉም ሰው አንተ እግዚአብሔርን እንደምታከብር ያስባል፣ ሁሉም ሰው አንተ እውነተኛ ሰው እንደሆንክ ያስባል፡፡ እነዚህ ነገሮች ግን እውነት ሊሆኑ አይችሉም፣ ምክንያቱም አንተ እግአብሔርን ተስፋ ማድረግ አቁመሃ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ፍርሃትህ

ኤልፋዝ የኢዮብን እግዚአብን መፍራት ማለቱ ነው፡፡ "የአንተ እግዚአብሔርን መፍራት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

መንገዶችህ

እዚህ ስፍራ "መንገዶችህ" የሚለው የሚወክለው "ባህሪህ፣" "አደራረግህ፣" የሚለውን ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 4:7-9

ንጹህ ሆኖ ሳለ የጠፋ ማን ነው?

ኤልፋዝ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመው ኢዮብ ህይወቱን ከኃጢአት እንዲመረምር፣ የእግዚአብሔርን ጻድቅ ፈራጅነት እንደዚሁም ሁሉን ሊያጣ የቻለበትን ምክንያት አንዲ ሊያነሳሳው ነው፡፡ "ንጹህ ሆኖ ሳለ የጠፋ ማንም የለም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ትክክለኛ ሰዎች መች ተቆርጠው ጠፍተው ያውቃሉ?

ይህም ጥያቄ ሃሳብን ለማቅረብ የተሰነዘረ ነው፤ በአድራጊ ዐረፍት ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ትክክለኛ ሰው ሆኖ ሳለ ተቆርጦ የቀረ ሰው የለም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

ተቆርጦ የጠፋ

እዚህ ስፍራ ተቆርጦ መጥፋት የሚለው የሚገልጸው መደምሰስን ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እኩልነት ማጣትን ያርሳል… ችግርን ይዘራል… ያጭዳል

እዚህ ስፍራ የማረስ እና መዝራት ድርጊቶች የመወክሉት ለሌላው ሰው ለችግር ምክንያት መሆንን ነው፡፡ የማጨድ ድርጊት የሚወክለው አንድ ሰው ራሱ ባመጣው ችግር ምክንያት በመከራ መሰቃየትን ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በእግዚአብሔር እስትንፋስ ይጠፋሉ፣ በቁጣው መአት ይበላሉ

ጸሐፊው አንድን ሀሳብ ሁለት አይነት አገላለጽ በመጠቀም ያብራራል፡፡ ይህ በዕብራውያን ስነግጥም ትኩረት ለመስጠት፣ ሀሳብን ግልጽ ለማድረግ፣ ለማስተማር ወይም ለእነዚህ ለሶስቱም ጉዳዮች የሚውል ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔር እስትንፋስ

ይህ የእግዚአብሔርን ትዕዛዝ የመስጠት ድርጊት የሚወክል ሊሆን ይችላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የቁጣው መአት

ይህ አገላለጽ የሚጠቁመው አንዳንድ ጊዜ ሰው በጣም ሲቆጣ በአፍንጫው በከባዱ የሚተነፍሰውን አተነፋፈስ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የቁጣ… አተነፋፈስ

አንደኛው ቃል በሌላኛው ላይ ይመሰረታል፡፡ ውጤቱን ከፍ የሚያደርግ ትርጉሞችን በመጠቀም አንድን ነጥብ ይገልጻሉ፡፡ "ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ትንፋሽ ይሞታሉ፤ የቁጣው አውሎ ነፋስ ያጠፋቸዋል፡፡" (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ይጠፋሉ… ይበላሉ

ሁለተኛው ሀረግ በመጀመሪያው ላይ የተመሰረተ ነው፡፡ ሁለቱም ተመሳሳይ ነጥብን ይገልጻሉ፡፡ "ከእግዚአብሔር አፍ በሚወጣው ትንፋሽ ይሞታሉ፤ የቁጣው አውሎ ነፋስ ያጠፋቸዋል፡፡" (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ይበላሉ

እዚህ ስፍራ መፈጀት ወይም መበላት የሚለው የሚወክለው መገደልን ነው፡፡

Job 4:10-11

አጠቃላይ መረጃ፡

ጸሐፊው በእነዚህ ስንኞች ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤን የሚጠቀመው፣ በተለያየ አገላለጽ እግዚአብሔር ክፉ ሰዎችን የሚያጠፋ መሆኑን አጉልቶ ለማሳየት ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የአንበሳ ግሳት፣ የተቆጣ አንበሳ ድምጽ፣ የአንበሳው ጥርሶች ¬- ተሰብረዋል፡፡

እዚህ ስፍራ የአንበሳ ግሳት፣ ድምጹ፣ እና የጥርሱ መሰበር ክፉዎች እንደሚጠፉ መገለጫ ሆኖ አገልግሏል፡፡ ( ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ተሰብረዋል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "አንድ ነገር ሰብሯቸዋል" (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ያረጀ አንበሳ የሚያድነው በማጣቱ ይጠፋል፣ የአንበሳ ደቦሎች በየስፍራው ይበተናሉ

ኤልፋዝ ያረጀ አንበሳን በረሃብ መሞት እና የአንበሳ ቤተሰብ የመበተንን ዘይቤያዊ አገላለጾች የተጠቀመው ክፉዎች የሚጠፉ መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡

የአንበሳ ደቦሎች ተበተኑ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የአንበሳ ደቦሎችን አንድ ነገር በተናቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 4:12-13

አሁን አንድ ነገር በድብቅ ወደ እኔ መጥቷላ… ስለዚያም ነገር ጆሮዎቼ ሹክሹክታ ሰምተዋል

እነዚህ ሀረጋት አንድን ሀሳብ በተለያየ መንገድ ይገልጻሉ፡፡ ኤልፋዝ በሹክሹክታ መልእክት የመቀበሉን ሀሳብ ያስተላልፋሉ፡፡ የዚህ አይነቱ መደጋገም በዕብራውያን ሰነ ግጥም ውስጥ ትኩረት ለመስጠት፣ ለማስተማር ወይም ሃሳብን ግልጽ ለማድረግ አዘውትሮ በተግባር ላይ ይውላሉ፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሌት በራዕይ

"ህልም"

በሰዎች ላይ ከባድ እንቅልፍ ሲወድቅ

"ሰዎች ከባድ እንቅልፍ ሲተኙ"

Job 4:14-15

አጠቃላይ መረጃ፡

ጸሐፊው በእነዚህ ቁጥሮች የኤልፋዝን ስጋት ለማጉላት አንድን ሀሳብ የተለያዩ አገላለጾች በመጠቀም ለማስተላለፍ ንጽጽራዊ ዘይቤን ይጠቀማል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ፍርሃት እና መንቀጥቀጥ በላዬ መጡ

እዚህ ስፍራ ፍረሃት እና መንቀጥቀጥ የተገለጹት ወደ አንድ ሰው እንደሚመጡ ቁሶች ተደርገው ነው፡፡ "መፍራት እና መንቀጥቀጥ ጀመርኩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

የሰውነቴ ፀጉር ቆመ

ይህ ታላቅ ፍርሃትን ያመለክታል

የሰውነቴ ፀጉር

"በሰውነቴ ላይ የሚገኝ ፀጉር"

Job 4:16-17

አጠቃላይ መረጃ፡

ጸሐፊው በቁጥር 17 ላይ ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤን የተጠቀመው አንድን ሀሳብ በሁለት የተለያዩ አገላለጾች በእግዚአብሔር ፊት የሰውን ንጹህ አለመሆን ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አንድ ቅርጽ/መልክ በፊቴ ነበረ

"አንድ ነገር በዐይኔ ፊት ነበር፣" "አንድ ነገር ተመለከትኩ"

ደግሞም ሰማሁ

"ከዚያም ሰማሁ"

ሟች የሆነ የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ይልቅ ጻድቅ ይሆናልን?

ኤልፋዝ ይህንን ጥያቄ የሚያቀርበው ኢዮብ "ራሴን ከእግዚአብሔር ይልቅ ጻድቅ አድርጌ ቆጥሬያለሁን?" ብሎ እንዲጠይቅ ለማድረግ ወይም "ሟች የሆነ የሰው ልጅ ከእግዚአብሔር ይልቅ ጻድቅ ሊሆን አይችልም" እንዲል ለማድረግ ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ስርሱን ያበጀው

"የእርሱ ፈጣሪ"

Job 4:18-19

በሸክላ ቤት ውስጥ የሚኖሩ፣ መሰረታቸው አፈር የሆነ

ይህ ከምድር አፈር የተፈጠሩና አካላቸው እንደቤቶች የሆነ፣ ከሸክላ የተሰሩ መሰረታቸው ትቢያ የሆነ ሰዎችን በዘይቤያዊ መንገድ መግለጫ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ከብል ይልቅ ፈጥነው የሚጨፈለቁ

የዚህ ዘይቤያዊ አነጋገር ትረጉሞች ሊሆኑ የሚችሉት 1) "እግዚአብሔር ብልን ሊጨፈልቅ የሚችለውን ያህል በቀላሉ የሚያጠፋቸው" ወይም 2) "ዘመናቸው የብልን እድሜ ያህል አጭር የሆነ፡፡" (ዘይቤያዊ አገላለጽ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 4:20-21

አጠቃላይ መረጃ፡

እነዚህ ቁጥሮች ቀደም ሲል ያገለገሉት ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ ቀጣዮች ናቸው፣ እዚህ ስፍራ ሰዎች በድንገት ጥበብ ሳያገኙ እና ከሌሎችም ይሁንታ ሳይኖራቸው መሞታቸው በተለያየ መንገድ ትኩረት ተሰጥቶታል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በቀንና በምሽት መሃል ይጠፋሉ

ይህ የሚያመለክተው በፍጥነት የሚሆንን ነገር ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ ጠፍተዋል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እነርሱ ሞቱ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የድንኳኖቻቸው ማሰሪያዎች/ገመድ ከመሃላቸው አልተነቀለምን?

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ጠላቶቻቸው የድንኳኖቻቸውን ማሰሪያ ከመሃላቸው ስበው አልጣሉምን?" (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

የድንኳኖቻቸው ማሰሪያ/ገመድ

እዚህ ስፍራ የድንኳኖች ማሰሪያ የሚወክለው ድንኳኖችን ነው፡፡ አንዳንድ ጊዜ የአንድ ሰው ቤት እና ቤተሰብ እንደ ድንኳኑ ተደርጎ ይገለጻል፤ ይህ ሰውየው ያለውን ንብረት ሁሉ የሚወክል ሊሆንም ይችላል፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ እና ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 5

Job 5:1-3

ወዴትኛው ቅዱስ ፊትህን ትመልሳለህ?

ኤልፋዝ ይህንን ጥያቄ የሚያነሳው ኢዮብ ለእርዳታ ፊቱን ሊያቀና የሚችልበት ማንም እንደሌለ ለመግለጽ ነው፡፡ "ፊትህን ወደ እርሱ ልትመልስ የምትችለው ቅዱስ አለን?" ወይም "እርዳታ ፍለጋ ወደ እርሱ ፊትህን ልታቀና የምትችልበት አንዳችም ቅዱስ የለም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ቅዱስ የሆነ

ይህ መልአክንም ሆነ ሌላ መንፈሶች፣ አንድ እጅግ ሉዓላዊ የሚባልን ማንነት ያመለክታል፡፡

በቅናት እዚህ ግባ የማይባለውን/ሞኙን መግደል

"በሞኝነት እና በስሜት በመገፋፋት የሚያደርገውን ማናቸውንም በቅናት መግደል"

እዚህ ግባ የማይባል… ሞኝ ሰው

ይህ የሚያመለክተው ማናቸውንም የማይረባ ሰው እና ማናቸውንም ሞኝ ሰው ነው፡፡ (የስማዊ ሀረግ ክፍል የሚለውን ይመልከቱ)

ሞኝ ሰው በሞኝነቱ ስር ይሰዳል

እዚህ ስፍራ ሞኝ ሰው የተገለጸው እርሱ ራሱ ተክል እንደሆነ፣ ምናልባትም በጊዜ ውስጥ ይበልጥ ሞኝ እየሆነ እንደሚሄድ ነው፡፡ "ሞኝ ሰው በሞኝነት ስር እየሰደደ ይሄዳለል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ቤቱ

ይህ የሰውየውን ቤተሰብ እና ንብረቱን ሁሉ ያመለክታል

Job 5:4-5

አጠቃላይ መረጃ

ይህ ቁጥር ቀደም ሲል ያገለገለ ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ ቅጥያ ነው፣ እዚህ ስፍራ የሞኝ ሰው ልጆች በፍጹም ደህንተታቸው የተጠበቀ እንዳልሆነ በተለያዩ መንገዶች በትኩረት ተገልጽዋል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሱ ልጆች ደህንነትን/ጥበቃ ከማግኘት የራቁ ናቸው

"የእርሱ" የሚለው የሚያመለክተው በኢዮብ 5፡2 ላይ የሚገኘውን ሞኙን ሰው ወይም ሞኝ ሰዎችን ነው፡፡ "ልጆቻቸው ፈጽሞውን ደህንነታቸው የተጠበቀ አይደለም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ይፈጫሉ

እዚህ ስፍራ መፈጨት የሚለው የሚወክለው በፍትህ አደባባይ በጭቆና ስር መሆንን እና ጥቅምን መቀማትን ነው፡፡ ይህ ሀሳብ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አንድ ሰው ያደቅቃቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

የከተማ በር

የከተማ በር፣ ክርክሮች የሚፈቱበት እና ፍትህ የሚሰጥበት ስፍራ ሆኖ ያገለግል ነበር፡፡

የሚታደጋቸው ማንም የለም

"የሞኝ ሰዎችን ልጆች ከመከራቸው ለማውጣት ሊረዳቸው የሚችል ማንም የለም"

ሌላው ቀርቶ ከእሾህ መሃል ይህን ይወስዳሉ

ምናልባት ይህ የሚያመለክተው የእሾህ ተክል ከመኖሩ የተነሳ የከፋው ተክል የሚበቅልበትን ስፍራ ነው

ሃብታቸውን ተጠምቶ የሚፈልግ

እዚህ ስፍራ ስግብግብ ሰዎች የተገለጹት እንደ ተጠሙ ሲሆን፣ የሞኝ ሰው ሃብት ደግሞ እነርሱ ሊጠጡት እንደሚችሉት ነገር ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 5:6-7

ችግር ከአፈር ውስጥ አይወጣም፣ አሊያም መከራ ከምድር አይበቅልም

እዚህ ስፍራ ችግር እና መከራ የተገለጹት ተክል እንደሆኑ ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

የእሳት ፍንጣሪ ወደ ላይ እንደሚወጣው ሁሉ የሰው ልጅ የተወለደው ለመከራ ነው

ከእሳት ፍንጣሪው ወደላይ እንደሚወጣ ሁሉ ለሰው ልጆችም አንዴ ከተወለዱ በኋላ ችግር ማጋጠሙ ተፈጥሯዊ ነው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 5:8-10

አጠቃላይ መረጃ፡

በእነዚህ ቁጥሮች፣ ኤልፋዝ ንግግሩን ከኢዮብ 4፡1 ጀምሮ ይቀጥላል፡፡ ጸሐፊው ኢዮብ አስደናቂ ነገሮች የሚያደርገውን እግዚአብሔርን መለመን እንደሚገባው አጉልቶ ለማሳየት አንድን ሀሳብ ሁለት የተለያዩ አገላለጾች በመጠቀም ለማስተላለፍ በእያንዳንዱ ቁጥር ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ መጠቀሙን ይቀጥላል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ታላቅ እና የማይመረመሩ ነገሮች፣ ቁጥር የሌላቸው አስደናቂ ነገሮች

"ከመረዳት ባሻገር የሆኑ ታላላቅ ነገሮች፣ ሊቆጠሩ የማይችሉ አስደናቂ ነገሮች"

የማይመረመሩ ነገሮች

ይህ የሚያመለክተው የሰው ልጅ ሊረዳቸው የማይችሉ ነገሮችን ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ታላቅ እና የማይመረመሩ ነገሮች

እዚህ ስፍራ ጸሐፊው "እና" በሚል የተያያዙ ሁለት ራሳቸውን የቻሉ ቃላትን የሚጠቀመው የእግዚአብሔርን ስራ ታላቅነት ለማጉላት ነው፡፡ "በታላቅነት ጥልቅ/መሰረታዊ የሆኑ ነገሮች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሄንዲየዲስ/ሁለት ቃላት ‘እና' በሚል አያያዥ ቃል የሚገኛኙበትና አንድን ጥልቅ ሀሳብ ለመግለጽ የሚያገለግል ዘይቤያዊ አነጋገር)

አስደናቂ ነገሮች

"አስገራሚ ነገሮች" ወይም "አስደናቂ ነገሮች"

Job 5:11-13

አጠቃላይ መረጃ፡

ጸሐፊው በእያንዳንዱ ቁጥር ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤን አንድን ሀሳብ ሁለት የተለያዩ መግለጫዎችን በመጠቀም የሚያስተላልፈው እግዚአብሔር የተጠቁትን ከወደቁበት እንደሚየነሳ እና ተንኮለኞችን እንደሚያወርድ ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ይህንን የሚያደርገው ዝቅ ባለ ስፍራ ያሉትን ከፍ ለማድረግ ነው

የትሁታን መጎዳት የተገለጸው በዝቅተኛ ስፍራ እንደ ተቀመጡ ተደርጎ ነው፡፡ እግዚአብሔር በሚታደጋቸው ጊዜ፣ ክብርን ይቀበላሉ፡፡ ይህ በሚሆንበት ጊዜ ከፍ ተደርገው በከበረ ስፍራ እንደተቀጡ ተደርጎ ይነገርላቸዋል፡፡ "እግዚአብሔር ይሰቃዩ የነበሩ ትሁታንን ለማዳን እና እነርሱን ለማክበር ይህንን ያደርጋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

እቅዳቸውን ይሰብራል

እዚህ ስፍራ የተንኮለኞችን እቅድ ማስቆም የተገለጸው እነርሱ በአካል እንክት ተደርገው እንደሚሰበሩ ነገሮች ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ተንኮለኛ ሰዎችን በራሳቸው ክፉ ስራ ያጠምዳቸዋል

እዚህ ስፍራ ተንኮለኞችን በራሳቸው ክፉ ስራ እንዲጨነቁ ማድረግ የተገለጸው እነርሱን በወጥመድ እንመያዝ ተደርጎ ነው፡፡ የራሳቸው ድርጊቶች የተነገሩት እነዚያ ወጥመዶች እንደሆኑ ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ጠመዝማዛ ሰዎች

እዚህ ስፍራ በብልጣብልጥነት የሚደረግ ክፋት የተገለጸው ጠመዝማዛ መሆን ተደርጎ ነው፡፡ "ብልጣብልጥ የሆኑ" ወይም "ቅን ያለሆኑ" ወይም "ብልጦች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 5:14-16

አጠቃላይ መረጃ፡

ጸሐፊው በእያንዳንዱ ቁጥር ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤን አንድን ሀሳብ ሁለት የተለያዩ መግለጫዎችን በመጠቀም የሚያስተላልፈው እግዚአብሔር ክፉ ሰዎችን እንሚያዋርድ እና ድሆችን እንደሚያድን ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በቀን ብርሃን ጨለማ ይገጥማቸዋል

እዚህ ስፍራ ለእግዚአብሔር የማይመቹ ክፉዎች እና ጨካኝ ሰዎች ፀሐይ በአናት ትክክል ሳለች፣ በቀን ብርሃን እነርሱ ግን በጨለማ ውስጥ እንደሚገኙ ይናገራል፡፡ ማድረግ የሚፈልጉትን አንዳች ነገር ማድረግ አይችሉም፣ ምክንያቱም ማየት አይችሉም፡፡ "ተንኮለኞች፣ በእኩለ ቀን እንኳን በጨለማ ውስጥ ናቸው" (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ዳበሳ

እንደ ዐይነ ስውር ዙሪያን መዳሰስ

እኩለ ቀን

የቀኑ እኩሌታ፣ ፀሐይ በአናት ትክክል የምትሆንበትና ከፍተኛ ብርሃኗን የምትሰጥበት ጊዜ

እርሱ ግን ደሃውን ከአንደበታቸው ካለ ሰይፍ ያድነዋል

እዚህ ስፍራ ሰዎች የሚናገሯቸው ስድቦች እና ማስፈራሪያዎች በአንደበታቸው ለይ የሚገኝ ሰይፍ እንደሆነ ተደርጎ ተገልጽዋል፡፡ "እርሱ ግን ደሃውን ከታላላቆች ማስፈራራት ያድነዋል" ወይም "እርሱ ግን ደሃውን ታላላቆች ሲያስፈራሩት ወይም ሰድቡት ይታደገዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ፍትህ አልባነት አንደበቷን ትዘጋለች

ፍትህ አልባ ሰዎች የተገለጹት መናገርን ማቆም ያለባቸው ተደርገው እና ራሱን ፍትህ አልባነትን ሆነው ነው፡፡ "ይህ ፍትህ አልባነት የራሷን አንደበት እንደምትዘጋ ያህል ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 5:17-19

አጠቃላይ መረጃ፡

ጸሐፊው በቁጥር 18 እና 19 ላይ ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤን አንድን ሀሳብ ሁለት የተለያዩ መግለጫዎችን በመጠቀም የሚያስተላልፈው የእግዚአብሔርን ቅጣት እና ፈውስ ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ያስተካክላል… ሁሉን ቻይ የሆነው ይቀጣል

እዚህ ስፍራ እግዚአብሔር የቀረበው እንደሚያርም ወላጅ ወይም ልጅን እንደሚመራ ወላጅ ሆኖ ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚያርመው ሰው የተባረከ ነው "እግዚአብሔር እርሱ የሚያርመውን ሰው በእርግጥም ተቀብሎታል"

አታቃል

"አትቃወም" ወይም "ጥቅም እንደሌለው ነገር አድርገህ አትቁጠር"

መቅጣት

"መምራት" ወይም "ማረም" ወይም "ስርአት ማስያዝ"

እርሱ ያቆስላል እርሱ ይጠግናል፣ እርሱ ያቆስላል ደግሞም የእርሱ እዶች ይፈውሳሉ

"እርሱ ቢያቆስልም እርሱ ይጠግናል፣ እርሱ ያደቃል የእርሱ እጆች ይፈውሳሉ"

እጆቹ ይፈውሳሉ

እዚህ ስፍራ "የእርሱ እጆች" የሚለው የሚገልጸው እግዚአብሔርን ነው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ከስድስት ችግሮች ያድንሃል፤ በእርግጥ በሰባተኛው ችግር የትኛውም ክፉ አያገኝህም

ቁጥሮችን ከፍ እያደረጉ "ስድሰት" እና "ሰባት" እንደሚለው መጠቀም ብዙ ብዙ ጊዜ የሚለውን ሀሳብ ይወክላል፡፡ "እርሱ ደግሞ ደጋግሞ ከችግር ያወጣሃል፣ በእርግጥ፣ ከጊዜ ጊዜ አንዳች ክፉ አይነካህም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 5:20-22

አጠቃላይ መረጃ፡

በኢዮብ 5፡19 የሚጀምረው "እርሱ" ከሚለው "አንተ" ወደሚለው የተዋላጠ ስም/የስም ምትክ ሽግግር ማድረግ እሰከ ኢዮብ 5፡29 ማለትም የኤልፋዝ ንግግር እስከሚያልቅበት ድረስ ይቀጥላል፡፡ በረሃብ ጊዜ ይቤዥሃል እዚህ ስፍራ ማዳን የተገለጸው መቤዤት፣ መልሶ መግዛት እንደሆነ ተደርጎ ነው፡፡ "በርሃብ ጊዜ እግዚአብሔር ከአደጋ ያድንሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

የሰይፍ እጆች

እዚህ ስፍራ "እጆች" ምናልባት የሚወክለው ሰይፎችን ጨምሮ በመሳሪያ ጥቃት የሚያደርሱ ሰዎችን ሊሆን ይችላል፡፡ "ጥቃት የሚያደርሱ ሰዎች" ወይም "አንተን የሚያጠቁ ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ከጥፋት

እዚህ ስፍራ "ጥፋት" የሚለው የሚያመለክተው በጠላት መደምሰስን ነው፡፡ "ያገኘህ ማንኛውም ጠላት ያጠፋሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

በጥፋት እና ረሃብ ላይ ትስቃለህ

እዚህ ስፍራ "ሳቅ" የሚለው የሚገልጸው አለመፍራትን ነው፡፡ "ማናቸውንም የጥፋት አደጋ ወይም ረሃብ አትፈራም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ምልክታዊ/ትዕምርታዊ ቋንቋ የሚለውን ይመልከቱ)

የምድር አራዊት

ይህ የሚያመለክተው የዱር አራዊት ነው፡፡"የዱር እንስሳት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 5:23-25

አጠቃላይ መረጃ፡

ጸሐፊው በእያንዳንዱ ቁጥር ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤን አንድን ሀሳብ ሁለት የተለያዩ መግለጫዎችን በመጠቀም ማቅረቡን የሚቀጥለው ደህንነትን ከተፈጥሮ ዓለም፣ ከቤት እና ከአንድ ሰው ትውልዶች ጋር በማያያዝ ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በማሳህ ከሚገኙ ድንጋዮች ጋር ትዋዋላለህ

እዚህ ስፍራ በገበሬ ማሳ ውስጥ የሚገኙ ድንጋዮች የተገለጹት አንድ ሰው አብሯቸው የሚዋዋላቸው ሰዎች ተደርገው ነው፡፡ "በእርሻህ ውስጥ የሚገኙ ድንጋዮች በአንተ ላይ አንዳችም ችግር ላያመጡ ቃል እንደገቡ ሰዎች ይሆናሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

የዱር አራዊት

ይህ አደገኛ የዱር አራዊትን ያመለክታል፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ድንኳንህ በሰላም እንዳለ ታውቃለህ

እዚህ ስፍራ "ድንኳን" የሚወክለው የአንድን ሰው ቤተሰብ፣ ቤቱን፣ እና ያለውን ሀብት ሁሉ ነው፡፡ "ቤተሰብህ፣ አገልጋዮችህ፣ እና ያለህ ሁሉ በሰላም መጠበቁን ታውቃለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

በረትህን ስትቃኝ አንዳች አይጎድልም

"ምሽት በረትህን ስትመለከት፣ መንጋህን በሙሉ በዚያ ታገኛለህ"

ዘርህ ታላቅ ይሆናል

እዚህ ስፍራ "ዘር" የሚለው የሚወክለው የአንድን ሰው ትውልዶች ነው፡፡ "ዘርህ ብዙ ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ትውልድህ በምድር ላይ እንዳለ ሳር ይሆናል

እዚህ ስፍራ "ትውልድ" የሚለው የተገለጸው ታጭዶ እንደተከመረ ሳር ብዙ ተደርጎ ነው፤ ምናልባትም በብዙ እንዳደገ ሳር ተደርጎ ተገልጽዋል፡፡ "ትውልድህ እንደ ሚያድግ ሳር ብዙ ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 5:26-27

እድሜ ጠግበህ ወደ መቃብር ትመጣለህ

"እጅግ አርጅተህ ትሞታለህ"

በጊዜው እንደሚሰበሰብ የእህል ነዶ

በዚህ ተነጻጻሪ ዘይቤ ሰብል የሚለው በሚገባ ደርሶ መታጨዱን ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ በእርጅና እድሜው ሲሞት በጣም ደካማ አይሆንም ወይም ደግሞ ያለ ጊዜውም እንደማይሞት፡፡ (ቅጽ 1 የትርጉም ማብራሪያ) እና (ቅጽ 1 የተነጻጻሪ ዘይቤ ትርጉም የሚሉትን ይመልከቱ)

እነሆ፣ ይህንን ጉዳይ እኛ መርምረነዋል፤ ነገሩ ይህን ይመስላል፣ አድምጥ መርምረህ ድረስበት

"እኛ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የኢዮብን ወዳጆች እንጂ ኢዮብን አይደለም፡፡ "እነሆ፣ እኛ ስለዚህ ጉዳይ አስበንበታል፡፡ የምነግርህን አድምጥና ነገሩ እወነት መሆኑን ተረዳ" (የሚያጠቃልል እና የማያጠቃልል "እኛ" የሚለውን ይመልከቱ)

Job 6

Job 6:1-3

ምነው ጭንቀቴ ቢመዘን፣ ስጋቴ በሚዛን ላይ ቢቀመጥ

እዚህ ስፍራ ጸሐፊው አንድ ሃሳብን፣ ይኸውም የኢዮብን መከራ ሸክም ለመግለጽ ሁለት የተለያዩ አገላለጾችን ይጠቀማል፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "መከራዬን መመዘን ብችል፣ ደግሞም ስጋቴን ሁሉ በሚዛን ላይ ባስቀምጥ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

በሚዛን ላይ

"በመለኪያ ላይ"

ከባህር አሸዋ የከበደ ይሆናል

ኢዮብ የመከራውን ክብደት ከአሸዋ ክብደት ጋር ያነጻጽራል፤ ሁለቱም አንድን ሰው ማድቀቅ የሚችሉ ናቸው፡፡ "ጭንቀቴ እና ስጋቴ በባህር ዳር ካለ አሸዋ ይከብዳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ንግግሬ የማያስገርሙ ነበሩ

"በግዴለሽነት ተናገርኩ" ወይም "በችኮላ ተናገርኩ"

Job 6:4-6

አጠቃላይ መረጃ፡

ጸሐፊው በእያንዳንዱ ቁጥር አንድን ሃሳብ ለማስተላለፍ ሁለት የተለያዩ አገላለጾችን በመጠቀም የኢዮብን ከባድ መከራ ለማማረሩ መነሻ ምክንያት አድርጎ ለማጉላት ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤን መጠቀሙን ይቀጥላል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ ቀስቶች በእኔ ስጋ ውሰጥ ናቸው

ይህ የኢዮብን መከራ የሚገልጽ ዘይቤ ነው፡፡ ብዙ መከራውን እግዚአብሔር በቀስቱ ገላውን እንደ ወጋበት ቀስት አድርጎ ያነጻጽረዋል፡፡ "መከራዬ ሁሉን ቻይ የሆነው ቀስቶችን ወደ አካሌ እንደወረወረ ያህል ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ነፍሴ መርዝ ተጎነጨች

"ነፍሴ የቀስቱን መርዝ ጠጣች፡፡" ይህ መርዝ ያለባቸው መሆኑን በማመልከት እና ኢዮብ በመንፈሱ ስቃዩ የተሰማው መሆኑን በመግለጽ በቀስቱ የተነገረውን ዘይቤ ይቀጥላል፡፡ መከራውን ሲናገር መንፈሱ መርዝ እንደጠጣ አድርጎ ይገልጻል፡፡ "በውስጠኛው ሰውነቴ የመርዛቸው ስቃይ ይሰማኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔር አስጨናቂነት በእኔ ላይ በተራ ተሰልፎብኛል

እግዚአብሔር ብዙ ነገሮች ኢዮብን እንዲያስጨንቅ ማድረጉ የተገለጸው፤ የእግዚአብሔር ማሰጨነቅ ኢዮብን ለማጥቃት እንደ ተሰለፉ ወታደሮች ተደርጎ ነው፡፡ "በሰራዊት ውስጥ እንደሚገኝ ወታደር የእግዚአብሔር ማስጨነቅ ራሱን አሰልፎብኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

የሜዳ አህያ ሳር እያለው ያናፋል ወይስ በሬ ድርቆሽ እያለው እምቧ ይላል?

ኢዮብ ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚያቀርበው ለማመረር ምክንያት እንዳለው ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በገለጻ መልክ ሊቀርብ ይችላል፡፡ "የሜዳ አህያ ሳር እያለው ካለ ምክንያት እንደማያናፋ ወይም በሬ ድርቆሽ/ገለባ እያገኘ በረሃብ እምቧ እንደማይል እኔም ምክንያት ባይኖረኝ ኖሮ ባላጉረመረምኩ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ማናፋት

አህያ የሚያሰማው ድምጽ

እምቧ ማለት

በሬ የሚያሰማው ድምጽ

ድርቆሽ/ገለባ

የእንስሳ ምግብ

ጣዕም የሌለው ካለ ጨው ሊበላ ይችላልን? ወይስ የእንቁላል ውሃ ይጣፍጣልን?

ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ኢዮብ ባለበት ሁኔታ ደስ አለመሰኘቱን የሚያነጻጽረው ሰዎች ጣዕም የሌለውን ምግብ ካለመውደዳቸው ጋር ነው ወይም 2) ኢዮብ በወዳጆቹ ምክር ደስ አለመሰኘቱን የሚያነጻጽረው ሰዎች ደስ የማያሰኝን ምግብ ካለመውደዳቸው ጋር ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አገላለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ጣዕም የሌለው ካለ ጨው ሊበላ ይችላልን? ወይስ የእንቁላል ውሃ ይጣፍጣልን?

ኢዮብ ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚጠቀመው የራሱን ደስ አለመሰኘት ለማጉላት ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በገለጻ መልክ ሊቀርብ ይችላል፡፡ "በእንቁላል ውሃ ውሰጥ ጣዕም እንደሌለ፣ ጣዕም የሌለው ምግብ ካለ ጨው ሊበላ አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ጣዕም የሌለው ሊበላ ይችላልን?

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ጣዕም የሌለውን መብላት ትችላለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 6:7-9

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ ስለ መከራው መናገሩን እና መሞት መፈለጉን በገለጸ መጠን በእነዚህ ቁጥሮች ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤን መጠቀሙን ይቀጥላል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱን መንካት አልፈልግም

"እነርሱ" የሚለው የሚያመለክተው መጥፎ ጣዕም ያላቸውን ምግቦች ነው፡፡

እኔን ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ለማድቀቅ

ይህ ማለት እግዚአብሔር እርሱ/ኢዮብ እንዲሞት ቢፈቅድ ማለቱ ነው፡፡ "ቢያደቀኝ እና እንድሞት ቢተወኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዩፊሚዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚለውን ይመልከቱ)

ምነው ፈጥኖ እጆቹን ቢያነሳ እና ከዚህ ህይወት ቢቆርጠኝ

"ፈጥኖ እጆቹን ቢያነሳ" የሚለው ሀረግ ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን በፍጥነት ማድረግን ይገልጻል፡፡ እንደዚሁም፣ "ከዚህ ህይወት ቢቆርጠኝ" የሚለው ሀረግ መግደል ለሚለው ዩፊሚዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት/ ነው፡፡ "ምነው ፈጥኖ ህይወቴን በአጭር ቢቆርጠው" ወይም "ፈጥኖ መጨረሳዬን ቢያደርገው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ዩፊሚዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት እና የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 6:10-11

ይህ እንኳን መጽናናት በሆነኝ ነበር

"ይህ መጽናናት ያምጣልኝ፡፡" "ይህ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው እግዚአብሔር እርሱ/ኢዮብ እንዲሞት መፍቀድን ነው፡፡ "ሞቴ መጽናናት በሆነኝ" ወይም "መሞቴ ያጽናናኝ" (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በመከራዬ ብፈነድቅ እንኳን ይህም ጭምር ስቃዬን አይቀንሰውም

"ማብቂያ በሌለው ስቃይ ደስታን ላገኝ እቸኩላለሁ" ወይም "የማይጠፋ መከራ በጽናት እታገሳለሁ"

መፈንደቅ

"መደሰት"

አይቀንስም

"አይጠፋም"

የቅዱሱን ትዕዛዝ አልተላለፍኩም

"እግዚአብሔርን አልካድኩምና፡፡" ይህ በአዎንታዊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ሁልጊዜም ቅዱሱን ታዝዣለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

እታገስ ዘንድ ብርታቴ ምንድን ነው? ህይወቴ ይረዝም ዘንድ መጨረሻዬ ምንድን ነው?/ህይወቴ ስለ ምን ይቀጥላል?

ኢዮብ እነዚህን ጥያቄዎች የሚያነሳው መኖርን እንዲቀጥል የሚያደርግ ምንም ምክንያት እንደሌለው ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች ሁሉም ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ በገለጻ መልክ ሊጻፉ ይችላሉ፡፡ "በህይወት ለመቀጠል በቂ ጥንካሬ የለኝም፤ ህይወቴ የሚቀጥልበት ምንም ምክንያት የለም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 6:12-13

አጠቃላይ መረጃ፡

ጸሐፊው በእነዚህ በእያንዳንዳቸው ቁጥሮች ትይዩ ንጽጽራዊ ጥያቄዎችን የተጠቀመው ኢዮብ መከራውን ለመቋቋም አቅም ማጣቱን ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ብርታቴ የድንጋይ ጥንካሬ ነውን? ወይንስ ስጋዬ የተሰራው ከነሀስ ነው?

ኢዮብ የሰውነቱን ደካማነት ለማጉላት እንደ አለት እና ነሀስ ጠንካራ አይደለሁም በማለት ይገልጻል፡፡ እነዚህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄዎች በገለጻ መልክ ሊቀርቡ ይችላሉ፡፡ "እንደ አለት ጠንካራ አይደለሁም፡፡ ስጋዬ እንደ ብረት ጠንካራ አይደለም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ…. በውስጤ እርዳታ የሚሆነኝ አለመኖሩ እውነት አይደለምን?

ኢዮብ ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚጠቀመው እውቀት እንዳጣ እና ደካምነቱን አጉልቶ ለማሳየት ነው፡፡ እንደዚሁም ደግሞ፣ "በውስጤ እርዳታ የሚሆነኝ የለም" የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ " እኔ…የቀረ አቅም የሌለኝ መሆኑ እውነት ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ጥበብ ከውስጤ ተሟጦ ወጥቷል

"ስኬቴ ከእኔ ተወስዷል፡፡" ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ጥበቤ ከእኔ ርቋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 6:14-17

እያበቃለት/እየደከመ ላለ ሰው፣ ወዳጆቹ ታማኝነትን ሊያሳዩት ይገባል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አበቃልኝ/ደከምኩ ላለ ሰው ወዳጁ ታማኝ ሊሆንለት ይገባል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

እየደከመ ያለ ማን ነው

ይህ የሚናገረው፣ በአካል እየደከመ የመጣ ስለሚመስል፣ ተስፋ ስለ ቆረጠ እና በችግሩ ስለተዋጥ ሰው ነው፡፡ "ተስፋ የቆረጠ ማን ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሁሉን ቻይ የሆነውን ፍርሃት ለሚፈልግ እንኳን

"ሁሉን ቻይ የሆነውን አምላክ መፍራት ቢያቆም እንኳን፡፡" ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) የደከመ/ያበቃለት ሰው እግዚአብሔርን አይፈራም ወይም 2) የእርሱ ወዳጆች እግዚአብሔርን አይፈሩም

ወንድሞቼ ለእኔ የነበራቸው ታማኝነት እንደ በረሃ ጅረት ነበር

ኢዮብ ወዳጆቹ ለእርሱ ታማኝ አለመሆናቸውን የሚገልጸው በድንገት እንደሚደርቅ "በክረመት እንደሚሞላ ደረቅ ወንዝ" ነው፡፡ እንደዚሁም ኢዮብ እዚህ ስፍራ ወዳጆቹን በምጽት "ወንድሞች" እያለ ይገልጻቸዋል፡፡ "ወዳጆቼ ለእኔ ታማኝ አይደሉም፡፡ እነርሱ እንደ በረሃ ጅረት ናቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻታሪ ዘይቤ እና ምጸት የሚሉትን ይመልከቱ)

ወዴትም እንደማይደርስ የውሃ ቦይ

"እንደሚደርቅ ጅረት ውሃ፡፡" ኢዮብ ስለ ወዳጆቹ እንደ ሚደርቅ ወራጅ ሊታመኑባቸው የማይቻል መሆኑን መናገሩን ይቀጥላል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ደግሞም ራሱን በውስጣቸው ከሚደበቀው በረዶ የተነሳ…በላያቸው ካለው በረዶ የተነሳ የሚጠቁሩ/የሚደፈርሱ

እነዚህ ሁለት ሀረጋት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ወራጁ ውሃ/ትንሽ ወምዝ በክረምት እንዴት በበረዶ እንደተሞላ ይገልጻሉ፡፡ "በክረምት በበረዶ በመሸፈናቸው ጠቁረው/ደፍርሰው ይታያሉ፤ ደግሞም በቀለጠው በረዶ/አመዳይ ይሞላሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

ከበረዶው የተነሳ ራሱን በእነርሱ ውስጥ የሚደብቅ

ይህ የሚናገረው በረዶው እየቀለጠ ራሱን በወራጁ እንደሚደብቅ ውሃው ወደ ወንዙ እንደሚሄድ ነው፡፡ "ምክንያቱም በረዶው እየቀለጠ ወደ እነርሱ ይሄዳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አየሩ ሲሞቅ/በጋ ሲመጣ፣ ይጠፋሉ… ሞቃት ሲሆን ከስፍራቸው ይቀልጣሉ

እነዚህ ሁለት ሀረጋት ተመሳሰይ ትርጉም አላቸው፡፡ በበጋ/በሞቃቱ ወቅት ወራጁ ወንዝ እንዴት እንደሚደርቅ ይገልጻሉ፡፡ "በጋ ሲመጣ፣ በረዶ ይቀልጣል ወራጁም ወንዝ ይደርቃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 6:18-20

አያያዥ ሀሳብ

ኢዮብ ወዳጆቹ እንደሚደርቅ ወራጅ ውሃ ሊታመኑባቸው የማይቻል መሆኑን መግለጹን ይቀጥላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሲራራ/ተጓዥ ነጋዴዎች ውሃ ፍለጋ መንገዳቸውን ይቀይራሉ

"ሲራራ ነጋዴዎች መንገዳቸውን የሚቀይሩት ውሃ ፍለጋ ነው" ወይም "ሲራራ ነጋዴዎች ውሃ ለማግኘት የሚጓዙበትን መንገድ ይቀይራሉ"

ሲራራ ነጋዴዎች

በረሃ አቋርጠው ግመል እየነዱ በርካታ የሆኑ ተጓዦች ናቸው

በረሃ

"ጠፍ መሬት" ወይም "ምንም የሌለበት መሬት"

ቴማን..ሳባ

እነዚህ የቦታ ስሞች ናቸው፡፡ የእነዚህ ስፍራዎች ሰዎች በሌላ አገር ከሚኖሩ ሰዎች ጋር ነገሮችን ለመነገድ ቅፍለት/ብዙ ግመሎች ይጠቀማሉ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

የሳባ መንገደኞች

"ከሳባ የሚመጡ መንገደኞች"

በእነርሱ ተስፋ ያደረጉ

"በእነርሱ ላይ ተስፋ ያደረጉ" ወይም "ተስፋቸውን በእነርሱ ላይ የጣሉ"

ነገር ግን ተታለው ነበር

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ነገር ግን እነርሱ ተስፋ ቆርጠው ነበር" ወይም "ነገር ግን እነርሱ አልረኩም ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 6:21-23

አጠቃላይ መረጃ፡

በእነዚህ ቁጥሮች ኢዮብ ወዳጆቹን ለመገሰጽ እና ከእነርሱ አንዳች እርዳታ አለመጠየቁን ለማጉላት አራት ጥያቄዎችን ያነሳል፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

አሁንም

ኢዮብ ይህንን ሀረግ የሚጠቀመው እየተናገረ የሚገኘውን ነገር ዋና ክፍል ለመጀመር ነው

እናንተ ወዳጆቼ ለእኔ አንዳች አላደረጋችሁም

"የእናንተ ወዳጅነት ለእኔን ምንም አልባኝም"

ፈርታችኋል

ይህ ማለት ኢዮብ ያለበትን ችግር አይተዋል፤ እናም በተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ እንዳይገቡ ፈርተዋል፡፡ "እግዚአብሔር ተመሳሳይ ነገር ያደርስብናል ብላችሁ ፈርታችኋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እናንተን ‘አንዳች ነገር አድርጉልንኝ ብያችኋለሁ?' ወይስ፣ ‘ከሀብታችሁ ስጦታ ስጡኝ ብያችኋለሁ?' ወይስ፣ ‘ከጠላቴ እጅ አድኑኝ ብያችኋለሁ?' ወይስ ‘ከጨቆነኝ እጅ ተቤዡኝ ብያችኋለሁ?'

ኢዮብ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የተጠቀመው እርሱን ወዳዶቹ አንድም ነገር እንዲሰጡት ወይም እንዲያደርጉለት አለመጠየቁን ለማጉላት ነው፡፡ "ገንዘብ ወይም ስጦታ እንድትሰጡን ጠየቅኳችሁን፡፡ ወይንስ ከጠላቶቼ ወይም ከጨቋኞቼ እንድታድኑኝ ጠይቄያችኋለሁ፡፡በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ከጠላቶቼ እጅ እንድኑኝ…ከጨቋኞቼ እጅ ተቤዡኝ

እነዚህ ሁለቱም አገላለጾች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ እንደዚሁም፣ እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚወክለው ሃይልን ወይም መቆጣጠርን ነው፡፡ "ከጠላቶቼ ወይም ከጨቋኞቼ አድኑኝ" ወይም "ከባላኝጣዎቼ አድኑኝ" በሚው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ዘይቤያዊ አና ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

ተቤዡኝ

"አድኑኝ"

Job 6:24-25

አስተምሩኝ…አድርጉልኝ

እዚህ ስፍራ "አስተማረ" እና "አደረገ" የሚሉት ግሶች የተጻፉት በሁለተኛ መበድ ብዙ ቁጥር ሲሆን የሚገልጹትም የእርሱን/ኢዮብ መዳጆች ነው፡፡ (አንተ የሚለው ተውላጠ ስም ልዩ ልዩ መለኮች የሚለውን ይመልከቱ)

ሰላሜን እይዛለሁ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "ዝም እላለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የእውነት ቃላት ምን ያህል ይከብዳሉ! የእናንተ ንግግር ግን እንዴት አድርጎ በእርግጥ እኔን ሊቃወም/ሊወቅስ ይችላል?

የመገኛ ቋንቋው/ዋናው ቋንቋ ትክክለኛ ትርጉም በእርግጠኝነት አይታወቅም፡፡ አንዳንድ ቅጂዎች "እንዴት ያስጨንቃሉ" ብለው የሚተረጉሙት "እንዴት ደስ ያሰኛሉ" እንደማለት ነው፡፡ "አንድ ሰው እውነቱን ሲፈልግ፣ ይህ ማንንም አይጎዳም፡፡ የእናንተ ክርክር ግን ዕውነት አይደለም ስለዚህም እንዴት አድርጎ እኔን ሊገስጸኝ ይችላል?" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ነገር ግን የእናንተ ክርክር፣ በእርግጥ እንዴት እኔን ሊገስጸኝ ይችላል?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው ወዳዶቹን ለመገሰጽ እና እነርሱ የሚናገሩት ነገር በእርሱ ላይ እንደማይሰራ/ትክክለኛ እንዳልሆነ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በገለጻ መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እናንተ እኔን ለመገሰጽ በምታቀርቧቸው ምክንያቶች ምንም እንኳን በጥብቅ ልታርሙኝ ብትሞክሩም በእኔ ላይ ግን አይሰሩም/እውነትነት የላቸውም፡፡" ወይም "በእኔ ላይ የምታቀርቡት ክርክር ዕውነት አይደለም፣ ስለዚህም ነገራችሁ በእርግጥ ሊገስጸኝ አይችልም!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

የእናንተ ክርክር

"የምታቀርቧቸው ምክንያቶች" ወይም "እናንተ ነው የምትሉት"

Job 6:26-27

ቃሌን ቸል ልትሉ ታስባላችሁ፣ ተስፋ የቆረጠውን ሰው ቃል እንደ ነፋስ ታዩታላችሁን/ትቆጥራላችሁን?

ኢዮብ ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የተጠቀመው ወዳጆቹን ለመገሰጽ ነው፡፡ የእርሱን ቃላት ከነፋስ ጋር የሚያነጻጽረው፣ የወዳጆቹን ድርጊት እንደ እርሱ ቃላት ባዶ እና ረብ የሌላቸው መሆኑን ለማብራራት ነው፡፡ "እናንተ ቃሌን ቸል ብላችኋል! እኔ ተስፋ የቆረጥኩ ሰው ነኝ፣ እናንተ ደግሞ ቃሎቼን እንደ ነፋስ እርባና ቢስ አድርጋችሁ ታያላችሁ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

እናንተ

"እናንተ" ሁለተኛ መደብ ብዙ ቁጥር ነው፡፡ (አንተ የሚለው ተውላጠ ስም ልዩ ልዩ መለኮች የሚለውን ይመልከቱ)

አባት በሌላቸው ልጆች ላይ ዕጣ ትጣጣላላችሁ

"ወላጅ አልባን ለማሸነፍ ቁማር እንኳን ትጫወታላችሁ"

እጣ ትጥላላችሁ… በወዳጆቻችሁ ላይ ትከራከራላችሁ

እዚህ ስፍራ "እናንተ" እና "የእናንተ" የሚሉት በሁለተኛ መደብ ብዙ ቁጥር የተጻፉ ናቸው፡፡ (አንተ የሚለው ተውላጠ ስም ልዩ ልዩ መለኮች የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ሸቀጥ ንግድ በወዳጆቻችሁ ላይ ትከራከራላችሁ

ይህ አንድ ሰው ሸቀጥ እንደሚሸጥ እንዴት ወዳጁን እንደሚሸጠው ያነጻጽራል፡፡ "ወዳጆቻችሁን በገንዘብ ለመሸጥ ትከራከራላችሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 6:28-30

አሁን

ኢዮብ ይህንን ቃል የተጠቀመው አዲስ መረጃ ለመስጠት/ለማስተዋወቅ ነው፡፡

እባካችሁ ተመልከቱ

"ተመለከተ" የሚለው ግስ በሁለተኛ መደብ ብዙ ቁጥር የተጻፈ ነው፡፡ (አንተ የሚለው ተውላጠ ስም ልዩ ልዩ መለኮች የሚለውን ይመልከቱ)

በፊታችሁ አልዋሽም

"እናንተ" የሚለው ቃል የኢዮብን ወዳጆች ያመለክታል፡፡ እዚህ ስፍራ የእርሱ ወዳጆች የተወከሉት በእነርሱ ፊት በሚለው ነው፤ ይህም ያገለገለው እርሱን እየተመለከቱት መሆኑን አጉልቶ ለመግለጽ ነው፡፡ "ፊት ለፊት እየተመለከትኳችሁ ልዋሻችሁ አልችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ይቅር እንድትሉኝ እለምናችኋለሁ

"እባካችሁ ይቅር በሉኝ" ወይም "እባካችሁ እኔ የምለምናችሁ፣ እንዲህ መናገራችሁን እንድታቆሙ ነው"

ፍርደ ገምድልነታችሁን ከእናንተ አስወግዱ

ይህ በአዎንታዊ መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ቅን ፍረዱ" (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

በእርግጥ ይቅር በሉኝ

Job 7

Job 7:1-3

አጠቃላይ መረጃ፡

ጸሐፊው በእነዚህ በእያንዳንዳቸው ቁጥሮች ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚጠቀመው አንድን ሀሳብ በሁለት የተለያዩ ገለጻዎች ለማስተላለፍ ሲሆን፣ የእርሱ ግላዊ መከራ ሁሉም ሰው የሚደርስበት የጋራ መከራ ክፍል መሆኑን ትኩረት ለመስጠትም ይጠቀምበታል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰው በምድር ላይ ከባድ ስራ የለበትምን?

ኢዮብ ይህንን አሉታዊ ጥያቄ የሚያቀርበው፣ ሁሉም ሰው ከባድ ስራ እንደሚሰራ የእርሱን ግንዛቤ ለማጉላት ነው፡፡ ይህ በአዎንታዊ ዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "በምድር ላይ እያንዳንዱ ሰው የሚሰራው ከባድ ስራ አለ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

በምድር ላይ

ይህ ሰው በምድር ላይ በሚኖርበት ጊዜ ለሚለው አጠቃላይ አስተያየት ነው፡፡ "በምድር በሚኖርበት ዘመን" (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)

ዘመኑ እንደ ምንደኛ/ለእለት ስራ ተቀጣሪ/ ዘመን አይደለምን?

ኢዮብ ይህንን አሉታዊ ጥያቄ የሚያቀርበው ሁሉም ሰው በህይወት ውስጥ ትግል እንዳለበት ያለውን ግንዛቤ በትኩረት ለማቅረብ ነው፡፡ "ቀናቸው እንደ የእለት ተቀጣሪ ሰው ቀናት ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

እንደ አንድ ባሪያ… ልክ እንደ የእለት ተቀጣሪ ሰው… እኔ እንደዚያ ነበርኩ…በመከራ የተሞሉ ምሽቶች የተሰጡኝ

ኢዮብ መከራውን እና ችግሩን ከባሪያና ከተቀጣሪ ሰው ጋር ያነጻጽራል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የምሽት ጥላ

"ቀዝቃዛ ጥላ፡፡" በስውር የተጠቆመው መረጃ የምሽት ጥላ ቅዝቃዜን ይሰጣል፣ ደግሞም ከፀሐይ ይከልላል የሚለው ነው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የተቀጠረ ሰው/ተቀጣሪ

"የቀን ሰራተኛ፡፡" ይህ ለአንድ ቀን ስራ የተቀጠረ እና በእያንዳንዱ በሰራበት ቀን መጨረሻ ላይ የሚከፈለው ሰው ነው፡፡

የሰራበትን እንደሚጠብቅ

"ክፍያውን እንደሚጠብቅ"

እኔም፣ መከራ የበዛባቸውን ምሽቶች አግኝተውኛል፣ የወራት መከራን እንድታገስ ተደርጌያለሁ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ስለዚህም የወራት መከራ ታግሻለሁ፤ መከራ የባዘባቸው ምሽቶች ገጥመውኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ እና ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የመከራ ወራት/ጊዜያት

"መከራ" የሚለው ረቂቅ ስም "መከረኛ" በሚል ቅጽል ሊተረጎም ይችላል፡፡ "የመከራ ወራት/ጊዜያት" ወይም "ከንቱ ወራት/ጊዜያት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 7:4-5

ጋድም በምልበት ጊዜ

በውስጠ ታዋቂነት የቀረበው መረጃ ኢዮብ በምሽት ለመተኛት ጋድም በሚልበት ጊዜ ማለት ነው፡፡ "ለመተኛት ጋደም በምልበት ጊዜ" (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ለራሴ እንዲህ እላለሁ

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ በተለይ ለሌላ ለማንም ሰው አያቀርብም፡፡ "እኔ እጠይቃለሁ" ወይም "እኔ እገረማለሁ" (ከባለቤቱ ጋር የሚጣቀስ ተውላጠ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

መቼ ከመኝታዬ እነሳለሁ መቼ ለሊቱ ይነጋል?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው መተኛት ባለበት ሰአት ምን ያህል መከራው ጽኑ እንደሆነ አጉልቶ ለመግለጽ ነው፡፡ "ከመኝታዬ መነሳት ብችል እወዳለሁ፣ ነገር ግን ምሽቱ አይነጋም/ይቀጥላል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡(ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ፊት እና ወደ ኋላ ስገላበጥ

"ወደ ኋላ እና ወደፊት ስዟዟር፡፡" ይህ የሚያመለክተው ኢዮብ ካለ አንዳች እንቅልፍ ሌሊቱን በመኝታው ላይ ሲገላበጥ እንደሚያድር ነው፡፡

ስጋዬ በትሎች እና በአቧራ ጓል ተሸፍኗል

ትሎቹ እና የአቧራው ጓል ብዛት የተገለጸው ልብስ ሆነው እንደ ሸፈኑት ተደርጎ ነው፡፡ "ስጋዬ በትሎች እና በአቧራ ተሸፍኗል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ስጋዬ

ይህ መላ አካሉን ያመለክታል፡፡ "መላ አካሌ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

የአቧራ ጓል

ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ አማራጭ ትርጉሞች 1) የእድፍ ቅርፊት ወይም ጓል ወይም 2) በቆዳ ላይ ቅርፊት/ማፈክፈክ

አመርቅዟል

"ዳግም ቆስሏል"

Job 7:6-7

አጠቃላይ መረጃ፡

ጸሐፊው የኢዮብን የእድሜ ጥቂትነት ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ እንዲሁም አንድን ሀሳብ ሁለት የተለያዩ ገለጻዎችን በመጠቀም ለማስተላለፍ በእነዚህ በእያንዳንዳቸው ቁጥሮች ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ መጠቀሙን ይቀጥላል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ቀኖቼ/ዘመኔ ከሸማኔ መወርወሪያ ይልቅ ፈጣኖች ናቸው

ኢዮብ ህይወቱን ከሸማኔ መወርወሪያ ፈጣንነት ጋር ያነጻጽራል፡፡ "ህይወቴ በጣም በቶሎ ያልፋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሸማኔ

ክር በማዳወር ልብስ የሚሰራ ሰው

የሸማኔ መወርወሪያ

ክሩን የሚይዘው ተንቀሳቃሽ ክፍል፣ ወይም ልብሱ ሲሰራ ከሸማኔው ዕቃ ውስጥ ክሩ ወደፊት እና ወደ ኋላ በፊጥነት እንዲንቀሳቀስ የሚያደርግ

አስብ

"አስታውስ፡፡" "አስብ" የሚለው ሀረግ እግዚአብሔር ይረሳል ማለት አይደለም፡፡ ኢዮብ የህይወቱ ዘመን ጥቂት መሆኑን እግዚአብሔር እንዲያይለት እየጠየቀ ነው፡፡

ህይወቴ የእስትንፋስ ያህል ናት

ኢዮብ የህይወቱን ጥቂትነት ከእስትንፋስ አጭርነት ጋር ያነጻጽራል፡፡ "ህይወቴ የአንዲት እስትንፋስ ያህል አጭር ናት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከእንግዲህ ዐይኖቼ አንዳች መልካም ነገር አያዩም

እዚህ ስፍራ "ዐይኖቼ" የሚለው የሚወክለው የኢዮብን መላ ሰውነት እና ነገሮችን የማየት ወይም የማድረግ ችሎታ ነው፡፡ "ዳግም በፍጹም መልካም ነገር አላይም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 7:8-10

አጠቃላይ መረጃ፡

ጸሐፊው ኢዮብ ከሞት በኋላ እግዚአብሔርም ሆነ እርሱን የሚያውቁት ሰዎች ዳግም እንደማያዩት ያለውን ሀሳብ ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ እንዲሁም አንድን ሀሳብ ሁለት የተለያዩ ገለጻዎችን በመጠቀም ለማስተላለፍ በእነዚህ በእያንዳንዳቸው ቁጥሮች ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ መጠቀሙን ይቀጥላል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የሚመለከተኝ የእግዚአብሔር ዐይን ከእንግዲህ አያየኝም

በርካታ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጉሞች ይህንን "የሚመለከቱኝ ዐይኖች ከእንግዲህ አያዩኝም" በሚል ተርጉመውታል፡፡ "የእግዚአብሔር" ቃሎች በዚህ ሀረግ ላይ የተጨመሩት በይዘቱ ውስጥ የተካተቱ/የተጠቆሙ በመሆኑ ነው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የሚመለከተኝ የእግዚአብሔር ዐይን… የእግዚአብሔር ዐይን በእኔ ላይ ይሆናል

እዚህ ስፍራ እግዚአብሔር ምን እንደሚመለከት ትኩረት ለመስጠት የተወከለው በእርሱ "ዐይን" ነው፡፡ "እኔን የሚመለከት እግዚአብሔር… እግዚአብሔር ይመለከተኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ደመና እንደሚበን እና እንደሚጠፋ፣ ወደ ሲኦል የሚወርድ ዳግም አይመለስም

ኢዮብ ሞትን የሚገልጸው በኖ እንደሚጠፋ ደመና ነው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚልን ይመልከቱ)

ደመና እንደሚበተን

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ደመና እንደሚበን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ሲኦል የሚወርድ ዳግም አይመለስም

"የሞተ ተመልሶ አይመጣም"

በእርሱ ስፍራ/በስፍራው

"በእርሱ ስፍራ" የሚሉት ቃላት በእርሱ ስፍራ የሚኖሩትን ይወክላል፡፡ "በእርሱ ስፍራ የሚኖሩ ሰዎች" ወይም "የእርሱ ቤተሰቦች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 7:11-12

በመንፈሴ ጭንቀት እናገራለሁ፣ በነፍሴን መራርነት አማርራለሁ

ኢዮብ ዝም የማይልበትን ምክንያት ለማጉላት ሁለት የተለያዩ ገለጻዎችን በመጠቀም አንድን ሃሳብ ያስተላልፋል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አፌን አላቅብም

እዚህ ስፍራ አፍ የሚወክለው ንግግርን ነው፡፡ "ንግግሬን አልገድብም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በመንፈሴ ምሬት

"በመንፈሴ ሀዘንተኝነት" ወይም "በመከራዬ ስቃይ፡፡" "ጭንቀት" የሚለውን ረቂቅ ስም "ስቃይ" የሚለውን ተውሳከ ግስ ተጠቅሞ መተርጎም ይቻላል፡፡ "መንፈሴ ተጨንቆ ሳለ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

በነፍሴን መራርነት

እዚህ ስፍራ ሀዘን የተገለጸው መራራ ጣዕም እንዳለው ተደርጎ ሲሆን፣ "ነፍስ" ደግሞ የሰውን ሁለንተና የሚያመለክት ሆና ተነግራለች፡፡ "በቁጣ እና ቅር በመሰኘት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚሉትን ይመልከቱ)

በእኔ ላይ ጠባቂ ታኖር ዘንድ እኔ ባህር ነኝ፣ ወይንስ የባህር አውሬ ነኝ?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የሚያቀርበው በእግዚአብሔር ላይ ማዘኑን ለመግለጽ ነው፡፡ ኢዮብ ራሱን ከባህር ወይም ከባህር አውሬ ጋር በማነጻጸር እግዚአብሔር እርሱን አሰቃቂ ፍጥረት አድርጎ እንደቆጠረው ይናገራል፡፡ ይህ በገለጻ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "እኔ ጠባቂ የሚያስፈልገው የባህር አውሬ ወይም ባህሩን አይደለሁም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 7:13-15

አጠቃላይ መረጃ፡

ጸሐፊው የኢዮብን ጥልቅ መከራ ለማጉላት ሁለት የተለያዩ አገላለጾችን በመጠቀም እንድን ሃሳብ ለማስተላለፍ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ቁጥሮች ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤን መጠቀሙን ይቀጥላል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

መኝታዬ ያጽናናኛል፣ መከዳዬ ማጉረምረሜን ቀለል ያደርግልኛል

እዚህ ስፍራ "መኝታ/አልጋ" እና "መከዳ" የሚሉት "እንቅልፍ" ለሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ ኢዮብ ለመተኛት ጋደም ሲል አረፍ ለማለት ተስፋ ያደርጋል፡፡ ይህ ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ሰብአዊ ባህሪያትም ደግሞ አሉት፤ የማጽናናት እና ሰውን አረፍ የማድረግ አቅም አላቸው፡፡ "መኝታዬ እና መከዳዬ እንደ ሰው ያሉ ነገሮች ናቸው፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ሰውኛ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

አልጋዬ/መኝታዬ… መከዳዬ

እነዚህ ሀረጋት ተመሳሳይ ነገርን ያመለክታሉ፡ "አልጋዬ…መኝታዬ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

አንተ አሰደነገጥከኝ/አስፈራኸኝ

እዚህ ስፍራ "አንተ" የሚለው የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ነው

ማነቅ

አንድን ሰው ጉሮሮውን ጨምቆ እና ትንፋሹን አቁሞ መግደል

እነዚህ የእኔ አጥንቶች/አጥንቶቼ

እዚህ ስፍራ ኢዮብ "አጥንቶች" የሚለውን ቃል የተጠቀመው አካሉን ለማመልከት ነው፡፡ "ይህ የእኔ አካል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 7:16-18

አያያዥ ሃሳብ፡

ጸሐፊው የኢዮብ መከራ በእርሱ ማንነት እርባና ግንዛቤ ላይ ትኩረት ለመሰጠት ሁለት የተለያዩ አገላለጾችን በመጠቀም እንድን ሃሳብ ለማስተላለፍ በመጀመሪያዎቹ ሁለት ቁጥሮች ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤን መጠቀሙን ይቀጥላል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ህይወቴን ጠላሁ

"ህይወቴን ናቅኩት"

ሁሌም በህይወት ለመኖር

"ለዘለአለም ለመኖር"

ቀናቴ/ዘመኔ እርባና ቢስ ናቸው

"ዘመኔ አለ ፍሬ ነው" ወይም "የህይወቴ ቀናት ከንቱ/ባዶ ናቸው"

ትከታተለው ዘንድ …. ሰው ምንድን ነው?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው እግዚአብሔር ለሰው ለምን ትኩረት እንደሚሰጥ መደነቁን ለማጉላት ነው፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ትከታተለው ዘንድ…ሰው ምንድን ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ልብህን ታሳርፍበት ዘንድ

እዚህ ስፍራ ልብ/አእምሮ የመሚለው የሚወክለው ሃሳብን እና ትኩረት መስጠትን ነው፡፡ "ልብህን ታሳርፍበት ዘንድ" ማለት ትኩረት መስጠት ማለት ነው፡፡ "ትኩረትህን ወደ እርሱ ታደርግ ዘንድ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ሰውኛ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

እርሱን ተመልከተው

"እርሱን በጥንቃቄ መርምረው"

Job 7:19-20

ምራቄን ለመዋጥ…ይህ ለምን ያህል ጊዜ ይሆና?

እዚህ ስፍራ ኢዮብ ሁለት የተለያዩ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄዎችን በመጠቀም አንድን ሀሳብ የሚገልጸው እግዚአብሔር እርሱን መከታተሉን ቢያቆም ደስ እንደሚለው ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ "እኔን መከታተልህን አቁም! የራሴን ምራቅ የምውጥበትን ያህል ጊዜ እንኳን ፋታ ስጠኝ!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚሉትን ይመልከቱ)

ምራቅ

አፍ እርጥበቱን እንዲጠብቅ እና ምግብን ለመዋጥ የሚረዳ በሰዎች አፍ ውስጥ የሚፈጠር ፈሳሽ

ኃጢአት ብሰራ እንኳን … ሸክም ሆንኩብህ?

ኢዮብ እነዚህን ጥያቄዎች የሚያቀርበው እግዚአብሔር የማይገባ ነገር እንዳደረሰበት ከእርሱ ጋር ለመከራከር ነው፡፡ " ኃጢአት ብሰራ እንኳን፣ አንተ ሰዎችን ሁሉ ስለምታይ ያ በአንተ ላይ አንዳች አያደርግም፡፡ ሸክም እሆንብህ ዘንድ፣ ለምን ኢላማህ እንዳደረግከኝ ንገረኝ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 7:21

ስለ ምን መተላለፌን ይቅር ብለህ በደሌን ከእኔ አታርቅም?

እዚህ ስፍራ ኢዮብ ከቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ ጋር ሃሳቡን ለማጉላት ሁለት ተመሳሳይ ሐረጎችን ይጠቀማል፡፡ ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች፡ 1) ኢዮብ ለምን እግዚአብሔር ይቅር እንደማይለው ይጠይቃል፡፡ "መተላለፌን ለምን ይቅር እንደማትለኝ እና ኃጢአቴን እንደማታርቅልኝ ንገረኝ፡፡" ወይም 2) ኢዮብ እግዚአብሔርን ምናልባት በድዬ ቢሆን እንኳን ለምን ስህተቴን እንዳላየህ ሆነህ አታልፈኝም፡፡ "በደሌን እና መተላለፌን ለምን እንዳልተውክልኝ ንገረኝ፡፡" በሚሉት ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚሉትን ይመልከቱ)

ውሰድ/አርቅ

"አስወግድ"

አሁን በአፈር ውስጥ እጋደማለሁን

"በአፈር ውስጥ መጋደም" የሚለው ሀረግ ሞትን የሚወክል ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "እኔ አሁን እሞታለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በህይወት አልኖርም

"እዚህ አልሆንም" ወይም "እኔ እሄዳለሁ"

Job 8

Job 8:1-3

አያያዥ ሃሳብ

በዚህ ምዕራፍ፣ በልዳዶስ ስለ ኢዮብ ማማረር መናገር ይጀምራል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡

ቁጥር 2 እና ቁጥር 3 እያንዳንዳቸው ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ሁለት የተለያዩ ጥያቄዎችን ይይዛሉ፡፡ በልዳዶስ እነዚህን ጥያቄዎች የሚያውላቸው/የሚጠቀምባቸው ኢዮብን ለመገሰጽ ነው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ከዚያም ሹሐዊው በልዳዶስ እንዲህ ሲል መለሰ

"በልዳዶስ" የሹሐ ነገድ አባል የወንድ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

እስከ መቼ የአፍቃል እንደ ታላቅ ነፋስ ይሆናል

በልዳዶስ የኢዮብን ቃል የሚገልጸው ባዶ እና እንደ ነፋስ በውስጣቸው ምንም ፍሬ ነገር እንደሌለባቸው አድርጎ ነው፡፡ ይህ በገለጻ አይነት ሊተረጎም ይችላል፡፡ "የአፍህ ቃላት እንደ ታላቅ ነፋስ ምንም ጥቅም የሌላቸው ናቸው፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያው አነጋገር እና ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚሉትን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ፍትህን ይከለክላልን? ሁሉን ቻይ የሆነው ጽድቅን ያጣምማልን?

እዚህ ስፍራ "እግዚአብሔር" እና "ሁሉን ቻይ የሆነው" የሚሉት ሁለቱም ያህዌን የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች በመግለጫ ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ "እግዚአብሔር ፍትህን አያጣምምም፤ ሁሉን ቻይ የሆነው ጽድቅን አያጣምም፡፡" (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ፍትህን ያጣምማልን?... ጽድቅን ያጣምማልን?

"ትክክል ያለሆነውን ማረጋገጫ ሰጥቶ ያደርጋልን?.. ጽድቅ ያልሆነውን ማረጋገጫ ሰጥቶ ይፈጽማልን?"

Job 8:4-5

ለእጃቸው ኃጢአት አሳልፎ ሰጥቷቸው ከሆነ

እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚወክለው የኃጢአትን ሀይል ወይም ውጤት ነው፡፡ በልዳዶስ እግዚአብሔር የኢዮብን ልጆች የገደላቸው በኃጢአታቸው ምክንያት እንደሆነ ያመለክታል፡፡ "የልጆችህ ኃጢአት እግዚአብሔር እንዲገድላቸው ምክንያት ሆኖታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

ነገር ግን አንተ ምናልባት እግዚአብሔርን በትጋት ፈልገህ ጥያቄህንም ሁሉን ቻይ ለሆነው አቅርበህ ይሆናል

በልዳዶስ ኢዮብ ከእግዚአብሔር ጋር በትክክል ቢስማማ ምን ሊሆን ይችል እንደ ነበረ እየተናገረ ነው፤ ነገር ግን በልዳዶስ ኢዮብ ይህንን ማድረጉን አያምንም፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

በትጋት እግዚአብሔርን መፈለግ… ሁሉን ቻይ ለሆነው ጥያቄህን ማቅረብ

እነዚህ ሁለት ሀረጋት ኢዮብ እግዚአብሔርን እርዳታ ወይም ምህረት መጠየቁን ያመለክታሉ፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

በትጋት እግዚአብሔርን መፈለግ

"ከልብ እግዚአብሔርን እርዳታ መጠየቅ"

Job 8:6-7

አጠቃላይ መረጃዎች፡

በልዳዶስ ኢዮብ ንጹህ ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር ይረዳው ነበር ይላል‹ ነገር ግን በልዳዶስ ኢዮብ ንጹህ መሆኑን አያምንም፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ንጹህ እና ትክክለኛ ብትሆን

"ንጹህ እና ጻድቅ ሰው ብትሆን ኖሮ" ወይም "እግዚአብሔርን ታዝዘህ ቢሆን እና ትክክለኛ የሆነውን ነገር የምታደርግ ቢሆን ኖሮ"

እርሱ ስለ አንተ ይነሳል

እዚህ ስፍራ ያህዌ የተገለጸው ኢዮብን ለመርዳት ከእንቅልፉ እንደተነሳ ተደርጎ ነው፡፡ "አንተን ሊረዳህ" ወይም "ለአንተ መልካም ነገሮችን ለማድረግ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አንተን ወደ ትክክለኛ ስፍራ ይመልስሃል

ይህ የሚያመለክተው ኢዮብ ያጣቸውን ነገሮች፤ ቤተሰቡን ጨምሮ፣ ሀብቱን እና ክብሩን መልሶ እንደሚሰጠው ነው፡፡

ምንም እንኳን ጅማሬህ እጅግ ታናሽ ቢሆንም፣ ፍጻሜህ ግን እጅግ ታላቅ ይሆናል

እዚህ ስፍራ ሀብትን ማጣት የተገለጸው "ታናሽ ጅማሬ" እንደሆነ ተደርጎ ነው፡፡ "በህይወትህ መነሻ ላይ ደሃ ብትሆንም፣ በዕድሜህ የኋልኛ ዘመን እግዚአብሔር እጅግ ባለጠጋ ያደርግሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 8:8-10

አጠቃላይ መረጃ፡

በልዳዶስ አባቶቻቸው እርሱ ለኢዮብ ከሚነግረው ሃሳቦች ጋር የሚስማሙ መሆኑን አጉልቶ ለመግለጽ ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤን በእነዚህ ቁጥሮች ሁሉ መጠቀሙን ይቀጥላል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልቱ)

አባቶቻችን ያስተምሯቸው ለነበሩ ነገሮች ዋጋ ስጥ

"አባቶቻችን ይናገሩ የነበረውን በጥንቃቄ ተረዳ" ወይም "አባቶቻችን የተዉልንን ትምህርቶች ስፍራ ስጣቸው"

በምድር ላይ የሰው ዘመን ጥላ ነው

የህይወት አጭርነት የተገለጸው በፍጥነት የሚጠፋ ጥላ እንደሆነ ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ አያስተምሩህምን፣ ደግሞስ አይነግሩህምን? እነርሱ ከልባቸው ቃል አይነግሩህምን? በልዳዶስ እነዚህን ቃለ

ምልልሳዊ ጥያቄዎች የሚጠቀመው ኢዮብን ከእርሱ እና ከአባቶቻቸው ጋር ባለመስማማቱ ሊወቅሰው ነው፡፡ ይህ በገለጻ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "እነርሱ ያስተምሩሃል፣ ደግሞም ይነግሩሃል፤ በእውነት የሚያምኑበትንም ይነግሩሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ከልባቸው

እዚህ ስፍራ "ልብ" የሚወክለው ውስጣዊ እምነትን ነው፡፡ "እነርሱ በእውነተኝነት የሚያምኑበትን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 8:11-12

አጠቃላይ መረጃ፡

ከቁጥር 11-14 ያለው የበልዳዶስ ትምህርቶች ስለመሆኑ ግልጽ አይደለም፣ ወይም በልዳዶስ ከኢዮብ 8፡8-10 ያለውን የአባቶች ትምህርት ጠቅሶ ሊሆን ይችላል፡፡

ረግረግ በሌለበት ደንገል ይበቅላልን? ውሃ በሌለበት ቄጠማ ይድጋልን?

በልዳዶስ እነዚህን ትይዩ ንጽጽራዊ ጥያቄዎች የሚጠቀመው ሰዎች ያለ እግዚአብሔር መኖር እንደማይችሉ ይህን አንድ ሀሳብ ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ እዚህ ስፍራ ተክሎች ሰውን ሲወክሉ፣ ውሃ ደግሞ እግዚአብሔርን ይወክላል፡፡ ጥያቄው በግልጽ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "የደንገል ተክል ከረግረግ ርቆ ሊያድግ አይችልም፡፡ ቄጠማም ያለ ውሃ ሊያድግ አይችለም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለምልልሳዊ ጥያቄ እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እንደዚሁም ዘይቤያው አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

ደንገል

ጥልቀት በሌለው ውሃ ላይ የሚያድግ ረጅም ቄጠማ መሰል ተክል

ገና አረንጓዴ ሳሉ እና ሳይቆረጡ ከሌላው ተክል ፈጥነው ይደርቃሉ

ውሃ በሚያጥርበት ጊዜ እንደሚደርቁ ተጠቁሟል፡፡ ይህ ይበልጥ ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ "ማንም ባይቆርጣቸውም እንኳን እነዚህ ተክሎች ውሃ በሚያጥርበት ጊዜ ማደግ አይችሉም፤ ደግሞም ፈጥነው ይደርቃሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ይጠፋሉ

"ይደርቃሉ"

Job 8:13-15

አጠቃላይ መረጃ፡

ከቁጥር 11-14 ያለው የበልዳዶስ ትምህርት ስለመሆኑ ግልጽ አይደለም፣ ወይም በልዳዶስ የአባቶችን ትምህርት ከኢዮብ 8፡8-10 ካለው ክፍል ጠቅሶ ሊሆን ይችላል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡

ከቁጥር 14-18፣ "እርሱ" እና "የእርሱ" የሚሉት ተውላጠ ስሞች የሚያመለክቱት በአጠቃላይ እግዚአብሔር የለሽ ሰዎችን የሚወክል እግዚአብሔር የለሽ ሰውን ነው፡፡ "እነርሱ" እና "የእነርሱ" የሚሉትን የብዙ ቁጥር ተውላጠ ስሞች/የስም ምትኮች/ መጠቀም አንባቢያንን ሊያግዝ ይችላል፡፡ (የስማዊ ሀረግ ክፍሎች የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔርን የሚረሱ/የሚተዉ ሁሉ መንገዳቸው እንዲህ ነው

እዚህ ስፍራ "መንገድ" የሚወክለው የአንድን ሰው የወደፊት ጊዜ እና በእርሱ ላይ የሚደርሱ ነገሮቸን ነው፡፡ "እግዚአብሔርን በሚረሱ ሁሉ ላይ ተመሳሳይ ነገር ይደርሳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔር የለሾች ተስፋ ይጠፋል

"አምላክ የለሽ ሰው የሚሻቸው ነገሮች አይጸሙም"

የእርሱ ልበ ሙሉነት የንኮታኮታል/ይሰበራል… መታመኛው እንደ ሸረሪት ድር ደካማ ነው

እነዚህ ሁለት ሀረጋት ተመሳሳ ትርጉም አላቸው፤ ደግሞም አገላለጾቹ አምላክ የለሽ ሰው ሊያድነው በማይችል ነገር እንደሚታመን ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልቱ)

እምነቱ እንደ ሸረሪት ድር ደካማ ነው

እዚህ ስፍራ በልዳዶስ የአምላክ የለሽ ሰዎችን እምነት ከሸረሪት ድር ጋር ያነጻጽራል፤ ሁለቱንም ጥቂት ሀይል ያፈራርሳቸዋል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በቤቱ ላይ ይደገፋል፣ ነገር ግን ይህ አይደግፈውም፤ እርሱ ይህን ይይዛል፣ ነገር ግን የያዘው ጸንቶ አይቆምም፡፡

ይህ ሀሳብ የሚያመለክተው ምናልባት ለደህንነቱ ንብረቱን እና ሀብቱን መታመኛ ያደረገን ሰው ሊሆን ይችላል፡፡ እንዲህ ከሆነ ደግሞ እዚህ ስፍራ "ቤት" የሚወክለው የባለቤቱን ንብረት እና ሀብት ነው፡፡ "ሀብት ስላለው በደህንነት የሚጠበቅ እንደሆነ ያስባል፣ ነገር ግን ደህንነቱ አይጠበቅም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሀብቱ አይደግፈውም

ይህ አሉታዊ ሀሳብ ተቃራኒውን ነገር ያጎላል፡፡ ይህ በአዎንታዊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እርሱ ይወድቃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ምፀት/ላይዶክስ የሚለውን ይመልከቱ)

አይቆምም

ይህ አሉታዊ ሀሳብ ተቃራኒውን ነገር ያጎላል፡፡ ይህ በአዎንታዊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ይህ ይወድቃል"

Job 8:16-18

አጠቃላይ መረጃ፡

እዚህ ስፍራ "እርሱ" እና "የእርሱ" የሚሉት ተወላጠ ስሞች የሚያመለክቱት በአጠቃላይ እግዚአብሔር የለሽ ሰዎችን የሚወክል እግዚአብሔር የለሽ ሰውን ነው፡፡ "እነርሱ" እና "የእነርሱ" የሚሉትን የብዙ ቁጥር ተውላጠ ስሞች/የስም ምትኮች/ መጠቀም አንባቢያንን ሊያግዝ ይችላል፡፡ (የስማዊ ሀረግ ክፍሎች የሚለውን ይመልከቱ)

ከፀሐይ በታች አረንጓዴ ነው፣ ቅርንጫፉ ሁሉ በስፍራ ሁሉ ይስፋፋል

እዚህ ስፍራ በልዳዶስ እግዚአብሔር የለሽ ሰውን ከጤናማ ተክል ጋር ያነጻጽራል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከፀሐይ በታች አረንጓዴ ነው

የዕብራይስጡ ጽሁፍ ትርጉም ግልጽ አይደለም፡፡ ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትረጉሞች 1) በቀን ጤናማ ነው ወይም 2) ፀሐይ ከመውጣቱ አስቀድሞ ውሃ ይጠጣል

ስሮቹ በድንጋይ ክምር ላይ ይጠመጠማሉ… በአለት መካከል መልካም ስፍራ ይፈልጋል

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ ሆኖም ትርጉማቸው ግልጽ አይደለም፡፡ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) እያንዳንዱን ቀዳዳ በሚገባ በመጠቀም በአለት ላይ ስር የሰደደ ይመስላል ወይም 2) ስሩ ለም መሬት ማግኘት ስላልቻለ በአለቶች መሃል አልሚ ምግብ ለማግኘት መሞከር አለበት፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

ይህ ሰው ከስፍራው ከተደመሰሰ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አንድ ሰው ከስፍራው አስለቅቆታል" ወይም "አትክልተኛው ከስፍራው ከነቀለው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ስፍራው

"አለታማው መሬት" ወይም "የተተከለበት ስፍራ"

ስፍራው ሊክደው እና እንዲህ ሊለው ይችላል ‘በፍጹም አይቼህ አላውቅም'

የአትክልቱ/የተተከለበት ስፍራ የተገለጸው የመናገር ችሎታ እንዳለው ተደርጎ ነው፡፡ ስፍራው ወዲያውኑ የእርሱን መኖር ረስቷል፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 8:19-20

ይህ እንዲህ ያለው ሰው የ"ደስታ" ባህሪይ ነው

በልዳዶስ እግዚአብሔር የለሽ ሰው አንዳች ደስታ እንደሌለው በምጸት እየተናገረ ነው፡፡ "እግዚአብሔር የለሽ ከሆነው ድርጊታቸው የሚያተርፉት ደስታ ቢኖር ይህ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ምፀት የሚለውን ዘይቤያዊ አነጋገር ይመልከቱ፡፡

በተመሳሳይ አፈር ላይ በስፍራው ሌሎች ተክሎች ይበቅላሉ

በልዳዶስ ከኢዮብ 8፡16-18 ዘይቤውን ይቀጥላል፡፡ ሌሎች እግዚአብሔር የለሽ ሰዎች የተገለጹት የመጀመሪያው አምላክ የለሽ ሰው ሲሞት የስርሱን ስፍራ እንደወሰዱ ተክሎች ተደርገው ነው፡፡ "አንድ ክፉ ሰው ሲሞት፣ ሌላው የእርሱን ስፍራ ይወስዳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ይበቅላል

"ያድጋል"

በዚያው አፈር

"አለታማ ምድር" ወይም "ስፍራው/የአትክልቱ ቦታ"

በስፍራው

"አምላክ የለሽ በሆነው ሰው ቦታ"

እግዚአብሔር ንጹሁን ሰው አያጠፋም

ይህ በአዎንታዊ አረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር ንጹሁን ሰው ይቀበላል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

እርሱ የክፉ አድራጊዎችን እጅ አይዝም

እዚህ ስፍራ "እጅ መያዝ" የሚለው የሚያመለክተው መርዳት ወይም መደገፍ የሚለውን ነው፡፡ "እግዚአብሔር ክፉ የሚያደርጉ ሰዎችን አይደግፍም/አይረዳም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 8:21-22

እርሱ ገና የአንተን አፍ በሳቅ፣ ከንፈሮችህን በእልልታ/በደስታ ጩኸት ይሞላዋል

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖራቸው ኢዮብ ትሁት መሆን ቢችል እንደምን ተመልሶ ደስተኛ ሊሆን እንደሚችል ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ "እርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ሲሆን "የአንተ" ሚለው ኢዮብን ያመለክታል፡፡ "ንጹህ ብትሆን እግዚአብሔር ዳግም በጣም ደስተኛ ያደርግሃል" (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

አፍህን በሳቅ ይሞላል

እግዚአብሔር ኢዮብን በሳቅ እንዲሞላ ደርጋል የሚለው ሀሳብ የተገለጸው እግዚአብሔር በኢዮብ አፍ ሳቅ እንደሚጨምር ተደርጎ ነው፡፡ "ሳታቋርጥ እንድትስቅ ያደርጋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከንፈሮችህን በእልልታ/በደስታ ጨኸት

"ይሞላል" የሚለው ግስ በውስጠ ታዋቂነት በቀደመው ሀረግ ውስጥ ይገኛል፡፡ እግዚአብሔር የደስታ ጩኸት/ እልልታ እንዲያሰማ ማድረጉ የተገለጸው እግዚአብሔር በኢዮብ አፍ ደስታን እንደሚጨምር ተደርጎ ነው፡፡ "እግዚአብሔር በደስታ እንድትጮህ/እልል እንድትል ያደርጋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተዘለለ/የተተወ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

አንተን የሚጠሉ ሀፍረት ይለብሳሉ

እዚህ "ሀፍረት" የሚለው ቃል የተገለጸው እግዚአብሔር የኢዮብ ጠላቶች እንዲለብሱት እንደሚያደርገው ልብስ ተደርጎ ነው፡፡ ይህ ማለት እነርሱ በጣም ያፍራሉ ማለት ነው፡፡ "እግዚአብሔር አንተን የሚጠሉትን በጣም እንዲያፍሩ ያደርጋቸዋል" (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከእንግዲህ የክፉዎች ድንኳን አይገኝም

እዚህ "ድንኳን" የሚያመለክተው የክፉዎችን ቤት ነው፡፡ "የክፉዎች ቤት ይደመሰሳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ከእንግዲህ አይገኝም

"አይቀጥልም" ወይም "ይደመሰሳል"

Job 9

Job 9:1-3

ይህ እንዲህ እንደሆነ በእውነት አውቃለሁ

"አንተ እምትናገረው እውነት እንደሆነ ያንን አውቃለሁ"

ይህ እንዲህ ነው

እዚህ ስፍራ "ይህ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው በልዳዶስ የተናገረውን ነው፡፡

ሰው በእግዚአብሔር ፊት እንዴት ትክክል/ጻድቅ ሊሆን ይችላል?

"ማንስ ቢሆን እንዴት በእግዚአብሔር ፊት ንጹህ ሊሆን ይችላል?"

ክርክር

"ጠብ"

ከአንድ ሺህ ጊዜ አንዴም ሊመልስለት አይችልም

"ከሺህ አንዴ" የዚህ ፈሊጣዊ አነጋገር ትርጉም "በፍጹም" ማለት ነው፡፡ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች፡ 1) "ለእግዚአብሔር ምንም መልስ መስጠት አይችልም" ወይም 2) "እግዚአብሔር በፍጹም መልስ አይሰጠውም" (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አንድ ሺህ ጊዜ

"1,000 ጊዜ"

Job 9:4-6

በልቡ ጠቢብ

እዚህ ስፍራ ልብ የሚለው የሚወክለው ውስጣዊ ፍጥረትን ወይም ሀሳብን ነው፡፡ "በውሳኔው ጠቢብ የሆነ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በጥንካሬቀው ታላቅ

"ጥንካሬ" የሚለው ረቂቅ ስም "ጠንካራ" በሚለው ቅጽል ሊገለጽ ይችላል፡፡ "በጥንካሬው እንዴት ታላቅ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

በእርሱ ላይ ደንድኖ ስኬት ያገኘ ማን ነው?

ይህ "ማንም" የሚል ምላሽ የሚጠበቅበት ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ ነው፡፡ በገለጻ እንደገና ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ማንም በእርሱ ላይ ራሱን አደንድኖ ፍሬያማ የሆነ የለም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

በእርሱ ላይ ራሱን አደንድኖ

ራስን ማደንደን ማለት ግትር መሆን ማለት ነው፡፡ "እርሱን ተቃውሞ" ወይም "እርሱን ሳያከብር" (ከባለቤቱ ጋር የሚጣቀስ ተውላጠ ስም)

ተራሮችን ከስፍራቸው የሚያስወግድ

"እግዚአብሔር ተራሮችን ያስወግዳል"

በእርሱ ቁጣ

"ቁጣ" የሚለው ረቂቅ ስም "መቆጣት" በሚለው ቅጽል ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እርሱ ስለተቆጣ/እርሱ በመቆጣቱ ምክንያት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ምድርን የሚያናውጠው እርሱ

"እግዚአብሔር ምድርን ያናውጣል"

ምሰሶዎቿን ያንቀጠቅጣል

"መሰረቶቿ እንዲንቀጠቀጡ ያደርጋል"

Job 9:7-9

ከዋክብትን የጋረደ ማን ነው?

"ከዋክብትን ከመታየት የሚከለክል ማን ነው"

በራሱ ችሎታ ሰማያትን የዘረጋ ማን ነው

እግዚአብሔር ሰማያትን ካለ ማንም እርዳት እንደፈጠረ፣ ሰማያት እርሱ የዘረጋቸው ስራዎቹ መሆኑ ተነግሯል፡፡ (ከባለቤቱ ጋር የሚጣቀስ ተውላጠ ስም እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

የባህር ማዕበልን የሚከለክል

እግዚአብሔር ባህርን ጸጥ እንደሚያደርግ ተገልጽዋል፡፡ "እግሮቹን በባህረ ማዕበል ላይ ያሳርፋል" ወይም "የባህር መዕበልን ጸጥ ያደርጋል በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ድብ፣ ኦሪዮን፣ ፕልያዲስ

እነዚህ በሰማይ ላይ የተለየ ቅርጽ የሚሰሩ የሚመስሉ የከዋክብት ስብስብ ስሞች ናቸው፡፡ (የማይታወቀውን መተረጎም የሚለውን ይመልከቱ)

ኦሪዮን

በግሪኮች አፈታሪክ ውስጥ ዝነኛ የሆነ አዳኝ

ፕልያዲስ

በሰማይ የተቀራረቡ የሚመስሉ በርካታ ብሩህ ከዋክብት

የከዋክብት ስብስብ

በሰማይ ላይ የተለየ ቅርጽ የሚሰሩ የሚመስሉ የከዋክብት ስብስቦች

Job 9:10-12

አጠቃላይ መረጃ፡

ጸሐፊው በእነዚህ በእያንዳቸው ቁጥሮች ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤን በመገልገል ድርብ ሃሳቦችን ተጠቅሞ የእግዚአብሔርን ታላቅነት፣ የማይታይ መሆኑን እና ሉዓላዊነቱን በአንድ ሃሳብ ለማስተላለፍ ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የማይደረስባቸው/የማይመረመሩ ነገሮች

"ለመረዳት የማይቻሉ ነገሮች"

እነሆ

"ተመልከት" ወይም "አድምጥ" ወይም "ልነግርህ የተዘጋጀሁትን ለመስማት ትኩረት ስጥ፡፡"

እርሱ አለፈ

"እርሱ በዚያ አለፈ" ወይም "እርሱ ተንቀሳቀሰ"

እርሱ አንዳች ነገር ቢነጥቅ፣ ማን ሊያስቆመው ይችላል? እርሱን ‘ምን እያደረግህ ነው' ብሎ ሊጠይቀው የሚችል ምን ነው?

እነዚህ "ማንም" የሚል ምላሽ ሚጠበቅባቸው ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄዎች ናቸው፡፡ በገለጻ መልክ ሊጻፉ ይችላሉ፡፡ "እርሱ አንድ ነገር ቢወስድ፣ ማንም ሊያስቆመው አይችልም፡፡ ማንም ‘ምን እያደረግህ ነው?' ሊለው አይችልም፡፡ በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ አንዳች ነገር ቢነጥቅ

"እርሱ አንድ ነገር ቢወስድ" ወይም "እርሱ አንድ ነገር መንጠቅ ቢፈልግ"

Job 9:13-15

ረዓብን የሚረዱ ከእርሱ በታች ይሰግዳሉ

እዚህ ስፍራ "ከእርሱ በታች መስገድ" የሚለው መገዛትን ወይም መሸነፍን ይወክላል፡፡ "እርሱ የረዓብን ረዳቶች ያደቃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትምዕርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመለከቱ)

ረዓብ

እዚህ ስፍራ "ረዓብ" የሚለው ቃል የባህር አውሬን ያመለክታል፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ታዲያ ከእርሱ ጋር እሟገት ዘንድ ፣ ለእርሱስ ምክንያት ለማቅረብ ቃላት ማግኘት እችላለሁን?

ኢዮብ እግዚአብሔርን ለመግጠም አቅም እንደሌለው ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ሁለት ተመሳሳይ ጥያቄዎችን ያቀርባል፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች በገለጻ መልክት እንደገና ሊጻፉ ይችላሉ፡፡ "ስለዚህ በእርግጥ እኔ ለእርሱ መልስ ልሰጥ አልችልም ወይም ለእርሱ ምክንያት ለማቅረብ/ከእርሱ ጋር ለመከራከር ቃላት ልመርጥ አልችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 9:16-18

በአውሎ ነፋስ ሰብሮኛልና

ኢዮብ ከእግዚአብሔር ዘንድ የመጣበትን መከራ ከአውሎ ነፋስ ተጽዕኖ ጋር ያነጻጽረዋል፡፡ "በአውሎ ነፋስ እንደተጎዳሁ ጎድቶኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አውሎ ነፋስ

ጥቃት የሚያደርስ ሀያለኛ ነፋስ

ቁስሌን አበዛው

"ብዙ ቁስሎች አደረገብኝ" ወይም "ደጋግሞ አቆሰለኝ"

ያለ ምክንያት

"ምንም እንኳን እንዲህ እንዲያደርግ የሚያበቃ ጥፋት ባልሰራም" ወይም "ምንም እንኳን ንጹህ ብሆንም"

ትንፋሽ እንዳገኝ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን ትርጉሙ "ደግሜ መተንፈስ እንድችል" (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ በመራራነት ሞላኝ

ይህ ቁጥር እግዚአብሔር የኢዮብን ህይወት እንዲመረር በሚያደርጉ ነገሮች እንደሞላው ይናገራል፡፡ "መራርነት" የሚለው ረቂቅ ስም "መራራ" በሚለው ቅጽል ሊገለጽ ይችላል፡፡ "በመራራ ነገሮች ሞላኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 9:19-20

ይህ የጥንካሬ ጉዳይ ቢሆንም

"የጥንካሬ መፎካከሪያ ቢኖርም"

እነሆ፣ እርሱ ታላቅ ነው

"ተመልከት እርሱ ታላቅ መሆኑን ትረዳለህ" ወይም "እኔ ልነግርህ ለተዘጋጀሁት ነገር ትኩረት ስጥ፡ እርሱ ታላቅ ነው"

እርሱ ታላቅ ነው

"እርሱ ከሁሉ ታላቅ ነው"

ለእርሱ ማን የክስ መጥሪያ ሊያቀርብለት ይችላል?

ይህ ጥያቄ "ከቶ ማንም" የሚል ምላሽ እግዚአብሔርን ወደ ፍርድ ቤት ሊያቀርበው አይችልም የሚል ምላሽ ያሰጣል፡፡ ይህ በገለጻ መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ማንም ለእርሱ መጥሪያ ሊያቀርብለት አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡(ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ምንም እንኳን ጻድቅ/ትክክለኛ ብሆንም፣ የገዛ አንደበቴ ይፈርድብኛል፤ እንከን የለሽ ብሆንም ቃሎቼ ይኮንኑኛል፡፡

ይህ ሀረግ ተመሳሳይ ሃብን ሁለት ጊዜ ደግሞ በማቅረብ አጽንኦት ይሰጣል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ትክክለኛ/ጻድቅ ብሆንም

እዚህ ስፍራ "እኔ ትክክለኛ ነኝ" የሚለው ትክክለኛ የሆነውን ያረግኩት እኔ ነኝ ማለት ነው፡፡ "ምንም እንኳን ትክክለኛ ነገሮችን ባደርግም" ወይም "ምንም እንኳን እኔ ንጹህ ብሆንም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ስማዊ ቅጽሎች የሚሉትን ይመልከቱ)

የገዛ አንደበቴ ይኮንነኛል/በደለኛ ያደርገኛል

እዚህ ስፍራ "አንደበት" የሚለው የኢዮብን ቃላት ነው፡፡ "የራሴ ቃላት ይከሱኛል" ወይም " የተናገርኩት ይኮንነኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ነውር ባይኖርብኝም

"ጥፋት/እንከን ባይኖርብኝም"

የራሴ ቃሎች ጥፋተኛ መሆኔን ያሳያሉ

እዚህ ስፍራ "የራሴ ቃሎች" የሚለው የተገለጸው ቃላቶቹ ራሳቸው እርምጃ መውሰድ እንደሚችሉ ተደርጎ ነው፡፡ "እግዚአብሔር እኔ የተናገርኩትን የእኔኑ ጥፋተኝነት ለማረጋገጥ ይጠቀምበታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ጥፋተኛ

እዚህ ስፍራ ይህ ቃል "ገልበጥባጣ" ወይም "ጠማማ" የሚል ትርጉም አለው፡፡

Job 9:21-24

እኔ ነውር አልባ ነኝ

"እኔ ጥፋት የለብኝም"

ስለ ራሴ

"በእኔ ላይ የደረሰው"

ምንም ልዩነት አያመጣም

"ልዩነት የለውም" ወይም "ምንም ማለት አይደለም"

ጥፋት የሌለበትን እና ንጹሁን ሰው በአንድነት ያጠፋል

እዚህ ስፍራ "ነውር/ጥፋት የሌለበት" እና "ክፉ" የሚሉት ቃላት በመሃል ያሉትን ሁሉ የሚያካትት ሁለት ጽንፍ ነው፡፡ "እንከን የሌለውን እና ክፉውንም ሁሉንም ወደ ፍጻሜ ያመጣል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጽንፍ የሚለውን ይመልከቱ)

መቅሰፍት በድንገት ሲገድል

እዚህ ስፍራ "መቅሰፍት" የሚለው ቃል ለማኛቸውም አይነት ጥፋት ዘይቤ ነው፡፡ "በእንገት ጥፋት ሲደርስ እና ሰዎች ሞቱ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (በ [[፡en: at: vol1: translate: figs-metaphor]] ተመልከቱ)

የንጹህ ሰው ተስፋ መቁረጥ

"ተስፋ መቁረጥ" የሚለው ቃል ረቂቅ ስም ሲሆን "ተስፋ ቆረጠ" በሚለው ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ እዚህ ስፍራ ተስፋ እየቆረጠ ለሚገኝ ንጹህ ሰው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "ተስፋ የቆረጡ ንጹሀን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (በ [[፡en: at: vol12: translate: figs-metonymy]] ተመልከቱ)

ንጹህ

ይህ ስማዊ ቅጽል ነው፡፡ "ንጹህ ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (በ [[፡en: at: vol2: translate: figs-nominalized]] ተመልከቱ)

ምድር ተሰጥታለች

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር ምድርን ሰጠ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ምድር

እዚህ ስፍራ "ምድር" የሚለው የሚወክለው በምድር ላይ የሚኖሩ ዎችን ነው፡፡ "የዓለም ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በ…እጅ ውስጥ

እዚህ ስፍራ "እጅ" "መቆጣጠር ለሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "በ…ቁጥጥር ስራ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር የፈራጆቿን ፊት ሸፍኗል

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር እግዚአብሔር የምድር ፈራጆችን/ዳኞችን እውነት እና ሀሰት በሆነው መሃል መለየት እንዳይችሉ ከልክሏቸዋል፡፡ "እግዚአብሔር ፈራጆቿን አሳውሯል" ወይም "እግዚአብሔር ፈራጆቿ/ዳኞቿ በትክክል እንዳይፈርዱ ከልክሏቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ይህንን ያደረገው እርሱ ካልሆነ፣ ታዲያ ይህንን ያደረገው ማን ነው?

"እነዚህን ነገሮች ያደረገው እግዚአብሔር ካልሆነ፣ ማን አደረጋቸው ይባላል?"

Job 9:25-26

ቀኖቼ ከሯጭ መልዕክተኛ ይልቅ ፈጣኖች ናቸው

ኢዮብ ቀኖቹ እንዴት በፍጥነት እያለፉ እንደሆነ የገለጸው ከፈጣን ሯጭ ጋር በማወዳደር ነው፡፡ "ቀኖቼ በፍጥነት ያልፋሉ" (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሯጭ መልዕክተኛ

"ሯጭ" ወይም "የሚሮጥ ሰው"

ቀናቶቼ ይበራሉ

ይህ የኢዮብ የህይወቱ ቀናት እንደ ሰው መሮጥ እንደሚችል ተደርጎ ተስሏል፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የትም ስፍራ መልካምን ማየት አልቻሉም

ይህ የኢዮብን የህይወቱን ቀናት እንደ ሰው የሚያዩ ሆነው ተስለዋል፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አንዳች መልካም

"አንዳች መልካም ነገር"

እንደ ደንገል ታንኳ ፈጣኖች ናቸው

ኢዮብ ቀኖቹ እንዴት በፍጥነት እያለፉ እንደሆነ ከፈጣን ታንኳ ፍጥነት ጋር ያነጻጽራል፡፡ "እንደ ደንገል ታንኳ በፍጥነት ያልፋሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የቄጠማ ደንገል ታንኳ

"ከቄጤማ የተሰራ ታንኳ፡፡" ደንገል ቄጠማ ውስጡ ክፍት የሆነ በወንዝ ዳርቻ የሚበቅል ሳር መሰል ተክል ነው፡፡

ንስር ወደ ሚያድነው በፍጥነት ቁልቁል እንደሚወርድ

ኢዮብ ቀናቱ እንዴት በፍጥነት እንደሚያልፉ ትልቁ ወፍ ንስር ወደሚያድነው ነገር ቁልቁል እንዴት እንደሚወረወር በማነጻጸር ይናገራል፡፡ "ንስር ምግቡን ለማግኘት/ለመያዝ ከላይ ቁልቁል በፍጥነት ወደ ታች እንደሚወርድ/እንደሚበር" (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በፍጥነት ወደታች መውረድ

"በፍጥነት ቁልቁል መውረድ"

Job 9:27-29

ስለ ማማርርባቸው ነገሮች እረሳለሁ

"ምሬት" የሚለው ረቂቅ ስም "ማማረር" በሚለው ግስ መተርጎም ይችላል፡፡ "ማማረሬን አቆማለሁ" ወይም "በእግዚአብሔር ላይ ማማረሬን አቆማለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ማማረሬን

ኢዮብ በማን ላይ እንደሚያማርር በግልጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "በእግዚአብሔር ላይ ማማረሬን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ሃዘንተኛ ፊቴን መልሼ ደስተኛ እሆናለሁ

የኢዮብ ሀዘንተኛ ገጽ የተገለጸው አንድ ዞር ሊደረግ እንደሚችል ነገር ተደርጎ ነው፡፡ ሀዘንተኛ ሆኜ መታጠቴን አቁሜ ፈገግ እላለሁ፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሀዘኖቼ ሁሉ ያስፈሩኛል

ኢዮብ በቁጥር 27 የተናገረውን ቢያደርግ ሊከተል የሚችለውን ውጤት ቁጥር 28 እና 29 ይገልጻሉ፡፡ ይህ "ከዚያ" የሚለውን ቃል በመጨመር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ከዚያም ከሀዘኖቼ ሁሉ የተነሳ እፈራለሁ" (አያያዝ ቃለት/መስተጻምር የሚለውን ይመልከቱ)

ከሀዘኔ ሁሉ የተነሳ

"ሀዘን" የሚለው ረቂቅ ስም በግስ መልኩ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ከጎዱኝ ነገሮች ሁሉ የተነሳ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

እኮነናለሁ

"ተጠያቂ እሆናለሁ ደግሞም እቀጣለሁ፡፡" ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር ይፈርድብኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይምተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ታዲያ ስለምን በከንቱ እደክማለሁ?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የሚጠቀመው የእግዚአብሔርን ፊት ለማግኘት የሚያደደርገው ሙከራ ምንም ጥቅም እንደማያስገኝለት ማሰቡን በትኩረት ለመግለጽ ነው፡፡ ኢዮብ ሊያደርግ እየሞከረ ስለሚገኘው ነገር በውስጠ ታዋቂነት የሚገኘው መረጃ ግልጽ ሊደረግ ይቻላል፡፡ "የእግዚአብሔርን ፊት ለማግኘት መሞከሬ አንዳች ጥቅም የለውም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 9:30-31

ፊቴን በበረዶ ውሃ ብታጠብ እንኳን

"ሰውነቴን በንጹህ፣ የተራ ውሃ ብታጠብ"

የበረዶ ውሃ

ከሟሟ በረዶ የተገኘ ውሃ

በረዶ

ከደመና የሚወርድ የአየር ጸባዩ ቀዝቃዛ በሆነ ቦታ የሚወርድ ደቃቅ የቀዘቀዘ ውሃ

እጆቼን እጅግ ባነጻ

"እጆቼን ፍጹም ባነጻ፡፡" አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች "በጣም ጠንካራ በሆነ ሳሙና እጆቼን ባነጻ" ብለው ይተረጉሙታል፡፡

በዘአቅት ውስጥ ታሰምጠኛለሁ

"ወደ ጉድጓድ ትወረውረኛለህ"

የገዛ ልብሶቼ ይጸየፉኛል

እግዚአብሔር ወደ ጉድጎድ ከጣለው በኋላ የኢዮብ ልብሶች የተገለጹት ለኢዮብ አሉታዊ ምላሽ እንዳላቸው ተደርጎ ነው፡፡ "ገዛ ልብሶቼ እጅግ ይጸየፉኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 9:32-33

እመልስለታለሁ

ኢዮብ እግዚአብሔር ስህተት ሰርተሃል ብሎ እንደከሰሰው ያመለክታል፣ እርሱም ለክሶቹ መልስ መስጠት እንደሚፈልግ ይናገራል፡፡ "ላቀረበብኝ ክስ ምላሽ እንድሰጥ" ወይም "እራሴን እንድከላከል" ወይም "ከእርሱ ጋር ስለ ንጹህነቴ እንድከራከር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

አብረን ወደ ፍርድ/ችሎት እንግባ

"ወደ ፍርድ/ችሎት አብረን እንግባ፡፡" እዚህ ስፍራ "ፍርድ ቤት" የሚለው ሰዎች ቀርበው ዳኛ ለክርክራቸው መፍት የሚሰጥበትን ቦታ ነው፡፡ "አብሮ ወደ ፍርድ ቤት መግባት" እርስ በእርስ ተካሶ ወደ ፍርድ ቤት መሄድን የሚያመለክት ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "እውነቱ እንዲወጣ በዳኛ ፊት አንዱ ከሌላው ጋር መከራከር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በመካከላችን ዳኛ የለም

ይህ ማለት በኢዮብ እና በእርሱ መሃል ከእግዚአብሔር የሚበልጥ ምን ትክክል እንደሆነ ሊወስን የሚችል ዳኛ የለም ማለት ነው፡፡

በሁለታችንም ላይ እጁን የሚጭን

እዚህ ስፍራ "እጁን የሚጭን" ማለት የበለጠ ስልጣን ወይም ሃይል ያለው ማለት ነው፡፡ "እጁን በሁለታችንም ላይ የሚያኖር" ወይም "በሁለታችንም ላይ ስልጣን ያለው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 9:34-35

አያያዥ ሃሳብ፡

እነዚህ ቁጥሮች በኢዮብ እና በእግዚአብሔር መካከል ገብቶ ሊዳኝ የሚችል ከእግዚአብሔር የሚበልጥ ማንም እንደሌለ ቀደም ሲል የቀረበውን ክርክር ይቀጥላሉ

የአግዚአብሔርን በትር ከእኔ ውሰድ

እዚህ ስፍራ "የእግዚአብሔር በትር" የሚለው እግዚአብሔር ኢዮብን መቅጣቱን ወይም ማረሙን የሚገልጽ ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "እግዚአብሔር እኔን መቅጣቱ ይቁም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ማስፈራራቱ ከእኔ ይቁም

"ፍርሃት" የሚለው ረቂቅ ስም "አስፈራራ" በሚል ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "እርሱ እኔን ማስፈራራቱን እና ማስፈራቱን ማን ባስቆመልኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ከዚያ እኔም እናገራለሁ

"ቀጥሎ እናገራለሁ"

ነገሮች አሁን ባሉበት

"ምክንያቱም አሁን ነገሮች እንዲህ ናቸውና"

Job 10

Job 10:1-3

ህይወቴ ዝላለች

"መኖር ሰልችቶኛል/ደክሜያለሁ"

የማማርርበትን ምክንያት በግልጽ እናገራለሁ

"መግለጽ" እና "ማማረር" የሚሉት ረቂቅ ስሞች "ገለጸ" እና "አማረረ" በሚሉ ግሶች ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ "የማማርርበትን ነገር በግልጽ እናገራለሁ" ወይም "በግልጽ እከራከራለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

በነፍሴ ምሬት እናገራለሁ

ኢዮብ እንዴት እንደተሰማው የተገለጸው የተነጻጸረው ከመራራ ጣዕም ጋር ነው፡፡ "መራርነት" የሚለው ረቂቅ ስም "በመራርነት" በሚለው ተውሳከ ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ውስጣዊ ማንነቴ በመራርነት ይናገራል" ወይም "እኔ በመራርነት እናገራለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)

እኔን መጨቆንህ ለአንተ መልካም ነገር ማድረግ ነውን፣ በክፉዎች እቅድ ፈገግ እያልክ የእጆችህን ስራዎች መናቅህስ መልካም ነውን?

ይህ ጥያቄ "አይደለም" የሚል ምላሽ ይጠበቅበታል፤ ደግሞም በገለጻ መልክ ሊቀርብ ይችላል፡፡ "በክፉዎች ስራ ፈገግ እያልክ፣ እኔን መጨቆንህ መልካም አይደለም፤ የእጆችህን ስራ መናቅህ ትክክልአይደለም፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይልከቱ)

የእጆችህ ስራዎች

እዚህ ስፍራ እግዚአብሔር የተወከለው በእርሱ "እጆች" ነው፡፡ "አንተ የፈጠርከው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

በክፉዎች እቅድ ይስቃል

እዚህ ስፍራ "ይስቃል" የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር የሚወክለው የእግዚአብሔርን መስማማት፡፡ "የክፎዎችን እቅድ ያጸድቃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 10:4-7

የስጋ ዐይን አለህን? ሰው እንደሚያይ ታያለህን?

እነዚህ ሁለት ጥያቄዎች ታራራቢ ትርጉም አላቸው፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች እግዚአብሔር ሰው እንደማያይ ወይም ሰው በሚረዳበት መንገድ ነገሮችን እንደማይረዳ ትኩረት ለመስጠት አሉታዊ ምላሽ ይጠብቃሉ፡፡ ጥያቄዎቹ በገለጻ መልክ ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ "አንተ የስጋ ዐይን የለህም፣ አንተ ሰው እንደሚያይ አታይም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚሉትን ይመልከቱ)

የአንተ ቀኖች እንደ ሰው ቀናት ናቸውን ወይስ የአንተ አመታት እንደ ሰው አመታት ናቸው… ደግሞም ከእጆችህ የሚያድነኝ ማንም የለም?

እነዚህ ጥያቄዎች እግዚአብሔር ዘለዓለማው መሆኑን እና የሰው ዘመን ጥቂት መሆኑን ትኩረት ለመስጠት አሉታዊ ምላሽ ይጠብቃሉ፡፡ ይህ በገለጻ መልክ ሊቀርብ ይችላል፡፡ "የአንተ ቀናት እንደ ሰው ቀናት አይደሉም የአንተ አመታት እንደ ሰው አመታት አይደሉም…ደግሞም ከአንተ እጅ የሚያድነኝ ማንም የለም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

የአንተ ቀናት እንደ ሰው ቀናት…የአንተ አመታት እንደ ሰው አመታት

እነዚህ ሁለት ሀረጋት ተቀራራቢ ትርጉም አላቸው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የአንተ ቀናት

"የአንተ ቀናት ቁጥር"

የአንተ አመታት

"የአንተ አመታት ቁጥር"

በእኔ ስሀተት ላይ ጥያቄ ታነሳለህ… ኃጢአቴን ትከታተላለህ

እነዚህ ሁለት ሀረጋት ተቀራራቢ ትርጉም አላቸው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጥያቄ ታነሳለህ

"ትከታተለኛለህ"

ከእጆችህ

እዚህ ስፍራ "እጆችህ" የሚለው የሚወክለው የእግዚአብሔርን ሀይል ነው፡፡ "ከአንተ ሃይል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 10:8-9

የአንተ እጆች

እዚህ ስፍራ "እጆች" የሚለው የሚወክለው የእግዚአብሔርን እና የእርሱን የመፍጠር ድርጊት ነው፡፡ "አንተ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

የአንተ እጆች አበጁን ሰሩኝም

ኢዮብ እግዚአብሔር እንዴት በጥንቃቄ እርሱን እንደፈጠረው ለመግለጽ ሸክላ ሰሪ ሸክላውን የሚያበጅበትን አሰራር በዘይቤ ይጠቀማል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አበጀኝ ሰራኝም

"ቅርጽ ሰጠኝ ሰራኝ" "ቅርጽ ሰጠኝ" እና "አበጀኝ" የሚሉት ቃላት በትርጉም ተመሳሳይ ናቸው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

ልብ በል

"አስታውስ"

ዳግም ወደ አፈር አምጣኝ

"እንደገና ወደ አፈር መልሰኝ"

Job 10:10-11

አጠቃላይ መረጃ፡

በእነዚህ ሀረጋት፣ ኢዮብ እግዚአብሔር እንዴት በእናቱ ማህጸን ውስጥ እንዳበጀመው ለመግለጽ የሸክላ ሰራተኛን ቋንቋ ይጠቀማል፡፡ (ስነ ግጥም የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ወተት አላፈሰስከኝምን፣ እንደ እርጎስ አላረጋኸኝምን?

ይህ አዎንታዊ ምላሽ የሚጠብቅ ጥያቄ ነው፡፡ "እንደ ወተት አፈሰስከኝ እንደ እርጎ አረጋኸኝ" ወይም "ፈሳሽ ወተት እርጎ እንደሚሆን በማህጽን አበጀኸኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

አንተ

እዚህ ስፍራ "አንተ" የሚለው የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ነው

እኔ

እዚህ ስፍራ "እኔ" የሚለው የሚያመለክተው ኢዮብን ነው፡፡

ቆዳ እና ስጋ አለበስከኝ

እግዚአብሔር የኢዮብን አካል በቆዳ እና ስጋ መሸፈኑ የተገለጸው እግዚአብሔር ኢዮብን እንዳለበሰው ተደርጎ ነው፡፡ "ሰውነቴን በቆዳ እና ስጋ ሸፈንክ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በአንድነት አገጣጠምከኝ

"በአንድነት ሸመንከኝ፡፡" እግዚአብሔር የኢዮብን አካል በማህጸን ማዋደዱ የተገለጸው እግዚአብሔር ጨርቅን እንደሸመነ ተደርጎ ነው፡፡ "አዋደድከኝ/በአንድነት አደረግከኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ጅማቶች

ጡንቻን ከአጥንት ወይም ከሌላ የሰውነት ክፍል ጋር የሚያያይዝ እና ነጭ ጠንካራ ማስተሳሰሪያ

Job 10:12-14

ህይወት እና የቃል ኪዳን ታማኝነት ሰጠኸኝ

"ህይወት" እና "ታማኝነት" የሚሉት ረቂቅ ስሞች "ህያው" እና "ታማኝ" በሚል ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ "አንተ ለቃል ኪዳንህ ታማኝ ነበርክ ደግሞም ህያው እንድሆን ፈቅደሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስያሜ የሚለውን ይመልከቱ)

የአንተ እርዳታ

"የአንተ እንክብካቤ"

መንፈሴን ጠበቀ

እዚህ ስፍራ ኢዮብ የተወከለው "በመንፈሱ" ነው፡፡ "ጠበቅከኝ" ወይም "እኔን በጥንቃቄ ተመለከትክ" ወይም "በደህንነት/በሰላም ጠበቅከኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

እነዚህ አንተ በልብህ የሰወርካቸው ነገሮች

እዚህ ስፍራ "እነዚህ ነገሮች" የሚለው የሚያመለክተው ከተከታዩ ቁጥር ላይ የሚገኘውን ነገር ነው

እነዚህ አንተ በልብህ የሰወርካቸው ነገሮች

እዚህ ስፍራ "አንተ በልብህ የሰወርካቸው" ማለት እግዚአብሔር ምስጢር አድርጓቸዋል ወይም ደብቆታል ማለት ነው፡፡ "አንተ ምስጢር ያደረካቸው እነዚህ ነገሮች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ ታውቀዋለህ

"አንተ ትጠብቀኛለህ"

Job 10:15-16

በክፋት አንድ ነገር ባደርግ

"ክፉ ነገሮቸን ባደርግ"

ወዮው ለእኔ

"ለእኔ ይህ እደምን መጥፎ ይሆናል"

ራሴን ቀና ባደርግ

ይህ ፈሊጥ እርግጠኛ ወይም ልበ ሙሉ መሆን ማለት ነው፡፡ "ራስን ቀና ባደርግ" ወይም "ልበ ሙሉ መሆን" ወይም "ስለ ራሴ እርግጠኛ ብሆን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በሀፍረት ተሞላሁ - መከራዬን ተመልከት

ሌላው ሊሰጥ የሚችል ትርጉም፣ "ውርደት ተሞልቻለሁ በመከራዬ ተይዣለሁ"፡፡ ውርደቱ መጥፎ ሆነ ሳለ መከራው ደግሞ የከፋ ነው፡፡

በውርደት ተሞልቻለሁ

"ሙሉ ለሙሉ አፍሬያለሁ" ወይም "ከዚህ በኋላ የሚያከብረኝ ማንም አይኖርም"

ውርደት

ሀፍረት

የደረሰብኝን ውርደት ተመልከቱ

"ተዋረደ" የሚለው ረቂቅ ስም "ውርደት" በሚለው ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር እንዴት እንዳዋረደኝ ተመልከቱ" (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ራሴን ቀና ባደርግ፣ አንተ እንደ አንበሳ ታደባብኛለህ

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1)ይህ ያልሆነ መላምታዊ ሁኔታ ነው ወይም 2) ይህ በተደጋጋ የተፈጸመ ሁኔታ መግለጫ ነው፡፡ "ራሴን ቀና ሳደርግ፣ እንደ አንበሳ ታደባብኛለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (መላምታዊ ሁኔታ የሚለውን ይመልከቱ)

ራሴ ቀና ባደርግ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር በራስ መተማመን ወይም ኩራት ማለት ነው፡፡ "ብኮራ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ከባለቤቱ ጋር የሚጣቀስ ተውላጠ ስም የሚለውን ይመለከቱ)

Job 10:17

አንተ በእኔ ላይ አዲስ ምስክር ታመጣለህ

ኢዮብ ከእግዚአብሔር ዘንድ የሚደርስበት መከራ የተገለጸው በእርሱ ላይ ምስክር የሚሆኑ ሰዎች እንደሆኑ ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በእኔ ላይ ቁጣህ ይጨምራል

"ቁጣ" የሚለው ረቂቅ ስም "ቁጡነት" በሚል ቅጽል ሊተረጎም ይችላል፡፡ "በእኔ ላይ ቁጡነቱ እየጨመረ መጣ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

በአዲስ ሰራዊት/ሀይል ታጠቃኛለህ

እግዚአብሔር ወደ ኢዮብ መከራ መላኩ የተገለጸው እግዚአብሔር ሳያቋርጥ በኢዮብ ላይ አዲስ ሰራዊት እንደሚልክ ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 10:18-19

ከማህጸን አወጣኸኝ

እዚህ ስፍራ ከማህጽን ማውጣት የሚወክለው ወደዚህ ዓለም መምጣትን/መወለድን ነው፡፡ "ከእናቴ ማህጽን አወጣኸኝ" ወይም "ወደዚህ ዓለም አመጣኸኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

መንፈሴን እሰጣለሁ

አንድ ሰው መንፈሱን መስጠቱ የሚወክለው መሞትን ነው፡፡ "ሞተ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ዐይኖች ለዘለአለም አይመለከቱኝም

እዚህ ስፍራ ኢዮብ "ዐይን" የሚለውን የተጠቀመበት ሰውን ሁሉ ለመጥቀስ ነው፡፡ ማንም ሰው ከማየቱ አስቀድሞ በተወለደበት ጊዜ ቢሞት ይመኛል፡፡ " አስቀደሞ ማንም ሰው ሳይመለከተኝ" ወይም "ከመወለዴ አስቀድሞ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ያልተፈጠርኩ ያህል ነው

"በፍጹም አልኖርኩም"

በወሰዱኝ ኖሮ/ወደ መቃብር

"አካሌ ወደ መቃብር ይወሰድ ነበር"

Job 10:20-22

ቀኖቼ ጥቂት አይደሉምን?

እዚህ ስፍራ "ቀኖቼ" የሚለው የሚወክለው የኢዮብን የህይወት ዘመን መጠን ነው፡፡ ይህ ጥያቄ ኢዮብ ጥቂት የቀናት እድሜ ብቻ እንዳለው ለማጉላት አዎንታዊ ምላሽ ይጠብቃል፡፡ ይህ በገለጻ መልክ ሊቀርብ ይችላል፡፡ "ከእንግዲህ በህይወት ለመቆየት የቀሩኝ ጥቂት ቀናት ብቻ ናቸው" ወይም "ህይወቴ በቅርቡ ያበቃለታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ምድሩ

እዚህ ስፍራ የሞቱ ሰዎች መንፈስ የሚሄድበት ቦታ የተገለጸው ምድር እንደሆነ ተደርጎ ነው፡፡ "ስፍራው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ጨለማው እና የሞት ጥላው

"የሞት ጥላ" የሚለው ሀረግ "ጨለማ" የሚለውን ሀሳብ ያጠናክራል፡፡ ሁለቱም ሀረጎች የሞቱ ሰዎች መንፈስ ወዴት እንደሚሄድ ይገልጻሉ፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

የሞት ጥላ

ይህ በኢዮብ 3፡5 ላይ እንዴት እንደተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

እንደ እኩለ ለሊት የጨለመ

የሞቱ ሰዎች መንፈስ የሚሄድበት ስፍራ ጥቁረት የተነጻጸረው ከእኩለ ለሊት ጨለማ ጋር ነው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ያለ አንዳች ስርአት

ይህ አሉታዊ ሀረግ በአዎንታዊ መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ግራ በመጋት የተሞላ" ወይም "ሁሉም ግራ የተጋባበት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ምፀት/ላይዶክስ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ እኩለ ለሊት የጨለመ

የሞቱ ሰዎች ነፍስ የሚሄድበት ስፍራ መጨለም የተነጻጸረው ከእኩ ለሊት ጋር ነው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 11

Job 11:1-3

ነዕማታዊው ሶፋር

ይህ ስም በኢዮብ 2፡11 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ "ከነዕማታ ግዛት የሆነው ሶፋር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደዚህ የበዙ ጥያቄዎች/ቃላት መልስ ሊያገኙ አይገባምን?

ሶፋር ጥያቄውን በአሉታ የሚያቀርበው የኢዮብ ቃላት/ንግግር መገታት አለበት የሚለውን ለማጉላት ነው፡፡ "ለእነዚህ ንግግሮች ሁሉ እኛ መልስ ልንሰጥ ይገባል!" ወይም "አንድ ሰው ለዚህ ሁሉ ንግግር መልስ መስጠት ይኖርበታል!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ እንዲህ ንግግር የሚያበዛ ሰው ሊታመን ይገባዋልን?

ሶፋር ይህንን ጥያቄ የሚጠቀመው ኢዮብ የሚናገረውን ማመን እንደማይኖርባቸው ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "ይህ ሰው በንግግር የተሞላ ነው፣ ነገር ግን ሰዎች ሊያምኑት አይገባም!" ወይም "ብዙ ንግግርህ ብቻውን አንተ ንጹህ መሆንህን አያሳይም!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

የአንተ መዘላበድ ሌሎች ዝም እንዲሉ ያደርጋልን?

ሶፋር ይህንን ጥያቄ የሚጠቀመው ኢዮብን ለመገሰጽ ነው፡፡ "አንተ ብዙ ስለተናገርክ ብቻ፣ ሌሎች ዝም ማለት አለባቸው ማለት አይደለም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ስትቀልድ፣ እንድታፍር የሚያደርግህ ሰው የለምን?

ሶፋር ይህንን ጥያቄ የሚጠቀመው ኢዮብን ለመገሰጽ ነው፡፡ ኢዮብ ቀለደ የተባለውን ይበልጥ ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ "እኛ በተናገርነው ላይ አንተ ትቀልዳለህ/ታሾፋለህ፡፡ አሁን እኛ አንተን እናሳፍርሀለን!" (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን እና (በ [[፡en: at: vol1: translate: figs-explicit]] ተመልከቱ)

Job 11:4-6

እምነቴ ንጹህ ነው

"መረዳቴ ትክክል ነው"

በአንተ ዐይኖች ንጹህ ነኝ

ዐይኖች አመለካከትን ይወክላል፣ ይህም እግዚአብሔርን የሚመዝንበት ዘይቤያዊ አነጋገር ነው፡፡ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ኢዮብ እግዚአብሔር ነውር አልባ አድርጎ እንደሚያየው መናገሩ፡፡ "አንተ ነውር እንደሌለብኝ ትናገራለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው ወይም 2) ኢዮብ ነውር እንደሌለበት እግዚአብሔር እንደሚፈርድላት እንደሚያምን፡፡ "እኔ ነውር/ እንከን እንደሌለብኝ እውቅና መስጠት ይገባሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር እንዲህ ይናገራል… ከንፈሩን ከፍቶ በእናንተ ላይ ይናገራል

"ከንፈሩን ይከፍታል" የሚሉት ቃላት ንግግር ለሚለው ሜቶኖሚ /ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ እነዚህ ሁለት ሀረጋት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ በአንድነት ሆነው ሶፋር እግዚአብሔር በኢዮብ ላይ በሀይል ይናገራል የሚለውን ፍላጎቱን ያጎላሉ፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

እርሱ የሚያሳየው… የጥበብ ምስጢር

"የጥበብ ምስጢር" የሚለው በግልጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "በኃጢያትህ ምክንያት መከራን እንደምትቀበል ያስረዳሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ከአንተ የሚጠብቀው/ለአንተ የከፈለው/ ለኃጢአትህ ከሚገባህ ያነሰውን ነው

ከኢዮብ የሚጠበቀው የሚለው የሚወክለው የኢዮብን መቅጣትን ነው፡፡ "እግዚአብሔር እየቀጣህ ያለው ልትቀጣ ከሚገባህ ያነሰውን ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 11:7-9

እግዚአብሔርን በመፈለግ ልትረዳው ትችላለህ/መርምረህ ትደርስበታለህ? ሁሉን ቻይ የሆነውን ሙሉ ለሙሉ ልታውቀው ትችላለህ?

እነዚህ ሁለት ትይዩ ጥያቄዎች ተመሳሳይ ነገርን ይጠይቃሉ፡፡ ጸሐፊው የጥያቄ መልክን የተጠቀመው ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "እግዚአብሔርን በመመርመር/በመፈለግ እርሱን መረዳት አትችልም፣ ሁሉን ቻይ የሆነውን ሙሉ ለሙሉ ልትረዳው አትችልም!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚሉትን ይመልከቱ)

ጉዳዩ

ይህ እግዚአብሔርን ማወቅ/ መረዳትን ያመለክታል፡፡ "እግዚአብሔርን ማወቅ/መረዳት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ መንግስተ ሰማይ ሩቅ ነው…ከሲኦል ይጠልቃል

እግዚአብሔርን መረዳት አለመቻል ወደ እነዚህ እጅግ ሩቅ ወደሆኑ ስፍራዎች መሄድ እንደማይቻለው አይነት ተደርጎ ተነግሯል፡፡ "በሰማይ ወዳለው ከፍ ያለ ስፍራ እንደማይደረስ… በሲኦል ካዳለው ጥልቅ ስፍራ ይልቅ የማይደረስበት ነው" (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ምን ማድረግ ትችላለህ?

ሶፋር ይህንን ጥያቄ የተጠቀመው አንድ ሰው እግዚአብሔርን ሙሉ ለሙሉ ለመረዳት አንዳች ነገር ማድረግ አይችልም የሚለውን ለማሳየት ነው፡፡ "አንዳች ነገር ማድረግ አትችልም" ወይም "በዚያ መታወቅ ያለበትን ሁሉ ማወቅ አትችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

መጠኑ

ይህ ሊያመለክት የሚችለው አማራጭ ትርጉሞች 1) የእጋዚአብሔርን ታላቅነት 2) የእግዚአብሔርን ጥበብ ታላቅነት

ከምድር ይረዝማል… ከባህር ይሰፋል

የእግዚአብሔር ታላቅነት ወይም ጥበብ የተገለጸው በርቀት እንደሚለካ ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 11:10-12

እርሱ.. በማንንም ላይ ቢዘጋ

"እግዚአብሔር… ማንንም በእስርቤት አስገብቶ ቢዘጋበት"

ማንንም ወደ ፍርድ ቢጠራ/ቢሰበስብ

"ፍርድ" የሚለው ረቂቅ ስም "ዳኘ" በሚል ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "አግዚአብሔር ሊፈርድበት ፈልጎ ማንንም ወደ እርሱ ቢጠራ/ቢሰበስብ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ማን ሊያስቆመው ይችላል?

ይህ ጥያቄ ማንም እግዚአብሔርን ማስቆም እንደማይችል ትኩረት ይሰጣል፡፡ "ማንም ሊያስቆመው አይችልም!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ይህን አያስተውልምን?

ይህ እግዚአብሔር ኃጢአትን እንደሚያይ ትኩረት ይሰጣል፡፡ "እርሱ በእርግጥ ይህንን ያያል!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ሞኝ ሰዎች ግን ማስተዋል/መረዳት የላቸውም

"መረዳት" የሚለው ረቂቅ ስም "ተረዳ" በሚለው ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ሞኝ ሰው ግን ይህንን አይረዳም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

የሜዳ አህያ ሰው ሲወልድ እነርሱ ይህን መረዳት ይችላሉ

የሜዳ አህያ በፍጹም ሰው መውለድ እንደማይችል ሁሉ ሞኝ ሰውም ይህን መረዳት ማግኘት አይችልም፡፡ "የሜዳ አህያ ሰው ከወለደ ብቻ ያን ጊዜ ሞኝ ሰው መረዳትን/ጥበብን ያገኛል" ወይም "አህያ ሰው ሊወልድ አንደማይችል ሁሉ ሞኝ ሰውም መረዳት/ጥበብን ማግኘት አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 11:13-14

ምናልባት ልብህን ቀና ብታደርግ

ልብ የሚወክለው አስተሳሰብን እና ዝንባሌን ነው፡፡ ልብን ማስተካከል የሚለው የሚወክለው ልብን ማረምን ነው፡፡ "ዝንባሌህን ብታስተካክል እንኳን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እጅህን ወደ እግዚአብሔር ብትዘረጋ

ይህ እግዚአብሔርን እርዳታ መጠየቅን የሚወክል ድርጊት ነው፡፡ "ወደ እግዚአብሔር ጸልይ ወደ እርሱ ልመናህን አቅርብ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

ምናልባት ያ ኃጢአት በእጅህ ይገኛል

እጅ የሚወክለው እንድ ሰው የሚያደርገውን ነገር ነው፡፡ "ባለፈው ዘመን ክፉ ነገር አድርገህ ቢሆን እንኳን" ሚለው ውሰጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ነገር ግን ከዚያ በኋላ ይህንን ከአንተ ታርቃለህ

ኃጢአትን ከኋላ መተው የሚወክለው ኃጢአትን መስራትን ማቆምን ነው፡፡ "ነገር ግን ከዚያ በኋላ ክፉ ነገሮችን ማድረግ ታቆማለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እርክሰት በድንኳንህ እንዲኖር አትፍቀድ

እርክሰት እንዲኖር የሚለው የሚወክለው ጽድቅ ያልሆነ ነገር የሚያደርጉ ሰዎችን ነው፡፡ "በቤትህ የሚኖሩ የረከሱ ነገሮችን እንዲያደርጉ አትፍቀድ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 11:15-17

ያለ ሀፍረት ምልክት ፊትህን ወደ ላይ አንሳ

"ፊትህን ወደ ላይ አንሳ" የሚለው የሚወክለው ልበ ሙሉ እና ጀግና የሆነ ሰውን ዝንባሌ ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

እንዳለፈ ውሃ ብቻ ታስታውሰዋለህ

ሶፋር መከራን አልፎ ከሄደ ወራጅ ውሃ ጋር ያነጻጽረዋል፡፡ "ታስታውሰዋለህ፣ ነገር ግን መከራው አልፎ እንደሄደ ውሃ ይረሳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ህይወትህ እንደ ማለዳ…ይሆናል

ሶፋር ትኩረት ለመስጠት ተመሳሳይ የሆነን ሃሳብ ይደግማል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ህይወትህ ከቀትር ብርሃን ይልቅ ብሩህ ይሆናል

ብሩህነት የሚወክለው ባለጸጋ እና ደስተኛ መሆንን ነው፡፡ "ህይወትህ ልክ እንደ እኩለ ቀን የብልጽግና እና የደስታ ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ምንም እንኳን ጨለማ ቢኖርም

ጨለማ እግርን እና ሃዘንን ይወክላል፡፡ "ምንም እንኳን ከባድ ችግር እን ሀዘን ቢኖርም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ማለዳ ይሆናል

ማለዳ የሚወክለው ብርሃን፣ ብልጽግናን እና ደስታን ይወክላል፡፡ "እንደ ማለዳ ብልጽግና እና ደስታ ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 11:18-19

ደህንነትህ የተጠበቀ ይሆናል…በሰላምም ታርፋለህ

ሶፋር ተመሳሳይ ሃሳብን ትኩረት ለመስጠት እና የሚቻል መሆኑን ለመግለጽ ሲል ይደግማል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና መላምታዊ ሁኔታዎች የሚሉትን ይመልከቱ)

በሰላም ታርፋለህ

እዚህ ስፍራ "በሰላም ማረፍ" የሚለው "ዕረፍት" ማለት ነው፡፡ "በሰላም" የሚለው ሀረግ "በደህና/በአስተማማኝ" በሚለው ቃል ሊገለጽ ይችላል፡፡ "በሰላም ማረፍ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር እና ረቂቅ ስም የሚሉትን ይመልከቱ)

የአንተ ስጦታ…ደግሞም በሰላም ትተኛለህ

ሶፋር ተመሳሳይ የሆነ ሃሳብ የሚደግመው ትኩረት ለመስጠት እና የሚቻል መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና መላምታዊ ሁኔታዎች የሚሉትን ይመልከቱ)

በሰላም ትተኛለህ

"ረፍት" የሚለው ረቂቅ ስም "አረፈ" ከሚለው ግስ ጋር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ጋድም ትላለህ ደግሞም ታርፋለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

Job 11:20

የክፉ ሰዎች ዐይኖች ይጨልማሉ

የእነርሱ ዐይኖች የሚወክሉት መረዳታቸውን ነው፡፡ "የክፉ ሰዎች መረዳት ይጨልማል" ወይም "ክፉ ሰዎች መረዳት/እውቀት ማግኘት አይችሉም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 12

Job 12:1-3

እናንተ እንደነዚህ አይነት ሰዎች መሆናች አያጠያይቅም፣ ጥበብ በእናንተ ዘንድ ትሞታለች

ኢዮብ በድርጊታቸው ይሳለቃል፣ ሀሳባቸው ምን ያህል የማይረባ እንደሆነ ያሳያቸዋል፡፡ "በእርግጥ እናንተ እንዲህ ያላችሁ ቁምነገረኞች ናችሁ፣ እውቀት ካለ እናንተ መኖር አትችልም" ወይም "እናንተ ብቸኛ ጥበብ ያላችሁ ሰዎች አድርጋችሁ ራሳችሁን ታሳያላችሁ፣ እናንተ በሞታችሁ ጊዜ ጥበብ ትጠፋለች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ምፀት የሚለውን ዘይቤ ይመልከቱ)

አያጠራጥርም

"በእርግጥ"

እናንተ

በቁጥር 2 እና 3 ይህ ብዙ ቁጥር ነው፡፡ (አንተ የሚለውን ተውላጠ ስም መልኮች ይመልከቱ)

እናንተ እነዚያ ሰዎች ናችሁ

"እናንተ ሁሉንም ነገር የምታውቁ ጠቃሚ ሰዎች ናችሁ"

በእርግጥ፣ እንደ እነዚህ ያሉ ነገሮችን የማያውቅ ማን ነው?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የሚጠቀመው ለአድማጮቹ ግልጽ መሆን ያለበትን እውነት ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ በገለጻ መልክ ሊቀርብ ይችላል፡፡ " በእርግጥ እንደ እነዚህ ያሉ ነገሮችን የማያውቅ ሰው የለም" ወይም "በእርግጥ እያንዳንዱ ሰው እነዚህን ነገሮች ያውቃል፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 12:4-6

ለወዳጆቼ መሳለቂያ ሆኛለሁ - እግዚአብሔርን የምጠራ እና እርሱም ምላሽ ይሰጠኝ የነበረ እኔ፣

በእነዚህ ሀረጎች መሃል ያለው ግንኙነት "ምንም እንኳን" በሚሉት ቃላት ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ "ምንም እንኳን እግዚአብሔርን ጠርቼ የመለሰልኝ ብሆንም፣ አሁን ግን የወዳጆቼ መሳለቂያ ሆኛለሁ!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አያያዥ ቃላት የሚለውን ይመልከቱ)

ትክክለኛ እና ያለ ነቀፋ የሆንኩት እኔ - አሁን መሳለቂያ ሆኛለሁ

በእነዚህ ሀረጋት መሃል ያለው ግንኙነት "ምንም እንኳን" በሚሉት ቃላት ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ "ምንም ያለ ነቀፋ እና ትክክለኛ ሰው ብሆንም፣ አሁን ግን የሰው መሳለቂያ ሆኛለሁ" (አያያዥ ቃላት የሚለውን ይመልከቱ)

በተመቸው ሰው አስተሳሰብ፣ መከራ የደረሰበት ሰው ይናቃል

"ሃሳብ"፣ "ምቾት"፣ "ንቀት"፣ "መከራ የደረሰበት/ዕደለ ቢስ" የሚሉት በሌሎች ሀረጋት ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ "ቀላል ህይወት የሚመራ ሰው መከራ የሚቀበለውን ሰው ይንቀዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

ብዙ መከራ ያመጣል

መከራ ማምጣት የሚወክለው ነገሩ እንዲሆን ምክንያት መሆንን ነው፡፡ "ብዙ መጥፎ ነገሮች እንዲፈጸሙ ምክንየት መሆን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እግራቸው ለሚንሸራተት

የእግር መንሸራተት የሚወክለው በአደጋ ወይም ችግር ውስጥ መሆንን ነው፡፡ "አሁንም በችግር ውስጥ ለሚገኙ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የዘራፊዎች ድንኳን ይበለጽጋል

የእነርሱ ድንኳን ይበለጽጋል የሚለው የሚወክለው ዘራፊዎች በድንኳናቸው ባለጸጋ እንደሚሆኑ ነው፡፡ "ዘራፊዎች በራሳቸው ድንኳን ውስጥ በብልጽግና ይኖራሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

የገዛ እጃቸው አማልክቶቻቸው ናቸው

"የገዛ እጃቸው" የሚለው ለጥንካሬ ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ሲሆን፤ "አማልክቶቻቸው" የሚለው ለኩራታቸው ዘይቤያዊ አገላለጽ ነው፡፡ "በችሎታቸው እጅግ ይመካሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 12:7-8

ነገር ግን አሁን ጠይቁ…ለእናንተ ያሳውቋችኋል

እነዚህ 4 ሃሳቦች፤ አውሬዎች፣ ወፎች፣ ምድር እና አሶች ሁሉም ከኢዮብ ወዳጎች ይልቅ እግዚአብሔርን መረዳት እንደሚችሉ ይገልጻሉ፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ምፀት የሚሉትን ይመልከቱ)

እናንተ

ይህ በኢዮብ ቁጥር 7 እና 8 ላይ ብዙ ቁጥር ነው፡፡ (አንተ የሚለውን ተውላጠ ስም መልኮች ይመልከቱ)

ነገር ግን አሁን አውሬዎችን ጠይቁ እነርሱም ያስተምሯችኋል

በዐረፍተ ነገሩ የመጀመሪያ ክፍል ላይ የሚገኘው ትዕዛዝ እንደ መላምታዊ ሁኔታ ሆኖ ያገለግላል፡፡ "አውሬዎችን ብትጠይቁ ኖሮ፣ እነርሱ ባስተማሩዋችሁ ነበር፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስልጣን እና ሃላፊነቶች - ሌሎች ጥቅሞች እንዲሁም መላምታዊ ሁኔታዎች የሚሉትን ይመልከቱ)

የሰማይ ወፎችን ጠይቁ፣ እነርሱም ይነግሯችኋል

በዐረፍተ ነገሩ የመጀመሪያ ክፍል ላይ የሚገኘው ትዕዛዝ እንደ መላምታዊ ሁኔታ ሆኖ ያገለግላል፡፡ የሰማይ ወፎችን ብትጠይቁ ኖሮ፣ እነርሱ ባስተማሩዋችሁ ነበር፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስልጣን እና ሃላፊነቶች - ሌሎች ጥቅሞች እንዲሁም መላምታዊ ሁኔታዎች የሚሉትን ይመልከቱ)

ወይም ከምድር ጋር ተነጋገሩ፣ እርሷ ታስተምራችኋለች

በዐረፍተ ነገሩ የመጀመሪያ ክፍል ላይ የሚገኘው ትዕዛዝ እንደ መላምታዊ ሁኔታ ሆኖ ያገለግላል፡፡ "ወይም ከምድር ጋር ብትነጋገሩ ኖሮ፣ ባስተማረቻችሁ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስልጣን እና ሃላፊነቶች - ሌሎች ጥቅሞች እንዲሁም መላምታዊ ሁኔታዎች የሚሉትን ይመልከቱ)

የባህር አሶች ያሳውቋችኋል

"የባህር አሶችን ጠይቁ" የሚለው ትዕዛዝ ከቀደሙት ዐረፍተ ነገሮች ለማለት የተፈለገው ይታወቃል፡፡ እንደ መላምታዊ ሁኔታ ሆኖ ይሰራል፡፡ "የባህር አሶችን ብትጠይቁ ኖሮ፣ ለእናንተ ያሳውቋችሁ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተዘለለ/የተተወ እና ስልጣንና ሃላፊነቶች - ሌሎች ጥቅሞች እንዲሁም መላምታዊ ሁኔታዎች የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 12:9-10

ይህንን… ከእነዚህ ሁሉ እንስሳት የማያውቅ የትኛው ነው?

ይህ ጥያቄ ሁሉም እንስሳት ያህዌ ይህን እንዳደረገ ያውቃሉ የሚለውን ያጎላል፡፡ ይህ ጥያቄ በገለጻ መለክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ " ይህን… ከእነዚህ ሁሉ መሃል እያንዳንዱ እንስሳ ያውቃል፡፡"በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

የያህዌ እጆች ይህን አድርጓል

የያህዌ እጅ የሚወክለው የእርሱን ሀይል ነው፡፡ "ያህዌ ይህንን በሀይሉ አድርጓል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

በእርሱ እጅ ህይወት… እና የሰው ሁሉ እስትንፋስ አለ

የያህዌ እጅ የሚወክለው የእርሱን ሀይል ወይም መቆጣጠር/መግዛት ነው፡፡ "እግዚአብሔር እስትንፋስ ያለውን ነገር ሁሉ ህይወት ይቆጣጠራል፤ ደግሞም ለሰው ሁሉ እስትንፋስን ይሰጣል፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

የሰው ሁሉ እስትንፋስ

እዚህ ስፍራ "እስትንፋስ" የሚወክለው ህይወትን ወይም ለመኖር ያለ አቅምን/ችሎታ ነው፡፡

Job 12:11-12

ላንቃ ጣዕምን እንደሚለይ ጆሮስ ቃላትን አይለይምን?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመው ሰዎች ሌሎች የሚናገሩትን በስማት ነገሩ መልካም መሆኑን ወይም አለመሆኑን እንደሚመዝኑ/እንደሚፈርዱ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ ጆሮ እና ላንቃ ለመስማት እና ጣዕም ለመለየት ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ናቸው፡፡ "ሰዎች የሚናገሩትን እንሰማለን ደግሞም ምግብን እንደምቀምስ እንቀምሰዋለን ደግሞም እናጣጥመዋለን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ዘይቤያዊ አነጋገር እንደዚሁም ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ጥበብ ከእድሜ ባለጸጎች ጋር ናት

"የእድሜ ባለጸጎች ጥበብ አላቸው፡፡" "ጥበብ" የሚለው ረቂቅ ስም "ብልህ" በሚለው ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ወንዶች" የሚለው ቃል በአጠቃላይ ሰዎች የሚለውን ያመለክታል፡፡ "አዛውንቶች ብልህ ናቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች እና ጥንካሬን የሚገልጹ ቃላት ሴቶችን ሲያካትቱ የሚለውን ይመልከቱ)

ቀናት ሲጨምሩ መረዳት/ዕውቀት ይገኛል

ይህ የሚገልጸው ሰዎች ረጅም እድሜ በኖሩ መጠን እውቀት/መረዳትን እያገኙ ይሄዳሉ የሚለውን ነው፡፡ "መረዳት" የሚለው ረቂቅ ስም "ብዙ መረዳት" በሚለው ሀረግ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ሰዎች ረጅም እድሜ ሲኖሩ መረዳት ይጨምራሉ/ያገኛሉ" ወይም "ብዙ ዘመን የኖሩ ሰዎች ብዙ መረዳት አላቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

Job 12:13-15

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ12፡13 እግዚአብሔር ጠቢብ እና ታላቅ ነው ይላል፡፡ የምዕራፉ ቀሪ ክፍል እግዚአብሔር ስለ ሰራቸው በጥበብ የተሞሉ እና ታላላቅ ስራዎች በመናገር ይህ እውነት መሆኑን ያሳያል፡፡

ጥበብ እና ታላቅነት የእግዚአብሔር ናቸው

"ጥበብ" እና "ታላቅነት" የሚሉት ረቂቅ ስሞች "ጠቢብ" እና "ታላቅ" በሚሉ ቅጽሎች ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ "እግዚአብሔር ጠቢብ እና ታላቅ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

እነሆ/ተመልከት

"እይ" ወይም "አድምጥ" ወይም "ልነግርህ ስላለው ነገር ትኩረት ስጥ"

ይህ ዳግም ሊገነባ አይችልም

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ይህን ማንም ዳግም ሊገነባው አይችልም" (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ያሰረውን፣ ሊፈታው የሚችል የለም

"መፍታት" የሚለው ረቂቅ ስም "ነጻ" በሚለው ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር ያሰረውን፣ ማንም ነጻ ሊያወጣው አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ውሆችን ከገደበ፣ ይደርቃሉ

ውሃን መገደብ/መያዝ የሚለው ሊኖረው የሚችለው ትርጉሞች 1) ዝናብ እንዳይዘንብ ቢከለክል፡፡ "ዝናብ እንዳይዘንብ ቢከለክል ምድር ትደርቃለች" ወይም 2) ወራጅ ውሃን ከመፍሰስ ቢያስቆም፡፡ "ውሃ እንዳይወርድ ቢያግድ ምድር ትደርቃለች" በሚሉት ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ቢለቃቸው፣ ምድሩን ያጥለቀልቃሉ

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች፤ እነርሱን መልቀቅ የሚለው ዘይቤ ነው ትርጉሙም 1) ዝናብ እንዲዘንብ ቢያደርግ/ዝናብን ቢያዘንብ፡፡ "ብዙ ዝናብ ቢያዘንብ፣ ምድሪቱ ትጥለቀለቃለች" ወይም 2) ውሃ እንዲወርድ/እንዲፈስ ቢያደርግ፡፡ "ብዙ ውሃ እንዲወርድ ቢያደርግ፣ ምድር ትጥለቀለቃለች" በሚሉት ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 12:16-18

ብርታት/ሀይል እና ጥበብ የእርሱ ናቸው

"ብርታት" እና "ጥበብ" የሚሉት ረቂቅ ስሞች "ብርቱ" እና "ጠቢብ" በሚሉ ቃላት ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ "እግዚአብሔር ብርቱ እና ጠቢብ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

የተታለሉ እና የሚያታልሉ ሰዎች ሁለቱም ከእርሱ ሀይል ስር ናቸው

በእግዚአብሔር ሀይል ስር የሚለው የሚገልጸው እግዚአብሔር በሁሉም ላይ ገዢ መሆኑን ነው፡፡ "በሀሰት የሚያምኑ እና ለሌሎች የሚዋሹ ሰዎች ሁለቱም በእርሱ ሀይል ስራ ናቸው" ወይም "እግዚአብሔር በሃሰት በሚያምኑ እና ለሌሎች ሃሰትን በሚናገሩ በሁለቱም አይነት ሰዎች ላይ ገዢ ነው" በሚሉት ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

እርሱ አማካሪዎችን በባዶ እግራቸው ይሰዳቸዋል

አማካሪዎችን በባዶ እግር መላክ የእነርሱን ጥበብና ስልጣን መቀማት ማለት ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በሀዘን

"ሀዘን" የሚለው ረቂቅ ስም "መመረር" ወይም "ማዘን" በሚሉ ቃላት ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ደግሞም በጣም ያዝናሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ፈራጆችን ሞኞች ያደርጋቸዋል

"እርሱ ፈራጆች ሞኞች እንዲሆኑ ያደርገል"

እርሱ የነገሥታት በሰንሰለት የማሰር ስልጣን ይወስድባቸዋል

ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ነገሥታት ከዚህ በኋላ ስልጣን እንዳይኖራቸው ያደርጋል ለሚለው ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "የነገሥታትን ስልጣን ይቀማቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ ወይም 2) ሰዎችን ነገስታት ከጫኑባቸው ቀንበር ነጻ ማውጣት ለሚለው ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት ነው፡፡ "እርሱ ነገሥታት በህዝቡ ላይ የጫኑትን ቀንበር ያነሳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እስከ ወገባቸው ድረስ ያለብሳቸዋል/ከወገባቸው በላይ ይራቆታሉ

ይህ ልብስ ምናልባት ባርያ የሚለብሰው ልብስ ይሆናል፡፡ ይህንን ልብስ ንጉሦችን ማልበስ የሚገልጸው ንጉሦችን ባሮች ማድረግን ነው፡፡ "እርሱ ነገሥታት የባሮችን ልብስ እንዲለብሱ ያደርጋል" ወይም "እርሱ ባሮች ያደርጋቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 12:19-21

ካህናቱን ባዶ እግራቸውን ይሰዳቸዋል

ካህናትን ባዶ እግራቸውን መስደድ ስልጣናቸውን መቀማትን ያመለክታል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በሀዘን

"ሀዘን" የሚለው ረቂቅ ስም "መመረር" ወይም "ማዘን" በሚሉ ቃላት ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ደግሞም በጣም ያዝናሉ" ወይም "ደግሞም ይመረራሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ታላላቆችን ያዋርዳል

"ሀይለኞችን ያሸንፋል"

ይታመኑ የነበሩትን ንግግራቸውን ያቀላል/ያርቃል

ንግግራቸውን ያቀላል/ያርቃል የሚለው የሚገልጸው መናገር እንዳይችሉ ያደርጋቸዋል ማለትን ነው፡፡ "ይታመኑ የነበሩትን መናገር የማይችሉ ያደርጋቸዋል" ወይም "ሌሎች ያምኗቸው የነበሩትን ጸጥ ያሰኛቸዋል" (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የሽማግሌዎችን እውቀት/መረዳት ይወስድባቸዋል

መረዳታቸውን ይወስዳል የሚለው የሚገልጸው መረዳት ወይም ጥሩ ውሳኔ መስጠት እንዳይችሉ ማድረግ ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ሽማግሌዎች

ሊሰጡ የሚችሉ ትረጉሞች 1) በእድሜ ትልቅ የሆኑ ሰዎች ወይም 2) መሪዎች የሚሉ ናቸው፡፡

በልዑላን ላይ ንቀትን ያፈሳል

በልዑላን ንቀት ማፍሰስ ህዝቡ እንዲንቃቸው ማድረግ ለሚለው (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የሃያላንን ቀበቶ/ወገብ ይፈታል

ቀበቶ የጥንካሬ ምልክት ነው፡፡ የሀያልን ሰው ቀበቶ መፍታት የሚወክለው አቅሙን ከእርሱ መንጠቅ እና ሰውየወን ደካማ ማድረግን ነው፡፡ "ሃያልንን ደካማ ያደርጋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 12:22-23

የጨለማን ጥልቅ ነገሮች ይገልጣል

ነገሮችን መግለጽ የሚወክለው እነርሱን እንዲታወቁ ማድረግን ነው፡፡ "በጨለማ ያሉ ጥልቅ ነገሮች" የሚወክለው ሰዎች የማያውቋቸውን ነገሮች ነው፡፡ "እርሱ ሰዎች የማያውቋቸውን ምስጢሮች እንዲታወቁ ያደርጋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ጥልቅ ጥላዎችን ወደ ብርሃን ያመጣል

ነገሮችን ወደ ብርሃን ማምጣት የሚወክለው እንዲታወቁ ማድረግን ሲሆን፣ እዚህ ስፍራ "ጥላዎች" በጥላ ውስጥ ለተደበቁ ነገሮች ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት ነው፡፡ ይህም በተራው እግዚአብሔር ከሰዎች ለደበቀው እውነት ዘይቤያዊ አገላለጽ ነው፡፡ "ማንም ሊመለከተው የማይችለውን ነገር እንዲታወቅ ያደርጋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

መንግሥታትን ታላቅ ያደርጋል

"እርሱ መንግሥታትን ትልቅ ያደርጋል" ወይም "እርሱ መንግሥታት ብዙ መሬት እንዲኖራቸው ያደርጋል"

እንደዚሁም እርሱ ከእስረኞች ጋር ይመራቸዋል

እግዚአብሔር አህዛብን ይመራል የሚለው የሚወክለው እግዚአብሔር ጠላቶቻቸው እንዲመሯቸው ያደርጋል የሚለውን ነው፡፡ "እነርሱ" የሚለው ቃል የሚወክለው ህዝቦችን ነው፤ እዚህ ስፍራ እነዚያን አገራት ሰዎች ነው፡፡ "እንደዚሁም እርሱ ጠላቶቻቸው እንደ እስረኛ እንዲመሯቸው ያደርጋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 12:24-25

ከምድር ህዝቦች መሪዎች ዘንድ ሁሉ እርሱ ማስተዋልን ይወስዳል

ማስተዋላቸውን መውሰድ የሚለው የሚወክለው እንዳያስተውሉ ማድረግን ነው፡፡ "እርሱ የምድር ህዝቦች መሪዎች እንዳያስተውሉ ያደርጋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

መንገድ በሌለበት በረሃ መንከራተት

መንገድ በሌለበት በበረሃ መንከራተት የሚለው የሚወክለው በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መሆንን እና መሄጃን አለማወቅን ነው፡፡ "መንገድ በሌለበት ጠፍ መሬት እንደሚንከራተት ምን ማድረግ እንዳለበት እንደማያውቅ ሰው እርግጠኛ አለመሆን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ብርሃን በሌለበት በጨለማ ይርመሰመሳሉ

ብርሃን በሌለበት በጨለማ መሆን የሚወክለው እውቀት ማጣትን ነው፡፡ "ሰዎች ያለ ብርሃን በጨለማ ለመራመድ እንደሚታገሉ እነርሱም ያለ እውቀት ውሳኔ ለመስጠት ይታገላሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እንደሰከረ ሰው እንዲንገዳገዱ ያደርጋቸዋል

እንደጠጣ/እንደሰከረ ሰው መንገዳገድ የሚለው የሚወክለው ያለ አላማ መኖርን ነው፡፡ "ሲራመድ እንደሚነገዳገድ የሰከረ ሰው ያለ አላማ እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል" ወይም "ወደ ፊት እና ወደ ኋላ እንደሚንገዳገድ እንደ ሰከረ ሰው ያለ አላማ ይንከራተታሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 13

Job 13:1-2

አያያዥ ሃሳብ

ኢዮብ ለወዳጆቹ መናገሩን ይቀጥላል፡፡

እነሆ/እይ

"ተመልከት" ወይም "አድምጥ" ወይም "ለምናገረው ትኩረት ስጥ"

ዐይኔ ይህን ሁሉ ተመልክቷል

ኢዮብ እነዚህን ነገሮች በዐይኑ በማየቱ ራሱን የሚገልጸው ዐይኖቹን አድርጎ ነው፡፡ "ይህንን ሁሉ አይቻለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ጆሮዎቼ ሰምተው ተረድተዋል

ኢዮብ እነዚህን ነገሮች በጆሮው በመስማቱ ራሱን የሚገልጸው ጆሮቹን አድርጎ ነው፡፡ "ይህን ሰምቼ ተረድቻለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

እናንተ የምታውቁትን፣ ያንኑ እኔም አውቃለሁ

"የምታውቁትን፣ እኔም አውቃለሁ" ወይም " እናንተ የምታውቁትን ያህል እኔም አውቃለሁ"

Job 13:3-5

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ ለወዳጆቹ መናገሩን ይቀጥላል

ከእግዚአብሔር ጋር መከራከር እፈልጋለሁ

የኢዮብ ወዳጆች እየፈረዱበት ነው፣ ነገር ግን እውነት እየተናገሩ አይደለም፡፡ ይልቁንም ኢዮብ ቅሬታውን እያቀረበ ከእግዚአብሔር ጋር እየተከራከረ ነው፡፡

እናንተ እውነትን በውሸት ኖራ ትሸፋፍናላችሁ

ኖራ መቀባት ወይም እውነትን መሸፈን የሚገልጸው እውነትን መተውን ነው፡፡ "እውነትን በሀሰት ትደብቃላችሁ" ወይም "ትዋሻላችሁ ደግሞም እውነትን ተዋላችሁ/ትጥላላችሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እናንተ ሁላችሁም ምንም የማትጠቅሙ ባለ መድሀኒቶች ናችሁ

ባለ መድሃኒት መሆን የሚወክለው ሌላውን የሚያጽናና ሰው መሆንን ነው፡፡ ምንም የማትጠቅሙ ማለት ማድረግ ያለባቸውን እንዴት እንደሚያደርጉ አያውቁም ማለት ነው፡፡ "ሰው እንዴት እንደሚፈውሱ እንደማያውቁ ባለመድሀኒቶች ናችሁ" ወይም "እናንተ ልታጽናኑኝ መጣችሁ፣ ነገር ግን ያልሰለጠነ መድሃኒተኛ እንዴት እንደሚፈውስ እንደማያውቅ ሁላችሁም እንዴት እንደምታጽናኑ አታውቁም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የእናንተ ሰላም ለእናንተ ይሁን/ሰላማችሁን ያዙት

ይህ አገላለጽ "ዝም በሉ" ወይም "መናገራችሁን አቁሙ" ማለት ነው፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ያንን ብታደርጉ ይህ ለእናንተ ጥበብ ይሆናል

እነርሱ ጥበብ የሞላበትን ነገር እየተናገሩ ይመስላቸዋል፣ ኢዮብ ግን መናገራቸውን አቁመው ዝም ቢሉ የበለጠ ጥበበኞች እንደሚሆኑ ይነግራቸዋል፡፡ "ጥበብ" የሚለው ረቂቅ ስም "ጠቢብ" በሚለው ቃል ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ያንን ብታደርጉ ጠቢብ ትሆናላችሁ" ወይም "መናገራችሁን ብታቆሙ፣ ጠቢብ መስላችሁ ትታያላችሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

Job 13:6-8

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ ለወዳጆቹ መናገሩን ይቀጥላል

የከንፈሮቼን ልመና ስሙ

እዚህ ስፍራ "ከንፈሮች" የሚለው የሚወክለው ተናጋሪውን ሰው ነው፡፡ "እኔ ራሴ የምለውነውን ነገር አድምጡ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ለእርሱ በሽንገላ … ያለ ጽድቅ/በክፉ ትናከራላችሁን?

ኢዮብ እነዚህን ሁለት ጥያቄዎች የሚጠቀመው ወዳጆቹ ያለ ጽድቅ/በክፉ በመናገራቸው ሊወቅሳቸው ነው፡፡ "እናንተ ለእግዚአብሔር የምትናገሩ ይመስላችኋላ፣ ነገር ግን በክፋት/ጽድቅ የሌለበትን ነገር እየተናገራችሁ ነው፡፡ በማታለል እየተናገራችሁ ነው፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

በማታለል መናገር

"መዋሸት" ወይም "ውሸት መናገር"

ለእርሱ ወገንተኝነትን ታሳያላችሁን? ለእግዚአብሔር ትከራከራላችሁን?

ለእግዚአብሔር ደግነትን ማሳየት የሚወክለው እግዚአብሔርን መርዳትን ወይም እግዚአብሔርን ከኢዮብ ማማረር መከላከልን ነው፡፡ ኢዮብ እነዚህን ጥያቄዎች የተጠቀመባቸው ወዳጆቹ ለእግዚአብሔር እንቆምለታለን ብለው በማሰባቸው ሊወቅሳቸው ነው፡፡ "እግዚአብሔር እንድትከራከሩለት ይፈልጋል ብላችሁ ታስባላችሁን? ጠበቃ በፍርድ ቤት እንደሚካከር ለእግዚአብሔር እንደምትከራከሩለት ታስባላችሁ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እንዳሁም ምፀት የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 13:9-10

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ ለወዳጆቹ መናገሩን ይቀጥላል

እርሱ መርምሮ በደረሰባችሁ ጊዜ ይህ ለእናንተ መልካም ይሆንላችኋልን?

እዚህ ስፍራ "ከውጭ ሲያገኛችሁ" በዘይበያዊ አነጋገር "ሲመረምራችሁ" የሚል ትርጉም አለው፡፡ ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመው እግዚአብሔር ወዳጆቹን በመረመራቸው ጊዜ ስህተተኞች ሆነው ስለሚያገኛቸው ሊያስጠነቅቃቸው ፈልጎ ነው፡፡ "እግዚአብሔር በመረመራችሁ ጊዜ፣ ለእናንተ መልካም አይሆንም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እናንተን ይወቅሳል

"እናንተን ይገስጻል"

በድብቅ ወገናዊነትን/አድልዎ ብታሳዩ

"ለሌላው በድብቅ አድልዎ ብታደርጉ፡፡" ወገናዊነትን ማሳየት የሚመለክተው፣ ዳኛው ያ ሰው መልካም ነው እንዲል ስለ አንድ ሰው መልካሙን ብቻ መናገርን ነው፡፡ ይህንን በድብቅ ማድረግ ማለት በትክክል የተናገሩ ማስመሰል ሲሆን፣ በእርግጥ ግን ሲታይ ከአንዱ ሰው ይልቅ ለሌላው ማድላት ነው፡፡

Job 13:11-12

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ ለወዳጆቹ መናገሩን ይቀጥላል

የእርሱ ግርማ አያስፈራችሁምን፣ ደግሞስ የእርሱ ፍራሃት አይወድቅባችሁምን?

ኢዮብ እነዚህን ጥያቄዎች የተጠቀመው ወዳጆቹን ለመገሰጽ ነው፡፡ ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ኢዮብ አግዚአብሔርን መፍራት አለባችሁ እያላቸው ነው፡፡ "ግርማው ሊያስፈራችሁ፣ እርሱን መፍራት ሊወድቅባችሁ ይገባል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ ወይም 2) ኢዮብ ወዳጆቹን እግዚአብሔርን ፍሩት ይላቸዋል፡፡ "ግርማው ያስፈራችኋል፣ ደግሞም የእርሱ ማስደንገጥ በላያችሁ ይወድቃል!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሱ ማስደንገጥ በላያችሁ ይወድቃል

ማስደንገጥ በሰዎች ላይ መውደቅ የሚለው የሚወክለው እነርሱ እጅግ ይፈራሉ የሚለውን ነው፡፡ "እናንተ እጅግ አትደነግጡምን" ወይም "ደግሞስ እጅግ አትፈሩም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የእናንተ ምርጥ ንግግሮች/ምሳሌዎች የሚባሉት ከአመድ የተበጁ ናቸው

አመድ የሚወክለው ጥቅም እና እድሜ የሌላቸውን ነገሮች ነው፡፡ "የእናንተ ምርጥ አባባሎች እንደ አመድ እርባና ቢሶች ናቸው" ወይም "የእናንተ ምርጥ አባባሎች/ምሳሌዎች ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስዳቸው አመድ ናቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

መከላከያዎቻችሁ

ይህ የሚያመለክተው ሊሰጥ የሚችለው ትርጉም 1) ራሳቸውን ለመከላከል የሚናገሩት ወይም 2) ለእግዚአብሔር ጥብቅና ለመቆም የሚናገሩት

Job 13:13-15

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ ለወዳጆቹ መናገሩን ይቀጥላል

የእናንተ ሰላም ለእናንተ ይሁን/ሰላማችሁን ያዙት

ይህ ፈሊጣው አገላለጽ ነው "ዝም በሉ" ወይም "መናገራችሁን አቁሙ" ማለት ነው፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እኔን ብቻዬን ተዉኝ

ይህ ፈሊጣው አገላለጽ ነው "እኔኝ መሳሰጨነቃችሁን አቁሙ" ወይም "እኔን ማስተጓጎላችሁን አቁም" ነው፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በእኔ ላይ የሚደርሰው ይድረስብኝ/ይምጣብኝ

በአንድ ሰው ላይ የሚመጡ ነገሮች የሚወክሉት በዚያ ሰው ላይ የሚሆኑ ነገሮችን ነው፡፡ ይህ አገላለጽ የሚጀምርበት "ይሁን" የሚለው አባባል በእርሱ ላይ ስለሚደርሰው ነገር ግድ የለውም ማለት ነው፡፡ "በእኔ ላይ ሊደርስ ያለው ማናቸውም ነገር ይድረስብኝ" ወይም "በእኔ ላይ ስለሚደርሰወ ነገር ግድ አይለኝም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ስጋዬን … በእጆቼ አይዛለሁ

እዚህ ስፍራ "ስጋ" የሚለው ለህይወት ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "ጥርስ" እና "እጆች" የሚሉት ራሱን ስለ መግዛቱ ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ናቸው፡፡ እነዚህ ሁለት ሀረጋት በአንድነት ኢዮብ ከእግዚአብሔር ጋር በመከራከር ህይወቱን አሳልፎ ለመስጠት ፈቃደኛ መሆኑን ያጎላሉ፡፡ "ህይወቴን አሳልፌ ለመስጠት ዝግጁ ነኝ" (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 13:16-17

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ ለወዳጆቹ መናገሩን ጨርሶ በቀጥታ ከእግዚአብሔር ጋር መናገር ይጀምራል፡፡

ይህ ለእኔ ነጻ መውጣት ምክንያት ይሆናል

"ነጻ መውጣት" የሚለው ረቂቅ ስም "ነጻነት" በሚለው ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር እኔን ነጻ የሚያወጣበት ምክንያት ይህ ነው" ወይም "እግዚአብሔር እኔን ከችግሮቼ የሚያድነኝ ከዚህ የተነሳ ነው" በሚሉት ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ሆይ፣ ስማኝ

ኢዮብ ንግግሩን የሚጀምረው በቀጥታ ወደ እግዚአብሔር በመጮህ/በመናገር ነው፡፡

ንግግሬን እድምጥ፣ የምናገረው ወደ ጆሮህ ይድረስ

እነዚህ ሁለት መስመሮች በመሰራታዊነት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ ደግሞም ኢዮብ እግዚአብሔር እንዲሰማው የሚያቀርበውን ጥያቄ አጉልተው ይገልጻሉ፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የምናገረው ወደ ጆሯችሁ ይድረስ

"መናገር/ማወድ" የሚለው ረቂቅ ስም "ተናገረ/አወጀ" በሚል ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ጆሯችሁ የሚለው የሚወክለው መስማትን ነው፡፡ "የምናገረውን ስሙ" ወይም "የምለውን ስሙ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች እና ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 13:18-19

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ ለእግዚአብሔር መናገሩን ይቀጥላል

እነሆ አሁን ተመልከት

ይህ ተከትሎ የሚነገረውን ያጎላል፡፡ "እነሆ አሁን ስማ" ወይም "እባክህ ስማኝ"

መከላከያዬን በስርአት አቀርባለሁ

መከላከያውን በስርአት ማቅረብ የሚወክለው ራሱን ለመከላከል የሚያቀርበውን መወሰንን ያመለክታል፡፡ "እርሴን እንዴት እንደምከላከል በሚገባ አስቤበታለሁ" ወይም "ያለኝን ሀሳብ እንዴት እንደምገልጽ ወስኛለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በፍርድ ቤት እኔን በደለኛ አድርጎ መከራከር የሚችል ማን ነው?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የሚጠቀምበት ትክክለኛ እስከሆነ ድረስ ከእርሱ ጋር ማንም ሊከራከር እንደማይችል ያለውን እምነት ለመግለጽ ነው፡፡ "በፍርድ ቤት ማንም ከእኔ ጋር ይከራከራል ብዬ አላምንም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህንን ለማድረግ ብትመጡ

"ከእኔ ጋር ለመከራከር ብትመጡ"

አንተ ብትመጣ

እዚህ ስፍራ "አንተ" የሚለው እግዚአብሔርን ራሱን ነው

ስህተተኛ መሆኑ ከተረጋገጠ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ስህተተኛ መሆኔን አንተ ካረጋገጥህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ህይወቴን አሳልፌ እሰጣለሁ

አንድ ሰው ህይወቱን አሳልፎ መስጠቱ ለሞት ዘይቤያዊ አነጋገር ነው፡፡ "እሞታለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 13:20-22

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ ለእግዚአብሔር መናገሩን ይቀጥላል

ከአንተ ፊት

"ፊት" የሚገለጸውን አካል ይወክላል፡፡ "ከአንተ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ከባድ እጅህን ከእኔ ላይ አንሳ

ከባድ/የሚጫን እጅ አንድን ሰው የሚጫን ነገር ማድገረግን የሚገልጽ ሜቶኖሚ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ እጅን ማንሳት እነዚያ ነገሮችን ማድረግ ማቆምን የሚገልጽ ዘይቤያዊ አነጋገር ነው፡፡ "እኔን መጫንህን አቁም/እጅህን ከእኔ አንሳ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

ማስጨነቅህ እንድፈራ አያድርገኝ

"ማስጨነቅህ" የሚለው ሀረግ የሚያመለክተው ሰዎች እግዚአብሔርን እንዲፈሩ የሚያደርጋቸውን ምክንያት ነው፡፡ "አታስጨንቀኝ/አታስፈራኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 13:23-25

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ ለእግዚአብሔር መናገሩን ይቀጥላል

እንደ ጠላትህ ….ስለምን ከእኔ ትደበቃለህ?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው እግዚአብሔር እያደረሰበት ስላለው ነገር ለማማረር ነው፡፡ ምናልባትም መልስ ለማግኘት ተስፋ እያደረገ ይሆናል፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ፊትህን ከእኔ ደበቅህ/ሰወርክ

ፊትን ከሌላው መደበቅ የሚወክለው ለመመልከት አለመፈለግን ወይም ለማየት መቃወምን ነው፡፡ "እኔን ማየት አልፈለግክም" ወይም "ተውከኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ ታሰቃያለህን…የደረቀውንስ እብቅ ትከታተላለህን?

ኢዮብ እነዚህን ጥያቄዎች የሚጠቀምባቸው እርሱ እዚህ ግባ የማይባል እና ደካማ ሳለ እግዚአብሔር ኢዮብን መከታተሉና ማሳደዱ ዋጋ እንደሌለው ለእግዚአብሔር ለመናገር ነው፡፡ "ቅጠል" እና "የደረቀ እብቅ" የኢዮብን ደካማነት፣ አቅመቢስነት እና ተሰባሪነት የሚገልጹ ዘይቤዎች ናቸው፡፡ "አንተ ታሳድደኛለህ፣ እኔ ግን ነፋስ እንደሚጠርገው ቅጠል እና እንደ ደረቅ እብቅ ደካማነኝ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እንደዚሁም ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 13:26-28

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ ጉዳዩን ለእግዚአብሔር ማቅረቡን ያበቃል

አንተ በእኔ ላይ መራራ ነገሮችን ታቀርባለህ/ትጽፋለህ

"መራራ ነገሮች" የሚለው የሚወክለው መክሰስን ነው፡፡ "አንተ በእኔ ላይ ክስን ታቀርባለህ/ትጽፋለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

መልካም ያልሆኑትን የወጣትነቴን ታማኝነት ማጣት/ኃጢአት እንድወርስ አደረግህ

የወጣትነቱን ታማኝነት ማጣት መውረስ ዘይቤያዊ አነጋገር ነው፡፡ ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች፡ 1) በወጣትነቱ ታማኝነት ማጣት/ኃጢአት በደለኛ መሆን፡፡ "በወጣትነቴ ኃጢአት አሁንም ድረስ በደለኛ አደርገኸኛል" ወይም 2)በወጣትነት ኃጢአቱ እየተቀጣ ይገኛል፡፡ "በወጣትነቴ በሰራሁት ኃጢአት እየቀጣኸኝ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የወጣትነቴ ኃጢአት

"ወጣት" የሚለው ረቂቅ ስም "ታዳጊ" ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ታዳጊ ሳለሁ የሰራሁት ኃጢአት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

እግሮቼንም ደግሞ በእግር ግንድ ታጣብቃለህ

ይህንን ማድረግ የሚወክለው ወንጀል የሰራ እና እስረኛ የሆነ ይመስል፣ ኢዮብን መቅጣትን እና በነጻነት እንዳይኖር መከልከልን ነው፡፡ "እግሮቼን በእግር ግንድ ያጣበቅከኝ ያህል ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በእግር ግንድ

ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች፡ 1) የእስረኛን እግሮች በፍጹም መንቀሳቀስ እንዳይችል አድርጎ በአንድ ስፍራ የሚይዝ ማሰሪያ ወይም 2) መንቀሳቀሱን ከባድ የሚያደርግበት በእስረኛ እግሮች ዙሪያ የሚደረግ ሰንሰለት፡፡ እነዚህ እንደ ቅጣት መልክ የሚያገለግሉ ናቸው፡፡

መንገዶቼ ሁሉ

"መንገዶች" የሚለው የሚወክለው ኢዮብ ያደረጋቸውን ነገሮች ነው፡፡ "ያደረግኳቸው ነገሮች በሙሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እግሮቼ የረገጡትን ስፍራ/ዱካዬን ሁሉ መረመርህ/ተከታተልክ

የእግሩ ጫማ የሚወክለው የሚራመደውን ሰው ነው፡፡ "የተራመድኩባቸውን ስፍራዎች ሁሉ መረመርህ/ተከታተልህ" ወይም "አንድ ሰው የረገጣቸው ቦታዎች ሁሉ እንደሚታዩ የሰራኋቸውን ነገሮች ሁሉ ተከታተልክ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደተበላሸ/ እንደበሰበሰ እና እንደተጣለ ነገር

ኢዮብ ህይወቱን ከበሰበሰ ነገር ጋር ያነጻጽራል፡፡ ቀስ በቀስ ወደ ሞት እየሄደ ነው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አይጦች እንደበሉት ጨርቅ

ኢዮብ ራሱን አይጦች በልተው ከቀዳደዱት ጨርቅ ጋር ያመነጻጽራል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 14

Job 14:1-3

አጠቃላይ መረጃ፡

በዚህ ምዕራፍ በኢዮብ 12፡1 የተጀመረው የኢዮብ ንግግር ይቀጥላል፣ ኢዮብ ከእግዚአብሔር ጋር ይነጋገራል፡፡

ከሴት የተወለደ፣ ሰው

ይህ ወደዚህ ዓለም የተወለደውን ሁሉ፣ ወንድንም ሴትንም በአጠቃላይ ሰውን ያመለክታል፡፡ (ጉልበትን/ጡንቻማነትን የሚያመለክቱ ቃላት ሴቶችን ሲያካትቱ የሚለውን ይመልከቱ)

ለጥቂት ቀናት የሚኖር

ይህ ሰው አጭር እድሜ እንዳለው በማጋነን የቀረበ አገላለጽ ነው፡፡ "በጣም አጭር ጊዜ ብቻ የሚኖር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)

በችግር የተሞላ

"በችግር የተሞላ" መሆን የሚወክለው ብዙ ችግር ማጋጠሙን ነው፡፡ "ብዙ ችግር አለው" ወይም "ብዙ ተሰቃየ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ አበባ ከምድር ይበቅላል፣ ደግሞም ይቆረጣል

የሰው እድሜ እንደ አበባ እድሜ አጭር ነው፣ ደግሞም በቀላሉ ይሞታል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ጥላ ይሸሻል፣ ደግሞም አይቆይም

የሰው አጭር ህይወት በፍጥነት ከሚጠፋ ጥላ ጋር ተነጻጽሯል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከእነዚህ አንዱን ተመልክተሃል?

ኢዮብ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ እንዲህ እንዲያተኩር አለመፈለጉን ይጠቁማል፡፡ "ከእነዚህ አንዱን አልተመለከትክም" ወይም "ለእነዚህ ብዙ ትኩረት አልሰጠህም፡፡ እባክህ በእኔ ላይ ብዙ አታተኩር፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ተመልከት

እዚህ ስፍራ አንድን አካል መመልከት የሚወክለው በእርሱ ላይ ለመፍረድ ትኩረት መስጠትን ነው፡፡ "ትኩረት ስጥ" ወይም "ከዚያ ላይ ስህተትን መፈለግ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

እኔን ከአንተ ጋር ወደ ፍርድ ታመጣለህን?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመው ኢዮብ እንደ አበባ በቶሎ ጠፊ ሆኖ ሳለ እግዚአብሔር በእርሱ ላይ መፍረዱ እንዳስደነቀው ለመግለጽ ነው፡፡ "ነገር ግን አንተ በእኔ ላይ ፈረድክ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 14:4-6

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገሩን ይቀጥላል፡፡

ማን ንጹህ ካልሆነ ነገር ንጹህ የሆነ ነገርን ማውጣት ይችላል? ማንም

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የሚጠቀመው እርሱ ንጹህ ስላልሆነ ነገር የሚያውቀውን እግዚአብሔር በኢዮብ ላይ እንዲያደርግ ለመገፋፋት ነው፡፡ "ማንም ንጹህ ካልሆነ ነገር ንጹህ ነገርን ማምጣት አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

የሰው ቀኖች የተወሰኑ ናቸው

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "አንተ የሰውን ቀናት ትወስናለህ" ወይም "አንተ ሰው የሚኖርበትን ዘመን ትወስናለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የወራቱ ቁጥር በአንተ ዘንድ ነው

ሰው የሚኖርበት ወራት ቁጥር በእግዚአብሔር ዘንድ መሆኑ የሚወክለው ሰው የሚኖርበትን ወራት ቁጥር የሚወስነው እግዚአብሔር መሆኑን ነው፡፡ "ምን ያህል ወራት እንደሚኖር አንተ ትወስናለህ" (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ሊያልፍ የማይችልበትን ገደብ አንተ ወስነሀል

ገደብን ማለፍ የሚለው የሚወክለው አንድ ሰው እንዲኖር እግዚአብሔር አስቀድሞ የወሰነለት ዘመን መኖር ነው፡፡ "አንተ የሚሞትበትን ጊዜ ወስነሃል፣ እናም ሰው ያንን አልፎ መኖር አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የተቀጠረ ሰው/ቅጥረኛ

አንድን ስራ ለመስራት የተቀጠረ እና ከዚያ ወደ ቤቱ የሚሄድ ሰው

Job 14:7-9

ለዛፍ ተስፋ ሊኖረው ይችላል

"ተስፋ" የሚለው ረቂቅ ስም "ተስፋ" በሚል ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ተስፋ ከቁር 7-9 ባለው ውስጥ ተብራርቷል፡፡ "ዛፍ ዳግም እንደሚኖር ተስፋ ልናደርግ እንችላለን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

ዳግም ሊበቅል ይችላል

"እንደገና መብቀል ሊጀምር /ሊያቆጠቁጥ ይችላል"

ስለዚህም ቅርንጫፉ ሊጠፋ አይችልም

መጥፋ የሚወክለው መሞትን ነው፡፡ "ስለዚህም አዳዲሶቹ ቅርንጫፎች አይደርቁም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ምንም እንኳን

"ቢሆንም እንኳን"

ጉቶ

ዛፉ ከተቆረጠ በኋላ ታች ከመሬቱ ላይ ብቅ ብሎ የሚቀረው ክፍል

የውሃ ሽታ ቢያገኝ ብቻ

ይህ የሚገልጸው የሞተው ጉቶ ልክ ውሃ ማሽተት እንደሚችል እና ውሃ በአቅራቢያው እንደሚገኝ ተደርጎ ነው፡፡ "ጥቂት ውሃ እንኳን በአቅራቢያው ቢኖር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ የሚለውን ዘይቤ ይመልከቱ)

ያቆጠቁጣል

"ማደግ/ማቆጥቆጥ ይጀምራል"

እንደ ተክል ቅርንጫፍ ያወጣል

ዛፍ ቅርንጫፍ ማውጣቱ የሚወክለው ቅርንጫፎች በዛፍ ላይ ማደጋቸውን ነው፡፡ "ቅርንጫፎች በጉቶው ላይ እንደ ተክል ማደግ ይጀምራሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ የሚለውን ዘይቤ ይመልከቱ)

Job 14:10-12

ከእንግዲህ የት ይገኛል?

ኢዮብ ይህንን ጥጣቄ የተጠቀመው ሰው በሞተ ጊዜ፣ እንደማይገኝ አጉልቶ ለማሳየት ነው፡፡ "የት እንደሆነ ማንም አያውቅም" ወይም "ላይመለስ ሄዷል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ውሃ ከሐይቅ እንደሚተን… ደግሞም ዳግምም እንደማይነሳ

ሞት ዳግም የሚከናወን ነገር አለመሆኑ የተነጻጸረው አንዴ የተነነ ውሃ ዳግም ሊመለስ ካለመቻሉ ጋር ነው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ውሃ እንደሚተን… ከወንዝ እንደሚነሳ

እነዚህ ሁለት ሀረጋት አንድ አይነት ሀሳብን ይገልጻሉ፤ ይህም መደጋገም የተደረገው ሞት የመጨረሻ ነገር መሆኑን ለማጉላት ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደዚሁም ሰዎች ይጋደማሉ

መጋደም የሚለው የሚወክለው መሞትን ነው፡፡ "እንደዚሁም ሰዎች ይሞታሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ዳግም አይነሱም

ዳግም መነሳት የሚወክለው ዳግም መኖር የሚለውን ነው፡፡ "ዳግም አይኖርም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ዳግም አይነቁም አሊያም ከተኙበት አይነሱም

እነዚህ ሁለት ሀረጋት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ በአንድነት ያገለገሉት ሞት የመጨረሻ መሆኑን ለማጉላት ነው፡፡ መተኛት የሚለው የሚወክለው መሞትን ሲሆን መንቃት ደግሞ የሚወክለው ዳግም መኖርን ነው፡፡ "የሞቱ ሰዎች ዳግም አይኖሩም፣ እናም ከሞት አይነሱም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 14:13-14

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገሩን ይቀጥላል፡፡

አቤቱ፣ እባክህ ሰውረኝ

ይህ ኢዮብ በጣም የሚፈልገውን ነገር ግን በእርግጥ ይሆናል ብሎ የማይጠብቀውን ነገር የሚያሳይ ቃለ አጋኖ ነው፡፡ "ብትሰውረኝ በወደድሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ አጋኖ የሚለውን ይመልከቱ)

ለብቻዬ አግልለኝ

"በእኔ ላይ ቆልፍ" ወይም "ሰውረህ አስቀምጠኝ"

አትርሳኝ

አንድን ሰው አለመርሳት/ማስታወስ ስለዚያ ሰው ማሰብን የሚገልጽ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "ስለ እኔ አስብ" ወይም "እኔን አስታውስ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የሞተ ሰው ዳግም ይኖራልን?

በውስጠ ታዋቂነት የተሰጠ ምላሽ "አይ" የሚል ነው፡፡ "የሞተ ሰው፣ ዳግም በህይወት አይኖርም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እንዲህ ከሆነ

"ከሆነ" የሚለው ምን እንደሚያመለክት ከቀደመው ሀረግ ይታወቃል፡፡ "እርሱ ዳግም ቢኖር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የድካም ጊዜያቶቼን ሁሉ በዚያ ለመቆየት

"ብደክም እንኳን ዘመኔን ሁሉ በዚያ ለመቆየት"

የመለቀቅ/የመታደስ ጊዜዬ እስኪደርስ

"መለቀቅ/መታደስ" የሚለው ረቂቅ ስም "ተለቀቀ/ታደሰ" በሚል ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እስከምለቀቅ ድረስ" ወይም "አንተ እስከምትለቀኝ/እስክታድሰኝ ድረስ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

Job 14:15-17

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገሩን ይቀጥላል፡፡

እኔ መልስ እሰጣለሁ

"እኔ ምላሽ እሰጣለሁ"

ትፈልገኛለህ/ትናፍቃለህ

"ፍላጎት" የሚለው ስም "ፈለገ" ወይም "ወደደ" በሚል ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "አንተ ትፈልጋለህ/ትናፍቃለህ" ወይም "አንተ ትወዳለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

የእጆችህ ስራ

እዚህ ስፍራ የእግዚአብሔር እጆች የሚወክሉት እርሱ ነገሮችን መስራቱን ነው፡፡ ኢዮብ ራሱን የእግዘአብሔር የእጆቹ ስራ አድርጎ ይገልጻል፡፡ "አኔን ያበጀኸኝ አንተ ነህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና አንደኛ፣ ሁለተኛ እና ሶስተኛ መደብ የሚሉትን ይመልከቱ)

ቁጥር እና መቆጣጠር/መከታተል

እነዚህ ሁለት ግሶች ሁለቱ በአንድነት አንድን ድርጊት ይገልጻሉ፡፡ "በንቃት ትከታተላለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሄንዲየዲስ/ሁለት ቃላት ‘እና' በሚል አያያዥ ቃል የሚገኛኙበትና አንድን ጥልቅ ሀሳብ ለመግለጽ የሚያገለግል ዘይቤያዊ አነጋገር)

የእግሬ ኮቴ/እርምጃዬ

እርምጃ/ኮቴ የሚለው የሚወክለው ህይወቱን ወይም ያደረገውን ነው፡፡ "ህይወቴ" ወይም "ያደረግኳቸው ነገሮች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

አትቆጥርብኝም… መተላለፌን ይቅር ትላለህ…አንተ ትሸፍንልኛለህ

እነዚህ ሶስት ሀረጎች ተመሳሳይ ሀሳብን ይገልጻሉ፣ በአንድነት የዋሉት እግዚአብሔር ይቅር እንደሚለው ያለውን እርግጠኝነት/ልበሙሉነት ለመግለጽ ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ኃጢአቴን አትቆጥርብኝም

የኢዮብን ኃጢአት አለመቁጠር የሚወክለው ስለ እርሱ ኃጢአት አለማሰብን ነው፡፡ "ኃጢያቴን አትመለከትም" ወይም "ስለ እኔ ኃጢአት አታስብም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

መተላለፌን በከረጢት ውስጥ ታትምበታለህ

መተላለፍን በከረጢት ማተም የሚለው የሚገልጸው ኃጢአትን መሸፈን እና ስለ እርሱ ማሰብን አለመፍቀድ ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አንድን ነገር በከረጢት ውስጥ እንደደበቀ ሰው መተላለፌን ማሰብ አትፈቅድም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በደሌን ትሸፍናለህ/ይቅር ታላለህ

እንዳይታይ የአንድን ሰው በደል መሸፈን የሚወክለው ስለዚያ ማሰብን አለመፍቀድን ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "በደሌን ትሸፍናለህ" ወይም "ኃጢአቴን ትተውልኛለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 14:18-19

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገሩን ይቀጥላል፡፡

ተራሮች ይወድቃሉ ከስፍራቸውም ይጠፋሉ

እዚህ ላይ "ከስፍራቸው ይጠፋሉ/መታሰቢያ ያጣሉ" የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ሲሆን ትርጉሙ ሙሉ ለሙሉ ይደመሰሳሉ ማለት ነው፡፡ ይህ ሀረግ "መውደቅ" የሚለውን ቃል በማብራራት ጥፋቱ ሙሉ ለሙሉ መሆኑን ያጎላል፡፡ "ታራሮች ሙሉ ለሙሉ ይፈራርሳሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

አለቶች ከስፍራቸው ይወገዳሉ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አለቶች ከስፍራቸው ቁልቁለል ይንከባለላሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ልክ እንደዚህ፣ የሰውን ተስፋ ትደመስሳለህ

በቋንቋችሁ ቀላል ከሆነ፣ ይህንን ሀረግ በቁጥር 18 መጀመሪያ ላይ መጻፍና ጽሁፉን በዚያው መሰረት ማስተካከል ትችላላችሁ፡፡ "ልክ እንደ ምድር አፈር፣… የሰውን ተስፋ ትደመስሳለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ ሚለውን ይመልከቱ)

አንተ የሰውን ተስፋ ትደመስሳለህ/ታጠፋለህ

ተስፋን መደምሰስ የሚወክለው/የሚገልጸው ሰዎች ተስፋ የሚያደረጓቸው ነገሮች እንዳይሆኑ ማድረግ ነው፡፡ "አንተ የሰው ተስፋ እውን እንዳይሆን ታግዳለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የሰው ተስፋ

"ተስፋዎች" የሚለው ረቂቅ ስም "ተስፋ" በሚለው ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ሰው ተስፋ የሚያደርጋቸው ነገሮች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

Job 14:20-22

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገሩን ይቀጥላል፡፡

አንተ ሁልጊዜም እርሱን ታሸንፋለህ

"እርሱ" የሚለው ቃል ማናቸውንም ሰው ያመልክታል፡፡ "አንተ ሁልጊዜም ሰውን ታሸንፋለህ" ወይም "አንተ ሁልጊዜም ሰዎችን ታሸንፋለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

እርሱ ያልፋል

ማለፍ የሚለው የሚወከወለው/የሚገልጸው ሞትን ነው፡፡ "እርሱ ይሞታል" (ዩፊምዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ ፊቱን ትለውጣለህ

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ከመሞቱ አስቀድሞ የሚገጥመው ስቃይ ፊቱ እንዲጨማደድ ያደርጋል ወይም 2) አንድ ሰው ሲሞት፣ እግዚአብሔር የሰውየውን ፊት የተለየ ያደርገዋል

እንዲሞት ይተወዋል/በሞት ይሸኘዋል

ይህ የሚገልጸው እንዲሞት ማድረግን/መፍቀድን ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ዝቅ ከተደረጉ/ከተዋረዱ

መዋረድ/ዝቅ መደረግ የሚለው የሚገልጸው ወይም የሚወክለው እንዲያፍር መደረግን ነው፡፡ "እንዲዋረዱ ከተደረገ" ወይም "ሰዎች ካሳፈሯቸው/ካዋረዷቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 15

Job 15:1-3

ቴማናዊው ኤልፋዝ

ይህ የወንድ ስም ነው፡፡ የቴማን ሰዎች ቴማናውያን ተብለው ይጠራሉ፡፡ ይህ ስም በኢዮብ 2፡11 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ብልህ ሰው እርባና ቢስ መልስ ይሰጣልን፣ ደግሞስ ራሱን በምስራቅ ነፋስ ይሞላልን?

ኤልፋዝ ይህን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚጠቀመው ኢዮብን ለመገሰጽ ነው፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር/መግለጫ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ብልህ ሰው እርባና ቢስ ምላሽ መስጠት የለበትም አሊያም ራሱን በምስራቅ ነፋስ መሙላት የለበትም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ራሱን በምስራቅ ነፋስ መሙላት

ነፋስ የሚወክለው ባዶነትን ነው፡፡ ይህ ሀረግ የሚናገረው ያ ሰው በነፋስ እንደተሞላ ሁሉ ባዶ እና ትርጉም አልባ ቃላትን የሚናገርን ሰው ነው፡፡ "ራሱን በባዶ ቃላት የሞላ" ወይም "ትርጉም የለሽ ቃላት ብቻ ያሉት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የምስራቅ ነፋስ

"ሞቃት አየር" ወይም "የበረሃ ነፋስ"

ትርፍ በሌለው ወሬ ወይም አንዳች መልካም ማድረግ በማይችልበት ንግግሮች ምክንያት ማቅረብ/መከራከር ይኖርበታልን?

ኤልፋዝ ይህን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚጠቀመው ኢዮብን ለመገሰጽ ነው፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር/መግለጫ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ትርፍ በሌለው ወሬ አሊያም አንዳች መልካ ማድረግ በማይችልበት ንግግር ምክንያት ማቅረብ/መከራከር የለበትም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 15:4-6

የእግዚአብሔርን ክብር ቀንሰሃል

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "በተናገርከው እና ባደረግከው ምክንያት፣ ሌሎች ከእንገዲህ እግዚአብሔርን አያከብሩም" ወይም 2) "አንተ ከእንግዲህ እግዚአብሔርን አታከብርም"

መቀነስ

ማሳነስ/ትንሽ ማድረግ

ለእርሱ ያለን መሰጠት ዘግተሃል

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) " ሌሎች ራሳቸውን ለእግዚአብሔር እንዳይሰጡ ይህን አስቸጋሪ አድረገሃል" ወይም 2) "አንተ ከእንግዲህ ራስህን ለእግዚአብሔር አሳልፈህ አትሰጥም"

መዝጋት

የአንድን ሰው መንገድ ማገድ

መሰጠት

"በተመስጦ" ወይም "ግድ መሰኘት/ዋጋ መስጠት"

ኃጢአትህ አንደበትህን ታስተምራለች

ይህ የሚገልጸው "ኃጢአት" አስተማሪ እንደሆነ ተደርጎ እና የኢዮብ አንደበት/አፍ ደግሞ የተገለጸው ይህን እየተማረ እንደሆነ ተደርጎ ነው፡፡ ይህ ማለት ደግሞ ንግግሩ በኃጢአቱ እጅግ ተጽዕኖ አድሮበታል ማለት ነው፡፡ "ኃጢአትህ እንደ አስተማሪ ነው አፍህ ደግሞ እንደ ተማሪ ነው" ወይም "አሁን እንደምትምትናገረው እየተናገርክ የምትገኘው በኃጢአትህ ምክንያት ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

አፍህ/አንደበትህ

ይህ ስለ ኢዮብ ይናገራል፣ ነገር ግን ለተናገረው ትኩረት ለመስጠት የሚያመለክተው ስለ "አንደበቱ/አፉ" ነው፡፡ "አንተ ተናገርክ" ወይም "የተናገርከውን የተናገርከው አንተ ነህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

የተንኮለኛ ሰው ምላስ መያዝ

ይህ የሚያመለክተው ተንኮለኛ ሰው እንደ "ምላሱ" የሚናገርበትን መንገድ ነው፡፡ "ተንኮለኛ ሰው በሚናገርበት መንገድ መናገር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ተንኮለኛ ሰው

ለእነርሱ በመዋሸት ሌሎችን የሚጎዳ ሰው

የእኔ ሳይሆን፣ የገዛ አንደበትህ ይወቅስሃል

ይህ በተናገሩት ላይ ትኩረት ለመስጠት በ"አንደበታቸው/አፋቸው" አማካይነት ኢዮብን እና ኤልፋዝን ያመለክታል፡፡ "አንተ እኔ በተናገርኩት ሳይሆን ራስህ በተናገርከው በራስህ ላይ ትፈርዳለህ" ወይም "የምፈርድብህ እኔ ሳልሆን በተናገርከው በራስህ ላይ ትፈርዳለሁ" በሚለው ወስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

የራስህ ከንፈሮች ይመሰክራሉ

ይህ ስለ ኢዮብ ይናገራል፣ ነገር ግን በተናገረው ላይ ትኩረት ለመስጠት "ከንፈሮቹን" ያመለክታል፡፡ "የገዛ ቃላቶችህ" ወይም "አንተ ትመሰክራለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 15:7-9

አጠቃላይ መረጃ፡

እያንዳንዱ ቁጥር ሁለት ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄን የያዘ ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚሉትን ይመልከቱ)

በመጀመሪያ የተወለድከው/የተፈጠርከው ሰው አንተ ነህን?

እዚህ ስፍራ በውስጠ ታዋቂነት የተቀመጠው ምላሽ "አይደለም" የሚል ነው፡፡ ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር/በገለጻ መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "በመጀመሪያ የተወለድከው ሰው አንተ አይደለህም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ከኮረብቶች አስቀድሞ አንተ ወደ ህልውና መጥተሃልን/ኮረብቶች ሳይፈጠሩ ተፈጥረሃልን?

እዚህ ስፍራ በውስጠ ታዋቂነት የተቀመጠው ምላሽ "አይደለም" የሚል ነው፡፡ ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር/በገለጻ መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ከኮረብቶቸ አስቀድመህ አልተፈጠርክም/ከእነርሱ አስቀድመህ ወደ ህልውና አልመጣህም" ወይም "እግዚአብሔር ኮረብቶችን ወደ መኖር ከማምጣቱ አስቀድሞ አንተን ወደ መኖር አላመጣህም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ ነበርክን

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር አምጥቶህ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔርን ምስጢራዊ እውቀት ሰምተሃል?

እዚህ ስፍራ በውስጠ ታዋቂነት የተቀመጠው ምላሽ "አይደለም" የሚል ነው፡፡ ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር/በገለጻ መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አንተ የእግዚአብሔርን ምስጢራዊ እውቀት አልሰማህም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ጥበብን በራስህ ትወስናታለህ?

ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እውቀትን በራሱ ሊወስናት እንደማይችል ትኩረት ይሰጣል፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር/በገለጻ መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እውቀትን በራስህ ልክ ልትወስናት አትችልም" ወይም "ብቸኛው ጠቢብ ሰው አንተ አይደለህም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እኛ የማናውቀው አንተ የምታውቀው ምን ነገር አለ?

እዚህ ስፍራ በውስጠ ታዋቂነት የተቀመጠው ምላሽ "ምንም የለም" የሚል ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር/በገለጻ መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እኛ የማናውቀው አንተ የምታውቀው ምንም ነገር የለም" ወይም "አንተ የምታውቀውን ነገር ሁሉ፣ እኛም ደግሞ እውቃለን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

በእኛ ውስጥ የሌለ አንተ የምትረዳው ምን ነገር አለ?

ይህ የሚናገረው ሰዎቹ ያላቸው መረዳት "በውስጣቸው" እንዳለ አንድ ነገር ሆኖ ነው፡፡ "አንተ የምትረዳውን ማናቸውንም ነገር እኛም ደግሞ እንረዳዋለን" ወይም "አንተ የምታውቀውን ነገር ሁሉ እኛም ደግሞ እናውቃለን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 15:10-11

ከእኛ ጋር ፀጉራቸው ሽበት የሆነ እና በጣም ያረጁም ሰዎች ይገኛሉ

ኤልፋዝ ስለ ራሱ እና ከአዛውንቶች፣ እንደዚህም ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የመጣውን ጥበብን ስላገኙ ሌሎች ሰዎችም ልክ እነዚህ ሽማግሌዎች በአካል ከእነርሱ ጋር እንደሚገኙ አድርጎ ይናገራል፡፡ "እኛ ከአዛውንቶች፣ ከአባትህ አስቀድሞ ከተወለዱ ሰዎች ጥበብ አግኝተናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዘአብሔር ማጽናናት… በእርጋታ የተነገረህ ቃል አነሰብህን?

ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ ክስን ያዘለ ነው፣ ለዚህ ጥያቄ በውስጠ ታዋቀነት የቀረበው ምላሽ "አዎን" የሚል ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር/በገለጻ መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የእግዚአብሔር ማጽናናት ጥቂት ነገር ሆኖንሃል፣ በእርጋታ ወደ አንተ የመጣውን ምክር ንቀሃል"

ማጽናናት

"ማበርታት" ወይም "ርህራሄ/አዘኔታ"

Job 15:12-14

ስለምን ልብህ ያሸፍትሃል?

እዚህ ስፍራ "ልብ" የሚወክለው የአንድን ሰው ስሜት ነው፡፡ "ለምን ስሜትህ ይዞህ ይሄዳል?" ወይም "ለምን ስሜትህ ውሳኔህን እንዲመራ ትፈቅዳለህ?" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ፈሊጣው ነገጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

ለምን ዐይኖችህ ይፈጣሉ

ይህ ማንላበት ኢዮብ መቆጣቱን ሊያመለክት ይችላል፤ በተለይም የዐይኖቹን ሁኔታ ሊያመለክት ይችላል፡፡ "ስለ ምን ዐይኖችህ የተቆጡ መሰሉ" ወይም "ለምን ተቆጣህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

መንፈስህን መልስ

እዚህ ስፍራ "መንፈስህ" የሚለው የሚያመለክተው መላውን ማናነትን ነው፡፡ "ራስህን መልስ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

እንዲህ ያሉ ቃላትን ከአንደበትህ አስወግድ

ይህ የሚገልጸው የእርሱን ንግግር ነው፡፡ "አንተ በእርሱ ላይ የማይገባ ነገሮችን ተናግረሃል" (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የተወለደ እርሱ …ሰው ምንድን ነው

እነዚህ ሁለት ጥያቄዎች በመሰረቱ አንድ አይነት ናቸው፤ በአንድነት የቀረቡት ሰው ፍጹም መሆን እንደማይችል ለማጉላት ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ንጹህ ይሆን ዘንድ ሰው ምንድን ነው?

ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የተጠየቀው ሰው ሙሉ ለሙሉ "ንጹህ" መሆን እንደማይችል ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር/በገለጻ መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ሰው ሙሉ ለሙሉ ንጹህ ሊሆን አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ንጹህ

እግዚአብሔር በመንፈሳዊነት ተቀባይነት አለው ብሎ የሚቆጥረው ሰው በአካሉ ንጹህ እንደሆነ ተደርጎ ተገልጽዋል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከሴት የተወለደ ሰው ጻድቅ ይሆን ዘንድ እርሱ ማን ነው?

ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የተጠየቀው ሰው ሙሉ ለሙሉ "ጻድቅ" መሆን እንደማይችል ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር/በገለጻ መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ከሴት የተወለደ ሰው ሙሉ ለሙሉ ጻድቅ ሊሆን አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 15:15-16

እነሆ

ይህ ቃል እዚህ ስፍራ ያገለገለው የኢዮብን ትኩረት ቀጥሎ ወደሚነገረው ነገር ለመሳብ ነው፡፡ "አድምጥ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

የእርሱ ቅዱሳን

"የእርሱ መልአክት"

ንጹህ

እግዚአብሔር በመንፈሳዊነት ተቀባይነት አለው ብሎ የሚቆጥረው በአካል ንጹህ እንደሆነ ተደርጎ ተወስዷል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በእርሱ ዐይኖች/እይታ

እዚህ ስፍራ እይታ የሚወክለው ፍርድን ወይም ሚዛንን ነው፡፡ "በእርስ ፍርድ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አስፀያፊ እና ብልሹ

እነዚህ ሁለት ቃላት በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ ደግሞም ሰው ምን ያህል ክፉ እንደሆነ ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

ኃጢአትን እንደ ውሃ የሚጠጣ

ይህ ኃጢአት እንደ ውሃ ልትጠጣው የምትችለው ነገር እንደሆነ አድርጎ ይገልጻል፡፡ ክፉ ሰው ኃጢአት መስራትን ምን ያህል እንደሚፈልግ ያነጻጸረው በፈቃዱ ቀዝቃዛ ውሃ ለመጠጣት ካለው ፍላጎት ጋር ነው፡፡ "ንጹህ ኩባያ ውሃ ለመጠጣት ያላቸውን ፍላጎት ያህል ኃጢአትን የሚወዱ" ወይም "ውሃ የሚጠጡትን ያህል ደጋግመው ክፉ ስራ የሚሰሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 15:17-18

እኔ አሳይሃለሁ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "እኔ አብራራልሃለሁ" ወይም "እኔ ግልጽ አደርግልሃለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ አሳውቃለሁ

"እኔ አውጃለሁ"

አባቶቻቸው አልደበቁም

ኤልፋዝ አባቶቻቸው በአላማ እነዚህን ነገሮች እንዳስማሯቸው ትኩረት ይሰጣል፡፡ "አባቶቻቸው በግልጽ አስተምረዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ምፀት/ላይዶክስ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 15:19-21

ምድሪቱ ለብቻቸው የተሰጣቸው

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር ምድሪቱን ለብቻቸው የሰጣቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

በመካከላቸው ማንም እንግዳ አላለፈም

ይህ ማለት ምንም ባዕድ በመካከላቸው አልኖረም፣ በተለይ በአህዛብ ሃይማኖት ተጽእኖ ስር እንዳይወድቁ ይህ ሆነ፡፡ "ከሌላ አገር ማንም ሰው መጥቶ ስለ እግዚአብሔር የተሳሳተ ሃሳብ እንዲኖራቸው ምክንያት አልሆነም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በህመም ይጥመለመላል

"ብዙ ስቃይ ማየት፡፡" ይህ የአካል ወይም የስሜት ስቃይ ነው

የተመደቡ አመታት ቁጥር

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አግኢአብሔር የመደባቸው አመታት ሁሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የተመደቡ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "የተዘጋጁ" ወይም "የተለዩ" (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በጆሮቹ የፍርሃት ድምጽ

"ሳያቋረጥ የሚያስፈራውን ድምጽ ይሰማል"

Job 15:22-24

አያያዥ ሀሳብ፡

ኤልፋዝ በኢዮብ 15፡20 መግለጽ የጀመረውን ክፉ ሰው ማብራራቱን ይቀጥላል

ከጨለማ መመለስ

እዚህ ስፍራ "ጨለማ" ለእግር ወይም እድለቢስነት ዘይቤያዊ አገላለጽ ነው፡፡ "መጥፎ እድልን ማምለጥ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሰይፍ ይጠብቀዋል

እዚህ ስፍራ "ሰይፍ" ክፉ ሰውን ለመግደል የሚጠብቅን ጠላት የሚወክል ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ሰው ይገድከኛል ብሎ ፈርቷል፡፡ "አንድ ሰው ይገድለኛል ብሎ ፈርቷል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ ወይም 2) መገደሉ የተረጋገጠ ነው፡፡ "ሊገድለው የሚጠብቅ ሰው አለ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

ለእንጀራ/ለዳቦ

እዚህ ስፍራ "እንጀራ/ዳቦ" የሚያመለክተው በአጠቃላይ ምግብን ነው፡፡ "ለ እንጀራ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

የቀን ጨለማ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "የጥፋት ቀን" ወይም "የሞቱ ሰአት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በእጅ ላይ ያለ ነገር

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "በቶሎ የሚመጣ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ጥፋት እና ጭንቀት አስፈራርተውታል፤ በእርሱ ላይ አይለዋል

"ጥፋት" እና "ጭንቀት" የሚሉት ቃላት በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖራቸው፣ የስሜቱን ጥልቀት ያጎላሉ፡፡ እዚህ ስፍራ እነዚህ ስሜቶች ክፉውን ሰው የሚያጠቁ ጠላቶች እንደሆኑ ተደርገው ተነግረዋል፡፡ (ጥንድ ትርጉም እና ሰውኛ የሚሉትን ይመልከቱ)

አይለውበታል

"ከአቅም በላይ" ወይም "ማሸነፍ"

ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ንጉሥ

ይህ ጥፋቱ እና ጭንቀቱ ለጦርነት እንደተዘጋጀ ንጉሥ እንዴት በእርሱ ላይ እንዳየሉበት ያነጻጽራል፡፡ "ልክ ለጦርነት እንደ ተዘጋጀ ንጉሥ በእርሱ ላይ ተነስተውበታል/አይለውበታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 15:25-26

እጁን በእግዚአብሔር ላይ አንስቶ

"እጁን በእግዚአብሔር ላይ አወዛውዟል፡፡" ይህ የጠብ ምልክት ነው፡፡ (ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት)

በእግዚአብሔር ላይ መነሳት

ይህ ክፉ ሰው በእግዚአብሔር ላይ እርሱን ለማጥቃት ይመስል በጠብ የሚያደርገውን የሚገልጽ ነው፡፡ "እግዚአብሔርን ማጥቃት/መድፈር" ወይም "በእግዚአብሔር ላይ መነሳት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በበወፍራም ጋሻ

"በእርሱ ጠንካራ ጋሻ"

Job 15:27-28

ይህ እውነት ነው

"ይህ" የሚለው በቀደመው ቁጥር ክፉ ሰው በእግዚአብሔር ላይ መነሳቱን ያሳያል

ፊቱን በስቡ ሸፍኗል፣ ደግሞም በሽንጡ ስቡን አከማችቷል

ክፉ ሰው እንደ ሰባ እና ደካማ ሰው ተገልጽዋል፤ እርሱ ግን እግዚአብሔርን እስከሚያሸንፍ ድረስ ጠንካራ እንደሆነ እንደሚያምን ተደርጎ ቀርቧል፡፡ "እርሱ ፊቱ እና ሽንጡ በስብ የተሸፈነ ደካማ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)

ማንም ሰው በማይኖርበት

"ወና በሆነ ስፍራ"

ክምር

እርባና ቢስ የሆኑ ነገሮች ቁልል

Job 15:29-30

ባለጸጋ አይሆንም፣ ሀብቱ አይቆይም

እነዚህ ሁለት ምፀታዊ አገላለጾች የብልጽግና ተቃራኒው እንደሚደርስበት፣ ማለትም ደሃ እንደሚሆን ይናገራሉ፡፡ "ይደኸያል፣ ገንዘቡ ሁሉ ይጠፋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ምፀት/ላይዶክስ የሚለውን ይመልከቱ)

ከጨለማ ስፍራ

ጨለማ እዚህ ስፍራ ላይ ሞትን ይወክላል፡፡ "በሞት ጨለማ ውስጥ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ቅርንጫፎቹን እሳት ያደርቃቸዋል

እዚህ ስፍራ እሳት/ነበልባል የሚወክለው የእግዚአብሔርን ፍርድ ሲሆን፣ የቅርንጫፎች መድረቅ የሚወክለው አንድም የክፉ ሰው ሃብት መጥፋቱን፣ አሊያም የሚሞት መሆኑን ነው፡፡ "እሳት የእርጥብ እንጨትን እርጥበት እንደሚያደርቅ፣ እግዚአብሔር ያለውን ነገር ሁሉ ይወስድበታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔር አፍ እስትንፋስ

እዚህ ስፍራ የእግዚአብሔር "እስትንፋስ" የሚለው የሚወክለው የእርሱን ፍርድ ነው፡፡ "የእግዚአብሔር እስትንፋስ" ወይም "የእግዚአብሔር ፍርድ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ይሄዳል/ይሸኛል

ይህ የሚያመለክተው የእርሱን መሞት ነው፡፡ "እርሱ ይሞታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዩፊምዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 15:31-33

ሽላማቱ ረብ የለሽነት ይሆናል

ይህ የሚያመለክተው በማይረቡ ነገሮች ከታመነ የሚደርስበት ነገር ነው፡፡ "በእነርሱ ላይ ከታመነ፣ ሽልማቱ የማይረቡ ነገሮች ይሆናሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተተወ/የተዘለለ የሚለውን ይመልከቱ)

ቅርንጫፎቹ አይለመልሙም

ይህ የሚገልጸው ከግንዱ ተገነጥሎ እንደ ደረቀ ቅርንጫፍ የሚገረጣ ወይም የሞተ የሚመስልን ሰው ነው፡፡ "የሞተ ዛፍ ቅርንጫፍ እንደማይለመልም እርሱም የሞተ ይመስላል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ፍሬውን…ይጥላል፣ አበባውን … ያረግፋል

እነዚህ ሁለት መስመሮች ተመሳሳይ ትርጉን የሰጣሉ፤ የተደገሙት ነገሩ እንደሚሆን ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ወይን ተክል ያልበሰለ የወይን ፍሬውን ይጥላል

ይህ የሚናገረው ያልበሰለ የወይን ፍሬውን እደሚጥል የወይን ተክል ክፉ ሰው ይበልጥ እየደከመ እና እየሞተ የሚሄድ መሆኑን ነው፡፡ "የወይን ተክል ያልበሰለ ፍሬውን እንደሚጥል፣ ክፉ ሰው ጥንካሬው ይክደዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ወይራ ዛፍ አበባውን ያረግፋል

ይህ የሚናገረው የወይራ ዛፍ አበባውን እንደሚያረግፍ ክፉ ሰው እየደከመ እና እየሞተ እንደሚሄድ ነው፡፡ "የወይራ ዛፍ አበባውን እንደሚያረግፍ ክፉ ሰውም ጥንካሬው ይክደዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 15:34-35

እግዚአብሔር የለሽ የሆኑ ሰዎች ጉባኤ

"እግዚአብሔር የለሽ የሆኑ ሰዎች ስብስብ"

በጉቦ የተሰራውን ድንኳናቸውን እሳት ይበላዋል

"በጉቦ የተሰራ ድንኳን" የሚለው ሀረግ እነዚህ ክፉ ሰዎች ድንኳናቸው የገዙት በጉቦ ባገኙት ገንዘብ ነው ማለት ነው፡፡ "ከጉቦ ባገኙት ገንዘብ የገዙት ድንኳን በእሳት ይቃጠላል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሀብት ንብረት የሚለውን ይመልከቱ)

ተንኮልን ጸንሰው ኃጢአትን ይወልዳሉ፤ማህጸናቸው ማታለልን ይጸንሳል

ተመሳሳይ ሀሳብ ሶስት ጊዜ የሚደጋገመው እነዚህ ሰዎች ምን ያህል ክፉ ነገር እንደሚያደርጉ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ ይህ ክፉ ነገሮችን ለማድረግ የሚያቅዱ እና ያንንም የሚያደርጉ ሰዎች፣ ሴት ጸንሳ እንደምትወልድ እነዚህም ክፉ ነገርን ጸንሰው እንደሚወልዱ ይገልጻል፡፡ "እነርሱ ተንኮልን ለማድረግ አቅደው ክፉ ነገሮችን ያደርጋሉ፤ ሁልጊዜም ሌሎችን ለማታለል ያቅዳሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

ማህጸናቸው ይጸንሳል

እዚህ ስፍራ "ማህጸን" የዋለው ጸንስ የሚጸነሰው በማህጸን እንደሆነ ሁሉ ይህን ትኩረት ሰጥቶ ከሰው ጋር አያይዞ ለመግለጽ ነው፡፡ "ይጸንሳሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 16

Job 16:1-3

እናንተ ሁላችሁ የምታስጨንቁ አጽናኖች ናችሁ

"እኔን ከማጽናናት ይልቅ፣ ሁላችሁም ታስጨንቁኛላችሁ"

እስከ መቼ ማለቂያ የሌለው የማይረባ ቃል ትጠቀማላችሁ?

ኢዮብ ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚጠቀመው እርባና የሌላቸውን ቃላት መናገራቸውን እንዲያቆሙ መፈለጉን ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር/በገለጻ መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እርባና ቢስ የሆኑ ቃሎቻችሁ ማብቂያ ቢኖራቸው ምን ያህል ደስ ባለኝ!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በዚህ አይነት መልስ የምትሰጡት ምን ሆናችሁ ነው?

ኢዮብ ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚጠቀመው ኤልፋዝን ለመገሰጽ ነው፡፡ እዚህ ስፍራ "አንተ" የሚለው ቃል ነጠላ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተውም ከኢዮብ ጋር ንግግሩን የጨረሰውን ኤልፋዝን ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር/በገለጻ መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ኤልፋዝ ሆይ፣ ለእኔ እንዲህ ያለ መልስ መስጠትህን ማቆም ይኖርብሃል!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 16:4-5

እኔም ቃላትን አቀናብሬ ማሳመር እችላለሁ

ኢዮብ እርባና ስለሌላቸው ነገሮች ስለማሰብ የሚናገረው እርሱም ቃላትን አጠረቃቅሞ መናገር እንደማይቸግረው ለመግለጽ ነው፡፡ "እኔም ቃላትን አሳክቼ መናገር እችላለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እራሴን እነቀንቃለሁ

አይሆንም የሚለውን ለማሳየት የሚደረግ ድርጊት፡፡ (ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

በመሳለቅ

"መሳለቅ" የሚለውን ቃል በግስ መልኩ መጠቀም ይቻላል፡፡ "በእናንተ ላይ መሳለቅ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

በአንደበቴ አበረታታችሁ ነበር፣ የከንፈሬ ቃል ለእናንተ ረፍት በሆናችሁ ነበር!

"አንደበት/አፍ" እና "ከንፈር" ሰው አንደበቱን እና ከንፈሩን በመጠቀም ለሚናገራቸው ቃለት ወይም መልዕክቶች ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ እዚህ ስፍራ ኢዮብ በሽሙጥ እየተናገረ ሲሆን ከሚናገረው ተቃራኒውን ማለቱ ነው፡፡ "በእርግጥ ንግግሬ እናንተን አያበረታታም! በእርግጥ ሀዘናችሁን አያቀልም" ወይም "እናንተ አስቀድማችሁ እኔን በተናገራችሁበት መንገድ እናንተን በመናገር፣ እናንተን አላበረታታም ወይም ሀዘናችሁን አላቀልም!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ምፀት የሚሉትን ይመልከቱ)

በአንደበቴ/በአፌ

እዚህ ስፍራ የኢዮብ "አፍ" የሚወክለው እርሱ የተናገረውን ነው፡፡ "እኔ በምናገረው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በከንፈሬ ንግግር/በአፌ ቃል

እርሱ ለተናገራቸው ቃላት ወይም መልዕክቶች ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "የማጽናናት ቃሎቼ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ምፀት የሚሉትን ይመልከቱ)

እረፍት በሆናችሁ

ይህ ሀዘን አካላዊ ከባድ ሸክም እንደሆነ ይናገራል፡፡ "ሀዘናችሁን ያቀልላችኋል" ወይም "ሀዘናችሁ እንዲቀል ይረዳችኋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 16:6-8

ሀዘን

ኢዮብ ያልተጠበቀና በቃላት ለመግለጽ የሚያዳግት "ታላቅ ሀዘን እና የስሜት ስቃይ" ቤተሰቡን እና ጤናውን በማጣት አጋጥሞታል

እንዴት እጸናናለሁ?

ኢዮብ ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የተጠቀመው ዝም ማለቱ ስቃዩን ለማቃለል እንዳልረዳው ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በገለጻ/ዐረፍተ ነገር መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ይህ ምንም አልረዳኝም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ነገር ግን አሁን፣ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ

ኢዮብ አሁን ማጉረምረሙን ወደ እግዚአብሔር ዞር ያደርገዋል

ቤተሰቤን ሁሉ አጠፋህ

"ቤተሰቤን ሁሉ ደመሰስህ"

አንተ እኔን አደረቅኸኝ

ይህ ማለት የኢዮብ አካል ከሳ ቆዳው ተሸበሸበ ማለት ነው፡፡ "ከሰውነት ተራ ወጣሁ አካሌን አከሳኸው" (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ ራሱ ይመሰክርብኛል

ኢዮብ የሰውነቱን መክሳት በእርሱ ላይ ከሳሽ እንደሆነ አድርጎ ያቀርበዋል፡፡ "ደግሞም ይህ ሰዎች እኔን ኃጢአተኛ አድርገው እንዲያስቡ ያደርጋቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የሰውነቴ ክሳት በእኔ ላይ ተቃዋሚ ሆኖ ይነሳብኛል፣ ምስክርም ይሆንብኛል

ኢዮብ የአካሉን መክሳት በእርሱ ላይ ከሳሽ እንደሆነበት ይገልጻል፡፡ "ምን ያህል እንደከሳሁ ይመለከታሉ፣ ይህም ደግሞ እኔ ኃጢአተኛ እንደሆንኩ ያረጋግጣል ብለው ያስባሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ፊቴ ላይ

እዚህ ስፍራ ኢዮብ የተጠቀሰው በእርሱ "ፊቱ" ነው፡፡ "በእኔ ላይ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 16:9-10

እግዚአብሔር በቁጣው በጫጨቀኝ፣ ደግሞም አሳደደኝ… ቀዳዶ ጣለኝ

ይህ የሚገልጸው እግዚአብሔር በኢዮብ ላይ ስቃይ ያደረሰበት ያደነውን ገድሎ እንደሚመገብ እንስሳ አድርጎ ነው፡፡ "እግዚአብሔር በእኔ በጣም ስለተቆጣ የዱር አውሬ በጥርሱ እንደሚቦጫጭቅ አካሌን ጠላት ሆኖ በጣጥሶታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ጠላቴ

ኢዮብ እግዚአብሔርን ትልቅ መከራ እንዳደረሰበት እንደ "ጠላቱ" አድርጎ ይገልጻል

ዐይኖቹን በእኔ ላይ አጣብቋል/ተክሏል

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "ዐይኑን ተከለብኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሰዎች በመገረም አፋቸውን ከፍተዋል

"አፍ መክፈት" የሚለው በመደነቅ አፍን ከፍቶ መመለከት ማለት ነው

Job 16:11-12

አምላክን ለማይወዱ ሰዎች አሳልፎ ሰጠኝ፣ በክፉ ሰዎች እጅ ላይ ጣለኝ

እነዚህ ሁለት መስመሮች በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ በአንድነት ሆነው የኢዮብን በእግዚአብሔር የመካድ ስሜት ያጎላሉ፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አሳልፎ ሰጠኝ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "በቁጥጥራቸው ስር አደረገኝ"

በእጃቸው ላይ ጣለኝ

እዚህ ስፍራ የሰው "እጅ" የሚያመለክተው በ"ቁጥጥሩ ስር" ማድረግን ነው፡፡ "ከተጽዕኗቸው ነጻ አውጣኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ደግሞም እርሱ ሰባብሮኛል

ኢዮብ መከራውን እና ተስፋ መቁረጡን የሚገልጸው እርሱ ራ ወደ ትንንሽ ነገሮች እንደተሰባበረ አድርጎ ነው፡፡ "ነገር ግን የሚሰማኝ እርሱ እንደሰባበረኝ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ቆራርጦ ጣለኝ

ኢዮብ የሚናገረው እግዚአብሔር ስቃይ እንዳደረሰበት እና ተስፋ እንዳስቆጠረው፣ እንደዚሁም ወደ ቁርጥራጭ ነገርነት እንዳደቀቀው ነው፡፡ "አንገቴን አንቆ ትንንሽ ነገር አድርጎ አድቅቆኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ደግሞም አላማው አድርጎ አስቀምጦኛል

ኢዮብ ራሱን የእግዚአብሔር ጥቃት ትኩረት እንደሆነና እግዚአብሔር ቀስቱን የሚያነጣጥርበት ኢላማው እንዳደረገው ይናገራል፡፡ "ኢላማው አድርጎኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 16:13-14

የእርሱ ቀስተኞች ዙሪያዬን ከበውኛል

ኢዮብ ስለ ራሱ የሚናገረው የእግዚአብሔር ጥቃት ትኩረት እንደሆነ፣ እግዚአብሔር እርሱን እንደ ጥቃት ኢላማ ከፍ አድርጎ እንዳስቀመጠው የእግዚአብሔር ቀስተኞች ሊያጠቁት እንደከበቡት አድርጎ ነው፡፡ "የእርሱ ቀስተኞች ዙሪያዬን ከበውኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ኩላሊቴን በስቶታል፣ ለአፍታም አልተወኝም፣ ሀሞቴን በምድር ላይ አፍስሶቶታል

ኢዮብ የደረሰበትን መከራ ስሜት የሚገልጸው እግዚአብሔር አካሉን በቀስቶች እንደበሳው በማነጻጸር ነው፡፡ እዚህ ስፍራ "እግዚአብሔር" የሚለው የሚወክለው እርሱ የሚወረውራቸውን ቀስቶች ነው፡፡ "ኩላሊቴን እና ጉበቴን የእግዚአብሔር ቀስቶች እንደወጉኝ፣ ሀሞቴ በምድር ላይ እንደፈሰሰ ይሰማኛል፡፡ እርሱ አልተወኝም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ቅጥሬን አፈረሰው

ኢዮብ የተሰማውን ስቃይ የሚገልጸው ራሱን እግዚአብሔር ካፈረሰው ግንብ ጋር በማነጻጸር ነው፡፡ "እግዚአብሔር እንዳፈረሰው ግንብ እንደሆንኩ ይሰማኛል" ወይም "እግዚአብሔር እንዳደቀቀው ግንብ እንደሆንኩ ይሰማኛል፡፡ በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ጦረኛ ወደ እኔ ይሮጣል

ኢዮብ እግዚአብሔርን የሚገልጸው እርሱን እንደሚያጠቃ ወታደር ነው፡፡ "ሊያጠቃኝ ወደ እኔ እየሮጠ እንደሚመጣ ተዋጊ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 16:15-17

በቆዳዬ ላይ ማቅ ሰፍቻለሁ

ኢዮብ ከሰውነቱ ጋር እንደ ተያያዘ ሆኖ የተሰፋ ማቅ ስለ መልበስ ይናገራል፡፡ ሰዎች ብዙጊዜ ማቅ የሚለብሱት ሀዘናቸውን ወይም ታለቅ መከራ እንደደረሰባቸው ለመግለጽ ነው፡፡ "አዝኛለሁና ማቅ ሰፍቼ እለብሳለሁ" ወይም "ከማቅ የሰፋሁትን ልብስ እለብሳለሁ፣ ምክንያቱም አዝኛለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ቀንዴን በአፈር ውስጥ እቀብራለሁ

የኢዮብ "ቀንድ" የሚወክለው ቀድሞ የነበረውን አሁን ግን ከእርሱ ጋር የሌለውን ሀይሉን እና ስልጣኑን ነው፡፡ "አሁን እዚህ በትካዜ/በጣም በድባቴ ሆኜ በትቢያ ላይ እቀመጣለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በዐይኖቼ ሽፋሽፍት የሞት ጥላ አለ

እዚህ ስፍራ የኢዮብ ዐይኖች የተወከሉት በ "ዐይኖቹ ሽፋሽፍት" ነው፡፡ ኢዮብ የዐይኖቹን መጨለም የሚገልጸው ዐይኖቹ የሞተ ሰው ዐይን እንደመሰሉ አድርጎ ነው፡፡ "በዐይኖቼ ዙሪያ ጥቁር ክቦች አሉ" ወይም "ዐይኖቼ እንደ ሞተ ሰው ዐይን ጥቁር ናቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

በእጆቼ ላይ አመጽ የለም

"እጆች" የሚለው የሚወክለው የአንድን ሰው ችሎታ እና ድርጊት ነው፡፡ "በግፍ አንዳች አላደረግኩም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 16:18-19

ምድር ሆይ፣ ደሜን አትሸፍኚ

ኢዮብ ሃሳቡን ለማጉላት ባትሰማውም አንኳን በቀጥታ ለ"ምድር" ይናገራል፡፡ ምድር ከሞቱ በኋላ ደሙን አውቃ እንደምትሸፍን ተደርጋ በሰውኛ ተገልጻለች፡፡ "ደሜን ምድር ሳትመጠው ከላይ ተቀምጦ እንዴት እንደሞትኩ ምስክር ቢሆን እመኛለሁ" (አፖስትሮፊ/በተለይ በአጠገብ የማይገኝን ነገር አጋኖ ለማመልከት የሚነገር ዘይቤ እና ሰውኛ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ምድር ሆይ፣ ደሜን አትሸፍኚ

ኢዮብ ስለ ራሱ ሞት የሚናገረው እንደሚገደል አድርጎ ነው፡፡ እዚህ ስፍራ "ደም" የሚለው የእርሱን መሞት የሚያመለክት ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "ምድር ሆይ፣ በምሞትበት ሰአት፣ አለአግባብ መሞቴን አትደብቂ" ወይም "አለ አግባብ መሞቴ አይደበቅ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ጩኸቴ የእረፍት ስፍራ አያግኝ

ኢዮብ የእርሱ "ጩኸት" ሰው ሆኖ የደረሰበትን እና በፍጹም እረፍት ያሳጣውን ነገር ለሁሉም ሰው እንዲያሳውቅለት በመፈለግ ይናገራል፡፡ "ሁሉም ሰው በእኔ ላይ የደረሰውን ይስማ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እነሆ

ኢዮብ ይህንን ቃል የተጠቀመው ቀጥሎ ለሚናገረው ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "አድምጡኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ይመሰክርልኛል

"ጻድቅ መሆኔን ይመሰክራል"

በላይ ያለው

ይፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "በሰማይ" ወይም "በላይ በሰማይ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 16:20-22

በፌዝ

"ንቀት" ወይም "መሳለቅ"

ዐይኖቼ እንባ ያፈሳሉ

ኢዮብ ሀዘኑ ምን ያህል ብርቱ እንደሆነ ይገልጻል፡፡ ከዐይኖቼ እንባ ይጎርፋል በማለት ምን ያህል አዘውትሮ እንሚያለቅስ አጉልቶ ይናገራል፡፡ "በምጮህበት ጊዜ ዐይኖቼ በእንባ ይሞላሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)

ለዚህ ሰው

"ለእኔ፡፡" እዚህ ስፍራ ኢዮብ ራሱን በሶስተኛ መደብ ይጠቅሳል፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ እና ሦስተኛ መደቦች የሚለውን ይመልከቱ)

ሰው ከወዳጁ ጋር እንደሚያደርገው

"ሰው ለወዳጁ እንደሚያደርገው፡፡" ኢዮብ በሰማይ የሚኖረው ለእርሱ ምላሽ እንዲሰጥለት እንደሚፈልግ ይገልጻል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ አንድ ስፍራ እሄዳለሁ

እዚህ ስፍራ ኢዮብ እንደሚሞት እያመለከተ ነው፡፡ "ስሞት ወደ አንድ ስፍራ እሄዳለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 17

Job 17:1-3

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ መናገሩን ቀጠለ

መንፈሴ ደክሞአል

ኢዮብ ስለ ራሱ በ"መንፈሱ" አማካይነት የሚያመለክተው ውስጣዊ ስሜቱን በትኩረት ለመግለጽ ነው፡፡ ሁለንተናው እንደደከመ እና አንዳች ጥንካሬ በውስጡ እንዳልቀረ ይናገራል፡፡ "እኔ ደክሜያለሁ" ወይም "አቅሜ ሁሉ ተሟጧል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

ዘመኔ ተፈጽሟል

"የእኔ እድሜ አብቅቷል" ወይም "በቅርቡ እሞታለሁ"

መቃብር ተዘጋጅቶልኛል

ይህ ሀረግ "መቃብርን" የሚገልጸው ኢዮብን በእንግድነት እንደሚቀበል ሰው አድርጎ ነው፡፡ "በቅርብ እሞትና እቀበራለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በእርግጥ በእኔ ዘንድ ፌዘኖች አሉ

"በዙሪያዬ የሚገኙት በእኔ ላይ እያፌዙ ነው"

በእርግጥ

"በእርግጠኝነት" ወይም "ስለዚያ ነገር ጥርጥር የለውም"

ዐይኖቼ ሁሌም ማየት ያለባቸው

ኢዮብ ባየው ነገር ላይ ትኩረት ለመስጠት ራሱን በ "ዐይኖቹ" አማካይነት ይገልጻል፡፡ "እኔ ሁልጊዜም ማየት ያለብኝ" ወይም "ሁሌም መስማት የሚገባኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

የእነርሱ ትንኮሳ

"የእነርሱ ስድብ፡፡" "ትንኮሳ" የሚለው ቃል በግስ መልኩ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እነርሱ ተነኮሱኝ" ወይም "እነርሱ ሊያናድዱኝ ሞከሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ ቃል ግባልኝ፣ አንተ ዋስ ሁነኝ

ኢዮብ ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገር ይጀምራል፡፡ እዚህ ስፍራ ስለሚገኝበት ሁኔታ በእስርቤት ውስጥ እንደሚገኝ አድርጎ ይናገራል፡፡ ነጻ ይሆን ዘንድ ቃል እንዲገባለት እግዚአብሔርን ይጠይቃል፡፡ "እግዚአብሔር ሆይ፣ ከዚህ እስር እፈታ ዘንድ ቃል ግባልኝ" ወይም "ከእስር እንድፈታ ዋጋ ክፈል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የሚረዳኝ ሌላ ማን አለ?

ኢዮብ ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የተጠቀመው እርሱን ለረዳው የሚችል ሌላ ማንም እንደሌለ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በገለጻ/ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ሊረዳኝ የሚችል ሌላ ማንም የልም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 17:4-5

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ መናገሩን ቀጠለ

የእነርሱን ልቦች ይዘሃል

"እነርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የእርሱን ወዳጆች ነው፡፡ እነርሱ በ "ልቦቻቸው" የተገለጹት ስሜታቸው ላይ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "ይዘሃቸዋል" ወይም "ጓደኞቼን ይዘሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ እነርሱን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ አታደርግም

"እንዲያሸንፉኝ አትፈቅድላቸውም"

ማንም እርሱ

"ማንም ቢሆን"

ለጥቅም ብሎ ወዳጁን የሚያወግዝ

"ጥቅም ለማግኘት ብሎ ወዳጆቹን በሃሰት የሚወነጅል" ወይም "ሽልማት ለማግኘት ብሎ ወዳጁን የሚክድ"

የልጆቹ ዐይኖች ይጨልማሉ

እዚህ ስፍራ የሰውየው ልጆች የተገለጹት በ"ዐይኖቻቸው" ነው፡፡ ይህ ሀረግ የሚገልጸው አባቶቻቸው ወይም እናቶቻቸው በሰሩት ስራ ምክንያት ስለሚሰቃዩ ልጆች ነው፡፡ "ልጆቹ መከራ ይቀበላሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 17:6-8

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ መናገሩን ቀጠለ

ለሰው ሁሉ መተረቻ አደረገኝ

ይህ ማለት ሰዎች ስለ እረሱ በፌዝ ይናገራሉ፤ ስሙንም በነቀፌታ/ስድብ ያነሳሉ፡፡ "በእርሱ ምክንያት፣ ሰዎች የእኔን ስም እንደ ስድብ አደረጉት" ወይም "በእነርሱ ምክንያት፣ ሰዎች ስሜን መተረቻ አደረጉት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ፊቴ ላይ ተፉ

"ሰዎች ፊቴ ላይ ተፉ፡፡" በዚህ ባህል በአንድ ሰው ፊት ላይ መትፋት ታላቅ ስድብ ነበር፡፡ ፊት ላይ መትፋት በባህላችሁ የተለየ ትርጉም ካለው ይህንን በተለየ መልክ መጻፍ ትችላላችሁ፡፡ "ሰዎች ፊቴ ላይ በመትፋት እጅግ አዋርደው ሰደቡኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

ከሀዘን የተነሳ ዐይኔ ፈዘዘ

ኢዮብ እይታውን እንደ "ዐይኖቹ" አድርጎ ይናገራል፡፡ "እጅግ ከማዘኔ የተነሳ እይታዬ ደካማ ሆነ" ወይም "ከሀዘኔ የተነሳ የታወርኩ ያህል ሆንኩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

መላው የሰውነቴ ክፍሎች እንደ ጥላ የሳሱ ናቸው

ጥላ ምንም ውፍረት የለውም ይህ ነው በማይባል መጠን የሳሳ ነው፡፡ ይህ የኢዮብ የሰውነት ከፍሎች ምን ያህል ቀጭን እንደሆኑ የሚያሳይ ግነት ነው፡፡ "የአካል ክፍሎች ሁሉ በጣም የከሱ/ቀጭን ናቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ እና ኩሸት እንዲሁም አጠቃላይ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)

መላው የሰውነቴ ክፍሎች

ይህ መላ አካሉ ቀጭን መሆኑን ለማጉላት የዋለ አጠቃላይ አስተያየት ነው፤ ሆኖም በተለይ እጆቹን እና እግሮቹን ያመለክታል፡፡ "እጆቼ እና እግሮቼ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)

ይደነግጣሉ

"ይርበተበታሉ" ወይም "ይፈራሉ"

በዚህ

"በእኔ ላይ በደረሰው"

ራሱን በ…ተቃውሞ ያስነሳል

ይህ ፈሊጣው አነጋገር ነው፡፡ "በ…ምክንያት ይሰቃያል" ወይም "በ… በጣም ይቆጣል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 17:9-10

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ መናገሩን ቀጠለ

በመንገዱ ይጸናል

ይህ ፈሊጣው አነጋገር ነው፡፡ "በጽድቅ መንገድ መኖሩን ይቀጥላል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ንጹህ እጆች ያሉት

ይህ የሚናገረው ትሁት የሆነውን ሰው ንጹህ እጆች እንዳሉት ሰው አድርጎ ነው፡፡ "ትክክል የሆነውን የሚያደርግ እርሱ" ወይም "ትሁት የሆነ እርሱ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እያደር እየበረታ ይሄዳል/እየበረታ እና እየበረታ ይሄዳል

ይህ ስለ አካላዊ ጥንካሬ ብቻ አይናገርም፤ ነገር ግን ስለ ሰው ፈቃድ እና ስሜት ጥንካሬም ጭምር ይናገራል፡፡

እናንተ ሁላችሁ

ኢዮብ የሚናገረው ለኤልፋዝ፣ በልዳዶስ እና ሶፋር ነው፡፡

አሁን ቅረቡ

ኢዮብ ወዳጆቹን እርሱ የተናገረውን እንዲሞግቱ/እንዲከራከሩ ይጋብዛቸዋል፡፡ " አሁን ቅረቡ፣ ዳግም ከእኔ ጋር ተከራከሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 17:11-12

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ መናገሩን ቀጠለ

ቀኖቼ አልፈዋል

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "ጊዜዬ አልፏል" ወይም "ህይወቴ አብቅቷል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እቅዶቼ ተንኮታኩተዋል፣ የልቤ መሻቶችም እንደዚሁ

እዚህ ስፍራ የኢዮብ "ልብ" የሚወክለው ውስጣዊ ማንነቱን ነው፡፡ "እቅዶቼ መቼም አይፈጸሙም፣ እጅግ የተመኘኋቸው ነገሮችም እውን አይሆኑም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እነዚህ ሰዎች፣ እነዚህ ፌዘኞች

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ሰዎችን ያመለክታሉ፣ እነርሱም የኢዮብ ወዳጆች የሆኑት ኤልፋዝ፣ በልዳዶስ እና ሶፋር ናቸው፡፡ ሁለተኛው ሀረግ ወዳጅነት የጎደለውን ዝንባሌያቸውን ያጎላል፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

ምሽቱን ወደ ቀን ይለውጣሉ

ይህ የሚናገረው ሰዎቹ በእርግጥም ምሽቱን ወደ ቀን የለውጡ ይመስል ምሽቱን ቀን ነው እንደሚሉ ነው፡፡ "ምሽት ሆኖ ሳለ ቀን ነው ይላሉ" ወይም "ምሽት የቀን ተቃራኒ የሆነውን ያህል እውነት ከሆነው በተቃራኒ ይናገራሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ብርሃን ለጨለማ ቅርብ ነው

እዚህ ስፍራ የተጠቆመው ፌዘኞች ጨለማ ቀርቦ ሳለ ብርሃን ነው ማለታቸው ነው፡፡ "ብርሃን ለጨለማ ቅርብ ነው ይላሉ" ወይም " ጨለማው እየመጣ፣ እየነጋ ነው ይላሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 17:13-16

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ መናገሩን ቀጠለ

ብቸኛው ቤት ቢሆን እንኳን… ደግሞም እኔ ባነጥፍ …. ብዬ ብናገር እንኳን

እዚህ ስፍራ "ቢሆን" የሚሉት ሁኔታዎች ሁሉ "እስከ/ድረስ" የሚል ትርጉም አላቸው፡ ኢዮብ ሁሉም ነገሮች እውነት እንደሆኑ አድርጎ ይናገራል፡፡ "ብቸኛው ቤት ቢሆን … እስካነጥፍ ድረስ….ደግሞም እስከተናገርኩ ድረስ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (መላምታዊ ሁኔታ የሚለውን ይመልከቱ)

በጨለማ አልጋዬን አነጥፋለሁ

እዚህ ስፍራ ኢዮብ የሚናገረው፣ በጨለማ አልጋውን እያነጠፈ ባለበት ለሞት እየተዘጋጀ መሆኑን ነው፡፡ "በሞቱት መካከል ሄጄ ለመተኛት ራሴን አዘጋጅቻለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አልጋዬን አነጥፋለሁ

"አልጋዬን አዘጋጃለሁ"

ለጉድጓድ እንዲህ እለዋለሁ… ለትልም ደግሞ

እነዚህ ሁለት መስመሮች አንዱ ለሌላው አማራጭ ሲሆን በአንድ ላይ የኢዮብን ተስፋ መቁረጥ ጥልቀት ያጎላሉ፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጉድጓዱ

"መቃብሩ"

አንተ አባቴ ነህ

ኢዮብ በቅርቡ ወደ መቃብሩ የሚኖረውን ቅርበት የሚገልጸው ሰው ከአባቱ ጋር ከሚኖረው ቅርበት ጋር በማነጻጸር ነው፡፡ "አንተ የአባቴን ያህል ለእኔ ቅርብ ነህ" ወይም "ስቀበር፣ አንተ የአባቴን ያህል ትቀርበኛለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ትልን

"ትል/የስጋ ወይም የእበት ትል፡፡" ትሎች የሞተ አካልን የሚበሉ ትንንሸ ፍጥረት ናቸው፡፡

አንቺ እናቴ ነሽ ወይም አንቺ እህቴ ነሽ

ኢዮብ አንድ ሰው ከእናቱ ወይም ከእህቶቹ ጋር ከሚኖረው ቅርበት ጋር በማነጻጸር በቶሎ በመቃብር ውስጥ ከትል ጋር የሚኖረውን ቅርበት ይናገራል፡፡ "አንተ የእናቴ ወይም የእህቴን ያህል ለእኔ ቅርብ ነህ" ወይም "አንተ ለእኔ የእናትን ወይም የእህትን ያህል ቅርቤ ትሆናለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ታዲያ ተስፋዬ ወዴት አለ?

በውስጠ ታዋቂነት የተሰጠው መልስ "የትም የለም" የሚል ነው፤ ምክንያቱም ተስፋ ቆርጧል፡፡ ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ በገለጻ/ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እኔ ምንም ተስፋ የለኝም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው)

ተስፍዬን የሚያይልኝስ ማን ነው?

ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የዋለው ማንም ሰው እርሱ አንዳች ተስፋ ይኖረዋል ብሎ እንደማያስብ ለማጉላት ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በገለጻ/ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ማንም ሰው ስለ እኔ ተስፋ አይታየውም" ወይም "ማንም ሰው ከእንግዲህ እኔ ምንም ተስፋ እንደሚኖረኝ አይጠብቅም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው)

ወደ ትቢያ …ተስፋ ከእኔ ጋር ይሄዳልን?

በውስጠ ታዋቂነት የተሰጠው ምልስ "የለም" የሚል ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በገለጻ/ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ወደ ትቢያ…ተስፋ ከእኔ ጋር አይወርድም" ወይም "ወደ ትቢያ… ስወርድ ከዚያ ወዲያ ተስፋ አላደርግም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው)

የሲኦል በሮች

ሲኦል በእርግጥ በር የለውም፣ ነገር ግን ኢዮብ ወደ መቃብር ለመግባቱ ዘይቤያዊ አነጋገር ነው፡፡ "ወደ መቃብር ስወርድ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እኛ በ…ጊዜ

"እኔ እና ተስፋ ያደረኳቸው ነገሮች በ…ጊዜ" ወይም "እኔ እና ተስፋ ያደረኩት በ… ጊዜ" "እኛ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ኢዮብን እና ተስፋውን ነው፡፡

ወደ አፈር ስገባ

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "ሞቼ ስቀበር" ወይም "ወደ መቃብር ስወርድ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 18

Job 18:1-2

አጠቃላይ መረጃ፡

ሥነ ግጥም እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ

አጠቃላይ መረጃ፡

ሹሐዊው በልዳዶስ ከኢዮብ ጋር ይነጋገራል

ከዚያም ሹሐዊው በልዳዶስ እንዲህ ሲል መለሰ

"በልዳዶስ" የሹሐ ነገድ የሆነ ሰው የወንድ ስም ነው፡፡ ይህ በኢዮብ 8፡1 ላይ እንዴት እንደተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

ንግግርህን የምታቆመው መቼ ነው?

ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ ኢዮብ ለረጅም ጊዜ ሲናገር ነበር ማለት ነው፡፡ ይህ በገለጻ/ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ንግግርህን አቁም!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

አስተውል፣ ደግሞም

"ምክንያታዊ ሁን፣ ደግሞም" ወይም "ስለእነዚህ ነገሮች አስብ፣ ደግሞም"

Job 18:3-4

አጠቃላይ መረጃ፡

በልዳዶስ ከኢዮብ ጋር መነጋገሩን ቀጠለ

ለምን እኛ በአንተ ፊት እንደ አውሬ/አረመኔ እና የማይረቡ ሆነን ተቆጠርን?

በልዳዶስ ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የተጠቀመው ኢዮብ ወዳጆቹን እንደ እንስሳ እና ማሰብ ወይም መናገር እንደማይችሉ አድርጎ መውሰድ እንደሌለበት አጉልቶ ለማሳየት ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር በገለጻ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እኛን እንደ አውሬ ወይም ማሰብ እንደማይችሉ መቁጠር የለብህም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

እኛ ለምን

"እኛ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ምናልባት በልዳዶስን እና ሌሎቹን የኢዮብ ወዳጆች በመሆኑ አካታች አይደለም፡፡ (አካታች እና የማያካትት "እኛ" የሚለውን ይመልከቱ)

ተመልከት

እዚህ ስፍራ መመልከት፣ ማየት የሚሉት በሚገባ ማሰብ ወይም በሚገባ አለማሰብ ለሚለው ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በአንተ እይታ/ዐይን

እዚህ ስፍራ እይታ የሚወክለው ፍርድን ወይም ሚዛንን ነው፡፡ "በአንተ ሚዛን" ወይም "በአንተ አስተሳሰብ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የእናንተ እይታ

እዚህ ስፍራ "የእናንተ" የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ነው፡፡ በልዳዶስ ሽሙጥ በመጠቀም ኢዮብ ራሱን ታላቅ ሰው አድርጎ ማሰብ እንደሌለበት ይነግረዋል፡፡ "በአንተ ዐይን፣ በስህተት ትልቅ እንደሆንክ የምታስበው አንተ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አንደኛ፣ ሁለተኛ አና ሲስተኛ መደብ እንዲሁም ምፀት የሚሉትን ይመልከቱ)

በቁጣህ በራስህ ላይ የምታለቅሰው አንተ

እዚህ ስፍራ በልዳዶስ የሚናገረው ኢዮብ በጉዳት ልይ የሚገኘው ከራሱ ቁጣ እና አለመታዘዝ የተነሳ እንጂ ቀደም ሲል ኢዮብ ሲናገር እንደቆየው ከእግዚአብሔር የተነሳ አለመሆኑን ነው፡፡ እዚህ ስፍራ "እንባ"የሚለው ቃል "ጉዳት" ማለት ነው፡፡ "ከቁጣህ የተነሳ በራስህ ላይ ጉዳት ያመጣኸው አንተ ነህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በአንተ ምክንያት ምድር ከስፍራዋ ትጠፋለችን ወይስ አለቶች ስፍራቸውን ይለቃሉ?

ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚጠቁመው እነርሱ ጥፋተኛ አድርገው የሚቆጥሩትን ኢዮብን ዝም ማለት እና መተው መላውን ዓለም እንደመለወጥ ይቆጠራል፡፡ በልዳዶስ እዚህ ስፍራ እንዲህ ያለውን ታላቅ ማጋነን የሚጠቀመው ይህ ምን ያህል አስደንጋጭ እና አስፈሪ እንደሆነ እንደሚያስብ ለማጉላት ነው፡፡ በዐረፍተ ነገር/በገለጻ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "በደለኛ የሆንከውን፣ እግዚአብሔር ዝም እንዲልህ እና እንዲተውህ መለመን እግዚአብሔር ለአንተ ሲል ምድርን ቸል እንዲላት የመጠየቅን ያህል ወይም አንተን ለማስደሰት ሲል አለቶችን ከስፍራቸው እንዲያስወግድ የመጠየቅ ያህል የማይረባ ነገር ነው!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ኩሸት እንደዚሁም አጠቃላይ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)

ምድር ለአንተ ሲባል መተው/ባዶ መሆን አለባት

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ሁሉም ሰው ምድርን መተው/መልቀቅ አለበት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

አለቶችን ከስፍራቸው መወገድ አለባቸው

Job 18:5-6

አጠቃላይ መረጃ፡

በልዳዶስ ከኢዮብ ጋር መነጋገሩን ቀጠለ

በእርግጥ፣ የክፉ ሰው መብራት ትጠፋለች፤ የብርሃኑ ብልጭታ አያበራም

በላዳዶስ የክፉ ሰው አማሟት ሻማው ድርግም ብሎ እንደሚጠፋ አይነት መሆኑን ይናገራል፡፡ "የሚሆነው እንዲህ ነው፣ አንተ እንደሚያበቃልህ የክፉ ሰዎች ህይወት ሻማ ወይም የእሳት ነበላባል እንደሚጠፋ በፍጥነት ይጠፋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ይጠፋል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ይወገዳል/ያበቃለታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

በጎጆው ውስጥ ብርሃን ይጨልማል፣ ከበላዩ ያለው መብራት ይጠፋል

በልዳዶስ ስለ ክፉ ሰው አመሟት መናገሩን ይቀጥላል፡፡ ስለ ክፉ ሰው ህይወት በድንኳኑ እንዳለ ብርሃን አድርጎ ይናገራል፡፡ "በቤቱ ያለ ብርሃን ወደ ጨለማነት እንደሚለወጥ፣ ከበላዩ ያለ ብርሃን እንደሚጠፋ ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 18:7-8

አጠቃላይ መረጃ፡

በልዳዶስ ክፉውን ሰው መግለጹን ይቀጥላል

የጥንካሬው እርምጃዎች አጭር ይሆናል

ይህ የሚናገረው ክፉ ሰው ለመራመድ አቅም አንደሚያጣ ሆኖ በድንገት ጥፋት እንደሚገጥመው ነው፡፡ "ለመራመድ አቅም እንደሚያጣ ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የራሱ እቅድ ጠልፎ ይጥለዋል

"የራሱ ምክር እንዲወድቅ ያደርገዋል፡፡" ይህ ክፉ ሰው ልክ እንደሚወድቅ አይነት ጥፋት እንደሚደርስበት ይናገራል፡፡ "የራሱ እቅድ ወደ ጥፋት ይመራዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በገዛ እግሮቹ ወደ መረብ ይጣላል፣ ወደ ወጥመድ ይራመዳል

"የራሱ እግሮች ወደ መጥመድ/መረብ ይመሩታል፡፡" በልዳዶስ ይህንን ምስል የሚጠቀመው ክፉ ሰው ህይወቱን የሚኖርበት መንገድ ወደ ድንገተኛ ጥፋት ይመራዋል ለማት ነው፡፡ "በቀጥታ ወደ ወጥመድ እንደሚራመድ እራሱን ወደ መረብ የሚመራ ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

መረብ

ሲባጎ ወይም ገመድ በአንድነት በመሸመን ለወጥነድነት የሚሰራ ወንፊት/መረብ፡፡ ሰዎች እንስሳ ለማጥመድ መረብ ይተቀማሉ

ወጥመድ

እንስሳት በላዩ ሲረማመዱ ወደ ውስጥ እንደወድቁ ቅርንጫፎች እና ቅጠል በላዩ የተረበረበበት ጉድጓድ

Job 18:9-11

አጠቃላይ መረጃ፡

በልዳዶስ ሶስት ትይዩ ንጽጽራዊ ምስሎችን በመጠቀም ክፉ ሰው እንዴት በድንገት ጥፋት እንደሚገጥመው መግለጹን ይቀጥላል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ወጥመድ ይይዘዋል… መሰናክል ይገጥመዋል… ሸምቀቆ…. ደግሞም በመንገዱ እንቅፋት

እነዚህ አራት ሀረጎች ክፉ ሰው ጥፋት የሚደርስበት በወጥመድ እንደሚያዝ ሆኖ እንደሆነ ይናገራሉ፡፡ "ወጥመድ እንደሚይዘው ይሆናል… መሰናክል ይገጥመዋል… ሸምቀቆ .. ደግሞም በመንገዱ እንቅፋት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ማጥመጃ

ሰዎች እንዲህ አይነት ማጥመጃ ወፎችን ለመያዝ ይጠቀማሉ፡፡ ማጥመጃ ተሸምቅቆ የወፍን እግር ይይዛል፡፡

ተረከዙን ይይዛል

እዚህ ስፍራ "ተረከዝ" የሚያመለክተው በአቅላላው እግርን ነው፡፡ "እግሩን ይይዘዋል/ያጠምዳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ሸምቀቆ በምድር ላይ ተደብቆ ተቀምጦለታል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ " ይያዝበት/ይጠመድበት ዘንድ አንድ ሰው ሸምቀቆ በምድር ላይ በስውር አጥምዷል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ሸምቀቆ

እንስሳው በቋተሮም መሃል ሲረማመድ እግሩን ለማጥመድ ቋጠሮ ያለው ገመድ መጠቀም

ለእርሱ ወጥመድ

"ተደብቋል" የሚለው የሚታወቀው ቃላዊ ሀረግ ሊጨመር ይችላል፡፡ "እርሱን ለመያዝ ወጥመድ በመንገዱ ላይ ተደብቆ ተቀምጣል" ወይም "እርሱን በመንገዱ ላይ ለማጥመድ አንድ ሰው ወጥመድ ይደብቃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተዘለለ/ የተተወ የሚለውን ይመልከቱ)

በየእለቱ ሽብር ያስደነግጠዋል

"በዙሪያው ሽብር ያስፈራዋል"

ከስር ከስሩ/ከተረከዙ በታች ያሳድዱታል

ይህ የሚናገረው ክፉ ሰውን አስፈሪ ነገሮች ጠላት ሆነው እንደሚያሳድዱት ነው፡፡ "በሁሉም ስፍራ ሽብር እንደሚያሳድደው ሰው ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 18:12-13

አጠቃላይ መረጃ፡

በልዳዶስ ክፉውን ሰው መግለጹን ይቀጥላል

ሃብቱ ወደ ረሃብ ይለወጣል

ይህ የሚናገረው ክፉ ሰው ሃብቱ ወዳልሆነ ሌላ ነገር እንደሚለወጥና ደሃ እና ረሀብተኛ እንደሚሆን ነው፡፡ "ባለጠጋነቱ ጠፍቶ፣ ድሃ እና ረሃብተኛ ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

መቅሰፍት በጎኑ የተዘጋጀ ይሆናል

"በጎኑ የተዘጋጀ" የሚለው ሀረግ አንዳች ክፉ ነገር ሁሉም ከአጠገቡ አይታጣም ለሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "ሁሌም ጥፋት ይገጥመዋል" ወይም "መቅሰፍትን ማስቀረት የማይችል ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የሰውነቱ ክፍሎች ይበላሉ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ እንደዚሁም፣ ይህ ሰውነቱን የጎዳው ጥፋት እንስሳ እንዳጠቃው እና እንደበላው ተደርጎ ተነግሯል፡፡ "በሽታ ቆዳውን በልቶ ጨርሶታል" ወይም "በሽታ ቆዳውን አጥፍቶታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ እና ዘይቤያው አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

የሞት የበኩር ልጅ አካሉን ይበላዋል

እዚህ ስፍራ ብዙ ሰዎችን የገደለው በሽታ "የሞት የበኩር ልጅ" ተብሎ ተገልጽዋል፡፡ ይህ የተነገረው ሰውነቱን ያጠፋው በሽታ እርሱን እንዳጠቃና እንደበላው እንስሳ እንደሆነ ተደርጎ ነው፡፡ "ክፉ በሽታ የሰውነቱን የተለያዩ ክፍሎች ያጠፉታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 18:14-15

አጠቃላይ መረጃ፡

በልዳዶስ ክፉውን ሰው መግለጹን ይቀጥላል

በሰላም ከተቀመጠበት ድንኳኑ ይነቀላል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ጥፋት በሰላም ከተቀመጠበት ከድንኳኑ ያባርረዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ይነዳል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ነድቶ ያስወጣዋል" ወይም "ወጥቶ እንዲሄድ ያስገድደዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የሽብር ንጉሥ

ይህ በሞት ላይ ስልጣን አለው የሚባለው የአህዛብ አማልእክት ለሆነው "ንጉሥ ሞት" ለሚባለው መግለጫ ነው፡፡ "በሙታን ላይ የሚገዛው" ወይም " የሞት ንጉሥ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሱ ያልሆኑ ሰዎች

"የእርሱ ቤተሰብ ያልሆኑ ሰዎች"

በቤቱ ውስጥ ድኝ እንደተረጨ ከተመለከቱ በኋላ

ሰዎች በሽታን እየሞተ ከሚገኝ/በጽኑ ከታመመ ሰው ላይ ለማባረር ድኝን ይጠቀሙ ነበር፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "በቤቱ ላይ ሁሉ ድኝ ከበተኑ በኋላ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 18:16-17

አጠቃላይ መረጃ፡

በልዳዶስ ክፉውን ሰው መግለጹን ይቀጥላል

ስሩ ይደርቃል…ቅርንጫፉ ይቆረጣል

ይህ የሚናገረው ክፉ ሰው ሲሞት፣ ስሩ እንደ ደረቀ እና ቅርንጫፎቹ ጠውልገው አንዳች ፍሬ እንደማያፈራ ዛፍ ሁሉ ተከታይ ትውልድ እንደሚይኖረው ነው፡፡ "እርሱ ይሞታል ተከታይ ትውልድም አይኖረውም፣ ስሩ እንደ ደረቀ እና ቅርንጫፉ እንደ ጠወለገ ዛፍ ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ቅርንጫፉ ይቆረጣል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ቅርንጫፎቹ ይጠወልጋሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

መታሰቢያው ከምድር ይጠፋል፤ በጎዳና ምንም ስም አይኖረውም

እነዚህ ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ ደግሞም ከሞተ በኋላ ማንም የሚያስታውሰው እንደማይኖር ለማጉላት በአንድ ላይ ቀርበዋል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

መታሰቢያው ከምድር ይጠፋል

ይህ የክፉ ሰውን "መታሰቢያ" እንደ ሞተው ሰው አድርጎ ይናገራል፡፡ "በምድር ላይ ማንም ሰው አያስታውሰውም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በመንገድ/ጎዳና ላይ ምንም ስም አይኖረውም

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "በመንገድ የሚራመድ ማንም ሰው ስሙን እንኳን አያስታውሰውም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 18:18-20

አጠቃላይ መረጃ፡

በልዳዶስ ክፉውን ሰው መግለጹን ይቀጥላል

ከብርሃን ተወግዶ ወደ ጨለማ ይነዳል…ከዚህ ዓለም ይባረራል

እነዚህ ሀረጎች በአንድነት ክፉ ሰው፣ የሙታን መኖሪያ ወደ ሆነው ወደ ሲኦል እንደሚወርድ አጉልተው ይገልጻሉ፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከብርሃን ተወግዶ ወደ ጨለማ ይነዳል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር ክፉን ሰው ከብርሃን ወደ ጨለማ ይነዳዋል/ይወስደዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ከብርሃን ወደ ጨለማ

"ብርሃን" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ህይወትን ሲሆን፣ "ጨለማ" ደግሞ ሞትን ያመለክታል፡፡ "ከህይወት ብርሃን ወደ ሞት ጨለማ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ከዚህ አለም ይባረራል

ይህ እግዚአብሔር ክፉውን ሰው ምድርን ትቶ ሙታን ወደሚሄዱበት እንደሚያባርረው ይናገራል፡፡ "እግዚአብሔር ይህንን ምድር እንዲለቅ/እንዲተው ያደርገዋል" ወይም "እግዚአብሔር ሙታን ወደሚሄዱበት ይልከዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ይባረራል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር ያሳድደዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ልጅ አይኖረውም… አሊያም የሚቆይበት ቤተዘመድ አይኖረውም

እነዚህ ሁለት ሀረጎች በአንድነት የሚያጎሉት ቤተሰብ ወይም ቀሪ ትውልድ እንደማይኖረው ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የልጅ ልጅ

"የልጅ ልጅ"

ቤተ ዘመድ

"ዘመድ"

በምዕራብ የሚኖሩ…በምስረቅ የሚኖሩ በዚህ ነገር ይደነግጣሉ

"በምዕራብ" እና "በምስራቅ" የሚሉት ሀረጎች በየትኛውም ስፍራ ለሚኖሩ ሰዎች ጽንፍን የሚያመለክቱ ናቸው፡፡ ይህ ስለ ክፉ ሰዎች በምድር ላይ የሚኖር ሁሉ እንደሚሰማ በማጋነን የተነገረ ነው፡፡ "በመላው ዓለም የሚኖሩ በክፉ ሰው ላይ የደረሰውን ሲሰሙ ይደነግጣሉ ደግሞም በፍርሃት ይሞላሉ" ወይም "በምስራቅ እና በምዕራብ የሚኖሩ ብዙ ሰዎች በክፉ ሰው ላይ የደረሰውን ሲሰሙ ይደነግጣሉ ደግሞም በፍርሃት ይሞላሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጽንፍ እና ኩሸት እንዲሁም አጠቃላይ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)

አንድ ቀን

"በሆነ ቀን"

Job 18:21

አጠቃላይ መረጃ፡

በልዳዶስ ክፉውን ሰው መግለጹን ይቀጥላል

የኃጢአተኛ/ጻድቅ ያልሆኑ ሰዎች ቤቶች፣ እግዚአብሔርን የማያውቁ ሰዎች ስፍራ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም ሲኖራቸው የሚያመለክቱትም ተመሳሳይ ሰዎችን ነው፡፡ እዚህ ስፍራ እነዚህ ሰዎች የተጠቀሱት በሚኖሩበት ስፍራ ነው፡፡ "ኃጢአተኛ/ጻድቅ ያልሆኑ ሰዎች፣ እግዚአብሔርን የማያውቁ እነርሱ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 19

Job 19:1-2

አያያዥ ሀሳብ፡

ኢዮብ ከሶስቱወዳጆቹ ጋር ይነጋገራል፡፡

አጠቃላይ መረጃ፡

ስነ ግጥም እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ

እስከመቼ ታስጨንቁኛላችሁ፤ እስከ መቼስ በቃላት ታደቁኛላችሁ?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የሚጠቀመው ወዳጆቹ እንዴት እያዩት እንደሆነ ለማማረር ነው፡፡ "እንድሰቃይ ማድረጋችሁን እና በቃላት እኔን ማድቀቃችሁን አቁሙ/ይብቃችሁ" (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

በቃላት የምታደቁኝ

ኢዮብ ይህንን ምስል የሚጠቀመው ቃላቶቻቸው በጣም እንዲያዝን እና ተስፋ እንዲቆርጥ እንዳደረጉት ለመናገር ነው፡፡ "በቃላቶቻችሁ ከፍተኛ ስቃይ አድርሳችሁብኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 19:3-4

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ ከሶስቱ ወዳጆቹ ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል፡፡

በእነዚህ አስር ጊዜያት ዘልፋችሁኛል

"በእነዚህ አስር ጊዜያት" የሚለው ሀረግ የሚያመለክተው ወዳጆቹ ኢዮብን ሙሉ ለሙሉ/እጅግ እንደገሰጹት ነው፡፡ "እጅግ ዘለፋችሁኝ" ወይም "ብዙ ጊዜ ዘለፋችሁኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በጭካኔ ስትመለከቱኝ አላፈራችሁም

ኢዮብ ለዚህ ይገስጻቸዋል፡፡ ይህ በአዎንታዊ መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እጅግ በጭካኔ ስታዩኝ/ስትቀርቡኝ ልታፍሩ በተገባችሁ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

በጭካኔ ስታዩኝ/ስትቀርቡኝ

"ንቃችሁኛል" ወይም "በአደባባይ አዋርዳችሁኛል"

ተሳስታችኋል

"በድንገት መበደል" ወይም "ተሳስቶ ኃጢአት መስራት"

የእኔ ጥፋት የኔው ጉዳይ ሆኖ ይቆያል

ኢዮብ እርሱ ጥፋቱን እስከ ሰራ ድረስ ወዳጆቹ እነርሱ ሃላፊነት በማይወስዱበት ጥፋት ሳያቋርጡ እርሱን መውቀስ እንደሌለባቸው ይነግራቸዋል፡፡ "የእኔ ጥፋት የራሴ ተጠያቂነት ነው፣ ስለዚህ እኔን መገሰጻችሁን መቀጠል የለባችሁም" ወይም "የእኔ ጥፋት እናንተን አይጎዳም፣ ስለዚህ እኔን መገሰጻችሁን መቀጠል የለባችሁም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የእኔ ጥፋት

"የእኔ ኃጢአት" ወይም "የእኔ ስህተት"

Job 19:5-6

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ ከሶስቱ ወዳጆቹ ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል፡፡

በእርግጥ ራሳችሁን በእኔ ላይ ከፍ ከፍ ብታደርጉ

"ከእኔ ይልቅ እንደተሻላችሁ አድርጋችሁ ስለ ራሳችሁ ብታስቡ" ወይም "ከእኔ እንደተሻላችሁ አስካስመስላችሁ ድረስ"

መዋረዴን አይታችሁ በእኔ ላይ ከፍ ብትሉ

ወዳጆቹ ይህንን እንዴት እንሚያደርጉ በግልጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "መዋረዴ በእኔ ላይ ማስረጃ እንደሆነ ብትናገሩ" ወይም "መዋረዴን እኔ በደለኛ ለማድረግ ማስረጃ አድርጋችሁ ብትጠቀሙ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

መዋረዴን እኔ በደለኛ ለማድረግ ማስረጃ አድርጋችሁ ብትጠቀሙ

"ውርደት" የሚለው ረቂቅ ስም "ተዋረደ" በሚለው ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "የሆነውን ነገር በመናገር እኔን በማዋረድ ጥፋተኛ መሆኔን ለማረጋገጥ ተጠቀሙበት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስም የሚለውን ይመልከቱ)

በመረቡ/ወጥመዱ ያዘኝ

ኢዮብ እግዚአብሔር እርሱን በመጥመዱ የሚይዝ አዳኝ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ ይህ ዘይቤ የሚወክለው እግዚአብሔር ኢዮብን ተቆጣጥሮ የሚይዝ መሆኑን እና የኢዮብን የተስፋ ቢስነት ስሜት ነው፡፡ "አጠመድከኝ" ወይም "እኔን ተቆጣጥረህ ያዝከኝ/አላላውስ አልከኝ" ወይም "እኔ ተስፋ ቢስ እሆን ዘንድ፣ በእኔ ላይ የሚሆነውን ሁሉ ተቆጣጠርክ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 19:7-9

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ ከሶስቱ ወዳጆቹ ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል፡፡

እነሆ፣ እኔ አነባለሁ

"እኔ እጮሀለሁ፣ ትኩረት ስጡኝ/ልብ በሉ፣ ምክንያቱም ልናገረው ያልኩት ነገር እውነት ነው ደግሞም ጠቃሚ ነው፡፡"

ተበደልሁ!

ይህ የእርዳታ ጩኸት ነው፡፡ በግልጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ተበደልኩ! ድረሱልኝ!" ወይም "እርዱኝ! ጥቃት እየደረሰብኝ ነው!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ለእርዳታ ተጣራሁ

"ለእርዳታ ጮኹኩ" ወይም "እሪ አልኩ"

ነገር ግን ፍትህ የለም

"ፍትህ" የሚለው ረቂቅ ስም ትርጉሙን ግለጽ በሚያደርግ ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "በእኔ ላይ ስህተት ከሚፈጽሙ ሰዎች ማንም ሊከላከልልኝ አልቻለም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

እርሱ መንገዴን አጥሮታል…መንገዴን አጨልሞታል

ኢዮብ እነዚህን ምስሎች የሚጠቀመው እግዚአብሔር እንዴት ረዳት የለሽ እና ተስፋ ቢስ እንዳደረገው ለመግለጽ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ማለፍ እንዳልችል መንገዴን ቀጥሮታል

"እግዚአብሔር በምሄድበት መንገድ ላይ ግንብ አጥሮበታል" ወይም "መሄድ እንዳልችል መንገዴን ዘግቶታል"

ዘውዱን ከራሴ ላይ… እርሱ አንስቶታል

ኢዮብ እነዚህን ምስሎች የሚጠቀመው እግዚአብሔር ከእርሱ ላይ መልካሙን ማዕረጉን፣ ሀብቱን፣ ክብሩን እንደወሰደበት ለመናገር ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ክብሬን ከእኔ ከፏል

ኢዮብ ስለ ክብሩ የሚናገረው እግዚአብሔር ከእርሱ እንደ ገፈፈው ልብሱ አድርጎ ነው፡፡ "እርሱ ከእኔ ክብሬን ወሰደው/ገፈፈው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከራሴ ላይ ዘውዴን ወሰደው

ዘውድ የሚወክለው የኢዮብን ማዕረግ ወይም ክብር ነው፡፡ "እርሱ የእኔን ማዕረግ እና ክብር ገፈፈው" ወይም "ከራሴ ላይ ዘውዴን እንደወሰደብኝ ያህል ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 19:10-12

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ ከሶስቱ ወዳጆቹ ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል፡፡

በሁሉም አቅጣጫ እርሱ ሰብሮኛል

ኢዮብ እግዚአብሔር እርሱን እያጠፋው ያለው እግዚአብሔር እደመሰሰ የሚገኘውን እርሱ እየገነባ እንደሚገኝ ባለ ሁኔታ ነው፡፡ "እርሱ በሁሉም መንገድ አጥፍቶኛል" ወይም "እርሱ በሁሉም መንገድ አጥቅቶኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ ሄዳለሁ/አብቅቶልኛል

"መሄድ" የሚለው ዘይቤ የሚወክለው ሙሉ ለሙሌ መጥፋትን ነው፡፡ "እኔ ሙሉ ለሙሉ ጠፍቻለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ተስፋዬን እንደ ዛፍ ነቅሎታል

ኢዮብ የሚናገረው እግዚአብሔር እርሱን ከስሩ እንደተነቀለ ዛፍ ተስፋ እንዳይኖረው አድርጎ እንደነቀለው ነው፡፡ "እርሱ ሙሉ ለሙሉ ተስፋዬን አጥፍቶታል" ወይም "እርሱ ካደረገው ነገር የተነሳ፣ አንዳች መልካም ተስፋ መጠበቅ አልችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤያዊ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ዛፍ

ይህ ተነጻጻሪ ዘይቤ የተተወ/የተዘለለ ጭምርም ነው፡፡ የተዘለሉትን ቃላትም መጨመር ይኖርባችኋል፡፡ "አንድ ሰው ዛፍን ከስሩ በሚነቅልበት መንገድ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ እና የተተወ/የተዘለለ ሚሉትን ይመልከቱ)

ደግሞም እርሱ ቁጣውን በእኔ ላይ አንድዷል

ኢዮብ ስለ እግዚአብሔር ቁጣ የሚናገረው እሳት እንደሆነ አድርጎ ነው፡፡ "እግዚአብሔር በእኔ ላይ የቁጣ እሳቱ እንዲነድ ፈቅዷል" ወይም "እግዚአብሔር በእኔ እጅግ ተቆጥቷልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ከጠላቶቹ እንደ አንዱ አይቶኛል

"እርሱ እኔን እንደ ጠላቱ አስቦኛል"

የእርሱ ጦር በአንድነት መጣብኝ

ኢዮብ የሚናገረው እግዚአብሔር እርሱን ያጠቃው እርሱ ከተማ እንደሆነ እና እግዚአብሔር እርሱን እንዲያጠቁት ሰራዊት እንደላከ አድርጎ ነው፡፡ "እኔን እንዲያጠቁኝ እግዚአብሔር ሰራዊቱን በእኔ ላከ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በእኔ ላይ ከበባ ለማድረግ ድንጋይ ቆልለው ምሽግ ሰሩ

ኢዮብ የሚናገረው እግዚአብሔር እርሱን ያጠቃው እርሱ ከተማ እንደሆነ እና የእግዚአብሔር ሰራዊት በከተማይቱ ቅጥር ዙሪያ ቁልል ሰርተው ቅጥሩን ለመውጣት እና ከተማይቱን እንደሚያጠቁ አድርጎ ነው፡፡ "ወታደሮቹ በእኔ ግንብ ላይ ለመውጣት ቁልል ከመሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በድንኳኔ ዙሪያ ሰፈሩ

ኢዮብ እግዚአብሔር እርሱን እንዴት እንዳጠቃው የሚናገረው ኢዮብ በድንኳኑ ውስጥ እንደሆነ እና የእግዚአብሔር ሰራዊት በእርሱ ዙሪያ ሰፍሮ ሊያጠቃው እንደሚዘጋጅ አድርጎ ነው፡፡ "በድንኳኔ ዙሪያ ሰፍረው ሊያጠቁኝ እየተዘጋጁ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 19:13-14

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ ከሶስቱ ወዳጆቹ ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል፡፡

ወንድሞቼን ከእኔ አራቀ

"ከአንድ ሰው መራቅ" የሚለው የሚወክለው ወደዚያ ሰው ለመቅረብ ወይም ያንን ሰው ለመርዳት ፈቃደኛ አለመሆንን ነው፡፡ "እግዚአብሔር ወንድሞቼ ከእኔ እንዲርቁ አደረገ" ወይም "እግዚአብሔር ወንድሞቼ እኔን መርዳት እንዳይፈልጉ/እንዲጠሉ አደረገ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የቅርቤ የሆኑ በሙሉ ከእኔ ተለዩ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የቅርቤ የሆኑ በሙሉ ራሳቸውን ከእኔ ለዩ" ወይም "ወዳጆቼ እንደ እንግዳ ተመለከቱኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ዘመዶቼ ተዉኝ

"ቤተዘመዶቼ ካለ አንዳች እርዳታ ተዉኝ"

የቅርብ ወዳጆቼ

"የእኔ ናቸው የምላቸው ጓደኞቼ"

እኔን ረሱኝ

"እኔን ተዉኝ" ወይም "ቸል አሉኝ፡፡" ይህ ማለት እርስ በእርሳቸው ቀድሞ በነበራችው ግንኙነት መሰረት ሊመለከቱት አልፈቀዱም፡፡ ይህ እርሱን እንተዉት ያመለክታል፡፡

Job 19:15-16

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ ከሶስቱ ወዳጆቹ ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል፡፡

ተመለወከቱኝ/ትኩረት ስጡኝ

"ስፍራ ስጡኝ/ቦታ ስጡኝ"

በእነርሱ እይታ እኔ ባእድ/እንግዳ ነኝ

ኢዮብ ሰዎች አሁን እንዴት እንደ ውጭ ሰው እንደሚያዩት/እንደሚቆጥሩት ይገልጻል፡፡ እዚህ ስፍራ እይታ የሚለው ሚወክለው ፍርድን ወይም ሚዛንን ነው፡፡ "እኔን እንደ ባዕድ ይቆጥሩኛል/ያስቡኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ነገር ግን እርሱ ለእኔ አንዳች ምላሽ አልሰጠኝም

"ነገር ግን እርሱ ለእኔ አልመለሰልኝም" ወይም "ነገር ግን እርሱ ወደ እኔ አልመጣም" መልሱ ለኢዮብ ጥሪ ምላሽ ነው፡፡

ምንም እንኳን በአፌ ብለምነውም

"በአፌ" የሚለው ሀረግ የኢዮብን ንግግር የሚያለክት ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "ምንም እንኳን ከእርሱ ጋር ብናገር እና ብለምነውም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱን መለመን

"ለእርሱ ልመና ማቅረብ"

Job 19:17-19

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ ከሶስቱ ወዳጆቹ ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል፡፡

ትንፋሼ ለሚስቴ የሚያስጸይፍ ሆነባት

እዚህ ስፍራ "ትንፋሽ" የሚወክለው የእስትንፈሳሱን ሽታ ነው፡፡ አንድ ነገር ለአንድ ሰው የሚያስጸይፍ/ተቀባይነት የሌለው ከሆነ ተቀባዩ ጠልቶታል ማለት ነው፡፡ "ሚስቴ የትንፋሼን ሽታ ጠላችው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እኔን ናቀችኝ

"ጠላችኝ" ወይም "አልወደደችኝም"

በጠላትነት ተነሱብኝ

"መሳቂያ አደረጉኝ" ወይም "በእኔ ላይ ተሳለቁ"

የቅርብ ወዳጆቼ ሁሉ

"የቅርቤ/የራሴ የምላቸው ጓደኞቼ" ወይም "ምስጢሬን ያካፈልኳቸው ጓደኞቼ ሁሉ፡፡" ይህ የቅርብ ጓደኞቹን ያመለክታል፡፡

ጠሉኝ

"አስፀያፊ አድርገው ቆጠሩኝ"

በእኔ ላይ ተነሱ

"ካዱኝ"

Job 19:20-22

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ ከሶስቱ ወዳጆቹ ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል፡፡

አጥንቶቼ ከቆዳዬ እና ከስጋዬ ጋር ተጣበቁ

"ቆዳ እና አጥንቴ ብቻ ቀረ" ወይም "ቆዳዬ ከአጥንቴ ጋር ተጣበቀ፡፡" ኢዮብ ስለ አጥንቶቹ፣ ቆዳው እና ስጋው የሚናገረው ምን እንደሚምል ለመግለጽ ነው፡፡ እጅግ ከስቶ ነበር፤ ሰዎች የአጥንቱን አቀማመጥ /አጥንቱ መውጣቱን/ በቀላሉ ይመለከቱ ነበር፡፡ አንዳንድ ቋንቋዎች ለዚህ ፈሊጣዊ አነጋገር አላቸው፡፡

በአጥንቴ ቆዳ ብቻ ቀረሁ/ድዴ ብቻ ቀረ

ይህ ፈሊጣው አነጋገር የቀረው ሞቴ ብቻ ነው ማለት ነው፡፡ "በሞት አፋፍ ላይ ነኝ" ወይም "በህይወትና በሞት መሃል ላይ እገኛለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ለእኔ ሀዘኔታ ይኑራችሁ

"ለእኔ ርህራሄ ይኑራችሁ"

የእግዚአብሔር እጅ ነክታኛለችና

እዚህ ስፍራ "ነክታኛለች" የሚለው "መትቶኛል" ለሚለው ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "እጅ" የሚለው ደግሞ የሚወክለው የእግዚአብሔርን ሀይል ነው፡፡ ኢዮብ መሰቃየቱ የተገለጸው ያህዌ በአካል በእጁ እንደመታው ተደርጎ ነው፡፡ "ምክንያቱም እግዚአብሔር መትቶኛል፡፡ በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር አሳዶኛል … ለምን ታሳድዱኛላችሁ?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የሚጠቀመው ወዳጆቹ እርሱን እንዴት እንደሚይዙት/እንደሚያዩት በምሬት ለመግለጽ ነው፡፡ " እናንተ አታሳዱኝ … እግዚአብሔር አሳዶኛል!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እስከ መቼ በቁስሌ ደስ ትሰኛላችሁ?

ኢዮብ ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚጠቀመው ወዳጆቹ እርሱን ሰለሚያስተናግዱበት መንገድ ምሬቱን ለመግለጽ ነው፡፡ "ስጋዬን እስከሚበቃ ድረስ ፈጅታችኋል/ በልታችኋል!" ወይም "ስጋዬን መብላታችሁን አቁሙ!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

በስጋዬ ስቃይ መቼ እርካታ ታገኛላችሁ?

ኢዮብ የጓደኞቹን ጭካኔ የተሞላበት ንግግር የገለጸው የዱር አውሬ ሌላ እንስሳን እንደሚበላ ባለ መልክ ነው፡፡ "በሀይል ስሜን ማጥፋታችሁን አቁሙ፡፡" ወይም "በቃላቶቻችሁ እኔን ማጥቃታችሁን አቁሙ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 19:23-24

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ ከሶስቱ ወዳጆቹ ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል፡፡

አወይ፣ ምነው ቃሎቼ በተጻፉ

ይህ አጋኖ የሚናገረው ኢዮብ ምን እንደሚፈልግ ነው፡፡ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አንድ ሰው ቃሎቼን ቢጽፍ በወደድኩ" (ቃለ አጋኖ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

የእኔ ቃሎች/ቃሎቼ

"እኔ የምናገረው"

አወየው፣ ምነው በመጽሐፍ በተጻፉ

ይህ አጋኖ የሚናገረው ኢዮብ ምን እንደሚፈልግ ነው፡፡ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አንድ ሰው በመጽሐፍ ቢጽፋቸው በወደድኩ" (ቃለ አጋኖ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

አወይ፣ በብረት ብዕር እና እርሳስ ለዘለዓለም በአለት ላይ በተቀረጹ

ይህ አጋኖ የሚናገረው ኢዮብ ምን እንደሚፈልግ ነው፡፡ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አንድ ሰው የብረት ብዕር እና እርሳስ ተጠቅሞ ለዘለዓለም በአለት ላይ ቢቀርጻቸው በወደድኩ" (ቃለ አጋኖ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

የብረት ብዕር

"ጠብረት መሮ፡፡" ይህ ለመጻፊያ ያገለግል ነበር፡፡ ሰዎች ቃላቶችን በአለት ላይ እንዲቀርጹ ከብረት የተሰራ ነበር፡፡

እርሳስ

እርሳስ ለስላሳ ብረት ነው፡፡ ሰዎች አለት ሲጠርቡ አንዴት እርሳን ይጠቀሙ እንደነበር አናውቅም፡፡ ምናልባት ጽሁፉ ለረጅም ጊዜ እንዲቆይ የጽሁፉን ፊደላት በእርሳስ ይሞሉት ይሆናል

Job 19:25-27

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ ከሶስቱ ወዳጆቹ ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል፡፡

እኔን ነጻ የሚያወጣኝ

"እኔን የሚከላከል፡፡" እዚህ ስፍራ "ነጻ አውጪ" የሚለው የሚያመለክተው የኢዮብን ንጹህነት በማረጋገጥ ነጻ የሚያወጣውን፣ ክብሩን የሚመልስለትን፣ እና ፍትህ የሚሰጠው አካል ማለት ማለት ነው፡፡

በመጨረሻ እርሱ በምድር ላይ ይቆማል

ይህ የሚያመለክተው በፍርድ ቤት ለመናገር መቆምን ነው፡፡ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1)ነጻ አውጪው በፍርድ ቤት ቆሞ ለመናገር የመጨረሻው ሰው ይሆናል፡፡ "እርሱ እኔ ጥፋተኛ መሆን አለመሆኔን ይፈርዳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ ወይም 2) ነጻ አውጪው ኢዮብን ለመከላከል በዚህ በመጨረሻው ፍርድ ቤት ይቆማል፡፡ "በመጨረሻ እርሱ በፍርድ ቤት ቆሞ ለእኔ ይከላከላል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ስጋዬ… ከጠፋ በኋላ

ይህ ሊያመለክት የሚችለው ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) የእርሱ አካል በበሽታ መጥፋትን/መጎዳቱን ወይም 2) ከሞተ በኋላ አካሉ መበስበሱን

በስጋዬ እግዚአብሔርን አየዋለሁ

ስጋው የሚወክለው አካሉን ነው፣ ደግሞም "በስጋዬ" የሚለው በህይወት መኖርን ይወክላል፡፡ "በስጋዬ ውስጥ እየኖርኩ ሳለ፣ እግዚአብሔርን አየዋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የገዛ ዐይኖቼ/የራሴ ዐይኖች - እኔ፣ ራሴ ሌላ ሰው ሳይሆን

"የገዛ ዐይኖቼ/የራሴ" የሚለው ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ/ የሚያመለክተው ኢዮብን ነው፡፡ "የገዛ ዐይኖቼ" እና "ሌላ ማንም ሳይሆን" የሚሉት ሀረጎች የሚያጎሉት በእርግጥ ኢዮብ ራሱ እግዚአብሔርን እንደሚመለከት ነው፡፡ እግዚአብሔርን የሚመለከተው እና ስለ እር የሚነግረው ሌላ ማንም አይደለም፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ልቤ በመናፈቅ ዝሏላ

ሰዎች ስሜታቸው ባለበት በዚያ ልባቸው እንዳለ ያስባሉ፡፡ ስለዚህ የልብ መውደቅ የሚወክለው/የሚገልጸው እርሱ የተለያዩ ስሜቶች እንዳሉት ነው፡፡ "ስለዚህ ጉዳይ በጣም ስሜታዊ ነኝ" ወይም "ስለዚህ ሁኔታ ሳስብ ስሜቴ ሁለንተናዬን ይወርሰዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ልቤ በመናፈቅ ዝሏል

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ኢዮብ በተስፋ፣ በምስጋና ተሞልቷል ደግሞም ተድቷል ወይም 2) ኢዮብ አዳኙን በመጠበቅ ደክሟል፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 19:28-29

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ ከሶስቱ ወዳጆቹ ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል፡፡

እንዴት እናሳድደዋለን

ይህ ቃለ አጋኖ ነው፡፡ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) እነርሱ በእርግጥ ኢዮብን ያሳድዱታል ወይም 2) በከፋ ሁኔታ እነርሱ ያሳድዱታል፡፡ (ቃለ አጋኖ የሚለውን ይመልከቱ)

የችግሩ ስር በእርሱ ላይ አለ

"ስር" የሚወክለው መነሻን/መገኛን ነው፡፡ "እርሱ የችግሮቹ ሁሉ መገኛ/ምክንያት ነው" ወይም "ይህ ሁሉ ችግር ያጋጠመው ከሰራው ስራ/ካደረገው ነገር የተነሳ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እንግዲህ ሰይፍን ፍሩ

ሰይፍ ሊወክለው የሚችላቸው ትርጉሞች 1) እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ ይፈርዳል "እንግዲህ እግዚአብሔር ይፈርድብናል ብላችሁ ፍሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ ወይም 2) እግዚአብሔር እነርሱን ይገድላቸዋል፡፡ "እንግዲህ እግዚአብሔር ይገድለናል ብላችሁ ፍሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ምክንያቱም ቁጣ በሰይፍ መቅጣትን ያመጣል

"ቁጣ" እና "ቅጣት" የሚሉት ረቂቅ ስሞች "ተቆጣ" እና "ተቀጣ" በሚሉ ግሶች ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) የእግዚአብሔር ቁጣ ቅጣት ያስከትላል፡፡ "ምክንያቱም እግዚአብሔር በእናንተ ሊቆጣ እና ሊቀጣችሁ ይችላል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ ወይም 2) የኢዮብ ወዳጆች ቁጣ ቅጣትን ያስከትላል፡፡" ምክንያቱም እናንተ በእኔ ላይ እጅግ ብትቆጡ፣ እግዚአብሔር እናንተን ይቀጣል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ያመጣል

"ምክንያት ይሆናል" ወይም "ያስከትላል"

ፍርድ አለ

"ፍርድ" የሚለው ረቂቅ ስም "ፈረደ" በሚለው ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር በሰዎች ላይ ይፈርዳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

Job 20

Job 20:1-3

አጠቃላይ መረጃ፡

ሶፋር ለኢዮብ እንዲህ ሲልመለሰ፡፡

ናዕማታዊው ሶፋር

ይህንን ወንድ ስም በኢዮብ 2፡11 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ ይህ ሶፋር የሚናገርበት ሁለተኛ ጊዜ እንደመሆኑ፣ አንዳንድ ቅጂዎች/ትርጉሞች እዚህ ስፍራ "ናዕማታዊው" የሚለውን ይተዉታል፡፡

ሃሳቤ በፍጥነት እንድመልስ ያደርገኛል

የሶፋር ሃሳብ የሚለው አስተሳሰብ አንዳች ነገር ለማድረግ ያለውን ጠንካራ ፍላጎት ይወክላል፡፡ "በፍጥነት ልመልስልህ እጅግ እፈልጋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በውስጤ ባለው ጭንቀት ምከንያት

"ጭንቀት" የሚለው ረቂቅ ስም "ተጨነቀ" በሚለው ቅጽል ሊገለጽ ይችላል፡፡ ለመጨነቅ ምክንያት የሆነው ነገር በግልጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ምክንያቱም እኔ ስለአንተ በጣም ተጨንቄያለሁ" ወይም "ምክንያቱም አንተ በተናገርከው ነገር እኔ በጣም ከመጨነቄ የተነሳ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

እኔን የሚያዋርድ ግሳጼ ሰምቻለሁ

"ግሳጼ" የሚለው ረቂቅ ስም "ገሰጸ" በሚል ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ስትገስጹኝ እና እኔን በማቃለል ስትናገሩ ሰማኋችሁ" ወይም "በስድብ አቃለላችሁኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

መረዳት/ግንዛብ የሚሰጠኝ መንፈስ መልስ ይሰጠኛል

እዚህ ስፍራ "መንፈስ" የሚለው ምናልባት ሃሳብን ወይም አስተሳሰብን የሚያመለክት ሊሆን ይችላል፡፡ "መረዳት የሚሰጠኝ አስተሳሰብ መልስ ይሰጠኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

መረዳት/ግንዛብ የሚሰጠኝ መንፈስ መልስ ይሰጠኛል

እዚህ ስፍራ "መንፈስ" ወይም አስተሳሰብ የሚለው ቃል የተነገረው ለሶፋር መልስ ሊሰጥ እንደሚችል ሰው ተደርጎ ነው፡፡ ከመረዳቴ የሚመነጭ ሀሳብ አለኝ፤ እናም አሁን ማወቅ የምፈልገው ምን እንደሆነ አውቃለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

መረዳት/ግንዛብ የሚሰጠኝ መንፈስ መልስ ይሰጠኛል

የመረዳቱ ይዘት በግልጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ከመረዳቴ የሚመነጨው አስተሳሰብ ለአንተ እንዴት መልስ እንደምሰጥ ያሳውቀኛል" ወይም "ከመረዳቴ የሚመነጭ አስተሳሰብ አለኝ፣ እናም አሁን ለአንተ እንዴት ምላሽ እንደምሰጥ አውቃለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

መረዳት/ግንዛብ የሚሰጠኝ መንፈስ መልስ ይሰጠኛል

"መንፈስ" እና "መረዳት" የሚሉት ረቂቅ ስሞች "አሰበ" እና "ተረዳ" በሚሉ ግሶች ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ "ነገሮችን ስለምረዳ፣ ሃሰብ አለኝ እናም አሁን እንዴት ለአንተ እንደምመልስ አውቃለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

Job 20:4-5

አጠቃላይ መረጃ፡

ሶፋር ለኢዮብ መልስ መስጠቱን ቀጠለ፡፡

ለቅጽበት…ይህንን እውነታ ከጥንት ጀምሮ ታውቅ ነበርን?

ሶፋር ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የተጠቀመው እርሱ አሁን የሚናገረውን ነገር ኢዮብ በጥልቀት እንዲያስብበት ለማድረግ ነው፡፡ ይህ በገለጻ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ለአፍታ…አንተ በእርግጥ ከጥንት ጀምሮ ያለውን ታውቃለህ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

የክፉ ሰው ድል ለአጭር ጊዜ ነው

"ድል" የሚለው ረቂቅ ስም "ድል አደረገ" ወይም "ግብዣ አደረገ" በሚለው ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ክፉ ሰው የሚያሸንፈው ለአጭር ጊዜ ብቻ ነው" ወይም "ክፉ ሰው ግብዣ የሚያደርገው ለአጭር ጊዜ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

አምላክ የለሽ የሆነ ሰው ደስታ የሚቆየው ለአጭር ጊዜ ብቻ ነው

"ደስታ" የሚለው ረቂቅ ስም "ሀሴት" ወይም "ደስታ" በሚለው ቅጽል ሊገለጽ ይችላል፡፡ "አፍታ/ቅጽበት" የሚለው ቃል ጊዜው በጣም አጭር መሆኑን ለማጉላት የዋለ ግነት ነው፡፡ "አምላክ የለሽ ሰው ደስታው ለቅጽበት ነው" ወይም "አምላክ የለሽ ሰው ደስ የሚሰኘው ለአጭር ጊዜ ብቻ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች እና ኩሸት እንደዚሁም አጠቃላይ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 20:6-7

አጠቃላይ መረጃ፡

ሶፋር ለኢዮብ መልስ መስጠቱን ቀጠለ፡፡

እስከ ሰማይ ከፍ ቢል እንኳን

"የክፉ ሰው ከፍታ እስከ ሰማይ ቢደርስ እንኳን" "ከፍታ" የሚለው ረቂቅ ስም "ትልቅ/ረጅም" በሚል ቅጽል ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ምንም እንኳን እርሱ እስከ ሰማይ ቢረዝም/ቢተልቅ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

እስከ ሰማይ ከፍ ቢል እንኳን

የክፉ ሰው ከፍታ የሚለው የሚወክለው ክብሩን ወይም ኩራቱን ነው፡፡ እንደዚሁም እዚህ ስፍራ እስከ ሰማይ መድረስ" የሚወክለው በጣም ትልቅ መሆንን ነው፡፡ "ምንም እንኳን ክብሩ ታላቅ ቢሆንም" ወይም "ምንም እንኳን ኩራቱ ታላቅ ቢሆንም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ራሱ እስከ ደመና ይደርሳል

"ደግሞም ምንም እንኳን ራሱ እስከ ደመና ከፍ ቢልም" ይህም የሚወክለው ክብሩን ወይም ትልቅ በመሆኑ መኩራቱን ነው፡፡ ይህ ማለት ከቀደመው ሀረግ ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

እንደ ራሱ እዳሪ ለዘለዓለም ይጠፋል

እዳሪ ከመሬት ጋር ተደባልቆ ይጠፋል፡፡ ክፉ ሰው ከእዳሪ ጋር መነጻጸሩ እርባና ቢስ/ጥቅም የለሽ መሆኑን የሚጠቁም ነው፡፡ "በአፈር ውስጥ ሙሉ ለሙሉ እንደሚጠፋ እንደ ራሱ እዳሪ በዘላቂነት ይጠፋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ራሱ እዳሪ ለዘለዓለም ይጠፋል

ሰዎች እዳሪ በሚለው ቃል ደስ የማይሰኙ/የሚያሳፍር ከሆነ ሙሉ ለሙሉ ከሚጠፋ ሌላ ነገር ጋር ማመሳሰል ይቻላል፡፡ "ንፋስ እንደ በተነው አቧራ ለዘለዓለም ይጠፋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 20:8-9

አጠቃላይ መረጃ፡

ሶፋር ለኢዮብ መልስ መስጠቱን ቀጠለ፡፡

እርሱ

"ክፉ ሰው"

እንደ ህልም ይጠፋል… እንደ ምሽት ህልም ተሰዶ ይጠፋል

እዚህ ስፍራ "መጥፋት" እና "መባረር/መሰደድ" የሚሉት ቃላት የሚወክሉት መጥፋትነ ነው፡፡ ህልሞች እና ራዕዮች በረስዋቸው ጊዜ እንደሚጠፉ ሁሉ፣ እነዚህም ክፉዎች እንደሚረሱ ያመለክታል፡፡ "እንደ ህልም ይረሳሉ… በምሽት እንደ ታየ ህልም ይረሳሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ተነጻጻሪ ዘይቤ እና ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

አይገኝም

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ማንም ሊያገኘው አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የተመለከቱት ዐይኖች

ዐይን ሰውየውን ይወክላል፡፡ "እርሱን የተመለከተ ማንም ሰው" ወይም "እርሱን የተመለከቱ ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ስፍራው

"ስፍራው/የእርሱ ስፍራ" የሚለው ሀረግ የሚወክለው በእርሱ ስፍራ የሚኖሩትን ነው፡፡ "በእርሱ ስፍራ የሚኖሩ ሰዎች" ወይም "ቤተሰቦቹ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 20:10-11

አጠቃላይ መረጃ፡

ሶፋር ለኢዮብ መልስ መስጠቱን ቀጠለ፡፡

ልጆቹ

"የክፉ ሰው ልጆች"

እጆቹ ብልጽግናውን መልሰው ያመጡለታል

እዚህ ስፍራ "እጆች" የሚለው የሚወክለው የክፉ ሰው ልጆችን ነው፡፡ እርሱ በሚሞትበት ጊዜ፣ ልጆቹ እርሱ ከሌሎች ሰዎች የወሰደውን ለመመለስ ይገደዳሉ፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

አጥንቶቹ በጥንካሬ የተሞሉ ናቸው

"አጥንቶቹ" የሚለው የሚወክለው አካሉን/ሰውነቱን ነው፡፡ "ጠቃሚ በሆነ ጥንካሬ ሙሉ መሆን" የሚለው የሚወክለው እንደ ወጣት ሰው ጠንካራ መሆንን ነው፡፡ "ሰውነቱ እንደ ወጣት ሰውነት ጠንካራ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

ነገር ግን ይህ ከእርሱ ጋር አፈር ውስጥ ይገባል

"ይህ" የሚለው የሚያመለክተው የእርሱን ጠቃሚ ጥንካሬ ነው፡፡ "አፈር ውስጥ… ይጋደማል" የሚለው ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ የሚወክለው ሞትን ነው፡፡ የሞት ጥንካሬ የሚለው መጥፋት ለሚለው ዘይቤያዊ አነጋገር ነው፡፡ "ነገር ግን ጠቃሚ ጥንካሬው ከእርሱ ጋር አብሮ ይሞታል" ወይም "ነገር ግን የእርሱ ጠቃሚ ጥንካሬ/የሚመካበት እርሱ ሲሞት አብሮት ያከትማል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 20:12-14

አጠቃላይ መረጃ፡

ሶፋር ለኢዮብ መልስ መስጠቱን ቀጠለ፡፡

ምንም እንኳን ክፋት በአፉ ላይ ጣፋጭ ቢሆንለትም

እዚህ ስፍራ "ክፋት ጣፋጭ ቢሆንለትም" የሚለው የሚወክለው ክፉ ነገር በማድረግ ደስ የሚሰኝ ሰውን ነው፡፡ " ምንም እንኳን ክፉ ነገሮችን ማድረግ ጣፋጭ ምግብን እንደ መቅመስ ደስ የሚያሰኘው ቢሆንም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ምንም እንኳን ቢደብቅም … እንዲሄድ አይፈቅድም

አንድ ሰው ጣፋጭ ምግብን በመቅመስ ደስ መሰኘቱን መቀጠል እንደሚፈልግ ክፉ ሰው ክፉ በማድረግ ደስታ ለማግኘት መፈለጉን ይቀጥላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በአንጀቱ ውስጥ ያለ ምግብ መራራ ይሆንበታል

ምግብ በአንጀት ውስጥ ወደ መራራነት ሲቀየር፣ ስቃይን ያስከትላል ደግሞም መራራ ጣዕም ያመጣል፡፡ ይህ ክፉ በማድረጉ ምክንያት መጥፎ ለሚገጥመው የዋለ ዘይቤያዊ አነጋገር ነው፡፡ "እነዚያ ክፉ ነገሮች በሆድ ውስጥ ወደ መራራነት እንደ ተለወጠ ምግብ ይሆናሉ" ወይም "የእነዚያ ክፉ ነገሮች ውጤታቸው በሆድ ውስጥ ጎምዛዛ እንደሆነ ምግብ ስቃይ የሚፈጥሩ ናቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በውስጡ እንደ እባብ መርዝ ይሆናል

ምግብ በሆድ ውስጥ ወደ መራራነት ሲቀየር፣ ስቃይን ይፈጥራል ደግሞም መራራ ጣዕምን ያመጣል፡፡ ይህ ክፉ ነገሮችን በማድረግ መከራ ለሚቀበል ሰው የዋለ ዘይቤያዊ አነጋገር ነው፡፡ "እነዚያን ክፉ ነገሮች ማድረግ ውጤቱ በውስጡ የእባብ መርዝ የገባ ያህል መሰቃየት ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

መርዘኛ

"መርዛማ እባቦች

Job 20:15-16

አጠቃላይ መረጃ፡

ሶፋር ለኢዮብ መልስ መስጠቱን ቀጠለ፡፡

ባለጸግነትን ይውጣል… መልሶ ከሆዱ ያስወግዳቸዋል

ሶፋር ሀብት ማግኘትን እና ማጣትን የሚገልጸው አንድ ሰው በልቶ መልሶ እንደሚያስመስለው ምግብ አድርጎ ነው፡፡ "ክፉ ሰው ባለጸጋ ይሆናል፣ ነገር ግን የበላውን እንደሚያስመልስ ሰው ሀብቱን ያጣዋል፡፡ እግዚአብሔር ሃብቱን በሙሉ እንዲያጣ ያደርገዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሃብትን ይውጣል

"ሃብትን ይውጣል" ለሚለው ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ሀብት ያሰበስባል፣ ደግሞም በስስት ያከማቻል፡፡ "ክፉ ሰው ብዙ ሃብት ያገኛል፣ ደግሞም ሁሉንም ለራሱ ያደርገዋል" ወይም 2) ከክፋት መንገዶች ሀብት ማከማቸት፡፡ "ክፉ ሰው ብዙ ሀብት ይሰርቃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ከሆዱ ያስተፋዋል

"ከሆዱ ያስተፋዋል" የሚለው ሰውየው ያገኘውን በማስመለስ ያወጣዋል ለሚለው ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ ይህ ክፉ ሰው ሃብቱን ለሚያጣበት ምክንያት ዘይቤያዊ አነጋገር ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

ያስወግዳል

ያስወጣል

እዚህ ስፍራ "የእባብ መርዝ ይጠባል"

የሚለው የሚወክለው ክፉ ነገር ማድረግን ነው፡፡ ሁለቱም በጣም አደገኛ ናቸው፡፡ "ክፉ ነገሮችን ማድረግ የእባብ መርዝን እንደ መጥባት ነው" ወይም "ክፉ ነገሮችን ያደርጋል ደግሞም የእባብ መርዝን እንደሚጠባ ሰው ህይወቱን አደጋ ላይ ይጥላል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

መርዛም እባብ

መርዘኛ እባብ

የእፍኝት ምላስ ይገድለዋል

እፍኝት መርዛም እባብ ነው፡፡ ምላሱ የሚወክለው መርዛም ንክሻውን ነው፡፡ "የእፍኝት መርዛማ ንክሻ እርሱን ይገድለዋል" ወይም "እፍኝት ይነክሰዋል ከዚያም ይሞታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የእፍኝት ምላስ ይገድለዋል

እፍኝት የሚወክለው የሰውየውን ክፉነት ነው፡፡ "ክፋቱ እንደ እፍኝት ንክሻ ይገድለዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 20:17-19

አጠቃላይ መረጃ፡

ሶፋር ለኢዮብ መልስ መስጠቱን ቀጠለ፡፡

ጅረቶች፣ የቅቤ እና ማር ጎርፍ

"ጅረቶች" እና "ጎርፍ" ብዛትን የሚወክሉ ዘይቤያዊ አነጋገሮች ናቸው፡፡ "ማር" እና "ቅቤ" እግዚአብሔር ለሰዎች የሚሰጠውን መልካም ነገሮች የሚወክሉ ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ናቸው፡፡ "እግዚአብሔር ለህዝቡ የሚሰጠው መልካም ነገሮች ብዛት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

የስራው ፍሬ

በተለመደው አነጋገር "የስራው ፍሬ" በቀጥታ የሚያመለክተው የስራውን ውጤት ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ግን ክፉ ሰው የሰረቃቸውን ነገሮች ያመለክታል፡፡ "ለማግኘት የሰራቸው ነገሮች" ወይም "የሰረቃቸው ነገሮች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

ሊመገበው አይችልም

እዚህ ስፍራ የስራውን ፍሬ "ሊመገብ" የሚለው የሚወክለው በሰረቀው ነገር ደስ መሰኘቱን ይወክላል፡፡ "በእነርሱ ደስ ሊሰኝ አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 20:20-22

ሳይበላ የሚያስተርፈው ምንም ነገር የለም

ይህ ከአሉታዎቹ አንዱ ብቻ ተቀይሮ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ሁሉንም ነገር ፈጅቷል፣ ያስቀረው እንድም የለም" ወይም "የቀረ ምንም ነገር የለም ምክንያቱም እርሱ ሁሉንም በልቷል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ አሉታ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ያልበላው የቀረ ምንም ነገር የለም

እዚህ ስፍራ "መብላት" የሚለው የሚወክለው ነገሮችን ለራሱ መውሰድን ነው፡፡ "ለራሱ ያልወሰደው፣ ምንም የቀረ ነገር የለም" ወይም "እርሱ ሁሉንም ለራሱ ወስዷል፣ እናም ምንም ነገር አልቀረም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ችግር ላይ ይወድቃል

"በድንገት ችግር ያጋጥመዋል"

በችግር ላይ ያለ እጅ ሁሉ በእርሱ ላይ ይነሳሉ

እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚወክለው ሀይልን ነው፣ ደግሞም "እጅ… በእርሱ ላይ ይነሳል" የሚለው የሚወክለው እርሱን የሚያጠቁ ሰዎችን ነው፡፡ "ድህነት" የሚለው ረቂቅ ስም "ድህ" በሚለው ቅጽል ይገለጻል፡፡ "በድህነት ውስጥ ያለ ሁሉ እርሱን ያጠቃዋል" ወይም "ደሀ የሆነ ሁሉ እርሱን ያጠቃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 20:23-25

አጠቃላይ መረጃ፡

ሶፋር ከኢዮብ ጋር መነጋገሩን ቀጠለ፡፡

ሆዱን ለመሙላት

እዚህ ስፍራ "ሆዱን መሙላት" የሚለው ብዙ መብላት የሚል ትረጉም የሚሰጥ ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር በእርሱ ላይ የቁጣውን መአት ያወርድበታል

"የቁጣው መአት" የሚለው የሚወክለው የእግዚአብሔርን ቁጣ እና ቅጣት ነው፡፡ ቁጣውን ያወርድበታል የሚለው በከፍተኛ ደረጃ ይቀጣዋል ማለት ነው፡፡ "እግዚአብሔር ይቆጣል ደግሞም ቁጣውን ያወርድበታል" ወይም "እግዚአብሔር ይቆጣል ደግሞም እጅግ ይቀጣዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ይህን ያዘንብበታል

"እግዚአብሔር ይህን በእርሱ ላይ እንዲዘንብ ያደርጋል፡፡" እዚህ ስፍራ "ይህን በእርሱ ላይ ያዘንባል" የሚለው የሚገልጸው በሰውየው ላይ ብዙ ጥፋት እንደሚደርስ ነው፡፡ "እግዚአብሔር እጅግ ይቀጣዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከብረት መሳሪያ ያመልጣል

የብረት መሳሪያ የሚለው የሚወክለው መሳሪያውን የያዘውን ሰው ነው፡፡ "የብረት መሳሪያ ከያዘ ሰው ያመልጣል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የነሀስ ደጋን ይወጋዋል

ደጋኑ የሚወክለው በእርሱ ቀስት የሚወረውረውን ሰው ነው፡፡ "የነሀስ ደጋን የያዘ ሰው እርሱን ይወጋዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ጉበት

ይህ ትልቅ እና ጠቃሚ የሆነ የሰውነት ክፍል ነው፡፡ አንድ ሰው በቀስት ይህን የሰውነት ክፍል ቢወጋ፣ የተወጋው ሰው ይሞታል፡፡

ፍርሃት ይወርድበታል

በድንገት በጣም ይፈራል፡፡ "በፍርሃት ተዋጠ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 20:26-27

ሀብቱ ለድቅድቅ ጨለማ ተዳርጓል

እዚህ ስፍራ "ድቅድቅ ጨለማ" የሚለው ለጥፋት ዘይቤያዊ አነጋገር ነው፡፡ "ሀብቱ ለጥፋት ተዳርጓል " ወይም "ሀብቱ ይጠፋል/ይደመሰሳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ያልተራገበ እሳት ይበላዋል

እዚህ ስፍራ "መብላት/መፍጀት" የሚለው ዘይቤ ትርጉሙ መጥፋት/መደምሰስ ማለት ነው፡፡ "የልተራገበ እሳት ያጠፋዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ያልተራገበ እሳት ይበላዋል

"ያልተራገበ" የሚለው ሀረግ የሚያመለክተው ማንም ሰው እሳቱን እንደማይጀምር ነው፡፡ ይልቁንም፣ እግዚአብሔር እሳቱን ይፈጥራል፡፡ "በሰው ያልተጀመረ እሳት እርሱን ይበላዋል" ወይም "እግዚአብሔር እርሱን የሚበላ አሳት ያመጣል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ይበላዋል/ይፈጀዋል

እዚህ ስፍራ "መብላት/መፍጀት" የሚለው ዘይቤያዊ ትርጉም መጥፋት/መደምሰስ ነው፡፡ "እሳቱ ይደመስሰዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሰማያቱ… ምድሪቱ

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) በሰማያት እና በምድር የሚኖሩት ወይም 2) ሶፋር ሰማያትን እና ምድርን የሚገልጻቸው በፍርድ ቤት ቀርበው በክፉዎች ላይ ምስክር እንደሚሆኑ ሰዎች አድርጎ ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ሰውኛ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 20:28-29

አጠቃላይ መረጃ፡

ይህ ሶፋር ከኢዮብ ጋር የሚያደርገውን ንግግር ያጠቃልላል፡፡

ጠፋ

ተደመሰሰ

ንብረቶቹ ተጠራርገው ይሄዳሉ

እዚህ ስፍራ "ተጠራርገው ይሄዳሉ" የሚለው የሚወክለው ከእርሱ ይወሰዳሉ የሚለውን ነው፡፡ "ንብረቶቹ፣ በጎርፍ ላይ እየተንሳፈፉ እንደሚወሰዱ ነገሮች ከእርሱ ይወሰዳሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ንብረቶቹ

"ያለው ሃብት"

የእግዚአብሔር የቁጣ ቀን

እዚህ ስፍራ "ቁጣ" የሚለው የሚወክለው ቅጣትን ነው፡፡ "ቁጣ" የሚለው ረቂቅ ስም "ቀጣ" በሚለው ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር ሰዎችን በሚቀጣበት ቀን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ ከእግዚአብሔር ዘንድ የክፉ ሰው እድል ፈንታው/ድርሻው ነው

እዚህ ስፍራ "ከእግዚአብሔር ዘንድ እድል ፈንታው/ድርሻው" የሚለው የሚወክለው እግዚአብሔር የወሰነው በሰውየው ላይ መድረሱ አይቀርም የሚል ነው፡፡ ይህ ተገለጸው እግዚአብሔር ለሰውየው እንደሚሰጠው ነገር ተደርጎ ነው፡፡ "እግዚአብሔር በክፉ ሰው ላይ እንዲደርስ የወሰነው ነገር ይህ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በእግዚአብሔር ለእርሱ የተጠበቀለት ቅርስ

ይህ እግዚአብሔር ለአንድ ሰው እንዲሆንለት የወሰነውን ይወክላል/ይገልጻል፡፡ ይህ የተነገረው እግዚአብሔር እንደ ውርስ አድርጎ የሚሰጠው ነገር ተደርጎ ነው፡፡ "እግዚአብሔር ለእርሱ ሊሰጠው ያቀደው" ወይም "እግዚአብሔር ለእርሱ ይሁን ብሎ ያቀደው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 21

Job 21:1-3

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ ለሶፋር ክስ ምላሽ መስጠት ይጀምራል፡፡

ታገሱኝ

"ፍቀዱልኝ" ወይም "ትዕግስት ይኑራችሁ"

መሳለቅ

"በእኔ ላይ መሳለቃችሁን መቀጠል ትችላላችሁ፡፡" ኢዮብ ምጸት የተጠቀመው ጓደኞቹ የሚናገረውን ቸል በማለታቸው እና በእርሱ ላይ መሳለቅ በመቀጠላቸው ነው፡፡ (ምጸት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 21:4-6

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ ከወዳጆቹ ጋር መነጋገሩን ይቀጥላል፡፡

ቅሬታዬ በሰው ላይ ነውን? ትዕግስት ማጣት አይገባኝምን?

ኢዮብ ጥያቄዎችን የሚጠቀመው ቅር መሰኘቱን ለእግዚአብሔር መናገሩ ተገቢ መሆኑን ለማጉላት ነው፡፡ "ቅሬታዬን የማቀርበው ለሰው አይደለም፡፡ ትዕግስት ለማጣት መብቱ አለኝ/ትዕግስት ባጣም ይገባኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

እጃችሁን በአፋችሁ ላይ አድርጉ

"አፋችሁን በእጃችሁ ሸፍኑ፡፡" ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ይህ ለመገረም ምላሽ ነው፡፡ "አፋችሁን በእጃችሁ ሸፍኑ" እንደሚለው ወይም 2) ይህ አንድ ሰው እንደማይናገር ምልክት ነው፡፡ "አንዳች ነገር አትናገር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትምዕርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

አካሌን መንቀጥቀጥ ያዘው

"ፍርሃት ሰውነቴን አራደው/አንቀጠቀጠው" ወይም "በፍርሃት ተንቀጠቀጥኩ"

Job 21:7-9

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ ከወዳጆቹ ጋር መነጋገሩን ይቀጥላል፡፡

ክፉ ሰዎች ለምን ህልውናቸው ይቀጥላል፣ ለምን እስከ እርጅናቸው ይኖራሉ፣ ለምንስ ሀይላቸው እየጨመረ ይሄዳል?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው ወዳጆቹ ክፉ ሰዎች ሁሌም ስቃይ ይደርስባቸዋል ብለው ማሰባቸው ስህተት መሆኑን ሊያሳያቸው ነው፡፡ "በእርግጥ ክፉ ሰዎች መኖራቸውን ይቀጥላሉ፣ ያረጃሉ፣ ይበልጥ ባለጸጋም እየሆኑ ይሄዳሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

በአይናቸው እየተመለከቱ ከእነርሱ ጋር ትውልዳቸው ይታነጻል… ትውልዳቸው በዐይናቸው ፊት ጸንቶ ይኖል

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ ይህ እውነት መሆኑንም ያጎላሉ ፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እየተመለከቱ… በዐይናቸው ፊት

እነዚህ ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው ምክንያቱም "ዐይኖች" እይታን ያመለክታሉ፡፡ ክፉ ሰዎች ትውልዳቸው እያየለ እና እየበለጸገ ሲሄድ ያያሉ፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

ቤቶቻቸው

እዚህ ስፍራ "ቤቶች" በእነርሱ ውስጥ የሚኖሩ የቤተሰብ አባላትን ያመለክታሉ፡፡ "ቤተሰቦቻቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔር በትር

ይህ የእግዚአብሔርን ቅጣት ያመለክታል፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 21:10-12

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ ከወዳጆቹ ጋር መነጋገሩን ይቀጥላል፡፡

ላማቸው አትጨነግፍም

"ላማቸው አትጨነግፍም" ወይም "ጥጃዋ ጤናማ እና ጠንካራ ሆኖ ይወለዳል"

ህጻናቶቻቸው እንደ መንጋ ናቸው

ኢዮብ እነዚህን ህጻናት ከጥጆች ጋር የሚያነጻጽረው ህጻናቶቻቸው እንደሚቦርቁ፣ እንደሚጫወቱ እና ደስተኞች እንደሆኑ ለማጉላት ነው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከበሮ መሰል የሙዚቃ መሳሪያ/ታምብሪን

ላዩ ከበሮ የሚመስል በብረት ቁራጭ የሚመታ እና በዙሪያው ያሉ ቁርጥራጭ ብረቶች ሲርገፈገፉ ድምጽ የሚሰጥ የሙዚቃ መሳሪያ፡፡ (ማይተወቀውን መተረጎም የሚለውን ይመልከቱ)

Job 21:13-15

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ ከወዳጆቹ ጋር መነጋገሩን ይቀጥላል፡፡

ቀናቸው

"የህይወት ዘመናቸው"

በሰላም ወደ መቃብር/ሲኦል ይወርዳሉ

ይህ ትሁት በሆነ መንገድ ሞታቸውን መግለጽ ነው፡፡ "በሰላም ይሞታሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዩፊሚዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚለውን ይመልከቱ)

የአንተ መንገዶች/መንገድህን

ይህ የሚያመለክተው እግዚአብሔር ሰዎች ምን ማድረግ እንዳለበቸው እንደሚፈልግ ነው

እናመልከው ዘንድ፣ ሁሉን ቻይ የሆነው ምንድን ነው? ወደ እርሱ ብንጸልይ ምን ጥቅም እናገኛለን?

ክፉ ሰዎች እነዚህ ጥያቄዎች የሚጠይቁት በእግዚአብሔር ላይ ለመዘበት ነው፡፡ "ይህ ሁሉን ቻይ አምላክ የእኛ አምልኮ ይገባዋል ብለን አናምንም፡፡ እርሱ ለእኛ ምንም ሊያደርግ አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

Job 21:16-18

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ ከወዳጆቹ ጋር መነጋገሩን ይቀጥላል፡፡

እነሆ፣ ብልጽግናቸው በገዛ እጃቸው ላይ አይደለምን?

እዚህ ስፍራ "እጆች" የሚለው የሚያመለክተው ሀይላቸውን ወይም አቅማቸውን ነው፡፡ ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የሚጠቀመው ወዳጆቹን ለመገዳደር ነው፡፡ "እነሆ፣ እነዚህ ክፉ ሰዎች ራሳቸውን ባለጸጋ እንዳደረጉ ይናገራሉ!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚሉትን ይመልከቱ)

መቅሰፍት በላያቸው የሚመጣው… እስከ መቼ ነው?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የሚጠቀመው እግዚአብሔር ብዙ ጊዜ ክፉዎችን አይቀጣም ብሎ የሚያስበውን ለማጉላት ነው፡፡ "ብዙ ጊዜ መቅሰፍት… አያጋጥማቸውም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

የክፉ ሰዎች መብራት ይጠፋል

ኢዮብ መብራት ማትፋትን ከሰው ሞት ጋር ያነጻጽራል፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር በድንገት ይገድላቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

የክፉ ሰዎች መብራት

ኢዮብ የክፉ ሰዎችን ህይወት እየነደደ ከሚገኝ መብራት ጋር ያነጻጽራል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በቁጣው… ይህ ለምን ያህል ጊዜ ይሆናል?

ኢዮብ ይህን ሁለተኛ ጥያቄ የሚጠይቀው እግዚአብሔር ክፉዎችን ብዙ ጊዜ አይቀጣም ብሎ ስለሚያስብ ይህንን ለማጉላት ነው፡፡ "በቁጣው… ይህ ብዙ ጊዜ አይሆንም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

ማዕበል የሚወስዳቸው …ይህ ለምን ያህል ጊዜ ነው?

ኢዮብ ይህን ሦስተኛ ጥያቄ የሚጠይቀው እግዚአብሔር ክፉዎችን ብዙ ጊዜ አይቀጣም ብሎ ስለሚያስብ ይህንን ለማጉላት ነው፡፡ "ማዕበል የሚወስዳቸው…ይህ ብዙ ጊዜ አይሆንም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

በነፋስ ፊት እንደሚጠረግ ገለባ ይሆናሉ ወይም ዐውሎ ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው እብቅ ይሆናሉ

የክፉ ሰው ሞት የተነገረው ከገለባ ይልቅ እርባና ቢስ እንደሆኑ እና በቀላሉ ተጠርጎ እንደሚወሰድ እብቅ ተደርጎ ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ነፋስ ገለባን ጠርጎ እንደሚወስድ እግዚአብሔር ይወስዳቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 21:19-21

Job 21:22-24

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ ከወዳጆቹ ጋር መነጋገሩን ይቀጥላል፡፡

እርሱ ከፍ ባሉት ላይም ፈረጅ ስለሆነ እግዚአብሔርን የሚያስተምረው አለን?

ኢዮብ ይህንን የሚጠይቀው እግዚአብሔር ሁሉን እንደሚያውቅ ለማጉላት ነው፡፡ "እርሱ በሰማያት ባሉት ላይ እንኳን የሚፈርድ ስለሆነ፣ በእርግጥ ማንም እግዚአብሔርን ማስተማር አይችልም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ ከፍ ያሉት

ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "በሰማያት ያሉት" ወይም 2) "ሀያላን ሰዎች"

አንዱ በሙሉ ሀይሉ ሳለ ይሞታል

ኢዮብ በጤና እና በሰላም ኖሮ የሞተውን ይህንን ሰው በሀዘን እና በስቃይ ከሞተው በበኢዮብ 21፡25 ከተጠቀሰው ሰው ጋረ ያነጻጽራል፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰውነቱ ወተት ጠግቧል … የአጥነቱ መቅኔ እርጥብ ነው

እነዚህ ሁለቱም ሀረጎች ሰውየው በጣም ጤነኛ ነው የሚል ትርጉም አላቸው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰውነቱ ወተት ጠግቧል

"ወተት" የሚለው ቃል "ስብ" ለማለት ይሆናል፡፡ ተሸፍኗል/የተሞላ ማለት በሚገባ ተመግቧል ማለት ነው፡፡ "ሰውነቱ በስብ የተሞላ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የአጥንቶቹ መቅኔ እርጥብ ነው

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ሰውነቱ ብርቱ እና ጤናማ ነው ማለት ነው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 21:25-26

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ ከወዳጆቹ ጋር መነጋገሩን ይቀጥላል፡፡

ሌላው ሰው ይሞታል

ኢዮብ ይህንን ሰው በኢዮብ 21፡23 ላይ ከተጠቀሰው በሰላም ከሞተው ሰው ጋር ያነጻጽራል

በነፍስ መራራነት

እዚህ ስፍራ ሀዘን የተገለጸው መራራ ጣዕም እንዳለው ነገር ተደርጎ ነው፣ "ነፍስ" ደግሞ መላ የሰውን ማንነት ታመለክታለች፡፡ "በቁጣ እና በንዴት" ወይም "አሳዛኝ ህይወት ከመኖር በኋላ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚሉትን ይመልከቱ)

አንዳች መልካም ነገር ሳያገኝ/ሳያይ

ይህ በአዎንታዊ መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "መጥፎ ነገሮችን ብቻ አይቶ" እንደሚለው፡፡

እነርሱም እንደዚው በአፍር ውስጥ ተጋደሙ

ይህ እነርሱም ሞቱ የሚለው በትህትና መግለጫ መንገድ ነው፡፡ "እነዚህ ሁለቱም ሞተው ሰዎች ይቀብሯቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዩፊሚዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚለውን ይመልከቱ)

ሁለቱንም ትል ይሸፍናቸዋል

ትሎች የተያያዙት ከሞተ ሰውነት መበስበስ ጋር ነው፡፡ "በአፍር ውስጥ የሚገኙ ትሎች የሞቱ አካሎቻቸውን ይመገባሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 21:27-28

አያያዥ ሃሳብ፡

Job 21:29-30

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ ከወዳጆቹ ጋር መነጋገሩን ይቀጥላል፡፡

መንገደኞችን አልጠየቃችሁምን? በቁጣው ቀን…እነርሱ የመሚናገሩትን አታውቁምን?

ኢዮብ እነዚህን ጥያቄዎች የሚያነሳው ወዳጆቹ ከመንገደኞች መማር ባለመቻላቸው ሊወቅሳቸው ነው፡፡ "ወደ ሩቅ አገር የተጓዙትን ልታደምጧቸው ይገባል፡፡ በቁጣው ቀን … የሆነውን ጭምር ይነግሯችሁኋል፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ክፉ ሰው ከቁጣ ቀን ይጠበቃል… በቁጣ ቀን ከጥፋት ይርቃል

እነዚህ ሀረጎች ተመሳሳይ ትረጉም አላቸው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር በአንድ ስፍራ ጥፋት ሲያደርስ ክፉውን ሰው ይጠብቀዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 21:31-33

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ ከወዳጆቹ ጋር መነጋገሩን ይቀጥላል፡፡

የክፉውን ሰው መንገድ በፊቱ የሚወቅስ ማን ነው?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የሚያነሳው ክፉዎች ሁልጊዜም እንደሚፈረድባቸው የወዳጆቹን አስተሳሰብ ለመቃወም ነው፡፡ "ማንም ሰው ከፉ ሰውን በፊቱ አይኮንነውም/አይወቅሰውም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

በፊቱ

ይህ ማለት ማንም ሰው በቀጥታ ወደ ክፉ ሰው ሄዶ ፊት ለፊት አይወቅሰውም፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ለሰራው ስራ መልሶ የስራውን የሚከፍለው ማን ነው?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የሚጠቀመው ከፉ ሰዎች ይፈረድባቸዋል የሚለውን የወዳጆቹን እምነት ለመቃወም ነው፡፡ "ለሰራቸው መጠፎ ነገሮች ማንም ሰው መልሶ አይከፍለውም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ድጋፍ ያገኛል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ሰዎች ይደግፉታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የሸለቆ ጓል ለእርሱ ጣፋጭ ይሆንለታል

ኢዮብ የሞተው ክፉ ሰው በላዩ የተጫነው አፈር እንኳን ደስ እንደሚያሰኘው ይገምታል፡፡ ይህ ማለት ክፉ ሰው ሞቱ እንኳን መልካም እንደሚሆንለት እና ዘመኑ ሲያበቃ መልካም ቀበር ይደረግለታል ይላል፡፡ "ጓል" የሚያመለክተው መቃብር የሚሸፍን አፈርን ነው፡፡ "በሸለቆ አፈር መሸፈኑን ደስ ይሰኝበታል" ወይም "በሸለቆ አፈር መቀበሩ ደስ ያሰኘዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ከእርሱ በፊት አያሌ ሰዎች እንደነበሩ፣ ሰው ሁሉ እርሱን የከተለዋል

ኢዮብ ብዙ የህዝብ ስብስብ በክፉ ሰው ቀብር ላይ እርሱን ለማክበር እንደሚገኙ አጉልቶ ይናገራል፡፡ "ወደ ቀብሩ ስፍራ ብዙ ህዝብ ከፊሉ ከፊት፣ ከፊሉ ከኋላ አጅቦት ይሄዳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

Job 21:34

አያያዥ ሃሳብ፡

ይህ ኢዮብ ለወዳጆቹ የሚያደርገውን ንግግር ያጠቃልላል፡፡

በመልሶቻችሁ ውስጥ ከሀሰት በስተቀር ሌላ ነገር ሳይኖር እንዴት በማይረባ ነገር ልታጽናኑኝ ትችላላችሁ?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የሚጠቀመው ወዳጆቹን ለመገሰጽ ነው፡፡ "በማይረባ ነገር ልታጽናኑኝ አትችሉም፡፡ መልሶቻችሁ ሁሉ ሀሳት ናቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡(ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 22

Job 22:1-3

ቴማናዊው ኤልፋዝ

ይህ የወንድ ስም በኢዮብ 2፡11 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰው እግዚአብሔርን ሊጠቅመው ይችላልን? ብልህ ሰው ለእርሱ ጠቃሚ ሊሆን ይችላልን?

ሁለቱ ጥያቄዎች በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ኤልፋዝ ጥያቄዎቹን የተጠቀመባቸው የሰው ድርጊት እና ጥበብ እግዚአብሔርን እንደማይጠቅመው ለማጉላት ነው፡፡ "ሰው እግዚአብሔርን ሊጠቅም አይችልም፡፡ ጥበበኛ ሰው እርሱን ሊጠቅመው አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚሉትን ይመልከቱ)

አንተ ጻድቅ ብትሆን ሁሉን ቻይ ለሆነው አንዳች ደስታ ነውን? መንገድህን ያለ ነቀፋ ብታደርግ ለእርሱ ጥቅም ነውን?

ሁለቱ ሃሳቦች በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ኤልፋዝ ጥያቄዎቹን የተጠቀመባቸው የኢዮብ ድርጊት እግዚአብሔርን እንደማይረዳው ለማጉላት ነው፡፡ "አንተ ጻድቅ ብትሆን ሁሉን ቻይ የሆነው አንዳች ደስታ አይቀበልም፡፡ አንተ መንገዶችህን ያለ ነቀፋ ብታደርግ እርሱ አንዳች ነገር አያገኝም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 22:4-5

አያያዥ ሃሳብ፡

ኤልፋዝ ከኢዮብ ጋር መነጋገሩን ቀጠለ

ወደ ፍርድ የሚያቀርብህ እና የሚገስጽህ አንተ ለእርሱ ካለህ አምልኮ የተነሳ ነውን? ኃጢአትህ/ክፋትህ ታላቅ

አይደለምን? ለበደልህ ዳርቻ የለውምን? ኤልፋዝ እነዚህን ጥያቄዎች የተጠቀመው ኢዮብን ለመገሰጽ እና አስከፊ ኃጢአት ስለመስራቱ ሊከሰው ነው፡፡ "በእርግጥ እግዚአብሔር አንተን የገሰጸህ እና ወደ ፍርድ ያቀረበህ ለእርሱ የተሰጠህ ስለነበርክ አይደለም! አይደለም፣ እንደምታውቀው፣ የፈረደብህ ክፋትህ/ኃጢአትህ ታላቅ ስለሆነ እና በኃጢአተኛነትህ ስለቀጠልክበት/ከኃጢአትህ ስላልተመለስክ ነው!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 22:6-8

አያያዥ ሃሳብ፡

ኤልፋዝ ከኢዮብ ጋር መነጋገሩን ቀጠለ

ላበደርከው መያዣ ጠይቀሃል

ይህ የሚያመለክተው አበዳሪ ከተበዳሪው መልሶ መክፈል መቻሉን ለማረጋገጥ አንድ ነገር እንደሚወስድ ነው፡፡

የተራቆቱትን/ድሆችን ልብሳቸውን ገፈሃል

ኤልፋዝ ኢዮብን የሚከሰው ከእርሱ ከተበደሩ ድሆች ላይ መያዣ አድርጎ ልብሳቸውን እንደወሰደ አድርጎ ነው፡፡

እንጀራቸውን ከልክለሃል

እዚህ ስፍራ "እንጀራ" የሚያመለክተው በአጠቃላይ ምግብን ነው፡፡ " ምግብ ከልክለሃል" (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

መሬታቸውን ወርሰሃል/ቀምተሃል… በላይዋ ኖረሃል

ኤልፋዝ ኢዮብን የሚከሰው ከድሃ ሰዎች መሬታቸውን እንደ ቀማ እና በመሬታቸው እንዳይኖሩ እንደከለከላቸው አድርጎ ነው፡፡ ይህንን ነጥብ የሚያጎላው ነገሩን ሁለት ጊዜ ደጋግሞ በመናገር ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

መሬታቸውን ወርሰሃል/ቀምተሃል

ኤልፋዝ ኢዮብ የያዘውን መሬት መጠን የሚያጋንነው ኢዮብን ራስ ወዳድ አድርጎ ለማሳየት ነው፡፡ "እጅግ ሰፊ መሬት ይዘሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 22:9-11

አያያዥ ሃሳብ፡

ኤልፋዝ ከኢዮብ ጋር መነጋገሩን ቀጠለ

ባሎቻቸው የሞቱባቸውን መበለቶች ባዷቸውን ሰደሃል

"መበለቶች ባዷቸውን እንዲሄዱ አድርገሃል"

መበለቶች

ባሎቻቸው የሞቱባቸው ሴቶች

አባት የሌላቸው ክንዳቸው ተሰብሯል

እዚህ ስፍራ "ክንዶች" የሚለው የሚያመለክተው ሀይልን ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ወላጅ የሌላቸውን ሳይቀር ጨቁነሃል" (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

በዙሪያህ ወጥመድ አለ… ጨለማ ሆኗል… ብዙ ውሃ ሸፍኖሃል

እያንዳንዳቸው እነዚህ ዘይቤያዊ አነጋገሮች፣ ከኃጢአቱ የተነሳ ኢዮብን ችግር እና አደጋ ዙሪያውን እንደከበቡት ይገልጻሉ፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ብዙ ውሃ

"ጎርፍ"

Job 22:12-14

አያያዥ ሃሳብ፡

ኤልፋዝ ከኢዮብ ጋር መነጋገሩን ቀጠለ

እግዚአብሔር በሰማያት ከፍታ አይደለምን?

ኤልፋዝ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመው እግዚአብሔር የኢዮብን ኃጢአት እንደሚመለከት እና እንደሚፈርድበት ለመናገር ነው፡፡ "እግዚአብሔር በሰማያት ከፍታ ነው፤ በምድር የሚሆነውን ሁሉ ይመለከታል፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

ወደ ከዋክብት ከፍታ ተመልከት፣ እንደምን ከፍ ያሉ ናቸው!

ኤልፋዝ እግዚአብሔር ከከዋክብትም በላይ ከፍ ብሎ እንደሚገኝ እያመለከተ ነው፡፡ ይህ ይበልጥ ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ "ከዋክብት እንዴት ከፍ ብለው እንደሚገኙ ተመልከት፡፡ እግዚአብሔር ከከዋክብትም በላይ ከፍ ያለ ነው!"በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ምን ያውቃል? እርሱ በድቅድቅ ጨለማ ሊፈርድ ይችላልን?

ኤልፋዝ እነዚህን ጥያቄዎች የተጠቀመው ኢዮብ በእግዚአብሔር ላይ እነዚህን ነገሮች ተናግሯል ለማለት ነው፡፡ "እግዚአብሔር በምድር ላይ የሚሆነውን አያውቅም፡፡ እሱ በጥቁር ደመና ላይ ስለተቀመጠ በእኛ ላይ ለመፍረድ ሊመለከተን አይችልም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ በሰማያት ከፍታ ይራመዳል

እዚህ ስፍራ "ከፍታ፣ጣሪያ" የሚለው የሚያመለክተው የጥንት ሰዎች ምድርን እና ሰማይን ይለያል ብለው የሚያስቡትን መለያ ነው፡፡ "እርሱ እዚህ የሚሆነውን እጅግ ሩቅ በሰማያት ሆኖ ይመለከታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 22:15-17

አያያዥ ሃሳብ፡

ኤልፋዝ ከኢዮብ ጋር መነጋገሩን ቀጠለ

ኃጢአተኞች በሚሄዱበት አሮጌ መንገድ መሄድህን ትቀጥላለህ

ክፉ ስራ መስራት የተነጻጸረው በመንገድ ላይ ከመሄድ ጋር ነው፡፡ "ክፉ ሰዎች የሚያደርጉትን ማድረግህን ትቀጥልበታለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ተቀሙት እንደ እነርሱ

ሞት የተነጻጸረው እግዚአብሔር እነርሱን እንደ ቀማቸው ተደርጎ ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "የሞቱት እነርሱ" ወይም "እግዚአብሔር የወሰዳቸው እነርሱ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

መሰረታቸው እንደ ወንዝ ተጠርጎ የተወሰደው

የክፉ ሰዎች ሞት የተነጻጸረው መሰረታቸው በጎርፍ ከተወሰደ ህንጻዎች ጋር ነው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሁሉን ቻይ የሆነው በእኛ ላይ ምን ማድረስ ይችላል?

ኤልፋዝ የሚጠቅሰው ክፉዎች በእግዚአብሔር ላይ ለመሳለቅ የሚያነሱትን ጥያቄ ነው፡፡ "ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ በእኛ ላይ አንዳች ማድረግ አይችልም!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 22:18-20

አያያዥ ሃሳብ፡

ኤልፋዝ ከኢዮብ ጋር መነጋገሩን ቀጠለ

ሆኖም እርሱ ይሞላዋል

"ሆኖም እግዚአብሔር ይሞላዋል"

የክፉ ሰዎች እቅድ ከእኔ የራቀ ነው

"ከእኔ የራቀ" የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ትርጉሙ ኤልፋዝ እነርሱን ይቃወማል ማለት ነው፡፡ "እኔ ግን ክፉ እቅዳቸውን አልሰማም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እድል ፈንታቸውን ያያሉ

"በክፉዎች ላይ የሚደርሰውን ያውቃሉ"

በንቀት ይስቁባቸዋል

"በክፉዎች ላይ ይሳለቃሉ"

እነርሱ እንዲህ ይላሉ

"ጻድቃን እንዲህ ይላሉ"

በእርግጥ በእኛ ላይ ሚነሱ ይቆረጣሉ/ይጠፋሉ

እዚህ ስፍራ "እነርሱ የሚነሱብን" የሚለው የሚያመለክተው ክፉ ሰዎችን ነው፡፡ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "በእርግጥ እግዚአብሔር እኛን የጎዱትን ክፉ ሰዎች ያጠፋቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 22:21-22

አያያዥ ሃሳብ፡

ኤልፋዝ ከኢዮብ ጋር መነጋገሩን ቀጠለ

እነሆ

ኤልፋዝ ይህንን ቃል የተጠቀመው ሊናገር የፈለገውን ጠቃሚ ነገር ለማስተዋወቅ ነው፡፡

ከአፉ የወጣው ትዕዛዝ

እዚህ ስፍራ "ከአፉ የወጣው" የሚለው የሚወክለው እግዚአብሔር የተናገረውን ነው፡፡ "እግዚአብሔር የሰጠው/የተናገረው ትዕዛዝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ቃሉን አከማችቷል

የእግዚአብሔር ቃሎች የተነጻጸሩት ኢዮብ በግምጃ ቤት ሊያጠራቅመው ከሚችለው ሀብት ጋር ነው፡፡ "ትዕዛዛቱን ማከማቸት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ልብህ

እዚህ ስፍራ "ልብ" የሚያመለክተው የኢዮብን አስተሳሰብ ነው፡፡ "የአንተ አእምሮ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 22:23-25

አያያዥ ሃሳብ፡

ኤልፋዝ ከኢዮብ ጋር መነጋገሩን ቀጠለ

አንተ ትጸናለህ

ኤልፋዝ የኢዮብን መታደስ የሚያነጻጽረው ከወደቀ ቤት መልሶ መገንባት ጋር ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እርሱ ይፈውስሀል፣ ደግሞም መልሶ ባለጠጋ ያደርግሀል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

ከጎጆች ጽድቅ ያልሆውን ብታርቅ

ጽድቅ ያልሆነ የሚለው የተገለጸው ሊርቅ እንደሚገባው በኢዮብ ጎጆ እንደሚኖር ሰው ተደርጎ ነው፡፡ "አንተ እና በቤትህ የሚኖሩ ሁሉ ኃጢአት መስራትን ብታቆሙ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሀብትህን በአፈር ውስጥ ቅበር

ሀብትን በአፈር ውስጥ መቅበር፣ ሀብትን ጥቅም እንደሌለው ማድረግ ነው፡፡ "ብልጽግናህን እንደ አፈር ጥቅም የሌለው አድርገህ ቁጠረው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የኦፊርን ወርቅ በጅረቶች ድንጋይ መሃል

ወርቅን በወራጅ ውስጥ መጣል ከደንጋይ የተሻለ ምንም ጥቅም እንደሌለው አድርጎ መቁጠር ነው፡፡ "የኦፊር ወርቅ በወራጅ ውስጥ እንደሚገኝ ድንጋይ ጥቅም የሌለው ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ኦፊር

ይህ በወርቁ የታወቀ ቦታ ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ሁሉን ቻይ የሆነው ብልጽግና፣ እና ውድ ብር ይሆንልሃል

ይህ ማለት እግዚአብሔር ለኢዮብ ከማንኛውም ሀብት ይልቅ ዋጋ ያለው ይሆንለታል ማለት ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 22:26-28

አያያዥ ሃሳብ፡

ኤልፋዝ ከኢዮብ ጋር መነጋገሩን ቀጠለ

ፊትህን ወደ እግዚአብሔር ታነሳለህ

ይህ ማለት ኢዮብ ከእንግዲህ አያፍርም፣ ይልቁንም በእግዚአብሔር ይታመናል፡፡ "በሙሉ ልን ወደ እግዚአብሔር መቅረብ ይሆንልሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ ለአንተ ይረጋገጥልሃል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር ፍሬያማ ያደርግሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

በመንገዶችህ ብርሃን ይሆናል/ይበራል

የእግዚአብሔር በረከት የተነጻጸረው በኢዮብ መንገድ ላይ ሁሉ እንደሚሆን ብርሃን ነው፡፡ "በፊትህ በሚገኝ መንገድ ላይ እንደሚበራ ብርሃን ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 22:29-30

አያያዥ ሃሳብ፡

ይህ ኤልፋዝ ከኢዮብ ጋር ያለውን ንግግር ያጠቃልላል

ዝቅ ያሉ/የተዋረዱ ዐይኖች ያሉት

እዚህ ስፍራ "ዝቅ ያሉ ዐይኖች" የሚለው የሚያመለክተው ትህትናን ነው፡፡ "ትሁቱ ሰው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ትህት ያልሆነውን ሰው እንኳን ያድናል፤ በአንተ እጅ ንጽህና ግን የሚድነው ማን ነው

የኢዮብ ንጹህ መሆን የተነገረው አካላዊ እጁ ንጹህ እንደሆነ ተደርጎ ነው፡፡ "ማን ይድናል" የሚለው ሀረግ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አንተ ትክክል የሆነውን ስታደርግ ያኔ ያህዌ ንጹህ ያልሆውን ሰው እንኳን ያድናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

እርሱ ትህት ያልሆነውን ሰው እንኳን ያድናል፤ በአንተ እጅ ንጽህና ግን የሚድነው ማን ነው

አንዳንድ ቅጂዎች እንዲህ ይላሉ፣ "እርሱ ትሁቱን ሰው ያድናል፤ ስለዚህ የአንተ እጆች ንጹህ በሆኑ ጊዜ አንተን ያድንሃል"

Job 23

Job 23:1-2

ዛሬም እንኳን ሀዘኔ መራራ ነው

እዚህ ስፍራ "ዛሬም እንኳን" የሚለው የወዳጆቹ ክርክር የኢዮብን ሁኔታ ምንም እንዳለወጠው የሚያጎላ ነው፡፡ "እንንተ ከተናገራችሁት ሁሉ ባሻገር፣ የእኔ ሀዘን ዛሬም መራራ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ሀዘኔ መራራ ነው

ኢዮብ ስላልተመለሱ ጥያቄዎቹ በአፉ ውስጥ እንዳለ መራራ ጣዕም አድርጎ እግዚአብሔርን ተቃውሞ ይናገራል፡፡ "ያልተመለሱ ጥያቄዎቼ በአፌ ውስጥ እንደሚገኝ መራራ ምግብ ሆኖብኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የእኔ እጅ ... ከማቃሰቴ የተነሳ ከብዷል

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "ከማቃሰቴ የተነሳ እጄን ማንሳት እንኳን አልቻልኩም" ወይመም 2) "ከማቃሰቴ ባሻገር የእግዚአብሔር እጅ እኔን ማሰቃየቱን ቀጥሏል" እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚለው የሚያመለክተው እግዚአብሔር ለመቅጣት ያለውን ሀይል ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 23:3-5

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ መናገሩን ቀጥሏል

አወይ፣ ያ የት እንደሆነ አውቃለሁ… አወይ፣ እኔ ወደዚያ እመጣለሁ

እነዚህ ሁለት መስመሮች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ የሚያጎሉትም ኢዮብ ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት ያለውን ፍላጎት ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አገኘው ይሆናል

"እግዚአብሔርን አገኘው ይሆናል"

ጉዳዬን በፊቱ አቀርብ… አፌን በሞላው

እነዚህ ሁለት መስመሮች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ የሚያጎሉትም ኢዮብ ለእግዚአብሔር ሁኔታውን ለማስረዳት ያለውን ፍላጎት ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አፌን በክርክር ሞላው

እዚህ ስፍራ "አፌን ሞላው" የሚለው የሚያመለክተው ንግግርን ነው፡፡ "ክርክሬን ሁሉ አቀርባለሁ/እናገራለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ቃሎቹን እማራለሁ… እረዳቸዋለሁ

እነዚህ ሁለት መስመሮች በመሰረቱ ተመሳሳይ ትረጉም አላቸው፤ የሚያተኩሩትም ኢዮብ የእግዚአብሔርን መልስ ለመስማት ባለው ፍላጎት ላይ ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ለእኔ የሚሰጠኝን መልስ

"እርሱ ለእኔ የሚሰጠውን መልስ"

Job 23:6-7

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ መናገሩን ቀጥሏል

እርሱ …ይሆን

"እግዚአብሔር…ይሆን"

በዚያ

ይህ የሚያመለክተው እግዚአብሔር የሚገኝበትን ስፍራ ነው

ፈራጄ/ዳኛዬ ለዘለዓለም ነጻ ያወጣኛል

ይህ በዐድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የእኔ ዳኛ ለዘለአለም ነጻ ያወጣኛል" ወይም "የእኔ ዳኛ የሆነው እግዚአብሔር፣ ለአንዴ እና ለመጨረሻ ጊዜ ንጹህ መሆኔን ይናገራል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 23:8-9

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ መናገሩን ቀጥሏል

ወደ ምስራቅ… ወደ ምዕራብ… ሰሜን….ደቡብ

እነዚህን አራት አቅጣጫዎት በመጥራት፣ ኢዮብ ወደ ሁሉም ስፍራ መመልከቱን ያተኩራል

ራሱን የት እንደ ሰወረ

ኢዮብ ስለ እግዚአብሔር ራሱን እንደ ሰወረ ሰው አድርጎ ይናገራል

Job 23:10-12

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ መናገሩን ቀጥሏል

እርሱ እኔ የምወስደውን መንገድ ያውቃል

የኢዮብ ድርጊቶች የተገለጹት በመንገድ እንደሚሄድ ተደርገው ነው፡፡ "እግዚአብሔር የማደርገው ምን እንደሆነ ያውቃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ወርቅ ነጥሬ እወጣለሁ

ኢዮብ መከራው እርሱ እንደ ነጠረ ወርቅ መሆኑን እንደሚያረጋግጥ ያምናል፡፡ "ማናቸውም ንጹህ ያልሆነ ነገር በእሳት ተፈትኖ ሲወገድ፣ እኔ እንደ ወርቅ ንጹህ መሆኔን ይመለከታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እግሮቼ የእርሱን መንገድ ጠብቀዋል

እዚህ ስፍራ "እግሬ" የሚለው የሚያመለክተው ኢዮብን ነው፡፡ "እርሱ ያሳየኝን መንገድ ተከትያለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሱን መንገድ ጠብቄያለሁ

የኢዮብ ታዛዥነት የተገለጸው እግዚአብሔር ባሳየው መንገድ እንደሄደ ተደርጎ ነው፡፡ "እርሱ አደርገው ዘንድ የነገረኝን አድርጌያለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡(ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከዚያ ፈቀቅ አላልኩም

ይህ በአዎንታዊ መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "በትክክል ተከትያለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ከዚያ ወደ ኋላ አልልኩም/አላፈገፈግኩም

ይህ በአዎንታዊ መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ሁልጊዜም ታዝዣለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

የእርሱ ከንፈሮች

ይህ ሀረግ የሚያመለክተው እግዚአብሔር የተናገረውን መልዕክት ነው፡፡ "እርሱ የተናገረው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የአፉ ቃል

እዚህ ስፍራ እግዚአብሔር የተገለጸው በ "አፉ" ነው፡፡ "እርሱ የተናገረው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 23:13-14

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ መናገሩን ቀጥሏል

እርሱ ብቻውን ነው፣ ማን ሊመልሰው ይችላል?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመው እንደ እግዚአብሔር ያለ ማንም እንደሌለ እና እርሱን ይለውጠው ዘንድ የሚችል ማንም እንደሌለ ትኩረት ሰጥቶ ለመናገር ነው፡፡ "ነገር ግን እንደ እርሱ ያለ ማንም የለም፣ ማንም ሀሳቡን ሊያስለውጠው አይችልም፡፡" ወይም " ነገር ግን እርሱ ብቻ አምላክ ነው፣ ማንም ተጽኖ ሊያሳድርበት አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ የወደደውን ያደርጋል

"እርሱ ማድረግ የፈለገውን ሁሉ ያደርጋል"

በእኔ ላይ ትዕዛዙን አወጣ

"በእኔ ላይ አደርጋለሁ ያለውን አደረገ"

እንደነዚህ ያሉ ሌሎች ብዙዎች አሉ

"እርሱ ለእኔ ሌሎች ብዙ ተመሳሳይ እቅዶች አሉት"

Job 23:15-17

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ መናገሩን ቀጥሏል

አጠቃላይ መረጃ፡

እነዚህ እያንዳንዳቸው ሀረጋት ኢዮብ በዚያ ያደረጋቸውን ዋና ዋና ነጥቦች ለማጉላት የትይዩ ንጽጽር ዘይቤ መልኮች አላቸው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ ሚለውን ይመልከቱ)

ልቤን ደካማ አደረገው

ልቡ የደከመ ሰው ድንጉጥ ወይም በፍርሃት የተሞላ ነው፡፡ "እንድፈራ አደረግኸኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በጨለማ ወደ ፍጻሜ አልመጣሁም

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "ከፊቴ ያለው ድቅድቁ ጨለማ ዝም አላሰኘኝም" ወይም 2) "ጨለማ አላስቆመኝም" ወይም " እግዚአብሔር እንጂ ጨለማ አላስቆመኝም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የፊቴ ትካዜ

እዚህ ስፍራ ኢዮብ ራሱን የሚገልጸው በ"ፊቱ/ገጹ" ነው፡፡ "ትካዜዬ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 24

Job 24:1

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ መናገሩን ቀጥሏል

ሁሉን ቻይ በሆነው አምላክ የክፉ ሰዎች የፍርድ ጊዜ ለምን አይወሰንም

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመው እግዚአብሔር በክፉዎች ላይ አይፈርድም የሚለውን መረበሹን ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር በክፉ ሰዎች ላይ ሚፈርድበትን ጊዜ ለምን እንደማይወስን አይገባኝም" ወይም "ሁሉን ቻይ የሆነው በክፉ ሰዎች ላይ መቼ እንደሚፈርድ መወሰን አለበት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

ለእግዚአብሔር ተማኝ የሆኑ ለምን የፍርዱ ቀን ሲመጣ/ ሲደርስ አይመለከቱም?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመው ጻድቃን እግዚአብሔር በኃጢአተኞች ላይ ሲፈርድ ባለመመልከታቸው የሚሰማቸውን መረበሽ ለመግለጽ ነው፡፡ "እርሱን የሚታዘዙ እርሱ በኃጢአተኞች ላይ ሲፈርድ የሚመለከቱ አይመስልም" ወይም "እግዚአብሔር በኃጢአተኞች ላይ ሲፈርድ እርሱን የሚያውቁ ይህንን የሚመለከቱበትን ቀን ማሳየት/ማምጣት አለበት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 24:2-4

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ መናገሩን ቀጥሏል

ዳርቻን አመልካቾች

እነዚህ በተለያዩ ሰዎች የተያዙ መሬቶችን ድንበር የሚለዩ ድንጋዮች ወይም ሌሎች ቁሳቁሶች ናቸው፡፡

የግጦሽ መሬት

እንስሳት ለግጦሽ የሚሰማሩበት መሬት

ይነዷቸዋል

"ይሰርቃሉ"

አባቶች የሌሏቸውን

"የሙት ልጆች" ወይም "ወላጆቻቸው የሞቱባቸው ልጆች"

የመበለቶችን በሬዎች መያዣ አድርገው ይወስዳሉ

"የመበለቶችን በሬዎች ለተበደሩት ገንዘብ መያዣ አድርገው ይወስዳሉ"

መበለት

ባሏ የሞተባት ሴት

መያዣ አድርገው

አበዳሪው ከተበዳሪው መልሶ መክፈሉን ለማረጋገጥ አንድ ነገር ይወስዳል፡፡

ከመንገዳቸው ወጥተው

"ከመንገዳቸው ውጭ" ወይም "ከመንገዱ ውጭ"

የምድር ድሆች ሁሉም ራሳቸውን ይደብቃሉ

"ሁሉም" የሚለው ቃል ብዙ ድሆች እነዚህን ክፉ ሰዎች እንደሚፈሯቸው የሚያሳይ ግነት ነው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 24:5-7

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ መናገሩን ቀጥሏል

የሜዳ አህዮች ወደ በረሃ ምግብ ፍለጋ በጥንቃቄ እንደሚወጡ፣ እነዚያ ድሃ ሰዎች ወደ ስራቸው ይወጣሉ

እነዚህ ድሃ ሰዎች የተገለጹት ምግባቸውን ከየት ማግኘት እንደሚችሉ እንደማያውቁ የሜዳ አህዮች ነው፡፡ "እነዚህ ድሃ ሰዎች ምግብ ፍለጋ የሚወጡት በበረሃ እንደሚኖሩ የሜዳ አህዮች ባለ ሁኔታ ነው፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የሜዳ አህዮች

"ባለቤት ወይም ተንከባካቢ የሌላቸው አህዮች"

ድሆች በምሽት ያጭዳሉ…ወይን ይለቅማሉ

እነዚህ ሁለት መስመሮች ተመሳሳይ ነገርን ይገልጻሉ፤ በአንድነት የዋሉት እነዚህ ሰዎች እጅግ የተራቡ እና በምሽት ምግብ ለመስረቅ የተገደዱ መሆናቸውን ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ ሚለውን ይመልከቱ)

እርቃናቸውን ተጋድመዋል… የሚለብሱት የላቸውም

እነዚህ ሁለት መስመሮች ተመሳሳይ ነገርን ይገልጻሉ፤ በአንድነት የዋሉት እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን ከብርድ ለመከላከል ምንም ልብስ እንደሌላቸው ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ ሚለውን ይመልከቱ)

Job 24:8-10

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ መናገሩን ቀጥሏል

ከተራሮች በሚወርድ ዝናብ ርሰዋል

"በተራሮች ሲዘንብ ርሰዋል"

የሙት ልጆችን ከእናታቸው ጡት ያስጥላሉ

እዚህ ስፍራ "ጡት" የሚያመለክተው እናትን ነው፡፡ ይህ የሚያመለክተው እነዚህ ወላጅ የሞተባቸው ገና ልጆች መሆናቸውን ነው፡፡ ይህ ይበልጥ ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ "ወላጆች የሞቱባቸው ልጆች ከእናቶቻቸው እቅፍ ሲወጡ" ወይም "አባቶቻቸው የሞቱባቸው ጨቅላ ልጆች ከእናቶቻቸው ተነጠሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

ወላጅ የሞተባቸው

ይህ በአጠቃላይ ወላጅ የሌላቸውን ልጆች ያመለክታል፡፡ ሆኖም እዚህ ስፍራ በተለይ እናት ያላቸውን ነገር ግን አባት የሌላቸውን ልጆች ያመለክታል፡፡

ከድሆች ልጆቻቸውን በመያዣነት ይወስዳሉ

"የድሆችን ልጆች ድሆቹ ከክፉ ሰዎች የተበደሩትን መልሰው እንዲከፍሉ በመያዣነት ይወስዳሉ"

በመያዣነት

አበዳሪው ተበዳሪው መልሶ መክፈል መቻሉን ለማረጋገጥ ከተበዳሪው አንድ ነገር ይወስዳ/ ይይዛል፡፡ ይህ በኢዮብ 24፡3 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

ወደዚያ ሄደ

"ተዘዋወረ"

ያለ ልብስ የተራቆተ

"ያለ ልብስ" የሚለው ሀረግ "እርቃን" ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ "ሙሉ ለሙሉ እርቃን" ወይም "አንዳች ልብስ ስላልነበራቸው እርቃናቸውን ነበሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

የሌሎችን ነዶ ይሸከማሉ

ይህ ማለት ድካማቸው/ስራች የሚጠቅመው/ምግብ የሚያስገኘው ለእነርሱ ሳይሆን ለሌሎች ነው

Job 24:11-12

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ መናገሩን ቀጥሏል

ድሆች ዘይት ያዘጋጃሉ

ከወይራ ዘይት ለእነርሱ ዘይት ይጨምቃሉ

በክፉ ሰዎች አጥር ውስጥ

እዚህ ስፍራ "አጥር" የሚለው የሚወክለው በአጠቃላይ ቤቱን ነው፡፡ "በእነዚያ ክፉ ሰዎች ቤት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

በክፉዎች ወይን መጭመቂያ ይረግጣሉ

ወይን ለማዘጋጀት ይህንን እንደሚያደርጉ መግለጽ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ "ወይን ለማዘጋጀት የወይን ፍሬ ይረግጣሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ ራሳቸው በጥም ይሰቃያሉ

"ከጥማት የተነሳ ይሰቃያሉ" ወይም "ተጠምተዋል"

Job 24:13-14

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ መናገሩን ቀጥሏል

ብርሃን ላይ ማመጽ

ለ"ብርሃን" ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) የሚታይ ብርሃን ወይም 2) መንፈሳዊ ብርሃን፣ ይህ እግዚአብሔርን ሊያመለክት ወይም በጽድቅ መኖርን ሊያመለክት ይችላል፡፡ "የቀን ብርሃንን ጠላ" ወይም "ነገሮችን በገሃድ ለማድርግ አለመፈልግ" ወይም "በእግዚአብሔር ላይ ማመጽ" በሚሉት ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ መንገዱን አላወቁም፣ አሊያም በመንገድ አልቆዩም

እነዚህ ሁለት ምመሮች ተመሳሳይ ነገርን ይገልጻሉ፣ በአንድነት የዋሉት የብርሃንን መንገድ ለመከተል አለመፈለጋቸውን አጉልቶ ለመግለጽ ነው፡፡ "ስነ ምግባር ያለው ህይወት እንዴት እንደሚኖሩ አያውቁም፤ የጽድቅ ህይወት ከመኖር የራቁ ናቸው" በሚሉት ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ድሆች እና ጎስቋላ ሰዎች

"ድሃ" እና "ጎስቋላ" የሚሉት ቃላት የሚያመለክተው ተመሳሳይ ሰዎችን ነው፤ አጉልቶ የሚገልጸውም እነዚህ ሰዎች ራሳቸውን መርዳት አለመቻላቸውን ነው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ እንደ ሌባ ነው

ሌባ ማንም ሳያየው እንደሚሰርቅ ሁሉ ነብሰ ገዳዩም በድብቅ ይገድላል፡፡ "ሌባ በድብቅ እንደሚሰርቅ ሁሉ እርሱ/ነብሰ ገዳዩ ሰዎችን በድብቅ ይገድላል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 24:15-17

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ መናገሩን ቀጥሏል

የዘማዊ ዐይን

እዚህ ስፍራ "ዐይን" የሚለው የሚያመለክተው በጠቅላላ ሰውየውን ነው፡፡ "ዘማዊው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ጀንበር ስትጠልቅ

"ፀሐይ ስትጠልቅ"

የማንም ዐይን አያየኝም

እዚህ ስፍራ "ዐይን" የሚለው የሚያመለክተው በጠቅላላ ሰውየውን ነው፡፡ "ማንም አያየኝም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ክፉ ሰዎች ቆፍረው ወደ ቤት ይገባሉ

ወደ ቤቶች ቆፍረው የሚገቡት ከእነርሱ ለመስረቅ ነው፡፡ ይህ ይበልጥ ግልጽ ተደርጎ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ክፉ ሰዎች ወደቤቶች ቆፍረው የሚገቡት ከእነርሱ ለመስረቅ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በራሳቸው ላይ ይዘጋሉ

"እነርሱ በውስጥ ይደበቃሉ"

ለእነርሱ ለሁሉም፣ ድቅድቅ ጨለማ እንደ ንጋት ነው

ለጤናማ ሰው የንጋት ብርሃን ምቹ እንደሚሆንለት ለክፉዎች ድቅድቅ ጨለማ ምቹ ነው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የድቅድቅ ጨለማ ፍርሃት

"በጨለማ የሚሆኑ አስፈሪ ነገሮች"

Job 24:18-19

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ መናገሩን ቀጥሏል

በውሃ ላይ እንዳለ አረፈ

አረፋ የሚቆየው ለአጭር ጊዜ ብቻ ነው፡፡ ይህ እግዚአብሔር ክፉዎችን አንደምን በቶሎ እንደሚያጠፋ አጎልቶ ያሳያል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ምድራቸው የተረገመ ነው

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር ምድራቸውን ይረግማታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ድርቅ እና በረሃማነት/ሙቀት እንደሚያጠፉ… ኃጢአት የሰሩ

ኢዮብ፣ በሙቀት ጊዜ በረዶ እንደሚቀልጥ እና እንደሚጠፋ ኃጢአተኞች በሲኦል ይጠፋሉ ይላል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ድርቅ እና በረሃማነት/ሙቀት

እነዚህ ሁለት ቃላት በመሰረቱ ተመሳሳይ የአየር ንብረትን ይገልጻሉ፤ በአንድነት የቀረቡት ነገሩን በሙላት ለመግለጽ ነው፡፡ (ሄንዲየዲስ/ሁለት ቃላት ‘እና' በሚል አያያዥ ቃል የሚገኛኙበትና አንድን ጥልቅ ሀሳብ ለመግለጽ የሚያገለግል ዘይቤያዊ አነጋገር)

Job 24:20-21

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ መናገሩን ቀጥሏል

ማህጸን

ይህ የሚያመለክተው እናትን ነው፡፡ "እናት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ትሎች በደስታ ይመገቡታል

ይህ ማለት ይሞትና ትሎች በድኑን ይበሉታል ማለት ነው፡፡ "ትሎች በድኑን በመብላት ይረካሉ" ወይም "እርሱ ይሞታል ደግሞም በድኑ በትል ይበላል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡(ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከዚህ ወዲያ መታሰቢያ አይኖረውም

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ከዚህ በኋላ ማንም አያስታውውም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ክፋት እንደ ዛፍ ይቆረጣል

እግዚአብሔር በክፉ ሰው ላይ የሚያደርሰው ጥፋት የተገለጸው ዛፍን ቆርጦ እንደሚጥል ተደርጎ ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር ከፉ ሰውን የሚያጠፋው/ቆርጦ የሚጥለው ዛፍ እንደነበር አድርጎ ነው፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

ክፉዎች ይበላሉ

ይህ ዘይቤ ክፉ ሰው ምን ያህል ስር የለሽ እንደሆነ ያሳያል፡፡ "የዱር አውሬ የሚያድነውን እንደሚገድል፣ ክፉ ሰውም እንደዚያው ጉዳት ይደርስበታል" (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

መሃኒቱ ወለደች

የዚያን ዘመን ሰዎች መሀን ሴት በእግዚአብሔር እንደ ተረገመች አድርገው ይቆጥሩ ነበር፡፡ ስለዚህም ይህ እጅግ እድለቢስ የሆነችን ሴት ይወክላል፡፡

መበለት/ጋለሞታ

ባሏ የሞተባት ሴት

Job 24:22-23

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ መናገሩን ቀጥሏል

በእርሱ ሀይል

"ሀይሉን በመጠቀም" ወይም "ሀይለኛ በመሆኑ ምክንያት"

እርሱ ይነሳል ደግሞም በህይወት አያበረታቸውም

"በህይወት አያበረታቸውም" ማለት እግዚአብሔር በህይወት አያኖራቸውም/ህይወት አይሰጣቸውም ማለት ነው፡፡ "እግዚአብሔር ይነሳል፣ ክፉዎች በህይወት እንዲኖሩ አቅም አይሰጣቸውም" ወይም "እግዚአብሔር ይነሳል ደግሞም በህይወት እንዳይኖሩ ይገድላቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ነገር ግን ዐይኖቹ በመንገዳቸው ላይ ነው

እዚህ ስፍራ "ዐይኖች" የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ነው፡፡ "ነገር ግን ሁልጊዜም የሚያደርጉትን ይመለከታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 24:24-25

አያያዥ ሃሳብ፡

ይህ የኢዮብን ንግግር ያጠቃልላል

ወደ ህግ ይቀርባሉ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር ወደ ህግ ያቀርባቸዋል" ወይም "እግዚአብሔር ያጠፋቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደሌሎቹ ሁሉ ይሰበሰባሉ

አንዳንድ ትርጉሞች በተለየ ጥንታዊ ጽሁፍ/ጥቅስ ላይ የተመሰረቱ ናቸው፣ "እንደ አረም ጠውልገው ይጠፋሉ" እንደሚለው፡፡ (የጽሁፍ/ጥቅስ ልዩነቶች የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱም እንደ ሌሎቹ ሁሉ ይሰበሰባሉ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ሌሎች" የሚለው ምን እንደሚያመለክት በግልጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር ሌሎች ክፉ ሰዎችን እንደሰበሰበ እነዚህንም ይሰበስባል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

በምድር ገጽ ላይ እንደሚገኝ ቅንጣት እነርሱም ይቀረጣሉ

እነዚህ ክፉ ሰዎች በአዝመራ ወቅት እንደሚታጨድ ሰብል በተመሳሳይ መንገድ ይቆረጣሉ፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ገበሬ የእህልን አገዳ አናት እደሚቆርጥ እግዚአብሔር እነርሱን ይቆርጣቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

እንደዚህ ካልሆነ፣ የእኔን ሀሰተኝነት ማን ማረጋገጥ ይችላል፣ ማነድ ንግግሬን እርባና ቢስ ያደርገዋል?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመበት የክርክሩን እርግጠኝነት ለመግለጽ ነው፡፡ በውስጠ ታዋቂነት የቀረበው መልስ፡ "ማንም የለም" የሚል ነው፡፡ "ይህ እውነት ነው፣ ደግሞም ማንም እኔ ሀሰተኛ ሊያደርገኝ አይችልም፤ ማንም እኔ ስህተተኛ መሆኔን ማረጋገጥ አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ንግግሬን እርባና ቢስ የሚያደርግ

"የተናገርኩት ስህተት መሆኑን ማረጋገጥ የሚችል"

Job 25

Job 25:1-3

ሹሐዊው በልዶስ

ይህ የወንድ ስም በኢዮብ 2፡11 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ

ገናንነት እና መፈራት የእርሱ ናቸው

እዚህ ስፍራ "እርሱ" የሚለው የሚያመለክተው እግዚአብሔርን ነው፡፡ "ገናና/የበላይ" እና "ፍርሃት" የሚሉት ረቂቅ ስሞች በግስ መልክ ሊጻፉ ይችላሉ፡፡ "እግዚአብሔር በሁሉም ላይ ይገዛል፣ እናም ሰዎች እርሱን ብቻ ይፍሩት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ በሚገኝበት በከፍታ ስፍራ በላይ በሰማይ ስርአትን አበጅቷል

"በላይ በሰማይ ሰላምን አድርጓል"

ለሰራዊቱ ቁጥር ልክ/መጠን አለውን?

በልዳዶስ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመው እግዚአብሔር ምን ያህል ታላቅ እንደሆነ አጉልቶ ለመግለጽ ነው፡፡ በውስጠ ታዋቂነት ለጥያቄው የተሰጠው ምላሽ "የለውም" የሚል ነው፡፡ ይህ የሚያመለክተው የእግዚአብሔር ሰራዊት የሆኑተን መልአክትን ነው፡፡ "በእርሱ ሰራዊት ውስጥ የመላዕክቱ ቁጥር መጠን የለውም፡፡" ወይም "የእርሱ ሰራዊቶች ማንምሊቆጥራቸው የማይቻለው እጅግ ብዙ ናቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

የእርሱ ብርሃን የማያበራው በማን ላይ ነው?

በልዳዶስ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመው እግዚአብሔር ለሁሉም ሰው ብርሃን እንደሚሰጥ አጉልቶ ለመግለጽ ነው፡፡ "የእርሱ ብርሃን በላዩ የማያበራለት ማንም የለም" ወይም "እግዚአብሔር ብርሃኑ በሁሉም ላይ እንዲበራ አድርጓል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 25:4-6

አያያዥ ሃሳብ፡

በልዳዶ መናገሩን ቀጥሏል

ታዲያ ሰው እንዴት… በእግዚአብሔር ፊት…? ከ…የተወለደ ሰው እርሱ እንዴት?

እነዚህ ሁለት ጥያቄዎች በአንድነት የዋሉት ሰው በእግዚአብሔር ፊት ፍጹም ሊሆን እንደማይችል አጉልቶ ለመግለጽ ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚሉትን ይመልከቱ)

ሰው እንዴት በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሆኖ ሊገኝ ይችላል?

በውስጠ ታዋቂነት የሚሰጠው ምላሽ አይችልም የሚል ነው፡፡ "አንድ ሰው በፍጹም በእግዚአብሔር ፊት ጻድቅ ሊሆን አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ከ.. የተወለደ … በእርሱ ፊት እንዴት ተቀባይነት ያገኛል?

በውስጠ ታዋቂነት የጥያቄው ምላሽ አይችልም የሚል ነው፡፡ "ከሴት የተወለደ ሰው በእግዚአብሔር ፊት በፍጹም ንጹህ ሊሆን ወይም ተቀባይነት ሊያገኝ አይችልም" (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ከሴት የተወለደ እርሱ/ሰው

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ሁሉንም ሰው ያካትታል፡፡ "ማንኛውም ሰው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እነሆ

እዚህ ስፍራ "እነሆ" የሚለው ቃል ተከትሎ በሚመጣው ላይ ትኩረት ይጨምራል፡፡ "በእርግጥ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

በእርሱ ፊት ጨረቃ ብሩህነት የላትም

"ብሩህ" የሚለው ረቂቅ ስም በቅጽል መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "በእግዚአብሔር ፊት ጨረቃ በቂ ብሩህነት የላትም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

በእርሱ እይታ ከዋክብት ንጹሃን አይደሉም

እዚህ ስፍራ "ንጹህ" ማለት ፍጹም ማለት ነው፡፡ "እርሱ ከዋክብትን እንኳን ፍጹም አድርጎ አያያቸውም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ትል የሆነ፣ የሰው ልጅ … ሰው ምን ያህል ያንሳል

እነዚህ ሁለት መስመሮች ተመሳሳይ ነገር ይናገራሉ፤ በአንድነት ሆነው የሚያጎሉትም ሰው ፍጹም አለመሆኑን ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ትል ማን ነው

በልዳዶስ የሰው ልጆች እንደትሎች እርባና ቢስ መሆናቸውን ይገልጻል፡፡ "እንደ ትል እርባና ቢስ የሆነ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የሰው ልጅ

ይህ ሰው የተገለጸበት ሌላ መንገድ ነው፡፡ "አንድ ሰው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 26

Job 26:1-4

አቅም የሌለውን ክንድ … እርሱን እንዴት ረዳኸው

በዚህ ዐረፍተ ሀሳብ፣ ኢዮብ በልዳዶስን እየነቀፈው/እየከሰሰው ነው፡፡ "እርሱን" የሚለው የሚያመለክተው ኢዮብን ነው፡፡ "ክንድ" የሚለው ቃል ደግሞ የሚወክለው በአጠቃላይ ሰውየውን ነው፡፡ "እኔ አቅም የለኝም፤ ደግሞም አንዳች ጥንካሬ የለኝም፣ ነገር ግን አንተ እንደረዳኸኝ ያህል ትሆናለህ፣ ነገር ግን በእርግጥ አንተ ምንም አልረዳኸኝም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ምፀት እና ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚሉትን ይመልከቱ)

ጥበብ የሌለውን እንዴት መከርከው፤ እንዴት ጠቃሚነት ያለው እውቀት ሰጠው

ኢዮብ በልዳዶስ መልካም ምክር እና እውቀት እንዳልሰጠው እየተናገረ ነው፡፡ "አንተ የሚምልህ እኔ አንዳች ጥበብ እንሌለኝ እና አንተ እንደመከርከኝ፤ ደግሞም ጥሩ ምክር እንደሰጠኸኝ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)

ለእርሱ ተሰሚነት ያለው እውቀት ሰጠው

"ጥሩ ምክር ሰጠው"

እነዚህን ቃላት በማን እርዳታ ተናገርክ? አንተ…ይህ የማን መንፈስ ነበር?

በእነዚህ ጥያቄዎች ኢዮብ በበልዳዶስ ላይ መሳለቁን ይቀጥላል፡፡ ሁለቱም ጥያቄዎች ቃለ ምልልሳዊ ናቸው፤ ትርጉማቸውም በመሰረታዊነት አንድ ነው፡፡ በአንድነት የቀረቡት አንዱ ሀሳብ ሌላውን ለማጠንከር ነው፡፡ "እነዚህን ቃላት እንድትናገር እርዳታ ሳታገኝ አልቀረህም፡፡ ምናልባት እነዚህን ነገሮች እንድትናገር አንድ መንፈስ ሳይረዳህ አልቀረም!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 26:5-6

የሞቱት

ይህ የሚያመለክተው የሞቱ ሰዎችን ነው፡፡ "እነዚያ የሞቱት" ወይም "የሞቱት መንፈስ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስማዊ ቅጽሎች የሚለውን ይመልከቱ)

መንቀጥቀጥ

እግዚአብሔርን ስለፈሩ ተንቀጠቀጡ፡፡ ይህ ይበልጥ ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ "በፍርሃት ተንቀጠቀጡ" ወይም "እግዚአብሔርን በመፍራት ተንቀጠቀጡ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ከውሆች በታች የሚኖሩ

ይህ በፍርሃት የተንቀጠቀጡትን ሙታን ያመለክታል

በእነርሱ የሚኖሩ ሁሉ

ይህ የሚያመለክተው በውሆች ውስጥ የሚኖሩ የሞቱ ሰዎችን ነው

በእግዚአብሔር ፊት ሲኦል እርቃኑን ነው፤ ጥፋት ራሱ ምንም መሸፈኛ የለውም

ሲኦል የተገለጸው ሰው እንደሆነ ተደርጎ ነው፡፡ እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ "ራቁት" መሆን ወይም "መሸፈኛ" ማጣት አንዳች ነገር ለመደበቅ አለመቻል እና ሙሉ ለሙሉ መጋለጥ ማለት ነው፡፡ "ሲኦል በእግዚአብሔር ፊት የተራቆተ እንደሆነ ሁሉ፣ በሲኦል አንዳች ነገር እንደሌለ፣ የጥፋት ስፍራ እንደሆነ፣ ከእግዚአብሔር ፊት የራቀ/የተደበቀ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይልከቱ)

ጥፋት

ይህ የሲኦል ሌላው ስሙ ነው፡፡ "የጥፋት ስፍራ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

Job 26:7-8

እርሱ ሰሜናዊውን ሰማይ በህዋው ላይ ዘረጋው

ሰሜናዊ ሰማይ የሚለው የሚወክለው፣ እግዚአብሔር እርሱ ከፈጠራቸው ፍጥረታት ጋር የሚኖርበትን ስፍራ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ በእነዚህ ከባድ ደመናዎች ውሆችን ቋጥሯል

ደመናዎች የተነጻጸሩት እግዚአብሔር የዝናብን ውሃ ከጠቀለለበት ትልቅ ብርድ ልብስ ጋር ነው፡፡ "እርሱ ውሆችን በከባድ ደመናዎች ጠቅልሏል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 26:9-10

ደግሞም በእርሷ ላይ ደመናዎችን ዘርግቷል

ይህ ሀረግ የጨረቃን ገጽ እንዴት እንደሸፈነ ይገልጻል፡፡ በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ "ደመናዎቹን በእርሷ ፊት በመዘርጋት"

እርሱ በውሆች ገጽ ዙሪያ ክብ ዳርቻዎችን አበጅቷል

ይህ እግዚአብሔር በውቅያኖስ ላይ የዳርቻ ምልክት ያደረገ የሚመስልበትን ምድር ከሰማይ ጋር የገጠመ ሆኖ ስለሚታይበት ስለ አድማስ ይናገራል

Job 26:11-12

የሰማይ አምዶች ተናወጡ፣ በቁጣውም ራዱ

ሰዎች ሰማያት ወይም ሰማይ በአምዶች ላይ እንደቆሙ ያስባሉ፡፡ ኢዮብ ሰዎች እግዚአብሔር ሲቆጣ የሚርዱ አምዶች እንደሆኑ አድርጎ ይናገራል፡፡ "ሰማይን የተሸከሙ አምዶች እግዚአብሔር ሲቆጣቸው በፍርሃት ይናወጣሉ" ወይም "ሰማይን የተሸከሙ አምዶች እግዚአብሔር ሲገስጻቸው እንደሚርዱ ሰዎች ይናወጣሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ረአብን ይቆራርጣል/ይሰባብራል

"ረአብን ያጠፋል"

ረአብ

ይህ በውሃ ውስጥ የሚኖር አስፈሪ የሆነ አውሬ ስም ነው፡፡ ይህ በኢዮብ 9፡13 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 26:13-14

በእስትንፋሱ ሰማያትን ያነጻል

"እስትንፋስ" የሚለው ስም "ተነፈሰ" ወይም "እፍ አለ" በሚለው ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ ይህ ምሳሌ የሚወክለው እግዚአብሔር ደመናትን ለመበተን እግዚአብሔር ነፋሳትን እንደሚያነፍስ ነው፡፡ "እግዚአብሔር ሰማያት ንጹህ ይሆኑ ዘንድ ደመናዎችን ይበትናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እጆቹ በራሪውን አውሬ ወጋ

ይህ የሚያመለክተው እግዚአብሔር በእጆቹ ሰይፍ እንደ ያዘ እና እዚህ ስፍራ "የእርሱ እጅ" የሚለው ደግሞ የሚያመለክተው ያንን ሰይፍ ነው፡፡ "በሳው" መግደልን ያሳያል፡፡ "በሰይፉ በራሪ አውሬውን ወጋ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ እና ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

በራሪው አውሬ

"አውሬው ከእርሱ ለማምለጥ በሞከረ ጊዜ፡፡" ይህ በውሃ ውስጥ የሚኖረውን ረአብን ያሳያል፡፡ ኢዮብ 26፡12 ይመልከቱ፡፡

እነሆ፣ ይህ የመንገዱ ዘርፍ ነው

እዚህ ስፍራ "ዘርፍ" የሚወክለው ትልቅ ከሆነ ነገር ውስጥ አነስተኛ የሆነውን ክፈል ነው፡፡ "እነሆ፣ እነዚህ እግዚአብሔር የሰራቸው ነገሮች የሚያመለክቱት ከታላቅ ሀይሉ ውስጥ ጥቂቱን ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከእርሱ ምንኛ ታናሽ ሹክሹክታውን እንሰደማለን!

ይህ እኛ ስለመኖሩ እንኳን ከነጭርሱ የማናውቀው የኢዮብን አድናቆት አጋኖ የሚገልጽ እግዚአብሔር ከሰራቸው ታላላቅ ነገሮች አንዱ ነው፡፡ እግዚአብሔር ያደረገውን ማየት የተገለጸው የእግዚአብሔርን ድምጽ እንደመስማት ተደርጎ ነው፡፡ "ይህ የእርሱን ጸጥ ያለ ማንሾካሾክ እንደመስማት ነው!" (ቃለ አጋኖ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 27

Job 27:1-3

እንደ እግዚአብሔር ህልውና እርግጠኝነት ያለው

ይህ ሀረግ የሚያመለክተው ኢዮብ ማሃላ ማድረጉን ነው፡፡ ኢዮብ የእግዚአብሔርን ህልውና እርግጠኝነት የሚያነጻጽረው እርሱ ከተናገረው ነገር እርግጠኝነት ጋር ነው፡፡ ይህ በመሃላ ነገርን የማረጋገጥ መንገድ ነው፡፡ "ህያው እግዚአብሔርን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ፍትህን ከእኔ አራቀው

ፍትህ የተገለጸው ሊወሰድ ወይም ሊሰጥ እንደሚችል አካል/ቁስ ነው፡፡ መውሰድ የሚለው የሚገልጸው ለኢዮብ ተገቢውን ፍትህ መንፈግን ነው፡፡ "ለእኔ ፍትህ መስጠትን አልወደደም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ህይወቴን መራራ አደረገ

የኢዮብ "ህይወት" መራራ መሆን የሚወክለው ኢዮብ ለእግዚአብሔር ያለውን በቅሬታ የተሞላ ስሜት ነው፡፡ "ህይወቴ በቅሬታ የተሞላ እንዲሆን አደረገ" ወይም "በአግባብ ስላልተመለከተኝ በሀዘን ሞላኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ህይወቴ ገና በውስጤ እስካለች ድረስ

ይህ የሚያመለክተው በህይወት ለመኖር የቀረውን እድሜ ነው፡፡ "ህይወቴ በውስጤ በምትኖርበት በቀሪው ዘመን ሁሉ" ወይም "ህይወቴ በእኔ ውስጥ እስካለች ድረስ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ህይወቴ ገና በውስጤ እስካለች ድረስ

"ህይወት" የሚለው ረቂቅ ስም "መኖር" በሚል ቅጽል ወይም "ኖረ" በሚል ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "በህይወት እስካለሁ ድረስ" ወይም "በህይወት እስከ ኖርኩ ድረስ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔር እስትንፋስ በአፍንጫዬ ውስጥ አለ

"እስትንፋስ… በአፍንጫዬ አለ" የሚለው የሚወክለው መተንፈስ መቻልን ነው፡፡ "እስትንፋስ ከእግዚአብሔር ዘንድ" የሚለው የሚገልጸው እግዚአብሔር እርሱን መተንፈስ ማስቻሉን ነው፡፡ "እግዚአብሔር እስትንፋስ ሰጠኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

አፍንጫዎች

"አፍንጫ"

Job 27:4-5

ከንፈሮቼ ክፋትን አይናገሩም፣ ምላሶቼም ሽንገላን አያወሩም

እነዚህ ሁለት ሀረጋት በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፣ በአንድነት የቀረቡት በዚህ አይነት መንገዶች እንደሚናገር በትኩረት ለመግለጽ ነው፡፡ "ከንፈሮቼ" እና "ምላሴ" የሚሉት የሚወክሉት ራሱን ኢዮብን ነው፡፡ "ክፋትን አልናገርም ወይም አላታልልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚሉትን ይመልከቱ)

ክፋትን መናገር… ማታለል/ሀሰትን መናገር

"ክፋት" እና "ማታለል" የሚሉት ረቂቅ ስሞች "በክፋት" እና "በማታለል" በሚሉት ቃላት ሊገለጽ ይችላል፡፡ "በክፋት መናገር… በማታለል መናገር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

መቼም ቢሆን እናንተ ሶስታችሁ ትክክል ናቸው ብዬ መናገር አልችልም

"መቼም ቢሆን ሶስታችሁ ትክክል ናችሁ ስል ከእናንተ ጋር አልስማማም"

እናንተ ሶስታችሁ ትክክል ናችሁ

"እናንተ" የሚለው ቃል ብዙ ቁጥር ነው፡፡ የሚያመለክተውም የኢዮብን ወዳጆች ነው፡፡ (አንተ የሚለው ቃል ልዩ ልዩ መልኮች)

ቅንነቴን አልጥልም

"በፍጹም ትሁት መሆኔን ልክድ አልችልም" ወይም "ሁልጊዜም ቢሆን ትሁት መሆኔን እናገራለሁ"

Job 27:6-7

ጽድቄን አጥብቄ እይዛለሁ

እዚህ ስፍራ "አጥብቄ እይዛለሁ" የሚለው አንድን ነገር አጥብቆ ይዞ መቀጠል ለሚለው ዘይቤያዊ አነጋገር ነው፡፡ "ጽድቅ" የሚለው ረቂቅ ስም "ጻድቅ" በሚለው ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ጻድቅ ነኝ የሚለውን አጥብቄ ይዤ ለመቀጠል ወስኛለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)

እንዲሄድ አልፈቅድም

እዚህ ስፍራ "እንዲሄድ አልፈቅድም" የሚለው አንድን ነገር ለመተው/ለማቆም አለመፍቀድን የሚገልጽ ዘይቤ ነው፡፡ "ጻድቅ መሆኔን መናገርን አላቆምም" ወይም "እንደዚያ ማለቴን አላቆምም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሀሳቤ አይዘልፈኝም

እዚህ ስፍራ "ሀሳቤ/አስተሳሰቤ" የሚለው የሚወክለው ኢዮብን ነው፡፡ "በሃሳቤ እንኳን፣ ራሴን አልዘልፍም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ጠላቶቼ እንዲህ ይሁኑ… በእኔ ላይ የሚነሱ እንዲህ ይሁኑ

በእነዚህ ቃላት የሚጀምሩት እነዚህ ሁለት ሀረጋት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ በአንድነት የቀረቡት ይህ እንዲሆን ኢዮብ ያለውን ጠንካራ ፍላጎት በትኩረት ለመግለጽ ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጠላቶቼ እንደ ኃጢአተኛ ሰው ይሁኑ

እርሱ ጠላቶቹ እንዴት እንደ ኃጢአተኛ ሰው እንዲሆኑ እንደሚፈልግ ግልጽ ተደርጎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ጠላቶቼ እንደ ኃጢአተኛ ሰው ይቀጡ" ወይም "እግዚአብሔር ኃጢአተኛ ሰዎችን እንደሚቀጣ ጠላቶቼን ይቅጣቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በእኔ ላይ የሚነሳ እንደ ኃጢአተኛ ሰው ይሁን

ኢዮብ ይህ ሰው/ጠላቱ/ እንዴት እንደ ኃጢአተኛ ሰው ሊሆን እንደሚፈልግ ግልጽ ተደርጎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "በእኔ ላይ የሚነሳብኝ እርሱ ኃጢአተኛ ሰው እንደሚቀጣ ይቀጣ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በእኔ ላይ የሚነሳብኝ እርሱ

እዚህ ስፍራ "በእኔ ላይ የሚነሳብኝ" የሚለው ዘይቤያዊ አገላለጽ ሲሆን ትርጉሙ "የሚቃወመኝ" ማለት ነው፡፡ መላው ሀረግ የሚያመለክተው የኢዮብን ተቃዋሚዎች ነው፡፡ "እኔን የሚቃወመኝ እርሱ" ወይም "የእኔ ተቃዋሚ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 27:8-10

እግዚአብሔር ህይወቱን በሚሰበስባት/በሚወስድ ጊዜ… እግዚአብሔር የለሽ የሆነ ሰው ተስፋው ምንድን ነው?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመው እንዲህ ያለው ሰው ምንም ተስፋ የለውም ለማለት ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በቀላል ሀሳብ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር ነፍሱን ሲወስዳት… እግዚአብሔር የለሽ ለሆነ ሰው አንዳች ተስፋ የለውም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ሲቆርጠው፣ እግዚአብሔር ህይወቱን ሲወስዳት

ሁለቱ ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ "እግዚአብሔር እርሱን በሚቆርጠው እና ህይወቱን በሚወስድ ጊዜ" ወይም "እግዚአብሔር እርሱን ሲገድለው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱን ሲቆርጠው

የዚህ ዘይቤያዊ አነጋገር ትርጉም "እርሱን ሲገድለው" ወይም "እንዲሞት ሲያደርግ" ማለት ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ህይወቱን ሲወስድ

የዚህ ዘይቤያዊ አነጋገር ትርጉም "እርሱን ሲገድለው" ወይም "መኖሩ እንዲያበቃ ሲያደርግ" ማለት ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ችግር ደርሶበት ሲጮህ እግዚአብሔር ይሰማው ይሆን?

Job 27:11-12

እኔ አስተምርሃለሁ

በእነዚህ ሀረጎች "እናንተ" የሚለው በተገለጸ ጊዜ ሁሉ ብዙ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተውም የኢዮብን ሶስት ጎደኞች ነው፡፡

የእግዚአብሔር እጅ

የእግዚአብሔር "እጅ" የሚያመለክተው ሀይሉን ነው፡፡ "የእግዚአብሔር ሀይል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ሁሉን ቻይ የሆነውን ሀሳብ አልሸሽግም

"ሀሳብ" የሚለው ረቂቅ ስም "አሰበ" በሚለው ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ሁሉን ቻይ የሆነውን ሀሳብ ከእናንተ አልደብቅም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ታዲያ ለምን ይህንን የማይረባ ነገር ሁሉ ትናገራላችሁ?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመው ወዳጆቹ እንደዚህ ያሉ የማይረቡ ነገሮችን ስለተናገሩ ሊገስጻቸው ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በቀላል ሀሳብ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "እንዲህ ያለ የማይረባ ነገር መናገር አልነበረባችሁም!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 27:13-14

ይህ ከእግዚአብሔር ዘንድ የኃጢአተኛ ሰው አድል ፈንታው/ድርሻ ነው፡፡

"ይህ እግዚአብሔር ለኃጢአተኛ ሰው ያቀደለት ነው"

ሁሉን ቻይ ከሆነው ዘንድ የሚቀበለው የጨቆኝ ሰው/ሰውን የሚያሳዝን ሰው ድርሻው

እዚህ ስፍራ "የጨቆኝ/ ሰውን የሚያሳዝን ሰው ድርሻው" የሚለው በጨቆኝ ሰው/ሰውን በሚያሳዝን ሰው ላይ የሚደርሰውን ነገር የሚገልጽ ዘይቤ ነው፡፡ በዚህ ሰው ላይ እግዚአብሔር የሚያደርገው ነበር የተገለጸው እግዚአብሔር ለእርሱ የሚሰጠው ነገር ተደርጎ ነው፡፡ "ሁሉን ቻይ የሆነው በጨቆኝ ሰው/ሰውን በሚያሳዝን ሰው ላይ የሚያደርገው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ለሰይፍ ይሆናል

እዚህ ስፍራ "ለሰይፍ" የሚወክለው በጦርነት መሞትን ነው፡፡ "በጦርነት ይሞታሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 27:15-17

ከእርሱ ልጆች በህይወት የሚኖሩት

ይህ የኃጢአተኛውን ሰው ልጆች ያመለክታል፡፡ ይህ ይበልጥ ግልጽ ተደርጎ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ክፉ የሆኑት

አባቶቻቸው ከሞቱ በኋላ የሞኖሩት ልጆቻቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በመቅሰፍት ይቀበራሉ

እዚህ ስፍራ "ይቀበራሉ" የሚለው የሚወክለው ሞትን ነው፡፡ "በመቅሰፍት ይሞታሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

የእነርሱ መበለቶች…እነርሱ

"የእነርሱ" እና "እነርሱ" የሚሉት ቃላት የሚያመለክተው "ከእርሱ በኋላ የሚኖሩትን" ይኸውም የክፉ ሰውን ልጆች ነው፡፡

ብር እንደ አፈር መከመር

እዚህ ስፍራ "መከመር" የሚለው "ብዙ መሰብሰብ" ለሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ ኢዮብ ብር ማግኘት አፈር የማግኘት ያህል እንደሚቀላቸው ይናገራል፡፡ "የብር ቁልል ይሰበስባሉ" ወይም "አፈር መሰብሰብ የሚችሉትን ያህል በቀላሉ ብር ይሰበስባሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ልብስ እንደ ሸክላ ይከምራሉ

እዚህ ስፍራ "መከመር" የሚለው "ብዙ መሰብሰብ" ለሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ ኢዮብ ልብስ ማግኘት አፈር የማግኘት ያህል እንደሚቀላቸው ይናገራል፡፡ "የልብስ ቁልል ይሰበስባሉ" ወይም "አፈር መሰብሰብ የሚችሉትን ያህል በቀላሉ ልብስ ይሰበስባሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 27:18-19

ቤቱን እንደ ሸረሪት ይሰራል/ይገነባል

"ከሸረሪት" በኋላ "ድሯን ማድራት" የሚለው ሀረግ በግልጽ የሚታወቅ ነገር ነው፡፡ ይበልጥ ግልጽ ሊደረግ ይችላል፡፡ "ሸረሪት ድሯን እንደምታደራ ኃጢአተኛው ቤቱን ይሰራል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተተወ/የተዘለለ የሚለውን ይመልከቱ)

ቤቱን እንደ ሸረሪት ይሰራል

የሸረሪት ድር በቀላሉ ይበጣጠሳል፣ ደግሞም በቀላሉ ይጠፋል፡፡ "ሸረሪት ድሯን እንደምትሰራ ቤቱን ይገነባል" ወይም "የሸረሪት ድር በቀላሉ እንደሚበጣጠስ፣ ቤቱን እንደዚያው ይገነባል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ጎጆ

ጎጆ በጣም ጠንካራ ያልሆነ ጊዜያዊ ቤት ነው፡፡ "እንደ ጊዜያዊ ጎጆ/ድንኳን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በባለጸጋ አልጋ ይተኛል

"በመኝታው ሲጋደም ባለጸጋ ነው፡፡" ይህ የሚያመለክተው በምሽት በአልጋው ላይ መጋደሙን እና መተኛቱን ነው፡፡

ነገር ግን ይህንን ማድረጉን አይቀጥልም

"ነገር ግን በባለጸጋ አልጋ ላይ መተኛቱን አይቀጥልም" ወይም "በአልጋው ላይ በሚተኛበት ጊዜ ባለጸጋነቱ አይቀጥልም/ከመኝታው ሳይወርድ ባለጸጋነቱ ያበቃል"

ዐይኖቹን ሲከፍት

ዐይኖቹን ሲከፍት የሚለው የሚወክለው በጠዋት ሲነሳ የሚለውን ነው፡፡ "ከእንቅልፉ ሲነቃ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ያለውን ሁሉ አጥቶታል/ያለው ሁሉ ሄዷል

"ሀብቱ ሁሉ ጠፍቷል" ወይም "ሁሉም ነገር ከእርሱ ርቋል"

Job 27:20-21

ፍርሃት ውጦታል

እዚህ ስፍራ "እርሱን ውጦታል" የሚለው የሚወክለው በድንገት የሚደርስበትን ነው፡፡ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች "ጭንቀት/መሸበር" ለተከታዮቹ ሀሳቦች ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ 1) ሰዎች እንዲፈሩ የሚያደርጉ ነገሮች፡፡ "በድንገት በኃጢአተኛው ላይ የሚደርሱ ነገሮች" ወይም 2) ፍርሃት፡፡ "በድንገት ፍርሃት ዋጠው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

እንደ ውኆች

"ውኆች" የሚለው ቃል ጎርፍን ያመለክታል፡፡ ጎርፍ ሰዎች ሳይጠብቁት በድንገት ሊደርስ ይችላል፤ ደግሞም አደገኛ እና አስፈሪም ነው፡፡ "እንደ ጎርፍ" ወይም "በድንገት እንደሚሞላ ደራሽ ውሃ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አውሎ ነፋስ ይወስደዋል

"ሃይለኛ ነፋስ ጠርጎ ይወስደዋል"

ከስፍራው ይጠርገዋል

ኢዮብ ኃጢአተኛውን ሰው ከቤቱ ጠርጎ የሚወስደውን ነፋስ የገለጸው፣ ነፋስን እንደ ሰው በመግለጽ እና አቧራን ከቤት ከሚያስወግድ መጥረጊያ ጋር በማነጻጸር ነው፡፡ "ሴት ቆሻሻን በመጥረጊያ ጠርጋ እንደምታስወጣ ነፋስ ከስፍራው ይጠርገዋል" ወይም "ነፋስ በቀላሉ ከስፍራው ይጠርገዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ስፍራው

"ቤቱ"

Job 27:22-23

አጠቃላይ መረጃ፡

በኢዮብ 27፡ 22-23 ላይ ኢዮብ ስለ ነፋስ የሚናገረው ክፉዎችን እንደሚያጠቃ ሰው አድርጎ ነው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በኃጢአተኛው ላይ ይወድቅበታል

" በኃጢአተኛው ላይ ይወድቅበታል" የሚለው ሀረግ የሚወክለው ነፋሱ በኃጢአተኛው ላይ አደጋ እንደሚጥል ሰው ሆኖ በሃይል ይነፍስበታል ማለትን ነው፡፡ "አደጋ እንደሚጥል ሰው በእርሱ ላይ በሃይል ይነፍስበታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከእጁ አምልጦ ለመብረር ይሞክራል

እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚወክለው ነፋስ በክፉ ሰው ላይ ያለውን ሀይል ወይም አቅም ነው፡፡ "ከእርሱ ቁጥጥር ለማምለጥ ይሞክራል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ እና ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

በፌዝ እጆቹን ያጨበጭብበታል

አጆችን ማጨብጨብ በሌላ ሰው ላይ የማፌዝ መንገድ ነው፡፡ እዚህ ስፍራ ይህ የሚወክለው ነፋስ ከፍ ያለ ድምጽ ማሰማቱን/መስጠቱን ነው፡፡ "በእርሱ ላይ ለማፌዝ አንድ ሰው እጆቹን እንደሚያጨበጭብ ከፍ ያለ ድምጽ ያወጣል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት እና ሰውኛ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 28

Job 28:1-2

የማዕድን ስፍራ

ይህ ሰዎች ከመሬት የተለያዩ አለቶችን የሚያወጡበት ስፍራ ነው፡፡ አለቶች በውስጣቸው ብረት አላቸው፡፡

ማጣራት

ይህ በብረት ውስጥ የሚገኘውን አፈር ለማጣራት ብረትን የማቅለጥ ሂደት ነው

ብረት ከአፈር ውስጥ ይወጣል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ሰዎች ብረትን ከመሬት ያወጣሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

መዳብ ከማዕድን ድንጋይ ቀልጦ ይወጣል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ሰዎች መዳብን ከመሬት ያወጣሉ" ወይም "ሰዎች መዳብን ለማውጣት ድንጋይ ያቃጥላሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

መዳብ

ጠቃሚ የሆነ ቀይ ቡኒ ቀለም ያለው ብረት

ማቅለጥ

ይህ በአለቶች ውስጥ የሚገኘውን ብረት ለማግኘት ሲባል አለቶችን የማቃጠል ሂደት ነው

Job 28:3-4

ሰው ለጨለማ ዳርቻ ያበጅለታል

እዚህ ስፍራ "ለጨለማ ዳርቻ ማበጀት/ጨለማ ማስወገድ" የሚለው የሚወክለው በጨለማ ማብራትን ነው፡፡ ሰዎች ብርሃን ለማግኘት ፋኖስን ወይም ችቦን ይጠቀማሉ፡፡ "ሰው ወደ ጨለማ ስፍራ ብርሃን ይዞ ይሄዳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ሩቅ ወደሆነው ስፍራ

"ወደ ማዕድን ቁፋሮው ሩቅ ስፍራ"

ድብቅነት…ድቅድቅ ጨለማ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች በአንድነት አገልግሎት ላይ የዋሉት ማዕድን የሚገኝበት ስፍራ እጅግ ጨለማ መሆኑን ለመግለጽ ነው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

የጉድጓድ መግቢያ/አፍ

ወደ መሬት ወደ አለት ውስጥ የተቆፈረ ጠባብ ጥልቅ ጉድጓድ፡፡ ሰዎች ማዕድን ለማውጣት ወደ ጉድጓዱ ውስጠኛ ክፍል ይገባሉ፡፡

በማንም እግር ያልታወሱ ስፍራዎች

እግር የተገለጸው ማስታወስ እንደሚችል ሰው ተደርጎ ነው፡፡ "ሰዎች ያልሄዱባቸው ስፍራዎች" ወይም "ማንም ተራምዶባቸው የማያውቁ ስፍራዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ከሰዎች ርቆ ይቆያል

እንዴት እና የት እንደ ራቀበግልጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "በጉድጓዱ ውስጥ በገመድ ታስሮ ከሰዎች ርቆ ያቆያል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 28:5-6

ከመሬት እንጀራ ይወጣል

እዚህ ስፍራ "እንጀራ" የሚወክለው በአጠቃላይ ምግብን ነው፡፡ እንጀራ ከመሬት ይወጣል የሚለው እንጀራ ከመሬት ይበቅላል የሚል ዘይቤ ነው፡፡ "እንጀራ የሚወጣበት መሬት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

በእሳት እንደሆነ ነገር ከስር ተገልብጧል

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) አለቶችን ለመሰባበር ሰዎች ከምድር በታች እሳት አንድደዋል፡፡ "መአድን ቆፋሪዎች ባነደዱት እሳት ከምድር በታች ያለው ተንኮታኩቷል" ወይም 2) "ተገልብጧል" የሚለው ተለውጧል ለሚለው ዘይቤያዊ አነጋገር ነው፡፡ "ከስር በእሳት የጠፋ ያህል በከፍተኛ ደረጃ ተንኮታኩቷል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

እርሷ ተገልብጧለች.. የእርሷ አለቶች/ደንጋይ … የእርሷ አብዋራ/አፈር

"እርሷ" የሚለው የሚያመለክተው መሬትን ነው፡፡

ሰንፔር

በጥቂቱ ብቻ የሚገኝ ዋጋው የከበረ ሰማያዊ ቀለም ያለው ድንጋይ

Job 28:7-8

የትኛውም አዳኝ ወፍ ወደዚያ የሚወስደውን መንገድ አያውቅም… አሊያም የጭልፊት ዐይንም አላየውም

እነዚህ ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ "የትኛውም አዳኝ ወፍ ወይም ጭልፊት ወደ ማዕድን ስፍራ የሚወስደውን መንገድ አይቶት አያውቅም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አዳኝ ወፍ

"ሌሎች እንስሳትን የሚበላ ወፍ"

ጭልፊት

ይህ "አሞራ" ተብሎም ሊተረጎም ይችላል፡፡ እነዚህ ሁለቱም የሚያድኑ እና ሌሎች እንስሳት የሚመገቡ ወፎች ናቸው፡፡ ይህንን በባህላችሁ ውስጥ በሚገኝ አነስተኛ ወፍ ተክታችሁ መተረጎም ትችላላችሁ፡፡

ኩሩዎቹ እንስሳት በዚህ መንገድ አልሄዱም… አሊያም ሀይለኞቹ አንበሶች በዚያ አላለፉም

እነዚህ ሀረጎችም ደግሞ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ኩሩዎቹ እንስሳት

ይህ የሚያመለክተው በጣም ጠንካራ የሆኑ የዱር አራዊትን ነው

Job 28:9-11

በባልጩት/ጠንካራ አለቶች ላይ እጆቹን ያሳርፋል

ይህ የሚወክለው አለቶችን መሰባበርን ነው፡፡ "ጠንካራ አለት መቆፈር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ጠንካራ አለት

"ጠጣር አለት"

እርሱ ተራሮችን ከስራቸው ይገለብጣል

ተራሮችን እና ከስራቸው የሚገኘውን መሬት መቆፈር የሚለው አረምን ወይም ዛፎችን ከስራቸው መንቀል ለሚለው ዘይቤያዊ አገላለጽ ሲሆን ማዕድኖችን ከመሬት ቆፍሮ ማውጣትን አጋኖ ለመግለጽ የዋለ ነው፡፡ "እርሱ ስራቸውን ቆፍሮ በማውጣት ተራሮችን ከስራቸው ገለበጠ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት እንዲሁም ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

የእርሱ ዐይኖች

እዚህ ስፍራ "የእርሱ ዐይኖች" የሚለው የሚወክለው እርሱን ነው፡፡ "እርሱ ይመለከታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ጅረቶች እንዳይፈሱ/እንዳይወርዱ ያግድ ነበር

እዚህ ስፍራ " ጅረቶች እንዳይወርዱ" የሚለው ጅረቶችን ማገድ ወይም እንዳይፈሱ መከልከል ማለት ነው፡፡ "እርሱ ጅረቶች እንዳይወርዱ ያግዳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በዚያ የተደበቀው

ይህ የሚያመለክተው ሰዎች ከምድር በታች ወይም ከውሃ ስር በመሆናቸው ምክንያት ሊመለከቱ የማይችሉትን ነገር ነው፡፡

Job 28:12-14

አጠቃላይ መረጃ፡

በኢዮብ 28፡12-28 እውቀት እና ግንዛቤ ማግኘት በአንድ ስፍራ የሚገኙ እና ሰዎች የሚፈልጓቸው ውድ ሀብቶች እንደሆኑ ተደርጎ ተገልጽዋል፡፡ እውቀት እና ግንዛቤ ማግኘት የሚወክሉት ብልህ መሆንንና ነገሮችን በሚገባ መረዳትን መማርን ነው፡፡ በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ጥበብ ከወዴት ይገኛል? የመረዳትስ ስፍራው የት ነው?

እነዚህ ጥያቄዎች ተመሳሳይ ነገር ማለት ናቸው፤ የዋሉትም ጥበብን እና መረዳትን ማግኘት በጣም አስቸጋሪ መሆኑን ለማሳየት ነው፡፡ "ጥበብን እና መረዳትን ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚሉትን ይመልከቱ)

ጥበብ ከወዴት ይገኛል?የመረዳትስ ስፍራው የት ነው?

ብልህ መሆን እና ግንዛቤ ማግኘት የተገለጹት ጥበብን እና መረዳትን እንደ ማግኘት ተደርጎ ነው፡፡ "ሰዎች ብልህ የሚሆኑት እንዴት ነው? ሰዎች ነገሮችን በሚገባ መረዳት የሚችሉት እንዴት ነው?" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሰው ዋጋዋን አያውቅም

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ጥበብ የተገለጸችው ሰዎች ሊገዟት እንደሚችሉት ነገር ተደርጋ ነው፡፡ "ሰዎች የሚረባው ምን እንደሆነ አያውቁም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ ወይም 2) "ዋጋ" ተብሎ የተተረጎመው ቃል "ስፍራ" ማለት ነው፡፡ "ሰዎች የት እንደምትገኝ አያውቁም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በህያዋን ምድር አትገኝም

"እናም በህያዋን ምድር አትገኝም፡፡" የህያዋን ምድር" የሚለው የሚያመለክተው ሰዎች የሚኖሩበትን ይህንን ምድር ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እናም ማንም በዚህ ምድር ጥበብን ሊያገኝ አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ጥልቅ ውኆች… ‘በእኔ ውስጥ አትገኝም' ይላሉ፤ ባህር ‘በእኔ ውስጥ አትገኝም' ይላል፡፡

ጥልቅ ውኆች እና ባህር የቀረቡት መናገር እንደሚችል ሰው ተደርገው ነው፡፡ "ጥበብ ከምድር በታች ባለው በጥልቅ ውኆች ውስጥ አትገኝም፣ አሊያም በባህር ውስጥ አይደለችም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 28:15-17

በወርቅ አትገኝም

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ ይህ የሚያመለክተው ጥበብ ከወርቅ ይልቅ ጠቃሚ እንደሆነ ነው፡፡ "ሰዎች እውቀትን በወርቅ መግዛት አይችሉም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ብር ዋጋዋ ተደርጎ ሊመዘንላት አይችልም

ይህ የሚያመለክተው ጥበብ ከብር ይልቅ ጠቃሚነት እንዳላት ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ሰዎች ለእውቀት በቂየሆነ ብር መክፈል/መመዘን አይቻላቸውም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ዋጋዋ በሰንፔር… ሊመዘን/ሊለካ አይችልም

ይህ የሚያመለክተው ጥበብ ከኦፌር ወርቅ፣ ከከበረ መረግድና ሰንፔርና የበለጠ ዋጋ እንዳላት ነው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ኦፌር

ይህ የተጣራ ወርቅ የሚገኝበት ምድር ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

መረግድ የከበረ ድንጋይ

ጥቁር የከበረ ድንጋይ

ሰንፔር

ሰማያዊ የከበረ ድንጋይ

ወርቅ እና አብረቅራቂ መአድን/ብርሌ የእርሷን ያህል ዋጋ የላቸውም

ይህ የሚያመለክተው ጥበብ ከወርቅ እና ከከበረ ድንጋይ/አብረቅራቂ መአድን እጅግ እንደምትበልጥ ነው

የከበረ ድንጋይአብረቅራቂ መአድን/ብርሌ

ዋጋ ያለው የከበረ እንደ ብርጭቆ ንጹህ ቀለም ያለው ድንጋይ

በጠራ ወርቅ በተሰራ ጌጥም ቢሆን ልትለወጥ አትችልም

"እናም በጠራ ወርቅ በተሰራ ጌጥ አትለወጥም፡፡" ይህ የሚያመለክተው ጥበብ በጠራ ወርቅ ከተሰራ ጌጥ የሚበልጥ ዋጋ ያላት መሆኑን ነው፡፡

መለወጥ/መቀየር

"መነገድ"

Job 28:18-19

ዛጎል፣ ኢያስፔር እና አልማዝ ከእርሷ ጋር አይስተካከሉም

"እርሷን ከዛጎል እና ሰንፔር ጋር ማነጻጸር አይቻልም" ይህ የሚያመለክተው ጥበብ ከዛጎል እና ኢያስፔር እጅግ እንደምትበልጥ ነው፤ ስለዚህም ኢዮብ ስለነዚህ ነገሮች መናገር አላስፈለገውም፡፡ "ስለ ዛጎል ወይም ኢያስፔር መናገር አያስፈልገኝም" ወይም "ዛጎል፣ ኢያስፔር እና አልማዝ ከጥበብ ጋር ሲነጻጸሩ እርባና እንደሌለው ነገር ይቆጠራሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ዛጎል

ይህ ውብ የሆነ፣ ጠንካራ እና በውቅያኖስ ዳርቻ የሚገኝ ቁስ ነው፡፡

ኦፌር…ቀይ እንቁ…ቶጳዝዮን

እነዚህ የከበሩ ድንጋዮች/ማዕድናት ናቸው

የኩሽ ቶጳዝዮን አይስተካከሏትም

ይህሚያመለክተው ጥበብ ምርጥ ከተባለው ቶጳዝዮን እንደምትሻል ነው

ከንጹህ ወርቅ ጋርም ልትመዘን/ዋጋዋ ሊተመን አይችልም

"እናም ጥበብ በንጹህ ወርቅ ዋጋዋ ሊለካ አይችልም፡፡" ይህ ጥበብ ከንጹህ ወርቅ እጅግ እንደምትበልጥ ያሳያል፡፡

Job 28:20-22

ታዲያ ጥበብ ከወዴት ትገኛለች? የእውቀትስ ስፍራዋ የት ነው?

ኢዮብ እነዚህን ጥያቄዎች የሚጠቀመው ሰዎች ጥበብን እና እውቀትን ሰዎች ከየት እንደሚያገኙ ለመናገር ነው፡፡ "ጥበብ ከየት እንደምትገኝ እነግራችኋለሁ ደግሞም እውቀት ከወዴት እንደሆነች አስታውቃችኋል፡፡" ወይም "እንዴት ጥበበኛ መሆን እንደሚቻል እንደዚሁም ደግሞ እንዴት ነገሮችን መረዳት እንደሚቻል እነግራችኋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ታዲያ ጥበብ ከወዴት ትገኛለች

ጥበብ የተገለጸችው በአንድ ስፍራ እንደሆነችና ወደ ሰዎች እንደምትመጣ ተደርጎ ነው፡፡ የእርሷ መምጣት የሚወክለው ሰዎች ብልህ ሊሆኑ እንደሚችሉ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የመረዳት/እውቀት ስፍራዋ የት ነው

መረዳት/እውቀት የተገለጸችው በአንድ ስፍራ እንደምትገኝ ተደርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ጥብብ ከህያዋን ዐይኖች ሁሉ ተሰውራለች

ይህ ማለት ህያዋን ነገሮች ጥበብን ማየት አልቻሉም ማለት፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ማናቸውም ህያው ነገር ጥበብን ማየት/ማግኘት አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

ከሰማይ ወፎች ተደብቃ ተቀምጣለች

ይህ ማለት ወፎች ጥበብን ማየት አይችሉም ማለት ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "በሰማያት የሚበሩ ወፎች እንኳን ጥበብን ማየት አይችሉም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ጥፋት እና ሞት እንዲህ ይላሉ

እዚህ ስፍራ "ጥፋት" እና "ሞት" መናገር የሚችሉ ነገሮች ተደርገው ቀርበዋል፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 28:23-25

እግዚአብሔር የእርሷን መንገድ ያውቃል፤ እርሱ ስፍራዋን ያውቃል

ጥበብ የተገለጸችው በአንድ ስፍራ እንደምትገኝ ተደርጎ ነው፡፡ "እግዚአብሔር ጥበብ እንዴት እንደምትገኝ ያውቃል፡፡ እርሱ ጥበብ የት እንዳለች ያውቃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የምድራ ዳርቻ

"የምድር የመጨረሻው ሩቅ ስፍራ"

ውኆችን ይሰፍራል

ይህ የሚገልጸው እግዚአብሔር በእያንዳንዱ ስፍራ መገኘት ያለበትን የውሃ መጠን የወሰነ መሆኑን ነው፡፡ ይህ ለመወሰን የሚያመለክተው አማራጭ ትርጉም 1) በእያንዳንዱ ደመና ምን ያሀል ዝናብ መገኘት እንዳለበት ወይም 2) በእያንዳንዱ ባህር የሚገኘውን ውሃ መጠን፡፡ "በእያንዳንዱ ስፍራ የሚኖረውን ውሃ ወስኗል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 28:26-28

ለመብረቅ መንገድን

"እርሱ መብረቅ እንዴት መሰማት እንዳለበት ውስኗል" ወይም "እርሱ የመብረቅን መሄዳ ወስኗል"

እነሆ፣ እግዚአብሔርን መፍራት - ይህ ጥበብ ነው፡፡

"ፍርሃት" የሚለው ረቂቅ ስም "ፈራ" ወይም "አከበረ" በሚለው ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ጥበብ" የሚለው ረቂቅ ስም "ጠቢብ" በሚለው ቃል ሊገለጽ ይችላል፡፡ "አድምጡ፣ ጌታን ብትፈሩ ጥበበኛ ትሆናላችሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ከክፉ መራቅ ጥበብ/መረዳት ነው

እዚህ ስፍራ "ከክፉ መለየት" ክፉ ነገሮችን ለማድረግ አሻፈረኝ ማለት ነው፡፡ "መረዳት" የሚለው ረቂቅ ስም "ተረዳ" በሚለው ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ክፉ ማድረግን ባትፈቅድ፣ ከዚያ በኋላ ብዙ ነገሮችን ትገነዘባለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 29

Job 29:1-3

አወይ፣ ምነው ባለፉት ወራት እንደነበርኩት በሆንኩ ኖሮ

ኢዮብ ይህንን አጋኖ የተጠቀመው ምኞትን ለመግለጽ ነው፡፡ "በቀደሙት ወራት እንደነበርኩት ብሆን በወደድኩ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አጋኖ የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሱ ብርሃን በእኔ ራስ ላይ ሲበራ

የእግዚአብሔር ብርሃን በኢዮብ ላይ ማብራቱ የሚወክለው እግዚአብሔር ኢዮብን ያለውን መባረኩን ነው፡፡ "የእግዚአብሔር በረከት እንደ መብራት በላዬ በሚያበራበት ጊዜ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በእርሱ ብርሃን በጨለማ ውስጥ በማልፍበት ጊዜ

በጨለማ ውስጥ ማለፍ የሚወክለው አስቸጋሪ ሁኔታን ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 29:4-6

በመልካም ቀናቶቼ/በአጨዳ ቀናቶቼ

ኢዮብ ጠንካራ እና ወጣት ስለነበረበት ጊዜ የተናገረው እነዚያን ጊዜያት አዝመራ እንደሚታጨድበት ጊዜ አድርጎ ነው፡፡ "ወጣትና ጠንካራ በነበርኩበት ወቅት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔር ወዳጅነት በጎጆዬ በነበሩበት ወቅት

"ወዳጅነት" የሚለው ረቂቅ ስም "ወዳጅ" በሚለው ስም ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ጎጆ" የሚለው ቃል የኢዮብን ቤት ይወክላል፡፡ "እግዚአብሔር የእኔ ወዳጅ በነበረበት እና እኔን በሚጠብቅበት ጊዜ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች እና ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

መንገዴ በቅባት/ወተት እና የወተት ተዋጽኦ በተሸፈነበት ጊዜ

"መንገዴ በቅባት በተጥለቀለቀ ጊዜ" ኢዮብ ይህንን አጋኖ የተጠቀመው ብዙ ላሞች እንደመበሩት እና ላሞቹ ለእርሱ እና ለቤተሰቡ ከሚያስፈልገው ያለፈ ብዙ ቅባት ይሰጡት እንደነበረ ለመግለጽ ነው፡፡ "ላሞቼ እጅግ የበዛ ቅባት ይሰጡኝ በነበረ ጊዜ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት የሚለውን ይመልከቱ)

ደግሞም አለቱ የዘይት ፈሳሽ ይሰጠኝ ነበር

"ደግሞም አለቱ የዘይት ፈሳሽ ይሰጠኝ ነበር፡፡" ኢዮብ ይህንን አጋኖ የተጠቀመው ብዙ የወይራ ተክል እንደነበረው እና ብዙ የወይራ ዘይት ያመርት እንደነበር ለመግለጽ ነው፡፡ አለቱ አገልጋዮቹ ከወይራ ፍሬ ዘይት ይጨምቁበት የነበረበት ስፍራ ነው፡፡ "አገልጋዮቼ እጅግ ብዙ የወይራ ዘይት ይጨምቁ በነበረበት ጊዜ" ወይም "ዘይት እንደ ወንዝ ዘይት ከሚጨመቅበት አለት ይፈስ በነበረበት ጊዜ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 29:7-8

የከተማ አደባባይ

ይህ በመንደር ወይም በከተማ ውስጥ ሁለት ወይም ከዚያ የበለጡ መንገዶች የሚገናኙበት ስፍራ ነው፡፡

ለእኔ ተነስተው ይቆሙ ነበር

ይህ የአክብሮት ምልክት ነው፡፡ ይበልጥ ግልጽ ተደርጎ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ለእኔ በአክብሮት ተነስተው ይቆሙ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 29:9-10

ልዑላን እኔ ስመጣ ንግግራቸውን ያቋርጡ ነበር

ይህ የአክብሮት ምልክት ነበር፡፡ (ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

እጃቸውን በአፋቸው ላይ ይጭኑ ነበር

ይህን የሚያደርጉት እንደማይናገሩ ለማሳየት ነው፡፡ ይህ ለኢዮብ ያላቸውን አክብሮት የሚያሳዩበት ምልክት ነበር፡፡ (ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

የተከበሩ ሰዎች ድምጽ ጭጭ ይል ነበር

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የተከበሩ ሰዎች ጸጥ ይሉ ነበር" ወይም "የተከበሩ ሰዎች መናገራቸውን ያቆሙ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ምላሳቸው ከትናጋቸው ጋር ይጣበቅ ነበር

ይህ እነርሱ ለኢዮብ ካላቸው እጅግ ከፍ ያለ አክብሮት የተነሳ አንዳች የሚናገሩት ነገር እንዳልነበረ ያሳያል፡፡ "መናገር የማይችሉ ሆኖ ይሰማቸው ነበር" ወይም "አንዳች የሚሉት አልነበራቸውም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 29:11-13

ጆሯቸው እኔን ካደመጠ በኋላ … ዐይናቸው እኔን ካደመጠ በኋላ

ጆሮዎች የሚለው የሚወክለው እርሱን የሰሙትን ሰዎች ሲሆን፣ ዐይኖች የሚለው ደግሞ የሚወክለው እርሱን ያዩተን ሰዎች ነው፡፡ "የነገርኳቸውን ከሰሙ በኋላ… እኔን ከተመለከቱ በኋላ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ለእኔ ምስክርነት ይሰጡ፤ ደግሞም ያልኩትን ይቀበሉ ነበር

"የተናገርኩት ትክክል ነው በማለት ይመሰክሩ ነበር"

ድሃው ሲጮህ ካለበት ሁኔታ አወጣው ነበር

እዚህ ስፍራ "ድሃ የሆነው/ድሃው" የሚለው የሚያመለክተው ማንኛውንም ድሃ ሰው ነው፡፡ "ድሆች ሲጮሁ ደርሼ ካሉበት ችግር አወጣቸው ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የስማዊ ሀረግ ክፍል የሚለውን ይመልከቱ)

በሞት አፋፍ ላይ የደረሰው መርቆኛል

የአንድ ሰው ምርቃት/በረከት ወደ ሌላው መድረሱ የሚወክለው ያ ሰው ሌላውን መባረኩን ነው፡፡ "ሞት አፋፍ ላይ ደርሶ ነበረው ስረዳው ይባርከኝ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በሞት አፋፍ ላይ የደረሰው/ለመጥፋት የተቃረበው

ይህ የሚወክለው ሊሞት የተቃረበውን ማናቸውንም ሰው ነው፡፡ "ሊሞቱ የተቃረቡ/በሞት አፋፍ ላይ ያሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የስማዊ ሀረግ ክፍል የሚለውን ይመልከቱ)

የመበለቶች ልብ በሀሴት እንዲዘምር አድርጌያለሁ

እዚህ ስፍራ "የመበለቶች ልብ" የሚለው የሚወክለው ማንኛይቱንም መበለት ነው፡፡ "መበለቶች በደስታ እንዲዘምሩ ምክንያት ሆኛለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ እና የስማዊ ሀረግ ክፍል የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 29:14-16

ጽድቄን አበዛለሁ፤እንደልብስ ይሸፍነኛል

ብዙውን ጊዜ ሰዎች ጽድቅን እንደ ልብስ አድርገው ይገልጽዋታል፡፡ "ጽድቅ የሆነውን አደርግ ነበር፣ እርሷም ለእኔ እንደ ምለብሰው ልብስ ነበረች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ፍርዴ እንደ ልብስ እና እንደ ጥምጥም ነበረች

ብዙውን ጊዜ ሰዎች ጽድቅን እንደ ልብስ አድርገው ይገልጽዋታል፡፡ "ትክክል የሆነውን አደርግ ነበር፣ ፍትህ በእኔ ላይ እንደ ልብስ እና እንደ ጥምጥም ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤያዊ የሚለውን ይመልከቱ)

ጥምጥም

ወንዶች በራሳቸው ላይ የሚጠመጥሙት እና እንደ ኮፍያ የሚያደርጉት ረጅም ጨርቅ

ለዐይነ ስውራን ዐይን ነበርኩ

ይህ የሚወክለው ዐይነ ስውር የሆኑ ሰዎችን መርዳትን ነው፡፡ "ለዐይነ ስውራን ዐይን ነበርኩ" ወይም "ዐይነ ስውራንን እመራ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ለአንካሶች እግር ነበርኩ

ይህ አካል ጉዳተኞችን መርዳትን ያመለክታል፡፡ "ለአንካሶች እግር ነበርኩ" ወይም "አንካሶችን እደግፍ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ለችግረኞች አባት ነበርኩ

እዚህ ስፍራ "አባት ነበርኩ" የሚለው የሚወክለው ለሰዎች የሚያስፈልጋቸውን ማቅረብን ነው፡፡ "አባት ለልጆቹ የሚያስፈልጋቸውን እንደሚያቀርብ ለችግረኞች አቀርብላቸው ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 29:17-19

አጠቃላይ መረጃ፡

ከቁጥር/ስንኝ 18-20 ባለው ክፍል ኢዮብ በእርሱ ላይ መከራ ከመድረሱ በፊት ይናገራቸው ስለነበሩ ነገሮች ይገልጻል፡፡

የ… መንጋጋ እሰብር ነበር፣ …ምርኮኞችን ነጻ አወጣ ነበር

ኢዮብ ኃጢአተኞችን በጥርሳቸው ያደኑትን እንደሚነክሱ የዱር አራዊት ይገልጻቸዋል፡፡ "አንድ ሰው የዱር አውሬን መንጋጋ ሰብሮ ያደነውን ከጥርሶቹ መሃል እንደሚያስጥለው፣ እኔም ኃጢአተኞች ሰዎችን እንዳያሳድዱ እከልክላቸው ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በጎጆዬ ውስጥ እሞታለሁ

እዚህ ስፍራ "ጎጆ" የሚወክለው የኢዮብን ቤት እና ቤተሰብ ነው፡፡ ኢዮብ እርሱን እንደ ወፍ ልጆቹን ደግሞ እንደ ወፍ ጫጩቶች አድርጎ ይናገራል፡፡ "ከቤተሰቦቼ ጋር በቤቴ ውስጥ እሞታለሁ" ወይም "በቤቴ በሰላም እሞታለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እድሜዬን እንደ ምድር አሸዋ አበዛለሁ

በወንዝ ዳርቻ ማንም ሊቆጥረው የማይችለው አሸዋ አለ፡፡ ማንም ሊቆጥረው ከሚችለው በላይ እድሜ እኖራለሁ ማለቱ ረጅም እድሜ እንደሚኖር አጋኖ መናገሩ ነው፡፡ "በጣም ዘመን እኖራለሁ" ወይም "ብዙ አመታት እኖራለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት እንዲሁም ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

የእኔ ስር… የእና ቅርንጫፍ

ኢዮብ ስለ ጥንካሬው በሚገባ ውሃ እንዳገኘ ዛፍ አድርጎ ይናገር ነበር፡፡ በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 29:20-22

በውስጤ ያለው ክብር ሁሌም አዲስ ነው

" ክብር" የሚለው ረቂቅ ስም "ከበረ" በሚለው ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ እዚህ ስፍራ "አዲስ/ትኩስ" የሚለው የሚወክለው ያለማቋረጥ የሚሰጥን ክብር ነው፡፡ "ሰዎች ሁሌም/ሳያቋርጡ ክብር ይሰጡኝ ነበር" ወይም "ሰዎች ሁሌም ያከብሩኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

በእጄ ያለው ቀስት ሁሌም በእጄ ላይ አዲስ ነው

አዲስ ቀስት በጣም ጠንካራ ነው፡፡ የኢዮብ በእጁ የሚገኘው ቀስት ጥንካሬ የሚወክለው የእርሱን አካላዊ ብርታት ነው፡፡ "እኔ ሁልጊዜም እንደ አዲስ ቀስት ጠንካራ ነኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ንግግሬ እንደ ውሃ በላያቸው ይንጠባጠባል

እዚህ ስፍራ "እንደ ውሃ በላያቸው ይንጠባጠባል" የሚለው የሚወክለው እርሱን የሚሰሙ ሰዎች መታደሳቸውን ነው፡፡ "ንግግር" የሚለው ረቂቅ ስም "ተናገረ" ወይም "አለ" በሚለው ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ውሃ ሲፈስበት የሰዎች አካል እንደሚታደስ ንግግሬ ልባቸውን ደስ ያሰኝ ነበር" ወይም "እኔ እምናገራቸው ነገር በአካላቸው እንደሚፈስ ውሃ ያድሳቸው ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 29:23-24

ዝናብን እንደሚጠባበቅ ንግግሬን ይጠባበቁ ነበር

ሰዎች ኢዮብን በትግስት ይጠባበቁት ነበር፤ ደግሞም ከእርሱ መልካም ነገርን ለመስማት ይጠባበቁ ነበር፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከእኔ ቃላት ለመጠጣት አፋቸውን በሰፊው ይከፍታሉ

ይህ የሚወክለው ኢዮብ ከሚናገረው ተጠቃሚ ለመሆን በጉጉት መጠባበቅን ነው፡፡ "ከምናገረው ለመጠቀም እኔ እስከምናገር ድረስ በጉጉት ይጠባበቁ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የኋለኛውን ዝናብ እንደሚጠባበቁ

"ገበሬዎች የኋለኛውን ዝናብ በጉጉት እንደሚጠባበቁ"

የኋለኛው ዝናብ

ይህ ዝናብ የሌለበት/ደረቅ ወቅት ከመግባቱ አስቀድሞ የሚዘንበውን ብዙ መጠን ያለውን ዝናብ ያመለክታል፡፡

ፈገግ እልላቸው/እስቅላቸው ነበር

ፈገግ የሚልበት ምክንያት እነርሱን ለማበረታታት በመሆኑ፣ ይህ ይበልጥ ግልጽ ተደርጎ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እነርሱን ለማበረታታት ፈገግ እልላቸው ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የፊቴ ብርሃን

ይህ የሚወክለው በኢዮብ ገጽ ላይ የሚመለከቱትን ደግነት ነው፡፡ በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 29:25

መንገዳቸውን እመርጥላቸው ነበር

እዚህ ስፍራ "መንገዳቸውን እመርጥላቸው" የሚለው የሚገልጸው ምን ማድረግ እንዳለባቸው መወሰንን ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አለቃቸው ሆኜ እቀመጥ ነበር

እዚህ ስፍራ "መቀመጥ" የሚወክለው መግዛትን ወይም መምራትን ነው፡፡ አለቆች ከፍ ያለ ውስኔ የሚሰጡት ተቀምጠው ነው፡፡ "አለቃቸው ሆኜ እመራቸው ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

አለቃቸው ሆኜ እቀመጥ ነበር

ኢዮብ የእነርሱ አለቃ ነበር፡፡ "አለቃቸው ስለነበርኩ እመራቸው ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በሰራዊቱ መሃል እንደሚገኝ ንጉሥ እኖር ነበር

ኢዮብ ሰዎቹን እንዴት ይመራ እንደነበር፤ ራሳቸውን እንደ ሰራዊቱ፣ እርሱንም እንዴት እንደ ንጉሳቸው ያህል ቆጥረው ይታዘዙት እንደነበር ይናገራል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤያዊ የሚለውን ይመልከቱ)

ያዘኑትን አጽናና ነበር

ይህ ሀረግ ኢዮብ በእርግጥ ሰዎችን ያጽናና ነበር ማለት ነው፡፡ "ባዘኑ ጊዜ አጽናናቸው ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 30

Job 30:1-3

በእኔ ላይ ይሳለቃሉ

"መሳለቅ" የሚለው ረቂቅ ስም "ተሳለቁ" በሚለው ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "በእኔ ላይ ተሳለቁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

አባቶቻቸው መንጋዎቼን ከሚጠብቁ ውሾች ጋር እንዲቀመጠ/እንዲሰሩ እንኳን ያላፈቀድኩላቸው

ይህ የሚያመለክተው እነዚያን አባቶች ምን ያህል ይንቃቸው እንደነበረ ነው፡፡ መንጎቹን ከሚጠብቁ ከውሾቹ ጋር ለመሆን እንኳን የሚበቁ አልነበሩም፡፡ "እኔ የናቅኳቸው አባቶቻቸው፤ ከመንጎቼ ውሾቼ ጋር እንዲሆኑ ያልፈቀድኩላቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የመንጎቼ ውሾች

ውሾቹ ከመንጎቹ ጋር ያላቸው ግንኙነት ግልጽ ተደርጎ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "መንጎቼን የሚጠብቁ ውሾች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በእርግጥ፣ የአባቶቻቸው እጆች ጥንካሬ፣ እንዴት እኔን ሊያግዝ ይችላል… አልጠፋምን?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመበት በእነዚያ ሰዎች ጥንካሬ ላይ ለማፌዝ ነው፡፡ "የአባቶቻቸው ክንዶች ጥንካሬ ሊረዳኝ አልቻለም… ጠፍቷል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

የብስለት እድሜ ሃይላቸው የጠፋባቸው ሰዎች

የሃይላቸው መጥፋት ከእንግዲህ እየደከሙ እንጂ እየበረቱ እንደማይሄዱ የመሚገልጽ ዘይቤ ነው፡፡ "የብስለት እድሜ" የሚለው ማርጀታቸውን ያመለክታል፡፡ "ያረጁ እና ሀይላቸው የደከመ ሰዎች" ወይም "ያረጁ እና የደከሙ ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ ከድህነት እና ከረሀብ የተነሳ ከስተዋል

"እነርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሚያላግጡ/የሚቀልዱ ወጣቶችን አባቶች ነው፡፡

ከድህነት እና ከረሀብ የተነሳ ከስተዋል

"ረሃብ" የሚለው ረቂቅ ስም "ድሃ" በሚለው ቃል ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ረሃብ" የሚለው ረቂቅ ስም "መራብ" ወይም "ችጋር" በሚለው ቃል ሊገለጽ ይችላል፡፡ "በጣም ከሲታ የነበሩት ድሆች እና የተራቡ ስለነበሩ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

በደረቁ ምድር ላይ ያገኙትን ይቆረጣጥማሉ

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "ደረቅ ምድር" በደረቅ ምድር ላይ የሚበቅሉ ደረቅ ስሮች ለሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት ነው፡፡ "ከምድር ያገኙትን ደረቅ ስራስሮችን ይቆረጣጥማሉ" ወይም2) "ከደረቁ መሬት ላይ ያገኙትን ይቆረጣጥማሉ/ይበላሉ" የሚለው በደረቁ ምድር ያገኙትን ለመመገባቸው ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት ነው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 30:4-6

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ ስለሚሳለቁበት ሰዎች አባቶች መናገሩን ቀጥሏል በረሃብ ጊዜ ብቻ የሚበላ ጨው ጨው የሚል ተክል… የቁጥቋጦ ቅጠል… የክትክታ ዛፍ/ችፍርግ እነዚህ ሰዎች ሌላ የሚበላ ነገር ባጡ ጊዜ የሚበሏቸው ቅጠላቅጠሎች ናቸው፡፡

የክትክታ ስር ምግባቸው ነበር

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ሰዎች የክትክታ ቅጠል/ችፍርግ ይበሉ ነበር ወይም 2) ሰዎች የክትክታ ስራ ስሮችን በማንደድ ይሞቁ/ሙቀት ያገኙ ነበር

እንደ ሌባ… እየተከታተሉ ከሚጮሁባቸው ሰዎች ይሸሹ ነበር

"ይሸሹ ነበር" የሚለው ሀረግ "ለመሸሽ ይገደዱ ነበር" ማለት ነው፡፡ ይህ ሀረግ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ሰዎች እንደ ሌባ እያባረሩ ይጮሁባቸው ነበር… ደግሞም ለቀው እንዲሄዱ ያስገድዷቸው ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

አንድ ሰው ሌባን እንደሚያበርር እየጮሁ ያሳድዷቸው ነበር

"ሌባ የሆኑ ያህል ይጮሁባቸው ነበር"

Job 30:7-8

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ ስለሚሳለቁበት ሰዎች አባቶች መናገሩን ቀጥሏል

እንደ አህዮች ያናፉ ነበር

ኢዮብ በረሃብ ይጮሁ የነበሩ ሰዎችን ከፍ ያለ ድምጽ እንደሚያሰሙ የሜዳ አህዮች ይገልጻቸዋል፡፡ "ከረሃባቸው የተነሳ እንደ ሜዳ አህያ ይጮሁ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤያዊ የሚለውን ይመልከቱ)

በሳማ ስር በአንድነት ይሰባሰቡ ነበር

"ሳማ" ሹል እሾህ ያለው እጅብ ብሎ የሚበቅል ተክል ነው፡፡ ይህ የሚያመለክተው ቤት እንደሌላቸው ነው፡፡

የማይረቡ ሰዎች ልጆች ናቸው

እዚህ ስፍራ "የማርረቡ ሰዎች ልጆች" የሚለው የሚገልጸው የማይረባ/ጅል ባህሪይ እንዳላቸው ነው፡፡ "እንደ ጅሎች ነበሩ" ወይም "ሞኞች ነበሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በእርግጥ፣ ስም የለሽ ሰዎች ልጆች ነበሩ

"በእርግጥ" የሚለው ቃል ቀጥሎ የሚመጣውን ሀሳብ የሚያጠናክር ነው፡፡ እዚህ ስፍራ " የስም የለሽ ሰዎች ልጆች" የሚለው የሚገልጸው ስም እዚህ ግባ የሚባል ባህሪ እንዳሌላቸው ነው፡፡ "በእርግጥ፣ የሚረቡ ሰዎች አልነበሩም" ወይም "በእርግጥ፣ እርባና ቢስ ሰዎች ነበሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ስም የለሽ ሰዎች

እዚህ ስፍራ "ስም የለሽ" የሚለው የሚገልጸው አንዳች ክብር ወይም ከበሬታ የሌለው ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት እርባና ቢስ ነበሩ ማለት ነው፡፡ "እርባና ቢስ ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በአለንጋ እየተገረፉ ከምድሪቱ ይባረሩ ነበር

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) አለንጋ የሚለው እንደ ወንጀለኛ ይቀጡ እንደነበር ያመለክታል፡፡ "ሰዎች እንደ ወንጀለኞች ይመለከቷቸው እና ከአገራቸው በግድ ያስወጧቸው ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ ወይም 2) ሰዎች በአለንጋ እየገረፉ በግድ ያስወጧቸው ነበር፡፡ "ሰዎች ይገርፏቸው እና ምድሪቱን ለቀው እንዲወጡ ያስገድዷቸው ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ከምድሪቱ ይባረሩ ነበር

እዚህ ስፍራ "ምድሪቱ" የሚለው የሚያመለክተው ወደ በረሃ ከመሰደዳቸው አስቀድሞ የሚኖሩበትን ምድር ነው፡፡

Job 30:9-11

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ እንደገና ስለሚሳለቁበት ሰዎች መናገሩን ቀጥሏል ነገር ግን አሁን ለሚያንጓጥጥ ዘፈናቸው ሆኛለሁ "ዘፈን" የሚለው ረቂቅ ስም "ዘፈነ" በሚል ግስ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "በእኔ ላይ ለማንጓጠጥ ይዘፍናሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ለእነርሱ መተረቻ ሆኛለሁ

እዚህ ስፍራ "መተረቻ" የሚለው ሰዎች በጭከና ለማፌዛቸው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት ነው፡፡ "አሁን እነርሱ በጭካኔ የሚዘባበቱብኝ ሆኛለሁ" ወይም "ስለ እኔ በፌዝ ጭካኔ የተሞላበት ነገር ይናገራሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በፊቴ ላይ ምራቃቸውን ጢቅ ለማለት ወደኋላ አይሉም

ይህ በአዎንታዊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "በፊቴ ላይ አንኳን ይተፉብኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ምጸት የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ከእኔ ቀስቴን ሰብሮታል

የተሰበረ ቀስት ጥቅም የለውም፡፡ "ቀስቴን ሰብሮታል" የሚለው ሀረግ ኢዮብን አቅመቢስ ስለ ማድረግ ዘይቤያዊ አገላለጽ ነው፡፡ "እግዚአብሔር እራሴን እንዳልከላከል አቅሜን ከእኔ ወስዶታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በእኔ ላይ የሚያላግጡት

"በእኔ የሚቀልዱ"

በፊቴ ያለገደብ ክፉ ያደርጋሉ

ገደብ አንድ ሰው በነጻነት አንዳይንቀሳቀስ እና የሚፈልገውን እንዳያደርግ ያግዳል፡፡ እዚህ ስፍራ "መቆጠብ" የሚለው የሚገልጸው አንድ ነገር ከማድረግ መገታተትን፣ ሲሆን "ገደብን መስበር" የሚለው ደግሞ አንድ ነገር ከማድረግ አለመከልከልን ነው፡፡ በዚህ ሁኔታ ፌዘኞቹ በኢዮብ ላይ ክፉ ነገርን ከማድረግ አልተቆጠቡም፡፡ "ለእኔ ክፉ ከመሆን አልተገቱም" ወይም "በእኔ ላይ ማድረግ የሚፈልጉትን የጭካኔ ተግባር ሁሉ ያደርጋሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 30:12-13

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ እንደገና ስለሚሳለቁበት ሰዎች መናገሩን ቀጥሏል

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ ክፉ የሚያደርጉበትን ፌዘኞች በቡድን እንደሆኑ እና እንደ ሰራዊት በአንድላይ ሆነው እንደሚያጠቁት አድርጎ ይገልጻል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በቀኜ ጀሌዎች ተነሱብኝ

"በቀኜ ጀሌዎች ተነሱብኝ" የሚለው በሚከተሉት መንገዶች ሊተረጎም ይችላል 1) በኢዮብ ቀኝ እጅ ላይ መነሳት በእርሱ ጥንካሬ ላይ መነሳትን ሊወክል ይችላል፡፡ "ወሮበሎች አቅሜን መቱት/አጠቁኝ" ወይም በኢዮብ ቀኝ እጅ ላይ መነሳት የእርሱን ክብር ማጥቃትን ይወክላል፡፡ "ጀሌው ክብሬን አጠፋ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

አሳደዱኝ

"እንድሸሽ አስገደዱኝ"

የዐፈር ድልድል አዘጋጁብኝ

ሰራዊት አንዲትን ከተማ በቅጥሯ ላይ ተንጠላጥሎ ወጥቶ ለማጥቃት በቅጥሩ ስር አፈር ይከምራል፡፡ ኢዮብ በእርሱ ላይ የሚያፌዙት እንዲህ ያለ ነገር እንዳደረጉ ይናገራል፡፡ "ሰራዊት አንዲትን ከተማ ለማጥቃት እንደሚዘጋጅ እነርሱ እኔን ለማጥቃት ተዘጋጁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

መንገዴን ደመሰሱ

ይህ የሚገልጸው ኢዮብ ከጥቃታቸው እንዳያመልጥ ማድረጋቸውን ነው፡፡ "ከእነርሱ እንዳላመልጥ ከለከሉኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ጥፋትን ወደ እኔ አመጡ

እዚህ ስፍራ "ክፋትን ማምጣት" የሚለው የሚገልጸው ጥፋት እንደሆን ማድረግን ነው፡፡ "በእኔ ላይ ጥፋት እንዲደርስ ተጣጣሩ" ወይም "እኔን ለማጥፋት ሞከሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ማንም ሊያግዳቸው/ወደ ኋላ ሊመልሳቸው የማይችላቸው ሰዎች

እዚህ ስፍራ "ወደ ኋላ መመለስ/ማገድ" የሚለው የሚገልጸው አንድ ነገር እንዳያደርጉ እነርሱን መከልከልን/ማስቆምን ነው፡፡ "እኔን ከማጥቃት ማንም የማያስቆማቸው ሰዎች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 30:14-15

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ እንደገና ስለሚሳለቁበት ሰዎች መናገሩን ቀጥሏል

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ ክፉ የሚያደርጉበትን ፌዘኞች በቡድን እንደሆኑ እና እንደ ሰራዊት በአንድላይ ሆነው እንደሚያጠቁት አድርጎ ይገልጻል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በአንዲት ከተማ ትልቅ የቅጥር ፍራሽ/ብስ አልፎ እንደሚገባ ሰራዊት በእኔ ላይ መጡብኝ

ይህ የሚገልጸው ኢዮብን በሃይል ማጥቃታቸውን ነው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በላዬ በሃይል መጡብኝ

ይህ የሚገልጸው ታላቅ የውቅያኖስ ማዕበል በእርሱ ላይ እንደመጣበት ብዙ ሆነው በአንድነት መጥተው እንዳጠቁት ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ፍርሃት በላዬ ወረደ/መጣ

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ኢዮብ እጅግ ፈራ ወይም 2) ኢዮብ ኢንዲፈራ የሚያደርጉ ነገሮች እየሆኑ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በነፋስ ተጠርጎ እንሚወሰድ ክብሬ ተወሰደ

ኢዮብ ነፋስ በድንገት ጠርጎ እንደወሰደው ነገር ክብሩ ከእርሱ መወሰዱን ይናገራል፡፡ "ማንም እኔን አያከብርም" ወይም "እኔ አሁን ማንም የማያከብረው ሰው ሆኛለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ብልጽግናዬ/ሀብቴ እንደ ደመና አለፈ

ኢዮብ የሃብቱን መጥፋት በነፋስ እንደተጠረገ ደመና ይገልጻል፡፡ እዚህ ስፍራ "ሀብት/ብልጽግና" ደህንነትን ወይም ጥበቃን ሊያመለክት ይችላል፡፡ "ከእንግዲህ አንዳች የለኝም" ወይም "ከእንግዲህ ሰላም አይደለሁም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 30:16-17

አሁን ህይወቴ ከውስጤ ይፈሳል

ኢዮብ ህይወቱ ፈሳሽ እንደሆነ እና አካሉን ህይወቱን እንደያዘ እቃ/መያዣ አድርጎ ይገልጻል፡፡ መሞቻው እንደደረሰ ይሰማዋል፡፡ "አሁን እሞትኩ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ብዙ የመከራ ቀናት ይዘውኛል

ኢዮብ የማያቆርጥ መከራውን የሚገልጸው የመከራ ቀናቱ እርሱን አንቀው እንደያዙት አድርጎ ነው፡፡ "ለብዙ ቀናት ተሰቃየሁ፣ መከራው ግን አላበቃም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በውስጤ አጥንቴ ይወጋኛል

ኢዮብ በአጥንቱ ውስጥ የሚሰማውን ስቃይ የሚገልጸው አጥንቶቱ እየተበሱ እንደሚገኙ አድርጎ ነው፡፡ "አጥንቶቼን እጅግ ይቆረጥመኛል" ወይም "በአጥንቶቼ ውስጥ እጅግ አስጨናቂ ስቃይ ይሰማኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ካለ ማቋረጥ ይቆረጥመኛል

ኢዮብ የማያቋርጥ ስቃዩን ህይወት እንዳለው እና እንደሚነክሰው ደግሞም ለማቆም እምቢ እንዳለ ነገር አድርጎ ይገልጸዋል፡፡ "የሚያሰቃየን መከራ አያቋርጥም" ወይም "በማያቋርጥ ስቃይ ውስጥ ነኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 30:18-19

የእግዚአብሔር ታለቅ ሀይል በልብሴ አንቆ ይዞኛል

ኢዮብ፣ የእግዚአብሔር ሀይል አንዳች ነገር እያደረገ እንደሆነ እና እግዚአብሔር ሀይሉን እየተጠቀመ እንደሆነ ይናገራል፡፡ እዚህ ስፍራ "የእግዚአብሔር…ሀይል" የሚለው የቆመው/የሚገልጸው "እግዚአብሔርን" ነው፡፡ "እግዚአብሔር በታላቅ ሀይሉ በልብሴ አንቆ ይዞኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

መከራው እንደ ሸሚዜ ኮሌታ ዙሪያዬን አንቆታል

የእግዚአብሔር ሀይል በኢዮብ ዙሪያ መጠምጠሙ ዘይቤያዊ አነጋገር ነው፡፡ ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) የኢዮብን መከራ ይወክላል/ይገልጻል፡፡ "ስቃዬ እግዚአብሔር በሸሚዜ ኮሌታ አንቆ የያዘኝን ያህል ነው" ወይም
2) ይህ የሚገልጸው እግዚአብሔር በኢዮብ ላይ ብዙ መከራ እንዳደረሰበት ነው፡፡ "የሚሰማኝ እግዚአብሔር በታላቁ ሀይሉ በልብሴ አንቆ የያዘኝን ያህል ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ጭቃ ውስጥ ወረወረኝ

ኢዮብ እግዚአብሔር አዋርዶኛል እያለ ነው፡፡ "ያደረገኝ ልክ ጭቃ ውስጥ የመጣልን ያህል ነው" ወይም "እርሱ፣ ጭቃ ውስጥ የተጣለን ሰው ያህል አዋርዶኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ አዋራ እና አመድ ሆንኩ

ይህ የሚገልጸው ኢዮብ የተሰማውን እርባና ቢስነት ነው፡፡ "እንደ አብዋራ እና አመድ ጥቅም የማይሰጥ ሰው ሆንኩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 30:20-21

ጨካኝ

ይህ ቃል ደግነት የሌለው ማለት ነው

በክንድህ ጥንካሬ አሳደድከኝ

"እጅ" የሚለው ቃል የእግዚአብሔርን ሀይል ይገልጻል/ይወክላል፡፡ "በሀይልህ አሳደድከኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 30:22-23

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ ለእግዚአብሔር መናገሩን ቀጥሏል፡፡

በነፋስ አነሳኸኝ… በማዕበል አናወጥከኝ

እነዚህ አገላለጾች የሚወክሉት እግዚአብሔር ኢዮብ ጸንቶ እንዲያልፍበት ያደረገውን እጅግ ከፍ ያለ መከራ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እንዲያንገላታኝ አደረግህ

"ነፋሱ/ማዕበሉ እንዲገፋኝ አደረግህ"

ወደ ሞት ታደርሰኛለህ/ትገድለኛለህ

እዚህ ስፍራ "ወደ ሞት ታደርሰኛለህ" የሚለው የሚወክለው ኢዮብ እንዲሞት ማድረጉን ነው፡፡ "እንድሞት ታደርጋለህ/ትገድለኛለህ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ህያው ለሆነው ሁሉ የተዘጋጀለት ቤት

ኢዮብ ይህ እግዚአብሔር ለህያዋን ነገሮች ሁሉ ይሄዱበት ዘንድ ያዘጋጀው ቤት ይህ እንደሆነ ስለ ሙታን ዓለም እየተናገረ ነው፡፡ "በህይወት የኖረ ሁሉ የሚሄድበት የሙታን ዓለም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ህይወት ያለው ነገር ሁሉ

ይህ፣ አንድ ቀን የሚሞት ነገር ግን አሁን በህይወት ያለ ነገር ሁሉ፡፡

Job 30:24-26

አያያዥ ሃሳብ፡

ኢዮብ ለእግዚአብሔር መናገሩን ቀጥሏል፡፡

ሲወድቅ እጆቹን አንስቶ የማይለምን አለን? በችግር የወደቀ ሰው ለእርዳታ አይጣራምን?

ኢዮብ እነዚህን ጥያቄዎች የሚያነሳው/የሚጠቀመው ለእርዳታ ወደ እግዚአብሔር መጮሁ ተገቢ መሆኑን ለማረጋገጥ ነው፡፡ "ማንም ሰው በችግር ላይ በሚወድቅበት ጊዜ ለእርዳታ ወደ እግዚአብሔር እጆቹን ያነሳል፡፡ በችግር ውስጥ የሚገኝ ሁሉ እርዳታ ለማግኘት ይጣራል፡፡" ወይም "እኔ ወድቄያለሁ፣ ስለዚህ እርዳታውን ስለምነው እግዚአብሔር እንደተሳሳትኩ ሊመለከተኝ አይገባውም፡፡ እኔ በመከራ ውስጥ እገኛለሁ፣ ስለዚህም በእርግጥ እርዳታ ለማግኘት እጣራለሁ!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

በችግር …እኔ አላለቅስምን? ሰው… አያዝንምን?

ኢዮብ እነዚህን ጥያቄዎች የተጠቀመው ለሌሎች ጥሩ ነገሮችን ያደርግ እንደነበረ ለመናገር ነው፡፡ "እኔ እንደማለቅስ አንተ ታውቃለህ… የተቸገረ እና ያዘነ…ሰው!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

መልካምን ነገር ተስፋ ሳደርግ፣ ክፉ ደረሰብኝ

መልካምን መጠባበቅ የሚገልጸው መልካም ነገሮችን ተስፋ ማድረግን ነው፣ ደግሞም የክፉ መድረስ/መምጣት የሚወክለው ክፉ ነገሮች እንደሚሆኑ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ብርሃንን ተጠባበቅኩ… ጨለማ መጣብኝ/ሆነ

እዚህ ስፍራ "ብርሃን" የሚወክለው የእግዚአብሔርን በረከት እና ሞገስ ሲሆን "ጨለማ" ደግሞ የሚወክለው ችግርን እና መከራን ነው፡፡ "የእግዚአብሔርን ብርሃን በረከት ተጠባበቅሁ፣ ነገር ግን በምትኩ የጨለማ መከራ ደረሰብኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 30:27-29

ልቤ ተጨነቀ እረፍት አላገኘም

ኢዮብ ልቡ ሰው እንደሆነ አድርጎ ይገልጻል፡፡ "በልቤ ታወክሁ/ተጨነቅሁ፣ ደግሞም መከራው ማብቂያ የለውም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የመከራ ቀን መጣብኝ

የመከራ ቀን በኢዮብ ላይ መምጣቱ የሚወክለው ኢዮብ ለብዙ ቀናት በመከራ ውስጥ መቆየቱን ነው፡፡ "ለአያሌ ቀናት በመከራ ውስጥ ኖርኩ" ወይም "በየቀኑ መከራ ወረደብኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ኖርኩ/ቆየሁ

እዚህ ስፍራ "ኖርኩ/ቆየሁ" የሚለቀው የሚገልጸው በህይወት መቆየቱን ነው፡፡ "ኖርኩ" ወይም "አለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ፀሐይ ሳይመለከት፣ በጨለማ ውስጥ እንደሚኖር ሰው

እዚህ ስፍራ "በጨለማ ውስጥ መኖር" የሚለው አገላለጽ እጅግ ማዘንን የሚገልጽ ዘይቤያዊ አነጋገር ነው፡፡ "ነገር ግን ፀሐይን ሳይመለከት" የሚለው ሀረግ "በጨለማ ውስጥ መኖር" የሚለውን ፀሐይ ባለመውጣቷ ምከንያት ጨለማው አለመፈጠሩን የሚያብራራ ዘይቤ ነው፡፡ "እጅግ እንዳዘነ ሰው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የቀበሮዎች ወንድም፣ የሰጎን ወዳጅ

የእነዚህ እንስሳት ወንድም መሆን እንደ እነርሱ አይነት መሆን ለሚለው ዘይቤያዊ አነጋገር ነው፡፡ "በበረሃ እንደሚጮሁ ቀበሮዎች እና ሰጎኖች ሆንኩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 30:30-31

አጥንቶቼ በሙቀት ተቃጠሉ

እዚህ ስፍራ "አጥንቶች" የሚያመለክተው በትኩሳት የሚሰቃየውን መላ አካልን ነው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

በገናዬ ወደ ሀዘን እንጉርጉሮ ተለወጠ

እዚህ ስፍራ "በገናዬ" የሚለው የሚወክለው ኢዮብን ራሱን ነው፣ እንደዚሁም ደግሞ የሀዘን እንጉርጉሮ ብቻ መዘመር መፈለጉን ይወክላል፡፡ "በበገናዬ የሀዘን እንጉርጉሮ ብቻ እጫወታለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ዋሽንቴ ለሙሾ ማውረጃ ሆነ

እዚህ ስፍራ "ዋሽንቴ" የሚለው የሚወክለው ኢዮብን ራሱን ነው፣ እንደዚሁም ደግሞ የሀዘን እንጉርጉሮ ብቻ መዘመር መፈለጉን ይወክላል፡፡ "በዋሽንቴ የሀዘን እንጉርጉሮ ብቻ እጫወታለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ዋይታ/ለቅሶ

ዋይታ ከፍ ካለ ሀዘን ወይም ስቃይ የተነሳ ድምጽን በጣም ከፍ አድርጎ ማልቀስ ነው

Job 31

Job 31:1-2

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

ከዐይኖቼ ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ

ኢዮብ ዐይኖቹ ሰው የሆኑ ይመስል ስለሚመለከተው ነገር ከዐይኖቹ ጋር ቃል መግባቱን ይናገራል፡፡ "ስለምመለከተው ነገር ከዐይኖቼ ጋር ጽኑ ቃል ገባሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ሰውኛ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ከዐይኖቼ ጋር ቃል ኪዳን ገባሁ

ኢዮብ ምን ቃል ኪዳን እንደገባ ግልጽ ተደርጎ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ድንግሊቱን በአምንዝራ አይን እንዳልመለከት የጸና ኪዳን ገባሁ" ወይም "ወደ አንዲት ድንግል በአመንዝራነት ላለመመልከት ቃል ገባሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ታዲያ እንዴት ወደ አንዲት ድንግል በአመንዝራነት ፍላጎት እመለከታለሁ?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የሚጠቀምበት ቃልኪዳኑን በምንም ምክንያት እንደማያፈርስ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "ስለዚህ በእርግጥ ወደ አንዲት ድንግል በአመንዝራነት ዐይን አልመለከትም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ከላይ ከእግዘአብሔር ዘንድ ድርሻዬ፣ በከፍታ ካለው ሁሉን ቻይ ከሆነው ርስቴ ምንድን ነው?

ኢዮብ እግዚአብሔር ለሰዎች ባህሪ ያለውን ምላሽ የሚገልጸው እግዚአብሔር ለሰዎች የሚሰጠው ርስት ክፍል አድርጎ ነው፡፡ "በሰማይ የሚኖር አምላክ ለእኔ የሚመልሰው እንዴት ነው? በላይ የሚኖረው ሁሉን ቻይ አምላክ ምን ይፈጽማል? በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ከላይ ከእግዘአብሔር ዘንድ ድርሻዬ፣ በከፍታ ካለው ሁሉን ቻይ ከሆነው ርስቴ ምንድን ነው?

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች፤ ኢዮብ እነዚህን ጥያቄዎች የተጠቀመባቸው ተከታዬቹን ነጥቦች ለማጉላት ነው 1) እግዚአብሔር መጥፎ ባህሪ ያለውን አይባርከውም፡፡ "ወደ አንዲት ሴት በአመንዝራነት ዐይን ብመለከት፣ በላይ በሰማይ የሚኖር ሁሉን ቻይ አምላክ አይባርከኝም፡፡" ወይም 2) እግዚአብሔር መጥፎ ባህርይን ይቀጣል፡፡ "ወደ ሴት በአመንዝራነት ብመለከት፣ በሰማይ የሚኖር ሁሉን ቻይ አምላክ በእርግጥ ይቀጣኛል፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 31:3-4

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

እግዚአብሔር መንገዴን አይመለከትምን ደግሞስ እርምጃዬን አይቆጥርምን?

እዚህ ስፍራ "መንገዶቼ" እና "እርምጃዎቼ" የሚሉት ለኢዮብ ባህርይ መግለጫነት የቀረቡ ዘይቤዎች ናቸው፡፡ እዚህ ስፍራ "መንገዶቼን ተመልከት" እና "እርምጃዎቼን ሁሉ ቁጠር" የሚሉት ኢዮብ የሚያደርገውን ሁሉ እግዚአብሔር እንደሚያው ለመግለጽ የቀረቡ ዘይቤዎች ናቸው፡፡ ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመበት እግዚአብሔር እርሱ ያደረገውን ሁሉ እንደሚያውቅ ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ "በእርግጥ እግዚአብሔር ይመለከተኛል፣ ደግሞም ያደረግሁትን ነገር በሙሉ ያውቃል፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚሉትን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር መንገዶቼን አይመለከትምን ደግሞስ እርምጃዎቼን ሁሉ አይቆጥርምን?

ኢዮብ ምናልባትም እግዚአብሔር የእርሱን ጻድቅነት ማወቅ እንደሚገባው እና መቅሰፍት እና ጥፋት ለእርሱ እንደማይገባው እያመላከተ ሊሆን ይችላል፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 31:5-6

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

እንዲህ አድርጌ ቢሆን

በኢዮብ 31፡ 5-40 ውስጥ የእግዚአብሔር ቅጣት እንደሚይገባው የተለያዩ ሁኔታዎችን ይገልጻል፡፡ ይልቁንም፣ ጥፋት እንደሌለበት እና ንጹህ እንደሆነ ያውቃል፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

በሀሰት መንገድ ተመላልሼ እንደሆነ፣ እግሮቼ ወደ ማታለል ፈጥነው እንደሆነ

እዚህ ስፍራ "መመላለስ" እና "መፍጠን" የሚሉት ኢዮብ እንዴት እንደኖረ የሚገልጹ ዘይቤዎች ናቸው፡፡ "አንዳች ሀሰት የሆነ ነገር አድርጌያለሁን ወይስ ይሁን ብዬ የፈጸምኩት ማታለል አለን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በትክክለኛ ሚዛን ልመዘን

ሰዎች ነገሮችን ለመለካት እና ዋጋቸውን ለመወሰን ሚዛን ይጠቀማሉ፡፡ ይህ ምስል በንጹህነት መበየንን ይወክላል፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "በንጹህነት ልመዘን" ወይም "እግዚአብሔር እንደ ንጽህናዬ ይፍረድብኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 31:7-8

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ የእግዚአብሔር ቅጣት እንደማይገባው ሁኔታዎችን መግለጹን ቀጥሏል፣ ይልቁንም፣ ጥፋት እንደሌለበት እና ንጹህ እንደሆነ ያውቃል፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

እርምጃዎቼ ከመንገድ ፈቀቅ ብለው ቢሆን

እዚህ ስፍራ "እርምጃዎቼ" የሚለው የኢዮብን ባህርይ የሚገልጽ ዘይቤ ሲሆን "ከመንገድ ፈቀቅ ብለው ቢሆን" የሚለው ከትክክለኛ አኗኗር መውጣትን የሚያሳይ ዘይቤ ነው፡፡ "ከጽድቅ ህይወት ዘወር ብዬ ቢሆን" ወይም "ትክክለኛ የሆነውን ማድረግ አቁሜ ቢሆን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ልቤ ዐይኖቼን ተከትሎ ሄዶ ቢሆን

እዚህ ስፍራ "ልቤ" እና "ዐይኖቼ" የሚሉት ኢዮብ ለሚፈልጋቸው እና ለሚያያቸው ነገሮች ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ናቸው፡፡ ልብ ዐይንን ተከትሎ መሄድ የሚለው የተመለከተውን ለማድረግ መፈለግን የሚገልጽ ዘይቤ ነው፡፡ ይህ ኢዮብ የተመለከተውን በኃጢአት የተሞሉ ነገሮች ያመለክታል፡፡ "ከተመለከትኳቸው ክፉ ነገሮች አንዱን ለማድረግ ፈልጌ ቢሆን ኖሮ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

በእጄ ላይ አንዳች በደል ተገኝቶ ቢሆን

ይህ ጥፋተኝነትን ለማመልከት የሚውል ዘይቤ ነው፡፡ "በአንዳች በደል ውስጥ ብገኝ ኖሮ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እንዲህ ቢሆን፣ እኔ የዘራሁትን ሌላው ይብላው፣ ደግሞም የተከልኩት ከስሩ ይነቀል

ኢዮብ በእርግጥ በደል ፈጽሞ ቢሆን እነዚህ ክፉ ነገሮች ይድረሱብኝ እያለ ነው፡፡ በደል ፈጽሞ ቢሆን ከባድ የሆነውን የመዝራት ተግባር በእርሻው ላይ ያከናውናል ነገር ግን ከዚያ አንዳች መቅመስ አይችልም፡፡

የተከልኩት ከስሩ ተነቅሎ ይጥፋ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ሌላ ሰው መጥቶ ከእርሻዬ አዝመራዬን ይውሰድ፡፡ በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 31:9-10

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ የእግዚአብሔር ቅጣት እንደማይገባው ሁኔታዎችን መግለጹን ቀጥሏል፣ ይልቁንም፣ ጥፋት እንደሌለበት እና ንጹህ እንደሆነ ያውቃል፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ልቤ በሴት ተታሎ ቢሆን

እዚህ ስፍራ "ልቤ" የሚለው የሚወክለው ኢዮብን ነው፡፡ "ተታሎ" የሚለው ቃል "ማማለልን/የዐይን ዐምሮትን" የሚገልጽ ሃሳብ ነው፡፡ "ሴት" የሚለው ቃል "የሌላ ሰው ሚስት የሆነችን ሴት" ይገልጻል፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "የሌላ ሰው ሚስት ብትስበኝ" ወይም "የሌላ ሰውን ሚስት ብመኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

በወዳጄ በር አድብቼ ብጠባበቅ

በወዳጁ በር ለምን አድብቶ እንደሚጠባበቅ በግልጽ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ከሚስቱ ጋር ለመተኛት በወዳጄ በር አድብቼ ብጠባበቅ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ ቢሆን የእኔ ሚስት ለሌላው ወፍጮ ትፍጭ

ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ኢዮብ ሚስቴ ከሌላ ሰው ጋር ትተኛ የሚለውን በዩፊምዝም/ በማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት/ እየተናገረ ነው፡፡ 2) ይህ ማለት ሚስቱ ባሪያ ሆና ለሌላ ሰው ታገለግላለች፡፡ (ዩፊምዝም/ የማያስደስት ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 31:11-12

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ የእግዚአብሔር ቅጣት እንደማይገባው ሁኔታዎችን መግለጹን ቀጥሏል፣ ይልቁንም፣ ጥፋት እንደሌለበት እና ንጹህ እንደሆነ ያውቃል፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ ክፉ ወንጀል በሆነብኝ ነበር

"ይህ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የኢዮብ ከሌላ ሴት ጋር የመተኛትን ክፉ በደል ነው፡፡

ይህ በዳኞች ቅጣት የሚያስጥል ወንጀል ይሆናል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ይህ ዳኞች በእኔ ላይ ቅጣት ቢጥሉ/ቢፈጽሙ ትክክለኛ ናቸው የሚያሰኝ ወንጀል ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ እሳት ያለውን ሁሉ ይፍጀው፣ አዝመራዬንም ከስሩ ጭምር ያቃጥለው

ኢዮብ ከሌላ ሰው ሚስት ጋር መተኛት የሚያስከትለውን ጥፋት እሳት ሁሉንም ነገር ከማጥፋቱ ጋር ያነጻጽረዋል፡፡ "ይህ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ከሌላ ሰው ሚስት ጋር መተኛትን ነው፡፡ "ማመንዘር ሁሉንም ነገር ከጫፍ ጫፍ እንደሚያጠፋ እና አዝመራን ሁሉ እንደሚያቃጥል እሳት ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከዳር እዳር ይፍጅ/ያቃጥል

እነዚህ ቃላት ምናልባት "ለቀሪው ዘመኔ አንዳች ሳያስቀር ሁሉንም ነገር ያጥፋ" ለሚለው ሀሳብ ዘይቤያዊ አገላለጽ ሊሆን ይችላል፡፡ ምናልባትም ደግሞ ይህንን ቃል በቃል መተረጎም ያስፈልጋል፡፡ ተከታዩን ይመልከቱ ([[፡en: ta: vol1: translate: figs:-metaphor]])

አዝመራዬን ከስሩ ያቃጥል

እዚህ ስፍራ "ይህ" የሚለው ቃል ከሌላ ሰው ጋር የመተኛትን ድርጊት ያመለክታል፡፡ ይህ ድርጊት ኢዮብ ነገሩን አድርጎት ቢሆን ሊቀበለው ስለሚገባው ቅጣት በዘይቤ የቀረበ ነው፡፡ አዝመራውን የሚያቃጥል እሳት የደከመበትን ሁሉ ማጣት ለሚለው ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ/ ነው፡፡ "እኔን የሚቀጡ የደከምኩበትን ሁሉ ይውሰዱት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ተከታዩን ይመልከቱ ([[፡en: ta: vol2: translate: figs:-metonomy]]) እና([[፡en: ta: vol2: translate: figs:-synecdoche]])

Job 31:13-15

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ የእግዚአብሔር ቅጣት እንደማይገባው ሁኔታዎችን መግለጹን ቀጥሏል፣ ይልቁንም፣ ጥፋት እንደሌለበት እና ንጹህ እንደሆነ ያውቃል፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ኢዮብ እነዚህን ጥያቄዎች የሚያነሳው እግዚአብሔር በእርሱ ላይ እንዲፈርድ የሚያደርግ በደል ሰርቶ ራሱን ንጹህ

አድርጎ እንደማያቀርብ በትኩረት ለመግለጽ ነው፡፡ "እንዲህ ቢሆን ኖሮ እግዚአብሔር ሊፈርድብኝ ሲመጣ ራሴን ለመከላከል የማቀርበው አንዳች ነገር አይኖርም ነበር፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

በማህጸን ያበጀኝ እነርሱንስ አላበጀምን? ሁላችንንም በማህጸን የሰራን እርሱ አይደለምን?

ኢዮብ እነዚህን ጥያቄዎች የሚያነሳው ከእርሱም አገልጋዮቹ እንደማይለይ በትኩረት ለመግለጽ ነው፡፡ አገልጋዮቹን ከራሱ ዝቅ አድርጎ ቢመለከት እግዚአብሔር እንደሚቆጣ ይናገራል፡፡ "በማህጸን የሰራኝ እርሱ፣ አነርሱንም ፈጥሯል፡፡ እርሱ ሁላችንንም በማህጸን ሰርቶናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 31:16-18

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ የእግዚአብሔር ቅጣት እንደማይገባው ሁኔታዎችን መግለጹን ቀጥሏል፣ ይልቁንም፣ ጥፋት እንደሌለበት እና ንጹህ እንደሆነ ያውቃል፡፡ ሀሳቡን በቁጥር 16 እና 17 ላይ አይጨርስም፡፡ ይልቁንም በቁጥር 18 ላይ እነዚህ ለምን ጥፋተኛ እንዳልሆነ ያብራራል፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ለድሆች የሚያስፈልጋቸውን ከልክዬ ከሆነ

"ድሆች የሚፈልጉትን እንዳያገኙ ከልክዬ ከሆነ"

የመበለቲቱ ዐይኖች በለቅሶ እንዲፈዙ አድርጌ ከሆነ

እዚህ ስፍራ "እየፈዘዙ እንዲሄዱ/እንዲፈዙ" የሚለው የሚያመለክተው መበለት ብዙ በማንባት ዐይኖቿ ሊፈዙ መቻላቸውን ነው፡፡ "አንዲት መበለት በታላቅ ሀዘን እንድታለቅስ ምክንያት ሆኜ ቢሆን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ቁራሼን

"ምግቤን"

ምክንያቱም ከልጅነቴ አንስቶ አባት ለሌላቸው እንደ አባት ሆኜ አሳድጌያለሁ

እዚህ ስፍራ "ወላጅ የሌላቸው" የሚለው የሚያመለክተው በአጠቃላይ ወላጆቻቸው ሞቱባቸውን ነው፡፡ ኢዮብ ወላጅ የሌላቸውን እንዴት ይረዳ እንደነበር ይናገራል፡፡ "ምክንያቱም ገና ወጣት ሳለሁ እንኳን ወላጅ የሌላቸውን እንደ አባት ሆኜ እንከባከባቸው ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የስማዊ ሀረግ ክፍል የሚለውን ይመልከቱ)

በወጣትነቴ ምክንያት

"ከእነዚህ ነገሮች ውስጥ አንዱንም አልፈጸምኩም" የሚለው ሀረግ ትርጉም ከአውዱ/አገባቡ ግልጽ ነው፡፡ "ነገር ግን ከእነዚህ ነገሮች ውስጥ አንዱንም አልፈጸምኩም፣ ምክንያቱም ከወጣትነቴ አንስቶ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተተወ/የተዘለለ የሚለውን ይመልከቱ)

ከእናቴ ማህጸን አንስቶ መበለቲቱን ደግፌያለሁ

ኢዮብ መበለቶችን በእውነት እንዴት እንደ ደገፈ ይናገራል፡፡ "ከእናቴ ማህጸን አንስቶ" የሚለው ይህንን በህይወት ዘመኑ ሁሉ ማድረጉን በማጋነን ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ "ዘመኔን በሙሉ አባት የሌላቸውን ልጆች እናቶች ደግፌያለሁ" ወይም "ዘመኔን በሙሉ መበለቶችን ደግፌያለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 31:19-21

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ የእግዚአብሔር ቅጣት እንደማይገባው ሁኔታዎችን መግለጹን ቀጥሏል፣ ይልቁንም፣ ጥፋት እንደሌለበት እና ንጹህ እንደሆነ ያውቃል፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ልቡ ባርኮኝ ካልሆነ

"ልቡ/የእርሱ ልብ" የሚለው ሀረግ የሚወክለው ልብስ የሚፈልገውን የተራቆተ ድሃ ነው፡፡ "እርሱ አመስግኞኝ/ባርኮኝ ካልሆነ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ከበጎቼ ፀጉር ከተሸለተው ለብሶ ሞቆት ካልሆነ

እዚህ ስፍራ "የበጎቼ ፀጉር" የሚለው የሚገልጸው ከኢዮብ በጎች ፀጉር የተሰራን ብርድ ልብስ ወይም ልብስ ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ከበጎቼ ሱፍ የተሰራው ልብስ ሳያሞቀው ቀርቶ ቢሆን" ወይም "ከበጎቼ ሲፍ የተሰራ ልብስ ሳልሰጠው ቀርቼ ቢሆን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

አባት በሌላቸው ላይ እጆቼን አንስቼ ቢሆን

በአንድ ሰው ላይ እጅን ማንሳት ማለት ያንን ሰው መጉዳትን ይገልጻል፡፡ "አባት የሌላቸውን አግባብ የሌለው ሁኔታ አድርሼባቸው ቢሆን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ድጋፌን በከተማ መግቢያ አይቻለሁ

እዚህ ስፍራ "ማየት" የሚለው "ማወቅ፣" ለሚለው ዘይቤ ሲሆን "ድጋፍ" የሚለው "ማረጋገጫ" ለሚለው ዘይቤ ነው፡፡ "የከተማ መግቢያ/በር" የሚለው ደግሞ በከተማዋ በር ለሚቀመጡ መሪዎች ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ/ ነው፡፡ "በከተማዋ በር የሚቀመጡ መሪዎች ስለ እኔ እንደሚመሰክሩ አውቃለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

በከተማይቱ በር

ይህ የከተማይቱ ታላላቅ ሰዎች ውሳኔ ለመስጠት የሚቀመጡበት ስፍራ ነው

በእኔ ላይ ክሳችሁን አቅርቡ

ይህ ሀረግ በመጀመሪያው ጽሁፉ በቀረበበት ቋንቋ ወይም በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ውስጥ የለም፡፡ እዚህ የተጨመረው በኢዮብ ረዘም ያለ ንግግር ውስጥ ያለውን ሀሳብ ላለማጉደል ነው፡፡

Job 31:22-23

አጠቃላይ መረጃ፡

እንዲህ ከሆነ ትከሻዬ ከመጋጠሚያው ይነቀል፣ ክንዴም ደግሞ ከመታጠፊያው ይሰበር ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እንዲህ ከሆነ አንድ ሰው ትከሻዬን ከመጋጠሚያው ይንቀለው ደግሞም ክንዴን ከመታጠፊያው ይስበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሱን ግርማ … ፈርቻለሁና

ኢዮብ ከቁጥር 7 አንስቶ እስከ 21 ድረስ ከተናገረው ውስጥ በአንዱም እንዳልበደለ የተናገረበት ምክንያት ይህ/የእርሱን ግርማ/ መፍራቱ ነው

Job 31:24-25

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ የእግዚአብሔር ቅጣት እንደማይገባው ሁኔታዎችን መግለጹን ቀጥሏል፣ ይልቁንም፣ ጥፋት እንደሌለበት እና ንጹህ እንደሆነ ያውቃል፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ወርቅን ተስፋ አድርጌ ቢሆን

"ተስፋ" የሚለው ረቂቅ ስም "ታመነ" ወይም "ተስፋ አደረገ" በሚለው ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "በወርቅ ታምኜ ቢሆን" ወይም "የብዙ ወርቅ ባለቤት መሆን ይጠብቀኛል ብዬ ተስፋዬን ጥዬበት ቢሆን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ምርጥ የሆነውን ወርቅ ‘የታመንኩት በአንተ ነው' ብዬው ቢሆን

ይህ ስንኝ/ቁጥር ከላይኛው ቁጥር ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እጄ ብዙ ሀብት ነበረው

እዚህ ስፍራ "እጄ" የሚለው የሚገልጸው የኢዮብን ነገሮችን የማከናወን አቅም ነው፡፡ "በችሎታዬ ብዙ ሀብት አከማችቻለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እንዲህ ከሆነ በእኔ ላይ ክስ አቅርቡ

ይህ ሀረግ በመጀመሪያው ጽሁፉ በቀረበበት ቋንቋ ወይም በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ውስጥ የለም፡፡ እዚህ የተጨመረው በኢዮብ ረዘም ያለ ንግግር ውስጥ ያለውን ሀሳብ ላለማጉደል ነው፡፡

Job 31:26-28

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ የእግዚአብሔር ቅጣት እንደማይገባው ሁኔታዎችን መግለጹን ቀጥሏል፣ ይልቁንም፣ ጥፋት እንደሌለበት እና ንጹህ እንደሆነ ያውቃል፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

የጨረቃ አካሄድ

እዚህ ስፍራ "አካሄድ" የሚወክለው ቀስ ብሎ መንቀሳቀስን ነው፡፡ "ጨረቃ ሰማይን እያቋረጠች ስትንቀሳቀስ"

ጨረቃ በድምቀቷ ስትራመድ

"ድምቀት" የሚለው ረቂቅ ስም "ብሩህ" ወይም "በብሩህነት" በሚሉ ቃላት ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ብሩኋ ጨረቃ ሰማይን እያቋረጠች ስትንቀሳቀስ" ወይም "ጨረቃ ብሩህ ሆና በሰማይ ስትንቀሳቀስ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ልቤ በስውር ተስቦ ቢሆን

እዚህ ስፍራ "ልቤ" የሚለው የሚወክለው ኢዮብን ነው፡፡ ይህ ሀረግ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "በድብቅ ወደ እነርሱ ተስቤ ቢሆን" ወይም "በድብቅ እነርሱን ለማምለክ ፈልጌ ቢሆን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

በዚህም ምክንያት አፌ እጄን ስሞ ቢሆን

እዚህ ስፍራ "አፌ" የሚለው የሚወክለው ኢዮብን ነው፡፡ ይህ የፍቅር እና የተመስጦ ምልክት ነው፡፡ "ስለዚህም እጄን ስሜ ቢሆን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትምዕርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱን ለማምለክ

"ፀሐይን እና ጨረቃን ለማምለክ"

በዳኞች መቀጣት

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የትኛዎቹ ዳኞች እኔን ቢቀጡኝ ትክክለኛ ይሆናሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

በሰማይ ያለውን አምላክ ክጄ ቢሆን

"በላይ ላለው እግዚአብሔር አምላክ ታማኝ ሳልሆን ቀርቼ ቢሆን"

Job 31:29-30

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ የእግዚአብሔር ቅጣት እንደማይገባው ሁኔታዎችን መግለጹን ቀጥሏል፣ ይልቁንም፣ ጥፋት እንደሌለበት እና ንጹህ እንደሆነ ያውቃል፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

እኔን የሚጠሉ ሁሉ በሚጠፉበት ጊዜ

"ጥፋት" የሚለው ረቂቅ ስም "ጠፋ" በሚለው ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "እኔን የሚጠላ ማንም ቢሆን በሚጠፋበት ጊዜ" ወይም "እኔን በሚጠላ ማንም ሰው ክፉ ነገር በሚደርስበት ጊዜ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱን ጥፋት በሚውጠው ጊዜ

"ጥፋት ሲደርስበት"

እንዲህ ከሆነ/በዚይን ጊዜ በእኔ ላይ ክስ አቅርቡ

ይህ ሀረግ በመጀመሪያው ጽሁፉ በቀረበበት ቋንቋ ወይም በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ውስጥ የለም፡፡ እዚህ የተጨመረው በኢዮብ ረዘም ያለ ንግግር ውስጥ ያለውን ሀሳብ ላለማጉደል ነው፡፡

በእርግጥ፣ አፌ እንኳን ኃጢአት እንዲናገር አልፈቀድኩም

እዚህ ስፍራ "አፌ/አንደበቴ" የሚለው የሚወክለው የኢዮብን ንግግር ነው፡፡ "በእውነት ራሴን ለኃጢአት አሳልፌ አልሰጠሁም" ወይም "በእውነት፣ ኃጢአት አልሰራሁም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሱ ህይወት እንዲረገም በመጠየቅ

እዚህ ስፍራ "የእርሱ ህይወት እንዲረገም በመጠየቅ" የሚለው የሚገልጸው አንድ ሰው እንዲሞት መራገምን ነው፡፡ "ይሞት ዘንድ እርሱን በመርገም" ወይም "ህይወቱን በመርገም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 31:31-32

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ የእግዚአብሔር ቅጣት እንደማይገባው ሁኔታዎችን መግለጹን ቀጥሏል፣ ይልቁንም፣ ጥፋት እንደሌለበት እና ንጹህ እንደሆነ ያውቃል፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

የጎጆዬ/የቤቴ ሰዎች

ጎጆው የሚወክለው የኢዮብን ቤት ነው፡፡ የጎጆው ሰዎች የሚያጠቃልለው የቤተሰቡን አባላት እና አገልጋዮቹን ነው፡፡ እነዚህ ሁሉ ኢዮብን በሚገባ ያውቁታል፡፡ "የቤቴ ሰዎች" ወይም "የቤተሰቤ አባላት እና አገልጋዮቼ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ማን ከኢዮብ ገበታ ያልጠገበን ሰው ማግኘት ይችላል?

የኢዮብ ሰዎች ይህንን ጥያቄ ኢዮብ ለጋስ ሰው እንደሆነ በትኩረት ለመግለጽ ሊያነሱ ይችላሉ፡፡ "ሁሉም ከኢዮብ ገበታ በልቶ ጠግቧል!" ወይም "እኛ የምናውቀው ሁሉ የፈለገውን ያህል ከኢዮብ ምግብ ተመግቧል!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ባዕድ እንኳን በከተማ አደባባይ አይረሳም ነበር

ኢዮብ እንግዶችን እንዴት ይንከባከብ እንደነበር ተገልጽዋል፡፡ እዚህ ስፍራ "በከተማ አደባባይ መቀመጥ" የሚለው የሚገልጸው በከተማ አደባባይ ምሽቱን ማደርን ነው፡፡ "እንግዶች ፈጽሞውኑ በከተማይቱ አደባባይ በሜዳ ላይ አያድሩም ነበር" ወይም "እንግዶች/ባዕዳን ውጭ አያድሩም ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ሁሌም በሮቼን ለመንገደኞች ክፍት አደርግ ነበር

እዚህ ስፍራ "ለመንገደኞች በሬን እከፍት ነበር" የሚለው የሚወክለው ወደ ቤቱ መንገደኞችን መቀበሉን ነው፡፡ "ሁሌም መንገደኞችን በቤቴ እቀበል ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እናም ነገሩ ይህ ባይሆን፣ በዚያን ጊዜ በእኔ ላይ ክስ አቅርቡ

ይህ ሀረግ በመጀመሪያው ጽሁፉ በቀረበበት ቋንቋ ወይም በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ውስጥ የለም፡፡ እዚህ የተጨመረው በኢዮብ ረዘም ያለ ንግግር ውስጥ ያለውን ሀሳብ ላለማጉደል ነው፡፡

Job 31:33-34

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ የእግዚአብሔር ቅጣት እንደማይገባው ሁኔታዎችን መግለጹን ቀጥሏል፣ ይልቁንም፣ ጥፋት እንደሌለበት እና ንጹህ እንደሆነ ያውቃል፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ኃጢአቴን… ደብቄ/ሰውሬ ቢሆን

እዚህ ስፍራ "ኃጢአቴን ሰውሬ ቢሆን" የሚለው የሚወክለው እርሱ ኃጢአት መስራቱን ሰዎች እንዳያውቁበት ለመደበቅ ሞክሮ ያውቅ እንደሆነ ነው፡፡ "ኃጢአቴን… ሰዎች እንዳያውቁ ለመደበቅ ሞክሬ እንደሆነ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ኃጢአቴን በካቦርቴ ውስጥ በመሰወር

ይህ የሚወክለው እርሱ በደለኛ መሆኑን ሰዎች እንዳያውቁ ለመደበቅ መሞከርን ነው፡፡ "የበደሎቼን ማስረጃዎች በካቦርቴ ውስጥ በመሸሸግ" ወይም "በካቦርቱ ውስጥ የበደሉን ማስረጃዎች እንደሚሸሽግ ሰው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ብዙ ህዝብ በመፍራት፣ ከቤተሰብ የሚመጣን ንቀት በመፍራት

ኃጢአቱን ለመደበቅ ምክንያት ሊሆን የሚችለው ይህ ነው፡፡ እነዚህ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ትኩረት የሚሰጡት አንድ ሰው ኃጢአቱን የሚሸሽገው ሰዎች ስለ እርሱ የሚኖራቸውን አስተሳሰብ በመፍራት ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በዚያን ጊዜ በእኔ ላይ ክስ አቅርቡ

ይህ ሀረግ በመጀመሪያው ጽሁፉ በቀረበበት ቋንቋ ወይም በሌሎች የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ውስጥ የለም፡፡ እዚህ የተጨመረው በኢዮብ ረዘም ያለ ንግግር ውስጥ ያለውን ሀሳብ ላለማጉደል ነው፡፡

Job 31:35-37

አወይ፣ ምነው የሚሰማኝ ባገኘሁ!

ይህ አጋኖ የኢዮብን ፍላጎት/የሚመኘውን ይገልጻል፡፡ "የሚሰማኝ ባገኝ በመደድሁ" ወይም "የሚሰማን ሰው ባገኝ እወዳለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ አጋኖዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ፊርማዬ እነሆ

እዚህ ስፍራ "ፊርማዬ" የሚለው የሚገልጸው፣ ኢዮብ የተናገረው ነገር ሁሉ እውነት መሆኑን ቃል መግባቱን ነው፡፡ ስለ ደረሰበት ነገር ህጋዊ ሰነድ እንደጻፈ አድርጎ ይናገራል፡፡ "የተናገርኩት እውነት መሆኑን በእርግጥ ቃል እገባለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሁሉን ቻይ የሆነው እርሱ ይመልስልኝ!

እዚህ ላይ ምላሽ የሚለው የሚያመለክተው ምናልባት ኢዮብ ምን ስህተት እንደፈጸመ የሚከሰስበትን የሚነግረውን መፈለጉን ይሆናል፡፡ "ሁሉን ቻይ የሆነው እርሱ የሰራሁትን በደል ይንገረኝ" ወይም "ሁሉን ቻይ የሆነው የሰራሁት በደል ምን እንደሆነ ቢነግረኝ እወዳለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ተቃዋሚዎቼ በእኔ ላይ የጻፉትን የክስ ማስረጃ ባውቅ በወደድኩ!

ይህ የኢዮብን ፍላጎት ይገልጻል፡፡ ኢዮብ አንድ ሰው እርሱን ኃጢአተኛ አድርጎ ለመክሰሱ ማስረጃ አድርጎ የሚያቀርበው የደረሰበትን ችግር ነው፡፡ "የትኛውም ተቃዋሚ የሚያቀርብብኝ ክስ ቢኖር በወደድኩ" ወይም "ምነው ተቃዋሚዬ የሚያቀርብብኝን ክስ ማንበብ በቻልኩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ተቃዋሚዬ/ባለጋራዬ

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ይህ እግዚአብሔርን ሊያመለክት ይችላል ወይም 2) ሌላ አካልን ሊያመለክት ይችላል

በእርግጥ ክሱን በግልጽ በትክሻዬ እሸከመዋለሁ፤ እንደ ዘውድ በራሴ ላይ እጭነዋለሁ

ይህ የሚወክለው ክሱን ማንም ሊያነበው በሚችለው ስፍራ ማስቀመጥን/ማድረግን ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ልበ ሙሉ ልዑል ወደ እርሱ ዘንድ እሄዳለሁ

ይህ ማለት ኢዮብ ኃጠአት ባለመስራት አንዳች ፍራቻ ወደ እግዚአብሔር እንደሚቀርብ ይናገራል፡፡ ኢዮብ ይህን ማድረግ እንደሚችል የሚናገረው ጥፋተኛ ስላልሆነ ነው፡፡ "በድፍረት ወደ እርሱ እቀርባለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 31:38-40

አጠቃላይ መረጃ፡

ኢዮብ የእግዚአብሔር ቅጣት እንደማይገባው ሁኔታዎችን መግለጹን ያጠቃልላል፣ ይልቁንም፣ ጥፋት እንደሌለበት እና ንጹህ እንደሆነ ያውቃል፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

ምድሬ በእኔ ላይ ቢያለቅስብኝ፣ እርሻዩ በአንድነት ቢያለቅስ

ኢዮብ ጥፋተኛ ስላለመሆኑ የሚናገረው ምድሩ ሰው እንደሆነ እና እርሻውን በመበደሉ ምክንያት በእርሱ ላይ እንደሚያለቅስበት አድርጎ ነው፡፡ "እርሻዬን በሚመለከት አንዳች ስህተት ሰርቼ ቢሆን" ወይም "እርሻዬን/ መሬት ከሌላ ሰው ሰርቄ ቢሆን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ህይወታቸው እንዲያልፍ

ይህ ሞትን ያመለክታል፡፡ "እንዲሞት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በገብስ ፈንታ አረም

"ይሁን" እና "ይብቀል" የሚሉት ከቀደመው ሀረግ ይታወቃሉ፡፡ "በገብስ ፈንታ አረም ይብቀል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተተወ/የተዘለለ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 32

Job 32:1-2

እርሱ በራሱ ዐይኖች ፊት ጻድቅ ነበር

ዐይኖች የሚመክሉት ማየትን ስሆን፣ ማየት የሚወክለው ሃሳብን ወይም ፍርድን ነው፡፡ "ራሱን ጻድቅ አድርጎ ቆጥሯል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡(ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከዚያም የራም ቤተሰብ የሆነው የቡዛዊው የባሮክ ልጅ የኤሊሁ ቁጣ ነደደ፤ ቁጣው የነደደው በኢዮብ ላይ ነበር

ይህ የሚያነጻጽረው የኤሊሁን ቁጣ አንድ ሰው እሳት ከመለኮሱ ጋር ነው፡፡ እንደዚሁም፣ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ከዚያም የራም ቤተሰብ የሆነው የቡዛዊው የባሮክ ልጅ የኤሊሁ ቁጣ በኢዮብ ላይ እጅግ ነደደ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

ኤሊሁ… ባሮክ…ራም

እነዚህ የወንድ ስሞች ናቸው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ቡዛዊ

ይህ የህዝብ የወል/የቡድን ስም ነው፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ሳይለው ራሱን ጻድቅ አድረጓል

ይህ ማለት፣ ራሱን ንጹህ አድርጎ፤ እርሱን በመቅጣቱ እግዚአብሔር ጥፋተኛ እንደሆነ አምኗል፡፡ "ራሱን አጽድቆ እርሱን ስለቀጣው እግዚአብሔርን ጥፋተኛ ነው ብሏል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 32:3-5

የኤሊሁ ቁጣ የነደደው በሶስቱ ወዳጆቹም ላይ ጭምር ነበር

ይህ የኤሊሁን ቁጣ እሳትን ከመለኮስ ጋር ያነጻጽራል፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እንደዚሁም ደግሞ ኤሊሁ በሶስቱ ወዳጆቹ ላይ እጅግ ተቆጣ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

እነሆ/አሁን

ይህ ቃል በዚህ ስፍራ የዋለው በዋናው ታሪክ ላይ ማረፊያ ለማበጀት ነው፡፡ ይህ ስለ ኤሊሁ የመረጃ ዳራ/የቀደመ ማስረጃ ይሰጣል፡፡ (የመረጃ ዳራ/የቀደመ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በእነዚህ ሶስት ሰዎች አፍ አንዳች መልስ አልተገኘም

ይህ ማለት ሰዎቹ ከኢዮብ ጋር መነጋገራቸውን ጨርሰው/አብቅተው ነበር፡፡ ይህ፣ መልስ በሰዎቹ አፍ ላይ የሚገኝ ነገር ቢሆን ኖሮ ምናልባት መልስ ያገኙ እንደ ነበር ይገልጻል፡፡ "እነዚህ ሶስት ሰዎች ሌላ የሚናገሩት ነገር የላቸውም" ወይም "እነዚህ ሶስት ሰዎች ለኢዮብ የሚሰጡት ሌላ ምንም ተጨማሪ መልስ የላቸውም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ቁጣው ነድዶ ነበር

ይህ የኤሊሁን ቁጣ እሳትን ከመለኮስ ጋር ያነጻጽራል፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "በጣም ተቆጣ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 32:6-7

እናንተ አዛውንቶች ናችሁ/በጣም ሽማግሌዎች ናችሁ

እዚህ ስፍራ "እናንተ" የሚለው ብዙ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተውም ኢዮብን እና ሶስቱን ወዳጆቹን ነው፡፡ (አንተ የሚለውን ተውላጠ ስም መልኮች ይመለከቱ)

የቀናት እርዝመት መናገር መቻል አለበት፣ የአመታት ብዛት እውቀትን መስጠት አለበት

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ኤሊሁ ትኩረት የሰጠው ከወጣቶች ይልቅ አዛውንቶች ጥበብ የቀሰሙ በመሆናቸው የሚያውቁትን አስቀድሞ መናገር እንደሚገባቸው ነው፡፡ "ብዙ ዘመናትን የኖረ እርሱ መናገር አለበት፤ አዛውንት የሆነው እርሱ ጥበብን ማስተማር ይገባዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 32:8-10

አጠቃላይ መረጃ፡

ኤሊሁ ለኢዮብ እና ለእርሱ ወዳጆች መናገሩን ቀጥሏል

ሁሉን ቻይ የሆነው እስትንፋስ፤ በሰው ውስጥ መንፈስ አለ

ሁለቱ ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አቸላቸው፡፡ ኤሊሁ የሰው ጥበብ ከእግዚአብሔር እንደሚመጣ ትኩረት ይሰጣል፡፡ "በሰው ውስጥ መንፈስ አለ፣ ይህም፣ ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ እስትንፋስ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሁሉን ቻይ የሆነው አምላክ እስትንፋስ

እዚህ መንፈስ የሚለው የተወከለው በ"እስትንፋስ" ነው፡፡ "ሁሉን ቻይ የሆነው የእርሱ መንፈስ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 32:11-12

እነሆ

ኤሊሁ እዚህ ስፍራ ይህንን ቃል የተጠቀመው የሰዎቹን ትኩረት ቀጥሎ ወደሚናገረው ነገር ለመሳብ ነው፡፡ "አድምጡኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ቃላችሁን አደመጥኩ

"የተናገራችሁትን ስሰማ ቆየሁ፡፡" "እናንተ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የኢዮብን ወዳጆች ነው፡፡ (አንተ የሚለውን ተውላጠ ስም መልኮች ይመልከቱ)

ለእርሱ ቃላት ማን ምላሽ ሊሰጥ ይችላል

እዚህ ስፍራ "ምላሽ" የሚለው ቃል መልስ ማለት ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን ጠቃሚ የሆነ ምላሽ መስጠት ነው፡፡

Job 32:13-14

አጠቃላይ መረጃ፡

ኤሊሁ ለኢዮብ ወዳጆች መናገሩን ቀጥሏል

እኛ እውቀት አግኝተናልን/አለን

ይህ ማለት ጠቢብ ምን እንደሆነ ለይተው እንደሚያውቁ ያምናሉ ማለት ነው፡፡ "ጠቢብ ምን እንደሆነ እኛ አውቀናል/ደርሰንበታል"

ኢዮብን ለማሸነፍ

ይህ የሚገልጸው እግዚአብሔር ለኢዮብ ምላሽ እንደሚሰጥ እና እርሱን በጦርነት እንዳሸነፈ አድርጎ እንደሚያስተካክለው ነው፡፡ "ኢዮብን ለመቃወም" ወይም "ለኢዮብ መልስ ለመስጠት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በበአፍህ ቃል

"ያልከውን በማለትህ"

Job 32:15-16

አጠቃላይ መረጃ፡

ኤሊሁ መናገሩን ቀጥሏል

እጅግ መገረም

መደነቅ፣ መናገር አለመቻል

እነርሱ ስላልተናገሩ፣ በዚያ በጸጥታ ስለቆሙ እና መልስ መስጠት ስላቆሙ እኔ ዝም ማለት ይኖርብኛል?

ኤሊሁ ጥያቄውን የሚጠቀምበት ከእንግዲህ በኋላ ዝም ብሎ እንደማይቆይ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ ኤሊሁ በቀጣዩ ቁጥር ለጥያቄው ራሱ መልስ ይሰጣል፡፡ "ነገር ግን እናንተ ዝም ስላላችሁ፣ እኔ በእርግጥ ከእንግዲህ ዝም አልልም፤ እናንተ ዝም ብላችሁ ቆማችኋል ምላሽ መስጠትም አቁማችኋል፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 32:17-19

አጠቃላይ መረጃ፡

ኤሊሁ ትይዩ ተነጻጻሪ ዘይቤን በመጠቀም መናገሩን ቀጥሏል፡፡

እኔም የበኩሌን መልስ እሰጣለሁ

"እኔ አሁን በተራዬ መልስ እሰጣለሁ"

በቃላት ተሞልቻለሁ

ኤሊሁ በቃላት እንደመሞላቱ መጠን የሚናገረው ብዙ እንዳለው ይገልጻል፡፡ "ብዙ የምናገረው አለኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በውስጤ ያለው መንፈስ ግድ ይለኛል

"መንፈሴ እንድናገር ያስገድደኛል"

ደረቴ መተንፈሻ እንዳጣ እንደ ፈላ ወይን፣ እንደ አዲስ የወይን አቁማዳ፣ ለመፈንዳት ተዘጋጅቷል

ወይን በሚፈላበት ጊዜ፣ በመያዣው ውስጥ አየር ይታመቃል፡፡ አየሩ መውጫ ካላገኘ አቁማዳው ይፈነዳል፡፡ ኤሊሁ ይህንን ሲል ብዙ የሚናገረው እንዳለው እና ይህንን ካልተናገረ የሚፈነዳ ሆኖ እንደተሰማው መግለጹ ነው፤ ምንም እንኳን እነዚህ ሁለት ሃሳቦች ትይዩ ቢሆኑና ትርጉማቸው ግን ተመሳሳይ ቢሆንም፡፡ "የሚተመፍስበት እንዳጣ የፈላ ወይን ጠጅ እንደያዘ አቁማዳ ደረቴ የሚፈነዳ ሆኖ ይሰማኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ እና ትይዩ ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ደረቴ … ነው

ይህ የሚገልጸው ኤሊሁን ሲሆን፣ በተለይም መንፈሱን ነው፡፡ "መንፈሴ…ነው" ወይም "እኔ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 32:20-22

አጠቃላይ መረጃ፡

ኤሊሁ ትኩረት ለመስጠት ትይዩ ተነጻጻሪ ዘይቤን በመጠቀም መናገሩን ቀጥሏል፡፡

እታደስ ይሆናል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የተሸለ /እፎይታ ሊሰማኝ ይችላል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ከንፈሮቼን አንቀሳቅሳለሁ

እዚህ ስፍራ "ከንፈሮች" የሚለው የሚወክለው አፍን/አንደበትን ነው፡፡ "አፌን እከፍታለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ለማንም ሰው የከበረ መጠሪያ አልሰጥም

"ማንንም አላወድስም ወይም ለማንም የክብር ስም አልሰጥም"

ያበጀኝ/የሰራኝ

ይህ እግዚአብሔርን የሚያመለክት ስም ነው፡፡ "ያበጀኝ እርሱ እግዚአብሔር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ይወስደኛል

ይህ ማለት እርሱ ያጠፋዋል ማለት ነው፡፡ "ያጠፋኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዩፊሚዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 33

Job 33:1-3

አጠቃላይ መረጃ፡

ኤሊሁ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

ንግግሬን አድምጡ፤ ቃሎቼን ሁሉ ስሙ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርም አላቸው፡፡ ኤሊሁ ኢዮብ በጥንቃቄ ሊያደምጥ እንደሚገባው ትኩረት ሰጥቶ ይናገራል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ አፌን እከፍታለሁ… ምላሶቼ የአንደበቴን ቃል ይናገራሉ

እነዚህ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ኤሊሁ አሁን ለመናገር ዝግጁ መሆኑን በትኩረት ይገልጻል፡፡ የእርሱ "ምላስ" ንግግር የሚወክለው የራሱን ንግግር ነው፡፡ "አፌን ከፍቼ መናገር ጀምሬያለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

ቃሎቼ ከልቤ ቅንነት ይፈልቃሉ

እዚህ ስፍራ ኤሊሁ ትክክል መሆኑን የሚገልጸው በ"ልቡ" ቅንነት ነው፡፡ "በጽድቅ እናገራለሁ" ወይም "በሙሉ ቅንነት እናገራለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ከንፈሮቼ መልካም እውቀት ይናገራሉ

እዚህ ስፍራ ኤሊሁ በ"ከንፈሮቹ" ራሱን የሚወክለው ለንግግሩ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "በትክክለኛ አቋም እናገራለሁ" ወይም "በፍጹም ቅንነት እናገራለሁ" (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 33:4-5

አጠቃላይ መረጃ፡

ኤሊሁ ለኢዮብ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

የእግዚአብሔር መንፈስ … ህይወት ሰጠኝ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ኤሊሁ እግዚአብሔር እርሱን እንደሰራው እና ለሚናገረው ሀላፊነትን እንደሰጠው ትኩረት ይሰጣል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ቃሎችን አሰናድተህ በፊቴ ለመቆም ተዘጋጅ

ይህ የሚገልጸው ኢዮብ የሚናገረውን አካላዊ ቁሶችን እንደሚደረድር እንዲያሰናዳ ነው፡፡ "የምትናገረውን አሰናዳ፣ ከዚያም ቆመህ/ታጥቀህ መልስልኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 33:6-7

አጠቃላይ መረጃ፡

ኤሊሁ ለኢዮብ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

እነሆ

ኤሊሁ እዚህ ስፍራ ይህንን ቃል የተጠቀመው የኢዮብን ትኩረት ቀጥሎ ወደሚናገረው ነገር ለመሳብ ነው፡፡ "አድምጡኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

በእግዚአብሔር እይታ እኔም ልክ እንደ አንተ ነኝ

እዚህ ስፍራ እይታ የሚወክለው ፍርድን ወይም ሚዛንን ነው፡፡ "በእግዚአብሔር ፍርድ እኔም ልክ እንደ አንተ ነኝ" ወይም "እግዚአብሔር በአንተ ላይ በሚፈርድበት ተመሳሳይ መንገድ በእኔም ላይ ይፈርዳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እኔም ደግሞ የተበጀሁት ከሸክላ ነው

ምንም እንኳን ሰዎች ከሸክላ ባይሰሩም፣ ሸክላ ሰራተኛ ነገሮችን በጥንቃቄ ከሸክላ እንደሚያበጅ እግዚአብሔር ሁሉንም አበጅቷል፡፡ "ሸክላ ሰራተኛ ነገሮችን ከሸክላ እንደሚሰራ እግዚአብሔር ሁለታችንንም ሰርቶናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እኔም ደግሞ ተሰርቻለሁ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር እኔንም ደግሞ አበጅቶኛል" ወይም "እግዚአብሔር ሁለታችንንም አበጅቶናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የእኔ ማስደንገጥ አንተን አያስፈራህም

"እኔን ልትፈራ አያስፈልግም"

የእኔ ጫና በአንተ ላይ ሊከብድ አያስፈልግም

ይህ ማለት እርሱ ኢዮብን አያግደውም ወይም ሸክም አይጭንበትም፡፡ እርሱ ስሜታዊውን ሸክም የሚናገረው እንደ ከባድ አካላዊ ሸክም አድርጎ ነው፡፡ "እኔ በአንተ ላይ ሸክም አልጭንም" ወይም "በምናገረው ነገር ጫና አላሳድርብህም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 33:8-9

አጠቃላይ መረጃ፡

ኤሊሁ ለኢዮብ መናገሩን ቀጥሏል፡፡

እኔ ስሰማህ

"እኔ ልሰማህ በምችልበት"

አንደበትህ ሲናገር የሰማሁት

"ስትናገር የሰማሁህ"

ንጹህ

እግዚአብሔር በመንፈስ ተቀባይነት አለው ያለው ሰው፤ በአካል ንጹህ እንደነበረ ሰው ተደርጎ ይገለጻል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ኃጢአት የለብኝም

"ኃጢአት አልሰራሁም"

Job 33:10-12

አጠቃላይ መረጃ፡

ኤሊሁ ኢዮብ የተናገረውን መጥቀሱን ቀጥሏል፡፡

እነሆ

ተናጋሪው እዚህ ስፍራ ይህንን ቃል የተጠቀመው ቀጥሎ ወደሚናገረው ትኩረት ለመሳብ ነው፡፡ "አድምጠኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ እግሮቼን በግንድ አጣበቀ "ከግንድ ጋር ማሰሪያ" ይህ ከግንድ ጋር ተጣብቆ ማሰሪያ ሲሆን አሳሪው በእስረኛው እግር ዙሪያ እንቅስቃሴውን ለመገደብ የሚያደርገው ነው፡፡ ኢዮብ እስረኛ እንደሆነ የሚሰማው በግንድ ተጣብቆ እንደታሰረ በመናገር ነው፡፡ "እስረኛ እንዳደረገኝ ይሰማኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የእኔ መንገዶች

እነዚህ ቃላት ወዴት እንደሚሄድ ያመለክታሉ፡፡ እዚህ ስፍራ ወዴት እንደሚሄድ የሚለው የሚገልጸው ምን እንደሚያደርግ ነው፡፡ "የማደርገው ነገር ሁሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እኔ እመልስልሃለሁ

ኤሊሁ ለኢዮብ እየተናገረ ነው

Job 33:13-15

አጠቃላይ መረጃ፡

ኤሊሁ ከኢዮብ ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል፡፡

ለምን እርሱን በመቃወም ትታገላለህ?

ኤሊሁ ይህንን ጥያቄ የሚጠቀምበት ኢዮብ ከእግዚአብሔር ጋር መታገል እንደሌለበት ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ከእግዚአብሔር ጋር መታገል የለብህም" ወይም "ከእግዚአብሔር ጋር ለመከራከር መሞከር የለብህም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይልከቱ)

እርሱ በሚያደርገው ሁሉ አይጠየቅም

"እርሱ የሚያደርገውን ማናቸውንም ነገር ለእኛ ማብራራት አይኖርበትም"

እግዚአብሔር በአንድም- በሌላም መንገድ ይናገራል

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "እግዚአብሔር በተለያየ መንገድ ደግሞ ደጋግሞ ይናገራል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በህልም… በምሽት በራዕይ

እነዚህ ሀረጎች አንድ አይነት ትርጉም አላቸው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በሰዎች ላይ ከባድ እንቅልፍ ሲወድቅ፣ በአልጋ ላይ አንቀላፍተው ሳሉ

ይህ ሰዎች በከባድ እንቅልፍ ላይ ሳሉ፣ እንቅልፍ በእነርሱ ላይ እንደ ወደቀባቸው ወይም እነርሱን እንዳሸነፈ አድርጎ ይናገራል፡፡ "ሰዎች በአልጋቸው ላይ ተኝተው ሙሉ እንቅልፍ ወስዷቸው ሳለ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 33:16-18

አጠቃላይ መረጃ፡

ኤሊሁ ከኢዮብ ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል፡፡

በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር የሰዎችን ጆሮ ይከፍታል

ይህ የሚናገረው እግዚአብሔር ይሰሙ ዘንድ ጆሯቸውን በመክፈት ሰዎች ስለ ነገሮች እንዲረዱ ማድረጉን ነው፡፡ "በዚያን ጊዜ እግዚአብሔር ነገሮችን ለሰዎች ይገልጻል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሰውን ከሄደበት ለመመለስ

ይህ የሚናገረው እግዚአብሔር አንድ ሰው ክፉ ነገር እንዳይሰራ በአካል ወደ ኋላ የመጎተትን ያህል እየከለከለ ከክፉ ተግባሩ እንደሚጠብቀው ነው፡፡ "እርሱን ከ… ይጠብቅ ዘንድ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር የሰውን ህይወት ከጉድጓድ ይጠብቃል… ህይወቱ ወደ ሞት እንዳይሻገር ይጠብቀዋል

እነዚህ ሁለቱም ሃሳቦች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ "እግዚአብሔር ሰዎችን ከመቃብር እና ከሞት ያድናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጉድጓድ

ሰዎች ሲሞቱ የሚሄዱበት ስፍራ እዚህ ላይ "ጉድጓድ" ተብሎ ተጠቅሷል፡፡ "የሞቱ ሰዎች የሚገኙበት ስፍራ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የሰው ህይወት ይመለሳል…የእርሱ ህይወት

ይህ ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "ሰው ከመሞት እና…እርሱ ይጠብቀዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ሞት ከመሻገር

እዚህ ስፍራ "ሞት" የሚወክለው ሰዎች ሲሞቱ የሚሄዱበትን ስፍራ፣ ይኸውም፣ ሲኦልን ነው፡፡ "ወደ ሲኦል ከመሄድ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 33:19-20

አጠቃላይ መረጃ፡

ኤሊሁ ከኢዮብ ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል፡፡

እንደዚሁም ደግሞ ሰው ይቀጣል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር ደግሞ ሰውን ይቀጣል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

በአልጋው ላይ ሳለ በህመም

ይህ ማለት ሰው በአልጋው ላይ ታሞ ይተኛ ዘንድ እንዲህ ያለው መከራ ይደርስበታል፡፡ "በአልጋው ላይ በስቃይ ይተኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ስለዚህም ህይወቱ ምግብ ትጸየፋለች፣ ደግሞም ነፍሱ ምቾትን ትጠላለች

በመሰረቱ እነዚህ ሁለቱ ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ይኸውም ሰውየው መመገብ እንኳን እስከሚያቅተው ድረስ በታላቅ ስቃይ ውስጥ ነው ማለት ነው፡፡ ሰውየው የተገለጸው በ"ህይወቱ" እና በ"ነፍሱ" ነው፡፡ "ውጤቱ አንዳች የሚበላ አይፈልግም፣ እጅግ ምርጥ የሆነውን ምግብ እንኳን አይፈልግም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚሉትን ይመልከቱ)

ምቾትን መጸየፍ

"እጅግ ምርጥ የሆነውን ምግብ እንኳን መጥላት"

Job 33:21-22

አጠቃላይ መረጃ፡

ኤሊሁ ከኢዮብ ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል፡፡

ስጋው በአካሉ ላይ እስከማይታይ ድረስ ይሟሽሻል፣ በአንድ ወቅት የማይታዩ የነበሩ አጥንቶቹ አሁን ወጥተው ይታያሉ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ስጋው" የሚለው የሚያመለክተው ውፍራቱን እና ጡንቻዎቹን እንጂ የውጭ ሰውነቱን ቆዳ አይደለም፡፡ "በሽታ አጥንቶቹ እስኪታዩ ድረስ ሰውነቱን ደካማ እና ከሲታ አድርጎታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ እና ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

ነፍሱ ወደ ጉድጓድ ተቃርባለች

እዚህ ስፍራ ሰውየው የተገለጸው በ"ነፍሱ" ነው፡፡ "ወደ መቃብር ሊወርድ ተቃርቧል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ጉድጓድ

ሰዎች ሲሞቱ የሚሄዱበት ስፍራ እዚህ ላይ "ጉድጓድ" ተብሎ ተጠቅሷል፡፡ "የሞቱ ሰዎች የሚገኙበት ስፍራ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ህይወቱ ሊያጠፏት ለሚፈልጉ

እዚህ ስፍራ ሰውየው የተገለጸው በ"ነፍሱ" ነው፡፡ "ህይወቱ ሊያጠፏት ለሚፈልጉ" የሚለው ሀረግ ሰዎች ከሞቱ በኋላ የሚሄዱበትን ስፍራ ያመለክታል፡፡ "እናም የሞቱ ሰዎች ወደሚሄዱበት ስፍራ ለመሄድ ቅርብ ነው" ወይም "እናም በቅርቡ ወደ ሙታን ስፍራ ይሄዳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ እና ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 33:23-24

አጠቃላይ መረጃ፡

ኤሊሁ ከኢዮብ ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል፡፡

ለእርሱ

ይህ አንድን የተለየ ሰው አያመለክትም፡፡ ኤሊሁ ስለማንኛውም ሰው በአጠቃላይ መናገሩን ይቀጥላል፡፡

ከሺህ መላዕክት መሃል

በአንዳንድ ቋንቋዎች "በብዙ ሺህ" ከማለት ይልቅ "ብዙ/አእላፋት" ማለቱ ይበልጥ ተገቢ ይሆናል፡፡ "ከብዙ መላዕክት መሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ጉድጓድ

ሰዎች ሲሞቱ የሚሄዱበት ስፍራ እዚህ ላይ "ጉድጓድ" ተብሎ ተጠቅሷል፡፡ "የሞቱ ሰዎች የሚገኙት ስፍራ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ለእርሱ መቤዣ አገኛለሁ

ይህ ማለት መላዕክት ሰውየው እንዳይሞት ለኃጢአቱ ክፍያ የሚያደርጉበት መንገድ ያገኛሉ ማለት ነው፡፡ "እርሱ እንዳይሞት የምታደርግበትን መንገድ እኔ ለአንተ አግኝቻለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 33:25-26

አጠቃላይ መረጃ፡

ኤሊሁ ከኢዮብ ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል፡፡

ከዚያም

"ከዚይም" የሚለው ቃል እዚህ ስፍራ የዋለው እግዚአብሔር ለመላዕክቱ ጥያቄ ምላሽ ቢሰጥ ምን እንደሚሆን ለማመልከት ነው፡፡ "ከዚይም በውጤቱ" ወይም "መላዕክቱ ለእግዚአብሔር ከሚያቀርቡት ጥያቄ የተነሳ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ስጋው ከትንሽ ልጅ ገላ ይልቅ አዲስ ይሆናል

ይህ የሚናገረው የተፈወሰው ሰው አካሉ እንደ ህጻን አካል ታድሰሶ ዳግም እንደሚታደስ ነው፡፡ "የታመመው ሰው አካል ዳግም እንደ ወጣት ሰው አካል ይታደሳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከልጅ ይልቅ ታድሶ

በዚህ ንጽጽር፣ "አዲስ" የሚለው ቃል ግነት ነው፡፡ "እንደ ልጅ አዲስ ገላ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ኩሸት እና አጠቃላይ አስተያየት የሚሉትን ይመልከቱ)

የልጅ

ይህ የሚያመለክተው የልጅን ገላ ነው፡፡ "የልጅ ገላ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተተወ/የተዘለለ የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ወጣትነቱ ቀናት ጥንካሬ ይመለሳል

ይህ የሚናገረው ሰውየው ዳግም ወጣት እንደነበረበት ዘመኑ ጥንካሬ ያንኑ የወጣትነት ዘመኑን ብርታት እንደሚይዝ ነው፡፡ "ወጣት እንደነበረበት ዘመን ዳግም ብርቱ ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔርን ፊት በደስታ ይመለከታል

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ "በደስታ እግዚአብሔርን ያመልካል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔር ፊት

እዚህ ስፍራ እግዚአብሔር የተገለጸው በ "ፊቱ" ነው፡፡ "እግዚአብሔር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር ለሰው ድል ይሰጣል

"እግዚአብሔር ሰውን ያድናል" ወይም "እግዚአብሔር ለሰው ነገሮችን ዳግም ያስተካክላል"

Job 33:27-28

አጠቃላይ መረጃ፡

ኤሊሁ ከኢዮብ ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል፡፡

ነገር ግን ኃጢአቴ አልተቀጣም

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ነገር ግን እግዚአብሔር ለሰራሁት ኃጢአት አልቀጣኝም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ነፍሴን ወደ ጉድጓድ ከመውረድ አዳናት

እዚህ ስፍራ ሰውየው የተገለጸው በ"ነፍሱ" ነው፡፡ "ከሞት እና ወደ ጉድጓድ ከመውረድ አዳነኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ጉድጓድ

ሰዎች ሲሞቱ የሚሄዱበት ስፍራ እዚህ ላይ "ጉድጓድ" ተብሎ ተጠቅሷል፡፡ "የሞቱ ሰዎች የሚገኙት ስፍራ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ህይወቴ ብርሃን ማየቱን ይቀጥላል

እዚህ ስፍራ ሰውየው የተገለጸው በ"ህይወቱ" ነው፡፡ መኖር ደግሞ የተነገረው ብርሃንን ማየት ተደርጎ ነው፡፡ "መኖሬን እና የቀን ብርሃን ማየቴን እቀጥላለሁ" ወይም "መኖሬ ይቀጥላል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 33:29-30

አጠቃላይ መረጃ፡

ኤሊሁ ከኢዮብ ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል፡፡

እነሆ

ኤሊሁ እዚህ ስፍራ ይህንን ቃል የሚጠቀመው ቀጥሎ ለሚናገረው ነገር ኢዮብ ትኩረት እንዲሰጠው ለማድረግ ነው፡፡ "አድምጠኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ሁለቴ፣ አዎን፣ ሶስቴ አንኳን

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ "ደግሞ ደጋግሞ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሱ ነፍስ

ሰውየው የተገለጸው በ"ነፍሱ" ነው፡፡ "እርሱ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ነፍሱን ዳግም ከጉድጓድ ለመመለስ

ይህ የሚናገረው አንድ ሰው ሞቶ እንደ ነበረ እና ዳግም ከሞት አድኖ ወደ ህይወት እንደመመለስ አድርጎ ነው፡፡ "እርሱን ከሞት እና ወደ ጉድጓድ ከመውረድ መጠበቅ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ጉድጓድ

ሰዎች ሲሞቱ የሚሄዱበት ስፍራ እዚህ ላይ "ጉድጓድ" ተብሎ ተጠቅሷል፡፡ "የሞቱ ሰዎች የሚገኙት ስፍራ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ምናልባት እርሱ የህይወት ብርሃን ይበራለት ይሆናል

ይህ ፈሊጥ ነው፤ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽም ይችላል፡፡ "ምናልባት አስካሁን በህይወት በመቆየቱ ደስተኛ ሊሆን ይችላል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 33:31-33

አጠቃላይ መረጃ፡

ኤሊሁ ከኢዮብ ጋር መነጋገሩን ቀጥሏል፡፡

ኢዮብ ሆይ ልብ በል፣ ደግሞም አድምጠኝ

እነዚህ ሀረጋት ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ "ኢዮብ ሆይ፣ በጥንቃቄ አድምጠኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ ትክክል እንደሆንክ

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ "አንተ ቅን ነህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 34

Job 34:1-3

ኤሊሁም ቀጠለ

"ከዚያም፣ ኤሊሁ"

ኤሊሁ

ይህ የወንድ ስም በኢዮብ 32፡2 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡ (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

ቃሌን አድምጥ

"የምናገረውን ስማ"

እናንተ ጠቢባን … እናንተ አዋቂዎች

ኤሊሁ ኢዮብን እና ወዳጆቹን እየተቸ ነው፡፡ በእርግጥ ጠቢባን ናቸው ብሎ አያስብም፡፡ (ምጸት የሚለውን ይመልከቱ)

ላንቃ/ምላስ የምግብ ጣዕም እንደሚለይበት ጆሮም ነገርን ይለያል

ኤሊሁ ይህንን ማለቱ ሰዎች የምግብን ጣዕም ለመለየት ምግቡን እንደሚቀምሱ ሁሉ ትክክል የሆነውን ከስህተት ለመለየት በጥንቃቄ ያደምጣሉ ማለቱ ነው፡፡ እዚህ ስፍራ ሰዎች የተጠቀሱት በ"ጆሯቸው" እና በ"ላንቃቸው/ምላሳቸው" የሆነው ሰዎች እንደሚያጣጥሙ እና እንደሚያደምጡ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "መልካም የሆነውን ምግብ ለመለየት እንደምንቀምስ ሁሉ፣ መልካም የሆነውን ቃል ከክፉው ለመለየት እናደምጣለን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ እና ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 34:4-6

አጠቃላ መረጃ፡

ኤሊሁ ንግግሩን ቀጠለ፡፡

እኛ

እዚህ ስፍራ "እኛ" የሚለው የሚያመለክተው ኤሊሁን፣ ኢዮብን፣ እና ሶስቱን ወዳጆቻቸውን ነው፡፡ (አካታች "እኛ" የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ መብቴን ገፎኛል/ቀምቶኛል

"ፍትህ ሊሰጠኝ አልፈቀደም"

ሀሰተኛ ተደርጌ ተቆጠርኩ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር ሀሰተኛ አድርጎ ቆጥሮኛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ቁስሌ የማይድን ነው

እዚህ ስፍራ የኢዮብ ህመም እና መከራ የተወሰደው እንደ "ቁስል" ተደርጎ ነው፡፡ "እኔ ታምሜያለሁ ማንም ሊፈውሰኝ አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 34:7-9

አጠቃላ መረጃ፡

ኤሊሁ ንግግሩን ቀጠለ፡፡

እንደ ኢዮብ ያለ ሰው ማን ነው

ኤሊሁ ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚያነሳው ኢዮብን ለመገሰጽ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊቀርብ ይችላል፡፡ "እንደ ኢዮብ ያለ ሌላ ማንም ሰው የለም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ፌዝን እንደ ውሃ የሚጨልጥ/የሚጠጣ ማን ነው

ኤሊሁም ሰው ውሃ እንደሚጠጣ ያህል ኢዮብን በፌዝ እየከሰሰው ነው፡፡ "ውሃ እንደሚጠጣ ሰው ያህል እንደ ኢዮብ ማን አዘውትሮ በሌሎች ላይ ያፌዛል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ማን ከኃጢአተኛ ሰው ጋር ይሄዳል/ይራመዳል

እዚህ ስፍራ "መራመድ" የሚለው አንድ ሰው ለሚያደርገው ነገር ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "ማን እንደ ኃጢአተኛ ሰው ያደርጋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 34:10-12

አጠቃላ መረጃ፡

ኤሊሁ ንግግሩን ቀጠለ፡፡ እነዚህ እያንዳንዳቸው ቁጥሮች ትይዩ ሀረጎችን ይዘዋል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እናንተ አዋቂዎች

ኤሊሁ ኢዮብን እና ወዳጆቹን እየነቀፈ ነው፡፡ በእርግጥ ጠቢባን ናቸው ብሎ አያስብም፡፡ (ምፀት የሚለውን ዘይቤ ይመልከቱ)

ይህ ከእግዚአብሔር የራቀ ይሁን… ሁሉን ቻይ ከሆነው በደል የራቀ ይሁን

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው ደግሞም በአንድ ላይ የቀረቡት እግዚአብሔር እንደማይሳሳት ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ "ከእርሱ የራቀ ይሁን" የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ "ሁሉን ቻይ የሆነው እግዚአብሔር ስህተት ወይም ክፉ የሆነ ነገር አያደርግም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ምፀት የሚሉትን ይመልከቱ)

እርሱ ለሰው ዋጋውን መልሶ ይከፍለዋል

ይህ ማለት እርሱ ለአንድ ሰው ለሰራው ስራ የሚገባውን ይከፍለዋል ማለት ነው፡፡ እዚህ ስፍራ "ስራ" የሚለው ቃል አንድ ሰው ለሰራው ዘይቤያዊ አገላለጽ ነው፡፡ "እርሱ ለአንድ ሰው ለሰራው ስራ የሚገባውን መልሶ ይከፍለዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ እያንዳንዱ ሰው የራሱን መንገዶች ላይ ያለውን ዋጋ እንዲያገኝ ያደርጋል

"በራሱ መንገዶች" የሚለው ሀረግ አንድ ሰው ህይወቱን እንዴት እንደሚኖር ፈሊጣዊ አነጋገር ነው፡፡ ኤሊሁ ያንን እግዚአብሔር ለሰዎች የሚገባቸውን እንደሚሰጥ በትኩረት ይናገራል፡፡ "እርሱ እያንዳንዱ በኖረበት መሰረት ዋጋውን እንዲቀበል ያደርጋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 34:13-15

አጠቃላ መረጃ፡

ኤሊሁ ንግግሩን ቀጠለ፡፡

በምድር ላይ እርሱን የሚከስ ማን አለ? ማን መላዋን ምድር በእርሱ ስር አደረገ?

እነዚህ ሁለቱም ቃለምልልሳዊ ጥያቄዎች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ እናም፣ ቀድሞኑ የተረጋገጠ በመሆኑ ማንም የእግዚአብሔርን ስልጣን እንደማያረጋግጥለት ትኩረት ሰጥተው ይገልጻሉ፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች በዐረፍተ ነገር መልክ ሊጻፉ ይችላሉ፡፡ "በመላው ምድር ላይ ያሻውን እንዲያደርግ ማንም ለእግዚአብሔር ፈቃድ ሊሰጠው አያስፈልግም፡፡ እርሱ ምድርን ለመግዛት ሙሉ ስልጣን አለው፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚሉትን ይመልከቱ)

መቼም ቢሆን

ኤሊሁ እርሱ የማያምንበት ሁኔታ በፍጹም ሊሆን እንደማይችል ይገልጻል፡፡ (መላምታዊ ሁኔታዎች የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሱ መንፈስ እና እስትንፋሱ

ሁሉንም ህያዋን ነገሮች በህይወት የሚያኖረው የእግዚአብሔር "መንፈስ" እና "እስትንፋስ" ነው፡፡ "ለእኛ ህይወት የሰጠን የእርሱ መንፈስ እና እስትንፋስ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ስጋ ለባሽ ሁሉ

እዚህ ስፍራ ህይወት ያላቸው ነገሮች ሁሉ የተወከሉት በ"ስጋቸው" ነው፡፡ "ህይወት ያላቸው ነገሮች ሁሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰው የሆነ ሁሉ/ የሰው ልጅ ወደ አፈር ይመለሳል

ይህ ማለት ሁሉም ሰው ይሞታል፤ አካሉም በስብሶ አፈር ይሆናል፡፡ በመጀመሪያ እግዚአብሔር ሰውን የፈጠረው ከአፈር ነው፡፡ "የሰው ልጅ አካል በቶሎ ተመልሶ አፈር ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 34:16-17

አጠቃላ መረጃ፡

ኤሊሁ ንግግሩን ቀጠለ፡፡

እነሆ

ኤሊሁ ይህንን ቃል የተጠቀመው ቀጥሎ ወደሚናገረው ጠቃሚ ነገር ትኩረት ለመሳብ ነው፡፡

አንተ አለህ

እዚህ ስፍራ "አንተ" የሚለው ተውላጠ ስም ነጠላ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተው ኢዮብን ነው፡፡ (አንተ የሚለውን ተውላጠ ስም መልኮች ይመልከቱ)

የቃሌን ድምጾች ስማ

"የምናገረውን ስማ" ይህ ማለት ከዐረፍተ ነገሩ የመጀሪያ ክፍል ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ፍትህን የሚጠላ ያስተዳድራልን? አንተ ጻድቅ እና ታላቅ የሆነውን እግዚአብሔርን ትከሳለህን?

ኤሊሁ ይህንን ጥያቄ የሚያነሳው እግዚአብሔር ፍትህን ይጠላል ብለሃል በማለት ኢዮብን ለመገሰጽ ነው፡፡ "ፍትህን የሚጠላ በሰዎች ላይ ይገዛል ተብሎ ሊጠበቅ አይችልም፡፡ ስለዚህም አንተ ጻድቅ እና ሃያል የሆነውን እግዚአብሔርን በእርግጥ ልትወቅስ አትችልም፤ ደግሞም እርሱ የሚያደርገውን ስህተት ነው ልትል አትችልም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ፍትህን የሚጠላ ያስተዳድራልን?

ለዚህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ በውስጠታዋቂነት የተሰጠው ምላሽ "አይችልም" የሚል ነው፡፡ ይህ ጥያቄ የሚያሳየው እግዚአብሔር ፍትህን ቢጠላ ኖሮ አለምን ሊገዛ አይችልም ነበር የሚል ነው፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ፍትህን የሚጠላ ዓለምን ሊገዛ አይችልም" ወይም "በእርግጥ እግዚአብሔር በፍጹም ትክክል የሆነውን ሊጠላ እና ዓለምን ሊገዛ አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

ጻድቅ እና ታላቅ የሆነውን እግዚአብሔርን ትወቅሳለህን?

ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የዋለው ኢዮብ እግዚአብሔርን ለመውቀስ ስልጣን ወይም ምክንያት እንደሌለው ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ "ጻድቅ እና ታላቅ የሆነውን እግዚአብሔርን ልትወቅስ አትችልም!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 34:18-20

አጠቃላ መረጃ፡

ኤሊሁ ንግግሩን ቀጠለ፡፡

እንደ እግዚአብሔር ንጉሡን ‘አንተ የማትረባ ነህ' ወይም ከበርቴውን ‘አንተ ደካማ ነህ' የሚል ማን ነው?

ይህ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ ኢዮብ እግዚአብሔርን ሊወቅስ እንደማይችል ትኩረት ለመስጠት ከቀደመው ጥቅስ ይቀጥላል፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እርሱ ንጉሡን ‘አንተ የማትረባ ነህ' ይላል ከበርቴውንም ‘አንተ ደካማ ነህ' ይለዋል፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ንጉሡን የሚናገር፣ እግዚአብሔር

ይህ የቀደመው ጥያቄ ክፍል ነው፡፡ ከቀደመው ክፍል መረዳት እንደሚቻለው "አንተ እግዚአብሔርን ትውቀሳለህን" የሚለው ሊጨመር ይችላል፡፡ "አንተ ንጉሡን የሚናገረውን እግዚአብሔርን ትወቅሳለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተዘለለ/የተተወ የሚለውን ይመልከቱ)

የማይረባ

"ክፉ" ወይም "ዋጋ የሌለው"

እነርሱ የእጆቹ ስራዎች ናቸውና

እዚህ ስፍራ "እጆች" የሚለው የሚወክለው ሀይልን ነው፡፡ "እግዚአብሔር ሁሉንም አበጅቷልና" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በእኩለ ሌሊት

እኩለ ሌሊት አንዱ ቀን የሚያበቃበት እና ሌላው ቀን የሚጀምርበት ጊዜ ነው፡፡ እዚህ ስፍራ "እኩለ ሌሊት" የሚለው ያገለገለው እንደ ፈሊጣዊ አነጋገር ሆኖ ነው፡፡ "በምሽት" ወይም "ድንገት በምሽት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ሰዎች ይርዳሉ/ይንቀጠቀጣሉ ደግሞም ያልፋሉ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ይንቀጠቀጣሉ" የሚለው ሀረግ "ይመታሉ" ለሚለው ፈሊጣዊ አገላለጽ ነው፡፡ "እግዚአብሔር ይመታቸዋል ይሞታሉም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

ታላላቅ ሰዎች ይወሰዳሉ፣ ነገር ግን በሰዎች እጆች አይደለም

ይህ ማለት ሰዎች የሚሞቱት በእግዚአብሔር እንጂ በሰዎች አይደለም ማለት ነው፡፡ ይህም ደግሞ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ብዙ ሰዎች እንዲሞቱ ምክንያቱ እግዚአብሔር እንጂ ሰዎች አይደሉም" (ዩፊምዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

በሰዎች እጅ አይደለም

እዚህ ስፍራ ሰዎች የተወከሉት በ"እጆቻቸው" ነው፡፡ "በሰውልጅ አይደለም" ወይም "በሰዎች አይደለም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 34:21-23

የእግዚአብሔር ዐይኖች በሰው መንገዶች ላይ ነው

የእግዚአብሔር "ዐይኖች" የሚወክለው የእርሱን እይታ ነው፡፡ "የሰው መንገዶች" የሚለው ሀረግ ለሚያደርገው እና ለአኗኗሩ ፈሊጥ ነው፡፡ "እግዚአብሔር ሰው የሚያደርገውን ነገር ሁሉ ይመለከታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

እርሱ እርምጃዎቹን ሁሉ ይመለከታል

ይህ ማለት እርሱ ሁሌም አንድ ሰው የት እንደሚገኝ እና ወዴት እንደሚሄድ ያውቃል፡፡ "እርሱ ሰው ወዴት እንደሚሄድ ይመለከታል/የሰውን መንገድ ይመለከታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ጨለማ የለም፣ ጥልቅ ጨለማም የለም

"ጥልቅ ጨለማ" የሚሉት ቃላት "ጨለማ" ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ሲሆን ለጨለማው ጥልቀት ሰጥቶ ለመግለጽ የዋለ ነው፡፡ (ጥንድ ትርጉም የሚለውን ይመልከቱ)

በፍርድ

"ስለዚህ እርሱ ይፈርድበታል" ወይም "ፍርድ ለመቀበል"

Job 34:24-25

አጠቃላ መረጃ፡

ኤሊሁ ንግግሩን ቀጠለ፡፡

እርሱ ታላላቅ ሰዎችን ይሰባብራቸዋል

ይህ የሚገልጸው እግዚአብሔር እነዚህን ሰዎች አጥንታቸውን እንደሚሰባብር አድርጎ እንደሚያጠፋቸው ነው፡፡ "እርሱ ታላላቅ ሰዎችን ይደመስሳል" ወይም "እርሱ ከፍ ያሉትን ይደመስሳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ለመንገዳቸው ተጨማሪ ምርመራ አያስፈልገውም

እርሱ ያደረጉትን ጨምሮ መመርመር አያስፈልገውም ምክንያቱም ስለ እነርሱ ሁሉንም አስቀድሞ ያውቃል፡፡ "መንገዳቸውን አስቀድሞ ስለሚያውቅ፣ ተጨማሪ ምርመራ ማድረግ ሳያስፈልግ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

መንገዶቻቸውን

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ "እነርሱ ያደረጓቸው ነገሮች" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ሌሎችን በእነርሱ ስፍራ ያስቀምጣል

ይህ ማለት ሌሎች ሰዎች በእነርሱ ስፍራ ተቀምጠው እንዲመሩ ይሾማል፡፡ "እናም ሌሎች ሰዎች በእነርሱ ስፍራ እንዲመሩ ይመርጣል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በምሽት

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ "እነርሱ ነገሩን በማይጠብቁበት ጊዜ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ ይጠፋሉ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እናም ያጠፋቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 34:26-28

አጠቃላ መረጃ፡

ኤሊሁ ንግግሩን ቀጠለ፡፡

ሌሎች በግልጽ እየተመለከቱ፣ እንደ ወንጀለኛ ስለ ክፉ ስራቸው እርሱ ይገድላቸዋል

ይህ ሀረግ እነዚህ ሰዎች የሚሞቱበትን መንገድ ወንጀለኞች ከሚሞቱበት ሁኔታ ጋር ያነጻጽራል፡፡ "ወንጀለኞች የሆኑ ያህል በሰዎች ፊት እነርሱን ስለ ክፉ ስራቸው ይገድላቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ሌሎች በግልጽ እየተመለከቱ

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ "ሁሉም ሰው ሊመለከተው በሚችለው ስፍራ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ ይገድላቸዋል

ይህ ምንም እንኳን እግዚአብሔር ራሱ በሰይፍ ባይመታቸውም፣ እነዚህን ሰዎች እርሱ እንደሚገድላቸው ይገልጻል፡፡ ሌሎች ሰዎች እንዲገድሏቸው ሊያደርግ ወይም ጥፋት በላያቸው እንዲመጣባቸው ይችላል፡፡ "እንዲሞቱ ያደርጋል" ይህ ምንም እንኳን እግዚአብሔር ራሱ በሰይፍ ባይመታቸውም፣ እነዚህን ሰዎች እርሱ እንደሚገድላቸው ይገልጻል፡፡ ሌሎች ሰዎች እንዲገድሏቸው ሊያደርግ ወይም ጥፋት በላያቸው እንዲመጣባቸው ይችላል፡፡ "እንዲሞቱ ያደርጋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሱ መንገዶች

ይህ ሰዎች ምን ማድረግ እንዳለባቸው የእግዚአብሔርን ትዕዘዛ ያመለክታል፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ የድሆች ጩኸት ወደ እርሱ እንዲመጣ አድርገዋል

"ጩኸት" የሚለው ቃል በግስ መልኩ ሊገለጽ ይችላል፡፡ ይህ የሚናገረው እግዚአብሔር ጩኸታቸውን የሚሰማው ጩኸቱ ራሱ ሰው ሆኖ ወደ እርሱ እንደመጣ አድርጎ ነው፡፡ "እነርሱ ድሆችን አስለቅሰዋል፣ እግዚአብሔርም የድሆችን ጩኸት ሰምቷል፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች እና ሰውኛ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 34:29-30

አጠቃላ መረጃ፡

ኤሊሁ ንግግሩን ቀጠለ፡፡

እርሱ ዝም ሲል፣ ማን ሊወቅሰው ይችላል?

ኤሊሁ ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የተጠቀመው ኢዮብን ለማስተማር ነው፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እርሱ ዝም ለማለት ከወሰነ ማንም እግዚአብሔርን ሊተቸው አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሱ ፊት

እዚህ ስፍራ እግዚአብሔር የተገለጸው በ"ፊቱ" ነው፡፡ "እርሱ ራሱ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ማንም ሰዎችን አያጠምድም

ይህ አዳኝ እንስሳ እንደሚያድን ሁሉ አምላክ የለሽ መሪ ሰዎችን ከመጉዳቱ ጋር ያነጻጽራል፡፡ "ማንም ሰዎችን እንዳይጎዳ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 34:31-33

አጠቃላ መረጃ፡

ኤሊሁ ንግግሩን ቀጠለ፡፡

ማየት የማልችለውን አስተምረኝ

እዚህ ስፍራ "ማየት" ማለት ማወቅ ማለት ነው፡፡ "ሳላውቅ የሰራሁትን ስህተት አሳየኝ/አስተምረኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ እግዚአብሔር የሚያደርገውን እስከጠላህ ድረስ እርሱ የዚያን ሰው ኃጢአት ይቀጣል ብለህ ታስባለህን?

"እግዚአብሔር የሚያደርገውን እስከጠላህ ድረስ፣ እግዚአብሔር የዚህን ሰው ኃጢአት መቅጣት ይገባዋል ብለህ ታስባለህን?" ኤሊሁ ይህን ቃለምልልሳዊ ጥያቄ የተጠቀመው እግዚአብሔር ይህንን ሰው አይቀጣውም ብሎ ማሰብ አይኖርበትም የሚለውን ለማጉላት ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ምንም እንኳን እግዚአብሔር ያደረገውን አንተ ባትወደውም፣ በእርግጥ ምንም እንኳን እግዚአብሔር ይህንን ሰው ይቀጣዋል ብለህ ባታስብ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

የዚያ ሰው ኃጢአት

እዚህ ስፍራ ሰውን በኃጢአቱ ምክንያት መቅጣት የተጠቀሰው "የሰውየውን ኃጢአት" መቅጣት ተደርጎ ነው፡፡ "ያ ሰው በኃጢአቱ ምክንያት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ እስካልወደድክ ድረስ

"አንተ ባለመውደድህ ምክንያት"

ይህ አንተ የምታውቀው ምንድን ነው

"ስለዚህ አንተ የምታስበው"

Job 34:34-35

አጠቃላ መረጃ፡

ኤሊሁ ንግግሩን ቀጠለ፡፡

እኔን የሚሰሙኝ

"ስናገር የሚሰሙን እነርሱ"

Job 34:36-37

ኢዮብ በፈተና ቢቀመጥ ኖሮ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እኛ ኢዮብን በፈተና ሊናስቀምጠው ብንችል ኖሮ" ወይም "ኢዮብን ወደ ፍርድቤት ልናቀርበው ብንችል እና ዳኛ ሊያደምጠው ቢችል ኖሮ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

በትናንሽ ዝርዝር ጉዳዮቹ

ይህ ፈሊጥ ነው፡፡ "ጉዳዮቹን በጥልቀት ለመስማት" ወይም "የእርሱን ጉዳዮች በሙሉ በዝርዝር ለመስማት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ ንግግር የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ክፉ ሰዎች የሆነውን ንግግሩን

"እንዴት እንደ ክፉ ሰው እንደተናገረ"

አመጽን ጨምሯል

ይህ በእግዚአብሔር ላይ ማመጽን ያመለክታል፡፡ "እርሱ በእግዚአብሔር ላይ አመጽ ጨምሯል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በመሃከላችን ሆኖ በፌዝ እጆቹን አጨብጭቧል

በዚህ ክስ፣ ኢዮብ አጨበጨበ የተባለው በእግዚአብሔር ላይ አፊዟል የሚባለውን ለማጠናከር ነው፡፡ "በመካከላችን ሆኖ በእግዚአብሔር ሲያፌዝ እጆቹን አጨብጭቧል" ወይም "በፊት ለፊታችን በእግዚአብሔር ላይ አፊዟል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ እንዲሁም ትዕምርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚሉትን ይመልከቱ)

በእግዚአብሔር ላይ ብዙ ተናግሯል

ኤሊሁ ስለ "ቃላት" ሲናገር ቁሶች እንደሆኑ አድርጎ ነው፤ ብዙ ቃላትን ስለመናገር ሲናገርም እነዚያን ቁሶች አንዱን በሌላው ላይ እንደመከምር አድርጎ ነው፡፡ "እርሱ በእግዚአብሔር ላይ ብዙ ቃላትን ተናግሯል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 35

Job 35:1-3

ይህ ፍትህ ነው… ‘በእግዚአብሔር ፊት ያለኝ መብት ነው' ብለህ ታስባለህ?

ኤሊሁ ኢዮብን ለመገዳደር ጥያቄዎችን ያነሳል፡፡ "አንተ ትክክል እንደሆንክ ታስባለህ… ‘በእግዚአብሔር ፊት መብቴ ነው'" ትላለህ ወይም "ይህ ልክ አይደለም…‘በእግዚአብሔር ፊት መብቴ ነው'" ትላለህ፡፡ በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህን በማለትህ ልክ የሆንክ ይመስልሃል

"አንተ ይህን ማለትህ ልክ ይመስልሃል"

ይመስልሃል/እንዲህ ታስባለህ

እዚህ ስፍራ "አንተ" የሚለው ነጠላ ቁጥር ሲሆን የሚያመለክተውም ኢዮብን ነው፡፡ (አንተ የሚለው ተውላጠ ስም መልኮች የሚለውን ይመልከቱ)

በእግዚአብሔር ፊት ያለኝ መብት

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ኢዮብ በእግዚአብሔር ፊት ንጹህ መሆኑን እየተናገረ ነው፡፡ ወይም 2) ኢዮብ ከእግዚአብሔር ይልቅ እኔ ትክክል ነኝ እያለ ነው፡፡

አንተ ‘ይህ ለእኔ ምን ጥቅም አለው?' ብለህ ጠይቀሃል፡፡ ደግሞም፣ ‘ኃጢአት ባለመስራቴ ምን አተረፍኩ?' ብለሃል፡፡

ኤሊሁ ኢዮብ እነዚህን ሁለት ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄዎች እንዳነሳ ይጠቅሳል፡፡ "አንተ እንዲህ ብለሃል፣ ‘ይህ እኔን አልጠቀመኝም' ደግሞም፣ ‘ኃጢአት ብሰራ ከሚደርስብኝ ምንም የተሻለ አልሆነልኝም/ኃጢአት ባለመስራቴ አልተጠቀምኩም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 35:4-5

አጠቃላ መረጃ፡

ኤሊሁ ንግግሩን ቀጠለ፡፡

Job 35:6-8

አጠቃላ መረጃ፡

ኤሊሁ ንግግሩን ቀጠለ፡፡

ኃጢአት ብትሰራ… በእርሱ ላይ ምን ታደርጋለህ/ትጨምራለህ?

እነዚህ ሁለት መስመሮች ተመሳሳይ ትርጉም ይጋራሉ፡፡ ሁተኛው መስመር የመጀመሪያውን መስመር ትርጉም ያጠናክራል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ኃጢአት ብትሰራ፣ እግዚአብሔርን ምን ተጎዳዋለህ?

ኤሊሁ ይህንን ጥያቄ የሚያነሳው የኢዮብ ኃጢአት በእግዚአብሔር ላይ አንዳች ነገር እንደማያመጣ ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ "ኃጢአት ብትሰራ፣ እግዚአብሔርን አንዳች አትጎዳውም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

መተላለፍህ ወደ ላይ ቢከመር፣ እርሱን ምን ታደርገዋለህ?

ኤሊሁ ስለ "መተላለፎች" የሚናገረው ቁሶች እንደሆኑ አድርጎ ነው፤ ብዙ መተላለፎችን ማድረግ ደግሞ እነዚህን ቁሶች አንዱን በሌላው ጫፍ ወደ ላይ መከመር እንደሆነ አድርጎ ይገልጻል፡፡ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው ኢዮብ በመተላለፉ በእግዚአብሔር ላይ አንዳች ማምጣት ማድረግ እንደማይችል ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "አንተ ብዙ ታላላቅ መተላለፎችን ብትፈጽም፣ በእርሱ ላይ አንዳች ማድረግ አትችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚሉትን ይመልከቱ)

ጻድቅ ብትሆን፣ ለእርሱ ምን ልትሰጠው ትችላለህ? እርሱ ከአንተ እጅ ምን ይቀበላል?

ሁለቱ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄዎች በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም ያላቸው ናቸው፤ ሁለቱም የሚገልጹት የኢዮብ ጽድቅ ለእግዚአብሔር አንዳች ነገር እንደማይጨምር ነው፡፡ "አንተ ጻድቅ ብትሆን፣ ይህ አንተ ለእርሱ አንዳች ነገር እንድትሰጠው አያበቃህም፤ ደግሞም እርሱ ከአንተ እጅ የሚቀበለው አንዳች ነገር የለም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ከአንተ እጅ መቀበል

እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚለው ቃል የሚወክለው ኢዮብን ነው፡፡ "ከአንተ እጅ መቀበል"

ሌላ የሰው ልጅ

"ሌላ የሰው ልጅ" ወይም "ሌላ ሰው"

Job 35:9-11

አጠቃላ መረጃ፡

ኤሊሁ ንግግሩን ቀጠለ፡፡

በብዙ የተጽዕኖ ድርጊቶች ምክንያት

"ተጽዕኖ" የሚለው ቃል በግሳዊ ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ሰዎች ሌሎችን ለመጨቆን በሚያደርጓቸው በርካታ ነገሮች ምክንያት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ከታላላቅ ሰዎች ክንዶች እርዳታን ይፈልጋሉ

እዚህ ስፍራ "ክንዶች" የሚለው የሚያመለክተው ሀይልን ወይም ጥንካሬን ነው፡፡ "ከታላላቅ ሰዎች ሀይል ለማግኘት ጥሪ ያደርጋሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በምሽት ዝማሬዎችን የሚሰጥ ማን ነው

ኤሊሁ እግዚአብሔር ለሰዎች በችግር ጊዜ፣ በምሽት ሰአት የሚዘምሩት ዝማሬ አድርጎ ተስፋን እንደሚሰጥ ይናገራል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 35:12-14

አጠቃላ መረጃ፡

ኤሊሁ ንግግሩን ቀጠለ፡፡

እነርሱ ይጮሃሉ

"የተጨቆኑ ሰዎች ይጮሃሉ"

አንተ እርሱን ከምትጠባበቅበት… ምን ያህል ያነሰ ነገር ይመልስልሃል!

እግዚአብሔር የትዕቢተኞችን እና የክፉዎችን ጸሎት ስለማይሰማ፣ ይልቁንም ሙሉ ለሙሉ በእግዚአብሔር ላይ የተነሳውን የኢዮብን ጸሎት ይሰማል አይባልም፡፡ "ስለዚህ አንተ በትጠባበቀውም…እርሱ በእርግጥ ምላሽ አይሰጥህም!" (ቃለ አጋኖ የሚለውን ይመልከቱ)

የአንተ ጉዳይ በፊቱ ነው

"አንተ ጉዳይህን ለእርሱ አቅርበሃል"

አንተ እርሱን እየጠበቅህ ነው

" አንተ እርሱን እንዲመልስልህ እየጠበቅህ ነው"

Job 35:15-16

አጠቃላ መረጃ፡

ኤሊሁ ንግግሩን ቀጠለ፡፡

አሁን አንተ የእርሱ ቁጣ ቅጣት አያደርስም ብለሃል፣ ስለ መተላለፍ ጥቂት እርምጃ እንኳን አይወስድም ብለሃል

ኢዮብ ስለ እግዚአብሔር እውነት ያልሆኑ እነዚህን ነገሮች በመናገሩ ምክንያት፤ እግዚአብሔር ለኢዮብ ጸሎት ምላሽ አይሰጥም፡፡

የእርሱ ቁጣ ቅጣት አያስከትልም

እዚህ ስፍራ "የእርሱ ቁጣ" የሚለው "እርሱ" ለሚለው ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "እርሱ በመቆጣቱ ምክንያት በፍጹም ማንንም አይቀጣም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ ([[:en:ta:vol2:translate:figs-metonymy]] ይመልከቱ)

ያለ ዕውቀት ቃሎችን ደርድሯል/ብዙ ቃሎችን ተናግሯል

ኤሊሁ ስለ "ቃላት" ሲናገር ቁሶች እንደሆኑ አድርጎ ነው፤ ብዙ ቃላትን ስለመናገር ሲናገርም እነዚያን ቁሶች አንዱን በሌላው ላይ እንደመከምር አድርጎ ነው፡፡ "እውቀት" የሚለው ቃል በግሳዊ ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ስለ ምን እንደሚናገር ሳያውቅ ብዙ ቃላትን ተናግሯል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 36

Job 36:1-3

ጥቂት ነገሮችን አሳይሃለሁ

ኤሊሁ ለኢዮብ ነገሮችን ማስረዳትን የሚገልጸው እነዚያን ነገሮች ለኢዮብ እንደሚያሳየው አድርጎ ነው፡፡ "ጥቂት/አንዳንድ ነገሮችን አሳይሃለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እውቀት ከሩቅ ስፍራ አገኛለሁ

ኤሊሁ ስለ ተለያዩ ነገሮች እውቀትን ከሩቅ ስፍራ እንዳገኘ አድርጎ ይገልጻል፡፡ "ታላቁን እውቀቴን አሳይሃለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ጽድቅ የሰራኝ/የፈጠረኝ የእርሱ መሆኑን

እዚህ ስፍራ "ጽድቅ" የሚለው በቅጽል መልኩ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ፈጣሪዬ/የሰራኝ ጻድቅ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

Job 36:4-5

ቃሎቼ ሀሰት አይሆኑም

"እኔ የምናገረው ሀሰት አይሆንም"

በእውቀት የበሰለ አንድ ሰው ከአንተ ጋር አለ

"አንድ ሰው" የሚለው ቃል ኤሊሁ ራሱን ያመለክታል፡፡ በእውቀት የበሰለ በጣም አዋቂ ስለ መሆን ይናገራል፡፡ "እኔ፣ ከአንተ ጋር ያለሁት፣ በጣም በእውቀት የላቅሁ ነኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እነሆ

"ተመልከት" ወይም "ስማ" ወይም "ልነግርህ ላለው ነገር ትኩረት ስጥ"

እርሱ በመረዳት ባለጸጋነቱ ሃያል ነው፡፡

"በጥንካሬ ሃያል" የሚለው ሀረግ ጥንድ ትርጉም ይሰጣል፤ ይህም "በጣም ጠንካራ" ማለት ነው፡፡ ኤሊሁ ስለ እግዚአብሔር መረዳት/እውቀት ሁሉንም ነገር በፍጹምነት የሚናገረው የእርሱ መረዳት በጣም ጠንካራ እንደሆነ አድርጎ ነው፡፡ "እርሱ በመረዳቱ በጣም ጠንካራ ነው" ወይም "እርሱ ሁሉንም ነገር ሙሉ ለሙሉ ያውቃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 36:6-7

እርሱ ዐይኖቹን ከጻድቅ ሰው ላይ አያነሳም

ኤሊሁ እግዚአብሔር ለጻድቅ ሰው ሚያደርገውን ጥበቃ የመገልጸው እግዘአብሔር በዐይን እንደሚከታተላቸው አድርጎ ሲሆን እግዚአብሔር በእነርሱ ላይ የሚያደርገውን ጥበቃ ማቆሙን ደግሞ ዐይኖቹን ከላያቸው ማንሳት አድርጎ ይገልጸዋል፡፡ "እርሱ ጻድቃን ሰዎችን መጠበቁን አያቆምም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ንጉሥ በዙፋን ላይ ያስቀምጣቸዋል

ኤሊሁ እግዚአብሔር ለጻድቃን የሚሰጠውን ክብር የሚገልጸው እንደ ንጉሥ በዙፋን ላይ እንደሚያስቀምጣቸው አድርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ ከፍ ይላሉ

ኤሊሁ እግዚአብሔር ጻድቃንን የሚያከብራቸው ከፍ ወዳለ ስፍራ እንደሚያወጣቸው አድርጎ ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍት ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እርሱ ወደ ላይ ከፍ ያደርጋቸዋል" ወይም "እርሱ ያከብራቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 36:8-9

እነርሱ በሰንሰለት ቢታሰሩ እንኳን

እዚህ ስፍራ "እነርሱ" የሚለው የሚያመለክተው ኃጢአት ቢሰሩ እግዚአብሔር ለእርማት የሚቀጣቸውን ጻድቃን ነው፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "አንዱ በሰንሰለት ቢያስራቸው" ወይም "አንዱ እስረኛ ቢያደርጋቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

በመከራ ገመድ ቢያጠምዳቸው

ኤሊሁ በስቃይ ውስጥ እንዲገባ የተደረገን ሰው የሚገልጸው፤ ያ ሰው በገመድ እንደተያዘ እና እንዲሰቃይ እንደተደረገ ነው፡፡ "አንዱ ሰው እነርሱ እንዲሰቃዩ አድርጓል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

የእነርሱ መተላለፍ እና የእነርሱ ኩራት

ግሱ ከቀደመው ሀረግ ሊገኝ ይችላል፡፡ "መተላለፋቸውን እና ኩራታቸውን ለእነርሱ ይገልጥላቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተዘለለ/የተተወ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 36:10-12

እርሱ ጆሯቸውንም ደግሞ ይከፍታል

ኤሊሁ የሚናገረው የአንድን ሰው ጆሮ መክፈት ሰውየው እንዲሰማ ማድረግ መሆኑን ነው፡፡ "እርሱ እንዲሰሙም አድርጓል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በእርሱ ትዕዛዝ

"ትዕዛዝ" የሚለው ስም በግሳዊ ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "እርሱ ለሚያዛቸው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ከክፋት መመለስ

ኤሊሁ አንድን ድርጊት ማቆም ከዚያ መመለስ አድርጎ ይናገራል፡፡ "ክፉ ከማድረግ መመለስ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ቀኖቻቸውን በብልጽግና ይፈጽማሉ፣ አመቶቻቸውንም በእርካታ

"ቀናት" እና "አመታት" የሚሉት ቃላት ሁለቱም የሚያመለክቱት የአንድን ሰው የህይወት ዘመን ነው፡፡ "ዘመናቸውን/እድሜያቸውን በብልጽግና እና በእርካታ ይፈጽማሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ በሰይፍ ይጠፋሉ

ኤሊሁም የሚናገረው በሀይል በሰይፍ ስለሚጠፋ ሰው፣ በሰይፍ አንድ ሰው ስለገደላቸው ሰዎች ነው፡፡ "በአመጽ ይገደላሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 36:13-14

በልባቸው አምላክ የለሽ የሆኑ

እዚህ ስፍራ "ልብ" የሚለው የሚያመለክተው ሃሳብን እና ስሜትን ነው፡፡ ይህ ሀረግ ሰውየው እግዚአብሔርን ማመንን በግትርነት መቃወሙን ነው፡፡"በእግዚአብሔር ማመንን ማን ይቃወማል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

እግዚአብሔር በአንድ ላይ በሚያስራቸው ጊዜ እንኳን

ኤሊሁ እግዚአብሔር ሰዎችን መቅጣቱን በገመድ እንደሚያስራቸው አድርጎ ይገልጸዋል፡፡ "እግዚአብሔር በሚቀጣች ጊዜ እንኳን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ህይወታቸው በቤተ ጣኦት አመንዝሮች መሃል ያከትማል

እዚህ ስፍራ "የቤተ ጣኦት አመንዝሮች" የሚለው የሚያመለክተው በጣኦት አምልኮ ቤተመቅደስ ውስጥ የሚያገለግሉ ወጣት ወንዶች የአምልኳቸው ክፍል አድርገው የሚፈጽሙትን ስነምግባር የሌለው ወሲባዊ ድርጊት ነው፡፡ ለዚህ ሀረግ ሊሰጡ የሚችሉ አማራጭ ትርጉሞች 1) አምላክ የለሾች ስነምግባር በሌለው ባህሪያቸው መሞታቸውን ወይም 2) አምላክ የለሾች በሀፍረት እና በውርደት ይሞታሉ፡፡

Job 36:15-16

እርሱ ጆሮዎቻቸውን ከፍቷል

ኤሊሁ ያለ ችግር በሰፊ መከራ በሌለበት በሰፊ መኖርን ይገልጻል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ገበታህ ስብ በበዛበት ማዕድ ይሞላል

ኤሊሁ የሚናገረው ገበታ በምርጥ ምግቦች ተሞልቶ በብልጽግና ስለመኖር ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ገበታህ ይዘጋጃል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አገልጋዮችህ ገበታህን ያዘጋጃሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

በስብ የተሞላ ምግብ

ብዙ ስብ ያለው ስጋ የብልጽግና ምልክት ነበር፣ ምክንያቱም እንስሳቱ ጤናማ እና በሚገባ የተመገቡ እንደነበሩ ያሳያል፡፡ "እጅግ ምርጥ የሆነ ምግብ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 36:17-18

አንተ እንደ ክፉ ሰዎች በፍርድ ስር ነህ

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "እግዚአብሔር ክፉዎችን እንደሚቀጣ አንተንም እየቀጣ ነው" ወይም 2) "ክፉዎች በሚቀጡበት ቅጣት እየተቀጣህ ነው"

ፍርድ እና ብይን ይዘውሃል

ኤሊሁ እግዚአብሔር በኢዮብ ላይ እየፈረደበት እንደሆነ እና ፍርድ እና ብይን ኢዮብን እንደያዙት ሰዎች አድርጎ ይናገራል፡፡ "እግዚአብሔር ወደ ፍርድ አምጥቶሃል ደግሞም ብይን ሰጥቶሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ቁጣህ ወደ ፌዝ አይምራህ

አንዳንድ የመጽሐፍ ቅዱስ ቅጂዎች ይህንን "በሀብት አለመማለልህን ተጠንቀቅ" ይላሉ፡፡

Job 36:19-21

እንዳትጎዳ ሀብትህ ሊረዳህ ይችላልን፣ ወይም የጥንካሬህ ሀይል ሁሉ ሊያግዝህ ይችላል?

ኤሊሁ እነዚህን ጥያቄዎች የሚጠይቀው ገንዘብ እና ሀይል በትክክለኛ መንገድ እስካልሄደ ድረስ ኢዮብን ሊረዱት እንደማይችሉ ለመግለጽ ነው፡፡ "ሀብት ከመከራ ሊያወጣህ አይችልም፣ ደግሞም የትኛውም ሀይልና ጥንካሬ በሙሉ ሊረዳህ አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄየሚለውን ይመልከቱ)

የአቅምህ ጥንካሬ በሙሉ

"የታላቅ አቅምህ ጥንካሬ በሙሉ" ወይም "ታላቅ ጥረትህ በሙሉ"

ሰዎች ከስፍራቸው ሲወገዱ

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ይህ "ሰዎች" የሚለው በአጠቃላይ ሰዎችን ያመለክታል፣ "ከስፍራቸው ይቆረጣሉ" የሚለው ደግሞ ሌሎችን ከቤታቸው በሀይል ማስወገድን የሚገልጽ ዘይቤ ነው፡፡ "ሰዎች ሌሎችን ከቤታቸው ጎትተው ሲያስወጡ" ወይም 2) ይህ "ሰዎች" የሚለው የሚገልጸው አገርን ሲሆን "ከስፍራቸው ይቆረጣሉ" የሚለው ህዝቦች እንዲጠፉ መደረጋቸውን ይገልጻል፡፡ "አገራት ሲጠፉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አንተ በመከራ እየተፈተንክ ነው

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "መከራ እንድትቀበል በማድረግ እግዚአብሔር እየፈተነህ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 36:22-24

እነሆ፣ እግዚአብሔር

"ይህንን አስቀድሞውኑ ታውቃለህ፡ እግዚአብሔር"

እግዚአብሔር በሀይሉ ከፍ ያለ ነው

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "እግዚአብሔር እጅግ ሀያል ነው" ወይም 2) "ሰዎች እግዚአብሔርን ከፍ ያደርጋሉ ምክንያቱም እርሱ ሀያል ነው"

እንደ እርሱ አስተማሪ ማን ነው?

ኤሊሁ ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚጠይቀው እንደ እግዚአብሔር ያለ አስተማሪ የለም የሚለውን ለማጉላት ነው፡፡ "እንደ እርሱ ያለ አስተማሪ የለም" ወይም "እርሱ እንደሚያስተምር የሚያስተምር ማንም የለም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄየሚለውን ይመልከቱ)

Job 36:25-26

እነርሱ እነዚያን ድርጊቶች የተመለከቱት ከርቀት ብቻ ነው

ኤሊሁም የእግዚአብሔርን ስራዎች ከርቀት ብቻ በመመልከታቸው፣ ስራዎቹን በሙላት ሊረዱ ስላልቻሉ ሰዎች ይናገራል፡፡ "እነርሱ ስራዎቹን በሙላት አልተረዱም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እነሆ

"ተመልከት" ወይም "ስማ" ወይም "ልነግርህ ለተዘጋጀሁት ነገር ትኩረት ስጥ"

የእርሱ ዘመናት ቁጥር አይሰላም

ይህ የሚያመለክተው እግዚአብሔር ከመቼ አንስቶ እንደነበር ነው፡፡ "ሰዎች እርሱ ለምን ያህል ጊዜ እንደኖረ ማወቅ አይችሉም" ወይም "ሰዎች የእርሱን እድሜ ሊያውቁ አይችሉም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 36:27-29

እርሱ ከእንፋሎቱ ዝናብ ያዘንባል/ያነጥራል

"ማንጠር" የሚለው ቃል "ማጥራት" ወይም "ማጣራት" ማለትም ሊሆን ይችላል፡፡ ኤሊሁ እግዚአብሔር እንዴት የውሃ ጠብታን፣ ወይም ተንን እንዴት ወደ ዝናብነት እንደሚለውጥ ይገልጻል፡፡ "እርሱ ተኑን ወደ ዝናብ ይለውጠዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የደመናዎችን ታላቅ መበተንት፣ ከእርሱ ጎጆ የሚወጣውን መብረቅ የሚረዳ አለን?

ኤሊሁ ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚጠይቀው ማንም እነዚህን ነገሮች ማድረግ እንደማይችል ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "ማንም የደመናን መበተን እና ከእርሱ ጎጆ የሚወጣውን መብረቅ ሊረዳ አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄየሚለውን ይመልከቱ)

የደመናዎችን ታላቅ መበተንት

"ታላቅ መበተንት" የሚለው ሀረግ በግሳዊ ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "በሰማይ ሁሉ ላይ ደመና እንዴት እንደሚበተን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ከእርሱ ጎጆ

ኤሊሁ ሰማይን እግዚአብሔር እንደሚኖርበት "ጎጆ" አድርጎ ይገልጸዋል፡፡ "እግዚአብሔር ከሚኖርበት፣ ከሰማይ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 36:30-31

እነሆ፣ እርሱ ይበትናቸዋል

"በጥንቃቄ ተመልከት፣ ደግሞም እንዴት እንደሚበትናቸው እይ"

እናም የባህርን ስሮች ይሸፍናል

ኤሊሁ ባህር ተክል እንደሆነ እና ጥልቅ ስፍራው ስሩ እንደሆነ አድርጎ ስለባህር ጥልቅ ክፍል ይናገራል፡፡ ለዚህ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) ምንም እንኳን መብረቅ በሰማይ ብርሃን እንዲታይ ቢያደርግም፣ የባህር ጥልቅ ክፍሎች ግን ጨለማ እንደሆኑ ይቀራሉ፡፡ "ነገር ግን የባህር ጥልቅ ክፍል ጨለማ ሆኖ ይቀራል" ወይም 2) የሰማይ መብረቅ የባህር ጥልቅ ስፍራ ጭምር ብርሃን እንዲያገን ያደርጋል፡፡ "እናም ብርሃናት የባህርን ጥልቅ ስፍራ ያበራሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 36:32-33

እጆቹን በመብረቅ ይሞላል

ኤሊሁ ነጎድጓድ ስለሚያመጣው መብረቅ እግዚአብሔር መብረቅን በእጆቹ እንደያዛቸው እና እርሱ ወደ ፈለገው አቅጣጫ እንደሚጥላቸው ይናገራል፡፡ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) እግዚአብሔር የመብረቅን ሀይል ሊወረውራቸው በእጆቹ ይዟል፣ ወይም 2) እግዚአብሔር የመብረቅን ሀይል እስከሚጠቀምባቸው ድረስ በእጆቹ ደብቆ ይዟል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

መብረቆቹ

"በብልጭታ የሚፈጠረው መብረቅ" ወይም "መብረቁ"

አድምጥ እየመጣ ነው

"ሞገዱ እየመጣ መሆኑን ስማ"

Job 37

Job 37:1-3

ልቤ ተንቀጠቀጠ… ከስፍራው ሸሸ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፤ ደግሞም የፍርሃቱን ክብደት ያጎላሉ፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በዚህ ነገር ልቤ ራደ/ተንቀጠቀጠ

"ይህ" የሚለው የሚያመለክተው በኢዮብ 36፡33 ላይ የሚገኘውን ነጎድጓ ነው

ከስፍራው ሸሽቷል

ኤሊሁ ስለ ልቡ የሚናገረው ከደረቱ የሚወጣ እስኪመስል በሃይል እንደሚመታ ነው፡፡ "ከስፍራው ለቀቀ" ወይም "በሃይል ይመታል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

የድምጹ ነጎድጓድ፣ ከአፉ የሚወጣው ድምጽ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች በመሰረቱ ተመሳሳይ ነገሮችን ይናገራሉ፡፡ ኤሊሁ መብረቅን የእግዚአብሔር ድምጽ እንደሆነ አድርጎ ይገልጻል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እናትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

እስከ ምድር ዳርቻ ድረስ

ኤሊሁ በምድር ሩቅ ስፍራ የሚገኘውን ቦታ የምድር ዳርቻ እንደሆነ አድርጎ ይናገራል፡፡ "በምድር በሁሉም ስፍራ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 37:4-6

ከዚህ በኋላ ከፍ ያለ ድምጽ ይሰማል… የግርማው ድምጽ ይሰማል

ኤሊሁ ስለ ነጎድጓዱን እንደ እግዚአብሔር ድምጽ አድርጎ መግለጹን ይቀጥላል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከዚህ በኋላ ያጉረመርማል

"ከብልጭታው በኋላ ያጉረመርማል"

የግርማዊነቱ ድምጽ

"የእርሱ ግርማዊነት ድምጽ"

ድምጹ በሚሰማበት ጊዜ

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ሰዎች ድምጹን በሚሰሙበት ጊዜ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ልክ እንደዚሁ ለዶፍ ዝናብ

ግሱ ከቀደመው ሀረግ ሊወሰድ ይችላል፡፡ "ልክ እንደዚሁ፣ ለዶፍ ዝናብ ይናገረዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (የተዘለለ/የተተወ ሚለውን ይመልከቱ)

Job 37:7-9

እርሱ የሁሉንም ሰው እጅ ያቆማል

እዚህ ስፍራ "እጅ" የሚለው ቃል የሚወክለው መላውን ሰውነት ነው፡፡ "እርሱ ሁሉንም ሰው ያስቆማል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ሀይለኛው ዝናብ በደቡብ ካለው ማደሪያው ይወጣል፣ በረዶም/ቅዝቃዜ በሰሜን ካለው የተበታተነ ነፋስ ይወጣል

በእስራኤል፣ ጠንካራ የነፋስ ማዕበል ከደቡብ ይነፍሳል፤ ቀዝቃዛ አየር ደግሞ ከሰሜን ይመጣል፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ማዕበል በደቡብ ካለው ማደሪያው ይመጣል

ኤሊሁ አውሎ ነፋሱ እስኪመጣ ድረስ ማደሪያ ስፍራ እንዳለው አድርጎ እና ከደቡብ እንደሚነፍስ ይናገራል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 37:10-11

በእግዚአብሔር እስትንፋስ በረዶ ይሆናል

ኤሊሁ ቀዝቃዛው የሰሜን ነፋስ የእግዚአብሔር እስትንፋስ እንደሆነ ይናገራል፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "የእግዚአብሔር እስትንፋስ በረዶ ይሰጣል/ይፈጥራል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

እንደ ብረት ይጋገራል

ኤሊሁ የበረዶን ጥንካሬ ከብረት ጥንካሬ ጋር ያነጻጽራል፡፡ "እንደ ብረት ይጋገራል" (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ክምሩን ደመና እርጥበት ያሸክመዋል

ኤሊሁ እግዚአብሔር የደመናው ማዕበል እርጥበቱ ከብዶ በውሃ እንዲሞላ ማድረጉን ይናገራል፡፡ "እርሱ ከባዱ ደመና በእርጥበት እንዲሞላ ያደርጋል" (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 37:12-13

አንዳንድ ጊዜ ይህ ለእርማት ይሆናል

"እርማት/ቅጣት" የሚለው ቃል በግሳዊ ሀረግ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "የሚያርመው" አካል ሰዎች ናቸው፡፡ "አንዳንድ ጊዜ ህዝቡን ለመቅጣት ይህ ይሆናል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች እና ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚሉትን ይመልከቱ)

አንዳንድ ጊዜ ለምድሩ

ይህ ማለት ዝናብ ምድሩን አጠጥቶ ሰብል እንዲበቅል ያደርጋል፡፡ "አንዳንድ ጊዜ ምድሩን ለማጠጣት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

አንዳንድ ጊዜ እንደ ቃል ኪዳን ታማኝነት ተግባር

"ታማኝነት" የሚለው ረቂቅ ስም "ታማኝ"ነ ወይም "በታማኝነት" ተብሎ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አንዳንድ ጊዜ በታማኝነት ለቃል ኪዳኑ ለማድረግ" ወይም "አንዳንድ ጊዜ ለህዝቡ ታማኝ ለመሆን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

Job 37:14-15

እግዚአብሔር ደመናትን እንዴት እንደሰራ ደግሞም የመብረቆችን ብልጭታ እንዳበጀ ታውቃለህን?

ኤሊሁ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው ኢዮብ ይህን ማወቅ እንደማይችል ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "እግዚአብሔር እንዴት ደመናትን እንደሚያበጅ እና እንዴት መብረቅን እንደሚያበርቅ ልታውቅ አትችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

ደመናትን መስራት

"ደመናትን መቆጣጠር" ወይም "ደመናት እርሱን እንዲታዘዙለት እንደሚያደርግ"

Job 37:16-17

በእውቀቱ ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔርን አስደናቂ ስራዎች፣ የደመናትን መንሳፈፍ ማወቅ ትችላለህ?

ኤሊሁ ይህን ጥያቄ የሚጠይቀው ኢዮብ እነዚህን ነገሮች ማወቅ እንደማይችል ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "በእውቀት ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔርን አስደናቂ ስራዎች፣ የደመናትን መንሳፈፍ፣ መረዳት አትችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

የደማናትን መንሳፈፍ

"ደመናት እንዴት እንደሚንሳፈፉ"

የእግዚአብሔርን አስደናቂ ስራዎች

ግሱ ከቀደመው ሀረግ ሊገኝ ይችላል፡፡ "ወይስ የእግዚአብሔርን አስደናቂ ስራዎች ትረዳለህን?" ወይም "ደግሞም የእግዚአብሔርን አስደናቂ ስራዎች ልተረዳ አትችልም" (የተዘለለ/የተተወ የሚለውን ይመልከቱ)

ከደቡብ በሚመጣ… እንዴት ልብስህ እንደሚወብቅህ/እንደሚሞቅህ ትረዳለህ?

ኤሊሁ ይህን ጥያቄ የሚጠይቀው ኢዮብ እነዚህን ነገሮች እንደማያውቅ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "ከደቡብ በሚመጣ…ልብሶችን እንዴት እንደሚወብቁህ አታውቅም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

ልብሶችህ እንዴት እንደሚወብቁህ/እንደሚሞቁህ

"የለበስከው እንዴት ወበቅ እንደሚፈጥርብህ" ወይም "በልብስህ ውስጥ እንዴት እንደሚያልብህ"

ነፋሱ ከደቡብ እቀጣጫ ከመምጣቱ/ከመንፈሱ የተነሳ

በእስራኤል፣ ሞቃት ነፋስ የሚፍሰው ከደቡብ በረሃ ሲሆን ይህም ሞቃት የሙቀት መጠን ይፈጥራል፡፡ "ከሙቀቱ የተነሳ፣ ከደቡብ ደረቅ ነፋስ ይነፍሳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 37:18-20

ከብረት እንደተሰራ መስታወት…ሰማይን ልትዘረጋ ትችላለህ?

ኤሊሁ ይህንን ጥያቄ የሚጠይቀው ኢዮብ ይህን ማድረግ እንደማይችል ትኩረት ሰጥቶ ለመናገር ነው፡፡ ከብረት የተሰራ መስታወት የሚመስለውን ሰማይ…አንተ ሰማይን ልትረረጋ አትችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

ከብረት እንደ ተደተሰራ መስታወት ጥንካሬ ያለው

መጽሐፍ ቅዱስ በተጻፈባቸው ዘመናት፣ መስታወት የሚሰራው ከብረት ነበር፡፡ ኤሊሁ ሰማዩ እንደ ብረት ከመጠንከሩ የተነሳ ዝናብ አለመስጠቱን ይናገራል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የነጠረ ብረት

ይህ የሚያመለክተው፣ በማቅለጫ ውስጥ ተጨምሮ የቀለጠ እና ከዚያም ሲቀዘቅዝ የጠነከረ ብረትን ነው፡፡

እኛን ለእርሱ መናገር የሚገባንን ለእኛ አስተምረን

እዚህ ስፍራ "እኛን" እና "እኛ" የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት ኤሊሁን፣ ኤልፋዝን፣ በልዳዶስን እና ሶፋርን ሲሆን ኢዮብን አይጨምርም፡፡ ኤሊሁ ይህን ሀረግ የተጠቀመው በምጸት ነው፡፡ (አካታች የሆነ እና አካታች ያልሆነ "እኛ" የሚለውን ይመልከቱ)

ከአእምሯችን መጨለም የተነሳ

ኤሊሁ መረዳት አለመቻልን በአንድ ሰው አይምሮ ውስጥ እንደሚገኝ ጨለማ አድርጎ ይገልጻል፡፡ "እኛ ስለማንረዳ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከእርሱ ጋር መናገር እንደምፈልግ ለእርሱ ሊነገረው ይገባልን?

ኤሊሁ ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚጠይቀው ማንም ይህን ማድረግ እንደማይችል ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ "ከእርሱ ጋር መነጋገር እንደምፈልግ ለእርሱ የሚነግረው ሰው ማግኘት አልችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

ለእርሱ ሊነገረው ያስፈልጋል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ለእርሱ የሚነግረው ሰው ሊኖረኝ ያስፈልጋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

አንድ ሰው መዋጥ ሊፈልግ ያስፈልገዋልን?

ኤሊሁ ይህንን ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚጠይቀው ማንም ሰው ይህ እንዲደርስ እንደማይፈልግ ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ "ማንም ሰው ሊዋጥ አይፈልግም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

ለመዋጥ

ኤሊሁ አንድ እየጠፋ ያለን ሰው እየተዋጠ እንደሚገኝ ሰው ይገልጸዋል፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡"እግዚአብሔር እርሱን ስለሚያጠፋው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 37:21-22

ከሰሜን ወርቃማ ድምቀት ይመጣል

"ወርቃማ ድምቀት" የሚለው ሀረግ የሚገልጸው የወርቅን ክብር/ድምቀት ነው፡፡ ይህ በትርጉም ውስጥ ይበልጥ ግልጽ መደረግ ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር ከሰሜን በመርቃማ ክብር/ድምቀት ይመጣል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በእግዚአብሔር ላይ አስፈሪ ግርማ አለ

"አስፈሪ" የሚለው ቃል ትርጉሙ ፍርሃት ይፈጥራል ማለት ነው፡፡ ኤሊሁ ስለ እግዚአብሔር ግርማ የሚገልጸው በእግዚአብሔር ላይ እንዳረፈ ነገር አድርጎ ነው፡፡ "የእግዚአብሔር ግርማ ሰዎች እንዲፈሩ ያደርጋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 37:23-24

እኛ እርሱን ልናገኘው አንችልም

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "ወደ እርሱ ልንቀርብ አንችልም" ወይም 2) ይህ ዘይቤ ኤሊሁ ሰው እግዚአብሔርን ማግኘት እንደማይችል አድርጎ ቢያቀርብም ሰው እግዚአብሔርን ሙሉ ለሙሉ ሊረዳ እንደማይችል የገለጸበት ነው፡፡ "ሙሉ ለሙሉ ልናውቀው አንችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በራሳቸው አዕምሮ ጠቢባን ነን የሚሉ

እዚህ ስፍራ "አዕምሮ" የሚወክለው የሰውን ሀሳብ ነው፡፡ "በራሳቸው አስተሳሰብ ጠቢባን የሆኑ" ወይም "ራሳቸውን ጠቢባን አድረገው የቆጠሩ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 38

Job 38:1-3

ከዚያም ያህዌ መናገር ጀመረ

እዚህ ስፍራ "ከዚያም" የሚለው ቃል የመጽሐፉን አዲስ ክፍል መጀመር ያሳያል፡፡ በእናንተ ቋንቋ አዲስ ትዕይንትን ለመጀመር ተመሳሳይ ቃል ካለ ያንን መጠቀም ትችላላችሁ፡፡ "ያ ሁሉ ከሆነ በኋላ፣ ያህዌ መናገር ጀመረ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

ለኢዮብ ተናገረ

"ለኢዮብ መለሰለት" ወይም "ለኢዮብ ምላሽ ሰጠው"

ያለ እውቀት በቃላት ጨለማን ወደ እቅድ የሚመለስ/የሚያመጣ እርሱ ማን ነው?

ያህዌ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመበት ኢዮብ ስለማያውቀው ነገር መናገሩን ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "አንተ ጨለማን ያለ እውቀት በቃላት አማካይነት ወደ እቅዴ አስገብተሃል/አምጥተሃ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

ይህን የሚያመጣ እርሱ ማን ነው

"ይህ ለማምጣት አንተ ማን ነህ"

ወደ እቅዶች ጨለማ የሚያመጣ

"እቅዴን የሚያበለሽ" ወይም "ተግባሬን ግራ የሚያጋባ፡፡" ኢዮብ የእግዚአብሔርን እቅድ እንዴት እንዳበላሸ የተገለጸው የእግዚአብሔርን እቅድ ለማየት ይበልጥ ከባድ እንዳደረገ ተደርጎ ነው፡፡ "ጨለማ" የሚለው ረቂቅ ስም "አጨለመ" በሚል ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "እቅዶችን አጨለመ" ወይም "እቅዶች መታየት እንዳይችሉ ከባድ አደረገ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)

ያለ እውቀት በቃላት አማካይነት

"ስለማታውቃቸው ነገሮች በመናገር"

ያለ እውቀት በመናገር

"እውቀት" የሚለው ረቂቅ ስም በቅጽል መልኩ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "የማይታወቁ ቃላት" ወይም "እውቀት የሌለባቸው ቃላት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ

"ቀበቶህን እንደ ወንድ በወገብህ ዙሪያ እሰር፡፡" ወንዶች ከባድ ስራ ሲሰሩ በነጻነት እግራቸውን ማንቀሳቀስ እንዲችሉ በወገባቸው ዙሪያ ቀበቷቸውን ይታጠቃሉ፡፡ "እንደ ወንድ ወገብህን ታጠቅ" የሚለው ፈሊጣዊ አነጋገር እንደ ስራ፣ ውድድር፣ ወይም ጦርነትን የመሰለ አንድ ነገር ለማድረግ ተዘጋጅ የሚል ትርጉም አለው፡፡ ኢዮብ ለእግዚአብሔር መልስ መስጠትን ለመሰለ ከባድ ስራ መዘጋጀት ነበረበት፡፡ "ለከባድ ስራ ራስህን አዘጋጅ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 38:4-5

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ እርሱ እንጂ ኢዮብ ምድርን አለመፍጠሩን ትኩረት ሰጥተው በሚገልጹ በርካታ ጥያቄዎች ኢዮብን መገዳደር ጀመረ፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

እኔ የምድርን መሰረቶች መሰረትኩ

ያህዌ መሬትን መፍጠሩን የሚገልጸው መዋቅሮችን ይገነባ እንደነበረ አድርጎ ነው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እንግዲህ አንተ እጅግ ብዙ መረዳት ካለህ

"መረዳት" የሚለው ረቂቅ ስም "ተረዳ/አወቀ" በሚል ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "እጅግ ብዙ አውቀህ ከሆነ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

መጠኗን የወሰነው ማን ነው? ይህ ታውቅ እንደሆነ ንገረኝ

ይህንን በዐረፍተ ነገር መልክ መግለጽ ይቻለል፡፡ "የምታውቅ ከሆነ፣ መጠኗን ማን እንደወሰነ ንገረኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

መጠን

"ልክ"

በላይዋ የመለኪያ ገመዷን የዘረጋ ማን ነው?

ይህን ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ መግለጽ ይቻለል፡፡ "በላይዋ የመለኪያ ገመድ ማን እንደዘረጋ ንገረኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

የመለኪያ ገመድ

ሰዎች የአንድን ነገር ትክክለኛ መጠን እና ቅርጽ ለመለካት የሚጠቀሙበት ገመድ ወይም ሲባጎ

Job 38:6-7

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

አጠቃላይ መረጃ፡

"የእርሷን" የሚለው ቃል መሬተን ያመለክታል፡፤

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ታላቅነቱን ለማጉላት ብዙ ጥያቄዎችን ይጠቀማል፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

መሰረቷ የተጣለው በምን ላይ ነበር?

ይህ በዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "መሰረቷ በምን ላይ እንደተጣለ ንገረኝ" (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

መሰረቷ የተጣለው በምን ላይ ነበር

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እኔ መሰረቷን በምን ላይ መሰረትኩ" (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔር ልጆች በደስታ ሲጮኹ… በዚያን ጊዜ ማን ማዕዘኖቿን መሰረተ?

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ " የእግዚአብሔር ልጆች በደስታ ሲጮኹ… ያን ጊዜ ማን ማዕዘኖቿን እንደመሰረተ ንገረኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

የማለዳ ከዋክብት በአንድነት ሲዘምሩ ደግሞም የእግዚአብሔር ልጆች በደስታ ሲጮሁ

እነዚህ ሁለት መስመሮች በትርጉም ተመሳሳይ ናቸው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የማለዳ ከዋክብት በአንድነት ሲዘምሩ

የማለዳ ከዋክብት የተገለጹት ሰዎች እንደሚዘምሩ የሚዘምሩ ተደርገው ነው፡፡ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) በቀጣዩ መስመር እንደተገለጸው "የማለዳ ከዋክብት" ከ "እግዚአብሐር ልጆች" ጋር ተመሳሳይ ናቸው ወይም 2) "የማለዳ ከዋክብት" የሚለው የሚያመለክተው በሰማይ የሚገኙ ከዋክብትን ነው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የማለዳ ከዋክብት

"በማለዳ የሚያበሩ ደማቅ ከዋክብት"

የእግዚአብሔር ልጆች

ይህ የሚያመለክተው ሰማያዊ ፍጥረታት የሆኑተን መላዕክትን ነው፡፡ ይህ በኢዮብ 1፡6 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

በደስታ ሰጮኹ

"ደስታ" የሚለው ረቂቅ ስም "ደስተኛነት" በሚል ተውሰከ ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "በደስተኝነት ጮኹ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

በደስታ

"በደስታ ተሞልተው ስለነበር"

Job 38:8-9

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ሌላ ጥያቄ የተጠቀመው እርሱ እንጂ ኢዮብ ምድርን አለመፍጠሩን ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

በባህር ላይ በር የዘጋ ማን ነው… ደግሞስ ከባድ ጨለማን መጠቅለያው ያደረገለት ማን ነው?

ይህ በዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ማን በባህ ላይ በሮችን እንደዘጋበት ንገረኝ…ከባድ ጨለማንስ ማን መጠቅለያው እንዳደረገ ንገረኝ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

በባህር ላይ በሮችን የዘጋ

ያህዌ ባህር መላውን ምድር እንዳይሸፍን የከለከለበት መንገድ በባህሩ ላይ በር ከመዝጋት ጋር ተነጻጽሯል፡፡ "ውሃ ምድርን እንዳያጥለቀልቅ ከልክሏል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ከማህጸን የወጣ ይመስል

ያህዌ ባህርን የፈጠረበትን ሁኔታ ከልጅ መወለድ ጋር ያነጻጽረዋል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ልብሱ

"ለባህር ልብስ ሆኖ"

ጥልቅ ጨለማ መጠቅለያው ሆኖ

"ጨለማ" የሚለው ረቂቅ ስም "ጨለመ" በሚል ቅጽል ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ከባድ ጨለማን መጠቅለያው አደረግሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

መጠቅለያ ጨርቅ/መጠምጠሚያ

ልጆች እንደተወለዱ የሚጠቀለሉበት ረጅም ቁራጭ ጨርቅ

Job 38:10-11

ለባህር የእኔን ዳርቻን በጀሁለት

"ለባህር ዳርቻ አበጀሁለት"

ዳርቻ

ያህዌ ባህር እንዲያልፍ ያልተፈቀደለትን ድንበር አበጀለት"

መቀርቀሪያዎቹን እና በሮቹን አደረግሁለት

ያህዌ ለባህር ዳርቻ ያበጀበትን መንገድ የሚያነጻጽረው መቀርቀሪያ እና በሮች እንዲኖር ከማድረግ ጋር ነው፡፡ "መቀርቀሪያ አበጀሁለት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

መቀርቀሪያዎች

በር ለመዝጊያ የሚያገለግል ረጅም የአንጨት ቁራጭ ወይም ብረት

እኔ ስናገረው/ሳዝዘው

"እኔ ባህሩን ስናገረው፡፡" ያህዌ ባህሩን የሚናገረው/የሚያዘው ሰው እንደሆነ አድርጎ ነው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህን ያህል መቅረብ ትችላለህ፣ ከዚህ ወዲያ ግን አታልፍም

"ይህን ያህል" የሚለው ቃል ያህዌ እስከፈቀደለት ስፍራ ድረስ ማለት ነው፡፡ "እስከዚህ ድንበር ድረስ ልትመጣ ትችላለህ፣ ነገር ግን ከዚህ አታልፍም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

የማዕበልህ ኩራት

"ለማዕበልህ ሀይል፡፡"ማዕበል የተገለጸው ኩራት እንዳለው ተደርጎ ነው፡፡ "ኩራት" የሚለው ረቂቅ ስም "ኩሩ" በሚል ቅጽል ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ለኩሩ ማዕበልህ" ወይም "ለሀይለኛው ማዕበልህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 38:12-13

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ይህን ጥያቄ የተጠቀመው እርሱ እንጂ ኢዮብ ብርሃንን አለመፍጠሩን ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

ክፉው ከእርሱ እንዲወገድ … አንተ ነቅንቀኸዋልን?

ይህ ጥያቄ አሉታዊ ምላሽ ይጠበቅበታል፡፡ ይህ በዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አንተ ፈጽሞውኑ ክፉውን … ከእርሱ ነቅንቀህ አላስወገድክም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ለማለዳ ትዕዛዝ መስጠት

ያህዌ ማለዳ ትዕዛዝን መቀበል እንደሚችል እና እንደ ሰው ነገሮችን ማወቅ እንደሚችል ይናገራል፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይልከቱ)

ንጋት ስፍራውን እንዲያውቅ ማድረግ

"ንጋት ስፍራው የት እንደሆነ እንዲያውቅ ማድረግ"

ንጋት

በማለዳ ሰማይ ላይ ፀሐይ ከመውጣቷ አስቀድሞ የቀኑ ብርሃን መታየት

የምድርን ዳርቻ መያዝ

የንጋት ብርሃን የተገለጸው የምድርን አድማስ እንደያዘ ተደርጎ ነው፡፡ "የምድርን ዳርቻዎች መያዝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያው አነጋገር እና ሰውኛ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ክፉውን ከውስጧ ነቅንቆ ማስወገድ

የቀን ብርሃን የተገለጸው የማያስፈልጉ ነገሮች በመነቅነቅ እንደሚወገዱ ክፉ ሰዎችን እንደሚያስወግድ ተደርጎ ነው፡፡ "ክፉ ሰዎችን ከምድር ነቅንቆ ማስወገድ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 38:14-15

ከማህተም በታች እንዳለ ጭቃ/ሸክላ የምድር መልኳ ይለወጣል

በምሽት፣ ሰዎች በግልጽ መመልከቱ አይችሉም፣ ማለዳ ግን ማህተም በሸክላ ላይ ግልጽ ምስልን እንደሚፈጥር ብርሃን የሁሉንም ነገር ቅርጽ በግልጽ መለየት ያስችላል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ቁራጭ ጨርቅ እጥፋት በእርሷ ላይ የሚገኙ ነገሮች ሁሉ በግልጽ ይታያል

እዚህ ስፍራ "እርሷ" የሚለው የሚያመለክተው ምድርን ነው፡፡ ይህ ሀረግ በዚህ ስንኝ ከሚገኘው የመጀመሪያው ሀረግ ጋር ተመሳሳይ ትርጉም አለው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ እና ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

ከክፉ ሰዎች "ብርሃናቸው" ይወሰዳል

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ማለዳ የክፉ ሰዎችን ‘ብርሃን' ይወሰዳል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የእነርሱን ‘ብርሃን'

ክፉዎች ጨለማን ብርሃናቸው አድርገው ይቆጥራሉ፣ ምክንያቱም ክፉ ስራቸውን ሚሰሩት በጨለማ ሲሆን ደግሞም ከጨለማ ጋር ቅርርብ አላቸው፡፡ (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)

የተነሳው ክንዳቸው ይሰበራል

የተነሳው የክፉዎች እጅ የሚለው የሚወክለው ሀይላቸውን እና ክፉ ለማድረግ ያላቸውን ፍላጎት ነው፡፡ ነገር ግን የማለዳው ብርሃን ስወጣ ክፉዎች እነዚያን ክፉ ነገሮች ማድረጋቸውን ያቆማሉ፡፡ (ዘይቤያው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

Job 38:16-18

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ አምስት ጥያቄዎችን የተጠቀመው እርሱ እንጂ ኢዮብ ምድርን እና ባህርን አለመፍጠሩን ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

አጠቃላይ መረጃ፡

ቁጥር 16 እና 17 አያንዳንዳቸው ተመሳሳይ የሆነ ትርጉም ያላቸው ሀረጎችን ይዘዋል፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በስፋቷ… ሄደህባታል?

እነዚህ ጥያቄዎች አሉታዊ ምላሽ ይጠብቃሉ፡፡ ጥያቄዎቹ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ "ወደ ባህር ውሃ መሰረት አልሁድክም፣ ወይም በጥልቁ ታችኛ ክፈል አልተራመድክም፡፡ የሞት ደጆች ለአንተ አልተገለጹም፤ ደግሞም የሞት ጥላ ደጆችን አላየህም፡፡ ምድርን በስፋቷ አላወቅካትም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

የውኆች መሰረትን/መገኛ

"ምንጮች"

ጥልቅ

ይህ ጥልቅ ውሃ የሚገኝበትን ባህርን ወይም ውቅያኖስን ያመለክታል፡፡ "ጥልቁ ባህር" ወይም "የውቅያኖስ ጥልቀት" ወይም "ጥልቁ ውሀ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስማዊ ቅጽል የሚለውን ይመልከቱ)

የሞት ደጆች ለአንተ ተገልጸውልሃል

Job 38:19-21

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ሶስት ጥያቄዎችን የተጠቀመው እርሱ እንጂ ኢዮብ ብርሃንን እና ጨለማን እንደማይረዳ ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

አጠቃላይ መረጃ፡

እነዚህ ሁለቱ ሀረጎች እያንዳንዳቸው ሁለት ትይዩ ሀረጎች አላቸው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ብርሃን ማረፊያ ስፍራ ደግሞም ወደ ጨለማ የሚወስደው መንገድ የት ነው?

ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ወደ ብርሃን ወይም ወደ ጨለማ ስፍራ የሚወስደውን መንገድ አታውቅም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

የብርሃን ማረፊያ ስፍራ

"የብርሃን መኖሪያ፡፡" ብርሃን የተገለጸው ለእያንዳንዱ ቀን ተነስቶ የሚመጣበት ማረፊያ ስፍራ እንዳለው ተደርጎ ነው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ብርሃን

"የቀን ብርሃን" ወይም "የፀሐይ ብርሃን"

ብርሃንን እና ጨለማን ወደ ስራ ስፍራቸው ልትመራቸው ትችላለህን? ለእነርሱ ወደ ሆነው ቤታቸው መልሶ

የሚወስዳቸውን መንገድ ልታገኝ ትችላለህ? እነዚህ ጥያቄዎች አሉታዊ ምላሽ እንዲሰጥባቸው ይጠበቃል፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች በዐረፍተ ነገር መልክ ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ "ብርሃንን እና ጨለማን ወደ ስራ ስፍራቸው ልትመራቸው አትችልም ወይም ደግሞ የእነርሱ ወደ ሆነ ቤታቸው የሚመለሱበትን መንገድ ልታገኝ አትችልም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

ወደ ስራ ስፍራቸው

"ወደ አካባቢያቸው/መኖሪያቸው፡፡" ብርሃን እና ጨለማ የተነገሩት በእየዕለቱ የያህዌን ተግባር ለማከናወን እንደሚወጡና እንደሚገቡ ነው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ያለ ጥርጥር… እጅግ ትልቅ

ያህዌ ምፀታዊ ቀልድ የተጠቀመው ኢዮብ ብርሃንን እና ጨለማን እንደማይረዳ ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ "አንተ እንደማታውቅ ግልጽ ነው፣ ምክንያቱም እነርሱን ስፈጥራቸው አንተ ገና አልተወለድክም ነበር፣ ደግሞም አንተ በጣም አላረጀህም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)

በዚይን ጊዜ ተወልደህ እንደሆነ

"በዚያን ጊዜ አንተ ትኖር ነበር፡፡" "በዚያን ጊዜ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ብርሃን የተፈጠረበትን እና ከጨለማ የተለየበትን ጊዜ ነው፡፡ "እነርሱን በፈጠርኩበት ጊዜ አንተ ተወልደህ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

የቀኖችህ ቁጥር እጅግ ትልቅ ነው

"እጅግ ረጅም አመታት ኖረሃል"

Job 38:22-24

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ይህን ጥያቄዎችን የተጠቀመው እርሱ እንጂ ኢዮብ በተፈጥሮ ላይ እንደማይገዛ ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

ወደ በረዶ ቤተመዛግብት/መጋዘን ገብተሃል፣ ወይም የበረዶ ውሽንፍሩን ቤተመዛግብት አይተሃል… ደግሞስ ለጦርነት ቀን?

እነዚህ ጥያቄዎች አሉታዊ ምላሽ እንዲሰጥባቸው ይጠበቃል፡፡ እነዚህ ጥያቄዎች በዐረፍተ ነገር መልክ ሊገለጹ ይችላሉ፡፡ "አንተ በፍጹም ወደ በረዶ ቤተመዛግብት አልገባህም፣ ወይም የበረዶ ውሽንፍሩን ቤተመዛግብት… እና ለጦርነት ቀን" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

የበረዶ ግምጃ ቤት ገብተሃል… የበረዶውን ውሽንፍርን ቤተመዛግብት

እነዚህ ሁለት ሀረጎች በትርጉም ተመሳሳይ ናቸው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የበረዶ ቤተ ማዛግብት… የበረዶ ውሽንፍር ቤተመዛግብት

በረዶ እና የበረዶ ወሽንፍራ ያህዌ የእርሱን ፈቃድ ሊፈጽምባቸው ያጠራቀማቸው ተደርገው ተገልጸዋል፡፡ (ዘይቤያው አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

የበረዶ ውሽንፍር

የበረዶ ኳስ (ብዙ ጊዜ ትንንሽ ናቸው) አንዳንድ ጊዜ በሃይለኛ ዝናብ ወቅት ከሰማይ ይወርዳል፡፡

የመብረቅ ብልጭታ መንገዱ ወዴት ነው ወይም ከምስራቅ በምድር ላይ ሁሉ የነፋስ መሄጃው ወዴት ነው?

እነዚህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፉ ይችላሉ፡፡ "የመብረቅን ብልጭታ የምልክበት መንገድ ወዴት ነው ወይም ከምስራቅ በምድር ላይ ሁሉ ነፋሳትን የምበትነው ወዴት ነው?" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ነፋሳት ይበተናሉ

"ነፋሳት ይነፍሳሉ"

Job 38:25-27

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ይህን ጥያቄ ኢዮብን የጠየቀው እርሱ እንጂ ኢዮብ ዝናብ እንዲዘንብ እና መብረቅ እንዲበርቅ እንደማያደርግ ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

ለዝናብ መውረጃውን የሚፈጥርለት ወይም…ሳር እንዲበቅል የሚያደርገው ማን ነው?

ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊጻፈ ይችላል፡፡ "ለዝናብ መውረጃውን የማበጅለት፣ ሳር እንዲበቅል የማደርግ እኔ ብቻ ነኝ፣… እኔ ብቻ ይህንን አደርጋለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

የዝናብ መውረጃ

"የዝናብ ጎርፍ"

የመብረቅ መንገድ

"የመብረቅ ጉርምርምታ የሚሰማበት መንገድ"

ማንም ሰው በማይኖርበት መሬት፣ ማንም በማይኖርበት ምድረበዳ

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተቀራራቢ ትርጉም አላቸው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ማንም ሰው በማይኖርበት

"ሰዎች በሌሉበት"

ለማርካት

በውስጠ ታዋቂነት የቀረበው መረጃ ምድር ሳር እንድታበቅል የሚያደርገው ዝናብ ነው፡፡ "ስለዚህ ዝናብ ምድር እንድታበቅል ያደርጋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

አጠፋ ደግሞም አወደመ

"የፈራረሰ እና የተበላሸ፡፡" እነዚህ ሁለት ቃላት ተቀራራቢ ትርጉም አላቸው፤ ደግሞም የእነዚህን አካባቢዎች የፈራረሰ እና ባዶ ተፈጥሮ ትኩረት ይሰጣሉ፡፡ (ሄንዲየዲስ/ሁለት ቃላት ‘እና' በሚል አያያዥ ቃል የሚገኛኙበትና አንድን ጥልቅ ሀሳብ ለመግለጽ የሚያገለግል ዘይቤያዊ አነጋገር)

በሣር

"እየበቀለ ያለ ሣር" ወይም "በመብቀል ላይ የሚገኝ ሣር፡፡" ማደግ የጀመረ ይህ ሣር፡፡

ምድርን በአዲስ ሣር የሚሞላ

"ምድር አዲስ ሳር እንድታበቅል የሚያደርግ"

Job 38:28-30

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ኢዮብን አራት ጥያቄዎችን የጠየቀው እርሱ እንጂ ኢዮብ ዝንብን እንደማያዘንብ፣ ጤዛና እና በረዶን እንደማይፈጥር እንደዚሁም አመዳይን እንደማያበጅ ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

አጠቃላይ መረጃ፡

በእነዚህ ሶስት ስንኞች ውስጥ የሚገኙ እያንዳንዳቸው መስመሮች ተመሳሳይ ነገሮችን ይገልጻሉ፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አጠቃላይ መረጃ፡

ዝናብ፣ ጤዛ፣ በረዶ፣ እና አመዳይ የተገለጹት እንደ ሰዎች እንደሚወለዱ ነው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ዝናብ አባት አለውን፣ ወይስ፣ የጤዛ ጠብታ አባቱ ማን ነው? በረዶ ከማን ማህጸን መጣ? የሰማይን ነጭ አመዳይ ማን ወለደው?

እነዚህ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ "ዝናብ አባት እንዳለው፣ የዝናብ ጠብታዎችን ማን እንዳስገኘ ንገረኝ፡፡ በረዶ ከማን ማህጸን እንደወጣ፣ ደግሞም የሰማይን ነጭ አመዳይ ማን እንደወለደው ንገረኝ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

ለጤዛ ጠብታ አባቱ

ለጤዛ አባቱ የሆነው የሚለው ለመፈጠሩ ዘይቤያዊ አገላለጽ ነው፡፡ "የጤዛ ጠብታ እንዲኖር ምክንያት የሆነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

በረዶ

"ቀዝቅዞ ጠጣር የሆነ/የረጋ ውሃ"

መውለድ

"ልጅ መስጠት"

ነጭ አመዳይ

በቅዝቃዜ መሬት ላይ በረዶ/ጠጣር የሆነ ጤዛ፣ ደማና በሌለበት ምሽቶች

ራሳቸውን የደበቁ እና እንደ ድንጋይ ጠጣር የሆኑ ውኆች

ውኆች የተገለጹት መደበቅ እንደሚችሉ ተደርጎ ነው፡፡ በክረምት በረዶ ከስሩ ውሃ ይደብቃል፡፡ (ሰውኛ እና ከባለቤቱ ጋር የሚጣቀስ ተውላጠ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)

እንደ ድንጋይ ሆነ

የበረዶው ጠጣርነት የተገለጸው ድንጋይ እንደሆነ ተደርጎ ነው፡፡ "እንደ ድንጋይ ጠጣር/ጠንካራ ሆነ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ጥልቁ

ይህ የሚያመለክተው ውሃው በጣም ጥልቅ የሆነን፣ ባህርን ወይም ውቅያኖስን ነው፡፡ "ጥልቁ ባህር" ወይም "የውቅያኖስ ጥልቀት" ወይም "ጥልቁ ውሃ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስማዊ ቅጽሎች የሚለውን ይምለከቱ)

Job 38:31-33

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ኢዮብን አምስት ጥያቄዎችን የጠየቀው እርሱ እንጂ ኢዮብ ሰማያትን እንደማይገዛ ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

አጠቃላይ መረጃ፡

በእነዚህ ሶስት ስንኞች ውስጥ የሚገኙ እያንዳንዳቸው ሁለት መስመሮች ተመሳሳይ ነገሮችን ይገልጻሉ፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

በምድር ላይ ሁሉ…በሰንሰለቶች መቆለፍ ትችላለህ

እነዚህ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ "ፕልያዲስ የተባለውን ኮከብ በሰንሰለት ማሰር ትችል እንደሆነ፣ ወይም ኦርዮን የተባለውን ኮከብ ገመድ መበጠስ ትችል እንደሆነ ንገረኝ፡፡ የከዋክብት ክምችትን በተገቢው ጊዜያቸው እንዲታዩ መምራት ትችል እንደሆነ ነገረኝ፤ ወይም ድብ የተባለውን ኮከብ ከልጆቹ ጋር መምራት ትችላለህ፡፡ የሰማይን ስርአት የምታውቅ ከሆነ፣ ወይም የሰማይን ህግ በምድር ላይ ማድረግ ትችል እንደሆነ ንገረኝ፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

ሰንሰለት መፍታት

"የሰንሰለት እስራት ልጥበጥስ" ወይም "ሰንሰለት መበጠስ"

ፕልያዲስ…ኦርዮን… ድብ

እነዚህ የከዋክበት ክምችቶች ስሞች ናቸው፡፡ እነዚህ በኢዮብ 9፡9 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎሙ ይመልከቱ፡፡

የኦርዮንን ገመዶች ልትበጥስ

"ኦርዮን የተባለውን ኮከብ ያሰሩትን ገመዶች ልትፈታ"

የከዋክብት ክምችት

በሰማይ ላይ አንድ የተለየ ቅርጽ ሚፈጥሩ የከዋክብት ክምችት

በተገቢ ጊዜያቸው መታየት

"በትክክለኛ ጊዜያቸው ይታዩ ዘንድ"

ልጆቹ

"ግልገሎቹ"

Job 38:34-35

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ኢዮብን ሁለት ጥያቄዎችን የጠየቀው እርሱ እንጂ ኢዮብ የዝናብ ደመናዎችን እና መብረቅን እንደማይገዛ ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

‘እኛ በዚህ አለን' …አንተ ልትነሳ ትችላለህ?

እነዚህ ጥያቄዎች በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ "ብዙ የዝናብ ውሃ ይሸፍንህ ዘንድ ድምጽህን እሰከ ደመናት ድረስ ማሰማት ትችል እንደሆነ ንገረኝ፡፡ የመብረቅ ብልጭታን ይወጣ ዘንድ ልታዘው ትችል እንደሆነ ንገረኝ፤ እነርሱም ‘እዚህ አለን!' ይሉህ እንደሆነ ተናገር፡፡" በሚለው ውስጥ እንሚገኘ፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

ብዙ የዝናብ ውሃ

"ብዙ/የተትረፈረፈ" የሚለው ረቂቅ ስም "የበዛ" በሚል ቅጽል ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ብዙ የዝናብ ውሃ" ወይም "የውኆች ጎርፍ" በሚለው ውስጥ እንሚገኘ፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን መልከቱ)

እዚህ አለን

ይህ የሚያሳየው የመብረቅ ብልጭታዎች እንደ አገልጋይ ትዕዛዝ ለመቀበል ዝግጁ ነን ማለታቸውን ነው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 38:36-38

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ኢዮብን ሶስት ጥያቄዎችን የጠየቀው እርሱ እንጂ ኢዮብ ደመናዎችን እና ዝናብን እንደማይገዛ ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

ጥበብን በአንድነት አጥብቆ የያዘ…ማን ነው?

እነዚህ ጥያቄዎች በዐረፍተ ነገር ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ "ጥበብን በደመናዎች ያኖረ ማን እንደሆነ ደግሞም ለብዠታ መረዳትን የሰጠ ማን ነው፡፡ ማን በችሎታው ደመናትን ሊቆጥር እንደሚችል ንገረኝ፡፡ አፈር ወደ ጠጣርነት ሲለወጥ እንዲሁም የምድር ጓል በአንድነት ሲጣበቅ የሰማይ የውሃ አቁማዳን ማን ማንቆርቆር እንደሚችል ንገረኝ፡፡" በሚለው ውስጥ እንሚገኘ፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

ጥበብን በደመናት ውስጥ ያስቀመጠ ማን ነው ወይም ለብዠታ መረዳትን የሰጠ ማን ነው?

እነዚህ ሁለት መስመሮች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ ደመናት እና ብዠታን ማስወገድ ያህዌ ለሰዎች የሚያደርጉትን ነገር ይረዱ ዘንድ የሰጣቸው ጥበብ እና መረዳት ተደርገው ተገልጸዋል፡፡ "ጥበብ" እና "መረዳት" የሚሉት ረቂቅ ስሞች "ጠቢብ" በሚል ቅጽል እና "ተረዳ" በሚል ግስ ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ "ደማናትን ጠቢብ ያደረገ ማን ነው ወይም ብዥታን ግልጽ ያደረገ ማን ነው?" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና ሰውኛ ዘይቤ እንዲሁም ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)

በደማናት ውስጥ ጥብን ያኖረ

"ለደማናት ጥበብን የሰጠ"

በራሱ ጥበብ ደማናት መቁጠር የሚችል ማን ነው?

"ደማናትን መቁጠር የሚችል ማን ነው?"

የውሃ አቁማዳዎች

እነዚህ ሰዎች በአንድነት የሚሰፏቸው ሲሆኑ ውሃ ለመያዝ የሚያገለግሉ ናቸው፡፡ ያህዌ ከባድ ደማናዎችን ከ"ውሃ አቁማዳ" ጋር ያስተያያቸዋል፣ ምክንያቱም እንደ ውሃ አቁማዳ ብዙ ውሃ መያዝ ይችላሉ፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

አፈር ወደ ጠጣርነት ሲለወጥ እና የምድር ጓል በአንድነት ሲጣበቅ

እነዚህ ሁለት መስመሮች ተመሳሳይ ትርጉም አላቸው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አፈር ወደ ጠጣርነት ሲለወጥ

ዝናብ የላመውን ደረቅ አፈር በአንድነት ያጣብቀዋል፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ዝናብ አፈሩን በአንድ ላይ አጣብቆ ሲያድበለብለው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

የምድር ጓል በአንድነት ሲጣበቅ

"የአፈር ጓል በአንድነት ሲጣበቅ"

Job 38:39-40

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ኢዮብን ይህን ጥያቄ የጠየቀው እርሱ እንጂ ኢዮብ አንበሶችን እንዴት እንደሚመግብ አለማወቁን ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

አንተ አድብተህ ጠብቀህ… ማደን ትችላለህ?

ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አድብተህ ጠብቀህ…ማደን ትችል እንደሆን ንገረኝ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

የሚታደን

"ታዳኝ፡፡" ይህ አንድ አንበሳ አድኖ የሚበላው እንስሳ ነው፡፡

ሴት አንበሳ

ይህች ሴት አንበሳ ናት

የምግብ ፍላጎት

ረሃብ

የእርሷ የአንበሳ ግልገል

"የአንበሳ ግልግል/ደቦል" ለራሳቸው አድነው መመገብ የጀመሩ ደቦል አንበሶች

ዋሻ

"ዋሻ" አንበሳ የሚጠለልበት መኖሪያ/የአውሬ ዋሻ/ ነው

በሚደበቅበት ጊዜ የሚጠለልበት

"በቁጥቋጦ ውስጥ መደበቅ፡፡" አንበሶች ሲያድኑ ጥቅጥቅ ባለ ሳር ቅጠል ውስጥ ይደበቃሉ

አድብቶ መጠበቅ

በውስጠ ታዋቂነት የሚገኘው መረጃ አንበሶች ተደብቀው የሚያድኑት እንስሳ እስኪቀርብ ይጠብቃሉ፡፡ "ታዳኙን ተጋድሞ/አድፍጦ መጠበቅ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 38:41

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ኢዮብን ይህን ጥያቄ የጠየቀው እርሱ እንጂ ኢዮብ ለአሞሮች ምግብ እንደማይሰጣቸው ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

ምግብ ላጡ… ምግባቸውን የሚሰጣቸው ማን ነው?

ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ምግብ ላጡ… ለተጠቁት ማን ምግባቸውን እንደሚሰጣቸው ንገረኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

ለተራቡት ምግብ የሚሰጥ

"ምግብ የሚሰጥ፡፡" ይህ የሚያመለክተው ቁራዎች ለምግብነት የሚፈልጓቸውን እንስሳት ነው፡፡

ቁራዎች/ቁራ መሰል አሞራ

የሞቱ እንስሳትን የሚመገቡ የሚያብረቀርቅ ጥቁር ላባ ያላቸው ትላልቅ ወፎች

ወደ እግዚአብሔር መጮህ

በውስጠ ታዋቂነት የሚገኘው መረጃ ቁራዎች ምግብ ለማግኘት ይጮሃሉ የሚል ነው፡፡ "ለእርዳታ ወደ እግዚአብሔር መጮህ" ወይም "ምግብ እንዲሰጣቸው ወደ እግዚአብሔር ይጮሃሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

መንገዳገድ

ይህ ማለት ወዲያ ወዲህ በመንገዳገድ መራመድ

ምግብ በማጣት

"በምግብ በማጣት ምክንያት" ወይም "የሚበሉት በማጣታቸው ምከንያት"

Job 39

Job 39:1-2

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

አጠቃላይ መረጃ፡

ያህዌ ኢዮብን አራት ጥያቄዎች የጠየቀው እርሱ ከኢዮብ ታላቅ እንደሆነ ትኩረት ሰጥቶ ለመግለጽ ነው፡፡ ምክንያቱም ለእነዚህ የተራራ ዱር ፍየሎች እና አጋዘኖች እንክብካቤ የሚያደርገው እርሱ እንጂ ኢዮብ አይደለም፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

ልጆቻቸውን ምን ጊዜ እንደሚወልዱ… አንተ ታውቃለህን?

ይህ በዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "አንተ በእርግጥ መቼ ነገሮች ምቹ እንደሚሆኑ …አጋዘኖች መቼ ግልገሎቻቸውን እንደሚወልዱ ማወቅ አትችልም!"

አጋዘኖች መቼ ልጆቻቸውን እንደሚወልዱ መጠባበቅ ትችላለህ?

ይህ በዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ አጋዘኖች ግልገሎቻቸውን የሚወልዱበትን ሁሉም ነገር ምቹ የሚሆንበትን ገዜ በእርግጠኝነት መጠባበቅ አትችልም!" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

ግልገሎች የሚኖራቸው

"ግልገሎቻቸውን የመወልዱበት"

የእርግዝና ወራቶቻቸውን መቁጠር ትችላለህ?

ይህ በዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "እርጉዝ የሚሆኑበትን ወራት መቁጠር አትችልም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

እርጉዝ የሚሆኑበት

"እርግዝናቸው የሚያበቃበት"

እነርሱ

"እነርሱ" የሚለው ቃል ፍየሎችን እና አጋዘኖችን ያመለክታል

እርጉዞች

"እርጉዝ የሆኑ"

ግልገሎቻቸውን መቼ እንደሚወልዱ ጊዜውን ታውቃለህ?

ይህ በዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "በእርግጥ መቼ ግልገሎቻቸውን እንደሚወልዱ አታውቅም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

Job 39:3-4

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

እነርሱ ወደ ታች ቁጢጥ ይላሉ

"እነርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሜዳ ፍየሎችን እና አጋዘኖችን ነው፡፡

ግልገሎቻቸውን ይወልዳሉ

"ዘራቸውን ይሰጣሉ"

ከዚያም የምጣቸው ስቃይ ያጨርሳሉ

የሚሰጡ ትርጉሞች 1) ወልደው ሲጨርሱ የምጣቸው ስቃይ ያልፋል ወይም 2) "የምጥ ስቃይ" የሜዳ ፍየሎች እና የአጋዘኖች ግልገሎችን የሚያመለክት ሜቶኖሚ/ ነው፡፡ ምክንያቱም እነርሱ የእናቶቻቸው ምጥ እና ስቃይ ውጤቶች ናቸው፡፡ "ከማህጸናቸው ግልገሎቻቸውን ይወልዳሉ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ባዶ ሜዳዎች

"ገጠራማ አካባቢ" ወይም "ጫካ"

ተመልሰው አይመጡም

"ወደ እነርሱ አይመለሱም" ወይም "ወደ እናቶቻቸው አይመለሱም"

Job 39:5-6

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

የጨው ምድሩን…ማን ሰጠው?

ያህዌ ከኢዮብ ይልቅ ታላቅ መሆኑን በትኩረት ለመግለጽ ሁለት ጥጣቄዎችን ይጠቀማል፤ ምክንያቱም ያህዌ ለሜዳ አህዮች እንክብካቤ የሚያደርገው ያህዌ እንጂ ኢዮብ አይደለም፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

የሜዳ አህያን በነጻነት እንዲፈነጭ ያደረገው ማን ነው?

ይህ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "የሜዳ አህያን በነጻነት እንዲፈነጭ ያደረግኩት እኔ ነኝ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

የሜዳ አህያ…የዱር አህያ

ይህ ተመሳሳይ ለሆነ የአህያ አይነት የተሰጠ ስም ነው

በጨው ምድር …እስራቱን የፈታ ማን ነው?

ይህ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "በጨው ምድር…እስራቱን የፈታሁለት እኔ ነኝ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን መልከቱ)

ማሰሪያዎች

እንስሳት ሮጠው እንዳይሄዱ የሚታሰሩባቸው ገመዶች፣ ሰንሰለቶች፣ ወይም ማሰሪያዎች

በምድረበዳ የማንን ቤት ሰራሁ

ያህዌ አህያ ቤት እንዳለው ሰው አድርጎ ይገልጻል፡፡ "ምድረበዳን መኖሪያ አድርጌ ሰጠሁት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የጨው ምድር

በጨው ባህር አካባበ ያለው ምድር ብዙ ጨው ይገኝበታል

Job 39:7-8

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

እርሱ

"እርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው የሜዳ አህያን ነው

በንቀት ይስቃል

ያህዌ አህያን እንደ ሰው ይስቃል በማለት ይገልጻል፡፡ አህያው የሚስቀው በከተማ የሚኖሩ ከፍ ያለ ድምጹን እንዲሰሙ ሲሆን፣ እርሱ ግን በጸጥታ ስፍራ ይኖራል፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚልውን ይመልከቱ)

ነጂዎች

እንስሳው እንዲሰራ የሚያስገድድ

መሰማሪያ

እንስሳት በሜዳ የበቀለውን የሚግጡበት ስፍራ

Job 39:9-10

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

አጠቃላይ መረጃ፡

እዚህ ስፍራ ያህዌ አራት ጥያቄዎች የጠየቀው ኢዮብ እንደ ያህዌ እንዳልሆነ ትኩረት ለመስጠት ነው፤ ምክንየቱም ኢዮብ ጎሽን ሊቆጣጠር አይችልም፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ጎሽ

ሊሰጡ የሚችለሁ ምክንያቶች 1) በጫካ የሚኖር የበሬ ዝርያ/አይነት ወይም 2) በሬ የሚመስል የጎሽ አይነት

ደስተኛ መሆን

"ፈቃደኛ መሆን"

በግርግምህ ሊቆይ ይፈቅዳልን?

ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "በግርግምህ ሊቆይ አይፈቅድም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

በግርግምህ ሊቆይ ይፈቅዳል

"ምሽቱን በበረትህ ለማደር"

ግርግም

እንስሳት መመገብ እንዲችሉ ምግባቸውን መያዣ

በእርሻ ስፍራ ጎሽን ለማሰር ገመድ መጠቀም ትችላለህ?

ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ጎሽ የእርሻህን ትልም እንዲያርስ በገመድ ጠምደህ ልትቆጣጠረው አትችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ገመድ

ገበሬዎች እንስሳትን ለመምራት በጭንቅላታቸው ወይም ጫንቃቸው/አንገት ላይ ገመድ ያስራሉ

ትልሞች

እነዚህ በእርሻ ላይ ያሉ ረጃጅም ቦዮች ናቸው፡፡ ትልም የሚለው በኢዮብ 31፡38 እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

ሸለቆውን አንተን እየተከተለ ይከሰክስልሃል?

ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "በፍጹም አንተን እየተከተለ ሸለቆውን አይከሰክስልህም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

መከስከስ

አፈርን ማለስለስ

Job 39:11-12

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

አጠቃላይ መረጃ፡

እዚህ ስፍራ ያህዌ ሶስት ጥያቄዎች የጠየቀው ኢዮብ እንደ ያህዌ እንዳልሆነ ክርክሩን ለመቀጠል ነው፤ ምክንየቱም ኢዮብ ጎሽን ሊቆጣጠር አይችልም፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ሀይሉ ታላቅ ስለሆነ እርሱን ትተማመናለህን?

ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ሀይሉ ታላቅ ስለሆነ በእርሱ ልትተማመን አትችልም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱን ታምናለህ

"እርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው "ጎሽ"ን ነው፡፡

ይሰራው ዘንድ ስራህን በእርሱ ላይ ትጥላለህ/ትተዋለህ?

ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ለአንተ ይሰራልህ ዘንድ ስራህን ለእርሱ መተው አትችልም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ይሰራልህ ዘንድ ስራህን ለእርሱ መተው

"ከባዱን ስራህን ይሰራልህ ዘንድ"

እህልህን ይወቃልህ/ያበራይልህ ዘንድ…በእርሱ ትታመናለህ?

እነዚህ ሁለት ሀረጎች በመሰረቱ ተመሳሳይ ትርጉም ይይዛሉ፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "እህልህን እንዲወቃልህ …በእርሱ ላይ ልትታመን አትችልም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ትይዩ ንጽጽራዊ ጥያቄ የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 39:13-15

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

የሰጎን ክንፎች…የፍቅር ላባዎች እና ክንፎች ናቸው?

ያህዌ ይህንን ጥያቄ የሚጠቀመው ኢዮብ ሰጎኖች የሚያደርጉትን ለምን እንደሚያደርጉ ኢዮብ እንደማየውቅ ትኩረት ለመስጠት ነው፡፡ "የሰጎን ክንፎች እና ላባዎች በኩራት ሲቀዝፉ ይህን የሚያደርጉት በፍቅር ይሁን አይሁን አንተ አታውቅም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ሰጎን

በጣም በፍጥነት መሮጥ የምትችል ነገር ግን የማትበር በጣም ትልቅ ወፍ

በኩራት ማርገብገብ

"በደስታ መንቀሳቀስ"

ክንፍ

በወፍ ክንፍ ላይ የሚገኝ በጣም ረጃጅም ላባዎች

ላባ

የወፍ አካልን የሚሸፍኑ አነስተኛ ላባዎች

የፍቅር

የዕብራይስጡ ቃል እርግጠኛ አይደለም፡፡ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "የታማኝነት" ወይም 2) "የሺመላ፡፡" ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ የሽመላ ስም ትርጉሙ "ታማኝ የሆነው" ወይም "አፍቃሪ የሆነ" ማለት ነው፤ ምከንያቱም ሰዎች ሽመላ ለጫጩቶቻቸው በጣም መልካም ተንከባካቢ እንደሆኑ ያውቃሉ፡፡

በመሬት ላይ

"በምድር"

እነርሱን ያደቋቸዋል/ይቸጯቸዋል

"እነርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው እንቁላሎችን ነው

ይረጋግጧቸዋል

"በላያቸው ይቆማሉ/ይራመዱባቸዋል"

Job 39:16-18

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

እርሷ በጭካኔ ትተዋቸዋለች

"እርሷ የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሴቷን ሰጎን ነው

የእርሷ ምጥ

እንቁላሏን ስትጥል የምትሰራው ስራ

በከንቱ ሊሆን ይችላል

ጫጩቶቹ ከሞቱ፣ ስራዋ ሁሉ ዋጋ ቢስ ነበር፡፡ "ጫጩቶቹ የሚሞቱ ከሆነ ልፋቷ ከንቱ ነበር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ከጥበብ ተነጥላለች

"ጥበብን እንድትዘነጋ ተደርጋለች" ወይም "ጥበብ አልተሰጣትም"

የጥበብ ምስጢር

ይህ ቃል በኢዮብ 11፡ ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

እርሷ ስትሮጥ

ይህ ስንኝ ጫጩቶቿን ከመንከባከብ ከድካሟ ጋር በንጽጽር ይታያል፡፡ "ሆኖም፣ በምትሮጥበት ጊዜ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡

እርሷ በጋላቢው…ትስቃለች

በጋላቢው የምትስቀው ከፈረስ ፈጣን በመሆኖ እንደሆነ ተጠቁሟል፡፡ "በጋላቢው የምትስቀው… ከፈረስ ይልቅ ፈጣን በመሆኗ ነው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 39:19-20

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

አጠቃላይ መረጃ፡

እዚህ ስፍራ ያህዌ ሶስት ጥያቄዎች የጠየቀው ኢዮብ እንደ ያህዌ እንዳልሆነ ትኩረት ለመስጠት ነው፤ ምክንየቱም ኢዮብ የዱር/ያልተገራ ፈረስን ሊቆጣጠር አይችልም፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

አንገቱን በጋማ ትሸፍናለህን?

ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "አንገቱን በጋማ ልትሸፍን አትችልም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

አንገቱን በጋማ ልትሸፍን

የፈረስ "ጋማ" የተገለጸው የፈረስን አንገት እንደሚሸፍን ልብስ ተደርጎ ነው፡፡ "ጋማው አንገቱን እንደ ልብስ ይሸፍናል" (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በአንገቱ ላይ የወረደው ጋማ

በፈረሱ አንገት ላይ የሚገኘው ረጅም ፀጉር

በእውኑ አንተ እንደ አንበጣ እንዲፈናጠር ልታደርገው ትችላለህን?

ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "አንተ እንደ አንበጣ እንዲዘል ልታደርገው አትችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ትልቅ አንበጣ

በጣም በፍጥነት እና በጣም ሩቅ ሊዘል የሚችል ትልቅ የአንበጣ አይነት

ማሽካካት/ማንኮራፋት

ፈረሶች በአፍኝጫቸው የሚያወጡት በጣም ጉልህ ድምጽ

Job 39:21-23

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

እርሱ ይጎደፍራል/መሬቱን ይመታል

"እርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ፈረስን ነው፡፡ ፈረሱ ምድርን በእግሩ ይመታል/ይጎደፍራል ምክንያቱም ምግያው እንዲጀምር በጣም ቸኩሏል፡፡ "በጉጉት መሬቱን ይመታል ደግሞም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

መጎድፈር

"በኮቴው መሬቱን መቆፈር/መምታት"

መሳሪያውን ለማግኘት

እዚህ ስፍራ "መሳሪያ" የሚለው የሚወክለው ለጦርነቱ የሚጠቀሙበትን ነው፡፡ "ወደ ጦርነት ለመግባት" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

በፍርሃት ላይ ያፌዛል

"በፍጹም አይፈራም"

ያፌዛል

"ይስቃል"

መጨነቅ

"ተስፋ መቁረጥ"

ወደ ኃላ አይመለስም

"አይሸሽም"

ኮሮጆ

ፍላጻዎችን መያዣ

ማስፈራራት

መርገፍገፍ እና ድምጽ ማሰማት

ሽንጥ

የፈረሱ ጎን

ጦር

ሰዎች በጠላቶቻቸው ላይ የሚወረውሩት ጫፉ ሹል የሆነ ብረት ያለው ረጅም በትር

Job 39:24-25

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

እርሱ

"እርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ፈረስን ነው፡፡

ምድርን ይውጣል

የፈረሱ በምድር ላይ በፍጥነት መሮጥ ሰው ውሃን ሲጠጣ በፍነት ጭልጥ እንደሚያደርግ ፍጥነቱ ተገልጽዋል፡፡ "በምድር ላይ በፍጥነት ይሮጣል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመለከቱ)

በሃይል እና በቁጣ

ፈረሱ ስለጓጓ በፍጥነት እና በጥንካሬ ይንቀሳቀሳል

በመለከት ድምጽ

አንድ ሰው መለከት እንደሚነፋ ተደርጎ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ጦርነት መጀመሩን ለማወጅ አንድ ሰው መለከት ሲነፋ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

በአንድ ስፍራ መቆም አይችልም

"በአንድ ስፍራ ተረጋግቶ መቆም አይችልም/ይቅበጠበጣል"

አሃ፣ ይላል

"አሃ" የሚለው ቃል ሰዎች አንድ ነገር ሲያገኙ የሚያወጡት ድምጽ ነው፡፡ ፈረስ ድምጽ የሚያወጣው ጦርነት መኖሩን በማወቁ ምክያት ነው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ነጎድጓዳዊ ጩኸት

ይህ የሚያመለክተው ፈረሱ እነዚህን ነገሮች መስማቱን ነው፡፡ "እርሱ ነጎድጓዳዊ ጩኸቱን ሰምቷል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

ፉከራ

"የጦርነት ጩኸት፡፡" ሰዎች በጦርነት ጊዜ ጅግንነታቸውን እና ብርታታቸውን ለማሳየት እንዲሁም ጠላቶቻቸውን ለማስፈራራት የሚያሰሙት የተለየ ጩኸት አለ

Job 39:26

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

ወደ ደቡብ… ይህ በአንተ ጥበብ ነውን?

ያህዌ ይህን ጥያቄ የተጠቀመው ኢዮብ እንደ ያህዌ ታላቅ አለመሆኑን ለማረጋገጥ ነው፡፡ ለዚህ ጥያቄ በውስጠ ታዋቂነት የሚሰጠው ምላሽ "አይደለም" የሚል ነው፡፡ "ወደ ደቡብ…ይህ በአንተ ጥበብ አይደለም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ክንፎቹን ወደ ደቡብ የሚዘረጋው

እዚህ ስፍራ ክንፎችን መዘርጋት የሚያመለክተው መብረርን ነው፡፡ "ወደ ደቡብ መብረር" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

ወደ ደቡብ

በመጽሐፍ ቅዱሳዊው መልከአምድር ወፎች በክረምት በሞቃታማ የአየር ንብረት ለመኖር ወደ ደቡብ ይበራሉ፡፡

Job 39:27-28

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

ጎጇቸውን በከፍታ ስፍራ የሚሰሩት … በአንተ ትዕዛዝ ነውን?

ያህዌ ይህንን ጥያቄ የተጠቀመው ኢዮብ ንስሮችን ለማዘዝ አቅም እንደሌለው ለማረጋገጥ ነው፡፡ ለዚህ ጥያቄ በውስጠ ታዋቂነት የሚሰጠው ምላሽ "አይደለም" የሚል ነው፡፡ "አንተ ንስር በከፍታ ስፍራ ቤቱን እንዲሰራ ልታዝዘው አትችልም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

በአንተ ትዕዛዝ

"ትዕዛዝ" የሚለው ረቂቅ ስም በግስ መልኩ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እንዲህ እንዲያደርግ አንተ ስለ ነገርከው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ከፍ ብሎ እንዲወጣ

ይህ ማለት ወደ ላይ ይበራል ማለት ነው፡፡ "ወደ ሰማይ ይበራል" (ፈሊጣዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ጠንካራ ምሽግ

ታላቁ ገደል ለንስር ጠንካራ ምሽጉ ነው፤ ምክንያቱም ሊበላው የሚፈልገው እንስሳ ወደዚያ ስፍራ ሊደርስ አይችልም፡፡

Job 39:29-30

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

እርሱ የሚያድነውን ይፈልጋል

እዚህ ስፍራ "እርሱ" የሚለው የሚያመለክተው ንስርን ነው፡፡

የሚያድነው

"ገድሎ የሚመገበው እንስሰ"

የእርሱ ዐይኖች ይመለከቷቸዋል

እዚህ ስፍራ "የእርሱ ዐይኖች" የሚለው የሚያመለክተው ንስሩን ነው፡፡ "እርሱ ይመለከታቸዋል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ጫጩቶቹ

"ትንንሽ ንስሮች፡፡" ይህ የሚሆነው ንስር አድኖ ከገደለ በኋላ መሆኑን መግለጹ አስፈላጊ ሊሆን ይችላል፡፡ "ንስሩ አድኖ ከገደለ በኋላ፣ ጫጩቶቹ ንስሮች"

ደም ይጠጣል

"የገደለውን እንስሳ ደም ይጠጣል"

በድን ባለበት

"የሞቱ ሰዎች ባሉበት፡፡" ይህ ሀረግ የሚያመለክተው ምድር ውስጥ የተቀበሩትን ሳይሆን በሜዳ ላይ የወደቁትን በድኖች ነው፡፡

በዚያ እርሱ ይገኛል

ይህ በድን ለመብላት እንደሚመጣ ግልጽ ተደርጎ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "እነርሱን ለመብላት በዚያ አለ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ይሆናል ተብሎ የሚገመት ዕውቀት እና በውስጠ ታዋቂነት የሚገኝ መረጃ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 40

Job 40:1-2

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

ሁሉን ቻይ የሆነውን እንዲህ አድርግ ለማለት መድፈር የሚችል አለን?

ያህዌ ኢዮብን እየገሰጸው ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ማንም ቢሆን እኔን ለመንቀፍ ወይም ከእኔ ጋር ለመከራከር መሞከር የለበትም፣ እኔ ሁሉን ቻይ አምላክ ነኝና፡፡" ወይም "አንተ ሰው ሆነህ ሳለ፣ ሁሉን ቻይ አምላክ የሆንኩትን እኔን ለመንቀፍ ትፈልጋለህ፤ ደግሞም እኔን ለማረም መሞከር የለብህም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ከእግዚአብሔር ጋር የሚከራከር፣ እርሱ ምላሽ ይስጥ

ያህዌ ስለ ራሱ እና ስለ ኢዮብ ሌሎች ሁለት ሰዎች እንደሆኑ እና በየትኛውም ስፍራ የሚገኝ ማንኛም ሰው ከእግዚአብሔር ጋር መከራከር እንደሌለበት አድርጎ ይናገራል፡፡ "ከእኔ ጋር ትከራከራለህን፣ እንግዲያውስ መልስልኝ" (ተውላጠ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

Job 40:3-5

እነሆ እኔን ተመልከት

"እኔ መሆኔን ስትናገር አልተሳሳትክም" ወይም "እኔን ተመልከት እኔ መሆኔን ታያለህ"

እኔ ዋጋ የለኝም

"እኔ ጠቃሚ አይደለሁም"

እንዴት መልስ ልሰጥህ እችላለሁ?

ኢዮብ ይህንን ጥያቄ የሚጠቀመው እግዚአብሔርን በመሟገቱ/በመጠየቁ ምህረት ለመለመን ነው፡፡ "እኔ መልስ ልሰጥህ አልችልም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 40:6-7

እንደ ወንድ ወገብህን ታጥቀህ ተዘጋጅ

ቀበቶውን የታጠቀ ወንድ ለብርቱ ስራ የተዘጋጀ ነው፤ ኢዮብ ለእግዚአብሔር መልስ መስጠትን ለመሰለ ከባድ ስራ መዘጋጀት ነበረበት፡፡ ይህ በኢዮብ 38፡3 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ተመልከቱ፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ እና ዘይቤያዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 40:8-9

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገዳደሩን/መጠየቁን ቀጥሏል

በእርግጥ እኔን ትክክል አይደለህም ትላለህን?

"በእርግጥ" የሚለው ቃል ኢዮብ እርሱን ትክክል አይደለህም በማለቱ መደነቁን እና በእርግጥም ይህን ለማለት መፈለጉን እንዲያረጋግጥ እየጠየቀው መሆኑን ያመለክታል፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "እኔን ትክክል አይደለህም በማለትህ ተገርሜያለሁ" ወይም "እኔን ትክክል አይደለህም ለማለት መፈለግህን እርግጠኛ መሆን አለብህ፣ ምክንያቱም እያልክ ያለኸው ያንን ነው፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ራስህን ትክክለኛ አድርገህ እኔን ትኮንናለህን?

ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ራስህን ንጹህ አድርገህ በመቁጠር እኔን መኮነን ትችላለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

የእግዚአብሔርን ክንድ የመሰለ

ክንድ የሚለው በክንድ ውስጥ ለሚገኝ ጥንካሬ ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "እንደ እግዚአብሔር ጥንካሬ ብርቱ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚውን ይመልከቱ)

እንደ እርሱ በድምጽ መብረቅ ታወጣለህ?

ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "እግዚአብሔር በድምጹ እንደሚያርደው አንተ በእርግጥ በድምጽህ መብረቅ ማብረቅ አትችልም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ እና ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

እንደ እርሱ ድምጽ ያለ

"እርሱ በሚያደርግበት መንገድ እንዳለ ድምጽ" ወይም "እንደ እርሱ ድምጽ ያለ ድምጽ"

Job 40:10-11

ሰው እንደሚለብሰው ልብስ አድርገህ ራስህን በክብር እና በማዕረግ አጎናጽፍ፤ በሞገስ እና ግርማ አዘጋጅ

"ክብር፣" "ማዕረግ፣" "ሞገስ፣" እና "ግርማ" የሚሉት ረቂቅ ስሞች የተነገሩት ሰው እንደሚጎናጸፈው ልብስ ተደርገው ነው፡፡ እንደ ቅጽሎች እና ግሶች ሆነው ሊተረጎሙ ይችላሉ፡፡ "ራስህን ክቡር አድርግ፤ ሰዎች ያከብሩህ እና ከፍ ከፍ ያደርጉህ ዘንድ አንዳች ታላቅ ነገር አድርግ፤ ደግሞም ሰዎች እንደ ታላቅ ንጉስ እንዲመለከቱህ አድርግ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ረቂቅ ስሞች የሚሉትን ይመልከቱ)

የበዛውን ቁጣህን አፍስስ

"ቁጣ" የሚለው ረቂቅ ስም ብዙጊዜ የሚገለጸው በአንዳች መያዣ ነገር እንደሚያዝ ተደርጎ ነው፣ በዚህ ሁኔታ ግን አብሮ ሊሄድ የማይችለው በዙሪያ የሚፈስ ብዙ ነገር እንዳለው ተደርጎ፡፡ ይህ ሲበሳጭ ለሚወስደው እርምጃ ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ ለምን እንደሚቆጣ ግልጽ ማድረግ ሊያስፈልግ ይችላል፡፡ "ሰዎች ስለሚኮሩ እና ስለሚቀጣቸው በዚህ ምክንያት ይቆጣል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ረቂቅ ስሞች እንዲሁም ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚሉትን ይመልከቱ)

አዋርደው

"የሚኮራበትን ነገር ሁሉ ውሰድበት"

Job 40:12-14

የእነርሱን ፊቶች

"ፊት" የሚለው የሚወክለው ሰውየውን ነው፡፡ "እነርሱ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ስኔክቲክ/ የአንድን ነገር ስያሜ ከፊሉን በመውሰድ መላውን ነገር መግለጽ የሚለውን ይመልከቱ)

ስውር ስፍራ

ሰዎች ሲሞቱ መንፈሳቸው ስለሚሄድበት ስፍራ በዩፊሚዝም/የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት/ የቀረበ አገላለጽ፡፡ (ዩፊምዝም/ የማያስደስትን ቃል ሻል ባለ ቃል መተካት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 40:15-16

ብሄሞት

ትልቅ ውሃ ውስጥ የሚኖር እንስሳ፣ ምናልባት ጉማሬ ሊሆን ይችላል

እርሱ ይበላል

ብሄሞት ይበላል

እንደ በሬ ሳር ይበላል

ብሄሞትም በሬም ሁለቱም ሳር ይበላሉ፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የወገብ… የሽንጥ/ሆድ ጡንቻዎች

እነዚህ ሁለት ሀረጎች ተመሳሳይ የሰውነት ክፍልን ይገልጻሉ

Job 40:17-18

እንደ ጥድ

ጥድ በጣም ጠንካራ እንጨት ነው፣ እናም የጉማሬው ጭራ እንደ ጥድ በጣም ጠንካራ ነው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ናስ ቱቦዎች

እዚህ ስፍራ፣ የእንስሳውን ጥንካሬ ለመግለጽ አጥንቶቹ የተነጻጸሩት ከናስ ከተሰራ ቱቦ ጋር ነው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ ብረት መቀርቀሪያዎች

ይህ የመጨረሻው ማነጻጸሪያ የሚገልጸው የዚህን ትልቅ እንስሳ ጥንካሬ ነው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 40:19-21

የፍትረት አለቃ/ዋና

"ከፍጥረታት ሁሉ ዋናው" ወይም "ከፍጥረታት በጣም ጠንካራው"

የፍጥረታት አምላክ፡፡ እግዚአብሔር ብቻ

ያህዌ ራሱን እንደ ሌላ አካል አድርጎ ይናገራል፡፡ "የእኔ ፍጥረቶች፡፡ እኔ ብቻ፣ እግዚአብሔር" (ተውላጠ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ኮረብቶች ምግብ ያበቅሉለታል

ኮረብቶች የተገለጹት ምግብ መስጠት እንደሚችሉ ሰዎች ተደርገው ነው፡፡ "ለእርሱ በኮረብቶች ምግብ ይበቅላል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አስደሳች ተክሎች

በረግረጋማ አካባቢዎች በውሃ ላይ የሚበቅሉ አበባማ ተክሎች

ቄጠማ

በረግረጋማ ወይም አረንቋማ ስፍራ የሚገኝ ረጅም ሳር

Job 40:22-24

አስደሳች ተክሎች

በረግረጋማ አካባቢዎች በውሃ ላይ የሚበቅሉ አበባማ ተክሎች፡፡ ይህ በኢዮብ 40፡19 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

የወንዝ ዳርቻ ዛፍ

የወንዝ ዳርቻ ዛፎች በረግረጋማ ስፍራ የሚበቅሉ ትላልቅ ዛፎች ናቸው፡፡ በእናንተ ባህል ውስጥ የማይታወቁ ከሆኑ፤ በውሃ ዳር የሚበቅል ዛፍን ስም መጠቀም ትችላላችሁ፡፡

የወንዝ ዳርቻ

በወንዝ ዳርና ዳር

ዮርዳኖስ ከአፍ እስከ ገደፉ ቢሞላም

"ምንም እንኳን የዮርዳኖስ ወንዝ እስከ አፉ ቢሞላም"

አጥምዶ…በመንጠቆ ሊይዘው የሚችል አለን?

ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "ማንም በመንጠቆ ወይም በወጥመድ አፍንጫውን ሊይዝ አይችልም፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 41

Job 41:1-3

አጠቃላ መረጃ፡

እግዚአብሔር መናገሩን ቀጥሏል፡፡ ኢዮብን ለመገገዳደር ብዙ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄዎችን ይጠቀማል

አሳ በሚያዝበት መንጠቆ ሌዋታንን አጥምደህ ልታወጣው ትችላለህ?

እግዚአብሔር ይህንን ጥያቄ የተጠቀመው ኢዮብ እንደ ሌዋታን ጠንካራ አለመሆኑን ሊያስታውሰው ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊገለጽ ይችላል፡፡ "አሳ በሚጠመድበት መንጠቆ ሌዋታንን ማጥመድ እንደማትችል ታውቃለህ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

አጥምደህ ልታወጣው

ከውሃ ውስጥ ልታወጣው

የእርሱ…እርሱ

"የእርሱ" እና "እርሱ" የሚሉት ቃላት ሌዋታንን ያመለክታሉ፡፡

ወይስ በገመድ/ሲባጎ መንጋጋውን ታስራለህ?

"አንተ ትችላለህን?" የሚሉት ቃላት ከቀደመው ጥያቄ በመነሳት ሊታወቁ የሚችሉ ናቸው፡፡ እዚህ ስፍራ ሊደገሙ ይችላሉ፡፡ እግዚአብሔር ይህንን ጥያቄ ኢዮብ እንደ ሌዋታን ጠንካራ አለመሆኑን ሊያስታውሰው ተጠቅሞበታል፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ወይንስ መንጋጋውን በሲባጎ ልታስር ትችላለህን?" ወይም "ደግሞም መንጋጋውን በሲባጎ ማሰር እንደማትችል ታውቃለህ፡፡" (የተዘለለ/የተተወ እና ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚሉትን ይመልከቱ)

በአፍንጫው ውስጥ ገመድ ማስገባት… በመንጠቆ ልታጠምደው ትችላለህን?

እግዚአብሔር ይህን ጥያቄ የተጠቀመው ኢዮብ እንደ ሌዋታን ሀይለኛ አለመሆኑን ሊያስታውሰው ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "በመንጠቆ እንደማትይዘው…በሌዋታን አፍንጫ ገመድ ማስገባት እንደማትችል ታውቃለህ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ለአንተ ብዙ ልመና ያቀርባልን?

እግዚአብሔር ይህን ጥያቄ የተጠቀመው ኢዮብ እንደ ሌዋታን ሀይለኛ አለመሆኑን ሊያስታውሰው ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ " ለአንተ ልመና እንደማያቀርብልህ ታውቃለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ለአንተ ለስላሳ ቃላትን ይናገራል?

እግዚአብሔር ይህን ጥያቄ የተጠቀመው ኢዮብ እንደ ሌዋታን ሀይለኛ አለመሆኑን ሊያስታውሰው ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ለአንተ ለስላሳ ቃላትን እንደማይናገር ታውቃለህ፡፡" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 41:4-6

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገሰጹን ቀጥሏል፡፡ እርሱ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የተጠቀመው ኢዮብ እንደ ሌዋታን ጠንካራ አለመሆኑን ሊያስታውሰው ነው፡፡

ለዘለዓለም አገልጋዩ እንድታደርገው እርሱ ከአንተ ጋር ቃለኪዳን ይገባል?

ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ለዘለአለም አገልጋይህ እንድታደርገው ከአንተ ጋር ቃለኪዳን እንደማይገባ ታውቃለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ… የእርሱ

"እርሱ" እና "የእርሱ" የሚሉት ቃላት ሌዋታንን ያመለክታሉ፡፡

ከወፍ ጋር እንደሚጫወት ከእርሱ ጋር ትጫወታለህን?

ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ከወፍ ጋር እንደምትጫወት ከእርሱ ጋር መጫወት እንደማትችል ታውቃለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ለአገልጋይ ልጃገረዶችህ እርሱን ማሰር ትችላለህን?

ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ለአገልጋይ ልጃገረዶችህ እርሱን ማሰር እንደማትችል ታውቃለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

አሳ አጥማጆች ከእርሱ ጋር መደራደር ይችላሉን?

ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "አሳ አጥማጆች ከእርሱ ጋር ሊደረደሩ እንደማይችሉ ታውቃለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

በነጋዴዎች መሃል ሊነግዱበት እርሱን ይከፋፈላሉን?

ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "እርሱን ሊነግዱት በማህላቸው እንደማይከፋፈሉት ታውቃለህ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እነርሱ ይከፋፈሉታል

"አሳ አጥማጅ ቡድኖች ይከፋፈሉታል"

Job 41:7-9

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ኢዮብን መገሰጹን ቀጥሏል፡፡ እርሱ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የተጠቀመው ኢዮብ እንደ ሌዋታን ጠንካራ አለመሆኑን ሊያስታውሰው ነው፡፡

ቆዳውን በአንካሴ ወይም ጭንቅላቱን በአሳማጥመጃ ጦር ልትወጋው ትችላለህ?

ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ቆዳውን በአንተ ማደኛ መሳሪያ ልትበሳው አትችልም፣ አሊያም ጭንቅላቱን በአሳ ማጥመጃ ጦር ልትበሳው አትችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ… የእርሱ

"እርሱ" እና "የእርሱ" የሚሉት ቃላት ሌዋታንን ያመለክታሉ፡፡

አንካሴዎች

ሰዎች ትላልቅ የውሃ ውስጥ ፍጥረታትን ለማደን የሚጠቀሙባቸው ሹል ጫፍ ያላቸው ረጃጅም ጦሮች

እነሆ

"ተመልከት" ወይም "ስማ" ወይም "ቀጥሎ ለምነግርህ ትኩረት ስጥ"

በእይታው ብቻ ማንም ቢሆን ምድር ላይ አይወድቅምን?

ይህ ማጠቃለያ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ወደ እርሱ የሚመለከት ምድር ላይ እስኪወድቅ ድረስ እጅግ በፍርሃት ይዋጣል" (አድራጊ ወይም ተደራጊ እና ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚሉትን ይመልከቱ)

እርሱን ማየት

"ወደ እርሱ በመመልከት" ወይም "እርሱን በማየት"

Job 41:10-12

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ በመጠየቅ ኢዮብን መገሰጹን ቀጥሏል፡፡ እርሱ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የተጠቀመው ያህዌ ከሌዋታንም ሆነ ከኢዮብ ይልቅ እጅግ ጠንካራ መሆኑን ሊያስታውሰው ነው፡፡

ማን ሌዋታንን ሊደፍር ይችላል፣ ታዲያ ይልቁን በእኔ ፊት ማን ሊቆም ይችላል?

በያህዌ ፊት ከመቆም ሌዋታንን መንካት ቀላል ይሆናል፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ማንም ሌዋታንን ሌዋታንን ለመንካት እንደማይደፍር ታውቃለህ፣ ይልቁንም ማንም በፊቴ ሊቆም እንደማይደፍር በእርግጠኝነት ማወቅ ይኖርብሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ለእርሱ እመልስለት ዘንድ አስቀድሞ አንዳች ነገር ለእኔ የሰጠኝ ማን ነው?

ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ማንም ለእኔ አስቀድሞ አንዳች ነገር እንዳልሰጠኝ ታውቃለህ፣ ስለዚህም እኔ መልሼ ልከፍለው የሚገባኝ ማንም የለም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ… የእርሱ

"እርሱ" እና "የእርሱ" የሚሉት ቃላት አንድን ሰው ያመለክታሉ፡፡

… በተመለከተ ዝም አልልም…አሊያም ስለ… አሊያም ስለ

ይህ በአዎንታዊ መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "በእርግጥ እኔ ስለ…በእርግጠኝነት እናገራለሁ… እና ስለ…እና ስለ…" (ምፀት የሚለውን ይመልከቱ)

የሌዋትንን እግሮች በተመለከተ፣ አሊያም ስለ እርሱ ጥንካሬ፣ አሊያም ስለ አስፈሪ መልኩ

እነዚህ እግዚአብሔር ዝም የማይልባቸው ነገሮች ናቸው

የእርሱ

"የእርሱ" የሚለው ቃል ሌዋታንን ያመለክታል

Job 41:13-15

አያያዥ ሀሳብ፡

ያህዌ ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ በመጠየቅ ኢዮብን መገሰጹን ቀጥሏል፡፡

ውጫዊ ሽፋኑን ማን ሊያስወልቀው ይችላል?

ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ማንም ውጫዊ ልብሱን ሊያስወልቀው አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሱ

"የእርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሌዋታንን ነው፡፡

ድርብ የጦር ልብሱን ማን ሊበሳው ይችላል?

"የጦር ልብስ" የሚለው ጠንካራ ቅርፊች ወይም የጀርባው ቆዳ ለሚለው ዘይቤ ነው፡፡ ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ማንም ቢሆን በጣም ወፍራም ቆዳውን ሊበሳ አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር እና ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚሉትን ይመልከቱ)

አስፈሪ የሆነውን…ማን የአፉን ደጅ ሊከፍት ይችላል?

ይህ ጥያቄ በዐረፍተ ነገር መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ማንም አስፈሪ… መንጋጋውን መክፈት አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

ጋሻዎች

"ጋሻዎች" የሚለው ቃል ለሌዋታን ጠንካራ ቆዳ ዘይቤያዊ አገላለጽ ነው፡፡ ጋሻዎች እና የሌዋታን ቆዳ የሚሉት ሁለቱም ቀስቶችን የሚመክቱ እና ከሌሎችም መሳሪያዎች የሚከላከሉ ናቸው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

ተገጣጥመው እርስ በእርስ የተቀራረቡ ናቸው

ይህ ማለት "ጋሻዎቹ" እርስ በእርሳቸው የተቀራረቡ በመሆናቸው በመሃላቸው ምንም ነገር ሊገባ አይችልም፡፡

Job 41:16-18

አንዱ ወደ ሌላው እጅግ የቀረበ ነው

በአንዱ ረድፍ ሚገኙት ጋሻዎች ከሌላው ጋር እጅግ ቅርብ ነው፡፡ (ኢዮብ 41፡15)

የእነርሱ…እነርሱ

"የእነርሱ" እና "እነርሱ" የሚሉት ቃላት በመስመር የተደረደሩ ጋሻዎችን ያመለክታሉ፡፡ (ኢዮብ 41፡15)

ለየብቻ ሊለያዩ አይችሉም

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ማንም ሊገነጣጥላቸው አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ከመደንፋቱ/ከማሽካካቱ

"ሲደነፈፋ/ሲያሽካካ፡፡" በመኝታ ከሚሰማ አጭር ማንኮራፋት ጋር ይመሳሰላል፡፡ ሊሰጥ የሚችለው ሌላ ትርጉም "ከማስነጠሱ ጋር" ወይም "ሲያስነጥስ" የሚል ነው፡፡

ዐይኖቹ የንጋት ሽፋሽፍትን ይመስላሉ

ይህ ማለት ዐይኖቹ የማለዳ ሰማይ እንደሚቀላ የቀሉ ናቸው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

የእርሱ

"የእርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሌዋታንን ነው፡፡

Job 41:19-21

ከአፉ የሚነድ ችቦ ይወጣል፣ የእሳት ብልጭታ ይፈናጠራል

እግዚአብሔር በሌዋታን አስፈሪ መልክ ላይ ትኩረት ለመስጠት ተመሳሳይ ሀሳብን በሁለት የተለያዩ መንገዶች ይገልጻል፡፡ ይህንን የተተወውን ቃል በመጨመር ግልጽ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡ "ከአፉ የሚነድ ችቦ ይወጣል እና የእሳት ብልጭታ ይወጣል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ትይዩ ንጽጽራዊ ዘይቤ እና የተዘለለ/የተተወ የሚሉትን ይመልከቱ)

የእርሱ

"የእርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሌዋታንን ነው፡፡

አፍንጫዎቹ

የአፍንጫው ሁለቱ ቀዳዶች

እንደሚፈላ ገንቦ የሚጤስ

ጢስ እና የሚፈላ ገንቦ ሁለቱም በጣም ሞቃት ናቸው፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ከሰል ወደ ፍምነት ይቀጣጠላል

"ከሰል ፍም እንዲሆን"

Job 41:22-24

የእርሱ…እርሱ

"የእርሱ" የሚለው ቃል የሚያመለክተው ሌዋታንን ነው፡፡

ፍርሃት በፊቱ ያሸበሽባል

"ፍርሃት" የሚለው ረቂቅ ስም "ፈራ" በሚል ግስ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ሰዎች እርሱ ሲመጣ ሲመለከቱ፣ በጣም ይፈራሉ" (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ሊንቀሳቀሱ አይችሉም

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ማንም ሊያንቀሳቅሳቸው አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ልቡ እንደ ድንጋይ ጠንካራ ነው

አለት ወይም ድንጋይ ተለውጦ ለስላሳ አይሆንም፡፡ ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1)የሌዋታን ደረቱ እና በውስጡ ያሉ አካላት ጠንካራዎች ናቸው ወይም 2)ሌዋታን አንዳች ነገር አይፈራም ወይም 3) ሌዋታን የተገለጸው ያለ አንዳች ርህራሄ እንደሚገድል ሰው ተደርጎ ነው፡፡ (ተነጻጻሪ እና ሰውኛ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

የታችኛው ድርብርብ አለት

"ከአለቶች ሁሉ ይበልጥ ጠንካራ የሆነው፡፡" የታችኛው አለት ትልቅ እና ለእህል ወፍጮነት የሚያገለግል ከሁለቱ የላይኞቹ አለቶች ጠንካራ የሆነው ነው፡፡ ሰዎች ሊያገኙ ከሚችሏቸው አለቶች እጅግ ጠንካራዊ ነው፡፡

Job 41:25-27

እርሱ… እርሱ ራሱ…የእርሱ

"እርሱ፣" "እርሱ ራሱ" እና "የእርሱ" የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት ሌዋታንን ነው፡፡

አማልዕክቱ

ሊሰጡ የሚችሉ ትርጉሞች 1) "ታላላቅ ሰዎች" ወይም 2) "በጣም ጠንካራ ሰዎች"

ብረትን እንደ ገለባ ይቆጥራል

"ከብረት የተሰሩ መሳሪያዎችን ከገለባ እንደተሰሩ ይቆጥራቸዋል፡፡" ገለባ ቆዳውን አልፎ ሊገባ እንደማይችል ያህል፣ የብረት መሳሪያዎች ቆዳውን ሊበሱት አይችሉም/ ብረትን እንደ ገለባ ይቆጥራል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

ነሐስን ብል እንደበላው እንጨት ይቆጥራል

ይህንን የተተዉ ቃላትን በመጨመር ግልጽ ማድረግ ይቻላል፡፡ "ከነሐስ የተሰሩ መሳሪያዎችን ብል በበላው እንጨት እንደተሰሩ ይቆጥራቸዋል" (የተዘለለ/የተተወ እና ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚሉትን ይመልከቱ)

Job 41:28-30

ለእርሱ የወንጭፍ ድንጋይ ገለባ ይሆንለታል

ገለባ ሌዋታንን ሊጎዳው አይችልም፣ እንደዚሁም የወንጭፍ ድንጋይ ልክ እንደ ገለባ ሁሉ የማይጎዳው ይሆናል፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይመልከቱ)

እርሱ… እርሱ ራሱ…የእርሱ

"እርሱ፣" "እርሱ ራሱ" እና "የእርሱ" የሚሉት ቃላት የሚያመለክቱት ሌዋታንን ነው፡፡

በትርን እንደ ገለባ ይቆጠራል

ከገለባ የተሰራ መምቻ እርሱን ሊጎዳው እንደማይችል ሁሉ ከእንጨት የተሰራም በትር አይጎዳውም፡፡ ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊጻፍ ይችላል፡፡ "ዱላን እንደ ገለባ ይቆጥራል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

በተሰበቀ ጦር ላይ ይስቃል

ጦር የወረወረ ሰው ጦሩ ሌዋታንን እንደሚገድል ተስፋ ያደርጋል፣ ነገር ግን ጸሐፊው የሚገልጸው ሌዋታን ጦሩ እንደማይገድለው እንደሚያውቅ እና በተወረወረው ጦር እንደሚስቅ አድርጎ ነው፡፡ (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

እንደ መውቃያ መሳሪያ በጭቃ ውስጥ ምልክት ጥሎ ያልፋል

የመውቂያ መሳሪያ የሚወቃውን እህል እንደሚያደቅ፣ ሌዋታ ጭራውን እያወዛወዘ ሲራመድ በጭቃ ላይ ምልክት እያደረግ ያልፋል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 41:31-32

ጥልቁን በማሰሮ እንደሚፈላ ውሃ አረፋ ያደርገዋል

"በውሃ ውስጥ ሲያልፍ፣ ከኋላው በማሰሮ እንደሚፈላ ውሃ አረፋ እየተው ይሄዳል"

እርሱ

"እርሱ" የሚለው ቃል ሌዋታንን ያመለክታል፡፡

ባህሩን በገንቦ እንዳለ ቅባት ያደርገዋል

በገንቦ ውስጥ ያለ ቅባት አንድ ሰው ቢበተብጠው ይደፈርሳል፣ እንደዚሁ ሌዋታን ሲዋኝበት ባህሩ ይደፈርሳል፡፡ (ተነጻጻሪ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

አንድ ሰው ጥልቁ ሽበት እንዳለው አድርጎ ሊያስብ ይችላል

ይህ የሚሆንበት ምክንያት ያንቀሳቀሰው ውሃ አረፋ ስለሚነጣ ነው

Job 41:33-34

ለእርሱ አቻ የለውም

"የትኛውም ፍጥረት እንደ ሌዋታን አይደለም"

እርሱ ኩራተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ ይመለከታል

"እርሱ በጣም፣ በጣም ኩራተኛ ነው"

የእርሱ… እርሱ

"የእርሱ" እና "እርሱ" የሚሉት ቃላት ሌዋታንን ያመለክታሉ፡፡

እርሱ በኩራት ልጆች ላይ ሁሉ ንጉሥ ነው

ሌዋታን የተገለጸው ንጉሥ ሊሆን እና ሊኮራ እንደሚችል ሰው ተደርጎ ነው፡፡ "ሌዋታን በምድር ላይ ከማንም ይልቅ ሊኮራ የሚችልበት የበለጠ ምክንያት አለው" (ሰውኛ ዘይቤ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 42

Job 42:1-3

አንተ ሁሉንም ነገሮች መስራት እንደምትችል አውቃለሁ፣ ከስራዎችህ አነዱም ሊገታ አይችልም

"እኔ አውቃለሁ" የሚሉትን ቃላት መድገም ልትፈልግ ትችላለህ፡፡ "ሁሉንም ነገሮች መስራት እንደምትችል አውቃለሁ፡፡ የትኛውም ተግባርህ ሊገታ እንደማይችል አውቃለሁ" (የተዘለለ/የተተወ የሚለውን ይመልከቱ)

የትኛውም ተግባርህ ሊገታ አይችልም

ይህ በአድራጊ ዐረፍተ ነገር ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ማንም ከእቅዶችህ አንዱንም ማስቆም አይችልም" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (አድራጊ ወይም ተደራጊ የሚለውን ይመልከቱ)

ይህ ማን ነው

ዩኤልቢ እና በርካታ ዘመናዊ ቅጅዎች ኢዮብ ከ መጽሐፈ ኢዮብ 38፡2 ላይ እንደጠቀሰ ይስማማሉ፡፡ እናንተም ሃሳቡን ግልጽ ለማድረግ በዩዲቢ እንደቀረበው እግዚአብሔር ኢዮብን ይህንን ጥያቄ እንደ ጠየቀው እና ኢዮብ አሁን ይህንን እንደሚያስታውስ መወሰን ትችላላችሁ፡፡ "አንተ ለእኔ፣ ‘ይህ ማን ነው' ብለሃል" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ቃለ ምልልሳዊ ጥያቄ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 42:4-6

ነገር ግን አሁን ዐይኖቼ አንተን አይተዋል

ዐይኖች ማየትን ይወክላሉ፣ ማየት ደግሞ መረዳትን ይወከወላል፡፡ "ነገር ግን አሁን እኔ በእርግጥ አንተን እረዳለሁ/አውቃለሁ" (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይምልከቱ)

ራሴን እንቃለሁ

የኢዮብ እኔነት/ራሱ ለተናገረው ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ / ነው፡፡ "የተናገርኳቸውን ነገሮች እንቃለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

መናቅ

ጥልቅ የሆነ መጥላት

በአፈር እና በአመድ ላይ ተቀምጬ ንስሃ እገባለሁ

በአፈር እና በአመድ ላይ መቀመጥ ሰውየው ማዘኑን የሚገልጽ ምልክታዊ ድርጊት ነው፡፡ (ትምዕርታዊ/ምልክታዊ ድርጊት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 42:7-9

እንዲህም ሆነ

ይህ ሀረግ እዚህ ስፍራ የዋለው ጠቃሚ የሆነ ትዕይንት ወደ ታሪኩ ውስጥ መግባቱን ለማመልከት ነው፡፡ በእናንተ ቋንቋ ይህን መግልጽ የምትችሉበት መንገድ ካለ ይህን እዚህ ላይ መጠቀም ትችላላችሁ፡፡

ቴማናዊው ኤልፋዝ

ይህ የወንድ ስም በኢዮብ 2፡11 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

ቁጣዬ በእናንተ ላይ ነድዷል

እሳት ቁጣን ለመግለጽ የዋለ ዘይቤ ነው፡፡ እሳት መለኮስ ለመቆጣት ዘይቤ ነው፡፡ "እኔ በእናንተ ላይ እጅግ ተቆጥቻለሁ" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ዘይቤያዊ አነጋገር የሚለውን ይምልከቱ)

ሰባት ኮርማዎች

"7 ኮርማዎች" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

የሰራችሁትን አሳፋሪ ጥፋት እምር ዘንድ

"አሳፋሪ ጥፋት" የሚለው ረቂቅ ስም በቅጽል መልክ ሊተረጎም ይችላል፡፡ "ምንም እንኳን ያደረጋችሁት ሞኝነት ቢሆንም፣ የሚገባችሁን ቅጣት አልቀጣችሁም" (ረቂቅ ስሞች የሚለውን ይመልከቱ)

ሹሐዊው በልዳዶስ

ይህ የወንድ ስም በኢዮብ 2፡11 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

ናዕማታዊው ሶፋር

ይህ የወንድ ስም በኢዮብ 2፡11 ላይ እንዴት እንደ ተተረጎመ ይመልከቱ፡፡

ያህዌ ኢዮብን ተቀበለው

ሰውየው ለጸለየው ጸሎት ሜቶኖሚ/ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት/ ነው፡፡ "እግዚአብሔር ኢዮብ ለሶስቱ ወዳጆቹ የጸለየውን ጸሎት ተቀበለ" (ሜቶኖሚ/ ከአንድ ባህሪው በመነሳት ለነገሩ ስያሜ መስጠት የሚለውን ይመልከቱ)

Job 42:10-11

ያህዌ እድል ፈንታውን አደሰለት

"ያህዌ ሀብቱን መለሰለት" ወይም "ያህዌ ሀብቱን አደሰለት"

አስቀድመው ያውቁት የነበሩ ሁሉ

"አስቀድሞ ያውቃቸው የነበሩ ሰዎች"

Job 42:12-14

ከመጀመሪያው ይልቅ

"እርሱ ባረከው" እና "የኢዮብ ህይወት" የሚሉት ቃላት ከቀደመው ሀረግ የሚታወቁ ናቸው፡፡ እዚህ ስፍራ ሊደገሙ ይችላሉ፡፡ "የመጀመሪያውን የኢዮብ የህይወት ምዕራፍ ከባረከው ይልቅ" (የተዘለለ/የተተወ የሚለውን ይመልከቱ)

አስራ አራት ሺህ በጎች

14,000 በጎች (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ስድስት ሺህ ግመሎች

6,000 ግመሎች (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

አንድ ሺህ ጥማድ በሬዎች

1,000 ጥማድ በሬዎች (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ሰባት ወንዶች ልጆች እና ሶስት ሴቶች ልጆች

7ወንዶች እና 3 ሴቶች (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

ይማሚ… ቃሥያ… አማልቶያስ ቂራስ

የሴቶች ስሞች (ስሞች እንዴት ይተረጎማሉ የሚለውን ይመልከቱ)

Job 42:15-17

እንደ ኢዮብ ሴቶች ልጆች ያሉ ውብ ሴቶች አልነበሩም

"የኢዮብ ሴቶች ልጆች ከሌሎች ሴቶች ሁሉ የተዋቡ ነበሩ"

140 አመታተት ኖረ

"140 አመታት ኖረ" (ቁጥሮች የሚለውን ይመልከቱ)

እድሜ ጠገበ ደግሞም አርጅቶ

"እድሜ ጠግቦ" የሚሉት ቃላት "አረጀ" ከሚለው ጋር ተመሳሳይ ነው፡፡ ሁለቱ ሀረጎች የጋራ ፈሊጥ አላቸው፡፡ "በጣም ያረጀ ሰው" በሚለው ውስጥ እንደሚገኘው፡፡ (ጥንድ ትርጉም እና ፈሊጣዊ አነጋገር የሚሉትን ይመልከቱ)