ምዕራፍ
Chapter 1
1 ክፉዎች እንዲያደርጉ የሚመክሩአቸውን የማያደርጉ፣ የኃጢአተኞችን ባሕርይ እንዲሁም በእግዚአብሔር የሚያሾፉትን ሰዎቸ የማይከተሉ ምንኛ የታደሉ ናቸው? 2 ይልቁንም፣ ያሕዌ ደስ የሚሰኝባቸው እርሱ የሚያስተምረንን በሚረዱና በዚያም ደስ በሚላቸው ነው፡፡ 3 እነርሱ ሁልጊዜ እግዚአብሔር ደስ የሚሰኝበትን ነገር ያደርጋሉ፡፡ በወንዝ ዳር እንደተተከለ ፍሬውንም በየዓመቱ በትክክለኛው ጊዜ እንደሚሰጥ ቅጠሉም እንደማይግፍ ዛፍ ናቸው፡፡ የሚሠሩት ሁሉ ይከናወንላቸዋል፡፡ 4 ክፉ ሰዎች ግን እንደዚህ አይደሉም፣ ክፉ ሰዎች ከዛፍ እንደሚራገፉና ነፋስም ጠርጎ እንደሚወስዳቸው እንደማይጠቅሙ ገለባዎች ናቸው፡፡ 5 ስለዚህ፣ እግዚአብሔር በሰዎች ሁሉ ላይ በሚፈርድበት ጊዜ፣ ክፉዎችን ይኮንናቸዋል፡፡ ከዚህም ሁሉ በላይ፣ ያሕዌ ዱሳንን በአንድ ላይ በሚሰበስብበት ጊዜ፣ ክፉዎች በዚያ ሊገኙ አይችሉም፡፡ 6 ያሕዌ ቅዱሳንን ይመራቸዋል ይጠንቃቸዋልም፤ ክፉዎች የሚሄዱበት መንገድ ግን እግዚአበሔር እነርሱን ለዘላለም ወደሚየጠፋበት አቅጣጫ ይወስዳቸዋል፡፡
Chapter 2
1 የመንግሥታት መሪዎች በያሕዌ ላይ ስለምን አጉረመረሙ? ሰዎች በእርሱ ላይ በከንቱ ለማመጽ ለምን አቀዱ? 2 የምድር ነገሥታቶች ለማመጽ ተዘጋጁ፣ ገዢዎችም በአንድነት ያሕዌን እና እርሱ የቀባውን ለመዋጋት አሴሩ፡፡ 3 "ከእነርሱ ቁጥጥር ራሳችንን ነጻ ማድረግ አለብን፣ ከአሁን በኋላ እነርሱ ሊገዙን አይችሉም !" በማለት ጮሁ፡፡ 4 ነገር ግን በዙፋኑ ላይ የተቀመጠው እርሱ ይስቅባቸዋል፤ ጌታ እነዚህን ገዢዎች ያላግጥባቸዋል፡፡ 5 በእነርሱ ስለተቆጣ ይገስጻቸዋል፣ እርሱ በቁጣው እንደሚቀጣቸው በሚገነዘቡበት ጊዜ በፍርሃት እንዲዋጡ ያደርጋቸዋል፡፡ 6 ያሕዌ እንዲህ ይላል "እኔ ንጉሤን በጽዮን፣ በተቀደሰው ተራራዬ በኢየሩሳሌም አንግሼአለሁ፡፡" 7 የእርሱም ንጉሥ እንዲህ ይላል "ያሕዌ ያዘዘውን እናገራለሁ፣ እኔን እንዲህ ብሎኛል፣ "አንተ ልጄ ነህ፣ እኔ ዛሬ አባትህ ሆኛለሁ"፡፡ 8 መንግሥታትን እንድሰጥህ ለምነኝ፣ ለዘላለምም ያንተ ይሆኑ ዘንድ፣ እሰጥሃለሁ፡፡ በሩቅ ያሉ መንግሥታትም ሳየቀሩ የአንተ ይሆናሉ፡፡ 9 በብረት በትር ትቀጠቅጣቸዋለህ፣ ሸክላ ሰሪ በእጁ ያለውን ሸክላውን በመሬት ላይ ሲጥለው እንደሚሰባበር፣ እንዲሁ አንተም ትሰባብራቸዋለህ፡፡ 10 ስለዚህ፣ እናንተ ነገሥታት ሌሎችም የምድር ገዢዎች አስተውሉ፣ ያሕዌ የሚሰጣችሁን ማስጠንቀቂያ ስሙ! 11 ያሕዌን አምልኩ፣ ከልባችሁ አክብሩት፣ እርሱ በሠራው ደስ ይበላችሁ፤ ነገር ግን በፊቱ ተንቀጥቀጡ፡፡ 12 በልጁ ፊት በትህትና ስገዱ! ይህንን ባታደርጉ፣ ይቆጣል፣ በድንገትም ይገድላችኋል፡፡ ቁጣውን ሊያሳያችሁና በቅጽበት ሊገድላችሁ እንደሚችል አትዘንጉ! ነገር ግን እርሱ እንዲጠብቃቸው የሚለምኑት እንዴት የታደሉ ናቸው፡፡
Chapter 3
ከልጁ ከአቤሴሎም ፊት በሸሸ ጊዜ ዳዊት የጻፈው መዝሙር፡፡ 1 አምላኬ ያሕዌ፣ ጠላቶቼ በዙ! የሚቃወሙኝ ብዙ ሰዎች ናቸው፡፡ 2 ብዙ ሰዎች "እግዚአብሔር በእርግጥ አይረዳውም" እያሉ ስለ እኔ ይናገራሉ፡፡ 3 ነገር ግን ያሕዌ፣ አንተ ለእኔ እንደ ጋሻ ነህ ትጠብቀኛለህ፡፡ አንተ ከፍ አደረግኸኝ፣ አበረታታኸኝም፡፡ 4 ያሕዌ ወደ አንተ በተጣራሁ ጊዜ ጊዜ፣ አንተ ከቅዱሱ ተራራህ ከጽዮን መለስክልኝ፡፡ 5 በሌሊት እተኛለሁ አንቀላፋለሁም፣ በማለዳም ከእንቅልፌ እነሳለሁ፣ ያሕዌ፣ አንተ ሌሊቱን ሁሉ ትጠብቀኛለህ፡፡ 6 በሺህ የሚቆጠሩ የጠላት ወታደሮች በከብቡኝ እንኳን፣ አልፈራም፡፡ 7 አምላኬ፣ ያሕዌ ተነሥ፣ ዛሬም እንደገና ታደገኝ፣ ጠላቶቼን ጉንጫቸውን በጥፊ መትተህ ትዘልፋቸዋለህ፣ በምትመታቸውም ጊዜ፣ ማንንም መጉዳት እስከማይችሉ ድረስ፣ ኃይላቸውን ታጠፋለህ፡፡ 8 ያሕዌ፣ ሕዝቦችህን ከጠላቶቻቸው ያዳንካቸው አንተ ነህ፣ ያሕዌ፣ ሕዝብህን ባርክ፡፡
Chapter 4
ዳዊት ለመዘምራን አለቃ የጻፈው መዝሙር፣ በገና በሚደረድሩ ሰዎች የሚታጀብ መዝሙር ነው፡፡ 1 እግዚአብሔር ሆይ፣ ወደ አንተ ስጸልይ መልስልኝ፡፡ በአንተ መታመኔ ትክክል መሆኑን ለሰዎች ያሳየሃቸው አንተ ነህና፣ በታላቅ መከራ ውስጥ በነበርኩ ጊዜ አዳንከኝ፡፡ በምሕረትህ ተመልከተኝ፣ ጸሎቴንም ስማኝ፡፡ 2 እናንተ ሰዎች፣ እኔ ከማክበር ይልቅ የምታዋርዱኝ እስከመቼ ነው; እኔን በሐሰት መክሰስ ትወዳላችሁ፡፡ 3 ያሕዌን የሚያከብሩት ሁሉ የእርሱ ይሆኑ ዘንድ መርጦአቸዋል፡፡ ወደ እርሱ ስጸልይ ያሕዌ ይሰማኛል፡፡ 4 ያሕዌን መፍራት ይገባችኋል፣ ነገር ግን ፍርሃታችሁ ኃጢአትን ለማድረግ እንዲያስገድዳችሁ አትፍቀዱለት፡፡ በአልጋችሁ ላይ በተኛችሁ ጊዜ፣ በጸጥታ ሆናችሁ በውስጣችሁ የምታሰላስሉትን መርምሩ፡፡ 5 እንዲሁም፣ ለያሕዌ ትክክለኛውን መስዋዕት አቅርቡ፣ በእርሱም መታመናችሁን ቀጥሉ፡፡ 6 አንዳንድ ሰዎች "መልካምን ነገር ማን ያመጣልናል" በማለት ይጠይቃሉ፡፡ እኔ ግን፣ ያሕዌ፣ ለእኛ መልካም ማድረግህን ቀጥል እላለሁ፡፡ 7 ደስተኛ እንድሆን አድርገኸኛል፣ እጅግ ብዙ የስንዴ እና የወይን ምርት ካመረቱ ሰዎች ይልቅ እጅግ ደስተኛ ሆኜአለሁ፡፡ 8 በሰላም እተኛለሁ አንቀላፋለሁም፣ ያሕዌ አንተ ትጠብቀኛለህና እንቅልፌ የጣፈጠ ይሆናል፡፡
Chapter 5
ዳዊት ለመዘምራን አለቃ የጻፈው መዝሙር፣ ዋሽንት በሚጫወቱ ሰዎች የሚታጀብ መዝሙር ነው፡፡ 1 ያሕዌ፣ ጸሎቴን ስማ! ከደረሰብኝ ብርቱ መከራ የተነሣ ስቃትት በትኩረት ተመልከተኝ፡፡ 2 አንተ ንጉሤና አመልኬ ነህ፡፡ ወደ አንተ ስጣራ እንድትረዳኝም ስጠይቅህ፣ ስማኝ ምክንያቱም የምጸልየው ወደ አንተ ብቻ ነውና፡፡ 3 በየጥዋቱ ወደ አንተ ስጸልይ ስማኝ፣ መልስህንም እጠብቃለሁ፡፡ 4 በክፉ ሰዎች የመትደሰት አምላክ አይደለህም፣ ክፉ የሚያደርጉትን ሰዎች ፈጽሞ አትቀበልም፡፡ 5 የሚኮሩ ሰዎችን ወደ አንተ እንዲመጡና እንዲያመልኩህ አትፈቅድም፣ ክፉ የሚያደርጉትን ትጠላለህ፡፡ 6 ሐሰተኞችን ታስወግዳቸዋለህ፣ ነፍሰ ገዳዮችንና አታላዮችን ትጸየፋለህ፡፡ 7 ያሕዌ፣ አንተ በታማኝነት እጅግ ወድደኸኛልና፣ ወደ መቅደስህ እመጣለሁ፡፡ ለአንተ ታላቅ አክብሮት አለኝ፣ ስለሆነም በተቀደሰው መቅደስህ ላመልክህ እሰግዳለሁ፡፡ 8 ያሕዌ፣ አንተ ለእኔ በጽድቅ ታደርጋለህና፣ ላደርገው የሚገባኝን ትክክለኛ ነገር አሳየኝ፡፡ ብዙ ጠላቶች አሉኝና፣ በትክክለኛ መንገድ እነዴት መኖር እንዳለብኝ አሳየኝ፡፡ 9 ጠላቶቼ ትክክለኛ የሆነውን ነገር አይናገሩም፣ ከውስጣቸው የሚመኙት ሌሎችን ማጥፋት ነው፡፡ የሚናገሩት በአመጻ ማስፈራራትና ሞትን ነው፡፡ ሰዎችን ለማስደሰት አንደበታቸው መልካም ነገርን ይናገራል፡፡ 10 እግዚአብሔር ሆይ፣ ፍረድባቸው፣ ቅጣቸውም፡፡ በሌሎች ላይ ለማድረግ ያቀዱትን ክፉ ነገር በላያቸው ላይ አምጣባቸው፡፡ ብዙ ኃጢአትን ስላደረጉ፣ በአንተም ላይ ስላመጹ አጥፋቸው፡፡ 11 ይህን ሁሉ ግን በአንተ እንዲጠበቁ ወደ አንተ ለሚመጡ እንዲደሰቱበት አድርግላቸው፣ ለዘላለም ለአንተ በደስታ እንዲዘምሩ አድርጋቸው፡፡ አንተን የሚወዱትን ጠብቃቸው፣ ስላደረግህላቸው ነገር ሁሉ በእውነት ደስ ብሎአቸዋል፡፡ 12 ያሕዌ፣ በጽድቅ የሚሄዱትን ሁልጊዜ ባርካቸው፣ በጋሻው ራሱን እንደሚከላከል ወታደር ጠብቃቸው፡፡
Chapter 6
ዳዊት ለመዘምራን አለቃ የጻፈው መዝሙር፣ በገና በሚደረድሩ ሰዎች የሚታጀበ መዝሙር ነው፡፡ 1 ያሕዌ፣ በእኔ በተናደድክ ጊዜ አትገስጸኝ፣ በቁጣህም አትቅሰፈኝ፡፡ 2 ያሕዌ፣ በምሕረት ተመልከተኝ፣ ደክሜአለሁና ፈውሰኝ፣ ሥጋዬ ከሐዘን የተነሣ ይንቀጠቀጣል፡፡ 3 ያሕዌ፣ በውስጤ እጅግ ተረብሼአለሁ፡፡ እስከ መቼ ይህን እቋቋማለሁ? 4 ያሕዌ፣ እባክህ ናና ታደገኝ፣ አድነኝ ምክንያቱም አንተ ሁል ጊዜ ቃል ኪዳንህን ትጠብቃለህና፡፡ 5 ከሞትኩ በድኔ ሊያመሰግንህ አይችልም፣ ሙታን ባሉበት ማንም ሊያመሰግንህ አይችልም፡፡ 6 ከሕመሜ የተነሳ ደክሜአለሁ፡፡ ሌሊቱን ሙሉ ሳለቅስ ነበር፡፡ አልጋዬና ትራሴ በእንባዬ ርሰዋል፡፡ 7 እጅግ አልቅሻለሁና፣ በግልጽ ማየት አልችልም፡፡ ጠላቶቼን በመፍራት ያለማቋረጥ አንብቻለሁና ዓይኖቼ ደከሙ፡፡ 8 እናንተ ክፉ የምታደርጉ ሰዎች፣ ከእኔ ራቁ፣ ያሕዌ ጩኸቴን ሰምቶአልና! 9 ያሕዌ እንዲረዳኝ ወደ እርሱ ስጣራ ሰምቶኛል፣ ጸሎቴንም ይመልሳል፡፡ 10 ይህም ሲሆን፣ ጠላቶቼ ሁሉ ያፍራሉ፤ አሁን የሚፈሩት እነርሱ ናቸው፡፡ ተዋርደዋልና ከእኔ ፊታቸውን ያዞራሉ፣ እኔንም ማሳደድ ይተዋሉ፡፡
Chapter 7
ኩሽ ስለተባለው ቢኒያማዊ ዳዊት ለያሕዌ የዘመረው መዝሙር፡፡ 1 ያሕዌ የእኔ አምላክ፣ እንድትጋርደኝ ወደ አንተ እመጣለሁ፣ ሊጎዱኝ ከሚከታተሉኝ አድንኝ፣ ታደገኝም፡፡ 2 አንተ ካላዳንከኝ፣ እነርሱ ደርሰው አንበሳ ሊያጠቃቸው የሚፈልጋቸውን የዱር እንስሳት እንደሚቦጫጭቃቸው ይቆራርጡኛ፤ ከእጃቸው ማንም አያስጥለኝም፡፡ 3 ያሕዌ የእኔ አምልካ፣ ምናልባት እጥፍቼ ከሆነ፣ 4 ወይም በባልንጀራዬ ላይ ክፉ ነገር አድርጌ ከሆነ፣ ወይም ጠላቴን በከንቱ ጎድቼው ከሆነ፡፡ 5 ጠላቶቼ አሳድደው እንዲይዙኝ ፍቀድላው፡፡ በመሬት ላይ እንዲረግጡኝና፣ ሬሳዬንም በአቧራ ላይ እንዲጥሉት ፍቀድላቸው፡፡ 6 ያሕዌ፣ አንተ በሚያሳድዱኝ እጅግ ተቆጥተሃልና፣ የሚያጠቁኝን ልታጠቃቸው ተነሥ! ጽድቅ በሆነው ትእዛዝህ አድርግባቸው! 7 የመንግሥታት ሕዝቦች ሁሉ አንተን ለማጥቃት በአንድ ላይ መጡ፣ አንተ ግን ካለህበት ከሰማይ ሆነህ ትገዛቸዋለህ፡፡ 8 ያሕዌ፣ በመንግሥታት ሕዝቦች ላይ ፍረድ! ያሕዌ፣ በደል እንደሌለብኝ አሳያቸው፡፡ 9 እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ እያንዳንዱ ሰው በውስጡ ምን እንደሚያስብ ታውቃለህና አንተ ጻድቅ ስለሆንክ፣ ሁልጊዜ የምታደርገው ትክክል ነው፡፡ ስለዚህ ክፉ ሰዎች ክፉ ነገርን እንዳያደርጉ ከልክላቸው፣ ጻድቃን የሆንነውን ሁላችንን ተከላከልንን፡፡ 10 እግዚአብሔር ሆይ፣ ጋሻ ወታደሮችን እንደሚከላከልለቸው፣ ከልለኝ፤ በውስጣቸው ቅዱሳን የሆኑትን ሁሉ ታደጋቸው፡፡ 11 ለእያንዳንዱ በትክክል ትፈርዳለህ፣ በየእለቱ በሕግህ የሚቀልዱትን ኃጢአተኞች ትቀጣለህ፡፡ 12 ጠላቶች ንስሃ አንገባም ባሉበት ጊዜ ሁሉ፣ አንተ ልትገድላቸው ሰይፍህን ትስላለህ፣ ቀስትህንም ትገትራለህ፡፡ 13 የምትገድላቸውን ጠላቶችህን ለመምታት መሣሪያዎችህን አዘጋጅተሃል፣ የምትልካቸውም ፍላጻዎችህ የእሳት ነበልባል ናቸው፡፡ 14 ክፉ ሰዎች በሐሰታቸውና በዓመፃቸው አሴሩ፣ ርጉዝ ሴት ለመውለድ እንደምታቅድ፣ እነርሱም በሐሳባቸው ደስተኞች እንደሚሆኑ አቀዱ፡፡ 15 ነገር ግን ሌሎችን ለማጥመድ ጥልቅ ጉድጓድ ሲቆፍሩ፣ እነርሱ ራሳቸው በዚያ ጉድጓድ ይወድቃሉ፡፡ 16 በሌሎች ላይ እንዲደርስ ያቀዱት ክፉ ነገር ሁሉ፣ በራሳቸው ላይ ይደርስባቸዋል፤ በሌሎች ላይ እንዲደርስ በተመኙት የአመፃ ሥራ ራሰቸውን ይጎዳሉ፡፡ 17 ያሕዌን አመሰግናለሁ፣ እርሱ በጽድቅ ይፈርዳልና፡፡ ከማንኛውም አማልክት በላይ እጅግ ከፍ ያለውን፣ ያሕዌን ለማመስገን እዘምራለሁ፡፡
Chapter 8
ዳዊት ለመዘምራን አለቃ የጻፈው መዝሙር፣ በገና በሚደረድሩ ሰዎች የሚታጀብ መዝሙር ነው፡፡ 1 ያሕዌ ጌታችን፣ በምድር ያሉ ሰዎች ሁሉ አንተ ታላቅ እንደሆንክ ያውቃሉ! ሰማያትን ባየን ቁጥር ታላቅነትህን እባያለን! 2 ትናንሽ ልጆችንና ሕፃናትን አንተን እንዲያመሰግኑ አስተምረሃቸዋል፣ በእነርሱ ጠላቶችህንና ሊበቀሉህ የሚፈልጉትን ጸጥ ታደርጋቸዋለሁ፡፡ 3 በሌሊት ወደ ሰማይ ስመለከት አንተ የሠራሃቸውን ነገሮች አስተዋልሁ፣ ጨረቃንና ከዋክብትን በቦታቸው ያስቀመጥካቸውን፡፡ 4 ለእኛ ለሰዎች ማሰብህን ስመለከት፣ ለሰው ለጆች መጠንቀቅህን ሳየው እጅግ እደነቃለሁ! 5 መላእክትን ከእኛ በጥቂቱ እንዲበልጡ አድርገህ በሰማያት ሰራሃቸው፣ እኛንም እንደ ነገሥታት አደረግኸን፡፡ 6 በሠራሃቸው ሁሉ ላይ የበላይ አደረግኸን፣ ቡሉ ነገር ላይ ሥልጣንን ሰጠኸን፡፡ 7 በበጎችና በከብቶች በዱር አራዊት ሁሉ ላይ፣ 8 በወፎች፣ በአሳዎችና፣ በባሕር ውስጥ በሚዋኘው ነገር ሁሉ ላይ ስልጣንን ሰጠኸን፡፡ 9 ያሕዌ ጌታችን፣ በምድር ያሉ ሰዎች ሁሉ አንተ ታላቅ እንደሆንክ ያውቃሉ!
Chapter 9
ዳዊት ለመዘምራን አለቃ ‹‹የልጄ ሞት›› በሚል ቅላጼ እንዲዘመር የጻፈው መዝሙር፡፡ 1 ያሕዌ፣ ከልቤ ከውስጤም አመሰግንሃለሁ፣ ስለ ሠራሃቸው ድንቅ ነገሮች ሁሉ ለሌሎች እነግራለሁ፡፡ 2 አንተ፣ ከሌሎች አማልክት ይልቅ፣ እጅግ ታላቅ ነገር ስላደረግህ እዘምርልሃለሁ፡፡ 3 ጠላቶቼ አንተ እጅግ ኃያል መሆንክን ሲረዱ፣ ይሰናከላሉ፣ ይገደላሉም፡፡ 4 በሰዎች ላይ ልትፈርድ በዙፋንህ ላይ ተቀምጠሃል፣ ለእኔም በቅንነት ፈርደኽልኛል፡፡ 5 ሌሎች ሕዝቦችን ገሰጽካቸው፣ ክፉ ሰዎችን አጥፈተሃቸዋል፣ ስማቸውንም ለዘለለሙ ሰርዘሃል፡፡ 6 ጠላቶቼ ጠፍተዋል፣ ከተማቸውን ደምስሰሃል፣ ሰዎች ካሁን በኋላ ሊያስታውሱአቸው እንኳን አይችሉም፡፡ 7 ያሕዌ ግን ለዘላለም ይገዛል፡፡ በዙፋኑ ላይ ሆኖ በሰዎች ላይ ይፈርዳል፡፡ 8 በዓለም ባሉ ሰዎች ሁሉ ላይ በጽድቅ ይፈርዳል፣ ለሕዝቦች ሁሉ በቅንነት ይፈርዳል፡፡ 9 ያሕዌ ለተጨቆኑት ሁሉ መጠጊያቸው ነው፣ በተረበሹ ጊዜ እንደ መጠለያ ይሆናቸዋል፡፡ 10 ያሕዌን የሚያውቁ በእርሱ ይታመኑ፣ ለእርዳታ ወደ እርሱ የሚመጡትን ፈጽሞ አየተዋቸውም፡፡ 11 ያሕዌ ከጽዮን ተራራ ይገዛል፣ አመስግኑት ዘምሩለትም፡፡ የሠራውን አስደናቂ ነገር ለሰዎች ሁሉ ተናገሩ፡፡ 12 ሌሎችን የገደሉትን መቅጣቱን አይረሳም፣ ይቀጣቸዋል፣ መከራ ከመቀበላቸው የተነሳ የሚጮሁትን ሰዎች ቸል አይላቸውም፡፡ 13 ያሕዌ በምሕረትህ ተመልከተኝ! ጠላቶቼ በምን መንገድ እንደጎዱኝ ተመልከት፡፡ ከዚህ ጉዳተ የተነሣ እንድሞት አትፍቀድ፡፡ 14 ስላዳንከኝ በደስታ በኢየሩሳሌም ደጆች ላመሰግንህ መኖር እፈልጋለሁ፡፡ 15 የብዙ መንግሥታት ክፉ ሰዎች እኔ እንድወድቅበት ጉድጓድን ቆፈሩ፣ ነገር ግን እነርሱ ራሳቸው በዚያው በቆፈሩት ጉድጓድ ወደቁ፡፡ እኔን ለማጥመድ መረባቸውን ዘርግተው ነበር፣ ነገር ግን እግራቸው በዚያው ወጥመድ ተያዘ፡፡ 16 ከደረግኸው ነገር የተነነሣ፣ ሰዎች ጽድቅን እንዳደረግህ አውቀዋል፣ ክፉ ሰዎች ባደረጉት ክፉ ነገር እንዲጠመዱ አድርገሃል፡፡ 17 ክፉ ሰዎች ሁሉም ይሞታሉ በመቃብራቸውም ይቀበራሉ፣ መንፈሳቸውም አንተን ከረሱት ጋር ይሆን ዘንድ ይሄዳል፡፡ 18 ነገር ግን ድሆችን አትረሳም፣ በመተማመን የተጠባበቁት በከንቱ አይደለምና፡፡ 19 ያሕዌ፣ በመንግሥታት ከፉ ሰዎች ላይ ተነሥ ፍረድባቸውም፣ ጠንካሮች እንደሆኑና ፈጽሞ እንደማይቀጡ እንዲያስቡ አትፍቀድላቸው፡፡ 20 ያሕዌ፣ አንተን እንዲፈሩና እንዲያከብሩ አስተምራቸው፡፡ ሰዎች ብቻ መሆናቸውን እንዲረዱ አድርጋቸው፡፡
Chapter 10
1 ያሕዌ፣ ከእኛ የራቅኸው ለምንድን ነ ው; ስንረበሽ ለምን አታየንም? 2 ኩሩና ክፉ ሰዎች፣ ድሆችን ለማሰቃየት አስከፊ ፍላጎት አላቸው፡፡ እግዚአብሔር ሆይ! በሰዎች ላይ ያደረጉት ክፉ ነገር በእነርሱ ላይ እንዲደርስ፣ ባጠመዱት ወጥመድ ላይ እንዲወድቁ አድርጋቸው! 3 ክፉ ሰው ሊያደርገው በሚመኘው ክፉ ነገር ይኩራራል፡፡ ሌሎች ያላቸውን ነገር ለራሱ ለማድረግ ይመኛል፣ እርሱ ካለው በላይ ሌሎች እንዲኖራቸው አይፈልግም፡፡ ባለው ነገር እጅግ ይኩራራል፣ ያሽዌ፣ አንተንም ይራገማል፡፡ 4 ኃጢአተኛ ሰው እጅግ ኩራተኛ ነው እግዚአብሔርን ፈጽሞ አይፈልግም፣ ቢፈልግም ሊያገኘው አይችልም፡፡ እጅግ ኩራተኛ ነውና ስለ እግዚአበሔር ሊያስብ እንኳን አይፈልግም፡፡ 5 ገር ግን፣ የኃጢአተኛን ሕይወት ሲመለከቱት፣ የሚያደርገው ሁሉ የሚከናወንለት ይመስላል፡፡ እግዚአብሔር ሆይ፣ የአንተን ትእዛዝ መረዳት እንኳን አይችልም፣ በጠላቶቹ ያላግጣል፡፡ 6 በአዕምሮው ‹‹በሕይወት እስካለሁ፣ ምንም ክፉ ነገር አያገኘኝም፣ መከራም አይደርስብኝም›› በማለት ያስባለ፡፡ 7 ሲናገር ሁልጊዜ ይራገማል፣ ይዋሻልም፣ ሌሎችንም ያስፈራራል፡፡ በሚናገርበት ጊዜ ሌሎችን ስለማጥቃት እና ሰለማጥፋት ብቻ ይናገራል፡፡ 8 በገጠር የሚኖሩትን፣ ምንም ያላጠፉትን ሰዎች ለማጥቃት ያቅዳል፡፡ በአንዳንድ ሥፍራዎች ተደብቆ ራሳቸውን ለመከላከል የማይችሉትን፣ ብዙ ሰዎችን ለማጥቃት የሚችልበትን ሁኔታ ይጠባበቃል፡፡ 9 አንበሳ እንደሚያደባ በሚያጠቃቸው ላይ ያደባል፣ ልክ እንደ አንበሳ ራሱን በቁጥቋጦ ውስጥ ይሸሽጋል፡፡ እርሱ መረብን እንደሚዘረጋ አዳኝ፣ ራሳቸውን በማይከላከሉት ሰዎች ላይ መረቡን ይዘረጋል፣ ጎትቶም ያስወግዳቸዋል፡፡ 10 የሚረዳቸው የሌለ ሰዎች በኃጠአተኛ እቅድ እና፣ በሚያደርጋቸው ነገሮች ይጨፈለቃሉ፡፡ እጅግ ኃይለኛ ነውና ረዳት ከሌላቸው ሰዎች፣ የሚፈልገውን ሁሉ ይወስድባቸዋል፡፡ 11 ኃጢአተኛ ‹‹የደረግሁትን ሁሉ እግዚአብሔር ሊያስታውስ አይችልም፣ አይኖቹ ታውረዋል፣ ያደረግሁትን ሊያዩ አይችሉም›› ይላል፡፡ 12 ያሕዌ፣ ተነሥ ምታውም፣ የሚሰቃዩትን አትርሳ! 13 እግዚአብሔር ሆይ፣ እጅግ ክፉ የሆነ ሰው እንዴት አንተን ይራገማል; እንዴትስ ከአንተ ይሰወራል፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ፈጽሞ አይቀጣኝም›› ብሎ ያስብ; 14 እግዚአብሔር ሆይ፣ ኃጢአተኛ ሰው የሚፈጥረውን መከራና ሐዘን ተመልከት፡፡ አንተ ኃጢአተኛውን ትመታለህ ስለደረገውም ነገር ሁሉ ትቀጣዋለህ፡፡ 15 እግዚአብሔር ሆይ፣ የክፉውን ሰው ኃይል አጥፋ፣ ብርታቱንም ከእርሱ አስወግድ! ኃጢአተኛው ሰው ላደረገው ክፉ ነገር ሁሉ እንዲከፍል አድርገው! ሰለፈጸማቸው ክፉ ነገሮች ሁሉ እንዲከፍል አድርገው፣ እግዚአብሔር እንደሚቀጣው ፈጽሞ ባላሰባቸው ነገሮች እንዲከፍል አድርገው፡፡ 16 ይሕዌ ለዘላለም ንጉሥ ነው፣ እንግዳ ሰዎችን ከምድሩ ያስወጣቸዋል፡፡ 17 ያሕዌ፣ የሚሰቃዩ ሰዎች ወደ አንተ ሲጮሁ፣ ስማ፡፡ በሚጸልዩ ጊዜ ስማቸው፣ አበረታታቸውም፡፡ 18 ኃይለኞችና ክፉ ሰዎች ሊያጠቁአቸው ሲሞክሩ፣ ወላጅ አልባ የሆኑትን እና የተጨቆኑትን ሰዎች ተከላከልላቸው፡፡ ስለዚህም ማንም ከእንግዲህ አይጨነቅም አይፈራምም፡፡
Chapter 11
ዳዊት ለመዘምራን አለቃ የጻፈው መዝሙር፡፡ 1 እንደሚጠብቀኝ አምናለሁ፡፡ ስለዚሀ ወፎች ወደ ታራራ እንደሚበሩ አልበርም፡፡ 2 ክፉ ሰዎች ያሕዌን የሚያከብሩትነ ለመንደፍ ቀስታቸውን ገትረው፣ በጨለማ ውስጥ ተሰውረው የሚጠባበቁ መሆናቸው እውነት ነው፡፡ 3 ኃጢአተኞች ሕግን እየተላለፉ መከራ አይደርስባቸውም፣ ጻድቃን ምን አደረጉ? 4 ነገር ግን ያሕዌ በተቀደሰው መቅደሱ በሰማይ ዙፋኑ ላይ ተቀምጦአል፣ ሰዎች የሚያደርጉትን ነገር ሁሉ ይመለከታል፡፡ 5 ያሕዌ፣ ጻድቃን ያደረጉትንና ኃጥአን ያደረጉትን ይመረምራል፣ ሌሎችን ለመጉዳት የሚወዱትን ይጠላል፡፡ 6 ከሰማይ እሳቱንና ዲኑን በኃጢአተኞች ላይ ይሰድዳል፣ ሊቀጣቸውም ዐውሎ ንፋሱን ይልክባቸዋል፡፡ 7 ያሕዌ ትክክል የሆነውን ነገር ያደርጋል፣ ትክክል የሆነውን የሚያደርጉትን ይወዳል፣ እንዲህ ያሉ ሰዎች ወደ እርሱ ይቀርባሉ፡፡
Chapter 12
ዳዊት ለመዘምራን አለቃ የጻፈው መዝሙር፡፡ 1 ያሕዌ፣ አነተነ የሚያከብሩ የሉምና፣ እርዳን፣ ለአንተ ታማኝ የሆኑ ሁሉ ጠፍተዋልና፡፡ 2 እያንዳንዱ ለሌላው ውሸትን ይናገራል፣ ሌሎችን በከንቱ ውዳሴ ያታልሉአቸዋል፣ ነገር ግን ውሸታቸውን ነው፡፡ 3 ያሕዌ፣ ምላሳቸውን እንድትቆርጣቸው እንመኝ ነበር፣ ምክንያቱም ከዚያ በኋላ መታበያቸውን ሊቀጥሉ አይችሉምና፡፡ 4 እንዲህ ብለዋልና "ውሸት በመናገራችን የምንፈልገውን እናገኛለን፣ የተናገርነውንም እንቆጣጠራለን፣ ስለዚህ ማንም ማድረግ ያለብንን ሊነግረን አይችልም"፡፡ 5 ያሕዌ ግን እንዲህ ይላል፣ "ረዳት አልባ በሆኑ ሰዎች ላይ ያደረጉትን ክፉ ነገር አይቻለሁ፣ የእነዚያን ሰዎች መቃተት ሰመቻለሁ፣ ስለዚህ እነሣለሁ እንድረዳቸው የሚፈልጉትን እታደጋለሁ"፡፡ 6 ያሕዌ፣ አንተ ግን ሁል ጊዜ የገባኸውን ቃል ኪዳን ታደርጋለህ፣ የገባኸው ቃል ኪዳን በላዩ ላይ ያለውን ንጹህ ያለሆነ ነገር ለማስወገድ ሰባት ጊዜ በእሳት ውስጥ ገብቶ እንደተፈተነ ብር ውድ እና ንጹህ ነው፡፡ 7 ያሕዌ፣ ያከበርንህን እንደምትጠብቀን፣ 8 በኩራት ከሚመላለሱ በሚሰሩት ክፉ ሥራ ሰዎች ከሚያመሰግኑአቸው ከክፉ ሰዎችም እንደምትታደገን እናወቃለን፡፡
Chapter 13
ዳዊት ለመዘምራን አለቃ የጻፈው መዝሙር፡፡ 1 ያሕዌ፣ እስከመቼ ትረሳኛለህ? ከእኔ ራስህን ለዘላለም ትሰውራለህን? 2 እስከመቼስ በውስጤ እተክዛለሁ? በየቀኑ መበሳጨት አለብኝን? ጠላቴስ እስከመቼ ያጠቃኛል? 3 ያሕዌ አምላኬ፣ ወደ እኔ ተመልከት መልስልኝም፡፡ ኃይልን ስጠኝ አለበለዚያ እሞታለሁ፡፡ 4 ጠላቶቼ "አሸነፍነው" እያሉ እንዲታበዩብኝ አትፍቀድላቸው፡፡ እኔን አጥቅተው ደስ እንዲላቸው አትፍቀድላቸው! 5 ነገር ግን በታማኝነት እንደምትወደኝ አምናለሁ፣ ስትታደገኝ ሐሴት አደርጋለሁ፡፡ 6 ያሕዌ፣ ሌሎችም ብዙ ነገሮችን አድርገኸልኛል፣ ስለዚህም ለአንተ እዘምራለሁ፡፡
Chapter 14
ዳዊት ለመዘምራን አለቃ የጻፈው መዝሙር፡፡ 1 ለራሳቸው "እግዚአብሔር የለም" የሚሉ ሞኞች ሰዎች ብቻ ናቸው፣ እንዲህ የሚሉ ሰዎች ክፉ ነገርን ያደርጋሉ፣ አንዳቸውም መልካም ነገር ማድረግ አይችሉም፡፡ 2 ያሕዌ ከሰማይ እያንዳንዱን ሰው ይመለከታል፣ የትኛው አስተዋይ እንደሆነ፣ እርሱን ለማውቅ የትኛው ፍላጎት እንዳለው ያውቅ ዘንድ ይመለከታል፡፡ 3 ሁሉም ዐመጹ፣ አንዳቸውም መልካም የሆነውን አላደረጉም፡፡ 4 እነዚህ ክፉ ሰዎች እግዚአብሔር ስለሚያደርጉት ክፉ ነገር እንደሚቀጣቸው አይማሩምን? የያሕዌን ልጆች በክፋተ ይነሱባቸዋል፣ አንድ ሰው ምግቡን ጨርሶ እንደሚበላ ሊጨርሱአቸው ይፈልጋል፣ ወደ ያሕዌም ፈጽሞ አይጸልዩም፡፡ 5 ነገር ግን አንድ ቀን እጅግ ይፈራሉ ምክንያቱም እግዚአብሔር በጽድቅ የሚሄዱትን ይረዳቸዋልና እርሱን ያቁትን ይቀጣቸዋል፡፡ 6 ክፉን የሚያደርጉ ሰዎች ረዳት አልባ የሆኑት ሰዎቸ ያቀዱትን እንዳያደርጉ ይከለክሉአቸው ይሆናል፣ ነገር ግን ያሕዌ ይጠብቃቸዋል፡፡ 7 በያሕዌ ቦታ ሆኖ የእስራኤልን ሕዝብ የሚያድን ያሕዌ የሚልከው ይኖር ይሆን? ያሕዌ፣ ሕዝብህን እንደገና ስትባርክ፣ እኛ የያዕቆብ ዘር የሆንነው የእስራኤል ሕዝብ፣ ሐሴትን እናደርጋለን፡፡
Chapter 15
1 ያሕዌ፣ ወደ ተቀደሰው ድንኳንህ እንዲገቡ የተፈቀደላቸው እነማን ናቸው? በተቀደሰውስ ተራራህ ማን ይኖራል? 2 ትክክለኛ የሆነውን ሁል ጊዜ የሚያደርጉ ኃጢአትንም የማያደርጉ እና እውነትን የሚናገሩ ብቻ ናቸው፡፡ 3 የሌሎችን ስም አያጠፉም፡፡ ስህተት የሆነውን ነገር በሌሎች ላይ አያደርጉም፣ በማንም ላይ ክፉ ነገር አይናገሩም፡፡ 4 እግዚአብሔርን የሚያከብሩ ሰዎች እርሱ የሚጠላውን ይጠላሉ፣ ለያሕዌ፣ አክበሮት ያላቸውን ያከብራሉ፡፡ ምንም እንኳን መከራ የሚያስከትልባቸው ቢሆንም፣ ቃል የገቡትን ያደርጋሉ፡፡ 5 ገንዘባቸውን ለሌሎች ያለ አራጣ/ትርፍ/ ያበድራሉ፣ ምንም ስህተት ላልሰሩ ሰዎች ብለው ለመዋሸት ጉቦን አየቀበሉ፣ ይህን የሚያደርጉ በሰላም ይኖራሉ፡፡
Chapter 16
በዳዊት የተጻፈ መዝሙር፡፡ 1 እግዚአብሔር ሆይ፣ በሰላም እንድትጠብቀኝ ወደ አንተ አሄዳለሁና ከልለኝ፡፡ 2 ለያሕዌ እንዲህ ብዬዋለሁ፣ "አንተ ጌታዬ ነህ፣ ያገኘሁት መልካም ነገር ሁሉ ከአንተ ነው"፡፡ 3 በዚህ ምድር ቅዱሳን ሊሆኑ የሚወዱ ሁሉ የተመሰገኑ ናቸው፣ ከእነርሱ ጋር እኔም ደስ ይለኛል፡፡ 4 ሌሎችን አማልክት ለያመልኩ የሚመርጡ ብዙ ኃዘን የሚያስክትሉባቸው ነገሮች ያገኙአቸዋል፡፡ ለአማልክቶቻቸው መስዋዕትን ሲያቀርቡ እኔ ከእነርሱ ጋር አልሆንም፣ አማልክቶቻቸውን ሲጠሩ እንኳን ከእነርሱ ጋር አልሆንም፡፡ 5 ያሕዌ፣ እኔ ግን አንተን መርጫለሁ፣ አንተ ብዙ በረከትን ትሰጠኛለህ፡፡ አንተ ጠበቅኸኝ በእኔ ላይ የሚሆነውን ሁሉ ተቆጣጠርከው፡፡ 6 ያሕዌ፣ የምኖርበትን ያማረ ስፍራ ሰጠኝ፣ በሰጠኝ ነገሮች ሁሉ እጅግ ደስተኛ ነኝ፡፡ 7 ያሕዌን አመሰግናለሁ፣ እርሱ ያስተረኛል፣ ላደርገው የሚገባውን ትክክለኛ ነገር በሌሊት እንኳን ለልቤ ይናገራል፡፡ 8 ያሕዌ ሁልጊዜ ከእኔ ጋር እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ከእርሱ ማንም ሊነጥቀኝ አይችልም፡፡ 9 ስለዚህ ደስተኛ ነኝ፣ እርሱን ማመስገን ለእኔ ክብሬ ነው፣ በሰላምም አርፋለሁ 10 ምክንያቱም፣ አንተ ያሕዌ፣ ሙታን ባሉበት ሥፍራ እንድሆን አትፈቅድም፣ ለቃል ኪዳንህ ታማኝ የሆነውን ሰው በዚያ እንዲሆን አትፈቅድምና፡፡ 11 የዘላለም ሕይወት ወደምቀበልበት የሚመራኝን መንገድ ታሳየኛለህ፣ ከአንተ ጋር በምሆንበት ጊዜ ደስተኛ ታደርገኛለህ፣ በቀኝህ ስሆን የዘላለም ደስታ አገኛለሁ፡፡
Chapter 17
1 ያሕዌ፣ በጽድቅ እንድትፈርድልኝ ወደ አንተ ስማጸን አቤቱ ስማኝ፡፡ እንድትሰማኝ ወደ አንተ ስጣራ ስማኝ፡፡ በእውነት እናገራለሁና በጸሎቴ ለማነሳው ነገር ትኩረት ስጠው፡፡ 2 እኔ ንጹሕ ለመሆኔ ልትመሰክርልኝ የምትችል አንተ ነህ፣ እባክህ ለእኔ ትክክል የሆነውን ልታደርግ ፍቀድ፡፡ 3 የማስበውን ለማወቅ በሌሊት ወደ እኔ ብትመጣ፣ በልቤ የማስበውን ብታይ፣ ፈጽሞ ምንም ዓይነት ውሸት እንደማልናገር ቁርጠኛ መሆኔን ታውቃለህ፣ ክፉ ነገሮችንም እንደማላስብ ታያለህ፡፡ 4 አንትን እንደማያከብሩ አላደርግም፣ እኔ ሁል ጊዜ አንተ ባስተማርከኝ መንገድ እሄዳለሁ፣ ሕግህን እንደማያውቁ ሰዎች አልመላለስም፡፡ 5 አንተ ሁል ጊዜ እንዳደርግ የነገርከኝን አደርጋለሁ፣ ያዘዝከኝን ከማድረግ ወደ ኋላ አላልኩም፡፡ 6 ኦ አምላኬ፣ ወደ አንተ እጸልያለሁ መልስልኝ፣ የምናገረውንም አድምጥ፣ 7 ልታደርግ ቃል እንደገባኸው ፍቅርህን አሳየኝ፡፡ በአንተ የሚታመኑትን ሁሉ በታላቁ ኃይልህ ጠብቃቸው፣ ከጠላቶቻቸው በሰላም ጠብቃቸው፡፡ 8 ሰዎች ዓይኖቻቸውን እንደሚጠብቁ በጥንቃቄ ጠብቀኝ፣ ወፎች ልጆቻቸውን በክንፎቻቸው በታች እንደሚጠብቁአቸው ጠብቀኝ፡፡ 9 ክፉ ሰዎች እንዲያጠቁኝ አትፍቀድላቸው፣ የከበቡኝ ጠላቶቼ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉና፡፡ 10 እነርሱ በሀብታቸውና በስኬታቸው ይኮራሉና፣ ለማንም አይራሩም። 11 አደኑኝ አገኙኝም፡፡ ዙሪያዬን ከበቡኝ፣ በመሬት ላይ ሊጥሉኝና ሊገድሉኝ የተመቸ ጊዜ ይጠብቁ ነበር፡፡ 12 የያዙትን የዱር እንስሳ ለመገነጣጠል እንደሚዘጋጁ አናብስት እነዚህም ጠላቶቼ እንደዚያው ናቸው፣ በሚያድኑአቸው የዱር እንስሳት ላይ ዘልለው ለመውጣት እንደሚያደቡ ወጣት አንበሶች ናቸው፡፡ 13 ያሕዌ፣ ተነሥ፣ ጠላቶቼን አጥቃቸው፣ አሸንፋቸውም! ከእነዚያ ኃጢአተኛ ሰዎች በሰይፍህ አድነኝ! 14 ያሕዌ፣ በዚህ ዓለም ላይ ያሉትን ነገሮች ብቻ ከሚመኙ ሰዎች በኃይልህ አድነኝ፡፡ ነገር ግን ከልብ ለምትወዳቸው ለእነርሱ የተትረፈረፈ ምግብ ሰጠሃቸው፣ ልጆቻቸው የልጅ ልጆቻቸው የሚወርሱት ብዙ ነገር አላቸወ፡፡ 15 ያሕዌ፣ እኔ በትክክል ስለምሄድ፣ አንድ ቀን ከአንተ ጋር እሆናለሁ፡፡ ከሙታን ስነሳ፣ ፊት ለፊት አይሃለሁ፣ ደስተኛም እሆናለሁ፡
Chapter 18
የእግዚአብሔር አገልጋይ ዳዊት የጻፈው መዝሙር፣ ያሕዌ ከሳዖልና ከሌሎች ጠላቶቹ በታደገው ጊዜ የዘመረው ነው፡፡ 1 ያሕዌ፣ ጠንካራ እንድሆን ያስቻልከኝ፣ እወድሃለሁ፡፡ 2 ያሕዌ፣ እንደ ታላቅ አለት ነው፣ በዚህ አለት ላይ ስወጣ ጠላቴ አያገኘኝም፡፡ እንደ ጠንካራ መሸሸጊያ ነው፣ ለመሸሸግ ወደ እርሱ እሮጣለሁ፡፡ ጋሻ ወታደርን እንደሚከልለው እርሱ ይከልለኛል፣ የሚጠብቀኝ የምታመንበት እርሱ ነው፣ በታላቅ ኃይሉ ይከላከልልኛል፡፡ 3 ላመሰግነው የሚገበውን፣ ያሕዌን እጠራለሁ፣ ከጠላቶቼም ይታደገኛል፡፡ 4 በዙሪያዬ ያሉት ሁሉ ሊገድሉኝ የሚችሉ አደገኛ ሁኔታዎች ናቸው፣ በላዬ እንደሚወድቅና እንደሚያጠፋኝ ታላቅ ሞገድ ነው፡፡ 5 በዙሪያዬ ሙታን ገመዳቸውን ይዘው እንደ ከበቡኝ አይነት ነው፣ ወይም እንደሚያጠምደኝና እንደሚገድለኝ ወጥመድ ነው፡፡ 6 በጨነቀኝ ጊዜ፣ ያሕዌን ጠራሁት፣ እርሱም ከመቅደሱ ሆኖ ሰማኝ፣ ለእርዳታ ወደ እርሱ ስጣራ አዳመጠኝ፡፣ 7 ያሕዌ ተቆጣ፣ ምድርም ተንቀጠቀጠች፣ ተራሮችም ከመሠረታችው ተናወጡ! 8 ከአፍንጫው ጭስ እንደሚወጣ እጅግ ተቆጥቶአል፣ የሚነድ እቶን ከአፉ እነደሚወጣ ይመስላል፡፡ 9 ሰማያትን ሰንጥቆ ጥቁር ደመና ከእግሩ በታች ሆኖ ወደ ታች መጣ፡፡ 10 በፍጥነት በሚጓዙ መላእክት ላይ ሆኖ፣ ይበርራል፣ ነፋስም በአጠገቡ ይነፍሳል፡፡ 11 ጨለማ እንደ ብርድ ልብስ በዙሪያው አለ፣ ውኃ ያዘለ፣ ጥቁር ደመና፣ ከብቦታል፡፡ 12 የበረዶ ቋጥኞችና የእሳት ነበልባሎች በዙሪያው አሉ፣ በረዶና የእሳት ፍምም ከሰማይ ወረዱ፡፡ 13 ያሕዌ ከሰማይ ከፍተኛ ድምፁን ላከ፣ በጠላቶቹ ላይ፣ እንደ መብረቅ አንጎዳጎደባቸው፡፡ 14 ፍላጻዎቹንም ላከባቸው እንዲበታተኑም አደረጋቸው፣ ከሰማይ የሚልካቸው የእሳት ነበልባሎች ግራ እንዲጋቡ አደረጋቸው፡፡ 15 ያሕዌ ከቁጣው የተነሣ ጠላቶቹን በእስትንፋሱ ሲገስጽ የውቅያኖስ ታችኛው ክፍል ተገለጠ፣ የምድር መሠረትም በውኃ ሊሸፈን አልቻለም! 16 ከሰማይ ወርዶ ጥልቅ ከሆነው ውቅያኖስ እኔን ጎትቶ ያወጣኝ ያህል ነው፡፡ 17 ከሚጠሉኝና ከጠነከሩብኝ ከጠላቶቼ ታደገኝ፣ በጣም ጠንካሮች ነበሩና፣ በራሴ ላሸንፋቸው አልቻልኩም ነበር፡፡ 18 በመከራዬ ጊዜ፣ ጠላቶቼ አጠቁኝ፣ ነገር ግን ያሕዌ ተከላከለልኝ፡፡ 19 ሙሉ ለሙሉ በሰላም ውስጥ እንድሆን አደረገኝ፣ ወድዶኛልና አዳነኝ፡፡ 20 ትክክል የሆነውን አድርጌአለሁና፣ ያሕዌ ብድራቴን ይከፍለኛል፤ በንጹሕና ሄጄአለሁና እርሱ ይባርከኛል፡፡ 21 የያሕዌን ሕግ ታዝዤአለሁ፣ በእርሱ ላይ አላመጽኩም፡፡ 22 የእርሱን ትእዛዝ ተከትዬአለሁ፣ እርሱን መታዘዜን አላቆምኩም፡፡ 23 ስህተት እንዳልሠራሁ እና ኃጢአትን ከማድረግ ራሴን እንደጠበቅሁ እርሱ ያውቃል፡፡ 24 ትክክል የሆነውን ስላደረግሁ ብድራቴን መለሰልኝ፣ ኃጢአትን እንዳላደረግሁ እርሱ ያውቃልና፡፡ 25 ያሕዌ፣ የአንተን ቃል ኪዳን በታማኝነት ለሚጠብቁት፣ አንተ ታማኝ ነህ፣ ክፉ የሆነውን ለማያደርጉ አንተ ሁልጊዜ መልካምን ታደርግላቸዋለህ፡፡ 26 ለሌች ታማኝ ለሆኑ፣ መልካም ታደርግላቸዋለህ፣ ታምኝ ያልሆኑትን ግን በጥበብህ መልስ ትሰጣቸዋለህ፡፡ 27 ትሁታንን ታድናለህ፣ የሚታበዩትን ግን ታዋርዳቸዋለህ፡፡ 28 በሕይወት አኑረኸኛል፣ ይህንንም ትቀጥላለ፡፡ 29 ጠንካራ እንድሆን አስችለኸኛል፣ ስለሆነም የጠላቶቼን ወታደሮች መስመር ማጥቃትና ማሸነፍ እችላለሁ፣ በአንተ እርዳታ የጠላቶቼን ከተሞች ቅጥር እዘላለሁ፡፡ 30 የእኔ አምላክ ያሕዌ የሚያደርገው ሁሉ ፍጹም ነው፣ ስለዚህ ቃል ኪዳኑን እንደሚፈጽም በእርሱ ልንተማመን እንችላለን፡፡ የእርሱን ጥበቃ ፈልገው ወደ እርሱ ለሚሄዱ እርሱ ጋሻቸው ነው፡፡ 31 ያሕዌ እርሱ ብቻ አምላክ ነው፣ የምንሸሸግበት ትልቅ አለታችን እርሱ ብቻ ነው፡፡ 32 እግዚአብሔር ጠንካራ እንድሆን የሚያስችለኝና፣ በምሄድባቸውም መንገዶች ሁሉ የሚጠብቀኝ ነው፡፡ 33 አጋዘን በተራሮች ላይ እንደሚራመድ ያለ መሰናከል እንድጓዝ የሚያስችለኝ እርሱ ነው፡፡ 34 በጦርነት ወቅት ልጠቀምባቸው እንድችል ጠንካራ ቀስቶችን መገተር ያስተምረኛል፡፡ 35 ያሕዌ፣ በጋሻህ ጠብቀኝ አድነኝም፣ አንተ ኃያል ነህና በሰላም ልትጠብቀኝ ይቻልሃል፡፡ አንተ ረድተኸኛልና ጠንካራ ሆኜአለሁ፡፡ 36 መንገዴን አስተካከልህ፣ ስለዚህ አሁን እግሮቼ አይንሸራተቱም፡፡ 37 ጠላቶቼን አሳደድኳቸው ያዝኩአቸውም፣ ፈጽሜ ሁሉንም ድል እስካደርጋቸው ድረስ አልቆምም፡፡ 38 በመታኋቸው ጊዜ፣ ደግመው ሊነሱ አልቻሉም፣ ተሸንፈው፣ በመሬት ላይ ተዘረሩ፡፡ 39 በጦርነት ተዋጊ እንድሆንና ጠንካራ አድርገኸኛልና ጠላቶቸን አሸንፌአቸዋለሁ፡፡ 40 ጠላቶቼን አሳልፈኸ ሰጠኸኝ፣ አንገታቸውን እንድመታ አደረግኸኝ፡፡ የጠሉኝን ሁሉ አጠፋኋቸው፡፡ 41 የሚረዳቸው ፈልገው ጮሁ፣ ነገር ግን ማንም አላዳናቸውም፡፡ ወደ ያሕዌም ጮሁ፣ ነገር ግን እርሱም አልረዳቸውም፡፡ 42 ዱቄት አደረግኋቸው፣ ነፋስ ጠርጎ እንደሚወስደው አቧራ ሆኑ፣ ሰዎች ቆሻሻን ወደ መንገድ እንደሚጥሉ፣ እኔ|ም እነርሱን ጣልኳቸው፡፡ 43 የተዋጉኝን ሁሉ እንዳሸንፋቸው ረድተኸኛል፣ የብዙ ሕዝቦችም መሪ አድርገኸኛለ፣ ካሁን በፊት የማላውቃቸው ሰዎች በመንግስቴ ተገዝተውልኛል፡፡ 44 እንግዶች ሰዎች ስለ እኔ ሲሰሙ፣ ይሸማቀቃሉ ይታዘዙኝማል፡፡ 45 አንድም ብርታት የላቸውም፣ ከተደበቁበት ጉድጓድ ውስጥ እየተንቀጠቀጡ ወደ እኔ ይመጣሉ፡፡ 46 ይሕዌ ሕያው ነው! ትልቅ አለት የሆነኝና የተሸሸግሁበት እርሱ የተመሰገነ ይሁን! ያዳነኝን እግዚአብሔርን አከብራለሁ! 47 ጠላቶቼን እንድበቀላቸው አስችሎኛል፣ መንግሥታትን እንዳሸንፋቸውን በእነርሱም ላይ እንድገዛ አስችሎኛል፡፡ 48 ከጠላቶቼ ታድጎኛል፣ ከፍ ከፍ አድርጎኛል ስለዚህ ጠላቶቼ ሊደርሱብኝና ሊያጠቁኝ አይችሉም፡፡ 49 ስለዚህ አመሰግነዋለሁ፣ ለአሕዛም ያደረገውን ታላቅ ነገር እናገራለሁ፡፡ 50 ንጉሥ ያደረገኝ እርሱ፣ ጠላቶቼን በኃይል እንዳሸንፋቸው ያስቻለኝ፣ በቃል ኪዳኑ እንደተናገረው በታማኝነት ወድዶኛል፡፡ ንጉሥ ይሆን ዘንድ የመረጥኩት ዳዊት፣ በማለት ፍቅሩን ገልጾልኛል፣ ለእኔ ብቻ ሳይሆን ለዘሬ ሁሉ በታማኝነት ፍቅሩን ይገልጻል፡፡
Chapter 19
ዳዊት ለመዘምራን አለቃ የጻፈው መዝሙር፡፡ 1 ሰዎች እግዚአብሔር በሰማያት ያሰቀመጣቸውን ነገሮች ሁሉ ሲመለከቱ፣ እርሱ እጅግ ታላቅ እንደሆነ ሊያስተውሉ ይችላሉ፤ እርሱ ታላላቅ ነገሮችን ማየት ይችላሉ፣፣ 2 ቀን በቀን ፀሐይ የእርሱን ግርማ እንደምታውጅ አይነት ነው፣ በየሌሊቱም ጨረቃና ከዋክብት እርሱ የፈጠራቸው መሆኑን እንደሚያውቁ ይናገራሉ፡፡ 3 በእርግጥ እነርሱ አይናገሩም፣ ቃላትም የላቸውም፣ ማንም ሰው የሚሰማው ድምፅም የላቸውም፡፡ 4 ነገር ግን ስለ እግዚአብሔር የሚያውጁት በአለም ሁሉ ይሰማል፣ በምድር ዳርቻ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ያውቁታል፡፡ ፀሐይን በሰማይ ላይ አስቀምጦአታል፡፡ 5 ሙሽራው ከሰርጉ በኋላ ደስ እያለው ከመኝታ ቤቱ እንደሚወጣ፣ ፀሐይም በየማለዳው ትወጣለች፣ ልክ እንደ አንድ ጠንካራ ሯጭ ውድድሩን ለመጀመር እንድሚጓጓ አይነት ነው፡፡ 6 ፀሐይ ከሰማይ አንደኛው ዳርቻ ወጥታ ሰማዩን ሁሉ አቋርጣ ወደ ሌላኛው የሰማይ ዳርቻ ትጠልቃለች፣ ከእርሷ ሙቀት የሚሰወር የለም፡፡ 7 ያሕዌ የሰጠን ትእዛዛት ፍጹማን ናቸው፣ ያነቃቁናል፡፡ ያሕዌ የነገረን ሁሉ ፈጽሞ እንደማይቀየር እርግጠኞች ልንሆን እንችላለን፡፡ እነርሱን በመማር ካሁን ቀደም ያልተማሩ ሰዎች ጥበብን ያገኛሉ፡፡ 8 የያሕዌ ሕጎች በጎ ናቸው፣ በምንታዘዛቸው ጊዜ፣ ደስተኞች እንሆናለን፡፡ የያሕዌ ትእዛዛት ግልጽ ናቸው፣ በምናነባቸው ጊዜ እግዚአብሔር እንዴት ብንመላለስ እንደሚወድ መረዳት እንጀምራለን፡፡ 9 ሰዎች ያሕዌን ያከብሩት ዘንድ መልካም ነው፣ ያ ለዘላለም ሊያደርጉት የሚገባ ነገር ነው፡፡ ያሕዌ ያወጀው ሁሉ በጎ ነው፣ ሁልጊዜም ትክክል ነው፡፡ 10 እግዚአብሔር የወሰናቸው ነገሮች ሁሉ ፣ ከወርቅ፣ እጅግም ከነጠረው ወርቅ ይልቅ የከበሩ ናቸው፡፡ ከማርና ከማር ወለላም ይልቅ ጣፋጭ ናቸው፡፡ 11 ከዚህም በላይ፣ በማነባቸው ጊዜ የትኞቹ ነገሮች ባደርጋቸው መልካም እንደሆኑ፣ የትኞቹ ደግሞ ክፉ እንደሆኑ እማራለሁ፣ ለምንታዘዛቸውም ታላቅ ብድራት አለን፡፡ 12 ነገር ግን ማንም ስህተቱን ሊያስተውል አይችልም፣ ስህተት መሆናቸውን ሳላሰተውል ስላደረግኋቸው ነገሮች ሁሉ ይቅር በለኝ፡፡ 13 ስህተት መሆናቸውን እያወቅሁ ስህተትን እንዳላደርግ ጠብቀኝ፣ ለማድረግ ከምፈልጋቸው ክፉ ነገሮች ጠብቀኝ፡፡ እንዲህ ካደረግህ፣ እነዚህን ኃጢአቶች በማድረግ በደለኛ አልሆንም፣ ታላቂቱንም ኃጢአት በማድረግ በአንተ ላይ እጅግ ዐመጸኛ አልሆንም፡፡ 14 ኦ ያሕዌ፣ አንተ ለእኔ እንደ ታላቅ አለት ነህ በዚያ ለይ ወጥቼ እጠበቃለሁ፣ የምታድነኝ አንተ ነህና፡፡ የምናገረውና የማስበው ሁሉ በፊትህ ያማረ ይሁን፡፡
Chapter 20
1 በመከራ ጊዜ ወደ ያሕዌ ስትጮህ እርሱ እንዲረዳህ እንመኛለን! አባታችን ያዕቆብ ያከበረው እግዚአብሔር፣ ከጠላቶችህ እንዲጠብቅህ እንመኛለን፡፡ 2 ከተቀደሰው መቅደሱ እንዲደርስልህ፣ ከማደሪያው ከጽዮን ተራራ እርዳታው እንዲመጣልህ እንመኛለን፡፡ 3 በመሰዊያው የምታቀርበውን የሚቃጠለውን መሥዋዕት ሁሉ እና ሌሎቹንም መሥዋቶችህን እንዲቀበልህ እንመኛለን፡፡ 4 በልብህ የምትመኘውን ሁሉ እንዲሰጥህ፣ ለመሥራት የምታስበውን ሁሉ እንዲያከናውንልህ እንመኛለን፡፡ 5 ጠላቶችህን በምታሸንፍበት ጊዜ፣ በደስታ እንጮሃለነን፡፡ እግዚአብሔር እንደረዳህ ላማስታወቅ ምልክትን ከፍ አድርገን እናነሳለን፡፡ ያሕዌ የለመንከውን ሁሉ እንዲያደርግልህ እመኝልሃለሁ፡፡ 6 እኔ አሁን ንጉሥ እንድሆን የመረጠኝ ያሕዌ፣ እንደታደገኝ አውቃለሁ፡፡ ከሰማይ ከተቀደሰው ሥፍራው ይመልስልኛል፣ በታላቅ ኃይሉም ያድነኛል፡፡ 7 አንዳንድ ነገሥታት ብዙ ሰረገላ ስላላቸው ጠላቶቻቸውን እንደሚያሸንፉ ይተማመናሉ፣ ሌሎችም ፈረሶቻቸው ጠላቶቻቸውን ለማሸነፍ እንደሚያስችሉአቸው ይተማመናሉ፣ እኛ ግን በያሕዌ በአምላካችን ኃይል እንታመናለን፡፡ 8 እነርሱ ተሰነካከሉ ወደቁም፣ እኛ ግን ጠነከርን ጸንተንም ቆምን፡፡ 9 ጠላቶቻችንን እንድናሸንፍ፣ ያሕዌ ንጉሡን እርዳው! እንድትረዳን ወደ አንተ ስንጣራ መልስልን!
Chapter 21
ዳዊት ለመዘምራን አለቃ የጻፈው መዝሙር፡፡ 1 ያሕዌ፣ ንጉሥ ያደረግኸው ሰው እጅግ ደስተኛ ነው፣ ብርታት እንዲያገኝ አድርገኸዋልና፡፡ ጠላቶቹን እንዲያሸንፍ አስችለኸዋልና ሐሴትን አድርጎአል፡፡ 2 እጅግ የተመኘውን ነገር ሁሉ ሰጥተኸዋል፣ እንድታደርግለት የለመነህን ሁሉ አድርገህለታል፡፡ 3 እጅግ ታላላቅ ነገሮችን አድርገኸለታል፡፡ የወርቅ ዘውድን በራሱ ላይ አደረግህለት፡፡ 4 ረጅምንም ዕድሜ ለመነህ፣ ለረጅም ዘመን እንዲኖር ፈቀድክለት፡፡ 5 እንደ ንጉሥ ኃይሉ እጅግ ብርቱ ነው ምክንያቱም አንተ በጠላቶቹ ላይ ድልን ሰጥተኸዋልና፡፡ 6 አንተ ለዘላለም ትባርከዋለህ፣ በፊትህም ደሰተኛ እንዲሆን አድርገኸዋል፡፡ 7 ያሕዌ፣ አንተ ሁሉን ቻይ አምላክ ነህ፣ ንጉሡም በአንተ ይታመናል፡፡ አንተ በታማኝነት ወድደኸቃልና፣ አጥፊ ነገር በእርሱ ላይ አይሆንም፡፡ 8 ጠላቶቹን ሁሉ፣ የሚጠሉትንም ሁሉ እንዲያጠፋ ታስችለዋለህና፡፡ 9 በምትገለጥበት ጊዜ፣ በሚነደው እቶን ውስጥ ትጨምራቸዋለሀ፡፡ አንተ በእነርሱ ተቆጥተሃልና ትውጣቸዋለህ፣ እቶኑም ይበላቸዋል፡፡ 10 ልጆቻቸውንም ከዚሀ ምድር ታስወግዳለህ፣ ዝርያቸውም ሁሉ ይጠፋሉ፡፡ 11 አንተን ይጎዱ ዘንድ ፈለጉ፣ ነገር ግን ያቀዱት ሁሉ አይሳካም፡፡ 12 ቀስትህን ትልካለህ እነርሱም ይጠፋሉ፡፡ 13 ያሕዌ፣ አንተ እጅግ ኃያል መሆንህን አሳየን! ይህን ስታደርግ፣ ስለ ኃያልነትህ በምሥጋና እንዘምርልሃለን፡፡
Chapter 22
ዳዊት ለመዘምራን አለቃ የጻፈው መዝሙር፣ በንጋት ኃይል ቅላጼ የሚዘመር፡፡ 1 አምላኬ፣ አምላኬ፣ ስለምን ተውከኝ? ለምንስ ከእኔ ሩቅ ሆንክ? ስለምንስ አትሰማኝም? ስሰቃይና ስቃትት ለምን አትሰማኝም? 2 አምላኬ፣ በየቀኑ ወደ አንተ እጣራለሁ፣ አንተ ግን አትሰማኝም፡፡ በሌሊትም ጠራሃለሁ፣ ፈጽሞም ዝም አላልኩም፡፡ 3 ነገር ግን አንተ ቅዱስ ነህ፡፡ እንደ ንጉሥ በዙፋንህ ላይ ተቀምጠሃል፣ እኛ የእስራኤል ሕዝቦች እናመሰግንሃለን፡፡ 4 አባቶቻችን በአንተ ታመኑ፡፡ በአንተ ታመነዋልና፣ ታደግሃቸው፡፡ 5 ወደ አንተ ለርዳታ ሲጣሩ፣ አዳንካቸው፡፡ በአንተ ታመኑ፣ አላፈሩም፡፡ 6 ነገር ግን እኔን አልታደግኸኝም፣ ሰዎች ንቀውኛል፣ እንደ ሰውም አልቆጠሩኝም፡፡ ትል እንደሆንኩ ያስባሉ! እያንዳንዱ ያዋርደኛል፣ ይንቀኛልም፡፡ 7 የሚያየኝ ሁሉ ይሳለቅብኛ፡፡ ያሽሟጥጠኛል፣ እጃቸውን እያወዛወዙ ክፉ እንዳደረገ ሰው ይሰድቡኛል፡፡ እንዲህ ይላሉ 8 በያሕዌ ተማምኖአል፣ ያሕዌ ያድነው! ያሕዌ በእርሱ ደስ እንደሚሰኝ ተናግሮአል፣ እነደዚሀ ከሆነ፣ ያሕዌ ይታደገው! 9 ስወለድ እንዳደረግኸው አሁን የማትጠብቀኝ ለምንድን ነው; የእናቴን ጡት ስጠባ ጀምሮ፣ በአንተ መታመንን አስተምረኸኛል፡፡ 10 ልክ ገና ስወለድ ጀምሮ ወስደህ እንዳሳደግኸኝ ነው፡፡ ከኅፃንነቴ ጀምሮ አንተ አምላኬ ነህ፡፡ 11 የሚያስጨንቁኝ ጠላቶቼ በቅርብ ናቸውና፣ የሚረዳኝም የለምና ከእኔ አትራቅ፡፡ 12 ጠላቶቼ እንደ ዱር በሬዎች ከበቡኝ፣ ጠንካራ ሰዎችም፣ በባሻን አካባቢ በተራሮች ላይ እንደሚግጡ ብርቱ በሬዎች ከበቡኝ፡፡ 13 የሚያጠቃቸውን አራዊት ለመብላት እንደሚያገሣ አንበሳ፣ ሊገድሉኝ ወደ እኔ እየሮጡ ይመጣሉ፣ አፋቸው እንደተከፈቱ አንበሶች፣ የያዙአቸውን በጣጥሰው ለመብላት እንደተዘጋጁ ናቸው፡፡ 14 እኔ ሙሉ ለሙሉ ደክሜአለሁ፣ አጥንቶቼም ከመጋጠሚያቸው ለቅቀዋል፡፡ ከእንግዲህ እግዚአብሔር ያድነኛል ብዬ አልጠብቅም፣ ሙሉ በሙሉ ተስፋ ቆርጫለሁ፡፡ 15 ተሰብሮ በፀሐይ እንደ ደረቀ ሸክላ ኃይሌ ሁሉ አልቆአል፡፡ ምላሴ ከትናጋው ጋር እስኪጣበቅ ድረስ እጅግ ተጠምቼአለሁ፡፡ አምላኬ፣ እንድሞትና አቧራ እንድሆን የፈቀድክ ይመስለኛል! 16 ጠላቶቼ እንደ ዱር ውሾች ከብበውኛል፡፡ የክፉ ሰዎች ቡድን፣ ሊያጠቃኝ ተዘጋጅቶ ከብቦኛል፡፡ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ፡፡ 17 እጅግ ደከምኩ፣ ከመክሳቴ የተነሳ አጥንቶቼ ተቆጠሩ፡፡ ጠላቶቼ በሞት አፋፍ መሆኔን እያዩ ይፈነድቁ ነበር፡፡ 18 የለበስኩትን ልብስ ገፍፈው በእጣ ተከፋፈሉት፡፡ 19 ያሕዌ፣ ስለ እኔ ግድ ይበልህ! አንተ የብርታቴ ምንጭ፣ ፈጥነህ ና እርዳኝም! 20 በሰይፋቸው ሊገድሉኝ ከሚፈልጉት ታደገኝ፡፡ እንደ ዱር ውሾች ከመሰሉ ሰዎች ኃይል አድነኝ፡፡ 21 እንደ አንበሳ አፋቸውን መንጋጋቸውን ከከፈቱና ሊያኝኩኝ ከሚፈልጉ ነጥቀህ አውጣኝ! በቀንዶቻቸው ሌሎችን አራዊት የሚዋጉትን የዱር አራዊት ከሚመስሉ ሰዎች ጥቃት ጎትተህ አውጣኝ! 22 ከእነርሱ ካዳንከኝ፣ አንተ ታላቅ መሆንን ለእስራኤል ሁሉ አውጃለሁ፡፡ አንተን ለማምለክ ከተሰበሰቡት ሕዝብህ ጋር አብሬ አመሰግንሃለሁ፡፡ 23 ታላቅ አክብሮት ለያሕዌ ያላችሁ፣ እናንተ ሕዝቦች፣ አመስግኑት! የያዕቆብ ዘር ሁላችሁ፣ ያሕዌን አክብሩት! እናንት የእስራኤል ሕዝቦች ክብር ስጡት! 24 መከራ የሚቀበሉትን አልናቀምና፣ ለጩኸታቸውም ዝም አላለም፣ ፊቱንም ከእነርሱ አልሸሸገም፡፡ ለእርዳታ ወደ እርሱ ሲጮሁ ሰምቶአቸዋል፡፡ 25 ያሕዌ፣ በሕዝብሕ ታላቅ ጉባዔ፣ ስላደረግኸው ሁሉ አመሰግንሃለሁ፡፡ ለአንተ ታላቅ አክብሮት ባላቸው መካከል፣ ቃል የገባሁትን መሥዋዕት አቀርባለሁ፡፡ 26 ወደ ግብዣዬ የጋበዝኩአቸው ድሆች የፈለጉትን ያህል በልተው ይጠግባሉ፡፡ ያሕዌን ለማምለክ የመጡ ሁሉ ያመሰግኑታል፡፡ እግዚአብሔር ረጅምና ደስተኛ ሕይወት እንዲሰጣችሁ እጸልይላችኋለሁ፡፡ 27 አሕዛብ በሩቅም ያሉ ሕዝቦች ሁሉ፣ ስለ ያሕዌ ያስባሉ፣ ወደ እርሱም ይመለሳሉ፣ ከሁሉም ጎሳ የሆኑ ሁሉ ለእርሱ ተደፍተው ይሰግዳሉ፡፡ 28 ያሕዌ ንጉሥ ነውና፣ አሕዛብን ሁሉ ይገዛል፡፡ 29 በምድር ያሉ ባለጠጎች ሁሉ በፊቱ ይሰግዱለታል፡፡ አንድ ቀን ይሞታሉ፣ ከዚያ ሊያመልጡ አይችሉምና፣ ነገር ግን በፊቱ ለጥ ብለው ይሰግዳሉ፡፡ 30 በሚቀጥለው ትውልድ የሚኖሩ ሰዎች፣ ያሕዌን ያገለግላሉ፡፡ ለልጆቻቸውም ያሕዌ ስላደረገው ነገር ይነግሩአቸዋል፡፡ 31 ገና ያልተወለዱ ሕዝቦች፣ በሚቀጥሉት ዓመታት የሚኖሩ፣ ያሕዌ ሕዝቡን እንዴት እነደታደጋቸው ይማራሉ፡፡ ሕዝቡ "ያሕዌ አድርጎታል" ብለው ይነግሩአቸዋል፡፡
Chapter 23
በዳዊት የተጻፈ መዝሙር 1 ያሕዌ፣ እረኛ ለበጎቹ እንደሚጠነቀቅ ትጠነቀቅልኛለህ፣ ስለዚህ የሚያስፈልገኝ ሁሉ አለኝ፡፡ 2 እረኛ በጎቹን እንዲበሉ አረንጓዴ ሳር ወዳለበት ሥፍራ እንደሚያሰማራቸው፣ ውኃው በቀስታ የሚፈስስ ወንዝ ባለበት መስክም እንዲያርፉ እንደሚያደርጋቸው አንተም በላም እንዳርፍ ታስችለኛለህ ፡፡ 3 ኃይሌን አደስክልኝ፣ እንዳከብርህም፣ የቀናውን መንገድ አሳየኸኝ፡፡ 4 ልሞት በምችልባቸው አደገኛ ቦታዎች መካከል እንኳን ስራመድ፣ አንተ ከእኔ ጋር ስላለህ አንዳችም አልፈራም፡፡ እረኛ በጎቹን እንደሚጠብቅ ትጠብቀኛለህ፡፡ 5 ጠላቶቼ እኔን ሊያዩኝ በሚችሉበት ሥፍራ ታላቅ ገበታን አዘጋጀኽልኝ፣ እንደምታከብረው እንግዳም ተቀበልከኝ፡፡ እጅግ ብዙ በረከቶችንም ሰጠኸኝ፡፡ 6 በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ቸርነትህና ምሕረትህ እንደሚከተሉኝ እርግጠኛ ነኝ፣ ኦ ያሕዌ፣ በቤትህ ለዘላለም እኖራለሁ፡፡
Chapter 24
በዳዊት የተጻፈ መዝሙር፡፡ 1 ምድርና በውስጧ ያለው ሁሉ የያሕዌ ነው፣ በምድር ያሉ ሰዎች ሁሉ የእርሱ ናቸው፤ 2 ምድርን በውኃ ላይ መሥርቶአታል፣ በሥሯ ጥልቅ ፈሳሾች ይገኛሉ፡፡ 3 በኢየሩሳሌም ወደሚገኘው ወደ ጽዮን ተራራ ማን ይወጣል፣ ያሕዌን በተቀደሰ መቅደሱ ማን ያመልካል? 4 ተግባራቸውና አሳባቸው ንጹሕ የሆኑ ሰዎች ብቻ ናቸው፣ ጣዖትን የማያመልኩ፣ እውነትን ለመናገር ቃል የሚገቡ የማይዋሹ ናቸው፡፡ 5 ያሕዌ ይባርካቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ሲፈርድላቸው፣ ይታደጋቸዋል ስህተት እንዳልሰሩም ይመሰክርላቸዋል፡፡ 6 ወደ እግዚአብሔር የሚቀርቡ እነርሱ ናቸው፣ እኛ እስራኤላውያን የምናመልከውን እግዚአብሔርን የሚያመልኩ እነርሱ ናቸው፡፡ 7 የክብር ንጉሥ እንዲገባ በሮችን ክፈቱ! 8 የክብር ንጉሥ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ? እርሱ ብርቱ የሆነው ያሕዌ ነው፣ በጦርነት ጠላቶቹን ድል ያደረገ ያሕዌ ነው፡፡ 9 የክብር ንጉሥ እንዲገባ የመቅደሱን በሮች ክፈቱ! 10 ይህ የክብር ንጉሥ ማን እንደሆነ ታውቃላችሁ; የመላእክት ሠራዊት አዛዥ ያሽዌ ነው፣ የክብር ንጉሣችን እርሱ ነው!
Chapter 25
በዳዊት የተጻፈ መዝሙር፡፡ 1 ያሕዌ፣ ራሴን ለአንተ እሰጣሉ፡፡ 2 አምላኬ፣ በአንተ እታመናለሁ፡፡ ጠላቶቼ እንዲያሸንፉኝና እንዲያሳፍሩኝ አትፍቀድ፡፡ ጠላቶቼ እንዲያሸንፉኝና በእኔ ደስ እንዲላቸው አትፍቀድ፡፡ 3 በአንተ የሚታመኑትን አንዳቸውንም እንዲያፍሩ አትፍቀድ፡፡ በሌሎች ላይ በግብዝነት የሚያደርጉትን አሳፍራቸው፡፡ 4 ያሕዌ፣ ሕይወቴን የምመራበትን መንገድ አሳየኝ፣ አንተ እንደምትወደው እንድመላለስ አስተምረኝ፡፡ 5 የአንተን እውነት በመታዘዝ ሕይወቴን እንድመራ አስተምረኝ፣ ምክንያቱም አንተ ያዳንከኝ አምላኬ ነህና፡፡ ቀኑን ሙሉ በአንተ እታመናለሁ፡፡ 6 ያሕዌ፣ ለእኔ ያደረግኸውን ምሕረትህን እና ከቃል ኪዳንህ የተነሣ በታማኝነት እንደወደድከኝ አትርሳ፣ ከቀድሞ ጀምሮ ያደረግኸው እንዲህ ነበርና፡፡ 7 በወጣትነቴ ያደረግሁትን ኃጢአቴንና ዐመጻዬን ይቅር በለኝ፣ ይህን የምለምንህ አንተ በቃል ኪዳንህ ተስፋ እንደገባኸው ሕዝብህን በታማኝነት ስለምትወድና መልካምን ነገር ስለምታደርግላቸው ነው፡፡ ያሕዌ፣ አትርሳኝ! 8 ያሕዌ መልካምና ቅን ነው፣ ኃጢአተኛች ሕይወታቸውን እንዴት መምራት እንዳለባቸው መንገድን ያሳያቸዋል፡፡ 9 ለትሁታን ሰዎችም ሊያደርጉት የሚገባውን ትክክለኛ ነገር ያሳያቸዋል፣ እርሱ እንዲያደርጉት የሚወድደውን ነገርም ያስተምራቸዋል፡፡ 10 እርሱ ሁል ጊዜ በታማኝነት ይወደናል ቃል ኪዳኑን ለሚታዘዙትና እርሱ የሚያዛቸውን ለሚያደርጉት ቃል እንደገባው ያደርግላቸዋል፡፡ 11 ያሕዌ፣ አንተን እንዳከብርህ እጅግ ብዙ የሆኑትን ኃጢአቶቼን ይቅር በለኝ፡፡ 12 ለአንተ ታላቅ አክብሮት ላላቸው፣ ሕይወታቸውን የሚመሩበትን ትክክለኛውን መንገድ ታሳያቸዋለህ፡፡ 13 ሁልጊዜም ይበለጽጋሉ ዘራቸውም ምድሪቱን ይወርሳል፡፡ 14 ያሕዌ ለእርሱ ታላቅ አክብሮት ላላቸው ባልንጀራ ነው፣ ከእነርሱ ጋር የገባውን ቃል ኪዳን ያስተምራቸዋል፡፡ 15 እኔ ሁል ጊዜ ያሕዌን እንዲረዳኝ እለምናለሁ፣ እርሱም ከአደጋ ያወጣኛል፡፡ 16 ያሕዌ፣ እኔ ብቸኛ ነኝና፣ ከችግሬ የተነሳ ተስፋ ቆርጫለሁና፣ በምሕረትህ አትኩረህ እየኝ፡፡ 17 የማፍርባቸው ብዙ መከራዎች አሉብኝና ከእነዚህ ሁሉ አድነኝ፡፡ 18 እንደተጨነቅሁና እንደተረበሽኩ ተመልከት፣ ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር በለኝ፡፡ 19 ብዙ ጠላቶች እንዳሉብኝ ተመልከት፣ ምን ይኸልም እንደሚጠሉኝ ተመልከት፡፡ 20 ከእነርሱ ጠብቀኝ ታደገኝም፣ እንዳላፍር ጠላቶቼ እንዲያሸንፉኝ አትፍቀድላቸው፣ በአንተ ለመሸሸግ መጥቼአለሁና፡፡ 21 በአንተ ታምኜአለሁና መልካምንም ነገር በታማኝነት አድርጌአለሁና አድነኝ፡፡ 22 እግዚአብሔር ሆይ፣ እኛን እስራኤላውያን ሕዝብሕን ከመከራችን ሁሉ ታደገን!
Chapter 26
በዳዊት የተጻፈ መዝሙር፡፡ 1 ያሕዌ፣ እኔ ንጹሕ መሆኔን ፍረድልኝ፡፡ ሁልጊዜ ትክክል የሆነውን አድርጌአለሁና፣ በአንተ ታምኛለሁና እንደምትረዳኝም ፈጽሞ አልጠራጠርም፡፡ 2 ያሕዌ፣ ያደረግሁትን ሁሉ መርምር ፈትነኝም፣ በውስጤ ያለውን ጥልቅ የሆነውን አሳቤን መርምር፡፡ 3 አንተ ለቃል ኪዳንህ እውነተኛና እኔንም በታማኝነት የምትወደኝ መሆንህን ፈጽሞ አልረሳም፣ ሕይወቴን እንደታማኝነትህ እመራለሁ፡፡ 4 ከውሸተኞች ጋር ጊዜ አላጠፋም፣ ከግብዞችም ጋር አልሆንም፡፡ 5 ከክፉ ሰዎችም ጋር መሆንን አልወድም፣ ኃጢአተኞችንም ከእኔ አራቅሁ፡፡ 6 ያሕዌ፣ ንጽሕናዬን ለማሳየት እጆቼን ታጥቤአለሁ፡፡ በመሰዊያህ ዙሪያ ከሚጓዙ ጋር ስሄድ፣ 7 አንተን ለማመስገን መዝሙሮችን እንዘምራለን፣ አንተ ስለሠራኸው ታላቅ ነገር ለሌሎች እንናገራለን፡፡ 8 ያሕዌ፣ አንተ በምትኖርበት ቤት፣ ክብርህም በሚገለጽበት ሥፍራ መሆን እወዳለሁ፡፡ 9 ኃጢአተኞችን እንደምታጠፋ እኔን አታጥፋኝ፣ ሰዎችን የሚገድሉትን እንደምትገድል፣ 10 ክፉ ነገርን ለማድረግ ዝግጁ የሆኑትን ሰዋች፣ ሁልጊዜም ጉቦ የሚቀበሉትን እንደምትቀጣ እኔን አትግደለኝ፡፡ 11 እኔ ግን፣ ሁልጊዜ መልካም የሆነውን ለማድረግ እጥራለሁ፡፡ ስለዚህ በምሕረትህ ተመልከታኝ አድነኝም፡፡ 12 በቅንነት እቆማለሁና፣ ሕዝቦችህ ሁሉ ሲሰበሰቡ፣ አመሰግንሃለሁ፡፡
Chapter 27
በዳዊት የተጻፈ መዝሙር፡፡ 1 ያሕዌ ሕይወት የሰጠኝና ያዳነኝ ነው፣ ስለዚህ ማንንም አልፈራም፡፡ ያሕዌ መሸሸጊያዬ ነው፣ ፈጽሞ አልፈራም፡፡ 2 ክፉ አድራጊዎች ሊያጠፉኝ ወደ እኔ ቀረቡ፣ ነገር ግን ተሰነካከሉና ወደቁ፡፡ 3 ሠራዊት ቢከብበኝም እንኳን፣ ፈጸሞ አልፈራም፡፡ ቢያጠቁኝም እንኳ፣ በእግዚአብሔር እታመናለሁ፡፡ 4 ያሕዌን የለመንኩት አንድ ነገር ነው፣ የምሻውም እርሱኑ ብቻ ነው፣ በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በያሕዌ ቤት እርሱን በየቀኑ አመልክ ዘንድ፣ የያሕዌን ድንቅ ነገር እመለከት ዘንድ፣ እንዳደርገው የሚፈልገውን እጠይቀው ዘንድ ነው፡፡ 5 በመከራዬ ጊዜ ይጠብቀኛል፣ በተቀደሰው ድንኳኑ ይሸሽገኛል፡፡ በዓለት ላይም ከፍ ከፍ ያደርገኛል፡፡ 6 ስለሆነም በጠላቶቼ ላይ ድልን አገኛለሁ፡፡ በተቀደሰው ድንኳኑ ውስጥ መስዋዕትን ሳቀርብ በደስታ እልል እላለሁ፣ ለያሕዌ በዘማሬ ምሥጋናን አቀርባለሁ፡፡ 7 ያሕዌ፣ ወደ አንተ ስጣራ ስማኝ፡፡ በምሕረትህ ተመልከተኝ፣ ጸሎቴንም መልስልኝ፡፡ 8 ከውስጥ ማንነቴ አንተን ማምለክ እመኛለሁ፣ ያሕዌ፣ ወደ አንተ ለመጸለይ ወደ መቅደስህ እመጣለሁ፡፡ 9 እኔ የአንተ ባሪያ ነኝ፣ ተቆጥተህ አትጣለኝ፣ ፊትህንም ከእኔ አትሰውር፡፡ ሁልጊዜ ረድተኸኛል፡፡ ያዳንከኝ አንተ ነህ፡፡ ስለሆነም አትጣለኝ፡፡ 10 አባቴና እናቴ ቢተዉኝ፣ አንተ ግን ያሕዌ፣ ሁልጊዜ ትጠነቀቅልኛለህ፡፡ 11 ያሕዌ፣ አንተ የምትፈልገውን እንዳደርግ አስተምረኝ፣ ብዙ ጠላቶች አሉኝና በቀና መንገድ ምራኝ፡፡ 12 ጠላቶቼ የሚፈልጉትን በእኔ ላይ እንዲያደርጉ አትፍቀድላቸው፣ ስለ እኔ ብዙ ሐሰትን ተናግረዋልና፣ ሊያስፈራሩኝም ብዙ የዐመጻ ሥራ ሠርተውብኛል፡፡ 13 በሕይወት ዘመኔ ሁሉ አንተ ለእኔ መልካም መሆንህን ከማላምን ብሞት ይሻለኛል፡፡ 14 ስለዚህ በያሕዌ ታመን! በርታ ጠንክርም፣ የእርሱን እርዳታ በመተማመን ተጠባበቅ፡፡
Chapter 28
በዳዊት የተጻፈ መዝሙር፡፡ 1 ያሕዌ፣ ወደ አንተ እጣራለሁ፣ አንተ በላዩ ወጥቼ እንደምሸሸግበት ትልቅ አለት ነህ፣ ጸሎቴን ከመመለስ ዝም አትበ፣ ዝም ካልከኝ በመቃብር እንደሉት እሆናለሁና፡፡ 2 እንድትረዳኝ ወደ አንተ ስጣራ አድምጠኝ፣ ፊቴን ወደ ቅዱሱ ሥፍራህ አድርጌ እጆቼንም ወደ አንተ አንስቼ በተቀደሰው ድንኳንህ ስጸልይ ስማኝ፡፡ 3 ክፉ ከሚያደርጉ፣ ከኃጢአተኞች ጋር አትውሰደኝ፣ በውስጣቸው ጥላቻ ሞልቶ፣ መልካም ቃላትን ለሰዎች በማስመሰል ከሚናገሩት ጋር አትቁጠረኝ፡፡ 4 እነዚህን ሰዎች ለሠሩት ሥራ የሚገባቸው ነውና ቅጣቸው፣ እንደ ክፉ ሥራቸው ቅጣቸው፡፡ 5 ያሕዌ፣ ስለ ሠራኸው ድንቅ ሥራ ስለ ፈጠርከውም ነገር ሁሉ አላሰቡምና፣ ፈጽመህ አጥፋቸው፣ ዳገመኛም አይታሰቡ፡፡ 6 ያሕዌን አመሰግናለሁ፣ ወደ እርሱ ስጣራ ልመናዬን ሰምቶአልና! 7 ያሕዌ ጠንካራ አድርጎኛል፣ እንደ ጋሻም ከልሎኛል፣ በእርሱ እታመናለሁ፣ እርሱ ያድነኛል፡፡ ስለዚሀ በውስጤ እጅግ ደስ ይለኛል፣ ፈቅጄም አመሰግነዋለሁ ለእርሱ እዘምራለሁ፡፡ 8 ያሕዌ ኃይላችነ ነው እርሱ ይጠብቀናል፣ ንጉሥ እንድሆን የቀባኝን፣ እኔንም አድኖኛል፡፡ 9 ያሕዌ፣ ሕዝብህን አድን፣ የአንተ የሆኑትን ባርካቸው፡፡ እረኛ ለበጎቹ እንደሚጠነቀቅ ተጠንቀቅላቸው፣ ለዘላለም ጠብቃቸው፡፡
Chapter 29
በዳዊት የተጻፈ መዝሙር 1 እናንተ ታላላቅ ሰዎች፣ ያሕዌን አመስግኑ እርሱ ክቡርና ኃያል ነውና፡፡ 2 የተከበረ መሆኑን አውጁ፣ ምርጥ ልብሳችሁን ለብሳችሁ፣ ለያሕዌ ስገዱለት፡፡ 3 የያሕዌ ድምፅ ከውቅያኖሶች በላይ ተሰማ፣ የክብር አምላክ አንጎደጎደ፡፡ በብዙ ውኆች ላይ ታየ፡፡ 4 ድምፁ በኃይልና በታልቅ ክብር ነው፡፡ 5 የያሕዌ ድምፅ ታላቅ ዝግባን፡ የሊባኖስን ዝግባ ይሰብራል፡፡ 6 መሬት እንድትንቀጠቀጥ አድርጎ ሊባኖስን እንደ ጥጃ ያዘልላታል፣ አንድ ቀንድ እንዳለው አውሬ ልጅ የአርሞንኤም ተራራን ያንቀጠቅጠዋል፡፡ 7 የያሕዌ ድምፅ መብረቁን እንዲያበራ ያዝዘዋል፡፡ 8 ምድረ በዳውንም ያናውጣል፣ የቃዴስን ምድር በዳ ያናውጣል፡፡ 9 የያሕዌ ድምፅ ጫካዎችን ይገልጣል፣ ሕዝቡ በቤተ መቅደስ ‹‹እግዚአብሔር ይመስገን!›› እያሉ ሲጮሁ የዛፎቹ ቅጠሎች ይራገፋሉ፡፡ 10 ያሕዌ ምድርን በሚሸፍኑ የጥፋት ውኃዎች ላይ ገዢ ነው፣ እርሱ ለዘላለም የሚነግሥ ንጉሣችን ነው፡፡ 11 ያሕዌ ለሕዝቡ ኃይልን ይሰጣል፣ በሰላምም ይባርካቸዋል፡፡
Chapter 30
ዳዊት ለቤተ መቅደሱ ምረቃ የዘመረው መዝሙር፡፡ 1 ያሕዌ፣ አንተ ታድገኸኛልና አመሰግንሃለሁ፡፡ እንድሞት ወይም ጠላቴ እንዲያላግጥብኝ አልፈቀድክም፡፡ 2 ያሕዌ፣ አምላኬ፣ በቆሰልኩ ጊዜ እንድትረዳኝ ወደ አንተ ስጣራ፣ አንተ ፈወሰከኝ፡፡ 3 ከመሞት አዳንከኝ፣ ልሞት ተቃርቤ ነበርና፣ ነገር ግን አንተ እንደገና ጤናማ አደረግኸኝ፡፡ 4 ከያሕዌ ጋር ላለው ቃል ኪዳን ታማኞች የሆናችሁ ሁሉ፣ በምሥጋና ዘምሩ! እግዚአብሔር፣ ቅዱሱ፣ ያደረገውን አስታወሱ፣ አመስግኑ! 5 እርሱ ቢቆጣ፣ ለጥቂት ጊዜ ነው፣ መልካምነቱ ግን በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ነው፡፡ በመሸ ጊዜ አልቅሰን ይሆናል፣ ማለዳ ግን ደስታ ይሆናል፡፡ 6 እኔ ግን፣ ‹‹ማንም ሊያሸንፈኝ አይችልም›› ብዬ ለራሴ ስናገር በሰላም ውስጥ ነበርኩ፡፡ 7 ያሕዌ፣ አንተ ለእኔ መልካም ስለሆንክ፣ ከፍ እንዳለ ተራራ ጽኑ እንድሆን አድርገኸኛል፡፡ ነገር ግን ፊትህን ከእኔ እንደሰወርክ በመሰለኝ ጊዜ ፈራሁ፡፡ 8 ስለዚህ ወደ አንተ ተጣራሁ፣ እንድትረዳኝም ተማጸንሁ፡፡ 9 እንዲህም አልሁኝ ‹‹ያሕዌ፣ እኔ ብሞት ምን ትጠቀማለህ? ሙታን ወደአሉበት ሥፍራ ብሄድ በምን መንገድ ለአንተ ጥቅም ይሆናል? ብሞት አንተን ፈጽሞ ላመሰግን እንደማልችል እርግጠኛ ነኝ፣ የአንተን ታማኝነት ለሌሎች መናገር አልችልም! 10 ያሕዌ፣ ስማኝ፣ በምሕረትም ተመልከተኝ! ያሕዌ፣ እርዳኝ!›› 11 ነገር ግን አሁን ፈውሰኸኛል፣ ሐዘኔን ወደ ደስታ ቀይረህ ለወጥከኝ፡፡ ማቄን ከእኔ ወሰድክ፣ የደስታ ልብስም አለበስከኝ፡፡ 12 ስለዚህ ዝም አልልም፣ እዘምርልሃለሁ አመሰግንሃለሁም፡፡ ያሕዌ፣ አንተ አምላኬ ነህ፣ ለዘላለም አመሰግንሃለሁ፡፡
Chapter 31
ዳዊት ለመዘመራን አለቃ የጻፈው መዝሙር፡፡ 1 ያሕዌ፣ በአንተ ለመጠበቅ ወደ አንተ መጥቼአለሁ፣ እንድሸነፍና መሳለቂያ እንድሆን አትፍቀድ፡፡ አንተ ሁልጊዜ መልካም ስለምታደርግ፣ ታደገኝ! 2 ስማኝ፣ አሁን አድነኝ! በላዩ ወጥቼ የምድንበት ታላቅ አለት ሁነኝ፣ የምድንበት ጠንካራ መጠለያ ሁነኝ፡፡ 3 አዎ፣ አንተ አለቴና መጠጊያ ነህ፣ አንተን አመልክሃለሁና ምራኝ፡፡ 4 የጠበቅኸኝ አንተ ነህ፣ ስለዚህ ጠላቶቼ እኔን ለማጥመድ ባስቀመጡት ደብቅ መሰናክል እንዳልወድቅ ጠብቀኝ፡፡ 5 ያሕዌ፣ ልታመንብህ የምችል አምላክ ነህ፣ ስለምትታደገኝ ራሴን ለአንተ ጠበቃ ሰጥቼአለሁ፡፡ 6 ያሕዌ፣ የማይጠቅሙት ጣዖቶችን የሚያመልኩትን ጠላሁ፣ ነገር ግን በአንተ እታመናለሁ፡፡ 7 አንተ በታማኝነት ስለምትወደኝ ሐሴት አደርጋለሁ፡፡ በመከራ ውስጥ በነበርኩ ጊዜ አይተኸኛል፣ ጭንቀቴንና መከራዬን አውቀሃል፡፡ 8 ጠላቶቼ እንዲይዙኝ አልፈቀድክላቸውም፣ ነገር ግን ከአደጋ አዳንከኝ፡፡ 9 አሁን ግን፣ ያሕዌ በምሕረት ተመልከተኝ ተጨንቄአለሁና፡፡ ብዙ አልቅሼአለሁና በትክክል ማየት አልችልም፣ ሙሉ ለሙሉም ደክሜአለሁ፡፡ 10 ከመጨነቄ የተነሣ እጅግ ደክሜአለሁ፣ ዘመኔም እያጠረ ነው፣ ከመከራዎቼ የተነሣ ደካማ ሆኜአለሁ፣ አጥንቶቼ እንኳን እየደከሙ ነው፡፡ 11 ጠላቶቼ ሁሉ ያላግጡብኛል፣ ጎረቤቶቼም ንቀውኛል፣፣ ጓደኞቼ እንኳ አንተ እየቀጣኸኝ መስሎአቸው ፈሩኝ፡፡ በመንገድ ላይም ሲያዩኝ ይሸሹኛል፡፡ 12 ሰዎች ሙታንን እንደሚረሱ እኔንም ረስተውኛል፡፡ እንደ ተሰበረ ሸክላ ጥቅም እንደሌለኝ አሰቡ፡፡ 13 ሰዎች በእኔ ሲያላግጡ ሰማሁ፣ አስፈራሩኝም፡፡ ጠላቶቼ ሊገድሉኝ አቀዱ፡፡ 14 ነገር ግን ያሕዌ፣ በአንተ እታመናለሁ፡፡ በሙሉ መተማን የማመልክህ አምላኬ ነህ እላለሁ፡፡ 15 ሕይወቴ ጠቅላላ በእጅህ ነው፣ ከጠላቶቼ አድነኝ፣ ከሚያጠቁኝ ሁሉ አድነኝ፡፡ 16 ወደ እኔ በቅንነት ተመልከት፣ አድነኝም አንተ በታማኝነት ትወደኛለህና፡፡ 17 ያሕዌ፣ ወደ አንተ እጣራለሁ፣ ሌሎች እንዲንቁኝ አትፍቀድላቸው፡፡ ኃጢአተኞች እንዲናቁ እመኛለሁ፣ ሙታን በጸጥታ ወዳሉበት ስፍራ እንዲወርዱ እመኛለሁ፡፡ 18 ውሸት የሚናገሩትን መናገር እንዳይችሉ ታደርጋቸው ዘንድ እመኛለሁ፡፡ በሚኮሩና በጉረኝነት ሌሎችን በሚኮንኑት ላይ ይህን አድርግባቸው፡፡ 19 ለአንተ ታላቅ አክብሮት ላላቸው ብዙ መልካም ታላቅ ነገሮችን አዘጋጅተሃል፡፡ በአንተ ለመጠበቅ ወደ አንተ ለሚመጡ መልካም ነገሮችን አድርገሃል፣ እያንዳንዱ ይህን ስታደርግ ተመክቶአል፡፡ 20 በሕልውናህ ሰዎችን ከክፉ ሰወርካቸው፣ ሊገድሉአቸው ከሚያሴሩ ጠበቅሃቸው፡፡ ጠላቶቻቸው በእነርሱ ላይ ክፉ ሊናገሩ በማይችሉበት ሥፍራ ሸሸግሃቸው፡፡ 21 ያሕዌን አመስግኑ! ጠላቶቼ የምኖርበትን ከተማ ሲከቡ፣ እርሱ እኔን በታማኝነት እንደሚወደኝ አሳየኝ፡፡ 22 ፈርቼ ወደ አንተ በፍጥነት ስጮኽ ነበር፣ ‹‹ከያሕዌም ተጥዬ ነበር!›› ነገር ግን አንተ ሰማኸኝ ለጩኸቴም መልስ ሰጠኸኝ፡፡ 23 የያሕዌ ወገኖች የሆናችሁ እናንተ ሰዎች፣ ውደዱት! ለእርሱ ታማኝ የሆኑትን ይጠብቃል፣ ነገር ግን የሚኩራሩትን ይቀጣል፣ እንደሚገባቸው መጠን ይቀጣቸዋል፡፡ 24 ያሕዌ ለእናንተ ታላቅ ነገር እንደሚያደርግ በመተማመን የምትጠባበቁ፣ በርቱ ጠንክሩም!
Chapter 32
ሰዎች ጠቢባን እንዲሆኑ የሚረዳቸው የዳዊት መዝሙር 1 እግዚአብሔር አመጻቸውን ይቅር ያላቸው፣ ኃጢአታቸውንም የማይቆጥርባቸው እነርሱ የታደሉ ናቸው! 2 ያሕዌ በደላቸውን የደመሰሰላቸው እና በመንፈሳቸው የማይሸነግሉት ምስጉን ናቸው! 3 ኃጢአቴን ባልተናዘዝኩ ጊዜ፣ ደካማና በሽተና ሆንኩ ቀኑን ሙሉም ቃተትኩኝ፡፡ 4 ያሕዌ፣ ቀንና ሌሊት በብርቱ ቀጣኸኝ፡፡ በበጋ ሞቃት ቀን ውሃ እንደሚተን ኃይሌ እንዲሁ ተነነ፡፡ 5 ከዚያም ኃጢአቴን ለአንተ ተናዘዝኩ፣ ኃጢአቶቼን መደበቅም አቆምኩ፡፡ ለራሴ እንዲህ አልሁ፣ ‹‹የሠራሁትን በደሌን ሁሉ ለያሕዌ አነግራሁ፡፡›› ኃጢአቴን ስናዘዝ፣ ይቅር በለኝ፣ ዳግመኛም በኃጢአቴ በደለኛ አልሆንም፡፡ 6 ስለዚህ አንተን የሚያከብሩ ሰዎች በመከራቸው ጊዜ ወደ አንተ ጸለይ አለባቸው፡፡ ይህን ቢያደርጉ አስቸጋሪ ነገሮች እንደ ጎርፍ ወደ እነርሱ አይመጡም፡፡ 7 አንተ ከጠላቶቼ እንደምሸሸግበት ሥፍራ ነህ፣ ከመከራ ጠብቀኝ ወደ አንተም ለመጮህ እርዳኝ፣ ከጠላቶቼ ስላዳንከኝ እንዳመሰግንህም እርዳኝ፡ 8 ያሕዌ እንዲህ አለኝ፣ ‹‹ሕይወትህን እንዴት መምራት እንዳለብህ አስተምርሃለሁ፤ እመራሃለሁ፤ እከታተልሃለሁም፡ 9 ምንም እንደማይገባቸው፣ ወደምትፈልገውም አቅጣጫ እንዲሄዱልህ በልጓም እንደምታዛቸው እንደ ፈረሶችና በቅሎዎች አትሁን፡፡ 10 ኃጢአተኞች የሚያደርጓቸው ብዙ መከራ አለባቸው፣ ነገር ግን በያሕዌ የሚታመኑ የእርሱን የታመነ ፍቅር ሁልጊዜ ይለማመዳሉ፡፡ 11 ስለዚህ እናንተ ቅዱሳን ሁሉ፣ ያሕዌ ባደረገላችሁ ነገር ሐሴት አድርጉ፣ ልባችሁ ንጹሕ የሆነ፣ ደስ ይበላችሁ በደስታም እልል በሉ!
Chapter 33
1 እናንተ ጻድቃን ለያሕዌ በደስታ እልል በሉ፣ ለእርሱ የገባዋልና፡፡ 2 ያሕዌን በበገና አመስግኑት፣ አሥር አውታር ባለው በገና ዘምሩለት፡፡ 3 ለእርሱ አዲስ ዝማሬ ዘምሩ፣ የሙዚቃ መሣሪያዎቹንም እንደሚገባ ተጫወቱ፣ በደስታም እልል እያላችሁ ዘምሩ፡፡ 4 ያሕዌ አደርገዋለሁ ያለውን ሁልጊዜ ያደርጋል፣ የሚያደርገውም ሁሉ ትክክል መሆኑን እናምናለን፡፡ 5 የምናደርገውን ጽድቅና እውነተኛ ነገር እርሱ ይወዳል፡፡ ያሕዌ በምድር ላይ ያሉትን ሕዝቦች ሁሉ ይረዳል ምክንያቱም እርሱ ሁልጊዜ ይወዳቸዋልና፡፡ 6 ያሕዌ በሰማይ ላይ ያሉትን ነገሮች ሁሉ በትእዛዝ ፈጥሮአቸዋል፡፡ በትእዛዙ ከዋክብትን ሁሉ ፈጥሮአል፡፡ 7 ውኆችን ሁሉ ወደ አንድ ትልቅ ባሕር ሰብስቦአቸዋል፡፡ 8 በምድር ላይ ያሉ ሁሉ ያሕዌን ማክበር አለባቸው፣ በምድር ላይ ያሉ ሁሉ እርሱን ማክበር አለባቸው፡፡ 9 እርሱ በመናገሩ፣ ዓለምን ፈጥሮአል፡፡ አሁን ያለው ነገር ሁሉ ሕልውናውን ያገኘው በእርሱ ትእዛዝ ነው፡፡ 10 ያሕዌ ሌሎችን ሕዝቦች የፈለጉትን እንዳያደርጉ ከልክሎአቸዋል፡፡ ያቀዱትን ክፉ ነገር እንዳደርጉም ከልክሎአቸዋል፡፡ 11 እርሱ እንዲደረግ የወሰነው ግን ለዘላለም ይጸናል፡፡ ሊያደርግ ያቀደው ፈጽሞ አይለወጥም፡፡ 12 ያሕዌ ሕዝባችንን ባርኮአል፣ እርሱን የምናመልከው እኛ፣ ለዘላለም የእርሱ የሆንን፣ እንዴት የታደልን ነን! 13 ያሕዌ ከሰማይ ወደ ታች ሰዎችን ሁሉ ተመለከተ፡፡ 14 ከሚገዛበት ከሥፍራው፣ በምድር የሚኖሩትን ሰዎች ሁሉ ወደ ታች ተመለከተ፡፡ 15 የውስጥ አካላችንን እርሱ ሠርቶአል፣ የምንሠራውንም ሁሉ ይመለከታል፡፡ 16 ንጉሥ በሠራዊቱ ብዛት ጦርነት አያሸንፍም፣ ወታደሮቹ ጠንካሮች ስለሆኑ ጠላቶቹን ያሸንፋል ማለት አይደለም፡፡ 17 ፈረሶች ጠንካሮች ስለሆኑ፣ ጦርነት ያሸንፋሉ የሚጋልቡአቸውንም ያድናሉ ብሎ ማሰብ ሞኝነት ነው፡፡ 18 ያሕዌ የሚያከብሩትን የሚመለከት መሆኑን አትርሱ፣ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁትን በታማኝነት ይወድዳቸዋል፡፡ 19 ከሞት ያድናቸዋል፣ በረሐብም ጊዜ ይጠብቃቸዋል፡፡ 20 ያሕዌ እንደሚረዳን እንታመናለን፣ ጋሻ ወታደርን እንደሚከላከል ይጠብቀናል፡፡ 21 ስላደረገልን ነገር እጅግ ደስ ይለናል፣ እርሱ ቅዱስ ነውና በእርሱ እንታመናለን፡፡ 22 ያሕዌ፣ አንተ ሁልጊዜ በታማኝነት ትወደናለህ፤ ለእኛ ታላቅ ነገርን እንድታደርግልን በመተማመን እየጠበቅን እንጸልያለን፡፡
Chapter 34
ንጉሥ አቢሜሌክ በሰላም እንዲያሰናብተው ዳዊት በንጉሡ ፊት ራሱን እንደ እብድ ባስመሰለ ጊዜ የተጻፈ የዳዊት መዝሙር፡፡ 1 እኔ ሁልጊዜ ያሕዌን አመሰግናለሁ፣ ያለማቋረጥ አመሰግነዋለሁ፡፡ 2 ያሕዌን ስለ ሠራው ነገር ሁሉ አመሰግናለሁ፡፡ የሚቃወሙ ሁሉ ይስሙኝ ደስም ይበላቸው፡፡ 3 ያሕዌ ታላቅ መሆኑን ከእኔ ጋር ሆናችሁ ለሌሎች ተናገሩ! እናንተና እኔ በአንድነት ክብሩን እናውጃለን! 4 ወደ ያሕዌ አጸልያለሁ፣ እርሱም ይመልስልኛል፣ ከሚያስፈራሩኝ ነገሮች ሁሉ እርሱ ታድጎኛል፡፡ 5 እርሱ እንደሚረዳቸው የሚታመኑ ደስ ይላቸዋል፣ ፈጽሞ አያፍሩምና፡፡ 6 ተጨንቄ ነበር፣ ነገር ግን ያሕዌን ተጣራሁ፣ እርሱም ሰማኝ፡፡ ከመከራዬም ሁሉ አዳነኝ፡፡ 7 ለእርሱ ታላቅ አክብሮት ላላቸው፣ የያሕዌ መልአክ በዙሪያችሁ ሆኖ ይጋርዳቸዋል፣ ያጻቸዋልም፡፡ 8 ያሕዌ መልካም መሆኑን እዩ፣ ቅመሱትም! እንዲጠብቃችው በእርሱ የሚታመኑ የተመሰገኑ ናቸው፡፡ 9 የእርሱ ወገኖች የሆናችሁ ሁሉ፣ ለእርሱ የሚገባውነ ክብር ስጡት! ይህን የሚያደርጉ የሚፈልጉትን ያገኛሉ፡፡ 10 አንበሶች ጠንካሮች ናቸው፣ ነገር ግን አንዳንድ ጊዜ በረሀብ ደካሞች ይሆናሉ፡፡ በያሕዌ የሚታመኑ ግን የሚያስፈልጋቸውን ያገኛሉ፡፡ 11 የእኔ ተማሪዎች፣ ኑ ስሙኝ፣ ለያሕዌ የሚገባውን አክብሮት ስለ መስጠት አስተምራችኋለሁ፡፡ 12 ሕይወትን በደስታ ለመኖር ረጅምንም እድሜ ለማግኘት ከፈለጋችሁ፣ 13 ክፉ ነገር አትናገሩ! ሐሰትንም አትናገሩ! 14 ክፉ ማድረግን ተቃወሙ፣ ይልቁን መልካምን አድርጉ! ሰዎች እርስ በርሳቸው በሰላም እንዲኖሩ የተቻላችሁን አድርጉ፡፡ 15 ያሕዌ ጽድቅን የሚያደርጉትን በጥንቃቄ ይጠብቃቸዋል፣ ለእርዳታ ወደ እርሱ ሲጣሩ ሁልጊዜ ይመልስላቸዋል፡፡ 16 ነገር ግን ያሕዌ ክፉ የሚያደርጉትን ይበቀላቸዋል፣ ከሞቱም በኋላ በምድር የሚኖሩት ሰዎች ፈጽሞ ይረሱአቸዋል፡፡ 17 ያሕዌ ጻድቃን ወደ እርሱ ሲጣሩ ይሰማቸዋል፣ ከመከራቸው ሁሉ ያድናቸዋል፡፡ 18 ያሕዌ ተስፋ የቆረጡትን ለመርዳት ሁልጊዜ ዝግጁ ነው፣ ለማንኛውም መልካም ነገር ተስፋ የሌላቸውን ይታደጋቸዋል፡፡ 19 ጻድቃን መከራቸው ብዙ ነው፣ ነገር ግን ያሕዌ ከመከራቸው ሁሉ ያድናቸዋል፡፡ 20 ያሕዌ ከጉዳት ይጠብቃቸዋል፣ ጠላቶቻቸው ሲያጠቁአቸው፣ የጻድቃንን አጥንቶች ሊሰብሩ አይችሉም፡፡ 21 ጥፋት ኃጢአተኞችን ይገድላቸዋል፣ ጻድቃንን የሚቃወሙትን ያሕዌ ይቀጣቸዋል፡፡ 22 ያሕዌ እርሱን የሚያገለግሉትን ያድናቸዋል፡፡ በእርሱ የሚታኑትን አይኮንናቸውም፡፡
Chapter 35
በዳዊት የተጻፈ መዝሙር 1 ያሕዌ፣ የሚዋኝን ተዋጋቸው! ጠላቶቼ ሲዋጉኝ ከእኔ ጋር ሆነህ ተዋጋቸው! 2 እንደ ጋሻ ሆነህ ተከላከልልኝ መጥተህም እርዳኝ፡፡ 3 ጦርህን አንስተህ የሚከታተሉኝን ወጋቸው! ጠላቶቼን እንዳሸንፋቸው ቃል ግባልኝ፡፡ 4 ሊገድሉኝ ጥረት የሚያደርጉ፣ በሌሎች ይናቁ ይጎስቁሉም፡፡ ወደ ኋላ መልሳቸው በእኔ ላይ ክፉ ሊያደርጉ የሚያቅዱትን ግራ አጋባቸው፡፡ 5 መልአክህን ልከህ አሳድዳቸው ገለባ በንፋስ እንደሚበተን በትናቸው፡፡ 6 መንገዳቸውን ጨለማ አድርግ መልአክህ ሲያሳድዳቸው መንገዳቸው የሚያዳልጥ ይሁን! 7 እኔ በእነርሱ ላይ ክፉ አላደረግሁም፣ እነርሱ ግን የምወድቅበትን ጥልቅ ጉድጓድ ቆፈሩ፡፡ ሊይዙኝም መረብን በድብቅ አስቀመጡ፡፡ 8 በድንገት ጥፋት ይድረስባቸው! መረባቸው ራሳቸውን ያጥምዳቸው፡፡ ለእኔ በቆፈሩት ጉደጓድ እንዲወድቁ አድርጋቸው፣ በዚያም ይሙቱ! 9 ያሕዌ፣ አንተ ለእኔ ባደረግኸው እጅግ ደስ ይለኛል! ስለታደግኸኝ ደስ ይለኛል፡፡ 10 ከልቤ እንዲህ እላለሁ፣ ‹‹እንደ ያሕዌ ያለ ማንም የለም፣ ረዳት አልባ የሆኑትን ከኃይለኞች እጅ የሚያስጥል እንደ እርሱ ያለ የለም፡፡ ደካሞችንና ድሆችን ሊዘርፉአቸው ከሚፈልጉ የሚታደጋቸው እንደ እርሱ ያለ ማንም የለም፡፡ 11 ሐሰተኞች ሰዎች በፍርድ ቤት እኔ ስለማላውቀው ነገር ከሰሱኝ፡፡ 12 ባደረግሁት መልካም ነገር ፈንታ ክፉ ነገር አደረጉብኝ፣ በዚህ ብቸኝነት ተሰማኝ፡፡ 13 በታመሙ ጊዜ ማዘኔን አሳይቼአቸዋለሁ፡፡ ምንም ምግብ አልበላሁም፣ ራሴም ዝቅ አድርጌ ለእነርሱ ጸለይኩ፡፡ 14 ለወዳጆቼ እንደማደርገው ለእነርሱ አደረግሁ፣ ለእናቱም እንደሚያለቅስ ራሴን ዝቅ አድርጌ አለቀስሁ፡፡ 15 ነገር ግን እኔ መከራ ሲደርስብኝ፣ እነርሱ ሁሉም ደስ አላቸው፡፡ በእኔ ላይ ሊቀልዱ ተሰበሰቡ፡፡ እንግዳ ሰዎች በእኔ ላይ አላገጡ፣ አላቆሙምም፡፡ 16 ለማንም አክብሮት የሌላቸው ሰዎች ቀለዱብኝ፣ አላገጡብኝም፡፡ 17 ጌታ ሆይ፣ እንዲህ ሲያደርጉ እስከመቼ ትታገሳቸዋለህ? ከእነርሱ ጥቃት ታደረገኝ፣ አንበሳ ሌችን እንስሳት እንደሚያጠቃ በሚያጠቁኝ በእነዚህ ሰዎች እንዳለገደል ጠብቀኝ፡፡ 18 ስለዚህ፣ የአንተ ሰዎች በሚሰበሰቡበት ጊዜ፣ በሁላቸው ፊት አመሰግንሃሁ፣ አከብርሃለሁም፡፡ 19 በእኔ ላይ ሐሰት የሚናገሩትን፣ ጠላቶቼን እንዲያሸንፉኝና ደስ እንዲላቸው አትፍቀድ! የሚጠሉኝንና እንዲጠሉኝ የሚያደርጋቸው ምክንያት ሳይኖር፣ በመከራዬ ለሚደሰቱት አትፍቀድላቸው! 20 ለሰዎች በሰላም አይናገሩም፣ ይልቁኑ በምድረችን በማንም ላይ ጉዳት ባላደረሱ ሰዎች ላይ ሐሰትን ለመናገር መንገድን ይፈልጋሉ፡፡ 21 ሊከስሱኝ በእኔ ላይ ጮኹ፣ ‹‹ያደረግኸውን ስህተት አይተናል›› ሲሉ በሐሰት ተናገሩ! 22 ዝም አትበል! 23 አምላኬ፣ ተነሥ፣ በፍርድ ቤት ተፋረድልኝ፣ ተሟግተህ አሸንፍልኝ! 24 ያሕዌ፣ አምላኬ፣ አንተ ጻድቅ ስለሆንክ፣ እኔ ንጹሕ መሆኔን ፍረድልኝ፣ ጠላቶቼ በደለኛ በመሆኔ እንደተፈረደብኝ አድርገው አይደሰቱ፡፡ 25 ለራሳቸው ‹‹እንደተመኘነው አስወገድነው›› እንዲሉ አትፍቀድላቸው፡፡ 26 በመከራዬ የሚደሰቱትን ሙሉ ለሙሉ ግራ አጋባቸው ይፈሩም፣ ከእኔ እንደሚበልጡ አድርገው የሚኩራሩትን አዋርዳቸው አሳፍራቸውም፡፡ 27 አንተ እኔ ንጹሕ መሆኔን እንድትፈርድልኝ የሚመኙትን ደስ አሰኛቸው ሐሴትንም ያድርጉ፣ ‹‹ያሕዌ ታላቅ ነው! የአገልጋዮቼን ሰላም ይወዳል›› ይበሉ፡፡ 28 እኔም በጽድቅ መፍረድህን አውጃለሁ፣ ሁልጊዜም አመሰግንሃለሁ፡፡
Chapter 36
እግዚአብሔርን በታማኝነት ያገለገለው ዳዊት፣ ለመዘምራን አለቃ የጻፈው መዝሙር፡፡ 1 የማያቋርጥ የኃጢአት ፍላጎት በኃጢአተኞች ልብ ውስጥ አለ፡፡ ለእግዚአብሔር የሚገባውን ክብር አይሰጡም፡፡ 2 ስለ ራሳቸው መልካምነት ስለሚያስቡ፣ እግዚአብሔር እንደሚያውቅና ኃጢአታቸውንም እንደሚጠላ አያውቁም፡፡ 3 የሚናገሩት ሁሉ አሳሳቻና በሐሰት የተሞላ ነው፣ መልካም የሆነውን ነገር አያደርጉም ጥበበኞችም አይደሉም፡፡ 4 በመኝታቸው ላይ ሆነው፣ ሌሎችን ለመጉዳት ያቅዳሉ፣ መልካም ያልሆነውን ነገር ለማድረግ የቆረጡ ናቸው፣ ክፉ ከማድረግም አይመለሱም፡፡ 5 ያሕዌ፣ የአንተ ፍቅር እስከ ሰማይ ከፍ ያለ ነው፣ የገባኸውን ቃል ኪዳን በታማኝነት ማድረግህ እስከ ደመናት ይደርሳል፡፡ 6 ጽድቅህም ከፍ እንዳሉ ተራሮች የጸና ነው፣ በጽድቅ መፍረድህም እንደ ውቅያኖስ ጥልቀት ይቀጥላል፡፡ ሰዎችንና እንስሳንም ትጠብቃለህ፡፡ 7 እግዚአብሔር ሆይ፣ ለእኛ ያለህ ፍቅር እጅግ ውድ ነው፡፡ ወፎች ልጆቻቸውን ከክንፎቸው በታች እንደሚጠብቁአቸው እኛን ጠብቀኸናል፡፡ 8 ከተትረፈረፈው ማእድህም መግበኸናል፣ ታላቅ ስጦታዎችህ እንደ ወንዝ ፈስሰውልናል፡፡ 9 ሁሉ ነገር እንዲኖር ምክንያቱ አንተ ነህ፣ ስለ አንተ እውነቱን እንድናውቅ ብርሃንም አስችሎናል፡፡ 10 ለአንተ ታማኝ የሆኑትን መውደድህን ቀጥል፣ በጽድቅ የሚሄዱትንም ጠበቃቸው፡፡ 11 ኩሩ ሰው እንዲያጠቃኝ አትፍቀድ፣ ኃጢአተኞችም እንዲያሳድዱኝ አትፍቀድላቸው፡፡ 12 ክፉ ሰዎች እንደ ወደቁ ተመልከት፣ ተሸንፈዋል፣ ተጥለዋል፣ ተመልሰው ሊነሱ አይችሉም፡፡
Chapter 37
በዳዊት የተጻፈ መዝሙር 1 ኃጢአተኞች በሚያደርጉት ነገር አትቅና፡፡ በመጥፎ ሥራቸው የሚያገኙትን አትመኝ፡፡ 2 በሙቀት እንደሚጠወልግና እንደሚደርቅ ሣር ናቸውና፡፡ በበጋ ትኩሳት እንደሚጠፋ እጽዋት፣ ክፉ ሰዎችም እንዲሁ ይጠፋሉ፡፡ 3 በእግዚአብሔር ታመን፣ መልካምንም አድርግ፣ ይህን ብታደርግ፣ እንድትኖርበት በሰጠህ ምድር በሰላም ትኖራለህ፡፡ 4 ያሕዌ ለአንተ ባደረገልህ ሁሉ ደስ ይበልህ፣ ይህን ብታደርግ፣ የምትመኘውን ዋና ነገር ያደርግሃል፡፡ 5 ልታደርግ ያቀድከውን ሁሉ ለእግዚአብሔር አደራ ስጥ፣ የሚያስፈልግህን ሁሉ እርሱ ይሰጥሃል፡፡ 6 ንጹሕ መሆንህን እንደ ፀሐይ ብርሃን ያሳያል፣ የወሰንካቸው ነገሮች ሁሉ ጽድቅ እንደ ሆኑ እንድ እኩለ ቀን ብርሃን ያሳያል፡፡ 7 በያሕዌ ፊት ታምነህ እንዲያደርግልህ የምትፈልገውን በጸጥታ ጠብቅ፡፡ ኃጢአተኞች የሚያደርጉት ቢሳካላቸው፣ ያቀዱትንም ክፉ ነገር ማድረግ በመቻላቸው አትቅና፡፡ 8 ክፉ ሰዎች በሚያደርጉት ነገር አትናደድ፡፡ በራስህ ልትቀቃቸው አትፈልግ፡፡ አትመቅኝ፣ ይህን ብታደርግ ራስህን ትጎዳለህና፡፡ 9 አንድ ቀን ያሕዌ ክፉዎችን ያስወግዳቸዋል፣ በእርሱ የሚታኑት ግን በሰጣቸው ምድር በሰላም ይኖራሉ፡፡ 10 ኃጢአተኞች ፈጥነው ይጠፋሉ፡፡ ብትፈልጋቸው ቦታቸውን እንኳ አታገኝም፡፡ 11 ትሑታን ግን በምድራቸው በሰላም ይኖራሉ፡፡ ያሕዌ በሰጣቸው ነገሮች ሁሉ ደስ እያላቸው በሰላም ይኖራሉ፡፡ 12 ክፉ ሰዎች ጻድቃንን ለመጉዳት ያቅዳሉ፣ እንደ ዱር አራዊት ያደቡባቸዋል፡፡ 13 ነገር ግን ያሕዌ ይስቅባቸዋል ምክንያቱም አንድ ቀን በኃጢአተኞች ላይ ይፈርዳልና ይቀጣቸዋልም፡፡ 14 ኃጢአተኞች ሰይፋቸውን መዘዙ፣ ቀስታቸውንም ገተሩ፣ ድሆችን ለመግደልና በጽድቅ የሚኖሩትን ለማረድ ተዘጋጁ፡፡ 15 ነገር ግን በራሳቸው ሰይፍ ይገደላሉ፣ ቀስታቸውም ይሰበራል፡፡ 16 ምንም እንኳ ብዙ ንብረት ባይኖርህ ጻድቅ መሆንህ መልካም ነው፣ ነገር ግን ብዙ ንብረት ኖሮህ ኃጢአተኛ ብትሆን ያ መጥፎ ነገር ነው፡፡ 17 ያሕዌ የኃጢአትኞችን ኃይል ያጠፋል፣ በጽድቅ የሚኖሩትን ግን ያጸናቸዋል፡፡ 18 ምንም ዓይነት ክፉ ነገር ያላደረጉትን ያሕዌ ቀን በቀን ይጠብቃቸዋል፣ ያሕዌ የሚሰጣቸው ነገሮቸ ሁለ ለረጅም ጊዜ ይቆያል፡፡ 19 ጥፋት ሲከሰት ይተርፋ፣ በረሃብም ጊዜ፣ የሚመገቡት በቂ ምግብ ይኖራቸዋል፡፡ 20 ነገር ግን ኃጢአተኞች በበረሃ እንዳ የሚያምሩ አበቦች በፀሐይ ቃጠሎ እንደሚደርቁ፣ እንደ ጭስም እንደሚጠፉ፣ ይሞታሉ፡፡ 21 ኃጢአተኞች ይበደራሉ፣ ነገር ግን ብድራቸውን አይመልሱም፣ ጻድቃን በልግስና ለሌሎች የሚሰጡት በቂ ገንዘብ አላቸው፡፡ 22 ያሕዌ የባረካቸው በሰጣቸው ምድር በሰላም ይኖራሉ፣ የረገማቸውን ሰዎች ግን ያስወግዳቸዋል፡፡ 23 ያሕዌ የሚደሰትበትን የሚያደርጉ በእርሱ ይጠበቃሉ፣ ወደሚሄዱበት ሁሉ በመተማመን መሠማራት ይችላሉ፡፡ 24 ቢንገዳገዱ እንኳ አይወድቁም ያሕዌ በእጁ ይይዛቸዋል፡፡ 25 ወጣት ነበርኩ አሁን ግን አርጅቻለሁ ነገር ግን ጻድቃን ሲቸገሩ ልጆቻቸውም ምግብ ሲለምኑ አይቼ አላውቅም፡፡ 26 ጻድቃን ቸሮች ናቸው በደስታም ለሌሎች ያበድራሉ፣ ልጆቻቸውም ለእነርሱ በረከት ናቸው፡፡ 27 ክፉ ከማድረግ ራቅ፣ መልካምን አድርግ፡፡ ይህን ብታደርግ አንተና ዘርህ በምድርህ ላይ ዘላለም ትኖራላችሁ፡፡ 28 ይህ የሚሆነው ያሕዌ ሰዎች ጽድቅ የሆነውን ነገር እንዲያደርጉ ስለሚወድ ነወ፣ እርሱ ፈጽሞ ጻድቃንን አይጥላቸውም፣ ለዘላለም ይጠብቃቸዋል፣ የኃጢአተኞችን ልጆች ግን ያጠፋቸዋል፡፡ 29 ጻድቃን ያሕዌ ሲሰጣቸው ቃል የገባቸውን ምድር ይወርሳሉ፣ በዚያም ለዘላም ይኖራሉ፡፡ 30 ጻድቃን ጥበብ ያለበትን ምክር ለሌሎች ይሰጣሉ፣ ሰዎች በጽድቅ እንዲኖሩ ያበረታታሉ፡፡ 31 ልባቸው በእግዚአብሔር ሕግ የተሞላ ነው፣ ከእግዚአብሔር መንገድ አይወጡም፡፡ 32 ክፉ ሰዎች በቁጥቋጦ ውስጥ ተደብቀው ጻድቃን በዚያ ሲያልፉ ሊገድሏቸው ያደባሉ፡፡ 33 ነገር ግን ያሕዌ ጻድቃን በጠላቶቻቸው እጅ እንዲወድቁ አሳልፎ አይሰጣቸውም፡፡ ማንም ጻድቃንን በፍርድ ይኮንናቸው ዘንድ አይፈቅድም፡፡ 34 ያሕዌ ይረዳሃልና ታገስ ታምነህም በመንገዱ ተሠማራ፡፡ ይህን ብታደርግ፣ እርሱ ቃል የገባውን ምድር በመስጠት ያከብርሃል፣ ኃጢአተኞችንም ሲያጠፉ ታያለህ፡፡ 35 ኃጥእ ከፍ ከፍ ብሎ እንደ ሊባኖስም ዛር ለምልሞ አየሁት፡፡ 36 ስመለስ ግን አጣሁት፣ ቦታውን አላገኘሁትም፡፡ 37 ቅንነትን ጠብቅ፣ ክፉ የማያደርጉትን ተመልከት፣ ዘሮቻቸው የውስጥ ሰላም አላቸው፡፡ 38 ነገር ግን ያሕዌ ኃጢአተኞችን ያጠፋል፣ ዘሮቻቸውንም ያጠፋል፡፡ 39 ያሕዌ ጻድቃንን ይታደጋቸዋል፣ በመከራ ጊዜ ይጠብቃቸዋል፡፡ 40 ያሕዌ ይረዳቸዋል ያድናቸዋልም፣ ከክፉ ሰዎች ጥቃትም ይታደጋቸዋል፣ እንዲጠብቃቸው ወደ እርሱ መጥተዋልና፡፡
Chapter 38
እግዚአብሔር እንዳይረሳው የጠየቀበት፣ ዳዊት የጻፈው መዝሙር 1 ያሕዌ፣ በእኔ ስትናደድ፣ አትቆጣኝ አትቅጣኝም! 2 አሁን ግን ቀስትህን በእኔ ላይ እንዳደረግህ ነው፣ አቁስለኸኛልም፣ መትተህ ጥለኸኛል አድቅቀኸኝማል፡፡ 3 በእኔ ስለተናደድክ፣ ታላቅ ሕመም ያሰቃየኛል፡፡ ከኃጢአቴ የተነሣ መላ አካሌ በሽተኛ ሆኖአል፡፡ 4 ኃጢአቴ እንደ ጐርፍ በራሴ ላይ ወጥቶአል፣ እንደ ሸክምም በላዬ ላይ ነው፣ ልሸከመውም አልቻልኩም፡፡ 5 ካደረግሁት ስንፍና የተነሣ፣ ቁስሌ እየተባባሰ ሄደ፣ ሸተተም፡፡ 6 አንዳንድ ጊዜም በውርደት እመላለሳለሁ፣ አንዳንድ ጊዜም እጐሳቆላለሁ፣ ቀኑን ሙሉም እተክዛለሁ፡፡ 7 አካሌ በትኩሳት ተቃጠለ፣ እጅግም ታምሜአለሁ፡፡ 8 እኔ ሙሉ ለሙሉ ደክሜአለሁ፣ ምንም ኃይል የለኝም፡፡ ውስጤ እጅግ ደክሞአል ከሕመሜ የተነሣ አቃትታለሁ፡፡ 9 ያሕዌ፣ እንድትፈውሰኝ እንደምፈልግ ታውቃለህ፣ ስቃትት እባክህ ስማኝ፡፡ 10 ልቤ በኃይል ይመታለ፣ ኃይሌ ሁሉ አልቆአል፣ ማየት እንኳ አልችልም፡፡ 11 ከቁስሌ የተነሣ ጓደኞቼ እና ጐረቤቶቼ ከእኔ ራቁ፣ ቤተ ሶቦቼ እንኳን ከእኔ ራቁ፡፡ 12 እኔን ሊገድሉኝ የሚፈልጉ ሊይዙኝ ወጥመድን አዘጋጁ፣ ሊጐዱኝ የሚፈልጉ እኔን እንዴት ሊያስወግዱኝ እንደሚችሉ ተወያዩ፣ ቀኑን ሙሉ በእኔ አሴሩ፡፡ 13 እኔ ግን እንደ ደንቆሮ ሆንኩ የሚሉትን አልሰማም፡፡ መናገር እንደማይችልም ሰው ሆንኩ ምንም ልመልስላቸው አልቻልኩም፡፡ 14 ሰዎች ሲያናግሩት ምንም መመለስ እንደማይችል ሰው ሆንኩ፡፡ 15 ያሕዌ፣ እኔ ግን በአንተ እታናለሁ፡፡ ጌታ አምላኬ፣ ትመልስልኛለህ፡፡ 16 ለአንተ እንዲህ ብዬአለሁ፣ ‹‹አትግደለኝ ጠላቶቼም ደስ አይበላቸው! መከራ ቢያጠቃኝ ጠላቶቼ በእኔ ላይ እጅግ ክፉ ነገር ያደርጋሉ!›› 17 ይህን ያልኩት ልወድቅ ትንሽ ስለ ቀረኝ ነው፣ ያለማቋረጥ ሕመም ስላለኝ ነው፡፡ 18 ያደረግሁትን ስህተቴን ሁሉ እናዘዛለሁ፣ ስላደረግሁት ኃጢአት እጅግ አዝናለሁ፡፡ 19 ጠላቶቼ ጤነኛና ጠንካሮቸ ናቸው፣ ያለምክንያት የሚጠሉኝ ሰዎች ብዙ ናቸው፡፡ 20 እኔ ባደረግሁላቸው መልካም ነገር ፈንታ፣ በእኔ ላይ መጥፎ ነገር ያደርጉብኛል፡፡ 21 ያሕዌ፣ አትተወኝ! አምላኬ ከእኔ አትራቅ! 22 ልታድነኝ የምትችል አንተ ብቻ ነህ፣ በፍጥነት ወደ እኔ ና እርዳኝም!
Chapter 39
ዳዊት ኤዶታም ለተባለው የመዘምራን አለቃ የጻፈው መዝሙር 1 ለራሴ እንዲህ አልኩ፣ ‹‹በምናገረው ነገር ኃጢአት እንዳላደርግ እጠነቀቃለሁ፡፡ ኃጢአተኞች ወደ እኔ ቀርበው ሳሉ በአንተ ላይ አንዳች የማጕረምረም ቃል አልናገርም፡፡ 2 ስለዚህ ሙሉ ለሙሉ ጸጥ አልኩ፣ ስለ መልካም ነገር እንኳ አልተናገርኩም፣ ያም ቢሆን አልጠቀመኝም ምክንያቱም የበለጠ ተሰቃየሁ፡፡ 3 በውስጤ የበለጠ ድንጋጤ ሆነብኝ፡፡ ስለ መከራዬ ሳሰብ፣ የበለጠ ተጨነቅሁ፡፡ ስለሆነም በመጨረሻ እንዲህ አልኩ፡- 4 ‹‹ያሕዌ፣ ምን ያሕል ዘመን እንደምኖር እባክህ አሳየኝ፡፡ መቼ እንደምሞት ንገረኝ፡፡ ከአሁን በኋላ ምን ያህል ዘመን እንደምኖር ንገረኝ! 5 ጥቂት ዘመን ብቻ እንድኖር ያደረግኸኝ ይመስላልና፣ የእኔ የሕይወትህ ዘመን ለአንተ ምንም አይደለም፡፡ እኛ ሰዎች የምንኖረው የሕይወት ዘመን በአየር ላይ እንዳለ እስትንፋስ አጭር ነው፡፡ 6 እንደ ጥላ እንሰወራለን፡፡ የምናደርገው ነገር ሁሉ ለከንቱ ይመስላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ብዙ ገንዘቦችን እናገኛለን፣ ከሞትን በኋላ ማን እንደሚጠቀምበት እንኳን አናውቅም፡፡ 7 ስለዚህ አሁን፣ ያሕዌ፣ ከማንም አንዳች ነገር እቀበላለሁ ብዬ ተስፋ አላደርግም፡፡ በረከትን የምቀበለው ከአንተ ብቻ ነውና አንተን እጠባበቃለሁ፡፡ 8 ከሠራኋቸው ኃጢአቶቼ የተነሣ ከሚደርስብኝ ቅጣት አድነኝ፡፡ ሞች ሰዎች በእኔ እንዲያሾፉ አትፍቀድ፡፡ 9 ስትቀጣኝ ምንም አልተናገርኩም ምክንያቱም እንድሰቃይ ያደረግኸኝ አንተ መሆንህን አውቄአለሁ፡፡ 10 ነገር ግን አሁን፣ እባክህ እኔ መቅጣትህን አቁም! ይህን ካላደረግህ፣ እንድሰቃይ ስላደረግኸኝ መሞቴ ነው፡፡ 11 አንድን ሰው ስለ ሠራው ኃጢአት ስትገስጸውና ስትቀጣው፣ ብል ልብስን እንደሚበላ የሚወድደውን ነገሮች ታጠፋበታለህ፡፡ ሕይወታችን በአየር ላይ እንዳለ እስትንፋስ ይጠፋል፡፡ 12 ያሕዌኸ ወደ አንተ ስጸልይ ስማኝ፣ ወደ አንተ ስጮህ ተመልከተኝ፡፡ ሳለቅስ እርዳኝ፡፡ እንደ አባቶቼ እኔ በምድር ላይ ያለሁት ለአጭር ጊዜ ነው፡፡ 13 አሁን እባክህ ተወኝ አትጣኝ፣ ከመሞቴ በፊት ለጥቂት ጊዜ እንኳ ደስተኛ እንድሆን ፈገግ እንድልም አድርገኝ፡፡
Chapter 40
ለመዘምራን አለቃ ዳዊት የጻፈው መዝሙር 1 እግዚአብሔር እንዲረዳኝ በትዕግሥት ጠበቅሁኝ፣ ወደ እርሱ ስጣራ እርሱ ሰማኝ፡፡ 2 ብዙ መከራዎች በከበቡኝ ጊዜ፣ በጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ እንደገባሁ ይሰማኝ ነበር፡፡ ነገር ግን እርሱ ከጥልቅ ረግረግ፣ ከጭቃም ውስጥ አወጣኝ፣ እግሮቼንም በአለት ላይ አቆማቸው በሰላምም እንድራመድ አደረገኝ፡፡ 3 የምዘምረው አዲስ ዝማሬ ሰጠኝ፣ አምላካችን የሆነውን እርሱን የማመሰግንበት ዝማሬ ሰጠኝ፡፡ ብዙ ሰዎች እርሱ ለእኔ ያደረገውን ያውቃሉ፣ እርሱንያከብራሉ በእርሱም ይታመናሉ፡፡ 4 እግዚአብሔር እንዲጠብቃቸው በእርሱ የሚታመኑ እንዴት የተመሰገኑ ናቸው፣ በጣዖታት የማይታመኑ ሐሰተኛ ጣዖታትን ከሚያመልኩ ጋር ሕብረት የማያደርጉ የተመሰገኑ ናቸው፡፡ 5 ኦ እግዚአብሔር፣ አምላኬ፣ አንተ እጅግ አስደናቂ ነገሮችን አድርገሃል! ለኣ ያቀድከውን አስደናቂ ነገሮች ሁሉ ማንም ዘርሮ ሊገልጽ አይችልም፡፡ እኔም እነዚያን መልካም ነገሮች ሁሉ ለሌሎች ለመግለጽ ብሞክር ዘረዝራቸው አልቻልኩም ምክንያቱም ከቁጥር የበዙ ናቸውና፡፡ 6 አንተን የሚስደስትህ መሥዋዕትና ሌሎችም ስጦታዎች አይደሉም፡፡ ነገር ግን የአንተን ትእዛዝ እንድሰማ አስቻልከኝ፡፡ በመሰዊያ ላይ የሚቀርቡ የሚቀጠሉ የእንስሳ መሥዋዕትና ሌሎች መሥዋዕቶች አንተን አያስደስቱህም፡፡ 7 ስለዚህ ለአንተ እንዲህ አልኩ፣ ‹‹እግዚአብሔር ሆይ፣ በጥቅል መጽሐፍት የተጻፈውን ሕግህን ለመታዘዝ እነሆ በፊትህ አለሁ፡፡ 8 ኦ አምላኬ፣ አንተ የምትፈልገውን ማድረግ ያስደስተኛል፣ እኔ ሁልጊዜ በውስጤ ስለ ሕጎችህ አስባለሁ፡፡ 9 ሕዝቦችህ ሁሉ ሲሰበሰቡ ስላደረግኸው ትክክለኛ ነገር እንዳዳንከን እነግራቸዋለሁ፡፡ እግዚአብሔር ሆይ እኔ ይህን ከመናር እንዳልተቆጠብኩ አንተ ታውቃለህ፡፡ 10 አንተ በጽድቅ ያደረግኸውን መናር አልተቆጠብኩም፣ የአንተ ብዙ ሕዝቦች ሊያመልኩህ በተሰበሰቡ ጊዜ፣ አንተ ለእኛ ታማኝ እንደሆንክና እንዳንከን ነግሬአቸዋለሁ፡፡ አንተ በታማኝነት እንደወደድከንና የገባህልንን ተስፋ በታማኝነት እንደፈጸምክልን ሳልደብቅ ተናግሬአለሁ፡፡ 11 እግዚአብሔር ሆይ በምሕረትህ ወደ እኔ መመልከትህን አታቁም፡፡ አንተ በታማኝነት ስለምትወደኝ ለእኔም ስለምታስብልኝ፣ ሁልጊዜ ጠብቀኝ፡፡ 12 ብዙ መከራዎች አሉብኝ፣ ልቆጥራቸው አልችልም፡፡ ከኃጢአቴ የተነሣ አሁን በብዙ ነገሮች እየተሰቃየሁ ነው፡፡ ከእንባዬ የተነሣ ዓይኖቼ በትክክል ማየት አይችሉም፡፡ ኃጢአቶቼ ከጸጉሬ ቁጥር የበለጡ ናቸው፡፡ እኔ በጣም ተስፋ ቆርጬአለሁ፡፡ 13 እግዚአብሔር ሆይ እባክህ አድነኝ፡፡ ልትረዳኝ ፈጥነህ ወደ እኔ ና! 14 ስለ መከራዬ ደስ የሚላቸው ይፈሩ፣ እንዲዋረዱ አድርጋቸው፡፡ እኔን ለማስወገድ የሚጥሩትን አጥፋቸው፡፡ 15 አንተ ስታጠቃቸው በእኔ የሚያላግጡ ሁሉ እንደሚዋረዱ ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ 16 ነገር ግን አንተ ለማምለክ የሚሄዱ ሁሉ በአንተ ደስ ይበላቸው፡፡ የሚወዱህ ሁሉ ‹‹እግዚአብሔር ታላቅ ነው!›› እያሉ ደስታቸውን ይግለጹ፡፡ 17 እኔ ችግረኛና ምስኪን ነኝ፣ ነገር ግን ጌታ እንደማይረሳኝ አውቃለሁ፡፡ ኦ አምላኬ፣ የምታድነኝና የምትረዳኝ አንተ ነህ፣ ስለዚህ በፍጥነት ወደ እኔ ናና እርዳኝ!
Chapter 41
1 ለድሆች የሚያስቡ እንዴት የታደሉ ናቸው፣ ችግር በገጠማቸው ጊዜ እግዚአብሔር ይታደጋቸዋል። 2 እግዚአብሔር ይጠብቃቸዋል፣ ረጅምን እድሜ ይሰጣቸዋል። በእስራኤል ምድር ደስተኞች እንዲሆኑ ያስችላቸዋል፣ ከጠላቶቻቸውም ይታደጋቸዋል 3 በታመሙ ጊዜ ይፈውሳቸዋል፣ ያጠነክራቸዋልም። 4 እኔ በታመምኩ ጊዜ፣ እንዲህ አልኩ፣ “እግዚአብሔር ሆይ በምሕረትህ ተመልከተኝ ፈውሰኝም፣ በአንተ ላይ ኃጢአትን ከማድረጌ የተነሣ መታሜን አውቃለሁና። 5 ጠላቶቼ በእኔ ላይ ክፉ ነገር ተናገሩ፣ እንዲህ አሉ፣ ሁሉም ሰው እንዲረሳው በቶሎ እንዴት ይሞታል?” 6 ጠላቶቼ ወደ እኔ ሲመጡ፣ ስለ እኔ እንደሚያስቡ በማስመሰል ተናገሩ። ስለ እኔ ያለውን ክፉ ወሬ ሁሉ ግን በጉጉት ይሰሙ ነገር። ከዚያም ሄደው ለሰው ሁሉ በእኔ ላይ የደረሰውን ተናገሩ። 7 የሚጠሉኝ ሁሉ በእኔ ላይ አንሾካሾኩ፣ በእኔ ላይ አንሾካሾኩ፣ በእኔ ላይ ክፉ ነገር እንዲደርስብኝ ተስፋ አደረጉ። 8 እንዲህም አሉ፣ “ስለታማመ በቶሎ ይሞታል፣ ከተኛበት አልጋ ፈጽሞ ሊነሣ አይችልም።” 9 የቅርብ ጓደኞቼ እንኳን፣ እጅግ የማምናቸውና ብዙ ጊዜ ከእኔ ጋር የሚሆኑ አሳልፈው ሰጡኝ። 10 ነገር ግን፣ እግዚአብሔር ሆይ፣ እኔን በምሕረትህ አስበኝ፣ እንደገና ጤነኛ እንድሆን አስችለኝ። ይህን ብታደርግልኝ ለጠላቶቼ እመልስላቸዋለሁ። 11 ጠላቶቼ እንዳያሸንፉኝ ብታደርገኝ፣ በእኔ ደስ እንደተሰኘህ በዚህ አውቃለሁ። 12 እኔ በቅንነቴ እውነትን ስላደረግሁ እንደረዳኸኝ አውቃለሁ፣ ከአንተም ጋር ለዘላለም እንድሆን እንዳስቻልከኝም አውቃለሁ። 13 እኛ እስራኤላውያን የምናመልክህ፣ አምላካችን እግዚአብሔር ሆይ፣ ተመስገን፤ ለዘላለም አምስግኑት! አሜን! ለዝላለም ይህ ይሆን ዘንድ ምኞቴ ነው።
Chapter 42
1 ኦ እግዚአብሔር ሆይ ዋላ ከቀዝቃዛ ውሃ ምንጭ መጠጣት እንደሚናፍቅ እኔም እፈልግሃለሁ። 2 ታላቅ የሆንክ እግዚአብሔር ሆይ ከአንተ ጋር መሆን እመኛለሁ። ለራሴ እንዲህ አልኩ፡- “በእስራኤል ወዳለው መቅደስ መቼ እመለሳለሁ? በፊትህስ ሆኜ እንደገና መቼ አመልክሃለህ?” 3 በእያንዳንዱ ቀንና በእያንዳንዱ ሌሊት አለቀስሁ፣ የምጠጣውም እንባዬን ብቻ ነው፣ ይህን ባደረግሁ ጊዜ ሁሉ ጠላቶቼ እንዲህ ይሉኛሉ፣ “አምላክህ ስለምን አይረዳህም?” 4 ከብዙ ሰዎች ጋር በኢየሩሳሌም ወዳለው መቅደስ ለጸሎት የምገባበትን ያን ጊዜ አስባለሁ ከልቤ ወደ እግዚአብሔር እጸልያለሁ። ሕዝቡ ወደ መቅደሱ ሲሄድ እኔ እመራቸው ነበር፣ በኃይል እየጮህን እግዚአብሔርን በደስታ በዝማሬ እናምሰግን ነበር፣ ያደረገልንን እየቆጠርን እጅግ ብዙ ሆነን እናከብረው ነበር። 5 ስለዚህ አሁን እንዲህ እላለሁ፣ “ለምን አዝናለሁ? ለምንስ እታወካለሁ? እግዚአብሔር እንደሚባርከኝ በመተማመን እጠባበቃለሁ፣ እንደገናም አመሰግነዋለሁ አምላኬ ያዳንከኝ አንተ ነህ።” 6 ነገር ግን አሁን ያህዌ፣ ስለ አንተ እያሰብኩ እታወካለሁ የዮርዳኖስ ወንዝ እስከ አፍ ጢሞ ሞልቶ ሲፈስስ፣ ከአርሞንኤም ተራራ ከታናሹም ተራራ ከሚዛር የሚወርደው ውሃ ወደ ዮርዳኖስ ሲገባ አንተ በእስራኤል አለህ። 7 ነገር ግን በዚህ እኔ የሚሰማኝ ሃዘን በላዬ እንደሚያልፍ አንተ እንደላክኸው ታላቅ ውሃ ይመስላል፣ ልክ እንደ ታላቅ ፏፏቴ በላዬ ላይ ያልፋል። 8 ያሕዌ በየቀኑ እኔን በማማኝነት እንደሚወደኝ ያሳየኝ ዘንድ እመኛለሁ። ይህን ሲያደርግ በየሌቱ ለእርሱ እዘምራለሁ ሕያው ወደ አደረገኝ ወደ እርሱም እጸልያለሁ። 9 ለእግዚአብሔር እንዲህ እላለሁ፣ እንደ ታላቅ አለት መጠጊያ የሆነኝ ማን ነው? “ስለምን ረሳኸኝ፣ ጠላቶቼ ያመጡብኝን መከራ አንተ ታውቃለህ” 10 በእኔ እያላገጡ እንዲህ በማለት ይጠይቁኛል “አምላክህ ስለ ምን አይረዳህም?” እንዲህ እያሉ ሲያላግጡብኝ አጥንቶቼን የሚቀለጣጥም ቁስል ሆኖብኛል። 11 ነገር ግን ለራሴ እንዲህ እላለሁ፣ “ስለ ምን አዝናለሁ? እግዚአብሔር እንደሚባርከኝ በመተማመን እጠባበቃለሁ፣ እንደገና አመሰግነዋለሁ፣ አምላኬ ያዳነኝ እርሱ ነው።”
Chapter 43
አንተን የማያከብሩ 1 እግዚአብሔር ሆይ፣ ወንጀለኛ እንዳልሆንኩ ፍረድልኝ፡፡ ሰዎች በእኔ ላይ ክፉ ነገሮችን ሲናገሩ ተከላከልልኝ! ስለ እኔ እውነተኛ ያልሆነውን ነገር ከሚናገሩ እና ከሚያታልሉኝ ሰዎች ታደገን፡፡ 2 የምትጠብቀኝ አምላኬ፣ አንተ ነህ፣ ስለ ምን ትተወኛለህ? በእኔ ላይ ክፉ ነገር ከሚያደርጉ ከጠላቶቼ የተነሣ ሁልጊዜ እንዳዝን አይገባም፣ ትክክልም አይደለም፡፡ 3 እንድኖር የሚረዱኝን እውነተኛ ቃሎች ተናገር፡፡ በኢየሩሳሌም ወዳለው ቅዱስ ተራራህ፣ ወደ ጽዮን እንድመለስ ወደ ማደሪያህ ቤተ መቅደስ እንድገባ የሚያስችለኝን ትእዛዝ ስጥ፡፡ 4 ይህን ስታደርግ፣ ወደ መሰዊያህ እሄዳለሁ አመልክሃለሁም፣ አምላኬ፣ ደስ የምታሰኘኝ አንተ ነህ፡፡ በዚያ አመሰግንሃለሁ፣ የማመልክህ አምላኬ፣ በገናዬን እጫወታለሁ፡፡ 5 ለምን አዝናለሁ ለምንስ ተስፋ እቆርጣለሁ? እኔ እግዚአብሔር እንዲባርከኝ በመተማመኔ እጠባበቀዋሁ፣ አመሰግነዋሁም፣ የምታድነኝ፣ አንተ አምላ ነህ፡፡
Chapter 44
ከቆሬ ልጆች አንዱ ለመዘምራን አለቃ የጻፈው መዝሙር 1 እግዚአብሔር ሆይ፣ አባቶቻችንና እናቶቻችን የነገሩንን ሰማን፡፡ ከብዙ ዘመናት በፊት የሠራኸውን ተአምራት ነገሩን፡፡ 2 አንተን የማይፈሩትን ሰዎች ከምድራቸው እንዴት እንዳሳደድካቸው እኛንም በምድራቸው እንዴት እንደተከልኸን ነገሩን፡፡ እነዚያን አንተን የማይፈሩትን ሰዎች እንዴት እንደ ቀጣሃቸውና የራስህን ሕዝብ ምድሩን እንዲወርሱ እንዳደረግሃቸው ነገሩን፡፡ 3 በምድሪቱ ውስጥ የነበሩትን ሰዎች ያሸነፉአቸው በሰይፋቸው ኃይል አልነበረም፣ ባለ ድል የሆኑት በራሳቸው ብርታት አልነበረም፣ ይህን ያደረጉት በአንተ ኃይል ብቻ ነው፣ እነርሱ አንተ ከእኔ ጋር እንደ ነበርክና በእነርሱ ደስ እንደ ተሰኘህ እርግጠኞች ነበሩ፡፡ 4 ጠላቶቻችንን እንድናሸንፍ ያስቻልከን፣ አንተ ንጉሤና አምላኬ ነህ፡፡ 5 ጠላቶቻችንን የመታናቸውና በላያችን ላይ የቆሙትን ያዋረድናቸው በአንተ ኃይል ነው፡፡ 6 ቀስቴና ጦሬ ያድናል ብዬ በእነርሱ አልታመንም፡፡ 7 ከጠላቶቻችን የታደግኸን አንተ ነህ፣ ሌላ ማንንም አይደለም፣ የሚጠሉንን እንዲሸነፉና እንዲያፍሩ ያደረግሃቸው አንተ ነህ፡፡ 8 እኛ ሁልጊዜ እግዚአብሔር ባደረገልን ሁሉ እንኮራን፣ ለዘላለምም እናመሰግነዋን፡፡ 9 አሁን ግን ተውከን፣ እንድንዋረድም አደረግኸን፣ ጠላቶቻችን በጦርነት ሲዘምቱብን አንተ ከእኛ ጋር አትወጣም፡፡ 10 ከጠላቶቻችን ፊት እንድንሸሽ አደረግኸን፣ ከዚህም የተነሣ የኣ የሆነውን ነገር ሁሉ ወረሱ፡፡ 11 እንደሚታረዱ በጎች በፊታቸው ተመላለስን፣ በሩቅ ወደአሉ አሕዛብ መካከል በተንከን፡፡ 12 ይኽም ለጠላቶቻችን በትንሽ ዋጋ እንደሸትከን ያህል ነው፣ እኛን በመሸጥህ ያገኘኸው ትርፍ የለም! 13 በሌሎች አገሮች የሚኖሩ ህዝቦች በእኛ አላገጡ፣ ሳቁብን ቀለዱብንም፡፡ 14 የአገራችንን ስም በመጥቀስ ቀለዱ፣ ንቀታቸውንም ለማሳየት እራሳቸውን ነቀነቁብን፡፡ 15 ቀኑን ሙሉ ተጐሳቆልኩ፣ ፊቴን በማየት፣ ሰዎች ማፈሬን አወቁ፤ 16 የሚሳደቡና የሚያላግጡ ሰዎች፣ በጠላቶቼ ፊት ሊጐዱኝ በሚወዱ ፊት እንዳፈርኩ ሲናገሩ ሰማሁ፡፡ 17 ምንም እንኳ አንተን ባንረሳም፣ እነዚህ ሁሉ ነገሮች ሆኑብን፣ ከአባቶቻችን ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳን ያልታዘዝን አልነበርንም፡፡ 18 ለአንተ ታዛዦች መሆናችንን አልተውንም፣ እንድናደርገው የምትፈልገውን ከማድረግ ወደ ኋላ አላልንም፡፡ 19 ነገር ግን በጨካኝ አውሬዎች መካከል ያለ ረዳት እንድንሆን አደረግህ፤ በጥልቅ የጨለማ ዋሻ ውስጥ ብቻችንን ተውከን፡፡ 20 አምላካችንን ማምለክ ረስተን ቢሆን ኖሮ፣ እጆቻችንን ወደማይታወቁ አማልክት ዘርግተን ቢሆን ኖሮ፣ 21 በእርግጥ አንተ ይህን ሁሉ ታውቃለህ በድብቅ የምናስበውን ሁሉ ታውቃህና፡፡ 22 ነገር ግን እኛ የአንተ ወገኖች በመሆናችን ጠላቶቻችን ተከታትለው ይገድሉናል፡፡ በእነርሱ ፊት እንደሚታረዱ በጎች ተደርገን ተቆጥረናል፡፡ 23 ስለዚህ እግዚአብሔር ሆይ፣ ተነስ! ስለምንስ ትተኛለህ? ተነስ ለዘላለም አትጣለን! 24 ስለምን ወደ እኛ አትመለከትም? እየተሰቃየን መሆኑንና ጠላቶቻችን እየጨቆኑን እንዳሉ ለምን ትረሳለህ? 25 እጅግ ተረብሸናል፣ ምንም ልናደርግ አልቻልንም፣ እንደ ሞቱ ሰዎች ሆነናል፡፡ 26 አንድ ነገር አድርግ! ናና እርዳን! ቃል እንደገባኸው ትወደናለህና ታደገን፡፡
Chapter 45
ከቆሬ ልጆች አንዱ ለመዘምራን አለቃ ስለ ፍቅር ሊሊ በሚባል ቅላጼ የተዘመረ መዝሙር 1 እኔ በውስጤ ስለ አንድ መልካም ነገር ለመጻፍ ተነሣሣሁ፣ ለንጉሡ ዝማሬን ለመዘመር፡፡ የዚህ መዝሙር ቃሎች የተጻፉት የሰለጠነ ጸሐፊ በሆንኩት በእኔ ነው፡፡ ኦ ንጉሥ ሆይ፣ አንተ በዓለም ላይ እጅግ ውብ ሰው ነህ፣ ግግርህም እጅግ ያማረ ነው፣ እግዚአብሔር ሁልጊዜ እንደባረከህ እናውቃለን፡፡ 3 አንተ ኃያል ተዋጊ ሆይ፣ ተነሥ ሰይፍህንም ታጠቅ! አንተ እጅግ የከበርክና የምታስደንቅ ነህ፡፡ 4 እንደ ታቅ ንጉሥ በክብር ተቀምጠህ ስለ እውነት ተሟገታለህ፣ ትናገራለህም፤ በቅንነት ትፈርዳለህ! በብዙ ጦርነቶች ስለ ተዋጋህ፣ ጠላቶችህ የሚፈሩትነ ሥራ ታደርጋለህ፡፡ 5 ቀስቶችህ የተሳሉ ናቸው፣ የጠላቶችህን ልቦች ይወጋሉ፡፡ የብዙ መንግሥታት ወታደሮች በፊትህ ይወድቃሉ፡፡ 6 እግዚአብሔር የሰጠህ መንግሥት ለዘላለም ይጸናል፡፡ 7 የጽድቅ ጅራን ትወድዳለህ፣ ክፋትንመ ትጠላለህ፤ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ፣ ንጉሥ እድትሆን መረጠህ፣ ከማንኛውም ንጉሥ የበለጠ ደስተኛ እንድትሆን አደረገህ፡፡ 8 በልብሶችህ ሁሉ ላየ ልዩ ልዩ ሽቱዎች አሉባቸው፡፡ በዝሆን ጥርሶች በተሠራው ቤተ መንግሥትህ ሙዚቀኞች በሚያምሩ የሙዚቃ መሣሪያዎች ይጫወቱልሃል፡፡ 9 ከሚስቶችህ መካከል የነገሥታት ልጆች አሉ፡፡ በቀኝህ ንግሥቲቱ ከኦፊር ወርቅ የተሠራውን ልብሷን ለብሳ ተቀምጣለች፡፡ 10 አሁን ለሙሽራህ እናገራሁ፡፡ ‹‹በጥንቃቄ አድምጪኝ! በአገርሽ የነበሩትን ሰዎች እርሺአቸው፣ ዘመዶችሽንም እርሺ! 11 አንቺ ውብ ነሽና፣ ንጉሡም ከአንቺ ጋር መሆን ወድዶአልና፡፡ እርሱ ጌታሽ ነው፣ ስለዚህ ልትታዘዢው ይገባሻል፡፡ 12 የጢሮስ ሰዎች ስጦታን ያጡልሃል፣ ባለጠጐቻቸው ለእነርሱ ልካም ነገር ለማድረግ አንተን ይከተላሉ፡፡ 13 አንቺ፣ የንጉጅ ሙሽራ የወርቅ መጐናጸፊያ ልብስሽን ለብሰሽ ወደ ቤተ መንግሥት ግቢ፡፡ 14 ኦ ንጉሥ ሆይ! ባ ብዙ ቀለም መጐናጸፊያዋን ለበሳ፣ ሴቶች አገልጋዮቿ እየመሩአት ወደ አንተ ሲያመጧት ተመልከት፡፡ እርሷን የሚጅቡአት ሌሎች ብዙ ወጣት ሴቶች አሉ፡፡ 15 ወደ ቤተ መንግሥትህ ሲገቡ እጅግ ደስተኞች ናቸው፡፡ 16 አንድ ቀን፣ ወንድ ልጆችህ እና የልጅ ልጆችህ፣ አባቶችህ እንደ ሀኑት ነገሥታት ይሆናሉ፡፡ በሌሎች አገሮችም ገዢዎች እንዲሆኑ ታስችላቸዋለህ፡፡ 17 ለእኔ ግን፣ አንተ ያደረግኸውን ታላላቅ ነገሮች ሰዎች ያስታውሱ ዘንድ አደርጋቸዋለሁ፣ ለዘላለምም ያሰግኑሃል፡፡
Chapter 46
1 የሚጠብቀንና ጠንካሮች እንድንሆን የሚያደርገን እግዚአብሔር ነው፣ መከራ ሲያገኘን ሊረዳን ሁልጊዜ ዝግጁ ነው። 2 ምድር እንኳ ብትናወጥ አንፈራም። ተራሮች እንኳ ወደ ባሕር መካከል ቢወሰዱ፣ 3 በባሕር ያሉ ውሃዎች ቢናወጡና ቢጮሁ፣ ተራሮችም ቢንቀጠቀጡ እኛ ግን አንፈራም። 4 ከእግዚአብሔር የሚመጣ በረከት በከተማ ውስጥ ያሉትን ሰዎች እንደሚያስደስት ወንዝ ነው፣ አዚያ እግዚአብሔርን እናመልካለን። ከተማዋ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ የሚገኝባት ናት፣ እርሱ ከማንኛውም ሌላ አምላክ የበለጠ ታላቅ ነው። 5 እግዚአብሔር በከተማዋ ውስጥ አለ፣ ፈጽሞ አትጠፋም፣ እርሱ በየቀኑ ወደ ከተማዋ እየወረደ በውስጥዋ የሚኖሩትን ሕዝቦች ይረዳቸዋል። 6 እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ እንደ መብረቅ በከፍተኛ ድምፅ ሲናገር፣ አሕዛብ ይንቀጠቀጣሉ፣ ይፈራሉም፣ መንግሥታትም ይወድቃሉ። 7 የመላእክት ሠራዊ አዛዥ የሆነው ያሕዌ፣ ከእኛ ጋር ነው፣ ያዕቆብ ያመለከው እግዚአብሔር መጠጊያችን ነው። 8 ያሕዌ ያደረገውን ኑና እዩ! በምድር ሁሉ ያደገውን ተአምራት ኑና እዩ። 9 እርሱ በዓለም ሁሉ ላይ ጦርነት ይሽራል፣ ቀስትን ይሰብራል፣ ጥርንም ይቆርጣል ጋሻን በእሳት ያቃጥላል። 10 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ "ጸጥ በሉ እኔም አምላክ መሆኔን አስታውሱ! በምድር ያሉ አሕዛብ ሁሉ ያከብሩኛል፣ በምድር የሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ያከብሩኛል" 11 ያሕዌ የመላእክት ሠራዊት አዛዥ መሆኑን ፈጽማችሁ አትርሱ፣ እርሱ ከእኛ ጋር ነው፣ ያዕቆብ ያመለከው እግዚአብሔር መጠጊያችን ነው።
Chapter 47
1 በዓለም ያላችሁ ሰዎ ችሁሉ እጆቻችሁን አጨብጭቡ! እግዚአብሔርን ለማመስገን ድምፃችሁን በደስታ ከፍ አድርጉ! 2 ከሌሎች አማልክት እጅግ የላቀው ያሕዌ፣ እጅግ ድንቅ ነው፣ በዓለም ሁሉ ላይ የሚገዛ ንጉሥ ነው። 3 በከነዓን ይኖሩ የነበሩትን ጠላቶቻችን የሆኑትን ሕዝቦች እንድናሸንፍ እርዳን። 4 እኛ የእስራኤል ሕዝቦች እንኖርበት ዘንድ፣ ይህን ምድር መረጠልን፣ እርሱ ወድዶናልና ይህን ምድር ስለ ወረስን እንኮራለን። 5 እግዚአብሔር ወደ መቅደሱ ገባ፣ ሕዝቡም እርሱ ወደ ላይ ሲያርግ በደስታ እልል አሉ መለከትንም ነፉ። 6 አምላካችንን ለማመስገን ዘምሩ! አመስግኑ ዘምሩ፣ ለንጉሣችን ለእግዚአብሔር ዘምሩ! 7 በዓለም ባለው ነገር ሁሉ ላይ እርሱ ገዢ ነውና ለእርሱ ዘምሩ! 8 እግዚአብሔር በሕዝቦች ሁሉ ላይ ይገዛል፤ በተቀደሰውም መቅደሱ ይቀመጣል። 9 የምድር አሕዛብ መሪዎች ሁሉ የአብርሃም ልጆች በሆኑት በእግዚአብሔር ሕዝብ ፊት ተሰበሰቡ፣ እግዚአብሔር የምድር አሕዛብ ነገሥታት ካላቸው መሣሪያ ሁሉ የሚበልጥ ታላቅ ኃይል አለው፣ እርሱ ታላቅ ነው! በየትም ስፍራ ያሉሕዝቦች ሁሉ ያከብሩታል።
Chapter 48
1 ያሕዌ ታላቅ ነው፣ በሚኖርባት ከተማ፣ በጽዮን በተቀደሰው ተራራ ታላቅ ምስጋና ሊቀበል ይገባዋል። 2 በታላቁ ተራራ የተሰራችው ከተማ የምታምር ናት፣ እውነተኛ አምላክ የሚኖርባት ታላቁ ንጉሥ የሚኖርባት፣ በምድር ያሉ ሰዎች ሲመለክቱአት ሐሴት የሚያደርጉባት ናት። 3 እግዚአብሔር በዚያ ጠንካራ መጠጊያዋ ነው፣ በዚያ የሚኖሩትን ሕዝብ ሁሉ ይጠብቃቸዋል። 4 ከተማችንን ለማጥቃት፣ ብዙ ነገሥታት ከሠራዊታቸው ጋር ተሰበሰቡ፣ 5 ነገር ግን ሲመለከቷት፣ ተደነቁ፣ ፈሩም ወደ ኋላቸውም ሸሹ። 6 እጅግ ፈርተዋልና ሴት ምጧ በመጣ ጊዜ እንደምትንቀጠቀጥ ተንቀጠቀጡ። 7 የተርሴስ መርከቦች በታላቅ ነፋስ እንደሚናወጡ ተናወጡ። 8 ይህች ከተማ እጅግ ታላቅ እንደ ነበረች ሰምተናል፣ አሁን ይህ እውነት እንደሆነ አየን። የመላእክት ሠራዊት አዛዥ የሆነው ያሕዌ የሚኖርበት ከተማ ነች። እግዚአብሔር ለዘላለም የሚያጸናት ከተማ ናት። 9 እግዚአብሔር ሆይ በመቅደስህ እንደገባህልን ቃል ኪዳን እንደ ወደድከን አሰብን። 10 አንተ በኃይልህና በጽድቅ ስለምትገዛ በምድር ያሉ ሕዝቦች ሁሉ ያመሰግኑሃል። 11 በጽዮን ተራራ የሚኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ይደሰታሉ! በይሁዳ የሚኖሩ ሁሉ ሐሴትን ያደርጋሉ፣ በጽድቅ ትፈርድላቸዋለህና። 12 እናንተ የኢየሩሳሌም ሰዎች በጽዮን ተራራ እየዞራችሁ ግንበኛዋን ቁጠሩ፣ 13 ግንቦችዋንም አስተውሉ ጠንካራ ስፍራዋንም መርምሩ ለልጆቻችሁም መንገር ትችላላችሁ። 14 ለልጆቻችሁ እንዲህ በሉ፣ "ይህች የአምላካችን ከተማ ናት፣ እርሱ ለዘላለም ይኖራል፣ በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ለዘላለም ይመራናል።"
Chapter 49
1 አሕዛብ ሁላችሁ ይህን ስሙ! በዓለም የምትኖሩ ሕዝቦች ሁሉ አድምጡ፣ 2 ታላላቆችና ታናናሾሁ ሁሉ፣ ሀብታሞችና ድሆች ሁሉ፣ እያንዳንዳችሁ የምናገረውን ስሙ። 3 የማስበው ነገር እጅግ ጠቃሚ ነው፣ የተናገርኩት ጠቢባን እንድትሆኑ ያስችላችኋል። 4 የጥበብ ቃልን ልነግራችሁ አስባለሁ፣ በገናዬን እየተጫወትኩ የጥበብ ቃሎቹ ምን ማለት እንደሆኑ አብራራለሁ። 5 በመከራ ጊዜ አልጨነቅም በጠላቶች በተከበብኩ ጊዜ አልታወክም። 6 በብልጥግናቸው የሚመኩ፣ ነገሮች ሁሉ ለእነርሱ ከብልጥግናቸው የተነሣ መልካም እንደሚሆንላቸው የሚታምኑ ክፉ ሰዎች ናቸው። 7 ሀብታሞች ሊሆኑ ይችላሉ፣ ነገር ግን ለዘላለም ለመኖር ለእግዚአብሔር ገንዘብ ሊሰጡ አይችሉም! ማንም የዘላለም ለመኖር ለእግዚአብሔር በቂ ክፍይ ኣሊያደርግ አይችልም። 8 ለሕይወት የሚከፈል ክፍይ ኣእጅግ ትልቅ ስለሆነ ማንም ሊከፍል አይችልም 9 ለዘላለም ለመኖርና የማይሞትና የማይቀበር መሆን አይችልም። 10 ሞኞችና ደደብ ሰዎችም ሲሞቱ አይተናል፣ ጠቢባንም ሲሞቱ አይተናል፣ ሁሉም ንብረቶቻቸውን ትተው ይሄዳሉ ሌሎችም ይወርሱአቸዋል። 11 በአንድ ወቅት በመሬት ላይ ቤቶች ነበሩአቸው፣ አሁን ግን መቃብሮቻቸው ለዘላለም ቤቶቻቸው ሆነዋል፣ በዚያም ለዘላለም ይኖራሉ! 12 ሰዎች ምንም ያህል ታላቅ ቢሆኑ፣ ያ ከመሞት አያድናቸውም፣ እንስሳትም እንዲሁ ናቸው። 13 ባደረጉት ነገር በሚታመኑ ሞኞች ሰዎች ላይ የደረሰው ይኸው ነው፣ በንብረቶቻቸው ደስ በሚላቸውም ላይ የደረሰው ይኸው ነው። 14 ለመታረድ እንደሚነዱ በጎች እነርሱም ወደ ሞት ይሄዳሉ። በማለዳ ቅዱሳን በእነርሱ ላይ ይገዛሉ፣ እነዚያ ሀብታም ሰዎች ይሞታሉ አካላቸውም በመቃብር ውስጥ ፈጥኖ ይበሰብሳል፣ ከቤቶቻቸው ተለይተው ሙታን በተሰበሰቡበት ሥፍራ ይሆናሉ። 15 እግዚአብሔር እንደሚታደገኝ የተረጋገጠ ነው፣ ስለሆነም በሙታን ማደሪያ በሲዖን አልሆንም፣ እርሱ ወደ ራሱ ይወስደኛል። 16 አንድ ሰው ሲበለጽግና ቤቱም ከቀን ወደ ቀን የተንቆጠቆጠ ሲሆን አትጨነቁ። 17 በሚሞትበት ጊዜ፣ ከራሱ ጋር ምንም አይወስድም፣ ሁብቱ ከእርሱ ጋር አይሄድም። 18 ሀብታም ሰው፣ ራሱን ባርኮአል፣ ስኬታማ ስለሆኑም ሰዎች ያመሰግኑታል፣ 19 ነገር ግን ይሞታል ወደ አባቶቹም ይወርዳል ለዘላለምም ብርሃንን አያይም። 20 ምንም እንኳ ሰው ታላቅ ቢሆን ያ ታላቅነቱ ከምቶ ሊያድነው አይችልም፣ ይሞታል፣ እንስሳትም እንደሚሞቱት ይሆናል።
Chapter 50
1 በሁሉም ላይ ሥልጣን ያለው እግዚአብሔር ይናገራል፣ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ ያለውን ሕዝብን ሁሉ ይጠራል፡፡ 2 እጅግ ውብ በሆነችው በኢየሩሳሌም ከተማ ከጽዮን ተራራ የእግዚአብሔር ክብር ይታያል፡፡ 3 አምላካችን ይመጣል ዝምም አይልም፡፡ ታላቅእሳት በፊቱ ነው፤ በዙሪያውም ብዙ ዐውሎ ነፋስ አለ፡፡ 4 በሕዝቡ ላይ ለመፍረድ ይመጣል፤ በሰማይ ባሉት መላእክትና በምድር ባሉት ሕዝብ ላይ ይቆጣል፡፡ 5 እርሱም እንዲህ ይላል፡- ‹‹በታማኝነት የሚያመልኩኝንና መስዋዕትን በማቅረብ ከእኔ ጋር ቃል ኪዳን የገቡት ወደ እኔ ሰብስቡልኝ፡፡›› 6 በሰማይም መላእክት እንዲህ ያውጃሉ፡- ‹‹እግዚአብሔር ጻድቅና የበላይ ዳኛ ነው፡፡›› 7 ሕዝቤ የሆይ ስሙኝ፤ የእስራኤል ልጆች ሆይ ስሙኝ እኔ አምላካችሁ ነኝና ያደረጋችሁትን ኃጢአት ተናገሩ፡፡ 8 መስዋዕት በማቅረባችሁ አልዘልፋችሁም፤ በመስዊያም ስለሚቀርብ የሚቃጠል መስዋዕታችሁ አይደለም፡፡ 9 ነገር ግን ከቤታችሁም ፍሪዳ ከመንጋችሁም አውራ ፍየልን አልፈግም፡፡ 10 ምክንያቱም የምድረ በዳ አራዊት ሁሉ በሺህተራራዎች ያሉ እንስሶችም የእኔናቸው፡፡ 11 የሰማይ አዕዋፍ ሁሉ የእኔ መሆናቸውን አውቃለሁ፤በምድር ዙሪያ የሚንቀሳቀሱፍጥራታትሁሉየእኔ ናቸው፡፡ 12 ምግብ አስፈልጎኝ ብርበኝ ምግብ እንድታመጣልኝ ለአንተ አልነግርህም፤ ዓለምና ሞላው የእኔ ናቸውና፡፡ 13 ለመስዋዕት የምታቀርቡትን የፍሪደውን ሥጋ አልበላም፤ የፍየሉንም ደም አልጠጣም፡፡ 14 እንድታቀርብልኝ የምፈልገው እውነተኛ የምስጋናና የስእለትህን መስዋዕት ነው፡፡ 15 በመከራ ቀን ወደ እኔ ጸልይ፤ ይህን ስታደርግእኔ አድንሃለሁ ከዚያም ታመሰግለኛለህ፡፡ 16 ነገር ግን ለክፉ ሰዎች እንዲህ እላለሁ፡- ትእዛዛቴን ወይም ከእናንተ ጋር ስለገባሁት ቃል ኪዳን ትናገራላችሁ? 17 ምክንያቱም እኔ እንድመራችሁ ፈቃደኛ አልሆናችሁም፤ የነገረኩአቸሁንም አልተቀበላችሁም፡፡ 18 ሌባ ባየህ ጊዜ ሁሉ የእርሱ ወዳጅ ትሆናለህ፤ ውሎህና ኑሮህ ሁሉ ከአመንዝሮች ጋር ነው፡: 19 አፍህ ሁልጊዜ የሚናገረው ክፋትን ነው፤ ሁልጊዜም ሰዎችን ታታልላለህ፡፡ 20 ሁልጊዜም የራስን ቤተ ሰብ ትከሳለህ፤ ለእነርሱም ዕንቅፋት አኖርህ፡፡ 21 ይህን ሁሉ አድርገህ ዝም ሰለአልሁህ እኔን እንደ አንተ ኃጢአተኛ አድርገሃል፤ ነገር ግን አሁን በፊትህ ቆሜ እዘልፍሃለሁ፤ እወቅስሃለሁም፡፡ 22 ስለዚህ እኔ የምትረሱ ሁሉ ይህን አድምጡ፤ አለበለዚያ ግን ብትንትናችሁ እስወጣ ድረስ እቀዳችኋለሁ፤ ማንም አያድናችሁም፡፡ 23 እኔን የሚያከብረኝ መስዋዕት ስለሠራሁት ሥራ የሚቀርበው ምስጋና ነው፤ እኔ ሁልጊዜ የምፈልገውን የሚያደርጉትን አድናቸዋለሁ፡፡
Chapter 51
1 አቤቱ በእውነት ስለምትወደኝና መሐሪም ስለሆንህ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ፡፡ 2 ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ ከኃጢአቴም አንጸኝ፡፡ 3 ይህን የምልበት ምክንያትአንተን ያልታዘዝባቸውን መንገዶች ሁሉ አውቃለሁ፤ሁልጊዜም ልረሳቸው አልችልም፡፡ 4 አንተን ብቻ በደልሁ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ፣ አንተም ያደረግሁትን ሁሉ አይተሃል፤ በደለኛ ነህ ስትለኝ ትክክል ነው፤ በቅን ፍርድህም ብትቀጣኝ የሚገባኝ ነው፡፡ 5 እነሆ ከመወለዴ ጀምሮ ኃጢአተኛ ነኝ፤በርግጥም እናቴም በኃጢአት ፀነሰችኝ፡፡ 6 እነሆ አንተ እንደምትፈልገው በእኔ ውስጥ እንዲሆን እውነትን ወደድህ የማይታይ ስውር ጥበብን አስታወቅኸኝ፡ 7 ከኃጢአቴ ፈጽሞ አንጻኝ፣ እነጻማለሁ እጠበኝ ከበረዶም ይልቅ ነጭ እሆናሁ፡፡ 8 እንደገና ሐሤትንና ደስታን እንዲሰማኝ አድርገኝ፤መንፈሴን ሰብራሃልና፡፡ 9 ከኃጢአቴ ፊትህን መልስ በደሌንም ሁሉ ደምስስልኝ፡፡ 10 አቤቱ ንጹሕ ልብን ፍጠርልኝ የቀናውንም መንፈስ በውስጤ አድስ፡፡ 11 ከኃጢአቴ የተነሣ ከፊትህ አትጣለኝ ቅዱስ ፣ መንፈስህንም ከእኔ ላይ አትውሰድብኝ፡፡ 12 ከኃጢአቴ ነጻ እንዳደረግሃኝ እንዲታወቅ በውስጤ ደስታ ስጠኝ፤መንፈሴ ለአንተ እንዲታዘዝ አድርገው፡፡ 13 ይህን ብታደርግ እንደምትፈልገው እንዲያደርጉ ለሌሎች ኃጢአተኞች የሕግ መንገድ አስተምራለሁ፣ ኃጢአተኞችም ንስሓ ገብተው አንተን ይታዘዛሉ፡፡ 14 አቤቱ፤ የምታድነኝ አንተ ብቻ ነህ፤ ጠላቱ ያልነበረውን ሰው እንዲሞት ስላደረግሁት በደሌ ይቅር በለኝ፤ ይህን ስታደርግ ስለጽድቅህ በደስታና እንደሚገባ እዘምራለሁ፡፡ 15 አቤቱ ያዌህ፤ አፌም ምስጋናህን እንዲናገር እርደኝ፡፡ 16 ሰዎች በሚያቀርቡልህን መስዋዕት ብቻብትወድድ ኖሮባቀረብሁ ነበር፣ የሚቃጠለውም መሥዋዕት ደስ አያሰኝህም፡፡ 17 አቤቱ አንተ የምትወደው መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፣ የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ አትንቅም፡፡ 18 አቤቱ፣ በኢየሩሳሌም ለሚኖሪ ሰዎች መልካምን አድርግ፤ የከተማውንም ቅጥር እንዲያድሱእርዳቸው፡፡ 19 ያን ጊዜምየጽድቁን መሥዋዕት መባውንም የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በመሠዊያህ ላይ ፍሪዳወችን ይሠዋሉአንተም ትደሰታለህ፡፡
Chapter 52
1 አንተ ኩራተኛ ሰው፣ ኃያል እንደ ሆንክ ታስባለህ፣ በሌሎች ላይ መከራን በማምጣትህ ትኩራራለህ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር ሕዝቡን በታማኝነት ሁልቀን ከአንተ ይጠብቃል። 2 ቀኑን ሙሉ ሰዎችን ለማጥፋት ታቅዳለህ፣ የምትናገረውም እንደ ተሳለ ምላጭ ነው፣ ሁልጊዜም ሰዎችን ታታልላለህ። 3 መልካምን ከማድረግ ይልቅ ክፉውን ለማድረግ ትወዳለህ፣ እውነትን ከመናገር ይልቅ መዋሸትን ትመርጣለህ። 4 የምትናገረው ሁሉ ሰዎችን የሚያታልል ነው፣ ሰዎችን የሚጎዳ ነገር መናገርን ትወዳለህ! 5 ነገር ግን እግዚአብሔር ለዘላለም ያጠፋሃል፣ ይዞ ከቤትህ ጎትቶ ያወጣሃል፣ ሰዎች ከሚኖሩበት ከዚህ ምድር ወደ ልዋ ስፍራ ያፈልስሃል። 6 ጻድቃን ይህን በአንተ ላይ የተደረገውን ሲመለከቱ ይፈራሉ፣ በደረሰብህም ነገር ይስቃሉ እንዲህም ይላሉ፣ 7 "እግዚአብሔር እንዲጠብቀው በማይጠይቀው ሰው ላይ የደረሰብትን ተመልከት፣ የብልጥግናው ብዛት እንደሚያድነው ተመክቶ ነበር፣ ከሌሎች በክፉ ሥራው በወሰደው ገንዘብ ተመክቶ ነበር!" 8 እኔ ግን በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ውስጥ ስለማመልክ የተጠበቅሁ ነኝ፣ እንደ ጠንካራ የወይራ ዛፍ ነኝ፣ በታማኝነት ለዘላለም በሚወደን በእግዚአብሔር እታመናለሁ። 9 እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ክፉዎችን ስለምታጠፋቸው ሁልጊዜ አመሰግንሃለሁ። በአንተ ሕዝብ ፊት ስቆም፣ የአንተን መልካምነት አውጃለሁ።
Chapter 53
1 ሰነፍ ሰዎች ብቻ በልባቸው አምላክ የለም ይላሉ፡፡ እንዲህ የሚሉ ሰዎች ክፉዎች ከምንም የሚበልጥ ኃጢአት ያደርጋሉ፡፡ ከእነዚህም ሰዎች መካከል አንዳቸውም መልካም የለም፡፡ 2 የሚያስተውልናእግዚአብሔርን የሚፈልግ እንዳለ ያውቅ ዘንድ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ይመለከታል፡፡ 3 ነገር ግን ሁሉም ክፉና ረከሱ ናቸው ማንም መልካም የሚያደርግ የለም፡፡ 4 እነዚህ ክፉ ሰዎች እግዚአብሔር ለእነርሱ ያደረገላቸውን አያውቁምን? እርሱ ያዘጋጀውን ምግብ እየበሉ በያዌህ ሰዎች ላይ ክፉ ያደርጋሉ፡፡ ወደ ያዌህም አይጸልዩም፡፡ 5 ነገር ግን አንድ ቀን አነዚህ ሰዎች ከዚህ በፊት ፈርተው በማያቁት ሁኔታ ይፈራሉ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር ለሞት እንደተወው ያደርጋቸዋል አጥንታቸውንም ይበታትናቸዋል፡፡ እግዚአብሔርን ስለተው እንዲሸነፉና ፈጽሞ የተጣሉ ያደርጋቸዋል፡፡ 6 እግዚአብሔር መጥቶ የእስራኤል ልጆችን እንዲያድናቸው እወዳለሁ፤ እግዚአብሔር ሆይ ሕዝንህን እንደገና ስትባርክ የእስራኤል ልጆች የያዕቆብ ትውልድ ሁሉ ይደሰታሉ፡፡
Chapter 54
1 እግዚአብሔር ሆይ በኃይልህ ከጠላቶቼ አድነኝ፣ በዚህም ለሰዎች ምንም የተሳሳተ ነገር እንዳላደረግሁ አሳያቸው! 2 እግዚአብሔር ሆይ ጸሎቴን ስማ፣ ለአንተ የምናገረውን አድምጥ 3 እንግዳ ሰዎች ሊያጠቁኝ እየሞከሩ ነውና፣ ኩራተኛ ሰዎችም ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ፣ እነርሱ ለአንተ አክብሮት የሌላቸው ሰዎች ናቸው። 4 እግዚአብሔር ግን ይረዳኛል፣ ያሕዌ ከጠላቶቼ ይጠብቀኛል። 5 በእኔ ላይ እንዲደረግ የሚፈልጉት ክፉ ነገር በራሳቸው ላይ ያደርግባቸዋል፣ አንተ ለእኔ የገባህልኝን ቃል ኪዳን በታማኝነት ታደርጋለህና፣ አጥፋቸው። 6 ያሕዌ፣ በደስታ እሰዋልሃለሁ፣ ፈቅጄ አመሰግንሃለሁ፣ አንተ ለእኔ መልካም ነህና፣ 7 ከመከራዎቼ ሁሉ አድነኸኛል፣ ጠላቶቼን ስታሸንፋቸው አይቻለሁ።
Chapter 55
1 አቤቱ ጸሎቴን አድምጥ፣ ወደ አንተ እይጮኩ ሳለሁ ከእኔ አትራቅ፡፡ 2 ተመልከተኝ ስማኝም፡፡ በኀዘኔ ተቅበዘበዝሁ ተናወጥሁም፤ 3 ጠላቶቼ ያስፈራሩኛል፤ ክፉ ሰዎች ግፍ ያደርጉብኛል፡፡ በመከራ ውስጥም ጥለውኛል፤ ይቆጡኛል፣ ይጠሉኛልም፡፡ 4 በፍርሃት ላይ ወድቄአለሁ፤ እሞታሁ ብዬም ፈርቻለሁ፡፡ 5 ፍርሃትና እንቅጥቅጥ መጡብኝ ሙሉ ለሙሉ ፍርሃት ወደቀብኝ፡፡ 6 እንዲህም አልሁ፡- እንደ ርግብ ክንፍ ብኖረኝ ተመኘሁ፤ ክንፎች ብኖሩኝ በርሬ የእረፍት ቦታ አገኝ ነበር፡፡ 7 እነሆ፣ ኮብልዬ በራቅሁ በምድረ ባዳም በተቀመጥሁ፤ 8 ጠላቶቼ እንደ ዐውሎና ከብርቱ ነፋስ እንዳይጠቁኝ በፍጥነት ሸሽቼ መደበቂያ ቦታ ባገኘሁ አልሁ፡፡ 9 አቤቱ በኢየሩሳሌም ከተማ ውስጥ ግፍና ጠብን ሲያደርጉ አይችአለሁና ጠላቶቼን አሳውራቸው ዕቅዳቸውንም አክሽፍባቸው ፡፡ 10 በቀንና በሌሊት በቅጥርዋ ላይ ይሄዳሉ፣ ዓመፃን እያደረጉ መከራ በመጫን ላይ ናቸው፡፡ 11 በሁሉንም ስፍራ እያጠፉ ነው፤ በሕዝቡም ላይ ግፍ እያደረጉ በየገበያ ቦታዎችም ያጭበረብራሉ፡፡ 12 ይህን የሚያደርግብኝ ጠላትቢሆን ኖሮ፣ በታገሥሁ ነበር፤ የሚጠለኝና የሚንቀኝ ሌላ ሰው ቢሆን ኖሮ ከእርሱ ራሴን በሰወርሁ ነበር፡፡ 13 ነገር ግን ይህን የሚያደርግብኝ ልክ እንደ እኔ እኩያ የሆነ ወዳጄ ነው፡፡ 14 ቀደም ሲል መልካም ነገሮችን አብረን ተነጋግረን ነበር፤ በእግዚአብሔር ቤተ መቅደስም አብረን ተጉዘናል፡፡ 15 ጠላቶቼ በድንገት ይሞቱ ዘንድ እውዳለሁ፤ ገና ወጣት ሳሉ ሙታን ወዳሉበት ይውረዱ፡፡ 16 እኔ ግን ወደ ያህዌ አምላኬ እንዲያድነኝ እጸልያለሁ፤ እርሱም ያድነኛል፡፡ 17 በጥዋትናበቀትር በማታምለእርሱ እናገራለሁ እጮኻለሁ፣ ድምፄንም ይሰማኛል፡፡ 18 በእኔ ላይ ብዙ ጠላቶች አሉብኝ፤ እርሱ ግን ያድነኛል፣ ከውጊያ ስፍራም ወደ ምቹ ቦታ ያመጠኛል፡፡ 19 እግዚአብሔር ሁሉንም ነገሮች ለዘላለም የሚገዛ ነው፤ እርሱም ይሰማኛል፡፡ከክፉ ሥራቸው አልተመለሱምና ለእግዚአብሔርም ምንም ክብር አላሳዩምና እርሱ ጠላቶቼን እንዲሸነፉና እንዲጣሉ ያደርጋል፡፡ 20 ቀደም ሲል የጠቀስኩት ባለደረባዬ ወዳጆቹን አሳልፎ ሰጣቸው፤ ከእርሱ ጋር የገባውንም ቃል ኪዳን ሰፈረሰ፡፡ 21 እርሱ የተናገረው ቅቤ ለመዋጥ እንደሚቀል ለመስማት ይቀላል፡፡ ነገር ግን በልቡ ሕዝቡን ጠልቶአል፤ ቃሎቹም እንደ ዘይት እንደ ሰይፍ ሰዎችን ይጎዳል፡፡ 22 መከራህን ሁሉ በያህዌ ላይ ጣላው፤ እርሱም ይጠብቅሃል፤ እርሱ በቅዱሳ ላይ መከራ እንዲደርስባቸው አይፈቅድም፡፡ 23 አቤቱ አንተ ነፍሰ ገዳዮችንና ሐሰተኞችን ለመኖር ካሰቡት ግማሽ ሳይሞላቸው እንዲሞቱ ታደርጋቸዋለህ፡፡ እኔ ግን በአንተ እታመናለሁ፡፡
Chapter 56
1 አቤቱ ሰዎች ጥቃት አድርሰውብኛልና ምሕረትን አድርግልኝ፤ ቀኑን ሙሉ ጠላቶቼ እየተከተሉ ያስጨንቁኛል፡፡ 2 ጠላቶቼ ሁልጊዜ ያጠቁኛል፤ እነርሱም ብዜዎች ስለሆኑ በልበ ሙሉነት ያጠቁኛል፡፡ 3 ነገር ግን በፈራሁ ጊዜ ሁሉ በአንተ ታመንሁ፡፡ 4 አቤቱ አምላኬ የሰጠሃውን ተስፋ ስለምትጠብቅ አንተን አመሰግናለሁ፤ በአንተ ታምኛለሁና አልፈራም፤ ተራ ሰዎች ምንም ሊያደርጉብኝ አይችሉም፡፡ 5 ሁልጊዜ ጠላቶቼ ያልተናገርኩአቸውን እንደ ተናገርኩ አድርገው ክፉ ያስወሩብኛል፤ በእኔ ላይም የሚመክሩብኝ ሁሉ ለመጉዳት ነው፡፡ 6 በማደርጋቸው ሁሉ መከራ ሊያደርሱብኝ በሽምቅ ይከታተሉኛ፤ ዕድ ቢያገኙ ሊገድሉኝ ይፈልጋሉና፡፡ 7 ክፉ ሰለሚያደርጉበትም እግዚአብሔር ይቀጣቸዋል፤ በማሸነፍ እንደተቆጣህ አሳይ፡፡ 8 ሁልጊዜ ለብቻዬ ያሳለፍኩተን ሁሉ ትቆጥራለህ፤ ምን ያህል በፊትህ እንደጮኩም እንባዬን ሰፍረህ ቢሆን፤ እባዬን ቆጥራሃል ቁጥሩንም በመጽሐፍህ ጽፈሃል፡፡ 9 አንተን በጠራሁህ ጊዜ ጠላቶቼ በፊትህ ይሸነፉ፤ ይህም የሚሆነው አንተ ስለ እኔ ስለምትዋጋልኝ እንደ ሆነ አውቃለሁ፡፡ 10 የሰጠሃውን ተስፋ ስለምትጠብቅ አመሰግንሃለሁ፤ ለዚህም ሁልጊዜ ያህዌ አመሰግንሃለሁ፡፡ 11 በአንተ ስለምታመን አልፈራም ፤ ሰው ሊጎደኝ እንደማይችል አውቃለሁ፡፡ 12 አቤቱ ለአንተ የምስጋና ስእለት አቀርብልሃለሁ፤ አንተን ለማመስገን መስዋዕት አቀርብልሃለሁ፡፡ 13 ነፍሴን ከሞት እግሮቼንምከመሰናከል አድነሃልና አመሰግንሃለሁ፡፡ ማንም ሰው ሊጎደኝ አይችልም፡፡ በዚህም ምክንያት በሕያዋን ባሉበት በሚያበረውብርሃን አንተ ባለህበት መኖሬን እቀጥላለሁ፡፡
Chapter 57
1 እንድታድነኝ ወደ አንተ መጥቻለሁና አቤቱ ማረኝ፤ ማረኝ፡፡ 2 አቤቱ አንተ ከአማልክት ሁሉ ይልቅ ታላቅ ነህ፤ ወደምታድነኝ ወደ አንተ እጮኸለሁ፡፡ 3 ከሰማይ ሆነህ ትሰመኛለህ ታድነኛልም፡፡ነገር ግን እኔን የሚጎዱኝን እንዲሸነፉ ታደርጋለህ፤ ይናቃሉም፡፡ በሰጠኝም ተስፋ መሠረት እግዚአብሔር ሁልጊዜ ይወደኛል፡፡ 4 አንዳንድ ጊዜ ጊዜ ሰውን ከሚገድሉ አንበሶች ጠላቶቼ ተከብባለሁ፤ በጥርሳቸው እንደሚነክሱ እንስሳትን እንደሚገድሉ አንበሶች፤ ነገር ግን ጠላቶቼ ጥርሶችነ ሳይሆኑ ጦርና ቀስት ናቸው፤ የሐሰት ነገሮችን የሚናገሩትንም፡፡ 5 አቤቱ ከሰማያት ሆነህ ታላቅ መሆንህን አሳይ፤ ክብርህንም ለሰዎች ሁሉ በምድር አሳይ፡፡ 6 ጠላቶቼ እኔን ለማጥመድ መረብ ስዘረጉ እኔም በጣም አዘንኩ፤ በምሄድበት መንገድ ጥልቅ ጉድጓድ ቆፈሩ፤ ነገር ግን ራሳቸው ወደቁበት፡፡ 7 አቤቱ ልቤ ሙሉ ነው፤ ለአንተ እዘምራለሁ፤ በመዝሙርም አመሰግንሃለሁ፡፡ 8 እርሱን ከፍ ማድረግና ማመስገን ክብር ነው፤ በፀሐይ መውጫ ፊት እቆማለሁ፤ በበገናና በመሰንቆ አመሰግንሃለሁም፡፡ 9 አቤቱ በሕዝብ ሁሉ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ በወገኖችም መካከል አንተን ለማመስገን እዘመራለሁ፡፡ 10 ለእኛ ያለህ እውነተኛ ፍቅርህ ከምድር እስከ ሰማይ ድረስ ከፍ ያለ ነው፡፡ 11 አቤቱ ታላቅ መሆንህን በሰማያት ላይ አሳይ፤ በምድርም ላሉት ሕዝብ ሁሉ ክብርህን አሳይ፡፡
Chapter 58
1 እናንተ ኃያላን ሰዎች እውነትን ከቶ አተናገሩም፤ ስለሰዎች እውነትን ነገር አትፈርዱም፡፡ 2 በልባችሁ ሐሰት ስለማድረግ ብቻ ታስባላችሁ በዚህም እስራኤል ምድር ግፍን ታደርጋላችሁ፡፡ 3 ክፉ ሰዎች ከመወለዳቸው ጀምሮ ኃጢአትን ያደርጋሉ፤ ሐሰትንም ይናገራሉ፡፡ 4 አቤቱ ታላቅ መሆንህን በሰማያት ላይ አሳይ፤ በምድርም ለሰዎች ሁሉ ክብርህን አሳይ፤ ክፉ ሰዎች የሚናገሩት እንደ እባብ መርዝ የቆስላል፡፡መልካም ምክርን ለመስማት ጆሮአቸው የተደፈነ ነው፡፡ 5 እፉኝት ጆሮውን የሚደፍነው የእባብ አፍዛዦችን ድምፅ ወይም የአስማተኞችን ድግምት ላለመስማት ነው፡፡ 6 አቤቱ እንደ አንበሳ ደቦል ሊያጠቁን እንደሚፈልጉ ጠላቶቼ ጥርሳቸውን በአፋቸው ስበር፡፡ መንጋጋቸውንም አውልቅ፡፡ 7 ፈስሶ እንደሚያልቅ ውሃ ይጥፉ፤ በመንገድ ላይ እንደ በቀለ ሣር ተረጋግጠው ይርገፉ፡፡ 8 እየሄደ ሟምቶ እንደሚያቅ ቀንድ እጣ ሞቶ እንደ ተወለደና ብርሃንን ከቶ እንዳላየ ጭንጋፍ ይሁኑ፡፡ 9 እሾኽ በእሳት ላይ ተደርጎ ከመሞቁ በፊት ፈጥነህ ጠራርገህ አጥፋቸው፡፡ 10 እግዚአብሔር ክፉ ሰዎችን ሲቀጣቸው በማየታቸው ጻድቃን ደስ ይላቸዋል፡፡በክፉዎችም ደም እግሮቻቸውን ይታጠባሉ፡፡ 11 በዚያን ጊዜ ሰዎች በእውነትም ለጻድቃን የመልካም ሥራ ሽልማት አለ፤ እንዲሁም በዓለም ላይ የሚፈርድ አምላክ በርግጥ አለ ይላሉ፡፡
Chapter 59
1 አምላኬ ሆይ፣ ከጠላቶቼ አድነኝ፤ ከሚያጠቁኝ ሰዎችም ጠብቀኝ፡፡ 2 ከግፍ አድራጊዎች ታደገኝ ከነፍሰ ገዳይ ሰዎችም አድነኝ፡፡ 3 እነሆ፣ ነፍሰ ገዳዮችሽምቃውብኛልና ብርቱሰዎችም በላዬ ላይ ተሰበሰቡ፡፡ ያህዌ ሆይ ክፉ ሳላደርግም ይህን ያደርጉብኛል ተመልከተው፡፡ 4 በእነርሱ ላይ ምንም ሳላደርግ ሊያጠቁኝ ተዘጋጅተዋል፡፡ 5 ያህዌ አምላኬ ሆይ፣ እኛ የእስራኤል ልጆች የምንሰግድልህ የመላእክትን ጦር የምትመራ አንተን የማያከብሩትን የአህዛብን ሰዎችሁሉ ተነሥተህ ቅጣቸው፤ በእኛም ላይ ክፉ የሚያደርጉት ክፉ ሰዎችን ሁሉ አትማራቸው፡፡ 6 በየማታውም ይመላለሳሉ፤ በዚህ ከተማ እየጮኹ እንደ ሚመላለሱ ውሾች እያለከለኩ ይዞራሉ፡፡ 7 ድምፃቸውን ከፍ አድርገው ክፉ ነገሮችን ይናገራሉ፤ ነገሮችን ሰይፍ እንደሚያጠፈው ዓይነት ይናገራሉ፤ ማንም እንደማይሰማን ያስባሉ፡፡ 8 ያህዌ ሆይ አንተ ግን ትሥቅባቸዋለህ፤ አሕዛብንም ሁሉ ትንቃቸዋለህ፡፡ 9 አቤቱ አንተ ትልቅ ስለ ሆንህ በአንተ ላይ እደገፋሉ፤ አንተም መጠጊያዬ ነህ፡፡ 10 ስለምትወደኝ እንደ ተስፋ ቃልህ መሠረት ልታድነኝ ወደ እኔ ትመጣለህ፤ ጠላቶቼ አሸንፈህ ታሳየኛለህ፡፡ 11 ሌሎችን እንዴት እንደቀጠሃቸው አይተውህ ሕዝብን ሕግህን እንዳይረሱ ወድያውኑ አትግዳላቸው፤በዚህ ፈንታ ጌታ ሆይ እንደጋሻየምትጠብቀን በኃይልህ በትናቸው አሸንፋቸውም፡፡ 12 የሚናገሩት ኃጢአትስለ ሆነ አፋቸው ክንፈራቸውም መርገምንና ሐሰትን ስለሚናገሩ በትዕቢተታቸው ይጠመዱ፡፡ 13 በቁጣህ አጥፋቸው፤ እንዳይኖሩም አጥፈፋቸው፤እኛን የእስራኤል ልጆች የሆንነውን ሕዝብህንና ምድርን ሁሉ እንደምትገዛ ያውቁ ዘንድ ፈጽሞ አጥፋቸው፡፡ 14 በየማታው ይመላለሳሉ፤ እንደ ውሾችምበከተማው ይዞራሉ፡፡ 15 እነሱም ምግብ ፍለጋ ይዞራሉ፤ የሚበሉትንም ያላገኙ እንደ ሆነእንደ ውሾች እየተክለፈለፉ ይዞራሉ፡፡ 16 እኔ ግን ለኃይልህ እዘምራለሁ፤ በእውነት ስለምትወደን በማለደ በደስታ እዘምርልሃለሁ፤ በመከራዬም ቀን መጠጊያዬ ሆነኸኛልና እዘምርልሃለሁ፡፡ 17 አቤቱ ብርቱ አንድሆን ያደረግሃኝ አንተ ነህ፤ አንተም መጠጊያዬ ነህ፤ በቃል ኪዳንህ ተስፋ እንደሰጠሃኝ በእውነት ትወደኛለህና፡፡
Chapter 60
1 እንዲህ ብዬ እጸልያለሁ፡- አቤቱ አምላክ ሆይ በእኛ ላይ ስለተቆጠሃን እኛን እስራኤላውያንን ትተሃናል፤ ጠላቶቻችንም እንዲያሸንፉ አድርገሃናል፤ እባክህ እንደገና እንድንበረታ አድርግ፡፡ 2 ጠላቶቻችን ባሸነፉ ጊዜ ኃይለኛ የምድር መናወጥ ሆኖ ምድሪቱን ሰነጣጥቆአል፤ ስለዚህ የምድርን መሰንጠቅ እንደምታጠፋ ሁሉ ሠራዊታችን እንደገና ብርቱ እንሆን እርዳት፤ ምክንያቱም አገራችን በውድቀት ላይ ናትና፡፡ 3 እኛን ሕዝብህን እንድጨነቅ አድርገሃል፤ ከጠጣን በኋላ እንቅፋት እንድንሆነ ጠንካራ ወይን እንደጠጣን አድረግሃን፡፡ 4 ነገር ግን ከጠላቶቻቸው ቀስት እንዲያመልጡ አንተን ለሚያከብሩ ምልክትን ስጣቸው፡፡ 5 እኛ አንተ የምትወደን ሕዝብህ ከጠላቶቻችን እንድንድነ ጸሎታችንን ስማ ጠላቶቻችንንም እንድናሸንፍ በኃይልህ አስችለን፡፡ 6 እግዚአብሔር ጸሎቴን ሰማ ከመቅደሱ ሆኖ እንዲህ ተናገረ፡- ድል አድርጌ ሴኬምን ከተማ እሸነሽናለሁ፤ የሱኪትንም ሸለቆ ለሕዝቤ አከፋፍላለሁ፡፡ 7 የገለዓድ ምድር የእኔ ነው፤ የምናሴምነገድ የእኔ ናቸው፤ የኤፈርሬም ነገድ የራሴ መከላከያ ቁር ነው፤ ይሁዳም በትረ መንግሥቴ ነው፡፡ 8 የሞአብ ምድር መታጠቢያዬ ነው፤ ኤዶም የእኔ መሆኑን ለማረጋገጥ ጫማዬን አኖርበታለሁ፤ ፍልስጥኤምን ምድር ሁሉ ስላሸነፍሁ በድል ድምፄን ከፍ አደርጋለሁ፡፡ 9 የኤዶምን ሕዝብ ለማሸነፍ ስለምፈልግ ዙሪያዋጠንካራ ግንብ ወደተመሸገችው ዋና ከተማቸውሠራዊቴ በድል የሚመራ ማን ነው? 10 አምላክ ሆይ! አንተን እንፈልግሃለን በርግጥ አትተዋን፤ ሠራዊታችን ጠላቶቻችንን ለመዋጋት ሲዘምቱ አብረሃን ውጣ፡፡ 11 ከጠላቶቻችን ጋር ሲንዋጋ የአንተ ርዳታ ያስፈልገናል፤ ምክንያቱም የሰው ርዳታ ከንቱ ነው፡፡ 12 ነገር ግን በአንተ ከእኛ ጋር ከሆነህ እንሸንፋለን፤ እርሱ ጠላቶቻችንን ያዋርዳቸዋል፡፡ ስለዚህ ጠላቶቻችንን ድል እንድናደርግ አንተ አብቀን፡፡
Chapter 61
1 እግዚአብሔር ሆይ ስማኝ፣ ጸሎቴንም መልስ። 2 ተስፋ ቆርጬ ከቤቴም ርቄ ሳለሁ፣ ወደ አንተ እጣራለሁ። ወደ እዚያ ሄጄ፣ በላዩ ላይ ወጥቼ፣ እሸሸግበት ዘንድ፣ ከፍ ወደ አለ አለት ምራኝ። 3 አንተ መሸሸጊያዬ ነህ፣ ጠላቶቼ ሊደርሱ የምይችሉበት አንተ ለእኔ ጠንካራ አምባ ነህ። 4 በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በተቀደሰው ድንኳንህ አጠገብ እንድኖር ፍቀድልኝ! የወፍ ጫጩት በእናቷ ክንፍ ሥር እንደምትጠበቅ በአንተ እንድጠበቅ ፍቀድልኝ! 5 እግዚአብሔር ሆይ፣ ለአንተ ስእለቴን ሳቀርብ ሰምተኸኛልና፣ ለአንተ እጅግ ታላቅ አክብሮት ላላቸው ሰዎች የምትሰጠውን በረከቶች ሰጠኸኝ። 6 እኔ የእስራኤል ንጉሥ ነኝ፣ ለብዙ ዘመን እንድኖርና እንድገዛ ፍቀድልኝ፣ ልጆቼም እንዲሁ ይገዙ ዘንድ ፍቀድላቸው። 7 ለዘላለም እንገዛ ዘንድ ፍቀድልን፣ ተመልከተን፣ ጠብቀን፣ በገባህልን ቃል መሠረት ፍቅርህ በላያችን ላይ ይሁን አድርግልንም። 8 ይህን ብታደርግልን፣ ለስምህ ለዘላለም እዘምራለሁ። የተሳልኩትንም ስእለቴን ሁልጊዜ እፈጽማለሁ።
Chapter 62
1 ለውስጤ ሰላምን የሚሰጠኝ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ ከጠላቶቼም የሚያድነኝ እርሱ ነው፡፡ 2 ከለላ ማግኘት የምችልበት ዓለት እርሱ ብቻ ነው፤ እርሱም ጠላቶቼ መድረስ የማይችሉበተ ከፍ ያ ቅጥር ነው፡፡ 3 ጠላቶቼ እንዳያጠቁኝ መቼ ታስቆማቸዋለህ? እኔ ከአንተ ጋር ሲነፃፀር እንደ አረጀ ግድግዳና እንደ ተነቃነቀ አጥር ዐቅም ያነሰው ሰው ነኝ? 4 4 ሰዎች እንዳያከብሩኝ ጠላቶቼ ከጠቃሚ ቦታ ሊያስወግዱኝ አቅደዋል፡፡ ሐሰትን በመናገር ደስ ይላቸዋል፡፡ በቃላቸው ሰዎችን ይመርቃሉ፤ ነገር ግን በውጣቸው ይረግሙአቸዋል፡፡ 5 በውስጤ ሰላምን የሚሰጠኝ እግዚአብሔር ብቻ ነው፤ እንዲረደኝም በልበ ሙሉነት የምጠብቀው እርሱ ብቻ ነው፡፡ 6 እንደ ዓለት ከለላዬ የሚሆነኝ እርሱ ብቻ ነው፤ ጠላቶቼ ሊደርሱብኝ የማይችሉት እርሱ መጠጊያዬ ነው፡፡ 7 የሚያድነኝና የሚያከብረኝ እግዚአብሔር ነው፤ እርሱም መጠጊያ የማገኝበት ጠንካራ ዓለት ነው፡፡ 8 ሕዝቤ ሆይ! ዘውትር በእግዚአብሔር ታመኑ፤ እርሱ መተጊያችን ስለ ሆነ ችግራችሁን ሁሉ ለእርሱ ተናገሩ፡፡ 9 እንደ ማያስፈልጉ የተቆጠሩ ሰዎች የማይጠቅሙ እንደትንፋሽ አየር ናቸው፤ አስፈላጊ ሆነው የተቆተሩ ሰዎች ደግሞ በእርግጥ ምንም ዋጋ አይገኝባቸውም፡፡ ሁላቸውም በሚዛን ላይ ቢቀመጡ ከነፋስ ሽውታ ይቀላሉ፡፡ 10 ከሌሎች በተቀማ ገንዘብ አትታመኑ፤ ከሌሎች በመዝረፍለማትረፍ አትሞክሩ፤በጣም ሀብታም ብትሆኑ በገንዘባችሁ አትተማመኑ፡፡ 11 እግዚአብሔር ኃይል እንዳለው ከአንድ ጊዜ በላይ ሲናገር ሰምቻለሁ፡፡ 12 በሰጠው ተስፋ ቃል መሠረት በእውነት የሚወደን እግዚአብሔር ነው፤ለሁላችንም እንደየሥራችን ይከፍለናል፡፡
Chapter 63
1 እግዚአብሔር ሆይ አንተ የማመልክህ አምላኬ ነህ፤ በደረቅና ሞቃታማ በረሃ ውሃ እንደሚናፍቅ ሰው ከአንተን ጋር ለመሆን እፈልጋለሁ፡፡ 2 አንተ ፍቅርና ኀይል መሆንህን ለማየትበመቅደስህ ከአንተ ጋር ነበርኩ፡፡ 3 በቃል ኪዳንህ ተስፋ እንደሰጠህ ዘወትር ትወደኛለህ፤ ይህ ከአጠቃላይ ሕይወቴ ይበልጣል፤ ስለዚህም ሁልጊዜ አመሰግንሃለሁ፡፡ 4 በሕይወቴ ዘመን ሁሉ አመሰግንሃለሁ፤ ስጸልይም እጆቼን ወደ አንተ እዘረጋለሁ፡፡ 5 አንተን ማወቅ ከብዙ ግብዣ ይልቅ ያረከኛል፤ስለዚህ በደስታስዘምርልህ አመሰግንሃለሁ፡፡ 6 በመኝታዬም ሆኜ አስታውስሃለሁ፤ ሌሊቱንመ ሁሉ ስለ አንተን አስባለሁ፡፡ 7 ሁልጊዜ ስለረደኸኝ ወፍ ልጅዋን በክንፎችዋ እንደምትጠብቅ ስለምትጠብቀኝም በደስታ እዘምራለሁ፡፡ 8 አንተን በቅርበት እከታተላለሁ፤ እጅህም ይደግፈኛ፡፡ 9 ነገር ግን እኔን ለመግደል የሚፈልጉ ይሞታሉ ወደ ሙታንም ዓለም ይወርዳሉ፡፡ 10 በሰይፍ ይገደላሉ፤ ሬሳቸውንም ቀበሮዎች ይበሉታል፡፡ 11 ነገር ግን እኔ የእስራኤል ንጉሥ እግዚአብሔር በሠራው ደስ ይለኛል፤ እነርሱን ለመርገም እግዚአብሔርን የሚጠይቁ ሁሉ የሚያስመሰገነውን ተስፋ ሳያደርጉ ቢቀሩ ፤ ነገር ግን ሐሰተኞች ምንም እንዳይናገሩ ማድረግ ነው፡፡
Chapter 64
1 እግዚአብሔር ሆይ፣ የሚያስጨንቀኝን ነገር ስነግርህ ስማኝ፣ ጠላቶቼን ፈርቻለሁና፣ እባክህን ከእጃቸው አድነኝ። 2 ክፉ ሰዎች በእኔ ላይ ለማድረግ ካቀዱት ነገር ጠብቀኝ፣ ክፉ ነገር ከሚያደርጉ ቡድኖች ጠብቀኝ። 3 የሚናገሩት ክፉ ነገር እንደ ተሳለ ሰይፍ ነው፣ አስከፊው ቃላቸው እንደ ቀስት ነው። 4 ማንንም አይፈሩም፣ ሰዎችን ይዋሻሉ፣ ምንም ክፉ ያላደረጉ ሰዎችን ይነድፋሉ። በሽምቅ እንደሚያደባና ጠላቶቹን ሲያገኝ በቀስቱ እንደሚነድፍ ሰፍ ናቸው። 5 ያቀዱትን ክፉ ነገር ለማድረግ አንዳቸው ሌላቸውን ያደፋፍራሉ፣ ሰዎችን ለማጥመድ ምን ማድረግ እንደሚያስብ እርስ በርሳቸው ይነጋገራሉ። እንዲህም ይላል፦ "ማንም የምናደርገውን አያይም 6 ምክንያቱም እቅዳችን በምስጢር የተደረ።" ሰዎች በውስጣቸው የሚያስቡትና የሚያቅዱት በእውነት አስደናቂ ነው! 7 ነገር ግን እግዚአብሔር ቀስቱን ወደ እነርሱ ይልካል፣ በድንገትም ይቆስላሉ። 8 የተናገሩት በደለኛነታቸውን ስለሚያሳይ፣ እግዚአብሔር ያስወግዳቸዋ። 9 ከዚያም እያንዳንዱ ሰው ኃጢአት ማድረግን ይፈራል በክፉዎቹ ላይ የደረሰው እንዳይደርስበት ይፈራልና፣ ለሌሎችም እግዚአብሔር ያደረገውን ነገር ይናገራሉ፣ እነርሱም ስለ ጉዳዩ የበለጠ ያስቡበታል። 10 ቅዱሳን ያሕዌ ባደረገው ነገር ሐሴት ያደርጋሉ፣ መሸሸጊያ እንዲሆናቸው ወደ እርሱ ይሄዳሉ፣ እርሱን የሚያከብሩ ሁሉ ያመሰግኑታል።
Chapter 65
1 አምላክ ሆይ አንተን በኢየሩሳሌም ማመስገናችን ትክክል ነው፤ ለአንተ የተሳልነውንም መስጠት ይገባናል፡፡ 2 ጸሎታችን ስለሰማ ሰዎች ሁሉ ከሁሉ ቦታ ወደ አንተ ይመጣሉ፡፡ 3 ብዙ ኃጢአቶቻችን በላያችን ላይ ከባድ ሸክም ናቸው ፤ አንተ ግን በደላችንን ይቅር አልክልን፡ 4 በመቅደስህ ለመኖር በተመረጡት ትደሰታለህ፤ እኛም አንተን በተቀደሰው መቅደስህ ስናመልክህ ከመቅደስህ በሚገኘው ብዙ በረከት እንረካለን፡፡ 5 ጸሎታችንን ሰምተህ ድልን ታጎናጽፈናለህ፤ እኛንም ለማዳን ብዙ ድንቅ ነገሮችን ታደርጋለህ፤ ሩቅ ከሆነው ባሕር ማዶ ያሉት ሳይቀሩ የዓለም ሕዝቦች ሁሉ በአንተ ይታመናሉ፡፡ 6 ታላቅ መሆንህን ለማሳየት በብርታትህ ተራሮችን በቦታቸው ታስቀምጣለህ፡፡ 7 ከባሕሩ መናወጥ የተነሣ የሚያስገመግመውን የማዕበል ድምፅ ጸጥ ታደርጋለህ፤ ብዙ መከራ ሲያሳዩ የሕዝቦችንም ሁከት ዝም ታሰኛለህ፡፡ 8 ስላደረግሃቸው ተአምራት በሩቅ ምድር የሚኖሩ በሙሉ ተደንቀዋል፤ በአንተ ድንቅ ሥራ ምክንያት ከሩቅ ምዕራብ እስከ ምሥራቅ ያሉት የደስታ ድምፅ ይሰማል፡፡ 9 ብዙ መልካም ነገሮች እንዲያድጉ የምድርን አፈር ለመጠበቅ ዝናብን ተልካለህ፤ ምንጮችህን በውሃ ትሞላለህ፡፡እህልንም ታበቅላለህ፤ ይህ እንዲሆን አንተ የወሰንከው ነው፡፡ 10 ለታረሱ ማሳዎች በቂ ዝናብ ትልካለህ፤ እርሻውንም ውሃ ትሞላለህ፤ ዐፈሩንም በካፊያ ተለሰልሳለህ፤ ቡቃያዎችም በቅለው እንዲያድጉ ታደርጋለህ፡፡ 11 አፈሩን ስለባረክህ በመከር ጊዜ መልካም እህል አለ፤ በሄድክበት ሁሉ መልካም እህል በዝቶአል፡፡ 12 የግጦሽ ስፍራዎች በበጎችና በፍየሎች መንጋ ሞልተዋል፤ ይህም ተራራዎችደስ እንደሚላቸው ነው፡፡ 13 መስኮች የብዙ በጎችና ፍየሎች መሰማሪያ ሆነዋል፤ ሸለቆዎችም በሰብል ተሞልተዋል፤ ሁሉም በደስታድምፃቸውን ከፈ አድርገው ይዘምራሉ፡፡
Chapter 66
1 በምድር ለሚኖሩ ሕዝብ ሁሉ ንገራቸው፤ እግዚአብሔርን ለማመስገን በደስታ ይዘምሩ፡፡ 2 እግዚአብሔር ታላቅ ነው መዝሙሮችን ይዘምሩ፤ እርሱ እጅግ የተከበረ መሆኑንም ሰዎች ሁሉ ይናገሩ፡፡ 3 እግዚአብሔርን እንዲህም ይበሉት፤ ሥራህ እንዴት ድንቅ ነው ኀይልህ እጅግ ታለቅ ነው በዚህም ምክንያት ጠላቶችህ በፍርሃት በፊትህ ይጮኻሉ፡፡ 4 በምድር ያሉት ሁሉ ለእግዚአብሔር ይስገዱ፤ እርሱን በማመስገንና በማክበር ይዘምሩ፡፡ 5 ኑና እግዚአብሔር ያደረገውን ሁሉ ኑ እዩ፤ እርሱ በሰዎች መካከል ስላደረገው ድንቅ ሥራው አስቡ፡፡ 6 እርሱ ባሕሩን ወደ ደረቅ መሬት ለውጦአል፤ የቀድሞ አባቶቻችን ወንዙን በአግር ተሸግረዋል፤ እኛም እርሱ ባደረገው ነገር ደስ ብሎናል፡፡ 7 እርሱ በሥልጣኑ ለዘለዓለም የገዛል፤ክፉ ስለማድረጋቸውም አሕዛብን ሁሉ ይቆጣጠራል፤ ስለዚህ በእርሱ ላይ ለማመጽ የሚፈልጉ አሕዛብ መመካት የለባቸውም፡፡ 8 እናንተ ሕዝቦች ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ እንደምታመሰግኑም ሕዝብ ሁሉ እንዲያውቁ ድምጻችሁን ከፍ አድርጋችሁ አመስግኑ፡፡ 9 እርሱ በሕይወት እንድንኖር ጠብቆናል፤ በችግር እንዳንወድቅ አድርጎናል፡፡ 10 አቤቱ አምላክ፤ አንተ ፈተንከን ያልተጠራውን ብረት ሰዎች ለማጠራት ውድ ብረቶችን እንደሚያደርጉት ሕይወታችን በታላላቅ ችግሮች ውስጥ እንድናልፍ አድርገሃል፡፡ 11 በወጥመድ እንድንያዝ አደረግህ፤ በጀርባችን መሸከም የማንችለውን ከባድ ሸክምንም ጫንክብን፡፡ 12 ጠላቶቻችን በግፍ እንዲረግጡን አደረግህ፤ በእሳትና በጎርፍ መካከል አለፍን፤ አሁን ግን እንድንደላደል አደረግሃል፡፡ 13 የሚቃጠል መሥዋዕት ይዤ ወደ መቅደስህ እገባለሁ፤ ስእለቴንም አቀርብልሃለሁ፡፡ 14 መከራ በደረሰብኝ ጊዜ ካዳንከኝ መስዋዕት አቀርባለሁ አልኩ፤ አንተም ስላዳንከኝ ቃል የገባሁትን ስእለት አቀርብልሃለሁ፡፡ 15 በመሰዊያ ላይ የምቃጠል መሥዋዕት አድርጌ በጎችን አቀርባለሁ፤ እንዲሁም በሚቃጠልበት ጊዜ ጭሱ ወደ አንተ በመድረስ መዓዛው ደስ እንዲያሰኝ ኮርማዎችንና ፍየሎችንም አቀርብልሃለሁ፡፡ 16 እግዚአብሔር ያደረገልኝን ሁሉ እንድነግራችሁ፤ እግዚአብሔርን የምትፈሩና የምታከብሩ ሁሉ ኑ ስሙ፡፡ 17 እንዲረዳኝ ወደ እርሱ ጸለይኩ፤ በአንደበቴም አመስገንኩት፡፡ 18 ኃጢአቴን ሳልናዘዝ በልቤ ሰውሬ ቢሆን ኖሮ፣ እግዝአብሔር ጸሎቴን ባልሰማም ነበር፡፡ 20 አሁን ግን ኃጢአቴን ስለተናዘዝኩኝ እግዚአብሔር ሰማኝ፤ ጸሎቴንም አደመጠኝ፡፡ 19 ጸሎቴን ያልናቀኝን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፤ በቃል ኪዳኑ በሰጠኝ ተስፋ ሁልጊዜም ይወደኛል፡፡
Chapter 67
1 እግዚአብሔር ሆይ በምሕረትህ ወደ እኛ ተመልከት ባርከንም በርኅራኄም ተመልከተን። 2 ይህን በማድረግህ በዓለም የሚኖር እያንዳንዱ ሰው አንተ ሰዎች ሁሉ እዲያደርጉ የምትፈልገውን ያውቃሉ፣ እንዲሁም የየአገሩ ሕዝብ ሁሉ አንተ እነርሱን ለማዳን ኃይል እንዳለህ ያውቃሉ። 3 እግዚአብሔር ሆይ፣ ሰዎች ሁሉ አንተን እንዲያመሰግኑ እመኛለሁ፣ ሁሉም አንተን እንዲያመሰግኑ እሻለሁ፣ 4 የአገሩ ሕዝቦች ሁሉ አንተ ሕዝቦችን ሁሉ በእክልነት ስለምትፈርድላቸው በደስታ እንዲዘምሩልህ እሻለሁ፣ አንተ የምድር ሕዝቦችን ሁሉ ትመራለህ። 5 እግዚአብሔር ሆይ፣ የምድር አሕዛብ ሁሉ ያመስግኑህ፣ ሁሉም ያመሰግኑህ ዘንድ እሻለሁ! 6 መላክም ሰብል በምድራችን ላይ በቅሎአልና፣ እግዚአብሔር አምላካችን ባርኮናል። 7 እግዚአብሔር ስለባረከን፣ በምድር በየትም ስፍራ የሚገኙ ሰዎች ሁሉ ለእርሱ የሚገባው ታላቅ ክብር እንዲኖራቸው እመኛለሁ።
Chapter 68
1 እግዚአብሔር ሆይ፣ ተነሥ ጠላቶችህን በትናቸው፤ የሚጠሉህም ከፊትህ እንዲሽሹ አድርግ፡፡ 2 ጢስ በነፋስ በኖ እንደሚጠፋ ጠላቶችህ በነው ይጥፉ፡፡ ሰም በእሳት ቀልጦ እንደሚቀልጥ ክፍዎችም ከእግዚአብሔር ፊት ይጥፉ፡፡ 3 ጻድቃን ግን ደስ ይበላቸው፤ እግዚአብሔር በሚገኝበት ቦታ ሆነው ሐሴት ያድጉ፤ በደስታም ይፈንጥዙ፡፡ 4 ለእግዚአብሔር ዘምሩ እርሱን ለማመስገን ዘምሩ፤ በበረሃ ሜዳ ለሚጓዘው ለእርሱ መዝሙር ዘምሩ፤ ስሙም ያህዌ ነው፤ እርሱ በሚገኝበት ደስ ይበላቸሁ! 5 በተቀደሰ መኖሪያው ያለ አምላክ አባት ለሌላቸው ልጆች አባት ነው፤ ባሎቻቸው ለሞቱባቸውም ሴቶች ጠባቂ ነው፡፡ 6 መጠጊያ ላጡ ብቸኞች የሚኖሩበት መጠለያ ይሰጣቸዋል፤ እስረኞችም ነጻ ወጥተው በብልጽግና እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል፤ ዐመፀኞች ግን በሚያቃጥል በረሓ ይኖራሉ፡፡ 7 አምላክ ሆይ ከግብፅ ሕዝብህን መራህ፤ በበረሓም አብረሃቸው በተጓዝህ፡፡ 8 አንተ ወደ ሕዝብህ በቀረብህ ጊዜ በሲና ተራራ ምድር ተናወጠች፣ ከሰማይም ዝናብን ዘነበ ሕዝብህም አንተን አመለኩ፡፡ 9 በበረሓ ብዙ ዝናብ እንዲዘንብ አደረግህ፤ ለእኛም ለእስራኤል ልጆች በሰጠሃን ምድር እንደገና መልካም ሰብል እንዲበቅልና እንዲያድግ አደረግህ፡፡ 10 ሕዝብህም መኖሪያ ቤታቸወን እዚያ ሠሩ፤ በቸርነትህም ለድኾች የሚያስፈልጋቸውን ምግብ አዘጋጀህላቸው፡፡ 11 እግዚአብሔር ትእዛዝን ሰጠ ብዙ ሰዎችም መልእክቱን ወደ ሌሎች ቦታዎች አሠረጩ;; 12 እንዲህም አሉት፡- ነገሥታት ከነሠራዊታቸው ከሠራዊታችን ወደ ኋላቸው ሸሹ፤ ሠራዊታችን የማረኩአቸውን ነገሮች ወደ ቤታቸው ባመጡ ጊዜ፣ በቤት የቀሩ ሴቶችም ምርኮን ለራቸውና ለቤተ ሰባቸው ተካፈሉ፤ 13 ወደ ጦርነቱ ያልሄዱ በጎቹን ለመጠበቅ ወደ ኋላ የቀሩት ክንፎቻቸው በብር የተለበዱ አንጸባራቂ የሆኑ ከወርቅ የተሠሩ ላባ ያላቸው ርግቦችን አገኙ፡፡ 14 ሁሉን የሚቸል አምላክ ጠላቶችን፣ ነገሥታትን በበታተነ ጊዜ በረዶ በጻልሞን ተራራዎች ላይ እንዲዘንብ ያደረገውን ያስታውሰኛል፡፡ 15 በባለሳ ኮረብታ ረጅም ተራራ አለ፤ ብዙ ሠንሰለታማ የሆነ ተራራ ነው፡፡ 16 ነገር ግን በዚያ ተራራ አጠገብ የሚኖሩ ሰዎች እግዚአብሔር ለዘለዓለም ሊኖርበት በመረጠው፣ በጽዮን ተራራ አጠገብ የሚኖሩትን ሊሰልሉ አይችሉም፡፡ 17 ጠላቶቻችንን ሁሉ ካሸነፍን በኋላ፣ እግዚአብሔር በብዙ ሺህ ከሚቆጠሩት ታላላቅ ሠረገላዎች ጋር ታጅቦ ከሲና ወደ ተቀደሰው መቅደሱ ወደ ኢየሩሳሌም ይመጣል፡፡ 18 መቅደሱ ባለበት በቅዱስ ተራራ በላይ አስቀመጠ፤ በጦርነቱም የተሸነፉ ሰዎችን ከእርሱ ጋር ወሰደ፤ ከተሸነፋቸው ጠላቶች ሥጦታ ተቀበለ፡፡ በእርሱ ላይ ካመጹት እንኳ ሥጦታ ተቀበለ፤ አምላካችን ያህዌም በቅዱስ መቅደሱ ለዘለዓለም ይኖራል፡፡ 19 ከባድ ሸክማችንን እንድሸከም በየቀኑየሚረደንን እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ የሚረደንም እርሱ ነው፡፡ 20 አምላካችን እግዚአብሔር የሚያድ አምላክ ነው፤ በጦርነት ከሞት እንድናመልጥ የሚያደርገን አምላካችን ያህዌ ነው፡፡ 21 ነገር ግን እግዚአብሔር የጠላቶቹን ራስ፣ የኃጢአትን ባሕርይን የተላበሰ በረጅም ጠጉር የተሸፈነ አናታቸውን ይቀጠቅጣል፡፡ 22 ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፡- በየተገደሉትን ሬሳዎች መልሼ አመጣለሁ፤ እንዲሁም በጥልቅ ባሕር የሰጠሙትን መልሼ አመጣቸዋለሁ፡፡ 23 ይህን የማደርገው እግርህን በደማቸው ትታጠባለህ፤ ውሾችህም የጠላቶችን ደም ይልሳሉ፡፡ 24 አምላክ ሆይ ጠላቶችህን ማሸነፍህን እያበሰሩ በክብር አጀብ ወደ መቅደሱ በድል አድራጊነት በሰልፍ ስትገባ ብዙ ሰዎች ያያሉ፤ እንደ ንጉሥና ብዙ ሕዝብ ከአንተ ጋር እንዳጀበህ በሚያሳይ መልኩ ታልፋለህ፡፡ 25 ዘማሪዎች ከፊት ሙዚቀኞች ከኋላ አታሞ የሚመቱ ልጃገረዶች ከመካከል ሆነው ይታያሉ፡፡ 26 እነርሱም እንዲህ እያሉ ይዘምራሉ፡- እናንተ የእስራኤል ልጆች በምትሰበሰቡበት ጊዜ ሁሉ እግዚአብሔርን አመስግኑ፤ እናንተ የያዕቆብ ልጆች ሁሉ ያህዌን አመስግኑ፡፡ 27 በመጀመሪያ በቁጥር ትንሽ የሆነው የብንያም ነገድ ታየ፤ ቀጥሎም ይሁዳ መሪዎች ከነጭፍሮቻቸው ታዩ፡፡ በመጨረሻም የዛብሎንና የንፍታሌም መሪዎች ተከተሉ፡፡ 28 አምላክ ሆይ፤ ኀይልህን ለሰዎች ግለጥ፤ ከዚህ በፊት እኛን ያዳንክበትን ብርታትህን አሳይ፡፡ 29 ነገሥታት ሥጦታ ሲያመጡልህ ከኢየሩሳም መቅደስህ ኃይልህን ነ አሳይ፡፡ 30 በሸንበቆዎች ውስጥ የሚኖሩትን እንደ ግብፅ ያሉትን እንስሶች እንደ ጉመሬ ያሉትን ገሥጽ፤ ኮርማዎችና ጥጆች የመሳሰሉትን መንግሥታት ገሥጻቸው፤ ሁሉም ተንበርክከው ስጦታቸውን እስከሚሰጡህ ድረስ ገስፃቸው፤ ጦርነት ማድረግ የሚፈልጉትንም መንግሥታት በትናቸው፡፡ 31 ከዚያም የግብጽ መሪዎች ሥጦታቸውን ያመጡልሃል፤ የኢትዮጵያ ሕዝብም አንተን ለማመስገን እጆቻቸውን ለመዘርጋት ይፈጥናሉ፡፡ 32 እናንተ ሕዝብ የዓለም ነገሥታት ሁሉ ለአምላክ ዘምሩ፤ ለእግዚአብሔር የምስጋና መዝሙር አቅርቡ፡፡ 33 ከሰማይ ለሚሄደው ዘምሩ፤ ከብዙ ዘመናት በፊት በፈጠረው ሰማይ፤ በሚያስገመግም ብርቱ ድምፅ ሲናገርም አድምጡት፡፡ 34 እግዚአብሔር ኃይለኛ መሆኑን አውጁ፤ እርሱ እስራኤልን የሚገዛ ንጉሥ ነው፤ በሰማያትም ኃይሉን ያሳያል፡፡ 35 እግዚአብሔር ከቅዱስ መቅደሱ ሲመጣ ድንቅ ነው፤ እርሱ እኛ እስራኤል ልጆች የምናመልከው አምላክ ነው፤ እርሱ ለሕዝቡ ኃይልንና ብርታትን ይሰጣል፡፡ እግዚአብሔር ይመስገን፡፡
Chapter 69
1 እኔ በአደጋ ላይ ስለሆነኩኝ አምላክ ሆይ አድነኝ፤ የውሃ ሙላት እስከ አንገቴ ድረስ ደርሶአልና ልዋጥ ነው፡፡ 2 መቆሚያ ስፍ ስለ አጣሁ በጥልቅ ረግረግ ውስጥ ለመስረግ ተቃርቤአለሁ፤ በጥልቅ ውሃ ውስጥ እገኛለሁ፤ ውሃ ሙላት ሊያሰጥመኝ ተቃርቦአል፡፡ 3 ከመጮኼ ብዛት የተነሣ ደከምኩ፤ ጉሮሮዬም ቆሰለ፤ አምላኬን ለርዳታ በመጠባበቅ ዐይኖቼ ፈዘዙ፡፡ 4 ያለ ምክንያት የሚጠሉኝ ከራሴ ጠጉር ይልቅ በዝተዋል፤ ብዙዎች ጠላቶቼ ሊያጠፉኝ ይፈልጋሉ ያልሰረቅኹትን ነገር እንድመልስላቸው ይጠይቁኛል፡፡ 5 አምላክ ሆይ ሞኝነቴን አንተ ታውቃለህ፤ ኃጢአቴ ከአንተ የተሰወረ አይደለም፡፡ 6 አምላኬ ያህዌ ሆይ፣ አንተ የመላእክት ሠራዊት አዛዥ ነህ፤ በአንተ የሚደገፉ በእኔ ኃጢአት ምክንያት እንዳያፍሩ ያደረግሁትን ኃጢአት ዝም አትበል፤ አምላኬ ሆይ እኛ እስራኤል ልጆች የምናመልክህ እነርሱም እንዲያፍሩብኝ ዝም አትበልኝ፡፡ 7 ወደ አንተ በመቅረቤ ሰዎች ሰደቡኝ፡፡ እነርሱም ሙሉ ለሙሉ ንቀውኛል፡፡ 8 የገዛ ወንድሞቼ እንኳ እንደማያውቁኝ ይሆናሉ፤ በመካከላቸውም ባይተዋር ያደርጉኛል፡፡ 9 አንዳንድ ሰዎች መቅደስህን ያቃልላለ፤ ያንተን መቅደስ ቅድስናውን ስለጠበቅሁ፣ ሰዎች አስጨነቁኝ፤ ስለዚህ አንተን የሰደቡ ሰዎች እኔንም ሰደቡኝ፡፡ 10 በመቅደስህ ላይ አስጻያዊ ነገሮችን ሲያደርጉ አይቼ ማዘኔን ለማሰየት ራሴን ዝቅ በማደርግበትና በምትጾምበት ጊዜ በጣም አለቀስኩ፤ በዚያም ተሰደቡኩ፡፡ 11 ኀዘን ለመግለጽ የኀዘን ልብስ ስለብስ እየተዘባበቱ ይስቁብኛል፡፡ 12 የከተማው ሽማግሌዎች እንኳ ስለ እኔ መጥፎ ነገሮችን ይናገራሉ፡፡ የከተማውም ሰካራሞች ስለ እኔ አስጻያፊ መዝሙር ይዘምራሉ፡፡ 13 ነገር ግን ያህዌ ሆይ፣ እኔ ግን ወደ አንተ እጸልለሁ፤ ተስፋ በሰጠኻኝ መሠረት በእውነት ስለምትወደኝ አንተ በመረጥከው ጊዜ ጸሎቴን መልስ፣ አድነኝም፡፡ 14 በረግረግ ውስጥ ከመስረግ አድነኝ፣ ከጠሉኝም ጠብቀኝ፤ ከጥልቅ ውሃም ከመስጠም አድነኝ፤ 15 ጎርፍ እንዳይወስደኝ፣ ጥልቅ ባሕር እንዳያሰጥመኝም፣ መቃብር እንዳይውጠኝ ጠብቀኝ፡፡ 16 ያህዌ ሆይ፣ አንተ መልካምና በእውነት ስለምትወደኝ ጸሎቴን ስማ፤ እርዳኝም፡፡ 17 ራስህን ከእኔ አትሰውር፤ በካባድ ጭንቀት ላይ ስለ ሆንኩ ፈጥነህ ስማኝ፡፡ 18 ወደ እኔ ቅረብና አድነኝ፤ከጠላቶቼም አድነኝ፡፡ 19 ምን ያህል እንደተሰደብኩ፤ እንደተዋረድኩና ክብሬን ሰዎች እንደቀነሱ አንተ ታውቃለህ፤ ጠላቶቸም እነማን እንደሆኑ ታውቃለህ፡፡ 20 ስድባቸው ክፉኛ ሰብሮኛል፤ ረዳት እንደሌለኝ ይሰመኛል፡፡የሚያስተዛዝነኝ ሰው ፈለግሁ፣ ግን ማንም አልተገኘም፡፡ የሚያጽናናኝ ሰው ፈለግሁ፤ ግን ማንም አልተገኘም፡፡ 21 በዚህ ፈንታ፣ መርዝ የመሰለ ምግቤ ሰጡኝ፤ በጠማኝም ጊዜ ሆምጣጤ ወይን ሰጡኝ፡፡ 22 የራሳቸው ምግብ እንደሚገድላቸው ተስፋ አደርጋለሁ፤ ይህም የሚሆነው ፈጽሞ የተረጋጊ ሲመስላቸው እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ 23 ምንም እንዳያዩ ዐይናቸው ይጨልማል፤ ወገባቸውም ደካማ ይሆናል፡፡ 24 በጣም እንደተቆጠሃቸው አሳይያቸው፤ ከታላቅ ቁጣህ የተነሣ ገፍተህ አወጣቸው፤ አጥምደህም ያዛቸው፡፡ 25 መኖሪያቸው ወና እንዲሆን አድርግ፤ በድንኳናታቸውም ውስጥ አንድም ሰው አይኑር፡፡ 26 አንተ የቀጣሃቸውን ሰዎች ስለሚያሳድዱ ይህን አድርግባቸው፤ አንተ የቀጣሃቸው ሰዎች እንዴት እንደሚሠቃዩ ያያሉ፤ ለሌሎችም ያሳያሉ፡፡ 27 በበደላቸው ላይ በደልን ጨምርባቸው፤ ስላደረጉአቸው ክፉ ነገሮች ይቅርታም አታድርግላቸው፡፡ 28 ስሞቻቸው ከሕያዋን መዝገብ ደምስስ፤ ከጻድቃን ሰዎችም ጋር አይቆጠሩ፡፡ 29 እኔ ግን በሥቃይና ተስፋ በመቁረጥ ላይ ስለምገኝ አምላክ ሆይ፣ ጠብቀኝ፤ አድነኝም፡፡ 30 እግዚአብሔርን በመዝሙር አመሰግነዋለሁ፤ በምስጋናም መዝሙር ታላቅነቱን እገልጣለሁ፡፡ 31 ይህም የተሟላ ዕድገት ያለው ኮርማ ወይም ወይፈን ከመሠዋት ይልቅ ያህዌን የበለጠ ያስደስተዋል፡፡ 32 የተጨቆኑ ሰዎች እግዚአብሐር ሲታደገም ያያሉ፤ ደስም ይላቸዋል፡፡ ሁላችሁም እግዚአብሔር እንዲረዳቸው የምትጸልዩ ደስ እንድላችሁ እፈልጋለሁ፡፡ 33 ያህዌ የችግረኞችን ጩኸት ይሰማል፤ በእስር ቤት ያትን ወገኖቹንም ችላ አይላቸውም፡፡ 34 እያንዳንዱ ፍጥረት እግዚአብሔርን ያመሰግናል፤ በሰማይና በምድር፣ ባሕሮችና በውስታቸው የሚኖሩ ተንቀሳቃሽ ፍጥረቶችም ሁሉ እግዚአብሔርን ያመሰግናሉ፡፡ 35 እግዚአብሔር የኢሩሳሌምን ሕዝብ ከጠላቶቻቸው ይታደጋቸዋል፤ የይሁዳንም ከተሞች ያድሳል፤ ሕዝቡም በዚያ ይኖራሉ፤ ምድሪቱንም የራሳቸው ያደርጋሉ፡፡ 36 የእርሱም ትውልድ ይወርሱአታል፤ እርሱን የሚወዱ ሁሉ እዚያ ይኖራሉ፡፡
Chapter 70
1 እግዚአብሔር ሆይ፣ እባክህ አድነኝ፣ ያሕዌ ፈጥነህ ናና እርዳኝ! 2 በእኔ መከራ ደስ የሚላቸውን አዋርዳቸው፣ እኔን ለመግደል ጥረት የሚያደርጉትን አሳድዳቸው፣ የሁሉ ማፈሪያ አድርጋቸው፣ እኔ ስሰቃይ ማየትን ወድደዋልና። 3 በእኔ መከራ ተደስተዋልና እንዲጨነቁና እንዲያፍሩ እንደምታደርጋቸው ተስፋ አደርጋለሁ። 4 ወደ አንተ የሚጸልዩ ሁሉ በአንተ ደስ እንደሚላቸው አምናለሁ፣ አንተ እንድትታደጋቸው የሚጠባበቁ ሁሉ "እግዚአብሔር ታላቅ ነው!" ይላሉ። 5 እኔ ችግረኛና ምስኪን ነኝ፣ ስለዚህ እግዚአብሔር ሆይ ወደ እኔ ፈጥነህ ናና እርዳኝ! የምታድነኛን የምትረዳኝ አንተ ነህና፣ ስለዚህ ፈጥነህ ድረስልኝ!
Chapter 71
1 ያህዌ ሆይ፣ እንድትጠብቀኝ ወደ አንተ መጥቻለሁ፤ ከቶ አታሳፍረኝ፤ 2 ሁልጊዜም ትክክል ስለምታደርግ፣ እርዳኝ፣ አድነኝም፤ አድምጠኝ፤ አድነኝም፡፡ 3 ልድንበት እንድችል ዓለቴ ሁነኝ፤ መጠጊያዬ እንዲሆነኝ እንደረጅም ቅጥር ሁነኝ፡፡ ያለቋረጥም እኔን እንዲያድኑኝ መላእክትህን እዘዝ፡፡ 4 አምላኬ ሆይ፣ ከክፉ ሰዎች አድነኝ፤ ርኅራኄ ከሌላቸውና ከዐመፀኞች እጅ አድኘኝ፡፡ 5 ያህዌ አምላኬ ሆይ፣ እንድትረዳኝ ተስፋ የማደርግህ አንተን ነው፤ ከልጅነቴ ጀምሮ መታመኛዬ አንተ ነህ፡፡ 6 በሕይወቴ ዘመን ሁሉ በአንተ ላይ ተደግፌያለሁ፤ ከእናቴ ማኅፀን ጀምሮ የጠበቅኸኝ አንተ ነህ፤ ስለዚህም ዘወትር አመሰግንሃለሁ፡፡ 7 አንተ ብርቱ ተከላካይ ስለ ሆንክልኝ ሰዎች አይተውህ ሕይወቴ ለብዙዎች ምሳሌ ሆኖአል፡፡ 8 ቀኑን ሙሉ አንተን አመሰግንሃለሁ፤ የተከበርህ መሆንህን ዐውጃለሁ፡፡ 9 አሁን በእርጅናዬ ዘመን አትጣለኝ፤ ደካማ በምሆንበትም ጊዜም አትተወኝ፡፡ 10 ጠላቶቼ እኔን ለመግደል ይመክራሉ፤ ይህንንም እንዴት እንደሚያደርጉ ይነጋገራሉ ዕቅድም ያወጣሉ፡፡ 11 እግዚአብሔር ትቶታል ተከታትለን እንያዘው የሚያድነው ማንም የለም ይላሉ፡፡ 12 አምላክ ሆይ፣ ከእኔ አትራቅ፤ አምላክ ሆይ፣ ፈጥነህ እርዳኝ፡፡ 13 እኔን የሚከሱኝ ተቃዋሚዎቼ ይሸነፉ፤ ይጥፉም፤ ሊጎዱኝ ሚፈልጉ ይናቁ፤ ይዋረዱም፡፤ 14 እኔ ግን ዘወትር አንተን ተስፋ አደርጋለሁ፤ በበለጠም መላልሼ አመሰግንሃለሁ፡፡ 15 ምንም እንኳ እኔ መረዳት ከምችለው በላይ ቢሆንም፣ አንተ ትክክለኛ ነገር እንዳደረግህ ለሰዎች ሁሉ እናግራቸዋለሁ፤ በየቀኑም እንዴት እንዳደንሃኝ ለሰዎች ሁሉ ይናገራለሁ፡፡ 16 ያህዌ አምላኬ ሆይ፣ ስለ ኃያል ሥራዎችህን አመሰግንሃለሁ፤ እውነተኛ ፍርድ መሰጠት የምትችል የአንተ ብቻ መሆኑን ዐውጃለሁ፡፡ 17 አምላክ ሆይ፣ አንተ ከልጅነቴ ጀምረህ አስተማርከኛ፤ ገና አሁንም ድንቅ ሥራህን ለሰዎች እናገራለሁ፡፡ 18 አምላክ ሆይ፣ አርጅቼ እስክሸብት ድረስ አትተወኝ፤ ሥራህን ለሚመጣው ትውልድ፣ ኃይለህንም እስከ ትውልድ ድረስ ከእኔ ጋር ሁን፡፡ 19 እምላክ ሆይ፣ ብዙ ጽድቅህን ታደርጋለህ፤ ስፋቱም እስከ ሰማይ ደርሳል፤ ታላላቅ ነገሮችን አድረገሃል፡፡ አንተን የሚመስል ማንም የለም፡፡ 20 በብዙ ችግርና መከራ እንድሠቃይ አድገኸኛል፤ ሆኖም እንደገና ከሞት አስወጥተህ አዲስ ሕይወትን ትሰጠኛለህ፡፡ 21 ታላቅ ክብር ታመጣልኛለህ፤ እንደገናም ታጽናናኛለህ፡፡ 22 አምላኬ የእስራኤል ቅዱስ ሆይ፣ ስለ ታማኝነትህ በበገና አመሰግንሃለሁ፤ በመሰንቆም የምስጋና መዝሙር አቀርብልሃለሁ፡፡ 23 ድምፄን ከፍ አድርጌ በደስታ እዘምራለሁ፤ ስላዳነኸኝ በሙሉ ኃይሌ የምስጋና መዝሙር እዘምርልሃለሁ፡፡ 24 ያደረግሃውን ጽድቅ ቀኑን ሙሉ ለሰዎች ሁሉ እናገራለሁ፡፡ሊጎዱኝ የሚፈልጉ ሁሉ ይሸነፋሉ፤ ያፍራሉም፡፡
Chapter 72
1 አምላክ ሆይ፣ እስራኤል ላይ የሾምኸው ንጉሥ በጽድቅ እንዲፈርድ አብቃው፡፡ በፍትሕ እንዴት እንደሚፈርድ አሳየው፡፡ 2 በሕዝብህ ላይ በፍትሕ መፍረድ እንዲችል፤ የረጨቆኑትን ሕዝብህን በትከክል እንዲያስተዳድር አሳየው፡፡ 3 አገሪቱ ሁሉ በተራራዎችና በኮረብታዎች እንኳ ሕዝቡ በሰላምና በጽድቅ ይኖራል፡፡ 4 ለድኾች እንዲፈርድ ንጉሥህን እርዳው፤ እርዳታ የሚያስፈልጋቸውን እንዲያድንና የጨቆኑአቸውን እንዲያሸንፍ እርዳው፡፡ 5 ንጉሥህ በዘመናት ሁሉ የፀሐይና የጨረቃን ያህል ረጅም ዘመናት እያበራ ለዘለዓለም እንዲኖር እፈልጋለሁ፡፡ 6 ንጉሡ መስክ ላይ በሚዘንብ ዝናብ እንደሚያድግ ሰብል፣ በምድርም ላይ እንደሚወርድ ጠል በእርሱ አመራር ሕዝቡ ደስ እንዲሰኙ እፈልጋለሁ፡፡ 7 በእርሱ የግዛት ዘመን እንደሚኖሩ፤ እንደ ጨረቃ በሰላምና በብልጽግና ሕዝቡ እንደሚኖር ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ 8 የእስራኤል ንጉሥ ግዛቱ ከምሥራቅ እስከ ምዕራብ፣ ከኤፍጥስ ወንዝ እስከ ምድር ዳርቻ ይድረስ ይሆናል፡፡ 9 በበረሃ የሚኖሩ በፊቱ ይስግዳሉ፤ ጠላቶቹም ወደ መሬት ወድቀው ለንጉሣችን እጃቸውን ለመስጠት ይሰግዳሉ፡፡ 10 የተርሴስ ደሴቶች ነገሥታት ስጦታ ያቅርባሉ፤ የሳባና የዐረብ ነገሥታት እጅ መንሻ ያመጡለታሉ፡፡ 11 የዓለም ነገሥታት ሁሉ ለእስራኤል ንጉሥ ይሰግዱለታል፤ ሕዝቦችም ሁሉ ንጉሣችንን ያገልግሉታል፡፡ 12 ለእርዳታ ወደ እርሱ የሚጮኹትን ድኾች ያድናቸዋል፤የሚረዳቸው የሌላቸውን ችግረኞችንና የተጨቆኑትን ሰዎች ይረዳቸዋል፡፡ 13 ለደኾችና ለደካሞች ይራራል፤ በችግር ላይ ያትንም ሰዎች ከሞት ያድናል፡፡ 14 ንጉሣችን ከጭቆናና ከጭካኔ አገዛዝ ያድናቸዋል፤ ለንጉሣችን የእነርሱ ሕይወት ውድ ስለ ሆነ ነው፡፡ 15 ንጉሡ ረጅም ዘመን ይኖራል፤ ከሳባም ወርቅ ይመጣለታል፤ ስለ እርሱም ዘወትር ጸሎት ይደረጋል፤ሰዎችም ሁልጊዜ በየቀኑ ያመሰግኑታል፡፡ 16 በሊባኖስ ተራራ እንደሚበቅል ሰብል በምድሩቱ ተራራዎች ራስ ሳይቀር በሁሉም መስኮች ብዙ ሰብሎችን ያፈራሉ፤ መስኮች በሣር እንደሚሸፈን የእስራኤል ከተሞች በሕዝብ ይሞላሉ፡፡ 17 የንጉሡም ስም ለዘለዓለሙ ሲታወስ ይኑኖራል፤ ሕዝቡም ፀሐይ እያበራ እንደሚኖር ለዘመን ሁሉ ለዘለዓለም ይኖራል፡፡ ልክ የእስራኤልን ንጉሥ ስለባረከው፣ ሕዝብ ሁሉ የእስራኤልን አምላክ፣ ያህዌን ያመሰግናሉ፡፡ 18 እኛ እስራኤላውያን የምናመልከው፣ ያህዌ ይመስገን፤ እርሱ ብቻ ተአምትን የሚያደርገው፡፡ 19 እርሱ ለዘለዓለም ይመስገን፤ የእርሱ ዓለምን ሁሉ ይሞላል፡፡ አሜን! እንዲሁም ይሁን! 20 ይህ የእሴይ ልጅ የዳዊት ጸሎት ፍጻሜ ነው፡፡
Chapter 73
1 እግዚአብሔር ለእኛ ለእስራኤላውያን መልካም ነው፡፡ እግዚአብሔር የሚፈልገውን ሁሉ ለማድረግ ለሚፈልገው ለንጽሓን 2 እኔ በእግዚአብሔር መታመንን በአብዘኛው አቁሜአለሁ፤ ይህም በእርሱ ላይ ታላቅ ኃጢአት መፈጸሜ ነው፡፡ 3 ይህም የሆነው ሰዎች በልበ ሙሉነት እግዚአብሔር አያስፈልግም ሲሉ ሰምቻለሁ፤ እኔም እንደእነርሱ ለመሆን ፈለጌአለሁ፡፡ ክፉዎችና ኃጢአተኞች ሆኖ ሳሉ በልጽገው አይቻለሁ፡፡ 4 እነርሱም ምንም ሕመም ስለሌለባቸው፣ ሰውነታቸው ጠንካራና ጤናማ ነው፡፡ 5 እንደ ሌሎች ሰዎች አይጨነቁም፤ በሌሎች ለይ የሚደርሰው ሥቃይ በእነርሱ ላይ አይደርስም፡፡ 6 ስለዚህ በአንገቷ ላይ ያለው ጌጥ ለሌሎችም እያሳየች እንደምትኩራራ እነርሱም በዚህ ኮርተዋል፡፡ ሌሎች ሰዎች ቆንጆ ልብሳቸውን እንዲያዩ ሲያደርጉ፤ ምን ያህል ጨካኞች እንደሆነ ለማሳየት ነው፡፡ 7 ከውስጣቸውም ክፉ ሥራቸውን ያፈሳሉ፤ በውስጣቸውም ሁልጊዜ ተጨማሪ ክፉ ተግባራቸውን ለማድረግ ያስባሉ፡፡ 8 በሌሎች ሰዎች ላይ እያፌዙ የተንኮል ንግግርን ይናገራሉ፤ ሌሎችን ሰዎችን ለመጨቆን ሲያቅዱ በትዕቢት ይናገራሉ። 9 ስለ ክፉ ሥራ በሰማይ በሚኖር በእግዚአብሔር ላይ ይናገራሉ፤ በዚህም ምድር ስላደረጉአቸው ነገሮች በጉራ ይናገራሉ፡፡ 10 ሰዎች እነርሱ የሚናገሩት ትኩረት ሰጥተው የሰማሉ፤ የሚነግሩአቸወንም ሁሉ ይሰማሉ፡፡ 11 ክፉ ሰዎች ለራሳቸው የሠራነውን ሁሉ እግዚአብሔር አያውቅም ይላሉ፤ ሰዎች እርሱ ከሌሎች አማልክት ይበልጣል ይላሉ ግን እርሱ አይደለም፡፡ 12 እንግዲህ ክፉዎች እንደዚህ ናቸው፤ ስለማንኛም ነገሮች ግድ የላቸውም፤ ዘወትርም ተጨማሪ ሀብት ያገኘሉ፡፡ 13 ስለዚህ አምላክ ሆይ፣ አንተ የምተፈልገውን ማድረጌ ጥቅም እንደሌለ አስባለሁ፤ ኃጢአትንም አላደረግሁም፡፡ 14 ቀኑን ሙሉ ተሠቃየሁ፤ በየማለዳውም ትቀጠኛለህ፡፡ 15 ነገር ግን በሌሎች ፊት እነዚህን ነገሮች ከፍ አክርጌ ተናግሬ ቢሆን በሕዝብህ ላይ ኃጢአት ማድረጌ ነበር፡፡ 16 እነዚህን ነገሮች በፍጹምነት ለማሰብ ቢሞክር፤ ለመረዳት በጣም አስቸጋሪ ሆኖ አገኘሁት፡፡ 17 ነገር ግን ወደ መቅደስህ ሲገባ አንተ ትናገራኛለህ፤ ክፉ ሰዎች ከሞቱ በኋላ ምን እንደሚሆኑ ተረድቻለሁ፡፡ 18 እንግዲህ ወድቀው በሚኖቱበት በአደገኛ ቦታዎች ላይ በእርግጥ እነርሱን እንዳስቀመጥኻቸው አውቃለሁ፡፡ 19 በቅጽበት ይደመሰሳሉ፤ በአስደንጋጭ መንገድ ይሞታሉ፡፡ 20 ሰው ከነቃ በኋላ እንደሚጠፋ ቅዠት በፍጥነት ይጠፋሉ፤ እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ስትነሣ እነርሱን ታጠፋቸዋለህ፡፡ 21 በውስጤ ኀዘን ስሰማኝ፤ ስሜቴ ተጎዳ፡፡ 22 ጌታ ሆይ፣ የማልረባና ቸልተኛ ነኝ፤ በአንተ ዘንድ ከእንስሶች የማልሻል ሆኜዋለሁ፡፡ 23 ነገር ግን ዘወትር ወደ አንተ እቀርባለሁ፤ አንተም ቀኝ እጄን ትይዛህ፡፡ 24 እያስተማርከኝ ትመረኛለህ፤ በሕይወቴ መጨረሻም ትቀበለኛለህ፣ ታለብረማኛለሀም፡፡ 25 አንተ በሰማይ ነሀ፣ እኔም የአንተ ነኝ፤ በምድር ከዚህ የበለጠ የምፈልገው ነገር የለኝም፡፡ 26 አካሌና አእምሮዬ ሊደክሙ ይችላሉ፤ ግን እግዚአብሔር ሆይ፣ ሁልጊዜ ጠንካራ እንድሆን አድርገኝ፡፡ ለዘለዓለም የአንተ ነኝ፡፡ 27 እነሆ፣ ከአንተ የሚርቁ ይጠፋሉ፤ አንተን የሚክዱህን ሁሉ ትደመስሳዋለህ፡፡ 28 ለእኔ ግነ ወደ እግዚአብሔር መቅረቤ መልካም ነው፤ የአንተን ሥራ ሁሉ ለማብሠር እንድችል አንተን ያህዌን መጠጊያዬ አድረጌአለሁ፡፡
Chapter 74
1 እግዚአብሔር ሆይ ስለምን ተውከን? ለዘላለም ትጥለናለህን? አንተ የእኛ እረኝ እኛም የአንተ የማሰማሪያህ በጎች ሆነን እያለን ስለ ምን በእኛ ላይ ትቆጣለህ? 2 የመረጥከውን ሕዝብህን አትርሳ፣ በግብፅ ምድር ባሪያ ከምሆን ነፃ ያወጣኸውን ሕዝብህን አትርሳ፣ ከቀድሞ ጀምሮ የአንተ ጎሳ ነውና። ኢየሩሳሌምን አትርሳ በዚህ ምድር የአንተ ቤት ናትና። 3 ሁሉም ነገር እንደተበላሸ፣ በተቀደሰው መቅደስ ውስጥጠላቶቻችን ሁሉን ነገር እንዳጠፉ ተመልከት። 4 በተቀደሰው ሥፍራ ጠላቶችህ በድል አድራጊነት ይጮሃሉ፣ እንዳሸንፉን ለማሳየት ምልክታቸውን ተከሉ። 5 በቤተ መቅደስ ውስጥ የነበሩትን የተቀረጹትን እቃዎች እንጨት ቆራጭ ዛፎችን እንደሚቆርጥ ሰባበሩአቸው። 6 የተቀረጹ እንጨቶችን ሁሉ በመጥረቢያቸውና በመዶሻቸው አድቀቁአቸው። 7 መቅደስህን በእሳት አቃጠሉ፣ አንተ የምትመለክበትን ስፍራ፣ ልአምልኮ የማይመች አድርገው አበላሹት። 8 ለራሳቸው እንዲህ አሉ፣ "እስራኤላውያንን ፈጽመን እናጠፋቸዋለን" አንተን ለማምለክ የምሰበሰብባቸውን ሌሎች ሥፍራዎችን ሁሉ አቃጠሉ። 9 የተቀደሱት ምልክቶችን ሁሉ ጠፉ፣ አሁን ነቢያቶች የሉም፣ ይህ ሁኔታ እስከ መቼ ድረስ እንድሚቀጥል የሚያውቅ የለም። 10 እግዚአብሔር ሆይ ጠላቶቻችን እስከ መቼ ድረስ በእኛ ይቀልዳሉ? አንተንስ እስከ መቼ ያቃልላሉ? 11 ስለምን እኛን መርዳት እምቢ አልህ? ጠላቶችን ከማጥፋት ይልቅ ስለምን እጅህን ሰበሰብክ? 12 እግዚአብሔር ሆይ፣ ከግብፅ ከወጣንበት ጊዜ ጀምሮ ላለፉት አያሌ ዓመታት አንተ ንጉሣችን ነህ፣ ጠላቶቻችንን በእስራኤል ምድር ድል እንድናደርጋቸው አስችለኸናል። 13 በኃይልህ ባሕሩን ከፈልህ፣ እንደ ታላቅ የባሕር ዘንዶ የመሰሉትን የግብፅ ገዢዎች ራሳቸውን ቀጠቀጥክ። 14 የግብፅን ንጉሥ ራስ ቀጠቀጥክ፣ አካሉንም በምድረ በዳ ለሚኖሩ አራዊት ምግብ እንዲሆናቸው ሰጠሃቸው። 15 ምንጮችንና ፈሳሾችን እንዲፈስሱ አደረግህ፣ ደርቀው የማያውቁትን ወንዞች አደረቅህ። 16 ቀኖችንና ሌሊቶችን ፈጠርክ፣ ፀሐይንና ጨረቃን በስፍራቸው አስቀመጥህ። 17 ለውቅያኖሶች ገደብ አደረግህላቸው ምድርን የሚጀምርበትን ወሰንክ፣ ክረምትንና በጋን ፈጠርክ። 18 ያሕዌ፣ ጠላቶችህ በአንተ እንደሚስቁ አትርሳ፣ አንተን የሚንቁ ሞኞች ናቸው። 19 ረዳት አልባ የሆኑትን ሕዝቦችህን ጨካኞች በሆኑት ጠላቶቻቸው እጅ አሳልፈህ አትስጣቸው፣ መክራ ያዩትን ሕዝቦችህን አትርሳ። 20 ከእኛ ጋር የገባኸውን ቃል ኪዳንህን አስብ፣ በምድር ጨለማ በሆኑ ስፍራዎች አመፀኞች አሉ። 21 የተጨቆኑት ሕዝብህ እንዲቃለሉ አትፍቀድ፣ መልሰው እንዲያመሰግኑን ድሆችንና ምስኪኖችን እርዳቸው። 22 እግዚአብሔር ሆይ፣ ተነሥ ሕዝብህን አድን! ሞኞች ሰዎች ቀኑን ሙሉ በአንተ እንደሚያላግጡ አትርሳ! 23 ሞኞች ሰዎች በአንተ እንደሚበሳጩ አትርሳ! አንተን በመቃወም ጩኸታቸውን አያቆሙም።
Chapter 75
1 አምላካችን፣ ምስጋናን ለአንተ እንሰጣለን፣ እናመሰግንሃለን፣ አንተ ለእኛ አምላካችን፣ ምስጋናን ለአንተ እንሰጣለን፣ እናመሰግንሃለን፣ አንተ ለእኛ ቅርብ ነህ፣ ለእኛ ያደረግህልንን ድንቅ ነገሮች ለሌሎች እንነግራለን። 2 አንተ እንዲህ ብለሃል፣ "በሰዎች ላይ የምፈርድበትን ጊዜ ወስኜአለሁ፣ ለእያንዳንዱ በጽድቅ እፈርዳለሁ። 3 ምድር ብትንቀጠቀጥ፣ በምድር ላይ ያሉ ፍጥረታ ቢንቀጠቀጡ፣ መሠረቷን የማጸና እኔ ነኝ። 4 ለሚታበዩ ሰዎች እንዲህ እላለሁ፣ "መበደላችሁን አቁሙ"፣ ለኃጢአተኞችም እንዲህ እላለሁ "ታላቅነታችሁን ለማሳየት በኩራት አትታበዩ!" 5 እጅግ አትታበዩ፣ በኩራትም አትናገሩ! 6 በሰዎች ላይ የሚፈርደው ከምሥራቅ ወይም ከምዕራብ አይመጣም፣ ከምድረ በዳም አይመጣም። 7 በስዎች ላያ የሚፈርደው እግዚአብሔር ነው፣ አንዳንዶችን ያዋርዳል፣ ሌሎችንም ያከብራል። 8 ይህም ያሕዌ ጽዋውን በእጁ እንደ ያዘ ይመስላል፣ በውስጡ ወይንና ቅመም ተቀላቅሎበታል የሚጠጡትም እጅግ ይሰክራሉ፣ ያሕዌ ወይኑን ሲያፍሰው፣ ኃጢአተኞች ሁሉ እንዲጠጡት ያስገድዳቸዋል። እያንዳንዷ ጠብታ ይጠጡታል፣ አዎ ሁሉንም በከፍተኛ ሁኔታ ይቀጣቸዋል። 9 ለእኔ ግን፣ ያዕቆብ ያመለከው እግዚአብሔር ያደረገውን ከመናገር እ አላቆምም፣ እርሱን ለማመስገን መዘመሬን አላቆምም። 10 እርሱ እንዲህ ብሎ ቃል ገብቶአል፦ "የኃጢአተኞችን ኃይል አጠፋለሁ፣ ነገር ግን የቅዱሳንን ኃይል አበዛለሁ።"
Chapter 76
1 እግዚአብሔር እንዲያውቁ ሕዝብን በይሁዳ አደረገ፤ የእስራኤል ሕዝብ እርሱን ያከብራሉ፡፡ 2 በኢየሩሳሌም የእርሱ ቅዱስ ድንኳን አለ፤ እርሱም በጽዮን ተራራ ይኖራል፡፡ 3 በዚያም ጠላቶቹ የተኮሱትን የሚያጸባርቁ ፍላጻዎችን ሰበረ፤ በጦርነቱ የተጠቀሙበትን ጋሻና ሰይፍን፣ ሌሎችንም የጦር መሣሪያዎች ሁሉ ሰባበረ፡፡ 4 አምላክ ሆይ፣ አንተ የተከበርክ ነህ፤ ጠላቶችን አሸንፈህ ከተራራዎች ስትመለስ እንደ ንጉሥ ነህ፡፡ 5 ጀግኖች ወታደሮች ሞቱ፤ ከዚያ የገደሉአቸው ወታደሮቹ ያላቸውን ሁሉ ወሰዱባቸው፤ የሞቱ ጠላቶች ምንም ያህል መዋጋት አልቻሉም፡፡ 6 የያዕቆብ አምላክ ሆይ፣ ጠላቶችህን አንተ በገሠጽካቸው ጊዜ ፈረሰኞች ከነፈረሶቻቸው ሞቱ፡፡ 7 በርግጥ ሁሉም እንዲፈሩ አድርገሃል፡፡ አንተ ስተቆጣና ስትቀጣ በፊትህ የሚቆም አንድ እንኳ እይኖርም፤ 8 በሕዝብ ላይ እንደምትፈር ከሰማይ ዐወጅህ፤ በምድርም ያሉት ማንም ፈራ፤ ምንም መናገር አልቻሉም፡፡ 9 አንተ በምድር የተጨቆኑትን ሁሉ ለመቤዠት ክፉ ሰዎችን ለመቅጣት በተነሣህ ጊዜ ሁሉም ጸጥ አለ፡፡ 10 የተቆጣሃቸውን በምትቀጣበት ጊዜ አንተን ያመስግንሃል፤ ከጦርነት የተረፉትም በዓልህን ያከብራሉ፡፡ 11 የተሳላችሁትን ለያህዌ መስዋዕት በማቅረብ ፈጽሙ፤ እናንተ በቅርብ ያችሁ ሕዝቦች ኁሉ መባ አምጡለት፡፡ 12 ትዕቢተኞች የሆኑትን መሳፍንት ያዋርዳል፤ ታላላቅ ነገሥታትንም ያስፈራራል፡፡
Chapter 77
1 ወደ እግዚአብሔር እጮኻለሁ፤ ድምፄን ከፍ አድርጌ እጮኻለሁ፤ እርሱም ይሰማኛል፡፡ 2 በተጨነቅሁ ጊዜ ወደ እግዚአብሔር ጮኽ፤ ስጸልይም ሌሊቱን በሙሉ እጆቼን ወደ ላይ አነሠሁ፤ ነገር ግን ምንም አልተመቸኝም፡፡ 3 ስለ እግዚአብሔር በማስብበት ጊዜ እሸበራለሁ፤ በጥሞና ሳሰላስል መንፈሴ ተስፋ እቆርጣለሁ፡፡ 4 ሌሊቱን ሙሉ እንዳልተኛ አደረገኝ፤ ጭንቀቴም ስለ በዛ መናገር አልቻልኩም፡፡ 5 ስላለፉት ቀኖች አስባለሁ፤ ጥንት ስለ ነበሩት ዓመቶችም አስታውሳለሁ፡፡ 6 ሌሊቱን ሙሉ የማነጋው በጥልቅ አሳብ ነበር፤ ሳለላስል ሳለሁ ራሴን የምጠይቀው እንዲህ እያልኩ ነበር፤ 7 እግዚአብሔር ለዘወትር ይጥለኛልን? ከእንግዲህስ ወዲህ ለእኔ ደስ አልተሰኘምን? 8 እኛን በእውነት መውደዱን ፈጽሞ ትቶአልን? ተስፋ የሰጠውን ከእንግዲህ ወዲህ አያደርግልንምን? 9 እግዚአብሔር በምሕረቱ ለማድረግ የሰጠውን ተስፋ ረስቶአልን? ስለ ተቆጣኝ ርኅራኄውን አያደርግልኝምን? 10 ልዑል እግዚአብሔር ሆይ፣ እኔን ያስጨነቀኝ በታላቁ ኃይልህ እኛን ከመርዳት ማቆምህ ነው አልኩ፡፡ 11 ነገር ግን ያህዌ ሆይ፣ ያከናወንካቸውን ታላላቅ ሥራዎች አስታውሳለሁ፤ ባለፉት ዘመናት ያደረግቸው ተአምራት አስታውሳለሁ፡፡ 12 ሥራውችህን በጥሞና አሰላስላለሁ፤ ታላላቅ ሥራዎችህንም አስባለሁ፡፡ 13 አምላክ ሆይ፣ አንተ ያደርግሃው ሁሉ አስደናቂ ነው፤ እንደ አንተ ያለ ታላቅ አምላክ የለም፡፡ 14 ተአምራትን የምታደርግ አምላክ አንተ ነህ፤ አንተ በሕዝቦች መካከል ኃይልህን አሳይተሃል፡፡ 15 በኃይልህም ሕዝብህን ከግብፅ ታድገሃል፤ በኃይልህ የያዕቆብና የዮሴፍ ልጆች የሆኑትን ሕዝብህን ተቤዥተሃል፡፡ 16 አምላክ ሆይ፣ ውሃው አንተን ባየ ጊዜ ፈራ፤ ጥልቅ ባሕሮችም ተንቀጠቀጡ፡፡ 17 ከደመናዎች ዝናብ ወረደ፤ መብረቅ ከሰማይ አንጎደጎደ፤ የመብረቅ ፍላጻዎችም ከላይ ከሰማይ አንጸባረቁ፡፡ 18 18 የነጎድጓድህ ጩኹት በዐውሎ ነፋስ አስተጋባ፤ የመብረቅ ብልጭታ ዓለምን አበራ፤ ምድር ተናወጠች፣ ተንቀጠቀጠችም፡፡ 19 መንገድህ በባሕር መካከል ነበር፤ ያለፍከውም በታላላቅ ወንዞች በኩል ነበር፤ ነገር ግን የእግርህ ዱካ አልተገኘም፡፡ 20 እረኛ የበጎችን መንጋ እንደሚመራ፣ አንተም በሙሴና በአሮን አማካይነት ሕዝብህን መራህ፡፡
Chapter 78
የአሳፍ መዝሙር 1 ወዳጆቼ፣ የማስተምራችሁን አድምጡ፣ የምናገረውንም አስተውሉ። 2 ጠቢባን የተናገሩትን ጥቂት አባባል ልንገራችሁ። እነርሱ ጥንት ስለ ተፈጸሙ ነገሮች የተነገሩ ናቸው፣እነርሱን መረዳትም አስቸጋሪ ነበር። 3 አስቀድሞ የሰማናቸውና ያወቅናቸው ናቸው፣ወላጆቻችንና አያቶቻችን እነዚህን ነገሮች ነግረውናል። 4 ስለ ያህዌ ኃይልና እርሱ ስላደረጋቸው ድንቅ ነገሮች፣ እነዚህን ነገሮች ለልጆቻችን፣ ለልጅ ልጆቻችንም ደግሞ እንነግራቸዋለን። 5 ሕጉንና ትዕዛዙን ለእስራኤል ሕዝብ፣ የያዕቆብ ዘር ለሆኑ ለእነርሱ ሰጠ፣ ልጆቻቸውን እንዲያስተምሩም አባቶቻችንን አዘዘ፣ 6 ልጆቻቸው ያውቋቸው ዘንድ፣ እነርሱም በተራቸው ልጆቻቸውን ያስተምሯቸው ዘንድ። 7 በዚህ ሁኔታ እነርሱም በእግዚአብሔር እንዲታመኑ፣እርሱ ያደረገውንም እንዳይረሱ፤ ይልቁንም ትዕዛዙን እንዲጠብቁ ነው። 8 እግዚአብሔርን በመታመን እንዳልጸኑት፣እርሱን ብቻ እንዳላመለኩት፣ በእግዚአብሔር ላይ ልበ ደንዳኖችና አመጸኞች እንደ እንደነበሩት፣እንደ አባቶቻቸው እንዳይሆኑ ነው። 9 የኤፍሬም ነገድ ወታደሮች ቀስትና ፍላጻ ነበራቸው፣ከጠላቶቻቸው ጋር በተዋጉበት የጦርነት ቀን ግን ከጠላቶቻቸው ፊት ሸሹ። 10 ከእግዚአብሔር ጋር የገቡትን ኪዳን አልፈጸሙም፣ሕጉን ለመጠበቅም እምቢ አሉ። 11 እርሱ የሠራውን ረሱ፣ ሲፈጽማቸው ያዩአቸውን ተአምራቶቹንም ዘነጉ። 12 አባቶቻችን እያዩ፣ በግብፅ ሀገር በጣኔዎስ ከተማ አካባቢ እግዚአብሔር ተአምራትን አደረገ። 13 ከዚያም ቀይ ባህርን ከፈለ፣ ውሃውን በዚህና በዚያ እንደ ግድግዳ አቆመው፣አባቶቻችንም በደረቁ መሬት ተሻገሩ። 14 ቀኑን በብሩህ ደመና መራቸው፣ሌሊቱን በእሳት ብርሃን። 15 በምድረ በዳ ዐለቶችን ሰነጠቀ፣ ከምድር ጥልቅም ለአባቶቻችን ብዙ ውሃ ሰጣቸው። 16 ከዐለቱ የውሃ ምንጭ እንዲወጣ አደረገ፣ውሃውም እንደ ወንዝ ጎረፈ። 17 አባቶቻችን ግን በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአት መሥራታቸውን ቀጠሉ፣ ከአማልክት ሁሉ በላቀው ላይ በምድረ በዳ አመጹበት። 18 የተመኙትን ምግብ እግዚአብሔር እንዲሰጣቸው በመጠየቅ፣ የሚጠይቁትን ሁሉ መፈጸም ይቻለው እንደሆነ ለማወቅ ፈተኑት። 19 "በዚህ በበረሃ እግዚአብሔር ምግብ ሊሰጠን ይችላልን?" በማለት እግዚአብሔርን ተሳደቡ፣ 20 ዐለቱን መሰንጠቁ እውነት ነው፣ ከዚያም ውሃ መጉረፉ፣ ነገር ግን ለእኛ ለሕዝቡ አሁን እንጀራና ሥጋ ሊሰጠን ይችላል? 21 ያህዌ ይህን በሰማ ጊዜ እጅግ ተቆጣ፣ ከሕዝቡ ከእስራኤል ጥቂቱን እንዲበላ እሳትን ላከ። 22 በእርሱ አልታመኑምና፣ እንደሚያድናቸው አላመኑምና ይህንን አደረገ። 23 እግዚአብሔር ግን ከበላያቸው ላለ ሰማይ ተናገረ፣ እንደ በር እንዲከፈትም አዘዘው። 24 ከዚያም ምግብ እንደ ዝናብ ወረደላቸው፣ "መና" ብለው የጠሩትን ምግብ፣ እንጀራን ከሰማይ ሰጣቸው። 25 ስለዚህ ሕዝቡ መላእክት የሚበሉትን ምግብ በሉ፣ የፈለጉትንም መና ሁሉ እግዚአብሔር ሰጣቸው። 26 ከዚያም የምስራቅ ንፋስ እንዲነፍስ አደረገ፣ በኃይሉም ከደቡብ ደግሞ ንፋስን ላከ፣ 27 በባህር ዳርቻ ያለውን አሸዋ የሚያህሉ፣ ድርጭቶችን ንፋሱ አመጣ። 28 እግዚአብሔር ድርጭቶቹን በሰፈራቸው መካከል አወረደ። በድንኳኖቻቸው ዙሪያ ሁሉ ድርጭቶች ነበሩ። 29 ሕዝቡ ድርጭቶቹን አረዱ፣ እስኪጠግቡም ሥጋ በሉ፣ እግዚአብሔር የፈለጉትን ሰጥቷቸዋልና። 30 የፈለጉትን ሁሉ ግን አለበሉም፣ 31 በዚያን ጊዜም እግዚአብሔር እጅግ ተቆጣቸው፣ኃያሎቻቸውን ገደለ፣ የተመረጡትን በርካታ የእስራኤል ወጣቶች ደመሰሰ። 32 ይህም ሁሉ ሆኖ ሕዝቡ በኃጢአታቸው ቀጠሉ፣እግዚአብሔር ተአምራትን ሁሉ ቢያደርግም፣ አሁንም እርሱ እንደሚያስብላቸው አልታመኑበትም። 33 ስለዚህ ንፋስ እንደሚያልፍ ዘመናቸውን አሳጠረ፣ ድንገት በመታቸው እልቂት ሞቱ። 34 እግዚአብሔር አንዳንድ እስራኤላውያን በገደለ ጊዜ ሁሉ፣ ሌሎቹ ንሰሐ ገቡ፣ አዘኑና እግዚአብሔር እንዲያድናቸው አጥብቀው ጠየቁት። 35 እንደ ጽኑ ዐለት የከለላቸው እግዚአብሔር እንደሆነ አሰቡ፣ የጠበቃቸውም ከአማልክት ሁሉ የላቀው እርሱ መሆኑን። 36 እግዚአብሔርን በአንደበታቸው ሊያታልሉት ሞከሩ፣ ቃላቸው ሁሉ ውሸት ነበር። 37 ለእርሱ ታማኞች አልነበሩም፤ ከእነርሱ ጋር የገባውን ኪዳን ቸል አሉ። 38 እግዚአብሔር ግን ለሕዝቡ ራራ፣ ኃጢአታቸውን ይቅር አለ፣ አላጠፋቸውምም። ብዙ ጊዜ ከቁጣው ተመለሰ፣ መዓቱንም ከማፍሰስ ራሱን ዐቀበ። 39 የሚሞት ሰው ብቻ መሆናቸውን አሰበ፣ ሰዎች በንኖ እንደሚጠፋ ንፋስ መሆናቸውን። 40 በምድረ በዳ አባቶቻችን በእግዚአብሔር ላይ ብዙ ጊዜ አመጹ፣ እጅግም አሳዘኑት። 41 እነዚያን ነገሮች ሲያደርጉ እግዚአብሔር አይቀጣቸው እንደሆነ ለማየት ብዙ ጊዜ ክፉ ነገሮችን አደረጉ። በተደጋጋሚ ቅዱሱን የእስራኤል አምላክ አስቆጡት። 42 ከጠላቶቻቸው ያዳነበትን ጊዜ ረሱ፣ እንዲሁም ታላቅ ኃይሉን ዘነጉ። 43 ተኣምራት ያደረገባቸውን ጊዜያት ረሱ፣ በግብፅ ምድር በጣኔዎስ ከተማ አቅራቢያ። 44 የአባይን ወንዝ እንደ ደም አቀላው፣ የግብፅ ሰዎችም የሚጠጡትን ውሃ አላገኙም። 45 በግብፅ ሰዎች ላይ ተናካሽ የዝንብ መንጋ ላከባቸው፣ ጓጉንቸሮችን ላከ ሁሉንም በሉባቸው። 46 ሰብሎቻቸውን እንዲበሉ አንበጣን ላከ፣ በእርሻዎቻቸው የበቀሉትን ሌሎቹንም ነገሮች። 47 ወይናቸውን የሚያጠፋ በረዶ ላከ፣ ብርቱ በረዶ ልኮም በበለስ ዛፎቻቸው ላይ የነበሩትን ፍሬዎች አጠፋ። 48 ከብቶቻቸውን የሚገድል በረዶ፣ ላሞቻቸውንና በጎቻቸውን የሚገድል መብረቅ ላከ። 49 በግብፃውያን ላይ እግዚአብሔር በጽኑ ስለ ተቆጣ፣ እጅግ አስጨነቃቸው።የተመቱበት መቅሠፍት ሁሉን ያጠፉ የመላእክትን ሠራዊት ይመስላሉ። 50 ከቁጣው አልበረደም፣ ነፍሳቸውንም ከሞት አላተረፈም፤ ከእነርሱ ብዙዎችን የሚገድል መቅሠፍትን ላከ። 51 በመቅሠፍቱ የግብፃውያንን በኩር ወንድ ገደለ። 52 እረኛ በጎቹን እንደሚመራ ሕዝቡን ከግብፅ እየመራ አወጣቸው፣ በምድረ በዳ ሲጓዙም እርሱ መራቸው። 53 በሰላም መራቸው፣ እነርሱም አልፈሩም፣ ጠላቶቻቸው ግን በባህር ሰጠሙ። 54 ከዚያም ወደ ከነዓን አመጣቸው፣ ወደ ቀደሳት ምድር ወደ ጽዮን ተራራ፣ በዚያ የሚኖሩትን ሕዝቦች እንዲያሸንፏቸው በኃይሉ አበረታቸው። 55 የእርሱ ሕዝብ ወደ ፊት ሲገፋም የሕዝብ ወገኖችን ከፊታቸው አስወጣቸው፤ ለእያንዳንዱ ነገድ ምድሪቱን አካፈላቸው፣ የእነዚያን ሕዝቦች መኖሪያም ለእስራኤላውያን ሰጣቸው። 56 ይሁን እንጂ እስራኤላውያን ከአማልክት ሁሉ በላቀው በእግዚአብሔር ላይ ዐመጹበት፣ እግዚአብሔር የማይቀጣቸው ይመስል ሌላም ብዙ ክፉ ነገሮችን አደረጉ፣ ትዕዛዛቱንም አልጠበቁም። 57 ይልቁንም አባቶቻቸው እንዳደረጉት ሁሉ በእግዚአብሔር ላይ ዐመጹ፣ አልታመኑበትምም፤ ለማስፈንጠር ሲሞከር እንደሚሰበር እንደማያስተማምን ቀስት ነበሩ። 58 በኮረብቶቹ አናት ላይ ለአማላክቶቻቸው ምስል ስለ ሰገዱ፣ እግዚአብሔርን አስቆጡት። 59 ያደረጉትን አየ፣ እጅግም ተቆጣ፣ ስለዚህ የእስራኤልን ሕዝብ ተዋቸው። 60 በመካከላቸው ይኖርበት በነበረው የተቀደሰ ድንኳን፣ ከዚህ በኋላ በሴሎ አልተገለጠላቸውም። 61 ጠላቶቻቸው የኪዳኑን ታቦት እንዲማርኩ ፈቀደ፣የኃይሉና የክብሩ ምሳሌ የሆነውን። 62 በገዛ ሕዝቡ ላይ ተቆጥቶ ስለነበር፣ ጠላቶቻቸው እንዲገድሏቸው ፈቀደ። 63 ወጣቶቹ በጦር ሜዳ ተገደሉ፣ ስለዚህ ልጃገረዶቹን የሚያገባ አልተገኘም። 64 በርካታ ካህናት በጠላቶቻቸው ሰይፍ ተገደሉ፣ ሚስቶቻቸው እንዳያለቅሱም በሕዝቡ ተከለከሉ። 65 ከዚያም ጌታ ከእንቅልፉ እንደነቃ ሆነ፣ በወይን ብዛት ስለመስከሩ እንደተበሳጨ ጎልማሳ። 66 ጠላቶቻቸውን ወደ ኋላቸው መለሰ፣ ለረጅም ጊዜ እንዲያፍሩ አደረጋቸው፣ ተሸንፈው ነበርና። 67 የኤፍሬም ነገድ ሕዝብ በሰፈረበት ግን ድንኳኑን አልተከለም፤ ይህንን ለማድረግ ሰፈራቸውን አልመረጠም። 68 ከዚህ ይልቅ የይሁዳ ነገድ የሰፈረበትን አካባቢ መረጠ፤ የጽዮንን ተራራ መረጠ፣ እርሱ የወደደውን። 69 በሰማይ እንዳለው ቤቱ በዚያ መቅደሱ ከፍ ብሎ እንዲሠራ ወሰነ፤ እርሱንም እንደ ምድር አጸናው፣ መቅደሱ ለዘላለም እንዲኖር አሰበው። 70 በታማኝነት ያገለገለውን ዳዊትን መረጠው፣ በጎችን ከሚጠብቅበት ወሰደው፣ 71 የአባቱን በጎች ይጠብቅ ከነበረበት ስፍራ፣ የእስራኤላውያን መሪ እንዲሆን ሾመው፣ ሁሌም የእግዚአብሔር ሕዝብ የሚሆኑለትን። 72 ዳዊት የእስራኤልን ሕዝብ በቅንነትና በሙሉ ልቡ ተጠነቀቀላቸው፣ በብልኃትም መራቸው።
Chapter 79
የአሳፍ መዝሙር 1 እግዚአብሔር ሆይ፣ ሌሎች ሕዝቦች ምድርህን ወረሩ። ቤተ መቅደስህን አረከሱ፣ በኢየሩሳሌም የሚገኙትን ቤቶች ሁሉ አፈረሱ። 2 የገደሏቸውን የሕዝባችሁን ሬሳ ከመቅበር ይልቅ፣ ጥንብ አንሣዎች ሬሳዎቹን እንዲበሉት አደረጉ፣ ደግሞም የሕዝባችሁን ሬሳ የምድር አራዊት እንዲበሉ አደረጉ። 3 ሕዝባችሁን በገደሉ ጊዜ፣ የሕዝባችሁ ደም በኢየሩሳሌም ጎዳናዎች ላይ እንደ ውሃ ፈሰሰ፣ ሬሳዎቻቸውን ለመቅበር የተረፈ አንድ ሰው እንኳን አልነበረም። 4 በምድራችን ዙሪያ የሚኖሩ ሕዝቦች ይሰድቡናል፤ በእኛ ላይ ይስቁብናል፣ ይሳለቁብናልም። 5 ያህዌ፣ ይህ የሚሆነው እስከ መቼ ነው? ለዘላለምስ ትቆጣናለህን? ቁጣህስ ልክ እንደ እሳት በውስጥህ ይቃጠላልን? 6 እኛን ከምትቆጣን፣ አንተን የማያውቁህን ሕዝቦች ተቆጣቸው! ሕዝቦቿ ወደ አንተ በማይጸልዩ መንግሥታት ላይ ተቆጣ፣ 7 የእስራኤልን ሕዝብ ገድለዋልና፣ ከተማህንም አጥፍተዋልና። 8 አባቶቻችን ስለሠሩት ኃጢአት አትቅጣን! አሁን በምህረትህ ተመልከተን፣ እጅግ ተስፋ ቆርጠናልና። 9 እግዚአብሔር ሆይ፣ አንተ ብዙ ጊዜ አድነኸናል፣ ስለዚህ አሁንም እርዳን፤ ኃጢአታችንን ይቅር በለንና አድነን፣ ሌሎች ሕዝቦች ያከብሩህ ዘንድ። 10 ሌሎች ሕዝቦች "አምላካቸው ብርቱ ከሆነ ለምን አልረዳቸውም?" ሊሉን አይገባም፣ ከእኛ ብዙዎችን ስለገደሉና የሕዝብህን ደም ስላፈሰሱ በተራቸው ስትቀጣቸው አሳየን። 11 በወኽኒ ያለውን የሕዝብህን ሰቆቃ ስማ፣ ጠላቶቻችን ሊገድሏቸው የዛቱባቸውንም በታላቅ ኃይልህ ነጻ አውጣቸው። 12 አዘውትረው ሰድበውሃልና፣ ሰባት ዕጥፍ ተበቀላቸው! 13 ይህንን ስታደርግ እረኛ በጎቹን እንደሚጠብቅ የምትጠብቀን እኛም አንተን ማመስገናችንን እንቀጥላለን፤ ከትውልድ እስከ ትውልድ ለዘላለም እናመሰግንሃለን።
Chapter 80
ለመዘምራን አለቃ "የኪዳን አበባ" በሚል ቅኝት የሚዘመር የአሳፍ መዝሙር 1 እረኛ የበግ መንጋውን እንደሚመራ ሕዝብህን እስራኤልን የምትመራ ያህዌ ሆይ ስማን። በቤተ መቅደስህ ውስጥ እጅግ በተቀደሰው ስፍራ ከተቀረጹት ክንፋም ፍጥረታት በላይ በዙፋንህ ላይ ትቀመጣለህ። 2 ለኤፍሬም፣ ለብንያምና ለምናሴ ነገድ ሕዝቦች ራስህን ግለጥ! ኃይልህን አሳየን፣ መጥተህም አድነን! 3 እግዚአብሔር ሆይ፣ ሕዝባችንን እንደ ቀድሞው ብርቱዎች አድርገን፤ከጠላቶቻችን እንድንድን በቸርነትህ ተመልከተን! 4 የመልአክ ሠራዊት አዛዥ ያህዌ ሆይ፣ ወደ አንተ ስንጸልይ በእኛ በሕዝብህ ላይ የምትቆጣው እስከ መቼ ነው? 5 ብርጭቆ የሞላ ዕንባችንን ብቻ ለምግብና መጠጣችን የሰጠኸን መሰለ! 6 በዙሪያችን ያሉ ሕዝቦች የምድራችንን የትኛውን ክፍል እንደሚወስዱ እንዲከራከሩ አደረግህ፤ በእኛ ላይም ይስቃሉ። 7 የመልአክ ሠራዊት አዛዥ እግዚአብሔር ሆይ፣ ሕዝባችንን እንደ ቀድሞው አበርታው! እንድንም ዘንድ በቸርነትህ ተመልከተን! 8 አባቶቻችን ከግብፅ እንዳመጣኸው የወይን ተክል ነበሩ፤ ሌሎቹን ሕዝቦች ከዚህ ሀገር አስወጣህ፣ በሀገራቸውም ሕዝብህን አኖርክ። 9 ሰዎች ወይን ለመትከል መሬቱን እንደሚመነጥሩ፣ እንኖርበት ዘንድ በምድሪቱ የሚኖሩትን መነጠርህ። የወይኑ ተክል ሥሩ በምድር እንደሚጠልቅና እንደሚስፋፋ፣ አባቶቻችን በዚህ ሀገር ባሉት መንደሮች ሁሉ መኖር እንዲጀምሩና እንዲበለጽጉ አደረግኻቸው። 10 በጥላቸው ኮረብቶችን እንደሚሸፍኑ ታላላቅ የወይን ተክሎች፣ ቅርንጫፎቻቸውም ከዝግባ ዛፍ እንደሚረዝም፣ 11 ከነዓንን በሙሉ ሕዝብህ ገዛ፣ በምዕራብ ካለው ከሜዴትራንያን ባህር እስከ ምስራቅ የኤፍራጥስ ወንዝ ድረስ። 12 ታዲያ ለምን ተውከን? ጠላቶቻችንስ ቅጥሮቻችንን እንዲያፈርሱት ለምን ፈቀድክላቸው? የአንድን ሰው የወይን ቦታ የሚያፈርስን ሰው መሰልክ፣ ስለዚህ በዚያ የሚያልፉ ሰዎች ሁሉ ከወይኑ መስረቅ ይችላሉ፣ 13 የዱር አሳማዎች በወይኑ ላይ ይሔዱበታል፣ የዱር እንስሳትም የወይኑን ፍሬ መብላት ይቻላቸዋል። 14 የመልአክ ሠራዊት አዛዥ የሆንከው አንተ ወደ እኛ ተመለስ! ከሰማይ ቁልቁል ተመልከትና የደረሰብንን እይ! እንደ ወይንህ ቦታ የሆንነውን፣ 15 አንተ እንደተከልከውና እንዲያድግ እንዳደረግከው ለጋ የወይን ተክል መጥተህ አድነን! 16 በሀገራችን ያለውን ሁሉ ጠላቶቻችን አፈረሱትና አቃጠሉት፤ በቁጣ ተመልከታቸውና አጥፋቸው! 17 ነገር ግን የመረጥከንን ሕዝብህን አበርታን፣ ቀድሞ እጅግ ያበረታኸንን እኛን የእስራኤልን ሕዝብ። 18 ይህንን በምታደርግበት ጊዜ ዳግመኛ ከአንተ በፍጹም አንርቅም፤ አነቃቃን፣ እኛም እናመሰግንሃለን። 19 የመልአክ ሰራዊት አዛዥ ያህዌ ሆይ፣ አድሰን፤ በቸርነትህ ተመልከተንና ከጠላቶቻችን አድነን!
Chapter 81
ለመዘምራን አለቃ የአሳፍ መዝሙር 1 ከጠላቶቻችን ጋር ስንዋጋ የሚያበረታንን እግዚአብሔርን ለማመስገን ዘምሩ፤ የያዕቆብ ዘሮች ለምናመልከው ለእግዚአብሔር በደስታ ዕልል በሉ! 2 ከበሮውን መምታት፣ ሙዚቃውንም መጫወት ጀምሩ፣ በበገናና በመሰንቆ ጣፋጭ ሙዚቃ ተጫወቱ። 3 በየኣዲሱ የጨረቃ መውጫ በዓል ላይ መለከቶችን ንፉ፣ ጨረቃ ሙሉ በሚሆንበትና በሌሎች የበዓላት ወቅትም። 4 ይህንን አድርጉ ለእኛ ለእስራኤል ሕዝብ ሥርዓታችን ነውና፤ ለያዕቆብም ዘር ያደረገው የእግዚአብሔር ትዕዛዝ። 5 የግብፅን ምድር ሰዎች በቀጣቸው ጊዜ እርሱን ለእስራኤል ሕዝብ ሰጣቸው። በማላውቀው ቋንቋ ሲናገሩ የሰማሁት ይህንን ነው። 6 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣ "የግብፃውያን ገዢዎች እንደ ባሪያ እንድትሠሩ ባስገደዷችሁ ጊዜ፣ ከባዱን ሸክም ከጀርባችሁ አንከባለልኩ፣ ጡብ ለመሥራት ትሸከሙት የነበረውን ከባድ ቅርጫት ወዲያ እንድትጥሉ አስቻልኳችሁ። 7 እጅግ በተጨነቃችሁ ጊዜ ወደ እኔ ጮኻችሁ፣ እኔም አዳንኳችሁ፤ ከነጎድጓድ ደመናም ውስጥ ሰማኋችሁ። በኋላም በምድረ በዳው በመሪባ በነበራችሁ ጊዜ ውሃ እንደምሰጣችሁ ትታመኑብኝ እንደሆነ ፈተንኳችሁ። 8 ሕዝቤ ሆይ፣ ሳስጠነቅቃችሁ ስሙኝ! እናንተ የእስራኤል ሰዎች የምላችሁን ልብ ብትሉ እወዳለሁ! 9 የባዕዳን አማልክት ጣዖታት በመካከላችሁ አይኑሩ፤ ከእነርሱ ለየትኛውም ለመስገድ በፍጹም አትጎንበሱ! 10 እኔ አምላካችሁ ያህዌ ነኝ፤ ከእነዚያ አማልክት አንዳቸውም ከግብፅ አላወጧችሁም፣ ያንን ያደረግኹት እኔ ነኝ! እንዳደርግላችሁ የምትፈልጉትን ጠይቁኝ፣ እኔም አደርግላችኋለሁ። 11 ሕዝቤ ግን አልሰሙኝም፤ እነርሱም አልታዘዙኝም። 12 ልባቸው በጣም ስለደነደነ፣ የፈለጉትን ሁሉ እንዲያደርጉ ፈቀድኩላቸው። 13 ምነው ሕዝቤ በሰማኝ፣ የእስራኤል ሕዝብ እንዲያደርግ እንደምፈልገው ምነው በሔደልኝ። 14 ይህንን ቢያደርጉ ኖሮ ፈጥኜ ጠላቶቻቸውን ባሸነፍኩላቸው ነበር፤ እነዚያን የሚያስጨንቋቸውንም በገደልኳቸው ነበር። 15 እነዚያ የሚጠሉኝ ሁሉ በፊቴ ያለቅሳሉ፣ እኔም ለዘላለም እቀጣቸዋለሁ። 16 ነገር ግን እናንተ እስራኤላውያን መልካምን ስንዴ እሰጣችኋለሁ፣ ሆናችሁንም በበርበሃ ማር እሞላዋለሁ፥
Chapter 82
1 እግዚአብሔር በፈጠረው ፍጥረት ላይ በሾማቸው መናፍስት ጉባዔ በሰማይ ቆመ ይህንን እንደወሰነ ነገራቸው። 2 "በሰዎች መካከል በሐሰት መፍረዳችሁን ማቆም አለባችሁ፣ ክፉዎችን የሚያጸድቅ ውሳኔ መወሰን ካሁን በኋላ አትችሉም። 3 ለድሆችና ወላጅ አልባ ለሆኑ ሕፃናት ፍረዱላቸው፣ ለችግረኞችና ረዳት ለሌላቸው ጻድቅ አድርጉላቸው 4 ከክፉ ሰዎች ኃይል ታደጉአቸው!" 5 እነዚያ መሪዎች አያውቁም ምንም ነገር አይረዱም! አዕምሮአቸው የተበላሸ ነው፣ ከባሕሪያቸው መበላሽዐት የተነሣ፣ ልክ የምድር መሠረት የተናወጠ ያህል አስከፊ ሆነዋል። 6 እኔ አስቀድሜ ይህን ብዬአቸዋለሁ፣ "አማልክት እንደ ሆናችሁ ታስባላችሁ! ይህም ሁላችሁ የእኔ ልጆች እንደ ሆናችሁ ማለት ነው፣ 7 ነገር ግን ሁላችሁ እንደ ሰው ትሞታላችሁ። የሕይወታችሁ መጨረሻ እንደ አለቆች የሕይወት ፍጻሜ ነው። 8 እግዚአብሔር ሆይ ተነሥ! በምድር ላይ ባሉት ሁሉ ላይ ፍረድ ምክንያቱም በምድር ያሉ ሕዝቦች ሁሉ የአንተ ናቸው!
Chapter 83
የአሳፍ መዝሙር 1 እግዚአብሔር ሆይ፣ በዝምታህ አትቆይ! ምንም ባለመናገርም ጸጥ አትበል፣ 2 ጠላቶችህ በአንተ ላይ ጮኸውብሃልና፤ የሚጠሉህም አምፀውብሃልና! 3 እኛን ሕዝብህን የሚጎዳ ነገር ለማድረግ በስውር አሢረዋል፤ በምትጠብቀው ሕዝብ ላይ በአንድነት ሸምቀዋል። 4 እነርሱም፣ "ኑ፣ ትውልዳቸውን ማጥፋት አለብን፣ እስራኤል የሚባል እንደነበረ ማንም እንዳያስታውስ!" አሉ። 5 እስራኤልን ለማጥፋት ባላቸው ፍላጎት ላይ ተስማሙ፣ አንተን ለመዋጋትም በአንድነት ተስማሙ - 6 በኤዶም ድንኳኖች የሚኖሩ ሕዝቦች - እስማኤላውያን፣ ሞአብና አጋራውያን 7 ከጌባል፣ ከአሞናውያንና ከአማሌቃውያን ጋር አሤሩ፣ ከፍልስጥኤማውያንና በጢሮስ ከተማ ከሚኖሩ ሕዝቦች ጋር። 8 የአሶርም ሰዎች ተባበሯቸው፤ እነርሱ የሞአብና የአሞን ሕዝብ ወገን ደጋፊዎች ናቸው፣ የአብርሃም የወንድሙ ልጅ የሎጥ ዘሮች። 9 እግዚአብሔር ሆይ፣ በምድያም የሕዝብ ወገን ላይ ያደረግኸውን ነገር በእነዚህም ላይ አድርግ፣ በቂሶን ወንዝ አጠገብ በሲሳራና በኢያቢስ እንዳደረግኸው። 10 በዐይንዶር መንደር አጠፋኻቸው፣ ሬሳቸው በመሬት ላይ ተጋድሞ በሰበሰ። 11 በነገሥታቱ በሔሬብና በዜብ እንዳደረግኸው አድርግባቸው፤ ዛብሄልና ስልማናን ድል እንዳደረግኸቸው አለቆቻቸውን ድል አድርግ፣ 12 "እስራኤላውያን የእግዚአብሔር ነው! የሚሉትን ምድር የራሳችን እናደርጋለን" ያሉትን። 13 አምላኬ ሆይ፣ ዐውሎ ንፋስ ፈጥኖ እንደሚወስደው ትቢያ፣ ንፋስ እንደሚወስደውም ገለባ አጥፋቸው! 14 እሳት ጫካውን ፈጽሞ እንደሚያቃጥለው፣ ነበልባሉም በተራሮች ላይ እንደሚነድ፣ 15 በማዕበልህ አሳድዳቸው፣ በታላቅ ሞገድህም አስደንግጣቸው! 16 እጅግ እንዲያፍሩ አድርጋቸው፣ አንተ እጅግ ኃያል እንደሆንክ ያውቁ ዘንድ። 17 በመሸነፋቸው ለዘላለም እንዲያፍሩ አድርጋቸው፣ እያፈሩ እያሉ እንዲሞቱም አድርጋቸው። 18 ስምህ ያህዌ የሆንከውን አንተን፣ በምድር ባለው ሁሉ ላይ የበላይ ገዢ የሆንከውን እንዲያውቁ አድርጋቸው።
Chapter 84
ለመዘምራን አለቃ የቆሬ ልጆች መዝሙር 1 የመልአክ ሠራዊት አዛዥ የሆንክ ያህዌ ሆይ፣ መቅደስህ ምንኛ የተዋበ ነው! 2 በዚያ መሆንን እወዳለሁ፤ ያህዌ ሆይ፣ ያንን በጣም እፈልገዋለሁ። ሁሉን ቻይ አምላክ ለሆንክ ለአንተ ከልቤ በደስታ እዘምራለሁ። 3 ድንቢጦችና ዋኖሶች እንኳ በመቅደስህ አቅራቢያ ጎጆአቸውን ሠሩ፤ ሰዎች መሥዋዕት በሚያቀርቡልህ በመሰዊያው አጠገብ ጫጩቶቻቸውን ያሳድጋሉ፣ አንተ የመልአክ ሠራዊት አዛዥ ንጉሤና አምላኬ ነህ። 4 በመቅደስህ ያሉ ደስተኞች ናቸው፣ ባለማቋረጥም ምስጋናን ይዘምሩልሃል። 5 የምታበረታቸው አንተ መሆንህን የሚያውቁ፣ ወደ ጽዮን ተራራ ለመጓዝ አጥብቀው የሚመኙ ዕድለኞች ናቸው። 6 በደረቁ የቤካ ሸለቆ በሚያልፉበት ጊዜ፣ ስፍራውን የውሃ ምንጮች መፍለቂያ አደረግኸው፣ የበልጉ ዝናብም የውሃ መከማቻ እንዲሆን ሸለቆውን ይሞላዋል። 7 ስለዚህ በዚያ በኩል የሚጓዙ በረቱ፣ በጽዮን ተራራ ላይ በሀልዎትህ ፊት እንደሚቀርቡ አውቀዋልና። 8 የመልአክ ሠራዊት አዛዥ ያህዌ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤ የያዕቆብ ዘር የሆንን የምናመልክህ እግዚአብሔር ሆይ፣ ቃሌን አድምጥ! 9 እግዚአብሔር ሆይ፣ ለሚጠብቀን ለንጉሣችን ራራለት፣ ገዢያችን እንዲሆንም ለመረጥከው። 10 በሌላ ስፍራ ሺህ ቀናት ከምቆይ፣ በመቅደስህ ውስጥ አንድ ቀን መዋል ይሻለኛል፤ በክፉዎች ድንኳን ከመኖር፣ ወደ ውስጥ ለመግባት በመዘጋጀት በመቅደስህ መግቢያ በር መቆም ይሻለኛል። 11 አምላካችን ያህዌ እንደሚከልለን ጋሻና በላያችን ላይ እንደሚያበራ ፀሐይ ነው፤ ክብርንና ሞገስን ይሰጠናል። በጎውን የሚያደርጉትን ከመልካም ነገር አያሳጣቸውም። 12 የመልአክ ሠራዊት አዛዥ ያህዌ ሆይ፣ በአንተ የሚታመኑ ዕድለኞች ናቸው!
Chapter 85
ለመዘምራን አለቃ ከቆሬ ልጆች በአንዱ የተጻፈ መዝሙር 1 ያህዌ ሆይ፣ በዚህ ሀገር ለምንኖር ለእኛ በጎነትን አድርገሃል፤ እኛን የእስራኤልን ሕዝብ እንደገና አበለጸግኸን። 2 ሕዝብህ የሠራነውን ኃጢአት ይቅር አልከን፤ ኃጢአታችንንም ሁሉ ተውክለን። 3 በእኛ ላይ መቆጣትህን አቆምክ፣ በብርቱ ከመቅጣትም ተመለስክ። 4 አሁንም የምታድን እግዚአብሔር ሆይ፣ አቤቱ እኛን ከመቆጣት ተመለስ! 5 ለዘላለም ትቆጣናለህን? 6 እባክህ እንደገና እንድንበለጽግ አድርገን፣ እኛ ሕዝብህ ባደረግህልን ነገር ደስ እንዲለን። 7 ያህዌ ሆይ፣ ከመከራችን በማዳን፣ የታማኝነት ፍቅርህን አሳየን። 8 አምላካችን ያህዌ የሚናገረውን መስማት እፈልጋለሁ፣ ከንቱ ነገሮችን ወደ ማድረግ የማንመለስ ከሆነ፣ እኛ ሕዝቡ በሰላም የምንኖርበትን ተስፋ ይሰጠናልና። 9 ክብሩ በምድራችን ይኖር ዘንድ፣ የሚፈሩትን ለማዳን በርግጥ ዝግጁ ነው። 10 ይህ ሲሆን ሊወደንና ተስፋውን ሊፈጽምልን የታመነ ነው፤ ጽድቅን ያደርጋል፣ ሰላምንም ይሰጠናል፣ ይህም ሰላም ልክ እንደመተቃቀፍ ነው። 11 በዚህ በምድር ላይ ለእግዚአብሔር ታማኞች እንሆናለን፣ እግዚአብሔርም ከሰማይ በጽድቅ ይመልስልናል። 12 አዎን፣ ያህዌ መልካምን ያደርግልናል፣ በምድራችንም ላይ ብዙ ምርት ይሆናል። 13 ያህዌ ዘወትር በጽድቅ ያደርጋል፤ እርሱ በሚሔድበት ሁሉ በጽድቅ ያደርጋል።
Chapter 86
የዳዊት መዝሙር 1 ያህዌ ሆይ፣ የምለውን አድምጥና መልስልኝ፣ እኔ ደካማና ምስኪን ነኝና። 2 ላንተ ታምኛለሁና አሁን ከመሞት አድነኝ፤ አምላኬ ሆይ፣ በአንተ ስለምታመንና ስለማገለግልህ አድነኝ። 3 ጌታ ሆይ፣ ማረኝ፣ በየዕለቱ ወደ አንተ እጮኻለሁና። 4 ጌታ ሆይ፣ ደስ አሰኘኝ፣ ወደ አንተ እጸልያለሁና። 5 ጌታ ሆይ፣ አንተ ለእኛ መልካም ነህ፣ ይቅርም አልከን፤ ወደ አንተ የሚጸልዩትንም ሁሉ በታማኝነትህ እጅግ ትወዳቸዋለህ። 6 ጌታ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማ፤ እንድትረዳኝ ወደ አንተ ስጣራ አድምጠኝ። 7 በመከራዬ ጊዜ ወደ አንተ እጮኻለሁ፣ ትመልስልኛለህና። 8 ጌታ ሆይ፣ ከአሕዛብ አማልክት ሁሉ አንተን የሚመስልህ የለም፤ ከእነርሱ አንዱም አንተ ያደረግኸውን ታላቅ ነገር ያደርገ የለም። 9 ጌታ ሆይ፣ አንድ ቀን አንተ ከመሠረትካቸው ሕዝቦች ሁሉ ሰዎች በፊትህ መጥተው ይሰግዳሉ፣ አንተንም ያመሰግኑሃል። 10 አንተ ታላቅ ነህ፣ ድንቅ ነገሮችንም ታደርጋለህ፤ አንተ ብቻ እግዚአብሔር ነህ። 11 ያህዌ ሆይ፣ እንዳደርግ የምትፈልገውን አስተምረኝ፣ ፍጹም በሆነው ቃልህ ሕይወቴን እንድመራ። በሁለንተናዬ እንዳከብርህ አድርገኝ። 12 ጌታ አምላኬ ሆይ፣ በሁለንተናዬ አመሰግንሃለሁ፣ ለዘላለምም አከብርሃለሁ። 13 እንደ ተስፋ ቃልህ በታማኝነት እጅግ ወደኸኛልና፤ እንዳልሞት፣ ሙታንም ወደሚከማቹበት እንዳልሔድ ከለልከኝ። 14 እግዚአብሔር ሆይ፣ ትዕቢተኞች ግን ሊያጠቁኝ ሞከሩ፤ ጨካኝ ወንበዴዎችም ሊገድሉኝ ይፈልጋሉ፤ ለአንተ ምንም ዓይነት አክብሮት የሌላቸው ሰዎች ናቸው። 15 ጌታ ሆይ፣ አንተ ግን ዘወትር የምትምርና የምትራራ ነህ፤ ፈጥነህ አትቆጣም፣ በታማኝነት እጅግ ትወደናለህ፣ ዘወትርም የገባህልንን ተስፋ ትፈጽምልናለህ። 16 እናቴ እንዳደረገችው ወደማገለግልህ፣ ወደ እኔ ተመልከት፣ ማረኝም፤ አድነኝ አበርታኝም። 17 ያህዌ ሆይ፣ በጎነትህን ታሳየኝ ዘንድ አንድ ነገር አድርግልኝ፣ የሚጠሉኝ አንተ እንደረዳኸኝና እንዳገዝኸኝ ያዩ ዘንድ፣ ያፍሩም ዘንድ።
Chapter 87
1 ያሕዌ የመሠረታት ከተማ በተቀደሰው ተራራ ላይ ናት። 2 እርሱ ከተማዋን ይወድዳል፣ ከእስራኤል ስፍራዎች የበለጠ፣ ኢየሩሳሌምን ይወድዳል። 3 በኢየሩሳሌም ያላችሁ ሰዎች፣ በሌላ ስፍራ ያሉ ሰዎች ስለ እናንተ ከተማ አስደናቂ ነገር ይናገራሉ። 4 አምላካችንን ከሚያውቁ መካከል የግብፅ እና የባቢሎን፣ የፍልስጥኤም፣ የጢርስንና የኢትዮጵያ አንድ ቀን "ምንም እንኳ በኢየሩሳሌም ባልወለድም፣ የያሕዌ ስለሆንኩ በዚያ እንደተወለድኩ እቆጥራለሁ" ይላሉ። 5 ኢየሩሳሌምን በተመለከተ፣ ሰዎች እንዲህ ይላሉ፣ "እነዚህ ሰዎችም ሁሉ በዚያ ስለተወለዱ ሁሉን ቻይ አምላክ ከተማዋን ጸንታ እንድትቆም አድርጓታል" 6 ያሕዌ የእርሱ የሆኑትን ልዩ ልዩ ሕዝቦች ስም ዝርዝር ይጽፋል፣ ሁሉንም የኢየሩሳሌም ከተማ ዜጎች አድርጎ እንደሚቆጥራቸው ይናገራል። 7 ሁሉም በአንድነት እንዲህ እያሉ ይዘምራሉ፣ "ኢየሩሳሌም የበረከቶቻችን ምንጭ ናት።"
Chapter 88
ለመዘምራን አለቃ ከቆሬ ልጆች አንዱ በሆነው በዛራ ልጅ በኤማን ሐዘንን ለመግለጽ የተጻፈ መዝሙር 1 የምትታደገኝ አምላኬ ያህዌ ሆይ፣ በየቀኑ እንድትረዳኝ ወደ አንተ እጮኻለሁ፣ በሌሊትም ደግሞ ወደ አንተ እጣራለሁ። 2 እንድትረዳኝ ወደ አንተ ስጣራ፣ አቤቱ ጸሎቴን ስማ። 3 ብዙ መከራን አይቻለሁና፣ ልሞትና ሙታን ወዳሉበት ልሔድ ነው። 4 ኃይል አልቀረልኝምና፣ ሌሎች ሰዎችም ደግሞ ፈጥኜ እንደምሞት ቆጥረዋል። 5 እኔ እንደተተወ ሬሳ ነኝ፤ በመቃብራቸው እንደተጋደሙ ሙታን፣ ከእንግዲህ አታስብላቸውምና፣ ሰዎች ፈጽመው እንደሚረሷቸው ነኝ። 6 ሬሳ ወደሚጣልበት ቦታ፣ ወደ ጥልቅ ጨለማ የጣልከኝ ይመስላል። 7 በእኔ ላይ እጅግ የተቆጣህ፣ የውቅያኖስ ሞገድ ሰዎችን እንደሚሰባብር የሰባበርከኝ ይመስላል። 8 ባልንጀሮቼ እንዲያገልሉኝ አደረግህ፤ እኔም አስቀያሚ ሆንኩባቸው። በወኅኒ እንዳለ እና ሊያመልጥ እንደማይችል ሰው ሆኜ ነበር። 9 ከልቅሶዬ ብዛት የተነሣ ዓይኖቼ አጥርተው ማየት አይችሉም። ያህዌ ሆይ፣ እንድትረዳኝ በየዕለቱ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ በምጸልይበት ጊዜም እጆቼን ወደ አንተ አነሣለሁ። 10 ያለጥርጥር ለሙታን ተአምራትን አታደርግላቸውም! መንፈሳቸውም ሊያመሰግንህ አይነሣም! 11 በመቃብር ያሉ ሙታን ያለ ጥርጥር ለእኛ ስላለህ የታማኝነት ፍቅር አይናገሩም፣ ሰዎች በመጨረሻ በሚጠፉበትም ስፍራ፣ በታማኝነት ስለምታደርግልን ነገር የሚናገር ማንም አይኖርም። 12 መቼም ቢሆን በጥልቁ ጨለማ የሚኖር ማንም አንተ የምትፈጽመውን ተአምራት አያይም፣ ሰዎች ፈጽሞ ከሚረሱበት ቦታም ለእኛ ያደረከውን በጎነት የሚናገር አንድም አይኖርም። 13 እኔ ግን ያህዌ ሆይ፣ እንድትረዳኝ ወደ አንተ እጮኻለሁ፤ በየጠዋቱም ወደ አንተ እጸልያለሁ። 14 ያህዌ ሆይ፣ ስለምን ትጥለኛለህ? ፊትህንስ ለምን ትሰውርብኛለህ? 15 ከታናሽነቴ ጀምሮ ተሰቃየሁ፣ ወደ ሞትም ቀረብሁ፤ ያደረስክብኝን መከራ በመታገሴ ምክንያት ግራ ተጋባሁ። 16 ስለ ተቆጣኸኝ የሰባበርከኝ መስሎኛል፤ የምታደርስብኝ አስፈሪ ነገሮች ሊያጠፉኝ ነውና። 17 እንደጎርፍ የከበቡኝ፤ ከየአቅጣጫው የቀረቡኝ መሰለኝ። 18 ጓደኞቼና የምወዳቸው እንኳን እንዲርቁኝ አደረግህ፣ የቀረኝ ጓደኛ ጨለማ ብቻ ሳይሆን አይቀርም።
Chapter 89
ከዕዝራ ወገን በሆነው በኤታን የተጻፈ መዝሙር 1 ያህዌ ሆይ፣ ስለ ታማኝነት ፍቅርህ ለዘላለም እዘምራለሁ፤ የሰጠኸውን ተስፋ ሁሉ በታማኝነት መፈጸምህን ገና ያልተወለዱ ሕዝቦች ይሰማሉ። 2 ለዘላለም በታማኝነት እንደምትወደን ለሰዎች እናገራለሁ፣ የሰጠኸውን ተስፋ ለመፈጸም ያለህ ታማኝነት እንደ ሰማይ የጸና ነው። 3 ያህዌ እንዲህ አለ፣ "እንዲያገለግለኝ ከመረጥኩት ከዳዊት ጋር ስምምነት አድርጌአለሁ፣ ይህንን ጽኑ ኪዳን ከእርሱ ጋር ገብቻለሁ፤ 4 ከትውልድህ ብዙዎቹን ነገሥታት አደርጋቸዋለሁ፤ የዘርህም የንግሥና ሐረግ ለዘላለም አይቋረጥም"። 5 ያህዌ ሆይ፣ ስለምታደርጋቸው ድንቅ ነገሮች የሰማይ ፍጥረታት ሁሉ እንዲያመሰግኑህ እፈልጋለሁ፣ ቅዱሳን መላእክትህም ቃልህን በታማኝነት ስለመፈጸምህ ይዘምሩልሃል። 6 ያህዌ ሆይ፣ በማይ ከአንተ ጋር ሊወዳደር የሚችል አንድም የለም። ከአንተ ጋር እኩል የሚሆኑ መላእክት በሰማይ የሉም። 7 ቅዱሳን መላእክትህ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ፣ ልትከበር እንደሚገባህ ዐወጁ፤ ዙፋንህን ከሚከብቡት መላእክት ሁሉ ይልቅ እጅግ ድንቅ መሆንህን ይናገራሉ! 8 ሁሉን ቻይ የሆንክ ያህዌ ሆይ፣ ማንም እንዳንተ ያለ ኃያል የለም፤ ተስፋህን ሁሉ የምትፈጽምበት ታማኝነትህ ዘወትር እንደ ካባ ይከብሃል። 9 በብርቱ ባህሮች ላይ አንተ ትገዛለህ፤ ማዕበላቸው በሚነሣበት ጊዜ ጸጥ ታሰኛቸዋለህ። 10 ረአብ ተብሎ የሚጠራውን ታላቁን የባህር ፍጥረት የሰባበርከውና የገደልከው አንተ ነህ። በታላቅ ኃይልህ ጠላቶችህን ድል አድርገህ በተንኻቸው። 11 ሰማያት የአንተ ናቸው፣ ምድርም የአንተ ናት፤ አንተ ሁሉን ፈጥረሃልና በምድር ያለው ሁሉ የአንተ ነው። 12 ከሰሜን እስከ ደቡብ አንተ ሁሉን ነገር ፈጥረሃል። የታቦርና የአርሞንኤም ተራሮች በደስታ ያመሰግኑሃል። 13 አንተ ብርቱ ነህ፣ እጅግም ኃያል ነህ። 14 በሕዝብ ላይ በጽድቅና በፍትሐዊነት ትገዛለህ፣ ዘወትርም በታማኝነት ፍቅርህ የሰጠኸውን ተስፋ ትፈጽማለህ። 15 ያህዌ ሆይ፣ በዕልልታ የሚያመልክህ፣ ጠባቂው መሆንህን በማወቅ የሚኖር ሕዝብ ደስተኛ ነው። 16 ዕለት በዕለትም በሥራህ ደስ ይላቸዋል፣ እጅግ ቸር ስለሆንክላቸውም ያመሰግኑሃል። 17 የክብርህን ብርታት ትሰጠናለህ፤ ሞገስን ስለምትሰጠን ጠላቶቻችንን ድል እናደርጋለን። 18 ያህዌ ሆይ፣ የሚጠብቀንን ሰጠኸን፤ እስራኤላውያን የምናመልክህ ቅዱስ እግዚአብሔር፣ አንተ ንጉሥን መረጥክልን። 19 ከዓመታት በፊት ከባሪያዎችህ ለአንዱ በራዕይ እንዲህ ስትል ተናገርክ፣ "ዝነኛውን ወታደር አንግሼዋለሁ፤ ከሕዝቡ ሁሉ ንጉሥ እንዲሆንም መርጬዋለሁ። 20 ያም ሰው በታማኝነት የሚያገለግለኝ ዳዊት ነው፣ ንጉሥ እንዲሆንም በተቀደሰው የወይራ ዘይት ቀባሁት። 21 ብርታቴ ዘወትር ከእርሱ ጋር ይሆናል፤ በኃይሌም አበረታዋለሁ። 22 ጠላቶቹ እርሱን የሚረቱበትን መንገድ አያገኙም፣ ክፉዎች ሰዎችም በፍጹም አያሸንፉትም። 23 በፊቱ ጠላቶቹን እሰባብራለሁ፣ የሚጠሉትንም ከእርሱ አርቃቸዋለሁ። 24 ዘወትር ታማኝና መሓሪ እሆንለታለሁ፣ ጠላቶቹን እንዲያሸንፍም አስችለዋለሁ። 25 መንግሥቱም ከሜዴትራንያን ባህር እስከ ኤፍራጥስ ወንዝ ያለውን ምድር እንዲያካትት አደርጋለሁ። 26 እርሱም፣ አንተ አባቴ ነህ፣ የምታድነኝና የምትጠብቀኝ አምላኬ ይለኛል። 27 የበኩር ልጄ የሚሆንበትን መብት እሰጠዋለሁ፤ በምድር ላይ ታላቅ ንጉሥ ይሆናል። 28 ሁሌም ለእርሱ ታማኝ እሆናለሁ፣ ልባርከው የገባሁት ኪዳንም ለዘላለም ይኖራል። 29 ለትውልዱ ፍጻሜ እንዳይኖረው አድርጌ እመሠርተዋለሁ፣ ከትውልዱ ብዙዎች ንጉሥ መሆናቸው ይቀጥላል። 30 ነገር ግን ከትውልዱ አንዳንዶቹ በሕጌ ላይ ቢያምጹ፣ ትዕዛዜ እንደሚላቸው ባይሔዱ፣ 31 ሕግጋቴን ቸል ቢሉ፣ እንዳዘዝኳቸው ትክክል የሆነውን ነገር ባያደርጉ፣ 32 በብርቱ እቀጣቸዋለሁ፣ የማይገባውን ስለማድረጋቸውም መከራ እንዲገጥማቸው አደርጋቸዋለሁ። 33 ነገር ግን ለዳዊት ያለኝን ታማኝነት አላቋርጥም፣ ሁል ጊዜም የሰጠሁትን ተስፋ እፈጽማለሁ። 34 ከእርሱ ጋር ያደረግሁትን ስምምነት አላፈርስም፤ ከነገርኩት ቃል አንዱንም አልለውጥም። 35 ለዳዊት ከቶ ላይለወጥ አንዴ ምዬለታለሁና፣ እኔ እግዚአብሔር ነኝና ዳዊትን አልዋሸውም። 36 የትውልድ ሐረጉ ለዘላለም እንደሚነግሥ ቃል ገብቼለታለሁ፤ ፀሐይ በሚያበራበት ዘመን ሁሉ የጸና ይሆናል። 37 ያ ሐረግ እንደ ጨረቃ ቋሚ ይሆናል፣ እርሱም ዘወትር በዚህ ምድር ላይ ሁሉን ይመለከታል"። 38 ያህዌ ሆይ፣ አሁን ግን ጥለኸዋል! በቀባኸው ንጉሥ ላይ እጅግ ተቆጥተሃል። 39 ከአገለጋይህ ከዳዊት ጋር ያደረግኸውን ስምምነት ያፈረስክ ትመስላለህ፤ ዘውዱን በአቧራ ላይ የጣልክበት ይመስላል። 40 ከተማውን የሚጠብቅለትን ቅጥር አፍርሰሃል፣ ምሽጎቹ ሁሉ እንዲፈራርሱም ፈቅደሃል። 41 በዚያ የሚያልፉ ሁሉ ንብረቱን ይበዘብዙታል፤ ጎረቤቶቹም ይስቁበታል። 42 ጠላቶቹ እንዲያሸንፉት አስቻልካቸው፤ ሁሉም ደስ እንዲሰኙ አደረግኻቸው። 43 ሰይፉን ከጥቅም ውጪ አደረግህበት፣ በጦርነቶቹም አልረዳኸውም። 44 ግርማዊነቱ እንዲያበቃ አደረግህ፣ ዙፋኑንም ወደ ምድር ጣልክ። 45 ገና ወጣት ሆኖ ሳለ አስረጀኸው፣ እጅግ እንዲዋረድም አደረግኸው። 46 ያህዌ ሆይ፣ ይህ እስከ መቼ ይቀጥላል? ራስህን ለዘላለም ትሰውርብናለህን? ቁጣህ እንደ እሳት የሚነድብን እስከ መቼ ነው? 47 የሕይወት ዘመናችን እጅግ አጭር እንደሆነ አትርሳ፤ እኛን የሰው ልጆችን ሁሉ በከንቱ እንደ ፈጠርከን አትርሳ። 48 የማይሞትና ሕያው ሆኖ ሊኖር የሚችል አንድም የለም፤ ሙታን ካሉበት ስፍራ ራሱን ሊመልስ የሚችል አንድም የለም። 49 ያህዌ፣ ከዘመናት በፊት በታማኝነት ልትወደኝ ቃል ገባህ፤ ታዲያ ይህንን የማታደርገው ለምንድነው? ይህንን ለዳዊት ምለህለታልና! 50 ያህዌ፣ ሰዎች የሰደቡንን አትርሳ! አረመኔ ሰዎች ረገሙኝ! 51 ያህዌ፣ ጠላቶችህ የመረጥከውን ንጉሥህን ሰደቡት! በሚሔድበት ሁሉ ይሰድቡታል። 52 ያህዌ ለዘላለም እንደሚመሰገን ተስፋ አደርጋለሁ! አሜን! እንደዚሁ ይሁን!
Chapter 90
የነብዩ ሙሴ ጸሎት 1 ጌታ ሆይ፣ አንተ ለእኛ የዘወትር መጠለያችን ነህ። 2 ተራሮችን ከመፍጠርህ በፊት፣ ምድርንና በእርስዋ ላይ ያሉትን ሁሉ ከማበጀትህ በፊት፣ ከዘላለም የነበርክ አምላክ ነህ፣ ለዘላለምም አምላክ ሆነህ ትኖራለህ። 3 ሰዎች በሚሞቱበት ጊዜ ሬሳቸው እንደገና ዐፈር እንዲሆን ታደርጋለህ፤ ሬሳዎቻቸውን ልክ የመጀመሪያው ሰው ወደ ተፈጠረበት ትቢያ ትለውጠዋለህ። 4 ስለ ጊዜ ስታስብ፣ ሺህ ዓመት በቶሎ እንደሚያልፍ እንደ አንድ ቀን፤ እንደ ሌሊቱም ጥቂት ሰዓታት ትቆጥራቸዋለህ። 5 ሰዎች በድንገት እንዲሞቱ ታደርጋለህ፤ ለጥቂት ጊዜ ብቻ እንደሚቆይ ሕልም ለአጭር ጊዜ ብቻ ይኖራሉ። እነርሱ እንደሚበቅል ሣር ናቸው። 6 ሣሩ በጠዋት ያቆጠቁጥና ይለመልማል፣ በመሸ ጊዜ ግን ይጠወልግና ፈጽሞ ይደርቃል። 7 ልክ እንደዚሁ፣ እኛም በሠራነው ኃጢአት ምክንያት ተቆጥተኸናል፤ ታስደነግጠናለህ ከዚያም ታጠፋናለህ። 8 ኃጢአታችንን በፊት ለፊትህ ያስቀመጥክ ይመስል፣ በምስጢር ያደረግነውን ኃጢአታችንን እንኳ ልታያቸው ወደምትችልበት ታወጣለህ። 9 በእኛ ላይ ስለተቆጣህ ሕይወታችን እንዲያበቃ ታደርጋለህ፤ የምንኖርባቸውንም ዓመታት ፈጥኖ እንደሚያልፍ እስትንፋስ ታደርጋቸዋለህ። 10 ሰዎች ለሰባ ዓመታት ብቻ ይኖራሉ፤ አንዳንዶቹ ከበረቱ ሰማንያ ዓመት ይኖራሉ። ከዚያ ሲያልፍ ግን ብዙ ህመምና መከራ ይሆናል፤ ሕይወታችን ፈጥኖ ያበቃል፣ እኛም እንሞታለን። 11 በተቆጣኻቸው ጊዜ ያደረግህባቸውን ታላላቅ ነገሮች የተለማመደ ማንም የለም፣ ስለተቆጣኻቸው ሰዎች ቅጣትህን አልፈሩም። 12 ስለዚህ ጥቂት ጊዜ ብቻ እንደምንኖር እንድንገነዘብ አስተምረን፣ ጊዜአችንን በአግባቡ እንድንጠቀምበት። 13 ያህዌ ሆይ፣ የምትቆጣን እስከ መቼ ነው? ለአገልጋዮችህ ራራልን። 14 ቃል እንደገባህልን በየማለዳው ምህረትህን ብታሳየን ይበቃናል። በሕይወት ዘመናችን ሁሉ ደስ እንዲለንና እልል እንድንል ይህንን አሳየን። 15 በቀጣኸንና መከራን ባሳየኸን ዘመን ልክ አሁን ደስ አሰኘን። 16 የምታደርጋቸውን ታላላቅ ነገሮች እንድናይ አድርገን፣ ትውልጆቻችንም ደግሞ የክብርህን ኃይል እንዲያዩ። 17 ጌታ አምላካችን ሆይ፣ በረከቶችህን ስጠን፣ ስኬታማዎችም አድርገን፤ አዎን፣ በምንሠራው ሁሉ ስኬትን ስጠን!
Chapter 91
1 በሁሉን ቻይ አምላካ ጠበቃ ሥር የሚኖሩ፣ በጠበቃው ሥር በሰላም ማረፍ ይችላሉ። 2 ስለ ያህዌ እንዲህ በማለትእመሰክራለሁ፣ "አንተ ጠብቀኸኛል፤ እንደምከለልበት ምሽግ ነህ። የምታመንብህ አምላኬ አንተ ነህ"። 3 እርሱ ከወጥመድ ሁሉ ይታደግሃል፣ ከሚገድሉ በሽታዎችም ያድንሃል። 4 በክንፎቹ ይጋርድሃል። በጥበቃው ውስጥ ታርፋለህ። የምህረቱ ተስፋም እንደ ጋሻ ይጠብቅሃል። 5 በሌሊት ከሚያስፈራህ ነገር አትሰጋም፣ ወይም በቀን ጠላቶችህ ከሚወረውሩብህ ፍላጻዎች። 6 አጋንንት በሌሊት ሰዎችን ከሚያጠቁበት መቅሰፍት አትፈራም፣ ወይም በእኩለ ቀን ሰዎችን ከሚገድሉ የክፋት ኃይላት። 7 ሺህ ሰዎች እንኳን በቀኝህ ወድቀው ይሞታሉ፣ ዐሥር ሺዎችም በዙሪያ ይሞታሉ፣ አንተ ግን አትጎዳም። 8 እይ ተመልከትም፣ ክፉዎች ሰዎች ይቀጣሉ! 9 ያህዌ እንዲጠብቅህ ብትፈቅድ፣ ሁሉን ቻይ አምላክ እንደሚያስጠልልህ ብትታመን፣ 10 የትኛውም ክፉ አይደርስብህም፤ መቅሰፍትም ወደ ቤትህ አይቀርብም፣ 11 በምትሠራው ሁሉ ይጠብቁህ ዘንድ፣ ያህዌ መላእክቱን ያዝልሃልና። 12 በትልቅ ድንጋይ ላይ እግርህ እንዳይጎዳ፣ በእጆቻቸው ያነሡሃል። 13 በጠላቶችህ ከመጎዳት ትጠበቃለህ፤ ሳይጎዱህ በአናብስትና በመርዘኛ እባቦች ላይ እንደምትረግጥ ይሆንልሃል! 14 ያህዌ እንዲህ ይላል፣ "የሚወዱኝን እታደጋቸዋለሁ፣ እኔ ያህዌ መሆኔን አውቀዋልና እጠብቃቸዋለሁ። 15 በሚጠሩኝ ጊዜ እመልስላቸዋለሁ። በመከራቸው ጊዜ እረዳቸዋለሁ፤ አድናቸዋለሁ፣ አከብራቸዋለሁም። 16 ረጅም ዕድሜ እንዲኖሩ እሰጣቸዋለሁ፣ አድናቸዋለሁም"።
Chapter 92
በሰንበት ቀናት የሚዘመር መዝሙር 1 ያህዌ ሆይ፣ ሰዎች ቢያመሰግኑህ መልካም ነው፣ ከአማልክት ሁሉ ታላቅ የሆንከውን አንተን ለማመስገን ቢዘምሩ። 2 ማለዳ ማለዳ ምህረትህን ማወጅ መልካም ነው፣ ስለ ቃል ኪዳን ታማኝነትህም ዘወትር በየምሽቱ መዘመር፣ 3 ዐሥር አውታር ባለው በበገና በመታጀብ፣ እንዲሁም በመሰንቆ ድምጽ። 4 ያህዌ፣ ደስ አሰኝተኸኛል፤ አድርገህልኛልና በደስታ እዘምራለሁ። 5 ያህዌ፣ ሥራህ ታላቅ ነው! ሀሳብህን ሁሉ ለማስተዋል ግን አስቸጋሪ ነው። 6 ሰነፎች ሊያውቁት የማይቻላቸውን ነገሮች ታደርጋለህ፣ ማስተዋል የጎደላቸው ሰዎችም አይገነዘቧቸውም። 7 ሣር እንደሚያቆጠቁጥ ክፉዎች ቁጥራቸው ቢበዛም አያስተውሉም፣ ክፉ የሚያደርጉ ቢበለጽጉም፣ ፈጽመው ይጠፋሉ። 8 ያህዌ ግን ለዘላለም ትነግሣለህ። 9 ያህዌ ሆይ፣ ጠላቶችህ በርግጥ ይሞታሉ፣ ክፋትን የሚያደርጉም ይሸነፋሉ። 10 አንተ ግን እንደ አውራሪስ አጠነከርከኝ፤ እጅግም ደስ አሰኘኸኝ። 11 ጠላቶቼን ስታሸንፍ አይቻለሁ፣ ክፉዎች ሰዎች በሚታረዱበት ጊዜ ሲያለቅሱም ሰምቻለሁ። 12 ጻድቃን ግን የዘንባባ ዛፍ እንደሚለመልም፣ የሊባኖስ ዝግባም እንደሚያድግ ይበለጽጋሉ። 13 እነርሱ በያህዌ ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም ሰዎች እንደሚተክሏቸው ዛፎች፣ በአምላካችን መቅደስ አደባባይ አቅራቢያ እንዳሉ ዛፎች ናቸው። 14 ጻድቃን በሚሸመግሉበት ጊዜ እንኳን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝ ብዙ ነገር ያደርጋሉ። ከውስጥ ፈሳሾቻቸው ጋር እንደሚኖሩ ዛፎች ጠንክረውና ብርታትን ተላብሰው ይኖራሉ። 15 ይህም ያህዌ ጻድቅ መሆኑን ያመለክታል፤ እርሱ እንደምከለልበት ታላቅ ዐለት ነው፣ ከቶውንም ክፋትን አያደርግም።
Chapter 93
1 ያሕዌ፣ አንተ ንጉሥ ነህ! ክብርህና ኃይልህ እንደ ንጉሥ መታጠቂያ ናቸው። ዓለምን አጽንተህ አቁመኸዋል፣ ከሥፍራው አይነቃነቅም። 2 ከዘመናት በፊት ንጉሥ ሆነህ ገዝተሃል፣ አንተ ለዘላለም ትኖራለህ። 3 ያሕዌ፣ አንተ ምድርን ስትፈጥር፣ ውሃን ከሚያናውጠው የዓለም ክፍል ለየኸው፣ ውቅያኖስን አበጀህ፣ የውሃውም ሞገድ እስካሁን ይጮሃል። 4 ነገር ግን አንተ ከውቅያኖሶች ጩኸት ትበልጣለህ፣ ከባሕርም ሞገድ ይልቅ አንተ ታላቅ ነህ! አንተ ያሕዌ ነህ፣ ከየትኛውም አምላክ በላይ አንተ ነህ። 5 ያሕዌ፣ ሕጎችህ አይሻሩም፣ መቅደስህም ሁልጊዜ ቅዱስ ነው። ይህም ለዘላለም እውነት ነው!
Chapter 94
1 ያህዌ ሆይ፣ ጠላቶችህን መበቀል ተችሎሃል፣ ስለዚህ ልትቀጣቸው እንዳለህ አሳያቸው! 2 በምድር በሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ላይ የምትፈርድ አንተ ነህ፤ ስለዚህ ተነሥና የሚገባቸውን ስጣቸው። 3 ያህዌ ሆይ፣ እነዚያ ክፉ ሰዎች ደስ የሚሰኙት እስከ መቼ ነው? በደስታ መቀጠላቸው ትክክል አይደለም! 4 ክፉ ነገርን ያደርጋሉ፣ ያንን ስለማድረጋቸውም ይኩራራሉ፤ እንዲህ እንዲያደርጉ የሚፈቀድላቸው እስከ መቼ ነው? 5 ያህዌ፣ እነዚያ አመጸኞች እኛን ሕዝብህን የሰባበሩን መሰሉ፤ የፈጠርካቸውንና ላንተ ብቻ የሆኑትን ሕዝብ ያስጨንቃሉ። 6 መበለቶችንና የሙት ልጆችን ይገድላሉ፣ እንዲሁም በምድራችን የተጠለሉትን ስደተኞች። 7 እነዚያ አመጸኞች እንዲህ ይላሉ፣ "ያህዌ ምንም አያይም፤ ስለዚህ እስራኤላውያን የሚያመልኩት እግዚአብሔር የምንሠራውን ክፉ ሥራ አያይም"። 8 እናንተ እስራኤልን የምትገዙ ክፉ ሰዎች፣ እናንተ ሞኞችና ደንቆሮዎች ናችሁ ጠቢብ የምትሆኑት መቼ ነው? 9 እግዚአብሔር ጆሮዎቻችንን አበጀ፤ ስለዚህ የምትናገሩትን የማይሰማ ይመስላችኋልን? እርሱ ዓይኖቻችንን ፈጠረ፤ የምታደርጉትን ክፉ ነገር ማየት የማይችል ይመስላችኋልን? 10 የሌሎች ሕዝቦችን መሪዎች የገስጻቸዋል፤ እናንተንስ የማይቀጣችሁ ይመስላችኋልን? እርሱ ሁሉን ዐዋቂ ነው ታዲያ የምታደርጉትን የማያውቅ የሚመስላችሁ ለምንድነው? 11 ሰዎች የሚያስቡትን ሁሉ ያህዌ ያውቃል፤ የሚያስቡት ክፉና ከንቱ እንደሆነ ያውቃል። 12 ያህዌ ሆይ፣ ሕግህን እንድታስተምራቸው በሚፈልጉ ሰዎች፣ ተግሳጽህንም በሚቀበል ሕዝብ ደስ ይልሃል። 13 እንዲህ ያሉ ሰዎች መከራ ሲገጥማቸው ከእነርሱ ታርቅላቸዋለህ፣ ደግሞም አንድ ቀን ለአመጸኞች ጉድጓድን ትምስላቸዋለህ፣ በእነዚያ ጉድጓዶች ውስጥ ይወድቁና ይሞታሉ። 14 ያህዌ ሕዝቡን አይተውም፤ የእርሱ የሆኑትንም ቸል አይላቸውም። 15 አንድ ቀን ፈራጆች ለሰዎች ፍትሐዊ ውሳኔ ይሰጣሉ፣ በመሆኑም ታማኞች ሰዎች ሁሉ ደስ ይላቸዋል። 16 ክፉ ሰዎች ባስጨነቁኝ ጊዜ ግን፣ ማንም አልተሟገተልኝም! በእነዚያ ክፉ ሰዎች ላይ ሊመሰክርልኝ ማንም አልቆመም። 17 በዚያን ጊዜ ያህዌ ባይረዳኝ ኖሮ፣ በተገደልኩ ነበር፣ ነፍሴም ሙታን ወደማይናገሩበት ስፍራ በሔደች ነበር። 18 እኔም፣ "ወደ ጥፋት ወደቅሁ" አልኩኝ፣ አንተ ግን ያህዌ፣ በምህረትህ ደግፈህ አነሣኸኝ። 19 እጅግ በምጨነቅበት ጊዜ ሁሉ፣ ታጽናናኛለህ፣ ደስተኛ እንድሆንም ታደርገኛለህ። 20 ሰዎች ሐሰትን እንዲያደርጉ በመፍቀድ ሕግን ከሚያወጡ፣ ከአመጸኞች ዳኞችም ጋር ጉዳይ የለህም። 21 ከጻድቃን ለመራቅ ያቅዳሉ፣ ንጹሐን ሰዎች እንዲወገዱም ያውጃሉ። 22 ያህዌ ግን እንደ ምሽግ ሆነልኝ፤ አምላኬም እንደምከለልበት ታላቅ ዐለት። 23 እነዚያን አመጸኞች መሪዎች ስላደረጉት ነገር በተራቸው ይቀጣቸዋል፤ ስለ ሠሩትም ኃጢአት ያስወግዳቸዋል፤ አዎን፣ አምላካችን ያህዌ ይጠርጋቸዋል።
Chapter 95
1 ኑ፣ ለያሕዌ ዘምሩ፣ ላዳነንና ለጠበቀን በደስታ ዘምሩ! 2 በፊቱ ስንቀርብ ልናመሰግነው ይገባናል፣ ስናመሰግነውም በደስታ ልንዘምርለት ይገባናል። 3 ያሕዌ ታላቅ አምላክ ስለሆነ፣ በአማልክት ሁሉ ላይ የሚገዛ ታላቅ ንጉሥ ነው። 4 በምድር ሁሉ ላይ ከጥልቅ ስፍራ ጀምሮ እስከ ታላላቅ ተራሮች ድረስ እርሱ ይገዛል። 5 ባሕሮች የእርሱ ናቸው እርሱ ፈጥሮአቸዋልና፣ ደረቁንም ምድር የሠራ እርሱ ነው። 6 በእርሱ ፊት መጥተን ልንሰግድለትና ልናመለከው ይገባናል። በያሕዌ ፊት መንበርከክ ይገባናል፣ እርሱ ሠርቶናልና። 7 እርሱ እምላካችን ነው፣ እረኛ በጎቹን እንደሚጠብቅ፣ የጠበቀን እርሱ ነው። ዛሬ ያሕዌ ለእናንተ የሚናገረውን ትሰሙ ዘንድ ምኞቴ ነው። 8 እርሱ እንዲህ ይላል፣ "አባቶቻችሁ በመሪባ እንዳስቆጡት፣ በምድረ በዳም በማሳ እንደተፈታተኑት እልከኛ አትሁኑ። 9 በዚያ አባቶቻችሁ እኔ ሳልቀጣቸው ክፉ ነገርን ማድረግ ፈለጉ። ምንም እንኳ ብዙ ተአምራት ሳደርግ ቢያዩም፣ ምን ያህል እንደምታገሣቸው ማየት ፈለጉ። 10 ለአርባ ዓመታት አስቆጡኝ፣ እንዲህም አልኩ፣ እነዚህ ሰዎች የሚታመኑ አይደሉም። ትእዛዛቴን መታዘዝ እምቢ ብለዋል። 11 እጅግ ስላስቆጡኝ ስለ እነርሱ በከባድ ሁኔታ እንዲህ ብያለሁ፣ እንዲያርፉባት ወደፈቀድኩት ወደ ከነዓን ምድር አይገቡም!"
Chapter 96
1 ለያህዌ ዐዲስ መዝሙር ዘምሩ! በምድር የምትኖሩ ሁሉ ለያህዌ ዘምሩ! 2 ለያህዌ ዘምሩ፣ አመስግኑትም! ዕለት ዕለትም እኛን ማዳኑን ለሌሎች ዐውጁ። 3 ለሕዝብ ወገኖች ሁሉ ስለ ክብሩ ንገሩ፤ ለሕዝብ ወገኖች ሁሉ ያደርጋቸውን ድንቅ ነገሮች አውሩ። 4 ያህዌ ታላቅ ነው፣ እጅግ ሊመሰገንም ይገባዋል፤ ከሌሎች አማልክትም ይልቅ መከበር አለበት። 5 ሌሎች ሕዝቦች የሚያመልኳቸው አማልክቶች ሁሉ ጣዖታት ብቻ ናቸው፣ ያህዌ ግን በእውነት ታላቅ ነው፤ እርሱ ሰማያትን ፈጥሮአልና! 6 በሀልዎቱ ውስጥ የምትገኙ አብሩት፣ ታላቅ ንጉሥ እንደሆነም መመልከት ትችላላችሁ። እርሱ በመቅደሱ ውስጥ እጅግ ኃያልና እጅግም የተዋበ መሆኑን ማየት ይችላሉ። 7 በምድር የምትኖሩ ሕዝቦች ሁሉ ያህዌን አመስግኑ! ስለ ከበረው ኃይሉ ያህዌን አመስግኑ! 8 ምስጋና የተገባው ነውና ያህዌን አመስግኑ፤ መባን ይዛችሁ ወደ መቅደሱ ኑ። 9 በተቀደሰ መቅደሱ በሚገለጥበት ጊዜ በያህዌ ፊት ስገዱ፤ በምድር የሚኖሩ ሁሉ በፊቱ ይንቀጥቀጡ፣ እርሱ ቅዱስና ባለ ግርማ ነውና። 10 ለሕዝብ ወገኖች ሁሉ እንዲህ በሉ፣ "ያህዌ ንጉሥ ነው! ዓለምን በስፍራው አስቀመጠው፣ ሊያንቀሳቅሰው የሚችልም የለም። በሕዝብ ወገኖች ሁሉ ላይ በጽድቅ ይፈርዳል"። 11 በሰማይ የሚኖሩ ፍጥረታት ሁሉ ሐሴት ያድርጉ፣ በምድር የሚኖሩ ሰዎችም ሁሉ ደስ ይበላቸው። ውቅያኖሶችና በውስጣቸው የሚኖሩ ፍጥረታት ሁሉ ያህዌን ለማመስገን ይጩኹ። 12 መስኮችና በእነርሱ ላይ የሚበቅሉ ሁሉ ደስ ይበላቸው። ይህንን በሚያደርጉበት ጊዜ፣ በጫካ ውስጥ ያሉ ዛፎች ሁሉ 13 በያህዌ ፊት በደስታ ይዘምራሉ። በምድር በሚኖሩት ሁሉ ላይ ሊፈርድ በሚመጣበት ጊዜ ይህ ይሆናል። እውነቱን እንደማወቁ በሰዎች ሁሉ ላይ በጽድቅ ይፈርዳል።
Chapter 97
1 ያህዌ ንጉሥ ነው! ስለዚህ በምድር ያሉ ሁሉ ደስ እንዲላቸው እፈልጋለሁ፣ በውቅያኖሶች ባሉ ደሴቶች የሚኖሩትም ደግሞ ሐሴት እንዲያደርጉ! 2 በድቅድቅ ጨለማ የተሞላ ደመና በዙሪያው አለ፣ ሙሉ በሙሉ በጽድቅና በፍትሐዊነት ያስተዳድራል። 3 በፊት ለፊቱ እሳትን ይልካል፣ በዚህም እሳት ጠላቶቹን ፈጽሞ ያቃጥላቸዋል። 4 በምድር ዙሪያ ሁሉ እንዲያንጎደጉድ መብረቁን ይልካል፤ በምድር የሚኖሩ ሰዎች ያያሉ፣ በፍርሃትም ይንቀጠቀጣሉ። 5 በያህዌ ፊት ተራሮች እንደ ሰም ይቀልጣሉ፣ በምድር ሁሉ ላይ በሚገዛው ጌታ ፊት። 6 እርሱ በጽድቅ እንደሚያደርግ በሰማይ የሚኖሩ መላእክት ያውጃሉ፣ የሕዝብ ወገኖችም ሁሉ ክብሩን ያያሉ። 7 ጣዖታትን የሚያመልኩ ሁሉ ይፈሩ፤ ስለ ሐሰተኞች አማልክት የሚኩራሩ ሁሉ የአማልክቶቻቸውን ከንቱነት ይገንዘቡ። እነዚያ አማልክትም ያህዌን ለማምለክ ይሰግዳሉ። 8 በኢየሩሳሌም የሚኖሩ ሰዎች እግዚአብሔር ጻድቅ እንደ ሆነ ሰሙ፣ ደስም አላቸው፤ በሌሎች የይሁዳ ከተማ የሚኖሩት ሰዎችም ደግሞ ደስ አላቸው፣ በአመጸኞች ላይ ያህዌ ይፈርዳልና ይቀጣቸውማል። 9 በምድር ሁሉ ላይ ያህዌ የነገሥታት ንጉሥ ነው፤ እርሱ እጅግ ታላቅ ኃይል አለው፣ ሌሎች አማልክት አንዳችም ኃይል የላቸውም። 10 ክፉ የሚያደርጉ ሰዎችን የሚጸየፉትን ያህዌ ይወዳቸዋል፤ የሕዝቡንም ሕይወት ይጠብቃል፣ አመጸኞቹ ሊጎዷቸው በሚሞክሩበት ጊዜም ያታደጋቸዋል። 11 ጻድቃን በእውነት እንዲኖሩ ያደርጋቸዋል፤ ጻድቃን የሆኑትንም በውስጥ ማንነታቸው እንዲደሰቱ ያደርጋቸዋል። 12 እናንተ ጻድቃን ያህዌ ስላደረገው ነገር ደስ ይላበችሁ፣ ቅዱሱን አምላካችንንም አመስግኑት!
Chapter 98
1 ለያሕዌ አዲስ መዝሙር ዘምሩ እርሱ ድንቅ ነገር አድርጎአልና! በኃይሉ ጠላቶቹን ድል አድርጎአል። 2 እርሱ ድንቅ ጠላቶቹን ድል እንዳደረገ ለሕዝቡ አውጆአል፣ ጠላቶቹን እንደ ቀጣቸው አስታውቆአል፣ በዓለም ያሉ ሰዎች ሁሉ እርሱ ይህን እንዳደረገ አይተዋል። 3 ለእኛ ለእስራኤል ሕዝብ ቃል እንደገባልን፣ ወድዶናል ታማኝም ሆኖልናል። በሩቅ ሥፍራዎች የሚኖሩ ሰዎች አምላካችን ጠላቶቻን ድል እንዳደረገ አይተዋል። 4 በየሥፍራው ያላችሁ ሰዎችን ሁሉ ለያሕዌ በደስታ ልትዘምሩ ይገባል፣ ስትዘምሩ ድምፃችሁን ከፍ አድርጋችሁ አመስግኑት። 5 ለያሕዌ በመሰንቆ ዘምሩ፣ የሚያስደስት ሙዚቃ አቅርቡለት፣ 6 አንዳንዶቻችሁ መለከትን ንፉ፣ ሌሎቹ ደግሞ ለንጉሣችን ለያሕዌ እልል በሉ። 7 ውቅያኖሶች እና በውስጣቸውም የሚኖሩ ሁሉ ያሕዌን ለማመስገን ድምፃቸውን ከፍ ያድርጉ። በምድር ላይ ያለ ፍጥረት ሁሉ ይዘምር። 8 ወንዞች ያሕዌን ለማመስገን በእጆቻቸው እንደሚያጨበጭቡ ይሁኑ፣ ተራሮቹም በያሕዌ ፊት በደስታ እንደሚዘምሩ ይሁኑ። 9 እርሱ በእያንዳንዱ ላይ ሊፈርድ ወደ ምድር ይመጣልና! በዓለም በሚኖሩ ሕዝቦች ላይ በእውነትና በጽድቅ ይፈርዳል።
Chapter 99
1 ያሕዌ ታላቅ ንጉሥ ነው ስለዚህ በፊቱ ይንቀጠቀጣሉ! በላይ በስማይ ባለው መቅደሱ በኪሩቤል ላይ ይቀመጣል፤ ስለዚህ ምድር ትናወጣለች! 2 ያሕዌ በኢየሩሳሌም ታላቅ ንጉሥ ነው፣ በአሕዛብም ላይ ገዢ ነው። 3 እርሱ እጅግ ታላቅ ነውና ሊያመሰግኑት ይገባቸዋል፣ እርሱ ቅዱስ ነው። 4 እርሱ ጽድቅን የሚወድ ታላቅ ንጉሥ ነው፣ በእስራኤል በጽድቅና በእውንት ይፈርዳል። 5 አምላካችን እርሱ ያሕዌ ነው! በእግሩ መረገጫ ወድቃችሁ ስገዱ፣ በመቅደሱ፣ ሕዝቡን በሚገዛበት ቅዱስ ሥፍራው እርሱ ቅዱስ ነው። 6 ሙሴና አሮን የእርሱ ካህናት ነብሩ፣ ሳሙኤልም ወደ እርሱ ጸልዮአል። እነዚህ ሦስቱ ያሕዌ እንዲረዳቸው ወደ እርሱ ጮኹ፤ እርሱም መለሰላቸው። 7 እንደ ትልቅ አዕማድ በሚመስል ደመና ውስጥ ለሙሴና ለአሮን ተናገረ፣ እነርሱም እርሱ የሰጣቸውን ሕጎችና ትእዛዛት ታዘዙ። 8 ያሕዌ፣ አምላካችን፣ ሕዝቦችህ እንድትረዳቸው ወደ አንተ ሲጮሁ መልሰህላቸዋል ምንም እንኳ ስላደረጉት ክፉ ሥራ የቀጣሃቸው ቢህንም ያደረጉትን ኃጢአት ሁሉ ይቅር ያልካቸው አምላክ ነው። 9 ያሕዌ፣ አምላካችንን አመስግኑ፣ በተቀደሰው ተራራ በመቅደሱ አምልኩት ይህን ማድረግ የሚገባ ነው ምክንያቱም አምላካችን ያሕዌ ቅዱስ ነውና!
Chapter 100
1 በምድር ላያ ያለ ነገር ሁሉ ለያሕዌ በደስታ እልል ይበል! 2 ያሕዌን በደስታ ማምለክ አለብን! ወደ ፊት በደስታ በመቅረብ የምስጋና መዝሙር እንዘምራለን። 3 ያሕዌ አምላክ መሆኑን እናሳውቃለን፣ የሠራን እርሱ ነው፣ ስለሆነም እኛ የእርሱ ነን። የሚጠነቀቅልን ሕዝቦቹ ነን፣ እረኛ ለበጎቹ እንደሚጠነቀቅ የሚጠነቀቅልን በጎቹ ነን። 4 ወደ መቅደሱ እርሱን በማመስገን ግቡ፣ ወደ አደባባዮቹም ለእርሱ የምስጋና መዝሙር እየዘመራችሁ ግቡ! አመስግኑት ባርኩትም። 5 እርሱ ሁልጊዜ ለእኛ መልካም ነገሮችን ያደርጋልና። ለእኛ ቃል እንደ ገባልን በታማኝነት ይወድደናል፣ እርሱ የታመነ ነው።
Chapter 101
1 ያሕዌ፣ ለአንተ እዘምራለሁ! ስለ አንተ ታማኝነት እዘምራለሁ። 2 ሰዎችን ሳስተዳድር፣ ማንም እንዳይነቅፈኝ አድርጌ በጥንቃቄ ለመመላለስ ቃል እገባለሁ፣ ልትረዳኝ ወደ እኔ መቼ ትመጣለህ? ትክክለኛ የሆኑ ነገሮችን አደርጋለሁ። 3 ማንም ክፉ አድራጊ ወደ እኔ ይመጣ ዘንድ አልፈቅድም። ከአንተ ፊታቸውን የሚመልሱትን ጠላሁ፣ እንደዚህ ያሉትን ሰዎች ፈጽሞ አስወግጄአለሁ። 4 ታማኝነቴን ከእኔ አላርቅም፣ ከክፉም ጋር አልተባበርም። 5 ማንንም በምስጢር የሚያማውን ከእኔ አርቃለሁ፣ ኩራተኛና ትእቢተኛ ወደ እኔ ፈጽሞ አይቀርብም። 6 በዚህም ምድር ለአንተ የታመኑ ሰዎች እንዶሩ እፈቅዳለሁ፣ እነርሱ ከእኔ ጋር ይኖራሉ። እነርሱ እኔን ያገለግሉኛል ማንም አይነቅፋቸውም። 7 ሌሎችን የሚያታልል በእኔ ሥፍራ እንዲሠራ አልፈቅድለትም፣ ሐሰተኛም ለእኔ እንዲሠራ አልፈቅድለትም። 8 ክፉ ሰዎች ከዚህች ምድር እንዲወገዱ በየዕለቱ እሠራለሁ፣ ከከተማዋ አስወግዳቸዋለሁ። እርስዋ ያየሕዌ ከተማ ናትና።
Chapter 102
1 ያህዌ ሆይ፣ ጸሎቴን ስማኝ፤ ወደ አንተ ስጣራም አድምጠኝ! 2 ዝም አትበለኝ! ስማኝ፣ ወደ አንተ ስጮህም ፈጥነህ መልስልኝ! 3 ሕይወቴ በንኖ እንደሚጠፋ ጢስ አላቂ ነው፤ እሳት እንደሚያቃጥል ታላቅ ትኩሳት ሰውነቴን እያቃጠለኝ ነው። 4 እንደታጨደ ሣር ደርቄአለሁ፣ ምግብ የመብላት ፍላጎት በጭራሽ የለኝም። 5 ድምፄን ከፍ አድርጌ አቃስታለሁ፣ እጅግ ከስቻለሁና በቆዳዬ ውስጥ አጥንቶቼ ታዩ። 6 እኔ እንደተናቀና ለብቻው በምድረ በዳ እንዳለ ጥንብ አንሣ ነኝ፣ በኦና ቤት ውስጥ እንዳለም ጉጉት። 7 ያለ እንቅልፍ አድራለሁ፤ አንድም የሚያጽናናኝ የለምና፣ በጣሪያ ላይ ለብቻው እንደ ተቀመጠ ወፍ ሆንኩ። 8 ቀኑን ሁሉ ጠላቶቼ ይሰድቡኛል፤ ስሜን እያነሱም ይዘባበቱብኛል፣ በሚራገሙበት ጊዜም "እንደ እርሱ ያድርግህ" ይላሉ። 9 - 10 እጅግ ተቆጥተኸኛልና፣ አሁን እየተሠቃየሁ በአመድ ላይ እቀመጣለሁ፤ አመዱም በምበላው እንጀራ ላይ ይራገፋል፣ መጠጤም በእምባዬ የተደባለቀ ነው። ወደ ላይ አንሥተህ የወረወርከኝ ይመስለኛል። 11 የምኖርበት ዘመን አጭር ነው፣ እንደ ምሽት ጥላ ፈጥኖ ያልፋል። ሣር በፀሐይ ትኩሳት እንደሚጠወልግ ጠውልጌአለሁ። 12 ያህዌ ሆይ፣ አንተ ግን ለዘላለም የምትገዛ ንጉሣችን ነህ፤ መጪው ትውልድም ያስብሃል። 13 ትነሣና ለኢየሩሳሌም ሰዎች ቸርነትን ታደርጋለህ፤ ይህንን የምታደርግበት ጊዜም አሁን ነው፤ በጎነትን ልታደርግላቸው ጊዜው አሁን ነው። 14 ምንም እንኳን ከተማዪቱ ብትደመሰስም፣ አገልጋዮችህ ቀድሞ በቅጥሩ ላይ የነበሩትን ድንጋዮች አሁንም እንወዳቸዋለን፤ አሁን በየስፍራው ያለው ፍርስራሽ ነውና። 15 ያህዌ ሆይ፣ ሌሎች ሕዝቦችም አንድ ቀን ለአንተ ግሩም አክብሮት ይኖራቸዋል፤ ባለ ታላቅ ግርማ እንደሆንክ የምድር ነገሥታት ሁሉ ያያሉ። 16 ኢየሩሳሌምን እንደገና ትሠራታለህ፣ በዚያም በክብርህ ትገለጣለህ። 17 የቤት አልባ ሕዝብህን ጸሎት ትሰማለህ፣ እንድትረዳቸው ወደ አንተ ሲማጠኑም ዝም አትላቸውም። 18 ያህዌ ሆይ፣ እነዚህን ቃላት ለመጻፍ እወዳለሁ፣ በመጪዎቹ ዓመታት ሰዎች አንተ ያደረግኸውን እንዲያውቁ፣ ገና ያልተወለዱትም እንዲያመሰግኑህ። 19 ከስፍራህ ከሰማይ ቁልቁል መመልከትህን ያውቃሉ፣ ደግሞም በምድር ላይ የሆነውን ማየትህን። 20 የእስረኞችን ለቅሶ እንደምትሰማ፣ “ትገደላላችሁ” ተብሎ የተነገራቸውንም ነጻ እንደምታወጣ ያውቃሉ። 21 ስለዚህ ስላደረግኸው ነገር በኢየሩሳሌም ያሉ ሰዎች ያመሰግኑሃል። 22 ሌሎች በርካታ የሕዝብ ወገኖችና የሌሎች መንግሥታት ዜጎች አንተን ለማምለክ ይሰበሰባሉ። 23 አሁን ግን ገና ወጣት ሆኜ ሳለሁ ደካማ አደረግኸኝ፤ ሕያው ሆኜ ብዙ እንደማልቆይ አስባለሁ። 24 እንዲህ እልሃለሁ፣"አምላኬ ሆይ፣ ከማርጀቴ በፊት አሁን ከምድር አትውሰደኝ! በቀኜ ለዘላለም ሕያው ሁን! 25 ከዘመናት በፊት ምድርን ፈጠርካት፣ በእጆችህም ሰማያትን ሠራህ። 26 ሰማያትና ምድር ይጠፋሉ፣ አንተ ግን ትኖራለህ። ልብስ እንደሚያረጅ እነርሱ ያረጃሉ። ሰው ያረጀ ልብሱን እንደሚተወው ትተዋቸዋለህ፣ ወደ ፊትም አይኖሩም፣ 27 አንተ ግን እንደ ፈጠርካቸው ነገሮች አይደለህም፣ ሁሌም ያው ነህና፣ ከቶም አትሞትም። 28 ልጆቻችን አንድ ቀን በኢየሩሳሌም በሰላም ይኖራሉ፣ ዘሮቻቸውም በሀልዎትህ ፊት ሲኖሩ ይጠበቃሉ"።
Chapter 103
የዳዊት መዝሙር 1 ያህዌን ማምለክ እንዳለብኝ ለራሴ እነግረዋለሁ። እርሱ ቅዱስ ነውና አመሰግነዋለሁ። 2 ያህዌን ማምለክ እንዳለብኝ ለራሴ እነግረዋለሁ፣ ከቶም ያደረገልኝን በጎነት ሁሉ አልረሳም። 3 ኃጢአቴን ሁሉ ይቅር ይላል፣ ከበሽታዎቼም ሁሉ ይፈውሰኛል፤ 4 ከመሞት ይጠብቀኛል፣ ተስፋ እንደ ሰጠኝ በምህረቱና በቸርነቱ ይባርከኛል። 5 በሕይወት ዘመኔ ሁሉ መልካም ነገሮችን ይሰጠኛል። እንደ ንሥር ያጠነክረኛል፣ ወጣትነት እንዲሰማኝም ያደርጋል። 6 በሚበድሉት ሁሉ ላይ ያህዌ በጽድቅ ይፈርዳል። 7 ከረጅም ጊዜ በፊት ዕቅዱን ለሙሴ ገለጠለት፤ ያደረጋቸውንም ታላላቅ ነገሮች ለእኛ ለእስራኤላውያን አባቶች አሳያቸው። 8 ያህዌ መሓሪና ይቅር ባይ ነው፤ ኃጢአት በምናደርግበት ጊዜም ፈጥኖ አይቆጣም፤ ዘወትር በምህረቱ እንደሚወደን ያሳየናል። 9 እኛን መገሰጹን አያቆምም፣ ለዘላለምም አይቆጣም። 10 ስለ ኃጢአታችን የሚገባንን ቅጣት አልሰጠንም። 11 ሰማያት ከምድር እጅግ ከፍ ያሉ ናቸው፣ ለሚያከብሩት ሁሉ የያህዌ ምህረትም እንደዚሁ ታላቅ ነው። 12 የኃጢአተኝነታችንን ወቀሳ አስወገደ፣ ምስራቅ ከምዕራብ እንደሚርቅም ከእኛ አራቀው። 13 ልክ ወላጆች ለልጆቻቸው እንደሚራሩ፣ ያህዌም ለሚያከብሩት ይራራል። 14 ሰውነታችን ምን እንደሚመስል እርሱ ያውቃል፤ ከዐፈር እንደፈጠረንም ያስታውሳል፣ እርሱን ደስ ከሚያሰኘው ፈጥነን እንደምንሰናከል ጭምር። 15 እኛ ሰዎች ለዘላለም አንኖርም፤ እንደሚጠወልግና እንደሚደርቅ ሣር ነን። ለጥቂት ጊዜ እንደሚያብቡ፣ 16 ከዚያም ሙቅ ንፋስ ሲነፍስባቸው እንደሚጠፉ አበቦች ነን፤ እንደገና የሚያያቸው እንደማይኖር። 17 ያህዌ ግን እንደ ተስፋ ቃሉ፣ በሚያከብሩት ሁሉ ላይ ምህረቱ ለዘላለም ነው። ቸርነቱ በልጆቻችንና በልጅ ልጆቻችን ላይ ይሆናል 18 ሊባርካቸው ከእነርሱ ጋር የገባውን ኪዳን ለሚጠብቁ ሁሉ፣ እንዲፈጽሙት የነገራቸውን ለሚያደርጉ እንዲሁ ያደርግላቸዋል፣ ትዕዛዙንም ለሚጠብቁት ሁሉ። 19 ያህዌ ዙፋኑን እንደ ንጉሥ በሚገዛበት በሰማይ አድርጓል፤ እዚያ ሆኖ በሁሉም ነገር ላይ ይገዛል። 20 የያህዌ የሆናችሁ መላእክቱ አመስግኑት! እናንተ ትዕዛዙን የምትፈጽሙ ኃያላን ፍጥረታት ናችሁ፤ የሚያዛችሁንም ትታዘዛላችሁ። 21 የምታገለግሉትና ፈቃዱን የምትፈጽሙ እናንተ የመልአክ ሠራዊት ያህዌን አመስግኑ። 22 ያህዌ የፈጠራችሁ ፍጥረታት በሙሉ አመስግኑት፤ እርሱ በሚገዛበት በሁሉ ስፍራ አመስግኑት! እኔም ደግሞ ያህዌን አመሰግናለሁ!
Chapter 104
1 ያህዌን ማምለክ እንዳለብኝ ለራሴ እነግረዋለሁ። አምላኬ፣ ያህዌ ሆይ፣ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ! በልብሰ መንግሥቱ እንዳለ ንጉሥ፣ ክብርና ሞገስ በዙሪያህ አለ! 2 ብርሃንን ፈጠርክ፣ በስተኋላውም ተደበቅህ። ሰው ድንኳንን እንደሚዘረጋ መላውን ሰማይ ዘረጋህ። 3 ቤተ መንግሥትህን በደመናት ውስጥ መሠረትህ። እንደ ሠረገላዎች ይሸከሙህ ዘንድ ደመናዎችን ፈጠርህ። 4 ነፋሳትን እንደ መልዕክተኞችህ፣ የእሳት ነበልባሎችንም እንደ አገልጋዮችህ አደረግህ። 5 ምድርን በመሠረቱ ላይ አጽንተህ አቆምህ፣ በፍጹም መነቃነቅ እንዳይችል። 6 ከዚያም እንደ ብርድ ልብስ ምድርን በጎርፍ ሸፈንክ፤ ውሃም ተራሮችን ሸፈነ። 7 ውሃውን በገሰጽከው ጊዜ ግን ውቅያኖሶች በአንድ ቦታ ተከማቹ፤ ድምጽህ እንደ ነጎድጓድ ተናገረ፣ ውኆቹም ፈሰሱ። 8 ከውሃው ተራሮች ተገለጡ፣ ሸለቆዎችም ወደ ወሰንክላቸው መሠረት ሰመጡ። 9 እንዳያልፉ ለውቅያኖሶች ድንበርን አበጀህላቸው፤ ውኆቻቸው ዳግመኛ መላውን ምድር ከቶ እንዳይሸፍኑ። 10 ውሃ ወደ ጠባቦቹ ሸለቆዎች እንዲፈስ ምንጮችን አደረግህ፤ ውኆቻቸው በተራሮች መሐል ቁልቁል እንዲወርድ። 11 እንስሳቱ ሁሉ እንዲጠጡ እነዚያ ምንጮች ውሃን ያዘጋጁላቸዋል፤ የሜዳ አህዮች ውሃውን ይጠጣሉ፣ ወደፊትም አይጠሙም። 12 ወፎች በምንጮቹ አቅራቢያ ጎጆዎቻቸውን ይሠራሉ፣ በዛፎቹ ቅርንጫፎች መካከልም ይዘምራሉ። 13 በተራሮቹ ላይ ከሰማይ ዝናብን ትልካለህ፣ ምድርንም በፈጠርካቸው ብዙ መልካም ነገሮች ትሞላለህ። 14 ላሞች እንዲበሉት ሣርን ታበቅላለህ፣ እጽዋትንም ለሰዎች። በዚህ መንገድ እንስሶችና ሰዎች ከምድር ከሚበቅለው ምግባቸውን ያገኛሉ። 15 ወይን አዘጋጅተን እንድንጠጣና ደስ እንዲያሰኘን የወይንን ተክል እናገኛለን፤ ፊታችንን እንዲያበራ የወይራ ዘይት፣ ብርታት የሚሰጠንን እንጀራ ለማዘጋጀት ደግሞ ጥራጥሬን። 16 ያህዌ ሆይ፣ ዛፎችህን እንዲያጠጡ ብዙ ዝናብ ትልካለህ፣ በሊባኖስ የተከልካቸውን የዝግባ ዛፎች። 17 በእነዚያ ዛፎች ላይ አዕዋፍ ጎጆዎቻቸውን ይሠራሉ፣ ሽመላዎችም ጎጆዎቻቸውን በጥድ ዛፎች ውስጥ ይሠራሉ። 18 የሜዳ ፍየሎች ከፍ ባሉ ተራሮች ላይ ይኖራሉ፣ ሽኮኮዎችም በዐለቶቹ ውስጥ። 19 ያህዌ ሆይ፣ የበዓላቶቻችንን ጊዜ እንዲያመለክተን ጨረቃን ፈጠርክ፣ ምን ጊዜ መጥለቅ እንዳለበት የሚያውቀውን ፀሐይንም ፈጠርከው። 20 ጨለማን ታመጣለህ፣ ምሽትም ይሆናል፣ በዚያን ጊዜ በጫካ ውስጥ ያሉ እንስሳት ሁሉ ምግባቸውን ፍለጋ ይርመሰመሳሉ። 21 በምሽት የአንበሳ ግልገሎች የሚያድኑትን እንስሳ በመፈለግ ይጮኻሉ፣ ነገር ግን ምግባቸውን እንድትሰጣቸው አንተን ተስፋ ያደርጋሉ። 22 ፀሐይ ስትወጣም ወደ ዋሻዎቻቸው ተመልሰው ይተኛሉ። 23 ቀን በሆነ ጊዜ ሰዎች ወደየሥራቸው ይሰማራሉ፤ እስኪመሽ ድረስም ይሠራሉ። 24 ያህዌ ሆይ፣ አንተ ብዙ ልዩ ልዩ ዓይነት ነገሮችን አድርገሃል! እነዚያን ሁሉ ስትፈጥር አንተ እጅግ ጥበበኛ ነህ።ምድር በፈጠርካቸው ፍጥረታት ተሞልቷል። 25 እጅግ ሰፊ የሆነውን ውቅያኖስ እናያለን! እርሱም በብዙ ዓይነት ሕያዋን ፍጥረታት፣ በታላላቆችና በታናናሾች የተሞላ ነው። 26 የሚመላለሱባቸውን መርከቦች እናያለን! በባህሩ ላይ እንዲያንቦጫርቅ የፈጠርከውን ታላቁን አስፈሪ የባህር ፍጡር እናያለን። 27 እነዚህ ፍጥረታት ሁሉ አንተን ተስፋ ያደርጋሉ፣ የሚፈልጉትን ምግብ አንተ እንድትሰጣቸው።። 28 የሚፈልጉትን ምግብ በምትሰጣቸው ጊዜ ይሰበስቡታል። በእጅህ ያለውን ትሰጣቸዋለህ፣ ይመገቡታል፣ ይረካሉም። 29 ምግብ ባትሰጣቸው ግን፣ ይደነግጣሉ። መተንፈስ እንዲያቆሙ ስታደርጋቸውም ይሞታሉ፤ አካላቸው ይበሰብስና ተመልሰው ዐፈር ይሆናሉ። 30 ዐዲስ የተወለዱ ፍጥረታት መተንፈስ እንዲጀምሩ ስታደርጋቸው መኖር ይጀምራሉ፤ በምድር ላይ ላለ ፍጥረት ሁሉ ዐዲስን ሕይወት ትሰጣለህ። 31 የያህዌ ክብር ለዘላለም ይኑር። እርሱ ስለፈጠራቸው ነገሮች ሁሉ ደስ ይበለው። 32 ምድርን ወደ እርሷ በመመልከቱ ብቻ እንድትንቀጠቀጥ ያደርጋታል! ተራሮችን በመንካት ብቻ እሳትና ጢስ እንዲያወጡ ያደርጋቸዋል! 33 በሕይወት እስካለሁ ድረስ ለያህዌ እዘምራለሁ። እስክሞትም ድረስ አምላኬን አመሰግነዋለሁ። 34 ስለ እርሱ ባሰብኳቸው በእነዚህ ነገሮች ሁሉ ያህዌን ደስ ይበለው፣ እርሱን በማወቄ ደስ ይለኛልና። 35 ሆኖም፣ ኃጢአተኞች ከምድር ይጥፉ፤ ከእንግዲህ አመጸኞች በእርስዋ አይኑሩ! እኔ ግን ያህዌን አመሰግናለሁ! እርሱን አመስግኑት!
Chapter 105
1 ያህዌን አመስግኑ፤ እጅግ ታላቅ መሆኑንም ለሌሎች ንገሩ! ያደርገውን በምድር ላይ ላሉት ሁሉ አውሩ! 2 ዘምሩለት! በምትዘምሩለት ጊዜም አመስግኑት፤ ስለ አስደናቂ ተአምራቶቹ ለሌሎች ንገሯቸው። 3 እርሱ ቅዱስ መሆኑን ስለምታውቁ ደስ ይበላችሁ! ያህዌን የምታመልኩ ሕዝቦች ሐሴት አድርጉ! 4 እንዲረዳችሁና ብርታትን እንዲሰጣችሁ ያህዌን ጠይቁት፣ ዘወትር ከእርሱ ጋር መሆንንም ፈልጉ! 5 - 6 የእግዚአብሔር አገልጋይ የአብርሃም ዘር የሆናችሁ ሕዝቦች፣ እግዚአብሔር የመረጠው የያዕቆብ ዘሮች፣ ስላደረጋቸው ድንቅ ነገሮች ሁሉ አስቡ፤ ተአምራቶችን አድርጓል፣ ጠላቶቻችንንም ሁሉ ቀጥቷቸዋል። 7 ያህዌ እርሱ አምላካችን ነው። በምድር በሚኖሩ ሰዎች ሁሉ ላይ ይገዛል፣ ይፈርዳልም። 8 የገባውን ኪዳን ከቶ አይረሳም፤ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ቃል ኪዳንን አድርጓል። 9 ያ ከአብርሃም ጋር ያደረገው ኪዳን ነው፣ ያንኑ ኪዳን ለይስሐቅ ደገመለት። 10 በኋላም ለያዕቆብ ደግሞ አጸናለት፣ ለእስራኤልም ሕዝብ ለዘላለም የሚኖር ኪዳን አድርጎ። 11 እርሱ፣ "የከነዓንን ምድር እሰጥሃለሁ፤ ለዘላለም ለአንተና ለዘሮችህ ይሆናል" ብሎት ነበር። 12 ይህንን ያለው እነርሱ ጥቂቶች ብቻ በነበሩበት ጊዜ ነው፣ እንደ እንግዳ በምድሪቱ ላይ ታናሽ የሕዝብ ወገን በነበሩ ጊዜ። 13 እነርሱ ከአንዱ ስፍራ ወደ ሌላው ስፍራ ተንከራተቱ፣ ከአንዱ መንግሥትም ወደ ሌላው። 14 ሌሎች እንዲጨቁኗቸው ግን አልፈቀደላቸውም። እነዚያን ነገሥታት እንዲህ በማለት አስጠነቀቃቸው፣ 15 "በመረጥኩት ሕዝብ ላይ ክፉ እንዳታደርጉ! ነቢያቴንም እንዳትጎዷቸው!" 16 በከነዓን ላይ ድርቅን ላከ፣ ሕዝቡም የሚበላውን አጣ። 17 ስለዚህ የእርሱ ሕዝብ ወደ ግብፅ ሔደ፣ አስቀድሞ ግን አንድ ሰው ወደዚያ ላከ። ላባርነት ተሽጦ የነበረውን ዮሴፍን ላከው። 18 በኋላም፣ ዮሴፍ በግብፅ በውኅኒ እያለ፣ እግሮቹን በሚላላጡበት በእግር ብረት ውስጥ አስገቧቸው፣ በአንገቱም ዙሪያ የብረት ማነቆ አደረጉበት። 19 ዮሴፍ በወኅኒ ነበር፣ የተናገረው ቃል እስኪፈጸምና እውነትነቱ እስኪታወቅ ድረስ። 20 የግብፅ ንጉሥ ጠራው፣ ነጻም እወጣው፤ ይህ ገዢ ዮሴፍን ከወኅኒ ለቀቀው። 21 ከዚያም በንጉሡ ቤት ባለው ሁሉ ላይ ጠባቂ እንዲሆን ሾመው፣ ንጉሡ ያለውን ሁሉ እንዲጠብቅለት። 22 ዮሴፍ የንጉሡን የተከበሩ አገልጋዮች እንዲያዛቸው ተፈቀደለት፣ ዮሴፍ የሚፈልግባቸውን ማንኛውንም ነገር እንዲያደርጉ፣ ለግብፃውያን ሊያደርጉት የሚገባቸውን ነገር እንኳን ለንጉሡ አማካሪዎች እስኪነግራቸው ድረስ። 23 በኋላም የዮሴፍ አባት ያዕቆብ ወደ ግብፅ ደረሰ። በካም ዘሮች ምድር ላይ እንደ መጻተኛ ሆኖ ኖረ። 24 ከአመታት በኋላም ያህዌ የያዕቆብን ዘር ቁጥራቸውን አበዛ። በመሆኑም ጠላቶቻቸው ግብፃውያን እስራኤላውያን እጅግ መጠናከራቸውን ተገነዘቡ። 25 ስለዚህ የግብፅ ገዢዎች በእስራኤላውያን ላይ እንዲነሱባቸው አደረገ፣ እነርሱም ሕዝቡን መጨቆን ጀመሩ። 26 ያህዌ ግን እገልጋዩን ሙሴን ላከው፣ ከእርሱም ጋር ያህዌ አገልጋዩ እንዲሆን የመረጠውን የሙሴን ታላቅ ወንድም አሮንን። 27 እነዚህ ሁለቱ በግብፃውያኑ መካከል የሚገርሙ ትአምራቶችን አደረጉ፣ የካም ትውልድ በሚኖርበት በዚያ ምድር። 28 ግብፃውያን ምንም ማየት እንዳይችሉ ያህዌ ጨለማን ላከ፣ ሙሴና አሮን እስራኤላውያን ግብፅን ለቀው ይወጡ ዘንድ እንዲፈቅዱላቸው ባዘዙ ጊዜ የግብፅ ገዢዎች ግን ለመታዘዝ እምቢ አሉ። 29 ያህዌ በግብፅ ያለው ውሃ ሁሉ ደም እንዲሆን አደረገ፣ ያንን ማድረጉም ዓሳዎቹን ሁሉ ለሞት ዳረጋቸው። 30 ከዚያም ምድሪቱ በጓጉንቸሮች እንድትሞላ አደረጋት፤ ወደ ንጉሡና ባለሥልጣናቱ መኝታ ቤት እንኳ ሳይቀር ጓጉንቸሮቹ ገብተው ነበር። 31 ከዚያም ያህዌ ዝንቦች እንዲመጡ አዘዘ፣ የዝንብ መንጋም በግብፃውያን ላይ ወረደባቸው፣ የትንኝ መንጋም ደግሞ በሀገሪቱ ሁሉ ላይ። 32 ዝናብን ከመላክ ይልቅ ያህዌ አስፈሪ በረዶ ላከባቸው፣ በምድሪቱ ሁሉ ላይ መብረቅን አወረደ። 33 በረዶው የወይን ተክሎቻቸውንና የበለስ ዛፎቻቸውን አወደመው፣ ሌሎቹንም ዛፎች በሙሉ ሰባበረ። 34 አንበጣዎች እንዲመጡ አዘዘ፣ መንጋዎቻቸውም መጡ፤ ሊቆጥሩአቸውም የማይቻሉ ነበሩ። 35 አንበጣዎቹም በምድሩ ላይ የነበረውን ለምለም ሁሉ በሉት፣ ሰብሉንም ሁሉ አወደሙ። 36 ያህዌ በግብፃውያን ቤት ሁሉ የመጀመሪያ የሆነውን ወንድ ልጅ ገደለ። 37 ከዚያም የእስራኤልን ሕዝብ ከግብፅ አወጣቸው፤ እነርሱም ግብፃውያን የሰጧቸውን የወርቅና የብር ጌጣ ጌጥ ከባድ ሸክም ተሸክመው ነበር። ከእነርሱ በመታመሙ ምክንያት ወደ ኋላ የቀረ አንድም አልነበረም። 38 እስራኤላውያን ለቀው በወጡ ጊዜ ግብፃውያን ደስ ብሏቸው ነበር፣ እስራኤላውያኑን እጅግ ፈርተዋቸው ነበርና። 39 ከዚያም እስራኤላውያንን እንዲጋርዳቸው ያህዌ ደመናን ዘረጋላቸው፤ እርሱም በሌሊት እንዲያበራላቸው ከሰማይ እንደ ታላቅ እሳት ይሆንላቸው ነበር። 40 በኋላም እስራኤላውያን የሚበሉትን ሥጋ ጠየቁ፣ ያህዌም የድርጭትን መንጋ ሰደደላቸው፣ በየጠዋቱም ብዙ መና ከሰማይ ሰጣቸው። 41 አንድ ቀን ዐለትን ሰነጠቀና ይጠጡ ዘንድ ውሃ ወጣላቸው፤ እርሱም በዚያ ምድረ በዳ እንደ ወንዝ ፈሰሰላቸው። 42 ይህንን ያደረገውም ለአገልጋዩ ለአብርሃም የሰጠውን ቅዱሱን ኪዳኑን ስላሰበ ነው። 43 ስለዚህ ሕዝቦቹ ከግብፅ ባወጣቸው ጊዜ ደስ አላቸው፤ እነዚህ የመረጣቸው ሕዝቦቹ በሚጓዙበት ጊዜ በደስታ እልል ይሉ ነበር። 44 እርሱም ከነዓናውያን ይኖሩበት የነበረውን ምድር ሰጣቸው፣ ሀብታቸውንም ሁሉ እስራኤላውያኑ ወሰዷቸው። 45 ሕዝቡ እንዲያደርጉት ያዘዛቸውን ነገሮች ሁሉ ያደርጉ ዘንድ፣ እነዚህን ሁሉ ያህዌ አደረገ። ያህዌን አመስግኑ!
Chapter 106
1 ያህዌ ይወደስ! ያህዌ ይወደስ፤ ምክንያቱም ለእኛ መልካም ነገሮችን አድርጎልናል። 2 ያህዌ በርካታ ታላላቅ ነገሮችን ከማድረጉ የተነሣ ማንም ያህዌ ያደረጋቸውን ታላላቅ ነገሮች ሁሉ መናገር አይችልም፤ ማንም እርሱን በበቁ ሁኔታ ሊወድስ አይችልም። 3 ፍትሕን የሚያደርጉ ዘወትር ትክክለኛውን ነገር የሚፈጽሙ ደስተኞች ናቸው። 4 ያህዌ ሆይ ሕዝብህን ስትረዳ ለእኔም ቸርነት አድርግልኝ። ስትታደጋቸው እርዳኝ። 5 ሕዝብህ እንደገና ሲበለጽጉ እንዳይ ፍቀድልኝ። የአገርህ የእስራኤል ሕዝብ ሁሉ እንደገና ደስተኛ ሲሆኑ ከእነርሱ ጋር ደስተኛ እንድሆን ፍቀድልኝ! የአንተ ከሆኑት ሌሎች ሁሉ ጋር ላወድስህ እፈልጋለሁ። 6 እኛና አባቶቻችን ኃጢአትን ሠርተናል። እርጕምና ክፉ የሆነውን ነገር አድርገናል። 7 አባቶቻችን በግብጽ በነበሩ ጊዜ ያህዌ ላደረጋቸው አስደናቂ ነገሮች ትኵረት አልሰጡም። በታማኝነት እንደሚወዳቸው ለእነርሱ ያሳየባቸውን በርካታ ጊዜያት ረሱ በዚያ ፈንታ በቀይ ባሕር በነበሩ ጊዜ ከሌላ ከየትኛውም አምላክ በሚበልጠው በእግዚአብሔር ላይ ዐመጹ። 8 እርሱ ግን ኃያል መሆኑን ሊያሳያቸው እንዲችል ለገዛ ራሱ ስም ሲል ታደጋቸው። 9 የቀይ ባሕርን ገሠጸ፤ እርሱም ደረቀ። ከዚያም አባቶቻችንን ሲመራቸው እንደ ምድረ በዳ ደረቅ የሆነ ያህል በመካከሉ እየተራመዱ አለፉ። 10 በዚያ መንገድ ከጠላቶቻቸው ኃይል ታደጋቸው። 11 በዚያን ጊዜ ጠላቶቻቸው በቀይ ባሕር ውሃ ውስጥ ሰጠሙ። ከእነርሱ አንድም አልቀረም። 12 ያ በሚሆነበት ጊዜ አባቶቻችን ያህዌ ሊያደርግላቸው ቃል የገባላቸውን በእውነት እንዳደረገላቸው አመኑ። እርሱንም ለማወደስ ዘመሩ። 13 ነገር ግን ያደረገላቸውን በቶሎ ረሱ። ያህዌ እንዲያደርጉት የሚፈልገውን ለማወቅ ሳይጠባበቁ ነገሮችን ያደርጉ ነበር። 14 ቀደም ሲል በግብጽ የሚበሉትን ዓይነት ምግብ በጋለ ስሜት ፈለጉ። እግዚአብሔር ይቀጣቸው እንደሆነ ወይም እንዳልሆነ ለማወቅ ክፉ ነገሮችን አደረጉ። 15 እርሱም የጠየቁትን ነገር ሰጣቸው። ነገር ግን የሚጎዳቸውንም አሰቃቂ በሽታም አመጣባቸው። 16 በኋላ ላይ አንዳንድ ሰዎች በሙሴና ካሕን በመሆን ያህዌን ለማገልገል በተለየው በታላቅ ወንድሙ በአሮን ላይ ሲቀኑ፣ 17 መሬቷ ተከፍታ ዳታንን ዋጠች። አቤሮንን እና ቤተሰቡንም ቀበረች። 18 እግዚአብሔርም እሳት ከሰማይ ላከ፤ እነርሱን የሚደግፉትን ክፉ ሰዎች ሁሉ አቃጠለ። 19 ከዚያም እስራኤላውያን መሪዎች በሴና ተራራ የወርቅ ጥጃ ሐውልት ሠርተው አመለኩት። 20 የከበረውን አምላካችንን በማምለክ ፈንታ ሣር የሚበላ በሬ ሐውልት ማምለክ ጀመሩ! 21 በግብፅ ባደረጋቸው ታላላቅ ተአምራት የታደጋቸውን አምላክ ረሱ። 22 በግብፅ ያደረገላቸውን አስደናቂ ነገሮች በቀይ ባሕርም የፈጸመላቸውን አስገራሚ ነገሮች ረሱ። 23 ከዚያ የተነሣ እግዚአብሔር እስራኤላውያንን እንደሚያስወግዳቸው ተናገረ። 24 ከዚያ በኋላ አባቶቻችን ወደ ከነዓን ውብ ምድር ለመግባት እምቢ አሉ። ምክንያቱም ቃል እንደገባው እዚያ ይኖሩ ከነበሩት ሰዎች ምድሪቱን እንዲወስዱ እግዚአብሔር እንደሚያስችላቸው አላመኑም። 25 ድንኳኖቻቸው ውስጥ ቆይተው አጕረመረሙ። እግዚአብሔር ማድረግ የሚገባቸውን የነገራቸውን ትኵረት አልሰጡትም። 26 በመሆኑም አጠንክሮ ነገራቸው፤ በምድረ በዳ እዚያው እንዲሞቱ እንደሚያደርጋቸው 27 ዝርያዎቻቸውንም በእርሱ በማያምኑ የሌላ አገራት ሕዝቦችና ቡድኖች እንደሚበታትናቸውና በእነዚያም ምድሮች እንዲሞቱ እንደሚያደርግ፤ 28 በኋላ ላይ የእስራኤል ሰዎች በፌኦር ተራራ የበኣልን ጣኦት ማምለክ ጀመሩ። ለበኣልና ለእነዚያ ሕይወት የለሽ አማልክት የተሠዋውን ሥጋ በሉ። 29 ካደረጉት ነገር የተነሣ ያህዌ እጅግ ተቆጣ። እንደገናም አሰቃቂ በሽታ እንዲያጠቃቸው ላከባቸው። 30 ነገር ግን ፊንሐስ ተነሥቶ ያለልክ የበደሉትን ቀጣቸው። በውጤቱም መቅሰፍቱ ቆመ። 31 ፊንሐስ ያደረገውን የጽድቅ ሥራ ሰዎች አስታውሰዋል፤ በሚመጡ ዘመናትም ሰዎች ያስታውሱታል። 32 ከዚያም በመሪባ ምንጮች አባታችን እንደገና እግዚአብሔርን አስቆጡ። በውጤቱም ሙሴ ችግር ውስጥ ገባ። 33 ሙሴ እጅግ እንዲቆጣ አደረጉት። እርሱም ከንቱ የሆኑ ነገሮችን ተናገረ። 34 አባቶቻችን [እግዚአብሔር] እንዲያደርጉ የነገራቸውን ሌሎች ሕዝቦችን አላጠፉም 35 ይልቁንም ወንዶቹ የእነዚያን ሕዝቦች ሴትች ወሰዱ። እነዚያ ሰዎች የሚያደርጓቸውን ክፉ ነገሮች ማድረግ ጀመሩ። 36 አባቶቻችን የእነዚያን ሰዎች ጣኦታት አመለኩ። ይህም መጥፋትን እስከተለባቸው። 37 ከእስራኤላውያን አንዳንዶቹ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻቸውን እነዚያ ጣኦታት ለሚወክሏቸው አጋንንት መስዋዕት አድርገው አቀረቡ። 38 ምንም ጥፋት ያልፈጸሙትን ልጆች ገድለው ለከነዓን ጣኦታት መስዋዕት አድርገው አቀረቧቸው። በውጤቱም የከነዓን ምድር በእነዚያ ግድያዎች ተበከለች። 39 በተግባራቸውም እግዚአብሔር ሊቀበላቸው እንዳይችል አደረጉት። ምክንያቱም እግዚአብሔርን ብቻ በታማኝነት አላመለኩም። ከባሎቻቸው ጋር ብቻ በመተኛት ፈንታ ከሌሎች ወንዶች ጋር የሚተኙ ሴቶችን መሠሉ። 40 በመሆኑም ያህዌ በሕዝቡ እጅግ ተቆጣ። ሙሉ በሙሉም ተጸየፋቸው። 41 በውጤቱም በእርሱ የማያምኑ ሕዥቦች እንዲያሸንፏቸው ፈቀደላቸው። አባቶቻችንን የሚጠሏቸው እነርሱን ይገዟቸው ጀመር። 42 ጠላቶቻቸው ጨቆኑአቸው፤ ሙሉ በሙሉ በጠላቶቻቸው ቁጥጥር ሥር እንዲሆኑም አደረጓቸው። 43 ብዙ ጊዜ ያህዌ ታደጋቸው፤ እነርሱ ግን በእርሱ ላይ ማመጻቸውን ቀጠሉ። ከፈጸሟቸው ኃጢአቶች የተነሣም በመጨረሻ ተደመሰሱ። 44 ያህዌ ግን ወደ እርሱ በሚጮኹበት ጊዜ ዘወትር ይሰማቸው ነበር። በተጨነቁም ጊዜ አዳመጣቸው። 45 ስለ እነርሱ ብሎ እነርሱን ለመባረክ ስላደረገው ቃል ኪዳን አሰበ። ምክንያቱም እነርሱን እጅግ በጣም መውደዱን ከቶ አላቆመም እነርሱን ይበልጥ የመቅጣት ሃሳቡን ለወጠ። 46 እስራኤላውያንን ወደ ባቢሎን የወሰዷቸው ሰዎች ሁሉ እንዲያዝኑላቸው አደረገ። 47 አምላካችን ያህዌ ሆይ፣ ታደገን እንድናመሰግንህና በደስታ እንድንወድስህ ከእነዚያ ሕዝቦች መካከል ወደ እስራኤል መልሰህ አምጣን። 48 እኛ እስራኤላውያን የምናመልከው አምላክ ያህዌ ይወደስ አሁንና ለዘለዓለም ወድሱት! ሕዝቡ ሁሉ መስማማት ይገባቸዋል! ያህዌ ይወደስ!
Chapter 107
1 ለያህዌ ምስጋና አቅርቡ፤ ምክንያቱም ለእኛ ሁልጊዜ መልካም ነገሮችን ያደርግልናል! ቃል እንደገባልን ለእኛ ያለው የታማኝነት ፍቅሩ ለዘለዓለም ይኖራል! 2 ያህዌ ያዳናቸው ሰዎች ከጠላቶቻቸው እንደታደጋቸው ለሌሎች መንገር ይገባቸዋል። 3 ወደ ብዙ አገሮች ተግዘው የነበሩትን ሰብስቦአል፤ ከምሥራቅና ከምዕራብ፣ ከሰሜንና ከደቡብ በአንድነት ሰብስቦአችኋል። 4 ከእነዚያ አገሮች ከተመለሱት አንዳንዶቹ በምድረ በዳ ተንከራተቱ ጠፍተውም ነበር፤ የሚኖርባቸውንም ቤቶች አላገኙም። 5 ተርበውና ተጠምተው ነበር፤ እጅግም ተስፋ ቆርጠው ነበር። 6 በችግር ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ወደ ያህዌ ተጣሩ። እርሱም ከመጨነቃቸው ታደጋቸው። 7 ሊኖሩባቸው ወደሚችሉባቸው የከነዓን ከተሞች በደህና ሁኔታ በሚሄዱበት ቀጥተኛ መንገድ ላይ መራቸው። 8 በታማኝነት ስለወደዳቸውና ለሰዎች ስለሚያደርጋቸው አስደናቂ ነገሮች ያህዌን ማወደስ ይገባቸዋል። 9 ለተጠሙ ሰዎች የሚጠጡትን ብዙ ውሃ ይሰጣቸዋል። ለተራቡም ሰዎች የሚበላ በርካታ መልካም ነገሮች ይሰጣል። 10 አንዳንዶቹ ድቅድቅ ጨለማ እስር ቤቶች ውስጥ ነበሩ፤ እጆቻቸውና እግሮቻቸው ላይ ከታሰሩት ሰንሰለቶች የተነሣ የሚሰቃይ እስረኞች ነበር። 11 በእግዚአብሔር መልእክት ላይ ያመጹ ከመሆናቸው የተነሣ እስር ቤት ውስጥ ነበሩ። ከሌሎች አማልክት ሁሉ በሚልቀው በእግዚአብሔር የተሰጠውን ምክር ከመናቃቸው የተነሣ እዚያ ነበሩ። 12 አካላቸው ክአድካሚ ልፋት የተነሣ የዛለው ለዚያ ነው። በወደቁ ጊዜ የሚረዳቸው ማንም ሰው አልነበረም። 13 በችግር ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ወደ ያህዌ ተጣሩ። እርሱም ከመጨነቃቸው ታደጋቸው። 14 በእጆቻቸውና በእግሮቻቸው ላይ የነበሩትን ሰንሰለቶች ሰባብሮ ከእነዚያ ድቅድቅ ጨለማ እስር ቤቶች አወጣቸው። 15 በታማኝነት ስለወደዳቸውና ለሰዎች ስለሚያደርጋቸው አስደናቂ ነገሮች ያህዌን ማወደስ ይገባቸዋል። 16 ከናስ የተሠሩትን የእስር ቤት መዝጊያዎች ሰባብሮአል፤ ከብረት የተሠሩትን የእስር ቤት ዘንጎች ቆርጦአል። 17 አንዳንዶች በሞኝነት በእግዚአብሔር ላይ ዐመፁ፤ ለኃጢአታቸው መከራን ተቀበሉ። 18 ማናቸውንም ዓይነት ምግብ ለመብላት አልፈለጉም ነበር፤ ወደ ሞት አፋፍ ተቃርበው ነበር። 19 በችግር ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ወደ ያህዌ ተጣሩ። እርሱም በመጨነቃቸው ታደጋቸው። 20 እንዲፈወሱ ሲያዝዝ ተፈወሰ፤ ከመሞትም አዳናቸው። 21 በታማኝነት ስለወደዳቸውና ለሰዎች ስለሚያደርግላቸው አስደናቂ ነገሮች ያህዌን ማወደስ ይገባቸዋል። 22 አመስጋኝ መሆናቸውን ለማሳየት የሚቀርቡ ስጦታዎችን ሊሰጡት ይገባል። ስለ ሠራቸው ተአምራት በደስታ ሊዘምሩለትም ይገባል። 23 አንዳንዶቹ በመርከቦች ተጓዙ፣ እጅግ በራቁ ከተሞች የትለያዩ ዕቃዎችን ይሸጡ ነበር። 24 በመርከብ እየተጓዙም ያህዌ ያከናወናቸውን ተአምራትም በጥልቅ ባሕር በነበሩበት ጊዜ ያደረጋቸውን አስደናቂ ነገሮች አዩ። 25 ለነፋሳት ትዕዛዝ ሰጠ፤ እነርሱም ኃይለኛ ሆነው ከፍተኛ ሞገዶች አስነሱ። 26 ይጓዙባቸው የነበሩት መርከቦች ወደ አየር ላይ ከፍታ ተወረወሩ፤ ከዚያም በከፍተኛዎቹ ሞገዶች መካከል ወደ ታችኛ ክፍሎች ሰመጡ። ያኔ መርከበኞቹ ደንግጠው ጮኹ። 27 ተደነቃቅፈው እንደ ሰከሩ ሰዎች ተንገዳገዱ። የሚያደርጉትንም አያውቁም ነበር። 28 በችግር ውስጥ በነበሩበት ጊዜ ወደ ያህዌ ተጣሩ። እርሱም በመጨነቃቸው ታደጋቸው። 29 ማዕበሉን ጸጥ አደረገው፤ ሞገዱንም ዝም አሰኘው። 30 ፀጥታ በሰፈነ ጊዜ እጅግ ደስ አላቸው። ያህዌም እንደ ተመኙት ወደ አንድ ወደብ በደህና አደረሳቸው። 31 በታማኝነት ስለወደዳቸውና ለሰዎች ስለሚያደርጋቸው አስደናቂ ነገሮች ያህዌን ማወደስ ይገባቸዋል። 32 የእስራኤል ሕዝብ በአንድነት በተሰበሰቡ ጊዜ በመካከላቸው ሊያወድሱት ይገባል። በአገሪቱ መሪዎች ፊት ሊያወድሱት ይገባል። 33 አንዳንድ ጊዜ ያህዌ ወንዞች እንዲደርቁ ያደርጋል። በውጤቱም ምድሪቷ በረሃ ትሆናለች፤ የውሃ ምንጮችም ደረቅ መሬት ይሆናሉ። 34 አንዳንድ ጊዜ ብዙ ሰብል ያስገኘችውን ምድር ጨዋማ ጠፍ መሬት ያደርጋታል። በውጤቱም ሰብሎችን አያመርቱም። ያንን የሚያደርገው እዚያ የሚኖሩት ሰዎች እጅግ ክፉ ከመሆናቸው የተነሣ ነው። 35 አንዳንድ ጊዜ ግን በምድረ በዳ ውስጥ የውሃ ኩሬዎች ብቅ እንዲሉ ያደርጋል። እጅግ በደረቀ ምድርም ምንጮች እንዲፈስሱ ያደርጋል። 36 እዚያ እንዲኖሩና እዚያ ከተማዎችን እንዲገነቡ የተራቡ ሰዎችን ወደዚያ ምድር ያመጣል። 37 በማሳዎቻቸው ላይ ዘሮችን ይዘራሉ፤ ብዙ የወይን ሰብል የሚያስገኙ የወንይ ተክሎችን ይተክላሉ። 38 ሕዝቡን ይባርካቸዋል፤ ሴቶቹም በርካታ ልጆችን ይወልዳሉ። ብዙ የከብት መንጋዎችም ይኖራቸዋል። 39 የሕዝቦቹ ቁጥር እያነሰ ሲሄድና በጠላቶቻቸው በመጨቆን ሲዋረዱ እንዲሁም መከራ ሲደርስባቸው 40 የጨቆኗቸውን መሪዎቻቸውን ያህዌ ናቃቸው፤ መንገዶች በሌሉበት ምድረ በዳ እንዲንከራተቱ አደረጋቸው። 41 ነገር ግን ምስኪን ሰዎችን በመከራ ውስጥ ከመሆን ይታደጋቸዋል። ቤተሶቻቸውን እንደ በግ መንጋዎች ቁጥር እንዲጨምር ያደርጋል። 42 በትክክል የሚኖሩ ሰዎች እግዚአብሔር እነዚህን ነገሮች ሲያደርግ ያያሉ፤ ደስም ይላቸዋል። 43 ጥበበኛ የሆኑ ሰዎች ስለ እነዚህ ነገሮች በጥንቃቄ ማሰብ ይገባቸዋል። ያህዌ በታማኝነት እንደሚወዳቸው ለማሳየት ያደረጋቸውን ነገሮች ሁሉ ማጤን ይገባቸዋል።
Chapter 108
1 እግዚአብሔር ሆይ በአንተ ፍጹም እተማመናለሁ። አንተን ለማወደስ እዘምራለሁ። ከእንቅልፍ መንቃትና አንተን ማወደስ ክብር ነው። 2 ፀሐይ ከመውጣቷ በፊት እኔ እነሳለሁ። ትልቁን በገናዬንና መሰንቆዬን እየተጫወትሁ እወድስሃለሁ። 3 "ያህዌ ሆይ በሕዝቦች ሁሉ መካከል አመሰግንሃለሁ፤ በብሔሮች መካከል አንተን ለማወደስ እዘምራለሁ። 4 ምክንያቱም ለእኛ ያለህ የታማኝነት ፍቅር እስከ ሰማያት ይደርሳል። ቃልየባኸውን በታማኝነት መፈጸምህም እስከ ደመናት ድረስ እንዳለው ርቀት ታላቅ ነው። 5 ያህዌ እጅግ ታላቅ መሆንህን በሰማያት ላይ አሳይ፤ ክብርህን ደግሞ በምድር ሁሉ ላይ ላሉ አሳይ። 6 ጸሎቶቻችንን መልሰህ እኛ የምትወደን ሕዝብህ እንድንድን ጠላቶቻችንን ድል እንድንነሳ እርዳን" ብዬ እጸልያለሁ። 7 ያህዌ ጸሎታችንን መልሶ ከመቅደሱ እንዲህ ብሎ ተናገረ፤ "ጠላቶቻችሁን ድል ስለነሣሁ የሴኬምን ከተማ በደስታ አካፍላለሁ፤ በሱኮት ሸለቆ ምድሪቱን በሕዝቤ መካከል ድል አደርጋለሁ። 8 የገለዓድ ክልል የእኔ ነው፤ የምናሴ ነገድ ሕዝብ የእኔ ናቸው። የይሁዳ ነገድ እንደ በትረ መንግሥቴ ነው። 9 የሞዓብ ክልል እንደ መታጠቢያ ሳህኔ ነው። የኤዶም ክልል የእኔ መሆኑን ለማሳየት ጫማዬን በላዩ ላይ እወረውርበታለሁ። የፍልስጤም ክልል ሕዝቦችን ድል ከመንሣቴ የተነሣ በድል አድራጊነት እጮኻለሁ።" 10 የኤዶም ሕዝቦችን ለማጥቃት ስለምንፈልግ ሠራዊቴን በዙሪያዋ ጠንካራ ቅጥሮች ወዳሏት ዋና ከተማቸው በድል አድራጊነት ማን ይመራል? 11 እግዚአብሔር እንድትተወን አንፈልግም፤ ሠራዊታችን ጠላቶቻችንን ሊዋጋ ለሰልፍ ሲወጣ ከእኛ ጋር እንድትሄድ እንፈልጋለን። 12 ጠላቶቻችንን በምንዋጋበት ጊዜ እንድትረዳን እንፈልግሃለን፤ ምክንያቱም ሰዎች ሊሰጡን የሚችሉት እርዳታ ዋጋ ቢስ ነው። 13 አንተ ግን እኛን ስትረዳን እናሸንፋለን፤ ጠላቶቻችንን ድል እንድንነሣ ታስችለናለህ።
Chapter 109
1 እግዚአብሔር ሆይ የማወድሰው አንተን ነው፤ እባክህ ለጸሎቴ መልስ ስጠኝ። 2 ምክንያቱም ክፉ ሰዎች ይሰድቡኛል፤ ስለ እኔም ውሸት ይናገራሉ። 3 እንደሚጠሉኝ ባለማቋረጥ ይናገራሉ፤ ያለ ምንም ምክንያት ስለ እኔ ክፉ ነገሮችን ይናገራሉ። 4 ባልንጀራቸው መሆን እንደምፈልግ አሳያቸዋለሁ፤ ለእነርሱም እጸልያለሁ። ነገር ግን ለእኔ ቸር በመሆን ፈንታ ክፉ ነገሮች እንዳደረግሁ ይናገራሉ። 5 ለእነርሱ መልካም ነገሮችን ለማድረጌና እነርሱን ለመውደዴ በምላሹ ክፉ ነገሮችን ያደርጉብኛል፤ ይጠሉኛልም። 6 ስለዚህ ጠላቴን የሚዳኝ ክፉ ዳኛ ሹም፤ የሚነሳበትንና የሚከሰውን ከጠላቶቹ አንዱን አምጣበት። 7 ሙግቱ ሲጠናቀቅ ድኛው በደለኛ መሆኑን እንዲያውጅ አድርግ፤ የምሕረት ልመናው እንኳን እንደ ኃጢአት ይቆጠርበት። 8 ከዚያም በፍጥነት እንዲሞት አድርገውል የእርሱን ሥራ እንዲወስድበት ሌላ ሰው አምጣ። 9 ልጆቹ ከዚህ በኋላ አባት እንዳይኖራቸው አድርግ፤ ሚስቱም መበለት እንድትሆን አድርግ። 10 ልጆቹ ይኖሩባቸው የነቡትን የወደሙ ቤቶች ትተው እንዲሄዱና ምግብ በመለመን እንዲንከራተቱ አድርግ። 11 ገንዘብ ያበደሩት ሰዎች ሁሉ ንብረቱን እንዲይዙበት አድርግ፤ እንግዶች ለማግኘት የሠራውን ማንኛውንም ነገር ይውሰዱበት። 12 እርሱ በሕይወት እያለ ማንም ሰው ቸርነትን አያድርግለት፤ ከሞተ በኋላ ማንም ሰው ለልጆቹ እንዳይራራ አረጋግጥ። 13 ዝርያዎቹ ሁሉ እንዲሞቱ አድርግ፤ የልጅ ልጆቹ ማን እንደነበር እንዲረሱ አድርግ። 14 ያህዌ ሆይ አባቶቹ ያደረጓቸው ክፉ ነገሮችን ይቅር አትበል፤ እናቱ እንኳን የፈጸመቻቸውን ኃጢአቶች ይቅር አትበል። 15 ኃጢአቶቹን ባለማቋረጥ አስብበት፤ ስሙ ሙሉ በሙሉ እንዲረሳ አድርግ። 16 እነዚህን ነገሮች የምጸልየው ያ ሰው ጠላቴ ለማንም ቸርነት ከቶ የማያደርግ ከመሆኑ የተነሣ ነው። ምስኪንና ችግረኛ ሰዎችን አሳደደ፤ ረዳት የለሽ ሰዎችንም ገድሏል። 17 ሰዎችን መርገም ይወድ ነበር። ስለዚህ በሌሎች ላይ እንዲሆኑ የሚጠይቃቸው አስከፊ ነገሮች በእርሱ ላይ እንዲሆኑ አድርግ! ሌሎችን መባረክ አልፈለገም፤ ስለዚህ ማንም እንደማይባርከው አረጋግጥ! 18 ብዙ ጊዜ ሌሎች ሰዎችንም ይረግማል፤ በሌሎች ላይ እንዲሆኑ አድርግ። እንደሚጠጣው ውሃ አካሉ ውስጥ ይግባ። በቆዳው ላይ ሲቀባ የወይራ ዘይት ወደ ሰው አጥንቶች ገብቶ እንደሚያረሰርስ 19 እነዚህ አስከፊ ነገሮች እንደሚለብሰው ልብሱ እንዲጠበቅበት አድርግ። በየእለቱ እንደሚታጠቀው መቀነት በዙሪያው ይሁን። 20 ያህዌ ሆይ ጠላቶቼን ሁሉ በዚያ መንገድ ብትቀጣቸው እመኛለሁ ስለ እኔ ክፉ ነገሮችን የሚናገሩ ሰዎችን 21 ነገር ግን አምላኬ ያህዌ እርሱን እንዳከበረው መልካም ነገሮችን ያደርግልኛል። ቃል እንደገባኸው እኔን በታማኝነት ከመውደድህ የተነሣ ከጠላቶቼ ታደገኝ። 22 ይህንን እንድታደርግ የምጠይቅህ ምስኪንና ችግረኛ ከመሆኔ የተነሣ እና ውስጣዊ ማንነቴ በስቃይ ስለተሞላ ነው። 23 ወዲያው እንደሚጠፋ እንደምሽት ጥላ በሕይወት የመቆየት ጊዜዬ አጭር እንደሆነ አስባለሁ። አንበጣ በንፋስ እንደሚወሰድ እኔም እወሰዳለሁ። 24 አዘውትሬ ከመጾሜ የተነሣ ጉልበቶቼ ደካማ ናቸው። አካሌም እጅግ መነመነ። 25 የሚከሱኝ ሰዎች ይቀልዱብኛል። እኔን ሲያዩ ጭንቅላታቸውን እየነቀነቁ ይሰድቡኛል። 26 አምላኬ ያህዌ ሆይ እርዳኝ! በታማኝነት ስለምትወደኝ ታደገኝ! 27 በምታድነኝ ጊዜ ይህንን ያደረግኸው አንተ እንደሆንክ ጠላቶቼ እንዲያውቁ አድርግ! 28 እነርሱ ይረግሙኝ ይሆናል፤ አንተ ግን እንድትባርከኝ እጠይቃለሁ። የሚያሳድዱኝ እንዲሸነፉና እንዲዋረዱ አድርግ። እኔ ግን ደስ እንዲለኝ አድርግ! 29 የሚከሱኝ ሙሉ በሙሉ እንዲዋረዱ አድርግ፤ የለበሱትን ልብስ በቀላሉ ለማየት የሚችሉትን ያህል መዋረዳቸውን ሌሎች ሰዎች እንዲያዩ አድርግ! 30 ነገር ግን እኔ ያህዌን እጅግ በጣም አመሰግነዋለሁ። እርሱን በሚያመልኩት በብዙ ሕዝብ መካከል ስገኝ አወድሰዋለሁ። 31 እንደኔ ዓይነት ችግረኛ ሰዎችን ስለሚከራከርላቸው እና ልንገደል እንደሚገባን ከወሰኑ ሰዎች ስለሚያድነን ያንን አደርጋለሁ።
Chapter 110
1 ያሕዌ ጌታዬን ንጉሡን እንዲህ አለው፣ "ጠላቶችህን ፈጽሜ ድል እስካደርግልህና የእግርህ መረገጫ እስካደርጋቸው ድረስ፣ በዚህ የከፍታ ክብር ሥፍራ፣ ወደ እኔ ተጠግተህ ተቀመጥ!" 2 ያሕዌ እንደ ንጉሥ ኃይሌህን ከኢየሩሳሌም ወደ ሌላ ምድር አርዝሞታል፣ በጠላቶችህ ሁሉ ላይ ትገዛለህ። 3 ሠራዊትህን ወደ ጦር ሜዳ በምትመራበት እለት፣ ብዙ ሕዝቦች በፈቃዳቸው ሠራዊትህን ይቀላቀላሉ። የወጣትነትህ ኃይል ለም ምድርን በማለዳ እንደሚያጠጣ ጤዛ ይሆንልሃል። 4 ያሕዌ ታላቅ ቃል ኪዳን ገብቶልሃል፣ ፈጽሞም አያጥፈውም፣ ለንጉሡ እንዲህ ብሎአል። "አንተ እንደ መለከጼዴቅ ለዘላለም ካህን ትሆናለህ።" 5 ጌታ በየኝህ ይቆማል፣ በተናደደም ጊዜ፣ ብዙ ነገሥታትን ያጠቃል። 6 አሕዛብን ይቀጣል ይፈርድባቸዋልም፣ የተገደሉ የጠላት ወታደሮች ሬሳ በምድር ላይ ይረፈረፋል። በምድር ላይ ያሉትን ነገሥታት ሁሉ ያደቅቃቸዋል። 7 ንጉሡ ግን በመንገድ አጠገብ ካለው ምንጭ ይጠጣል፣ ጠላቶቹን ካሸነፈ በኋላ ኃይሉን ያድሳል።
Chapter 111
1 ያሕዌ ይመስገን! መልካም የሚያደርጉ ሰዎች አንተን ለማመስገን በተሰበሰቡ ጊዜ ሁሉ አቤቱ ከልቤ አመሰግንሃለሁ። 2 ያሕዌ ያደረጋቸው ነገሮች ሁሉ የሚደነቁ ናቸው! በእነዚህ ነገሮች የሚደሰቱ ሁሉ ሊያጠኗቸው ይመኛሉ። 3 እርሱ ታላቅ ንጉሥ ስለሆነና ታላላቅ ነገሮችን ስለሚያደርግ፣ ሰዎች ለእርሱ ታላቅ አክብሮት አላቸው፣ ያከብሩታልም፣ የሚያደርጋቸው ቅዱስ ነገሮች ለዘላለም ይኖራሉ። 4 ሰዎች ሁሉ የሚያስታውሱአቸውን አስደናቅ ነገሮች አድርጎአል፣ ያሕዌ ሁልጊዜ ምሕረትንና ይቅርታን ያደራል። 5 ለእርሱ ክብርን ለሚሰጡ ምግባቸውን ይሰጣቸዋል፣ ከአባቶቻችን ጋር የገባውን ቃል ኪዳን ፈጽሞ አይረሳም። 6 የሌሎችን ሕዝቦች ምድር እንዲይዙና እንዲወርሱ ሲያስችላቸው፣ ለእኛ ለሕዝቡ፣ ታላቅነቱን አሳይቶአል። 7 ሁሉን ነገር፣ እንደገባልን ቃል ኪዳን፣ መልካም አድርጎአል፣ እኛም እርሱ ያዘዘንን ለማድረግ እንዲረዳን በእርሱ እንታመናለን። 8 ያዘዘውን ትእዛዝ ለዘላለም መታዘዝ አለብን፣ እነዚያን ትእዛዛት ሲሰጠን በእውነትና በጽድቅ ነው። 9 እኛን ሕዝቡን በግብፅ ባሪያዎች ከመሆን ታድጎናል፣ ለዘላለም የሚጸና ቃል ኪዳን ገብቶልናል። እርሱ ቅዱስና የተፈራ ነው። 10 ያሕዌን መፍራትና ማክበር ጥበብ ነው። የእርሱን ትእዛዛት የሚያከብሩና የሚታዘዙ ለራሳቸው የሚወስኑትን መልካም ነገር ያውቃሉ። እርሱን ለዘላለም ማመስገን አለብን!
Chapter 112
1 ያሕዌ ይመስገን! ለእርሱ ታላቅ አክብሮት ያላቸው እንዴት የታደሉ ናቸው፣ እነርሱ በደስታ ትእዛዛቱን ይፈጽማሉ። 2 ልጆቻቸው በምድራቸው ይባረካሉ፣ እግዚአብሔር ዘራቸውን ይባርካል። 3 ቤተሰባቸው ሀታም ይሆናል፣ የጽድቅ ሥራቸው ለዘላለም ይጸናል። 4 ከእነርሱ እግዚአብሔርን ለሚያከብሩ፣ ለቅኖችና ለጻድቃንም ብርሃን በጨለማ ውስጥ የራላእቸዋል፣ 5 በልግስና ገንዘባቸውን ለሚያበድሩ፣ ሥራቸውንንም በታማኝነት ለሚሰሩ ነገሮች ሁሉ ይሳኩላቸዋል። 6 ጻድቃን በመከራ አይጠፉም፣ ሌሎች ሰዎች ሁልጊዜ ከእነርሱ ያተርፋሉ። 7 መጥፎ ዜና ሲያጥማቸው አይፈሩ፣ ሙሉ በሙሉ በያሕዌ ይታመናሉ። 8 እግዚአብሔር ጠላቶቻቸው እንደሚያጠፋላቸው ስለሚያውቁ የማይፈሩ ይልቁንም የሚታመኑ ናቸው። 9 ለድሆች በልግስና ይሰጣሉ፣ የርኅራኄ ሥራቸው ለዘላለም ይጸናል ይመሰገናሉ ይከብራሉም። 10 ክፉ ሰዎች እነዚህን ነገሮች ያያሉ ይበሳጫሉም፣ በንዴትም ጥርሳቸውን ያፋጫሉ፣ ነገር ግን ይጠፋሉ ይሞታሉም። ክፉ ሰዎች ሊያደርጉ የሚፈልጉት ፈጽሞ አይሆንም።
Chapter 113
1 ያሕዌ ይመስገን! ያሕዌን የምታገለግሉ እናንተ ሰዎች፣ አመስግኑት! አመስግኑት! 2 ዛሬም ለዘላለምም እያንዳንዱ ያሕዌን ያመስግን! 3 በምሥራቅና በምዕራብ የሚኖሩ ሕዝቦች፣ እያንዳንዱ ያሕዌን ማመስገን አለበት! 4 ያሕዌ በአሕዛብ ሁሉ ላይ ይገዛል፣ በሰማያት ክብሩ ታላቅ መሆኑን ያሳያል። 5 እንደ ያሕዌ ያለ ማንም የለም። አምላካችን፣ በላይ በሰማይት ከፍ ባለ ሥፍራ ይኖራል። 6 ከላይ ከሰማይ ወደ ታች ወደ ምድር ሰዎችን ሁሉ ይመለከታል። 7 ድሆችን ያነሣቸዋል ስለሆነም በአቧራ ላይ አይቀመጡም፣ ምስኪኖችን ያነሣቸዋል ስለሆነም በአመድ ላይ አይቀመጡም 8 ከመሪዎች ጋር የእርሱን ሕዝብ ከሚመሩ ጋር እንዲቀመጡ ያደርጋቸዋል። 9 መካኖችን ከልጆቻቸው ጋር እንደሚኖሩ እናቶች በቤታቸው እንዲኖሩ ያስችላቸዋል። ያሕዌ ይመስገን!
Chapter 114
1 የእስራኤል ሕዝብ ከግብፅ ሲወጣ፣ የያዕቆብ ልጆች የተለየ ቋንቋ ከሚናገሩ ሰዎች መካከል ተለይተው ሲወጡ. 2 የይሁዳ ምድር እግዚአብሔርን የሚያመልኩ ሰዎች ያሉባት ምድር ሆነች፣ እስራኤል እርሱ የሚገዛባት ምድር ሆነች። 3 ወደ ባሕሩም በመጡ ጊዜ፣ ልክ ወሃው እነርሱን አይቶ የሸሸ መሰለ! ወደ ዮርዳኖስ ወንዝም በመጡ ጊዜ፣ በወንዙ ውስጥ የነበረው ውሃ መፍሰሱን አቆመ፤ ስለሆንም እስራኤላውያን መሻገር ቻለ። 4 ወደ ሲና ተራራ በመጡ ጊዜ በዚያ ታላቅ የምድር መናወጥ ነር፣ ተራራው እንደ ፍየሎችና እንደ በግ ጠቦቶች የሚዘልል ይመስል ነበር። 5 "አንቺ ባሕር የሸሸሽ ስለምን ነው? በዮርዳኖስ ወንዝ ውስጥየነረውስ ውሃ መፍሰሱን ያቆመው ስለምንድን ነው? 6 ተራራው እንደ ፍየሎች ኮርብታውም እንደ በግ ጠቦቶች እንዲዘልል ያደረገው ምንድን ነው?" ብሎ የሚጠይቅ ቢኖር 7 በእርግጥ፣ ምድር ሁሉ በጌታ ፊት ትንቀጠቀጣለች! ያዕቆብ በሚያመልከው በእግዚአብሔር ፊት እያንዳንዱ ይንቀጠቀጣል! 8 የእስራኤል ሕዝ እንዲጠጡ አልቱን ያዘዘው እርሱ ነው፣ ደረቅ አለት ከሆነው ድንጋይ የምንድ የምንጭ ውሃ እንዲወጣ ያደረገው እርሱ ነው!
Chapter 115
1 ያሕዌ፣ ሰዎች ሊያመሰግኑህ ይገባቸዋል፣ ማመስገን አለባቸው፣ እኛ አይደለንም፣ አንተ እኛን በታማኝነት ወድደኸናል ሁልጊዜም የገባህልንን ቃል ኪዳን ታደርግልናለህ። 2 ሌሎች ሕዝቦች ስለ እኛ መናገራቸው ይተገባ አይደለም፣ "እነርሱ አምላካቸው ኃይል እንደ ሆነ ይናገራሉ፣ ያ እውነት ከሆነ፣ ስለምን አይረዳቸውም?" 3 የእኛ አምላክ በሰማይ ነው፣ የፈቀደውን እርሱ ያደርጋል! 4 ነገር ግን የአሕዛብ ጣዖቶች ከወርቅና ከብር የተሰሩ ሐውልቶች ናቸው፣ እነዚህ ሁሉ በሰዎች የሚሠሩ ናቸው። 5 ጣዖቶቻቸው፣ አፍ አላቸው ነገር ግን አይናገሩም፣ አይን አላቸው፣ ነገር ግን አያዩም። 6 ጆሮ አላቸው፣ ነገር ግን ምንም አይሰሙም፣ አፍንጫ አላቸው፣ ነገር ግን ምንም አያሸቱም። 7 እጆች አላቸው፣ ነገር ግን ምንም ስሜት የላቸውም። እግሮች አሉአቸው ነገር ግን አይራመዱም፣ በጉሮሮአቸው ምንም አይነት ድምፅ አያሰሙም። 8 እነዚህን ጣዖቶች የሚሰሩ ሰዎች እንደ ጣዖቶቹ ኃይል የሌላቸው ናቸው። በእነዚህ ጣዖቶች የሚታመኑ፣ እንደ ጣዖቶቻቸው ምንም የማይጠቅሙ ናቸው። 9 እናንተ፣ የእስራኤል ሕዝቦች፣ በያሕዌ እመኑ! እንደ ጋሻ የሚጠብቃችሁ እና የሚረዳችሁ እርሱ ነው። 10 እናንተ የኦሮን ልጆች፣ ካህናት፣ በያሕዌ ታመኑ! እንደ ጋሻ የሚጠብቃችሁ እና የሚረዳችሁ እርሱ ነው። 11 ለያሕዌ ታላቅ አክብሮት ያላችሁ፣ በእርሱ ታመኑ! እንደ ጋሻ የሚጠብቃችሁ እና የሚረዳችሁ እርሱ ነው። 12 ያሕዌ አልረሳንም፣ እርሱ እኛን እስራኤላውያንን ባርኮናል! ካህናቱን ባርኮአል፣ 13 ለእርሱ ታላቅ አክብሮት ያላቸውን ይባርካል፣ ታላላቆችንና ታናናሾችንም ሁሉንም ይባርካል! 14 ያሕዌ እናንተ የእስራኤል ልጆች ለእናንተና ለዘሮቻችሁ ብዙ ልጆችን እንዲሰጣችሁ እመኛለሁ። 15 ሰማይንና ምድርን የሠራ ያሕዌ ሁላችሁንም ይባርክ! 16 የሰማይ ሰማያት ሁሉ የያሕዌ ነው፣ በምድር ያሉትን ነገሮች ሁሉ ለእኛ ለሕዝቦቹ ሰጥቶናል። 17 ሙታን ያሕዌን ሊያመሰግኑ አይችሉም፣ ሙታን ወዳሉበት ሥፍራ ሲወርዱ ሊናገሩ አይችሉም አያመሰግኑትም። 18 ነገር ግን እኛ ሕያዋን የሆንን አሁንና ለዘላለም ያሕዌን እናመሰግናለን!
Chapter 116
1 እንዲረዳኝ ወደ እርሱ በጮኽኩ ጊዜ ስለሚሰማኝ ያህዌን እወደዋለሁ። 2 ያደምጠኛልና በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ወደ እርሱ እጣራለሁ። 3 በዙሪያዬ ያሉ ነገሮች ሁሉ እንደምሞት እንዳስብ ያደርጉኛል። መሞቴንና ሙታን ወዳሉበት ስፍራ መሄዴን እጅግ ፈራሁት። እጅግ ተጨንቄና ፈርቼ ነበር። 4 ነገር ግን "ያህዌ ሆይ እንድታድነኝ እመጸንሃለሁ!" ብዬ ያህዌን ተጣራሁ። 5 ያህዌ ቸር እና ትክክለኛውን ነገር የሚያደርግ ነው። እርሱ አምላካችን ነው፤ ምሕረትንም የሚያደርግልን ነው። 6 ረዳት የለሾችን ይከላከልላቸዋል። እንደምሞት ባሰብኩበት ጊዜ እኔንም አዳነኝ። 7 እግዚአብሔር እጅግ መልካም ነገሮችን ስላደረገልኝ ራሴን ማበረታታት ይገባኛል። 8 ያህዌ ከመሞት አድኖኛል፤ ከሚያስለቅሱኝም ችግሮች ጠብቆኛል። ከአደጋ ጠብቆኛል። 9 እነሆ ሰዎች በሕይወት በሚቆዩበት በምድር ያህዌ እየመራኝ እንደሆነ በማወቅ በሕይወት አለሁ። 10 "እጅግ ተቸግሬአለሁ፤" ባልኩበት ጊዜ እንኳን በያህዌ ማመኔን ቀጠልኩ። 11 በተጨነቅሁና "ማንንም ማመን አልችልም" ባልኩበት ጊዜ እንኳን በያህዌ መታመኔን ቀጠልኩ። 12 ለእኔ ካደረገልኝ መልካም ነገሮች ሁሉ የተነሣ በመሆኑም ለያህዌ ምን እንደማቀርብ እነግራችኋለሁ። 13 እኔን ስላዳነኝ እርሱን ለማመስገን የወይን ጽዋ አቀርብለታለሁ። 14 የያህዌ ከሆኑት ከብዙዎቹ ሕዝቦች ጋራ በአንድነት በምሆንበት ጊዜ እንደምሰጠው ከልቤ ቃል የገባሁለትን መስዋዕት አቀርብለታለሁ። 15 ከሕዝቦቹ አንዱ በሚሞትበት ጊዜ ያህዌ እጅግ ያዝናል። 16 ያህዌን ከሚያገለግሉ ሰዎች አንዱ እኔ ነኝ። እናቴ እንዳደረገችው አገለግለዋለሁ። ችግሮቼን ሁሉ ፍጻሜ አበጅቶላቸዋል። 17 ስለዚህ ላመሰግነው መስዋዕት አቀርብለታለሁ። ወደ እርሱም እጸልያለሁ። 18 - 19 የያህዌ ከሆኑት ከብዙዎቹ ሕዝቦች ጋር በአንድነት በምሆንበት ጊዜ በኢየሩሳሌም በቤተ መቅደሱ የውጪ አደባባይ፣ እንደምሰጠው ከልቤ የገባሁለትን መስዋዕት አቀርብለታለሁ። ያህዌ ይወደስ!
Chapter 117
1 አሕዛብ ሁላችሁ ያሕዌን አመስግኑ! ወገኖችም ሁሉ አመስግኑት 2 ምክንያቱም እርሱ በታማኝነት ወድዶናልና፣ የገባልንንም ቃል ኪዳን ለዘላለም ይጠብቃል። ያሕዌን አመስግኑ!
Chapter 118
1 ላደረገላችሁ መልካም ነገሮች ሁሉ እጅግ በጣም እንደምታመሰግኑት ለያህዌ ንገሩት። እኛን ሕዝቡን ለዘለዓለም በታማኝነት ይወደናል። 2 እናንተ የእስራኤል ሕዝብ "እኛን ሕዝቡን ለዘለዓለም በታማኝነት ይወደናል!" ብላችሁ በተደጋጋሚ መጮህ ይገባችኋል። 3 እናንተ የአሮን ዝርያዎች የሆናችሁ ካህናት፦ "እኛን ሕዝቡን ለዘለዓለም በታማኝነት ይወደናል!" ብላችሁ በተደጋጋሚ መጮህ ይገባችኋል። 4 እርሱን የሚፈሩ ሁሉ፦ "እኛን ሕዝቡን ለዘለዓለም በታማኝነት ይወደናል!" ብላችሁ በተደጋጋሚ መጮህ ይገባችኋል። 5 በተጨነቅሁ ጊዜ ወደ ያህዌ ተጣራሁ፤ እርሱም መልሶ ሰጠኝ፤ ከጭንቀቶቼም ነጻ አወጣኝ። 6 እግዚአብሔር በእኔ በኩል ነው፤ በመሆኑም ማናቸውንም ነገር አልፈራም። ማንም እግዚአብሔር እኔን ለዘለዓለም እንዳይባርከኝ የሚከለክል ምንም ነገር ማድረግ አይችልም። 7 አዎ እግዚአብሔር በእኔ በኩል ነው፤ በመሆኑም ጠላቶቼን ሲያሸንፋቸው በድል አድራጊነት እመለከታቸዋለሁ። 8 በሰዎች ላይ ከመደገፍ ይልቅ በያህዌ መታመን ይሻላል። 9 ተደማጭነት ያላቸው ሰዎች ይከላከሉልናል ብሎ ከመታመን ይልቅ ያህዌ እንዲከላከልልን መታመን ይሻላል። 10 የብዙ ሕዝቦች ሰራዊቶች ከበቡን፤ ያህዌ ግን በኃይሉ ድል እንድንነሳቸው አስቻለን። 11 ሙሉ ብሙሉ ከብበውን ነበር፤ ነግር ግን በያህዌ ኃይል ሁሉንም አሸነፍናቸው። 12 እንደ ተቆጡ ንቦች ዙሪያዬን በብዛት ወረሩኝ። በእሾህ ቁጥቋጦ ውስጥ እንደሚንቦጎቦግ እሳት ነበሩ። ነገር ግን በያህዌ ኃይል አሸነፍናቸው። 13 ጠላቶቻችን በቁጣ ጥቃት አደረሰብን፤ ሊያሸንፉንም ምንም አልቀራቸውም ያህዌ ግን ረዳን። 14 ብርቱ የሚያደርገን ያህዌ ነው። እኔም ሁልጊዜ የምዘምርለት እርሱ ነው። እርሱ ከጠላቶቻችን አድኖናል። 15 እግዚአብሔርን የሚያከብሩ ሕዝቦች ድንኳኖች ውስጥ የሚዘመሩትን አስደሳች የድል መዝሙሮችን አድምጡ። ያህዌ ሙሉ በሙሉ አሸንፏቸዋል።" 16 ጠላቶቹን በማሸነፉ መደሰቱን ለማሳየት ጠንካራውን ቀኝ እጁን ዘረጋ፣ ያሕዌ ሙሉ ለሙሉ ድል አድርጎአቸዋል፡፡ 17 በውጊያ ውስጥ አልገደልም። ያህዌ ያደረጋቸውን ታላላቅ ነገሮች ለማወጅ በሕይወት እኖራለሁ። 18 ያህዌ በጥብቅ ቀጥቶኝ ነበር፤ ነገር ግን እንድሞት አልፈቀደም። 19 እናንተ ደጅ ጠባቂዎች ወደ ቤተ መቅደሱ ውስጥ ገብቼ ያህዌን እንዳመሰግን ደጆቹን ክፈቱልኝ። 20 ያህዌን ለማምለክ ወደ ቤተ መቅደሱ የምንገባባቸው ደጆች እነዚያ ናቸው። እግዚአብሔርን የሚያከብሩ ሰዎች በእነዚያ ደጆች በኩል ይገባሉ። 21 ያህዌ ሆይ ጸሎቴን ስለመለስክልኝ እና ከጠላቶቼም ስላዳንከኝ አመሰግንሃለሁ። 22 ያህዌ የመረጠው ንጉሥ ግንበኞች ቤት በሚገነቡበት ጊዜ እንደጣሉት ድንጋይ ነው። ነገር ግን ያ ድንጋይ የማዕዘኑ ድንጋይ ሆነ። 23 ይህ በያህዌ የተደረገ ነበር፤ እኛም ስናየው አስደናቂ ነገር ነው። 24 ያህዌ ጠላቶቻችንን ድል ለመንሳት ኃይለኛ ሥራ መሥራቱን የምናስታውስበት ቀን ይህ ነው። ዛሬ ድስ ይለናል፤ ሐሴትም እናደርጋለን። 25 ያህዌ ሆይ እኛን ከጠላቶቻችን ማዳንህን እንድትቀጥል እንማጸንሃለን ያህዌ ሆይ ማድረግ የምንፈልገውን ነገር እንድናከናውን እርዳን። 26 ያህዌ ሆይ በአንተ ኃይል የሚመጣውን ባርከው። ከመቅደሱም እናንተን ሁላችሁንም እንባርካችኋለን። 27 ያህዌ አምላክ ነው፤ ብርሃኑም በእኛ ላይ እንዲመጣ አድርጓል። ኑ የሚሰዋ እንስሳ ከመጡና በመሠዊያው ቀንዶች ላይ እሰሩት። 28 ያህዌ ሆይ እኔ የማመልከው አምላክ አንተ ነህ፤ እወድስሃለሁ! አንተ አምላኬ ነህ፤ ታላቅ መሆንህንም ለሰው ሁሉ እነግራለሁ። 29 መልካም ነገሮችን ስለሚያደርግልን ያህዌ ይመስገን! ቃል እንደገባልን በታማኝነት ለዘለዓለም ይወደናል።
Chapter 119
1 ያህዌ ስህተት የሆኑ ነገሮች እንዳደረጉ ማንም በእውነት ሊናገርባቸው በማይችሉ ሰዎች ሁልጊዜም የያህዌን ሕግጋት በሚታዘዙ ሰዎች ይደሰታል። 2 ያህዌ እርሱ የሚፈልግባቸውን በሚታዘዙ፣ ያንን እንዲያደርጉም እንዲረዳቸው በመላው ውስጣዊ ማንነታቸው በሚጠይቁት ሰዎች ይደሰታል። 3 ስህተት የሆኑ ነገሮችን አያደርጉም። ያህዌ እንደሚፈልጋቸው ጸባያቸውን ያሳመሩ ናቸው። 4 ያህዌ ሆይ የመልካም ምግባር መርሆዎችህን ሰጥተኸናል። በታማኝነት እንድንታዘዛቸውም ነግረኸናል። 5 ያዘዝኸውን ማንኛውንም ነገር በታማኝነት መጠበቅ እፈልጋለሁ። 6 ለትዕዛዛትህ ዘወትር ትኩረት እሰጣለሁ፤ አልዋረድም። 7 ሐቀኛ ደንቦችህን ሁሉ በምማርበት ጊዜ በንጹሕ ውስጣዊ ማንነት እወድስሃለሁ። 8 ሥርዓትህን ሁሉ እታዘዛለሁ፤ አትተወኝ! 9 አንድ ወጣት በንጹሕ መንገድ እንዴት ሊኖር እንደሚችል አውቃለሁ፤ ትዕዛዛትህን በመታዘዝ ነው። 10 በመላው ውስጣዊ ማንነቴ ላገለግልህ እሞክራለሁ፤ አንተ ካዘዝከው ርቄ እንድሄድ አትፍቀድልኝ። 101 ቃልህን እንድታዘዝ ክፉ ጸባይን ሁሉ ሸሽቻለሁ። 102 እያጠናኳቸው እያለ እላስተማርከኝ እነርሱን መታዘዝን እምቢ አላልኩም። 103 ቃልህን ሳነብ እንደምበላው ማር ዓይነት ናቸው፤ አዎን ከማርም ይበልጥ የሚጣፍጡ ናቸው። 104 የመልካም ምግባር መርሆዎችህን ስለተማርኩ ብዙ ነገሮችን ለመገንዘብ የምችል ሆኛለሁ፤ ስለዚህም አንዳንድ ሰዎች የሚያደርጓቸውን ክፉ ነገሮች ሁሉ ጠላሁ። 105 ቃልህ ሊመራኝ እንደ ፋኖስ ልሄድበት የሚገባኝን መንገድ ሊያሳየኝ እንደ ብሃን ነው። 106 ደንቦችህን ዘወትር እንደምታዘዝ አጥብቄ ቃል ገብቻለሁ፤ እንደገናም አጥብቄ ቃል እገባለሁ፤ ሁሉም ፍትሐዊ ናቸው። 107 ያህዌ ሆይ እጅግ በጣም እየተሰቃየሁ ነው፤ ልታደርግ ቃል እንደገባኸው እንደገና ብርቱ እንድሆን አድርገኝ። 108 ያህዌ ሆይ በምጸልይበት ጊዜ ሳመሰግንህ ላንተ መስዋዕት እንደማቀርብ ነው። እባክህን ተቀበለው፤ ደንቦችህንም አስተምረኝ። 109 ጠላቶቼ ሊገድሉኝ ብዙ ጊዜ ይሞክራሉ፤ እኔ ግን ሕግህን አልረሳም። 110 አዳኝ እንስሳን በወጥመድ ለመያዝ እንደሚሞክር ክፉ ሰዎች ሊይዙኝ ሞክረዋል፤ ነገር ግን የመልካም ምግባር መሮሆዎችህን አልጣስኩም። 11 በአንተ ላይ ኃጢአት እንዳልሠራ ትዕዛዛትህን በቃሌ አጥንቼአለሁ። 12 ያህዌ ሆይ እወድስሃለሁ፤ ሥርዓትህን አስተምረኝ። 111 የምትፈልግብንን ነገሮች ለዘለዓለም ይዣቸዋለሁ፤ ከእነርሱ የተነሣ በውስጣዊ ማንነቴ ደስተኛ ነኝ። 112 ትዕዛዛትህን እያንዳንዳቸውን ዘወትር ለመታዘዝ ወስኛለሁ። 113 እንደሚወዱህ በአፋቸው ብቻ የሚናገሩ ሰዎችን እጠላለሁ። እኔ ግን ሕግህን እወድዳለሁ። 114 አንተ ለእኔ ከጠላቶቼ ልደበቅ እንደምችልበት ስፍራ ነህ፤ ከእነርሱ የምከለልበት ጋሻ ዓይነት ነህ፤ በተስፋ ቃላትህም እታመናለሁ። 115 እናንተ ክፉ ሰዎች የእግዚአብሔርን ትዕዛዛት እንድታዘዝ ከእኔ ራቁ! 116 በሕይወት መኖር እንድቀጥል እንደምታደርገው ቃል እንደገባኸው ብርቱ እንድሆን አስችለኝ። እንደምታድሰኝ በመተማመን እየተጠባበቅሁ ነኝ፤ ቅር አታሰኘኝ። 117 ከአደጋ እንድጠበቅና ለትዕዛዛትህ ዘወትር ትኩረት እንድሰጥ ደግፈህ ያዘኝ። 118 ሥርዓትን የማይታዘዙትን ሁሉ ያስወግዳቸዋል፤ በማታለል ለማድረግ የሚያቅዱት ዋጋ ቢስ ነው። 119 ሰዎች ቆሻሻን እንደሚወረውሩ በምድር ላይ ያሉትን ክፉ ሰዎችን ሁሉ ታስወግዳቸዋለህ። ስለዚህም የምትፈልግብንን ነገሮች እወዳቸዋለሁ። 120 አንተን በመፍራቴ ተንቀጠቀጥኩ፤ ደንቦችህን የማይታዘዙትን ስለምትቀጣ እፈራለሁ። 121 እኔ ግን ትክክለኛና ፍትሐዊ የሆነውን ነገር አድርጌአለሁ፤ በመሆኑም ሰዎች እንዲጨቁኑኝ አትፈቀድ። 122 ለእኔ መልካም ነገሮችን ለማድረግ ኃላፊነትን ውሰድ። ትዕቢተኛ ሰዎች እንዲጨቁኑኝ አትፍቀድ። 123 እንደምታደርገው ቃል እንደገባኸው እንድትታደገኝ ለጅም ጊዜ በመጠበቅ ዓይኖቼ ደከሙ። 124 በታማኝነት እንደምትወደኝ ለማሳየት አንድ ነግር አድርግልኝ። ሥርዓትህንም አስተምረኝ። 125 እኔ አገልጋይህ ነኝ፤ የምትፈልግብንን መማር እንዳውቅ የምትፈልገውን እንድገነዘብ አስችለኝ። 126 ያህዌ ሆይ ሕግህን ባለመታዘዛቸው ሰዎችን የምትቀጣበት ጊዜ አሁን ነው። 127 በእውንት ወርቅ ከምወደው ይበልጥ ትዕዛዛትህን እወዳለሁ፤ እጅግ ንጹሕ ወርቅ ከምወደው ይበልጥ እወዳቸዋለሁ። 128 በመሆኑም ሕይወቴን በመልካም ምግባር መርሆዎችህ መሠረት እመራለሁ። አንዳንድ ሰዎች የሚያደርጓቸውን ክፉ ነገሮች ሁሉ እጠላለሁ። 129 የምትፈልግብን ነገሮች ድንቅ ናቸው፤ በምሆኑም በውስጣዊ ማንነቴ እታዘዛቸዋለሁ። 130 አንድ ሰው ቃልህን በሚያብራራበት ጊዜ ብርሃን እንደሚለኩስ ያህል ነው፤ የሚናገሩት ነገር ሕግህን ያልተማሩትን ሰዎች እንኳን ጠቢብ እንዲሆኑ ያደርጋቸዋል። 13 እንድናደርግ ያዘዝከንን ነገሮች ሁሉ ለሰዎች አስታውቄአለሁ። 14 አንተ ከእኛ የምትፈልጋቸውን ነገሮች በመታዘዝ ደስ ይለኛል፤ እጅግ ባለጠጋ ከመሆን የበለጠ በዚያ እደሰታለሁ። 131 መጠጣት ፈልጎ አፉን ከፍቶ እንደሚያለከልክ ውሻ ትዕዛዛትህን ለማወቅ በብርቱ እፈልጋለሁ። 132 ለሚወዱህ ሰዎች ሁሉ እንደምታደርገው አድምጠኝና ቸርነትን አድርግልኝ። 133 ቃል እንደገባህልኝ ምራኝ፤ ክፉ ሰዎች የማደርገውን ነገር እንዲቆጣጠር እትፍቀድ። 134 የመልካም ምግባር መርሆዎችህን እንድታዘዝ ከሚጨቁኑኝ ሰዎች ታደገኝ። 135 ቸርነትን አድርግልኝ፤ ሥርዓትህንም አስተምረኝ። 136 ብዙ ሰዎች ሕግህን ስለማይታዘዙ እጅግ በጣም አለቀስሁ። 137 ያህዌ ሆይ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ደንቦችህም ትክክለኛ ናቸው። 138 የምትፈልግብን ነገሮች እውነት ናቸው፤ እጅግ ትክክለኛና ፍትሐዊ ናቸው። 139 ጠላቶቼ ቃልህን ቸል በማለታቸው ተንገብግቤአለሁ። 140 የተስፋ ቃላትህ አስተማማኝ እንደሆኑ አውቄአለሁ፤ እነርሱንም እወድዳቸዋለሁ። 141 እኔ ብርቱ አይደለሁም፤ ሰዎችም ይንቁኛል፤ ነገር ግን የመልካም ምግባር መርሆዎችህን አልረሳም። 142 አንተ ጻድቅ ነህ፤ ለዘለዓለምም ጻድቅ ትሆናለህ፤ ሕግጋትህም በጭራሽ አይለወጡም። 143 ችግሮች ባለማቋረጥ ይደርሱብኛል፤ ደግሞም እጨነቃለሁ፤ ትዕዛዛትህ ግን ደስተኛ እንድሆን ያደርጉኛል። 144 የምትፈልግብን ነገሮች ዘወትር ፍትሐዊ ናቸው። በሕይወት መኖሬን እንድቀጥል እንድገነዘባቸው እርዳኝ። 145 ያህዌ ሆይ በመላው ውስጣዊ ማንነቴ ወደ አንተ እጣራለሁ፤ መልስልኝ፤ ሥርዓትህንም እታዘዛለሁ። 146 ወደ እንተ እጣራለሁ፤ "አድነኝ፤ ትዕዛዛትህንም እጠብቃለሁ።" 147 በየማለዳው ከመንጋቱ በፊት እነሳና እንድትረዳኝ ወደ አንተ እጣራለሁ ቃል የገባኸውን እንድታደርግ በመተማመን እጠባበቃለሁ። 148 ሌሊቱን ሙሉ የነቃሁ ነኝ፤ ትዕዛዛትህንና የተስፋ ቃላትህን አሰላስላለሁ። 149 ያህዌ ሆይ በታማኝነት ስለምትወደኝ ስጸልይ ስማኝ፤ ደንቦችህን ስለምጠብቅ ክአደጋ ጠብቀኝ። 150 የሚጨቁኑኝ ክፉ ሰዎች ወደ እኔ እየቀረቡ ናቸው፤ ለሕግህ ምንም ትኩረት አይሰጡም። 15 ያዘዝከውን ነገር ሁሉ አጠናለሁ፤ እንዴት መኖር እንዳለብኝ ላሳየኸኝም ትኩረት እሰጣለሁ። 16 ሥርዓትህን ለመታዘዝ ደስ ይለኛል፤ ቃላትህንም አልረሳም። 151 አንተ ግን ያህዌ ቅርቤ ነህ፤ ትዕዛዛትህም በጭራሽ እንደማይለወጡ አውቃለሁ። 152 ከረጅም ጊዜ በፊት ስለምትፈልግብን ነገሮች አወቅሁ፤ ለዘለዓለም እንዲኖሩ እንዳሰብካቸውም አውቃለሁ። 153 ሕግህን ስልማልረሳ ተመልከተኝ፤ እጅግ ብዙ መሰቃየቴን እይና ፈውሰኝ። 154 ሌሎች ሲከስሱኝ ተከላከልልኝ፤ ከእነርሱም ታደገኝ፤ እንደምታደርገው ቃል እንደገባኸው በሕይወት መኖር እንድቀጥል ፍቀድልኝ። 155 ክፉ ሰዎች ሥርዓትህን አይታዘዙም፤ በምሆኑም በእርግጥ አታድናቸውም። 156 ያህዌ ሆይ እኔን በብዙ መንገዶች በመርዳት ምሕረት አድርገሃል። በቀድሞ ጊዜ እንዳደረግኸው በሕይወት መኖር እንድቀጥል ፍቀድልኝ። 157 ብዙ ሰዎች ጠላቶቼ ናቸው፤ ብዙ ሰዎች እንድሰቃይ ያደርጋሉ፤ እኔ ግን ትዕዛዛትህን ቸል አልልም። 158 ለአንተ ታማኝ ያልሆኑትን ስመለክት የምትፈልግባቸውን ስለማይታዘዙ የመጸየፍ ስሜት ያድርብኛል። 159 ያህዌ ሆይ የመልካም ምግባር መርሆዎችህን እንደምወድ ተመልከት በታማኝነት ስለምትወድደኝ በሕይወት መኖር እንድቀጥል ፍቀድልኝ። 160 አንተ በተናገርከው ማንኛውም ነገር ላይ መደገፍ አችላለሁ። ደንቦችህ ሁሉ ለዘለዓለም ጸንተት ይኖራሉ። 161 ገዢዎች ያለ ምንም ምክንያት ያሳድዱኛል፤ በውሳዊ ማንነቴ ግን ለቃልህ እጅግ ታላቅ አክብሮት አለኝ። 162 ታላቅ ሀብት እንዳገኘ ሰው ደስታ ያህል በቃልህ ደስ ይለኛል። 163 ውሸትን ሁሉ ሙሉ ብሙሉ እጠላለሁ፤ ሕግጋትህን ግን እወድዳለሁ። 164 ሁሉም ፍትሐዊ ስለሆኑ ለትዕዛዛትህ በቀን ሰባት ጊዜ እወድስሃለሁ። 165 ሕግጋትህን ለሚወዱ ሁሉም ነገር በመልካም ይቀናላቸዋል፤ ምንም ነገር እነርሱን እንዲተዉ እያደርጋቸውም። 166 ያህዌ ሆይ ከችግሮቼ እንድትታደገኝ በመተማመን እጠባበቃለሁ፤ ትዕዛዝህንም እታዘዛለሁ። 167 እንድናደርግ የምትፈልግብንን እታዘዛለህ፤ ሁሉንም እጅግ እወደዋለሁ። 168 የመልካም ምግባር መሮሆዎችህን እታዘዛለሁ፤ የማደርገውን ማናቸውንም ነገር አንተ ታያለህ። 169 ያህዌ ሆይ እንድትረዳኝ ወደ አንተ ስጸልይ አድምጠኝ፤ ቃልህን እንድገነዘብ እርዳኝ። 170 ስጸልይ ስማኝ፤ እንደምታደርገው እንደተናገርክ ታደገኝ። 17 መኖር እንድቀጥልና በሕይወት ዘመኔ ሁሉ ቃልህን እንድታዘዝ ለማገለግልህ ለእኔ መልካም ነገሮችን አድርግ። 18 በሕግጋትህ ውስጥ የተጻፉትን አስደናቂ ነገሮች እንዳውቅ በአእምሮዬ እንድገነዘብ እርዳኝ። 171 ሕግህን ስለምታስተምረኝ ዘወትር እወድስሃለሁ። 172 ትዕዛዛትህ ሁሉ ፍትሐዊ ስለሆነ ስለ ቃልህ እዘምራለሁ። 173 የመልካም ምግባር መርሆዎችህን ለመታዘዝ ስለመረጥኩ ልትረዳኝ ዘወትር ዝግጁ እንድትሆን እጠይቅሃለሁ። 174 ያህዌ ሆይ ከጠላቶቼ እንድትታደገኝ በጉጉት እፈልጋለሁ በሕግህ ደስ ይለኛል። 175 ደንቦችህ እኔን መርዳታቸውን እንዲቀጥሉ አንተን ማወደሴን መቀጠል እንድችል መኖሬን እንድቀጠል ፍቀድልኝ። 176 መንጋውን እንደተወ በግ ኃጢአት አድርጌ ከአንተ ርቄ ሄጃለሁ፤ ትዕዛዝህን ስላልረሳሁ እኔን ፈልገኝ። 19 በዚህች በምድር ላይ የምኖረው ለአጭር ጊዜ ብቻ ነው፤ ከማስተዋል አታጉድለኝ። 20 በውስጣዊ ማንነቴ ድንጋጌዎችህን ሁልጊዜ ለማወቅ በብርቱ እፈልጋለሁ። 21 እብሪተኛ የሆኑትን ሰዎች ትገስጻለህ፤ ትዕዛዛትህን የማይታዘዙትን ሰዎች ትረግማለህ። 22 22 እኔን መሳደባቸውን እና መናቃቸውን እንዲቀጥሉ አትፍቀድላቸው። ይህንን የምጠይቀው የምትጠብቅብኝን ስለታዘዝሁ ነው። 23 ገዢዎች በአንድነት ተሰብስበው እኔን የሚጎዱባቸውን መንገዶች አቀደ፤ እኔ ግን ያዘዝከውን ነገር አሰላስላለሁ። 24 24 ከእኛ በምትፈልጋቸው ነገሮች ደስ ይለኛል። ይህም መካሪዎቼ የሆኑ ያህል ነው። 25 በቅርቡ እንደምሞት አስባለሁ፤ እንደምታደርገው ቃል እንደገባህልኝ ሕይወቴን አድናት። 26 ስላደረግኋቸው ነገሮች ሁሉ በነገርኩህ ጊዜ መልስ ሰጠኸኝ፤ ሥርዓትህን አስተምረኝ። 27 ጸባዬ እንዴት እንዲሆን እንደምትፈልግ እንዳውቅ እርዳኝ፤ በዚያን ጊዜ መመሪያዎችህን አሰላስላለሁ። 28 እጅግ ከማዘኔ የተነሣ ምንም ብርታት አልነበረኝም። እንደምታደርገው ቃል እንደገባህልኝ እንደገና ብርቱ ለመሆን አስችለኝ። 29 ጥፋትን ከማድረግ ከልክለኝ፤ ሕግጋትህንምን ለእኔ በማስተማር ቸርነትን አድርግልኝ። 30 በታማኝነት ልታዘዝህ ወስኛለሁ፤ ትዕዛዛትህን ለመከተል ቆርጫለሁ። 31 ያህዌ ሆይ ከእኛ የምትፈልጋቸውን ነገሮች በጥንቃቄ አጥብቄ ለመያዝ እሞክራለሁ። እንዳልዋረድ አትተወኝ። 32 እንዳደርግ የምትፈልገውን የበለጠ እንድገነዘብ ስለረዳኸኝ ትዕዛዛትህን በጉጉት እታዘዛለሁ። 33 ያህዌ ሆይ የሥርዓቶችህን ትርጕም አስተምረኝ፤ በዚያን ጊዜ ሙሉ በሙሉ እታዘዛቸዋለሁ። 34 በመላው ውስጣዊ ማንነቴ እንድታዘዛቸው ሕግጋትህን እንድገነዘብ እርዳኝ። 35 በትዕዛዛትህ ደስ ይለኛል፤ በመሆኑም ለእኔ በመረጥክልኝ መንገዶች ምራኝ። 36 ባለጠጋ ለመሆን መፈለግ ሳይሆን የምታዝዘውን ለማድረግ እንድፈልግ አድርገኝ። 37 ዋጋ ቢስ ወደ ሆኑ ነገሮች እንድመለከት አትፍቀድልኝ፤ እንደምታደርገው ቃል እንደገባህልኝ መኖርን እንድቀጥል ፍቀድልኝ። 38 እኔ የማገለግልህ ስለ ሆንኩ ለሚያከብሩህ ሁሉ ልታደርግ ቃል የገባህላቸውን ለእኔም እንደ ቃል ኪዳንህ አድርግ። 39 አንተን ስለማገለገል ጠላቶቼ ይሰድቡኛል፤ ስለምፈራቸው ከእኔ አርቅልኝ፤ ደንቦች ግን እጅግ መልካም ናቸው! 40 የመልካም ምግባር መርሆዎችህን መታዘዝ እጅግ እፈልጋለሁ። አንተ ጻድቅ ስለሆንክ በሕይወት መኖር እንድቀጥል ፍቀድልኝ። 41 ያህዌ ሆይ በታማኝነት እንደምትወደኝ አሳየኝ። እንደምታደርገው ቃል እንደገባልኝም ታደገኝ። 42 ያንን ካደረግን በኋላ በቃልህ ስለምታመን ለሚሰድቡኝ ሰዎች በምልስ መስጠት እችላለሁ። 43 በደንቦችህ መተማመን ስላለኝ እውነትህን ከመናገር በጭራሽ አትከልክለኝ። 44 ሕግጋትህን ዘወትር ለዓለምና ለዘለዓለም እታዘዛቸዋለሁ። 45 የመልካም ምግባር መርሆዎችህን ለመታዘዝ ስለሞከርሁ ዘወትር ያለ ጉዳት እሆናለሁ። 46 ለነገሥታት አንተ የምትፈልግብንን ነገር እነግራለሁ፤ አንተን ስላልተውሁም እንዳፍር አያደርጉኝም። 47 ትዕዛዛትህን ለመታዘዝ ደስ ይለኛል። እኔም እወድዳቸዋለሁ። 48 ትዕዛዛትህን አከብራቸዋለሁ፤ እወድዳቸውማለሁ፤ እንድናደርግ የምትፈልግብንን ሁሉ አሰላስላለሁ። 49 የተናገርከው ነገር ከአንተ መልካም ነገሮችን በመተማመን እንድጠባበቅ ስላደረገኝ ለማገለግልህ ለእኔ እንደምታደርግ የተናገርከውን አትርሳ። 50 መከራ በደረሰብኝ ጊዜ አንተ አጽናናኸኝ፤ ቃል የገባህልኝን ፈጽመህ በሕይወት ጠብቀህ አቆየኸኝ። 51 ትዕቢተኛ ሰዎች ዘወትር ይሳለቁብኛል። እኔ ግን ሕግህን ከመታዘዝ ዘወር አልልም። 52 ያህዌ ሆይ ከረጅም ጊዜ በፊት የሰጠኸንን ደንቦችህን ሳስብ ተጽናናሁ። 53 ክፉ ሰዎች ሕግህን ቸል ሲሉ ሳይ እጅግ እቆጣለሁ። 54 እዚህ በዚህች በምድር ላይ ለአጭር ጊዜ ስኖር ስለ ሥርዓትህ መዝሙሮችን ጽፌአለሁ። 55 ያህዌ ሆይ በሌሊት ስለ አንተ አስባለሁ፤ በመሆኑም ሕግህን እታዘዛለሁ። 56 ዘወትር ያደረግሁት ነገር የመልካም ምግባር መርሆዎችህን መታዘዝ ነው። 57 ያህዌ ሆይ የመረጥኩት አንተን ነው፤ ቃልህንም ለመታዘዝ ቃል እገባለሁ። 58 በመላው ውስጣዊ ማንነቴ መልካም እንድትሆንልኝ እማጸንሃለሁ፤ እንደምታደርገው ቃል እንደገባህልኝ ቸርነትን አድርግልኝ። 59 ስለ መልካም ምግባሬ/ጸባዬ አስቤአለሁ፤ የምትፈልግብንን ወደ መታዘዝ ለመመለስም ወስኜአለሁ። 60 ትዕዛዛትህን ለመታዘዝ ፈጠንሁ፤ ከቶም አልዘገይም። 61 አዳኝ አንድ እንስሳን በመረብ ለመያዝ እንደሚሞክር ክፉ ሰዎች ሊይዙኝ ሞክረዋል። እኔ ግን ሕግህን አልረሳሁም። 62 በእኩለ ሌሊት እነቃለሁ፤ ፍትሐዊ ስለሆኑት ትዕዛዛትህ እወድስሃለሁ። 63 ስለ አንተ ታላቅ አክብሮት ላላቸው ሰዎች ሁሉ የመልካም ምግባር መርሆዎችህን ለሚታዘዙ ባልንፈራ ነኝ። 64 ያሕዌ ሆይ በምድር ሁሉ ላይ ያሉትን ሰዎች በታማኝነት ትወዳለህ። ሥርዓትህን አስተምረኝ። 65 እንደምታደርግ ቃል እንደገባኸው ያህዌ ሆይ መልካም ነገሮችን አድርገህልኛል። 66 ምን እንደማደርግ ከመወሰኔ በፊት በጥንቃቄ ማሰብ አስተምረኝ ትዕዛዛትህን መታዘዝ ለእኛ ተገቢ/ትክክለኛ እንደሆነ ስለማምን ማወቅ የሚያስፈልጉኝን ሌሎች ነገሮች አስተምረኝ። 67 ጉዳት ሳይደርስብኝ በፊት ስሕተት የነበሩ ነገሮችን አድርጌአለሁ። አሁን ግን ቃልህን እታዘዛለሁ። 68 አንተ እጅግ መልካም ነህ፤ የምታደርገውም መልካምነው፤ ሥርዓትህን አስተምረኝ። 69 ትዕቢተኛ ሰዎች ስለ እኔ በርካታ ውሸቶችን ተናግረዋል፤ እኔ ግን የመልካም ምግባር መርሆዎችህን እታዘዛለሁ። 70 እነዚያ ሰዎች ሀሳበ ግትር ናቸው፤ እኔ ግን በሕግህ ደስ ይለኛል። 71 በውጤቱ ሥርዓትህን በመማሬ መከራ ያደረስክብኝ ለእኔ መልካም ነበር/ጠቅሞኛል። 72 የምትሰጠን ሕጎች ለእኔ ከወርቅ ይልቅ ከአእላፋት ወርቅና ብር ይልቅ የበለጠ ዋጋ ያላቸው ናቸው። 73 አንተ ፈጠርኸኝ፤ አካሌንም አበጃጀህ፤ ትዕዛትህን እንድማር ጠቢብ እንድሆን እርዳኝ። 74 በቃልህ እንደታመንኩ ስለሚያዩ ለአንተ ታላቅ አክብሮት ያላቸው ለእኔ ያደረግህልኝን አይተው ደስ ይላቸዋል። 75 ያህዌ ሆይ ደንቦችህ ትክክል እንደሆኑና ያለማቋረጥ ስለምትወደኝ መከራ እንድቀበል እንዳደረግህ አውቃለሁ። 76 እንደምታደርገው እንደተናገርከኝ በታማኝነት እንደምትወደኝ በማሳየት አጽናናኝ። 77 በሕግህ ደስ ስለምለኝ በሕይወቴ መኖሬን እንድቀጥል እንደ ምሕረትህ አድርግልኝ። 78 በሐሰት የሚከስሱኝ ትዕቢተኛ ሰዎች እንዲያፍሩ አድርግ፤ እኔ ግን [ሕግህን] ማሰላሰሌን እቀጥላለሁ። 79 የምታዝዘውን ነገር እንዲማሩ ለአንተ ታላቅ አክብሮት ያላቸው ወደ እኔ ተመልሰው እንዲመጡ አድርግ። 80 ሥርዓትህን ባለመጠበቄ እንዳላፍር እነርሱን በፍጹምነት እንድታዘዛቸው አስችለኝ። 81 ከጠላቶቼ እንድታድነኝ አንተን እየጠበቅሁ ነው፤ ምን እንደምታደርግ እንደምትነግረኝ በመተማመን እጠባበቃለሁ። 82 እንደምታደርግ ቃል የገባኸውን እንድታደርግ ለረጅም ጊዜ በመጠባበቅ ዓይኖቼ ደከሙ። "የምትረዳኝ መቼ ነው?" በማለትትም እጠይቃለሁ። 83 በቤት ውስጥ ለረጅም ጊዜ በመንጠልጠሉ እንደተጨማደደ አቁማዳ የማልጠቅም ሆኛለሁ፤ ነገር ግን ሥርዓትህን አልረሳሁም። 84 እስከ መቼ ድረስ መጠበቅ ይኖርብኛል? የሚያሳድዱኝን የምትቀጣው መቼ ነው? 85 ሕግህን የማይታዘዙ ትዕቢተኛ ሰዎች እንድወድቅበት ጥልቅ ጉድጓድ እንደቆፈሩልኝ ዓይነት ነው። 86 ትዕዛዛትህ ሁሉ ሊታመኑ የሚገባቸው ናቸው፤ ነገር ግን ሰዎች ስለ እኔ እየዋሹ ያሳድዱኛል፤ ስለዚህ እባክህ እርዳኝ። 87 እነዚያ ሰዎች ሊገድሉኝ ጥቂት ቀርቷቸው ነበር፤ እኔ ግን የመልካም ምግባር መርሆዎችህን መታዘዝ አላቆምኩም። 88 በታማኝነት ስለምትወደኝ መኖሬን እንድቀጥል ፍቀድልኝ። 89 ያህዌ ሆይ ቃልህ ለዘለዓለም ይቆያል፤ በሰማይ በጽኑ ተያይዞአል። 90 ገና ላልተውሰለዱት ማድረግህን በታማኝነት ትቀጥላለህ። ምድርን በስፍራዋ አኖርሃት፤ እዚያም ጸንታ ትኖራለች። 91 እስከዚህ ቀን ድረስ አንተ እንዲቆዩ ስለ ወሰንክላቸው በምድር ላይ ሁሉም ነገሮች ይኖራሉ። በምድር ላይ ሁሉም ነገር አንተን ያገለግላል። 92 ሕግህን በመታዘዝ ደስተኛ ባልሆን ኖሮ በደረሰብኝ መከራ ምክንያት እሞት ነበር። 93 የመልካም ምግባር መርሆዎችህን በጭራሽ አልረሳም፤ ምክንያቱም እነርሱን በመታዘዜ በሕይወት መኖር እንድቀጥል አስችለኸኛል። 94 እኔ ይአንተ ነኝ፤ የመልካም ምግባር መርሆዎችህን ለመታዘዝ በመሞከሬ ከጠላቶቼ አድነኝ። 95 ክፉ ሰዎች ሊገድሉኝ እየጠበቁኝ ናቸው፤ እኔ ግን ስለምትፈልግብን ነገሮች አስባለሁ። 96 ለሁሉም ነገር ገደብ እንዳለው ተምሬአለሁ፤ ትዕዛዛትህ ግን ገደብ የላቸውም። 97 ሕግጋትህን እጅግ በጣም እወድዳቸዋለሁ፤ ቀኑን ሙሉ አሰላስላቸዋለሁ። 98 ትዕዛዛትህን ስለማውቃቸውና ሁልጊዜ ስለ እነርሱ ስለማስብ ከጠላቶቼ ይበልጥ ጢብብ ሆኛለሁ። 99 አንተ የምታዝዘውን ነገር ስልማሰላስል ክአስተማሪዎቼ ይበልጥ እገነዘባለሁ። 100 የመልካም ምግባር መርሆዎችህን ስለምታዝዝ ከብዙ በዕድሜ የገፉ ሰዎች ይበልጥ እገነዘባለሁ።
Chapter 120
1 በጨነቀኝ ጊዜ፣ ወደ ያሕዌ ተጣራሁ እርሱም መለሰልኝ። 2 "ያሕዌ ከሚዋሹኝና ከሚያታልሉኝ አድነኝ" ብዬ ጸለይኩ። 3 እናንተ የዋሻችሁኝ ሰዎች፣ እናንተን ለመቅጣት እግዚአብሔር ምን እንደሚያደርግ እነግራችኋለሁ። 4 ወታደሮች እንደሚያደርጉት የተሳሉ ቀስቶችን ይልክባችኋል እንደ በረሃ እንጨት ፍም ያቃጥላችኋል። 5 በቄዳን ከሚኖሩ ጨካኝ ሰዎች ጋር መኖር ለእኔ እጅግ የከፋ ነገር ነው። 6 ከሌሎች ሰዎች ጋር በሰላም መኖር ከማይፈልጉ ሰዎች ጋር ለብዙ ዓመታት ኖሬአለሁ። 7 በሰላም አብሮ ስለመኖር ከእነርሱ ጋር በተነጋገርኩ ቁጥር እነርሱ ጦርነትን ስለ መጀመር ይናገራሉ።
Chapter 121
1 ወደ ኢየሩሳሌም ስንጓዝ፣ ወደ ተራሮች ተመለከትኩና እንዲህ ስል ጠየቅሁ፣ "የሚረዳኝ ማነው?" 2 መልሴ እንዲህ የሚል ነው የሚረዳኝ ያሕዌ ብቻ ነው እርሱ ሰማይንና ምድር የሠራ ነው። 3 የሚጠብቀን እግዚአብሔር አይተኛም እንድንወድቅም አይፈቅድም። 4 እስራኤልን የሚጠብቅ አይተኛም አያንቀላፋምም። 5 ይሕዌ ይመለከተናል፣ እርሱ ከፀሐይ ቃጠሎ እንደሚከልል ጥላ ነው። 6 ፀሐይ በቀን እንድትጎዳን አይፈቅድም፣ በሌሊትም ጨረቃ እንድትጎዳን አይፈቅድም። 7 ያሕዌ ከማንኛውም ዓይነት ጉዳት ይጠብቀናል፣ በሰላም ይጠብቀናል። 8 ቀን ቤታችንን ትተን ስንሄድ ማታ ተመልሰን እስክንመጣ ድረስ ይጠብቀናል፣ አሁንና ለዘላለምም ይጠቀናል።
Chapter 122
1 ሰዎች "በኢየሩሳሌም ወዳለው የያሕዌ ቤተ መቅደስ እንሄዳለን" ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ! 2 አሁን እኛ በኢየሩሳሌም በሮች አጠገብ ቆመናል። 3 ኢየሩሳሌም እጅግ ውብ ሆና የተሠራች ከተማ ናት። 4 እኛ፣ የያሕዌ የሆንን የእስራኤል ነገዶች፣ ያሕዌ እንዳዘዘን፣ ልናደርግና ልናመሰግነው ወደዚያ እንሄዳለን። 5 በዚያ የእስራኤል ነገሥታት፣ የንጉሥ ዳዊት ዘሮች፣ በዙፋኖቻችሁ ላይ ይቀመጣሉ፣ ሕዝቡም ያለውን ክርክር ሲያቀርብላቸው በጽድቅ ይፈርዳሉ። 6 በኢየሩሳሌም ሰላም እንዲሆን ጸልዩ፣ ኢየሩሳሌምን ለሚወዱ የሕይወት ስኬት ይሁንላቸው 7 በከተማዋ ግንቦች ውስጥ ሰላም ይሁን፣ በቤተ መንግሥት ውስጥ የሚኖሩትም በሰላም ይጠበቁ። 8 ለዘመዶቼና ለጓደኞቼ እንዲህ እላለሁ፣ "በኢየሩሳሌም ውስጥ ለሚኖር ሰላም ይሁን።" 9 የአምላካችንን የያሕዌን ቤተ መቅደስ ስለምወድ፣ በኢየሩሳሌም ውስጥ ለሚኖሩ ሰላም እንዲሆን እጸልያለሁ።
Chapter 123
1 ያሕዌ፣ ወደ አንተ ወደ ላይ ወደ ሰማይ ወደምትገዛበት እመለከታለሁ። 2 ሠራተኞች አሠሪአቸውን እንደሚጠይቁ የቤት ሠራተኛም እመቤቷን ስለሚያስፈልጋት ነገር እንደምትጠይቅ፣ ያሕዌ አምላካችን ስለምንፈልገው ነገር አንተን እንጠይቃለን አንተ በምሕረት እስከምትመልስልን ድረስ። 3 ያሕዌ፣ በምሕረትህ አስበን ምክንያቱም ጠላቶቻችን በከፍተኛ ጥላቻ ተመልከተውናል፣ 4 እብሪተኛ ሰዎች በእኛ ቀልደዋል፣ ኩራተኛ ሰዎችም ጨቁነውናል፣ እንደማንጠቅም ሰዎች ቆጥረውናል።
Chapter 124
1 እናንተ የእስራኤል ሕዝቦች፣ ይህንን ጥያቄ መልሱ፦ ያሕዌ ባይረዳን ኖሮ ምን ይሆንብን ነበር? 2 ጠላቶቻችን ባጠቁን ጊዜ፣ ያሕዌ ስለ እኛ ባይዋጋልን ኖሮ 3 ሁላችንንም በገደሉን ነበር በእኛ እጅግ ተናድደዋልና! 4 ጠራርጎ እንደሚወስድ ጎርፍ በሆኑብን ነበር፣ ውሃውም በላይችን በተከደነ ነበር፣ 5 እኛም በጎርፉ ውስጥ በሰጠምን ነበር። 6 ነገር ግን ያሕዌ ይመስገን ጠላቶቻችን እንዲያጠፉን አልፈቀደላችውም 7 ወፍ ከወጥመድ እንደሚተርፍ ከጠላቶቻችን እጅ አመለጥን፣ ጠላቶቻችን ያጠመዱብን ወጥመድ ተሰበረ እኛም አመለጥን! 8 የረዳን ያሕዌ ነው፣ እርሱ ሰማይንና ምድርን የሠራ ነው።
Chapter 125
1 በያሕዌ የሚታመኑ፣ ከስፍራው እንደማይነቃነቅ ወይም እንደማይናወጥ እንደ ጽዮን ተራራ ናቸው። 2 በኢየሩሳሌም ዙሪያ ያሉ ተራሮች እንደሚጠብቋት ያሕዌም ሕዝቦቹን ይጠብቀናል፣ እርሱ ለዘላለም ይጠብቀናል። 3 ጻድቃን በሚኖሩበት ምድር ክፉ ሰዎች እንዲገዙ አይፈቀድላቸውም። ይህን ካደረጉ፣ እነዚያ ቅዱሳን እነርሱም የተሳሳተ ነገር ማድረግ እንዳለባቸው ያስባሉ። 4 ያሕዌ፣ ለሌሎች መልካም ነገር ለሚያደርጉ ከልብ ትእዛዛትህን ለሚፈጽሙ መልካም ነገር አድርጉላቸው። 5 አንተን የማይታዘዙትን እስራኤላውያንን ስትቀጣቸው፣ እንደ ሌሎች ክፉ አድራጊዎች ትቀጣቸዋለህ። ይህም ለእስራኤል ሕዝብ ደህንነት ይሆናል።
Chapter 126
1 ያሕዌ ኢየሩሳሌምን እንደገና ባለጠጋ ሲያደርጋት እጅግ ደስተኞች ሆንን፣ ሕልም የምናይ ነበር የመሰለን። 2 እጅግ በጣም ደስተኞች ሆንን፣ በደስታም መጮሃችንን ቀጠልን። የሌላ አገር ሰዎች ስለ እኛ እንዲህ አሉ፣ "ያሕዌ ታላቅ ነገር አደረገላቸው!" 3 እኛም እንዲህ አልን፣ "አዎ፣ ያሕዌ በእውነት ታላቅ ነገር አደረገልን ደስም አለን። 4 ኦ ያሕዌ፣ በደቡብ የይሁዳ በረሃ እንዳሉ ወንዞች ምርኮአችንን መልስልን መንግሥታችንን እንደገና ታላቅ አድረገው። 5 ለብዙ ዓመታት ያልታረሰውን ምድር ስናርስ እጅግ ከባድ ሥራ ይሆንብናል ስለዚህ ዘር ለመዝራት እንጮሃለን። አሁን ግን ታላቅ ምርት ስላገኘን በደስታ እንዘምራለን። 6 በሄዱ ጊዜ ዘራቸውን ተሸክመው እያለቀሱ ተሰማሩ በተመለሱ ጊዜ ነዶአደውን ተሸክመው በደስታ ይመለሳሉ።
Chapter 127
1 ያሕዌ ሳይረዳቸው በራሳቸው ጥረት ብቻ ቤት ለመሥራት የሚጥሩ፣ በከንቱ ይደክማሉ። በተመሳሳይ ሁኔታ፣ ያሕዌ ከተማን ካልጠበቀ፣ ጠባቂዎች በሌሊት መንቃታቸው ከንቱ ነው። 2 በማለዳ መነሳታችሁና ብዙ ገንዘብ ለማግኘት ቀኑን ሙሉ እና እስከ ሌሊት መሥራታችሁ ከንቱ ነው፣ ያሕዌ እርሱ ለሚወዳቸው ምግብን ይሰጣቸዋል። 3 ልጆች የያሕዌ ስጦታዎች ናቸው፣ እነርሱ ያሕዌ የሚሰጣቸው ዋጋ ናቸው። 4 ወታደሩ ቀስትና ጦር በእጁ ቢኖረው ራሱን እንደሚከላከል፣ በጎልማስነት የወለዳቸው ልጆቹ ሲያድጉ እርሱንና ቤተሰቡን ይከላከሉለታል። 5 ብዙ ልጆች ያሉት ስደው ምናኛ የታደለ ነው፣ እርሱ ብዙ ቀስቶች እንዳሉት ወታደር ነው፣ ብዙ ልጆች ያሉት ሰው ጠላቶች ቢመጡበት፣ ሊያሸንፉት ፈጽሞ አይችሉም ያደጉት ልጆቹ ያግዙታል ጠላቶቹን ያሸንፉለታል።
Chapter 128
1 ለእርሱ ታላቅ አክብሮት ያለህ እና እንድታደርግ የሚፈልገውን የምታደርግ እንዴት የታደልክ ነህ። 2 ምግብህን በደስታ ትመገባለህ፣ መላምም ይሆንልሃል። 3 ሚስትህ ብዙ እንደሚያፈራ ወይን ናት፣ ብዙ ልጆችን ትወልዳለች። ልጆችህ በማዕድህ ዙሪያ ይቀመጣሉ፣ አንተም እንደ ብዙ ቅርንጫፎች እንዳሉት የወይራ ዛፍ ትሆናለህ። 4 ያሕዌ፣ ለእርሱ ታላቅ አክብሮት ያላቸውን ሰዎች እንዲህ ይባርካቸዋል። 5 እግዚአብሔር በጽዮን ተራራ በመቅደሱ አብዝቶ እንዲረዳህ እመ ኛለሁ፣ የኢየሩሳሌም ሰዎችም በየቀኑ ሲበለጽጉ በሕይወት ዘመንህ ትመለክታለህ! 6 አንተም ረጅም እድሜ ትኖራለህ፣ የልጅ ልጆችንም ታያለህ። ይህ ሁሉ መልካም ነገር ለእስራኤል ሕዝብ ሁሉ ይሁን!
Chapter 129
1 ከልጅነቴ ጀምሮ ጠላቶቼ ተሰለፉብኝ። አሁን እናንተ እስራኤላውያን ወገኖቼ፣ ያጥኑ ቃል እንድትደግሙት እጠይቃችኋለሁ። 2 "መንግሥታችን ከጀመረበት ጊዜ ጀምሮ ጠላቶቻችን ተሰለፉብን፣ ነገር ግን አላሸነፉንም! 3 ጠላቶቻችን ገበሬ መሬትን በማረሻ እንደሚያርስ፣ ጀርባችንን በጅራፍ ተለተሉት።" 4 ያሕዌ ግን ጻድቅ ነው፣ ለክፉ ሰዎች ባሪያ ከመሆን አድነን ነጻም አውጣን። 5 ስላሸነፍናቸው ማፈር አለባቸው፣ የኢየሩሳሌም ጠላቶች በሙሉ ይፈሩ። 6 እነርሱ፣ በቤት ጣሪያ ላይ እንደሚበቅል ሣር፣ የማይጠቅሙ ናቸው፣ በፀሐይ ሙቀት ይደርቃሉ አይበቅሉምም፣ 7 ማንም አጭዶ አያስራቸውም አይሸከማቸውምም። 8 በዚያ የሚያልፉ ሰዎች፣ "ያሕዌ ይባርካችሁ" አይሉአቸውም! ለእስራኤል ጠላቶች መልካም አይሆንም። እኛ፣ እንደ ያሕዌ ተወካዮች፣ እናንተ እስራኤላውያንን እንባርካችኋለን።
Chapter 130
1 ያሕዌ፣ ታላቅ መከራ ስላለብኝ፣ ወደ አንተ እጣራለሁ። 2 ያሕዌ፣ ወደ አንተ ስጣራ፣ ስማኝ ማረኝም! 3 ያሕዌ፣ የሠራነውን ኃጢአት ብትመዘግብብን፣ አንዳችንም ከመወንጀልና ከመቀጣት አናመልጥም! 4 ነገር ግን ማረን፣ ለአንተ ታላቅ አክብሮት አለንና። 5 ያሕዌ እንደሚረዳኝ ተናገረኝ፣ የተናገረውን አምናለሁ፣ ይህንንም እንዲያደርግ በጉጉት እጠብቃለሁ። 6 ንጋትን ከሚጠባበቅ ጠባቂ በላይ ያሕዌ እንዲረዳኝ ተጠባበቅሁ፣ አዎ፣ እነርሱ ከሚያደርጉት በላይ ጠበቅሁ! 7 እናንት፣ እስራኤላውያን ወገኖቼ፣ ያሕዌ እንደሚባርከን በመተማመን ተጠባበቁ። እነርሱ በእኛ ላይ ምሕረቱን አድርጎአልና ይባርከናል፣ ሊያድነንም ፈቀደኛ ነው። 8 ከሠራናቸው ኃጢአቶቻችን የተነሣ ከሚደርስብን ቅጣት እኛን እስራኤላውያንን ያድነናል።
Chapter 131
1 ያሕዌ፣ አልታበይም፣ የሚያስደንቅ ነገር በሕይወቴ እንዳገኘሁ አልኩራራም እኔ መልስ ለማላገኝላቸው ችግሮች አልጨነቅም። 2 ይልቁንም ክአናቱ ጋር መሆን ደስ እንደሚያሰኘው እንደ ሕፃን ልጅ በሰላም ጸጥ እላለሁ፣ በተመሳሳይ ሁኔታ በውስጤ ሰላም አለኝ። 3 እናንት እስራኤላውያን፣ ያሕዌ ለእናንተ መልካም ነገርን አሁንና ለዘላለም ያደርግላችኋል ይህንን ከእርሱ ተጠባበቁ።
Chapter 132
1 ያህዌ ሆይ ዳዊትን እና የታገሠውን መከራውን ሁሉ አትርሳ! 2 አባታችን ያዕቆብ ላመለከህ ኃያል አምላክ የከበደ ቃል ኪዳን አደረገ። 3 "እቤቴ አልሄድም፤ በአልጋዬ ላይ አላርፍም፤ 4 ከቶውንም አልተኛም 5 ለያህዌ ስፍራ ያዕቆብ ላመለክው ኃያል አምላክ ቤት እስካዘጋጅለት ደርስ" አለ። 6 በቤተልሔም ስለተቀደስው ታቦት ዜና ሰማን። ሄደን በቂርያት ኢያሪም አገኘነው፤ ወደ ኢየሩሳሌምም ወሰድነው። 7 ከዚያም፦ "በኢየሩሳሌም ወደ ያህዌ የተቀደሰ ድንኳን እንሂድ፤ እርሱ በተቀመጠበት በዙፋኑ ፊት በዚያ እናምልክ" አልን። 8 ያህዌ ሆይ ለዘለዓለም ወደምትኖርበት ስፍራ የተቀደሰው ታቦትህ ወዳለበት ስፍራ እጅግ ኃይለኛ መሆንህን ወደሚያሳየው ስፍራ ና። 9 የካህናትህ የጽድቅ ባሕርይ ዘወትር በግልጽ የሚታይ እንዲሆንና ሕዝብህ ዘወትር በደስታ ድምፃቸው ከፍ እንዲል እፈልጋለሁ። 10 የእስራኤል ንጉሥ ሆኖ እንዲያገለግልህ ዳዊትን መረጥከው፤ አታስወግደው! 11 ያህዌ ሆይ የማታጥፈው ቃል ኪዳን የከበደ ቃል ኪዳን ለዳዊት አደረግህ፤ "ዝርያዎችህ እንደ አንተ ንጉሦች ሆነው እንዲገዙ አደርጋለሁ፤ 12 ከእነርሱ ጋር የማደርገውን ቃል ኪዳኔን እና የምሰጣቸውን ትዕዛዛት ሁሉ ከታዘዙ ከአንተ ቀጥለው የሚወርሱ የነገሥታት ዘር ጭራሽ አያቆምም" አልክ። 13 ያህዌ ኢየሩሳሌምን መርጧል፤ ይቺን ከተማ ቤቱ ሊያደርጋት ፈልጓል። 14 "ለዘለዓለም የምኖርባት ከተማ ይህች ናት፤ መቆየት የምፈልግበት ቦታ ይህ ነው" አለ። 15 ለኢየሩሳሌም ሕዝብ የሚያስፈልጋቸውን ሁሉ እሰጣቸዋለሁ፤ እዚያ ያሉትን ምስኪን ሰዎች ለማርካት በቂ ምግብ እሰጣለሁ። 16 ካህናቱ ላዳንኳቸው ሰዎች በሚመጥን መልኩ እንዲኖሩ አደርጋቸዋለሁ እዚያ የሚኖሩ ሕዝቤ ሁሉ በደስታ ድምፃቸውን ክፍ ያደርጋሉ። 17 በዚያ በኢየሩሳሌም ከዳዊት ዝርያዎች አንዱ ታላቅ ንጉሥ እንዲሆን አደርጋለሁ። የእኔም የተመረጠ ንጉሥ ይሆናሉ። የዳዊት ወራሽ ዝርያ እንዲቀጥል የማደርገው በዚያ ነው። 18 ጠላቶቹን ድል እነሣና እጅግ እንዲያፍሩ አደርጋቸዋለሁ። ንጉሤ የሚደፋው አክሊል ግን ዘወትር ያበራል።"
Chapter 133
1 የእግዚአብሔር ሰዎች በሰላም በአንድነት ሲቀመጡ እጅግ ደስ ያሰኛል። 2 ሙሴ አሮንን ሲቀባው ከራሱ ጀምሮ በልብሱ መደረቢያ እንደወረደ የሽቱ ዘይት ነው። 3 በሰላም መሰብሰብ በአርሞንኤም ተራራ እንደሚወርድ በጽዮንም ተራራ እንደሚወርድ ጠል ነው። ያሕያዌ በዚያ የእስራኤልን ልጆች መንግሥታቸውንም በኢየሩሳሌም ለዘላለም እንዲኖር ይባርካል።
Chapter 134
1 ያሕዌን የምታገለግሉ ሰዎ ች ሁሉ፣ በሌሊት በመቅደሱ ልታገለግሉት በፊቱ ቁሙ፣ ኑና አመስጉኑት! 2 በመቅደሱ እጆቻችሁን አንስታችሁ ወደ እርሱ ጸልዩ በመቅደሱም አመስግኑት! 3 ሰማይንና ምድርን የሠራ ያሕዌ፣ ከማደሪያው በጽዮን ተራራ በመቅደሱ ይባርክህ።
Chapter 135
1 ያህዌ ይወደስ! እናንተ ያህዌን የምታመልኩ ወድሱት! 2 በአምላካችን በያህዌ ቤተ መቅደስ በአደባባዮቹ የምትቆሙ ወድሱት! 3 መልካም ነገሮችን ስላደረግልን ያህዌን ወድሱት፤ ቸርነትን ስላደረገልን ዘምሩለት። 4 እኛን የያዕቆብ ን ዝርያዎች መርጦናል። 5 እነዚህን ነገሮች የምለው ያህዌ ታላቅ እንደሆነ ክአማልክትም ሁሉ የበለጠ ታላቅ እንደሆነ ስለማውቅ ነው። 6 በሰማይና በምድር፣ በባሕሮችና በባሕር ታችኛ ክፍሎች ላይ ማድረግ የሚፈልገውን ነገር ሁሉ ያህዌ ያደርጋል። 7 በምድር ላይ ከራቁ ስፍራዎች ደመናት እንዲወጡ የሚያደርግ እርሱ ነው። ከዝናቡ ጋር መብረቅ እንዲያበራ ያደርጋል፤ እነርሱን ካከማቸባቸው ስፍራዎች ንፋሳትን ያመጣል። 8 በግብፅ በመጀመሪያ የተወለዱ ወንዶችን የሰዎችንም የእንስሳትንም የመጀመሪያዎቹን የገደለው እርሱ ነው። 9 በዚያም ንጉሡንና ባለሥልጣናቱን ሁሉ ለመቅጣት ብዙ ዓይነት ተአምራትን አደረገ። 10 ብዙ ሕዝቦችንና የሚገዟቸውን ኃይለኛ ነገሥታት አጠፋ። 11 የአሞር ሕዝብ ንጉሥን ሲሆንን፣ በባሳን ንጉሥ ይገዛ የነበረውን ክልል ኦግን፣ በከነዓን ምድር ሌሎች ነገሥታትን ሁሉ አጠፋ። 12 ምድራቸውን ለእኛ ለእስራኤል ሕዝብ ለዘለዓለም ለእኛ እንዲሆን ሰጠ። 13 የያህዌ ስም ለዘለዓለም ጸንቶ ይኖራል፤ ገና ያልተወለዱ ሕዝብም አንተ ያደረግኻቸውን ታላላቅ ነገሮች ያስታውሳሉ። 14 ያህዌ እኛ ሕዝቡ ያለ በደል መሆናችንን ይናገራል፤ በምሕረትም ያደርግናል። 15 ነገር ግን ሌሎች ሕዝቦች የሚያመልኳቸው ጣኦታት የብርና የወርቅ ሐውልቶች ሰዎች የሠሯቸው ነገሮች ናቸው። 16 ጣኦቶቻቸው አፍ አላቸው፤ ነገር ግን ምንም ነገር ማለት አይችሉም። ዓይኖች እሏቸው፤ ነገር ግን ምንም ነገር ማየት አይችሉም። 17 ጆሮዎች አሏቸው፤ ነገር ግን ምንም ነገር መስማት አይችሉም። ለመተንፈስ እንኳን አይችሉም። 18 እነዚህን ጣኦታት የሚሠሯቸው ሰዎች እንደ እነዚያ ጣኦታት ኃይል የለሽ ናቸው፤ በእነዚህ ጣኦታት የሚታመኑም ጣኦቶቻቸው ከሚችሉት በላይ ምንም ማከናወን አይችሉም! 19 ያገሬ ሕዝብ እስራኤላውያን ያህዌን አወድሱ! እናንተ የአሮን ተወላጆች ዝርያዎቹ ካህናት ያህዌን አወድሱ! 20 እናንተ የሌዊ ተወላጆች ዝርያዎቹ እናንተ ካህናቱን የምትረዱ ያህዌን አወድሱ! እናንተ ለያህዌ አምልኮአዊ አክብሮት ያላችሁ ሁሉ አወድሱት! 21 በኢየሩሳሌም በጽዮን ተራራ በሚኖርበት በቤተ መቅደሱ ውስጥ ያህዌን አወድሱ! ያህዌ ይወደስ!
Chapter 136
1 መልካም ነገሮችን ስለሚያደርግልን ያህዌን አመስግኑ። ቃል እንደገባው ለዘለዓለም ይወደናል። 2 ከሌሎች አማልክት ሁሉ በላይ ታላቅ የሆነውን እግዚአብሔርን አመስግኑ። 3 ቃል እንደገባው ለዘለዓለም ይወደናል። 4 ታላላቅ ተአምራትን የሚሠራ እርሱ ብቻ ነው። ቃል እንደገባው ለዘለዓለም ይወደናል። 5 በጠቢብነቱ ሰማያትን የፈጠር እርሱ ነው፤ ቃል እንደገባው ለዘለዓለም ይወደናል። 6 ምድርን ከጥልቁ ውሃ በላይ እንዲነሳ ያደረገ እርሱ ነው፤ ቃል እንደገባው ለዘለዓለም ይወደናል። 7 በሰማያት ላይ ታላላቅ ብርሃናትን የፈጠረ እርሱ ነው፤ ቃል እንደገባው ለዘለዓለም ይወደናል። 8 በቀኑ ክፍለ ጊዜ ፀሐይ እንድታበራ ፀሐይን ፈጠራት፤ ቃል እንደገባው ለዘለዓለም ይወደናል። 9 በማታው ክፍል ጊዜ እንዲያበሩ ጨረቃንና ከዋክብትን ፈጠረ፤ ቃል እንደገባው ለዘለዓለም ይወደናል። 10 በግብፅ በመጀመሪያ የተወለዱትን ወንዶች የገደለ እርሱ ነው፤ ቃል እንደገባው ለዘለዓለም ይወደናል። 11 እስራኤላውያንን ከግብፅ አውጥቶ መራቸው። ቃል እንደገባው ለዘለዓለም ይወደናል። 12 በብርቱ እጁ እየመራ አወጣቸው። ቃል እንደገባው ለዘለዓለም ይወደናል። 13 የቀይ/የደንቀል ባሕርን እንዲከፈል ያደረገ እርሱ ነው፤ ቃል እንደገባው ለዘለዓለም ይወደናል። 14 እስራኤላውያን በምካከሉ በደረቅ ምድር እንዲሄዱ አስቻላቸው። ቃል እንደገባው ለዘለዓለም ይወደናል። 15 የግብፅ ንጉሥና ሠራዊቱ ግን በውስጡ እንዲሰምጡ አደረገ። ቃል እንደገባው ለዘለዓለም ይወደናል። 16 ሕዝቡን በምድረ በዳ በደህና የመራ እርሱ ነው፤ ቃል እንደገባው ለዘለዓለም ይወደናል። 17 ኃይለኛ ነገሥታትን ገደለ፤ ቃል እንደገባው ለዘለዓለም ይወደናል። 18 ዝነኛ የነበሩ ነገሥታትን ገደለ፤ ቃል እንደገባው ለዘለዓለም ይወደናል። 19 የአሞርን ሕዝብ ንጉሥ ሲሆንን ገደለ፤ ቃል እንደገባው ለዘለዓለም ይወደናል። 20 የባጎንን ክልል ንጉሥ ኦግን ገደለ፤ ቃል እንደገባው ለዘለዓለም ይወደናል። 21 ምድራቸውን ለእኛ ለሕዝቡ ሰጠ፤ ቃል እንደገባው ለዘለዓለም ይወደናል። 22 እነዚያን ምድሮች ለምናገለግለው ለእኛ ለእስራኤል ሕዝብ ሰጠ፤ ቃል እንደገባው ለዘለዓለም ይወደናል። 23 ጠላቶቻችን ባሸነፉን ጊዜ ያልረሳን እርሱ ነው፤ ቃል እንደገባው ለዘለዓለም ይወደናል። 24 ከጠላቶቻችን ታድጎናል፤ ቃል እንደገባው ለዘለዓለም ይወደናል። 25 ሕይወት ኣላቸው ፍጥረታት ሁሉ ምግብን የሚሰጥ እርሱ ነው፤ ቃል እንደገባው ለዘለዓለም ይወደናል። 26 ስለዚህ በሰማይ የሚኖረውን አምላክ አምስግኑ፤ ምክንያቱም ቃል እንደገባው ለዘለዓለም ይወደናል።
Chapter 137
1 ከኢየሩሳሌም ርቀን ወደ ባቢሎን በተወሰድን ጊዜ፣ በዚያ ባሉ ወንዞች አጠገብ ተቀመጥን፣ በኢየሩሳሌም ያለውን በጽዮን ተራራ ያለውን ቤተ መቅደስ ስናስብ አለቀስን። 2 በወንዞችም አጠገብ በነበሩት ዛፎች ላይ መሰንቆዎቻችንን ሰቀልን፣ ምክንያቱም እጅግ አዝነናልና፣ ልንዘምርባቸው አልፈለግንም። 3 የማረኩንና አስገድደው ወደ ባቢሎን የወሰዱን ወታደሮች ለእነርሱ እንድንዘምርላቸው የግድ አሉን፣ እንድናዝናናቸው ተናገሩን፣ እንዲህ አሉን፣ "በኢየሩሳሌም ስትዘምሩአቸው ከነበሩት መዝሙሮች መካከል አንዱን ዘምሩልን!" 4 ነገር ግን እኛ እንዲህ ብለን አሰብን፣ "በያሕዌ እየተቀጣን ነውና አዝነናል፣ ወደዚህም ባዕድ ምድር መጥተናል፣ በዚህ እያለን ስለ ያሕዌ መዘመር አንችልም!" 5 ኢየሩሳሌምን ብረሳ፣ ማሲንቆውን እንዳልጫወት ቀኝ እጄ ከጥቅም ውጭ ትሁን! 6 ኢየሩሳሌምን ብረሳ፣ ፈጽሞ መዘመር የማልችል ልሁን፣ ከደስታዬ ሁሉ በላይ ኢየሩሳሌምን አስባለሁና። 7 ያሕዌ፣ የኤዶም ሰዎች የባቢሎን ወታደሮች ኢየሩሳሌምን በያዙ ጌ ስላደረጉት ነገር ቅጣቸው። "ሕንፃዎቻቸውን አፍርሱ! መሠረቶቹን ብቻ አስቀርታችሁ ሌላውን ሁሉ አፍርሱ" ያሉትን አትርሳ። 8 እናንት የባቢሎን ሰዎች፣ በእርግጥ ትጠፋላችሁ! በእኛ ላይ ስላደረጋችሁት ክፉ ነገር እናንተን የሚቀጡ እንዴት የተመሰገኑ ናቸው፣ 9 ሕፃናቶቻችሁን በአለት ላይ የሚቀጠቅጡአቸው እንዴት የተመሰገኑ ናቸው።
Chapter 138
1 ያሕዌ፣ ከልቤ አመሰግንሃለሁ። ጣዖቶቹን ለማቃለል በእነርሱ ፊት ለአንተ እዘምራለሁ። 2 ወደተቀደሰው ቤተ መቅደስ ስመለከት፣ አንተ የገባህልንን ቃል ኪዳን ሁሉ በታማኝነት አድርገሃልና፣ እሰግድልሃለሁ አመሰግንሃለሁም። አንተ ከምንም ነገር በላይ እንደሆንክ አሳይተሃል፣ ለማድረግ የገባኸውን ቃል ኪዳን ሁልጊዜ ትፈጽማለህ። 3 ወደ አንተ በተጣራሁበት ቀን፣ መልሰህልኛል፣ ጠንካራ እና ደፋር እንድሆን አስችለኸኛል። 4 ያሕዌ፣ አንድ ቀን የምድር ነገሥታት ሁሉ ያመሰግኑሃል ምክንያቱም የተናገርከውን ሁሉ ይሰማሉና። 5 ስላደረግኸው ሁሉ ይዘምራሉ፣ አንተ ታላቅ እንደ ሆንክ ይናገራሉ፣ ይዘምራሉም። 6 ያሕዌ፥ አንተ እጅግ ታላቅ ነህ፣ ነገር ግን ታናናሾችን ትጠብቃለህ፣ ትእቢተኛ ሰዎች ከአንተ የራቁና የሚታያቸው ስለሚመስላቸው የሚያደርጉትን ነገር ታውቃለህ። 7 በመከራ ውስጥ በሆንኩ ጊዜ፣ አንተ አዳንከኝ። በእኔ ላይ ከተናደዱ ከጠላቶቼ በክንዶችህ አስጣልከኝ። 8 ያሕዌ፣ የገባኽልኝን ቃል ኪዳን ሁሉ ታደርግልኛለህ፣ አንተ በታማኝነት ለዘላለም ወድደኸናል። ለእኛ የአንተ ሕዝብ ለሆንነው ለእስራኤላውያን፣ ልታደርግ የጀመርከውን ፈጽምልን።
Chapter 139
1 ያህዌ ሆይ በውስጣዊ ማንነቴ ውስጥ ያለውን ነገር መርምረሃል፤ ስለ እኔም ሁሉንም ነገር ታውቃለህ። 2 የምቀምጥበትንና የምነሳበትን ጊዜ ታውቃለህ፤ ከእኔ እጅግ የራቅህ ብትሆንም ምን እያሰብሁ እንዳለሁ ታውቃለህ። 3 በማለዳ ከምነሳበት ጊዜ አንስቶ በምሽት እስከምተኛበት ጊዜ ድረስ የማደርገውን ነገር ሁሉ ታውቃለህ። 4 ያህዌ ሆይ ምንም ነገር ከመናገሬ በፊት እንኳን ምን ልናገር እንደሆነ ሁሉ ታውቃለህ! 5 በሁሉም አቅጣጫ ትከልለኛለህ፤ እኔን በኃይልህ ለመከለል እጅህን በእኔ ላይ አደረግህ። 6 ስለ እኔ ሁሉንም ነገር ማወቅህን ልገነዘበው አልችልም። 7 ከመንፈስህ ለማምለጥ ወደየት መሄድ እችላለሁ? ከአንተ ለመራቅስ ወደየት መሄድ እችላለሁ? 8 ወደ ሰማይ ብወጣ አንተ እዚያ ትኖራለህ። የሞቱ ሰዎች ባለበት ስፍራ ብተኛ አንተ እዚያ ትኖራለህ። 9 ክንፎች ቢኖሩኝና እጅግ ወደራቀው ምሥራቅ ብበር ወይም ወደ ምዕራብ በርሬ በውቅያኖስ ውስጥ ባለ ደሴት ላይ የምኖርበትን ቦታ ባዘጋጅ፤ 10 እዚያም በእጅህ ልትመራኝ ትኖራለህ፤ ደግሞም ትረዳኛለህ። 11 ጨለማው እንዲደብቀኝ መጠየቅ እችላለሁ፤ ወይም ደግሞ ብርሃንን በዙሪያዬ ጨለማ እንዲሆን መጠየቅ እችላለሁ። 12 ያ ቢሆንም እንኳን ግን ጨለማው ለአንተ ጨለማ አይሆንም! ጨለማው ልአንተ የቀኑ ጊዜ እንደሆነው ያህል ብሩህ ነው፤ ምክንያቱም ለአንተ የቀን ብርሃንና ጨለማ ልዩነት የለውም። 13 አንተ የአካሌን ክፍሎች ሁሉ ፈጥረሃል፤ ገና በእናቴ ማኅፀን ውስጥ በነበርኩበት ጊዜ የአካሌን ክፍሎች በአንድነት አስቀምጠሃል። 14 አካሌን በሚያስገርምና በሚያስደንቅ ሁኔታ ስለ ሠራኸው አውድስሃለሁ። የምታደርገው ነገር ሁሉ አስደናቂ ነው! ያንን በሚገባ አውቀዋለሁ። 15 አካሌ ይሠራ በነበረበት ጊዜ ሌላ ማንም ሊያየው በማይችልበት ቦታ በአንድነት እየተገጣጠመ እያለ አንተ አይተኸዋል! 16 ከመወለዴ በፊት አይተኸኛል። እንድኖርባቸው የወሰንካቸው ቀናት ቁጥርን በምጽሐፍህ ውስጥ ጽፈሃቸዋል። ይህንንም ከእነዚያ ቀናት የትኛውም እንኳን ገና ሳይጀመር ነው! 17 እግዚአብሔር ሆይ ስለ እኔ የምታስበው ነገር እጅግ የከበረ ነው። የምታስባቸው ነገሮች መጠን ከፍተኛ ነው። 18 ልቆጥራቸው ብችል በባሕር ዳር ካሉ የአሸዋ ቅንጣቶች የበለጡ መሆናቸውን አያለሁ። በምነቃበት ጊዜም እስከዚያ ጊዜ ድረስ ከአንተ ጋር ነኝ። ስለኔ የምታስባቸው ገና ይበልጥ የሚቆጠሩ መኖራቸውንም አውቃለሁ። 19 እግዚአብሔር ሆይ ክፉ ሰዎችን ብትገድላቸው እመኛለሁ! በጥባጭ ስዎችም ሁሉ ቢተዉኝ እመኛለሁ! 20 ስለ አንተ ክፉ ነገሮችን ይናገራሉ፤ ስምህን ይሰድባሉ። 21 ያህዌ ሆይ የሚጠሉህን ሰዎች በእርግጥ እጠላለሁ! በአንተ ላይ የሚያምጹብህንም እጸየፋቸዋለሁ። 22 ሙሉ በሙሉ እጠላቸዋለሁ፤ ጠላቴ እንደሆኑም እቆጥራለሁ። 23 እግዚአብሔር ሆይ ውስጣዊ ማንነቴን መርምር፤ ምን እያሰብሁ እንዳለሁ እወቅ! 24 ውስጣዊ ማንነቴ ማናቸውም ክፉ ቢኖር አግኝ ክአንተ ጋር ለዘለዓለም ወደ መሆን በሚያደርሰኝም መንገድ ምራኝ።
Chapter 140
1 ያህዌ ሆይ በክፉ ሰዎች ከመጠቃት ታደገኝ፤ ይበልጡንም በበጥባጭ ሰዎች ከመጠቃት በደህና ጠብቀኝ። 2 ክፉ ነገሮችን ለማድረግ ዘወትር የሚያቅዱ ናቸው። ሰዎች ጠቦችን እንዲጀምሩም ዘወትር የሚያበረታቱ ናቸው። 3 በሚናገሩት ነገር እንደ መርዘኛ እባቦች ሰዎችን ይጎዳሉ። 4 ያህዌ ሆይ ከክፉ ሰዎች ኃይል ከልለኝ። ማጥፋትን ከሚያቅዱ በጥባጭ ሰዎች በደህና ጠብቀኝ። 5 ትዕቢተኛ ሰዎች ወጥመድ እንዳጠመዱብኝ ዓይነት ነው፤ ሊይዙኝ መረቦቻቸውን እንደዘረጉብኝ ያህል ነው፤ በመንገድ ላይ ሊይዙኝ እነዚህን ነገሮች እንዳስቀመጡ ያህል ነው። 6 "ያህዌ ሆይ አንተ አምላኬ ነህ" እልሃለሁ፤ እንድትረዳኝ ወደ አንተ ስጮህ አድመጠኝ። 7 ጌታዬ ያህዌ ሆይ በብርቱ የምትከላከልልኝ አንተ ነህ፤ በጭንቅላቴ ላይ የብረት ባርኔጣ እንዳስቀመጥክ ያህል በጦርነቶች ጊዜ ከልለኸኛል። 8 ያህዌ ሆይ ክፉ ሰዎች የሚመኟቸውን ነገሮች አትስጣቸው፤ ለማድረግ የሚያቅዷቸውን ክፉ ነገሮች እንዲያደርጉም አትፍቀድላቸው። 9 ጠላቶቼ እንዲታበዩ አትፍቀድላቸው፤ ይልቅስ በእኔ ላይ እንደሚያደርጓቸው የሚናገሯቸው ክፉ ነገሮች በእነርሱ ላይ እንዲሆኑ አድርግ። 10 የከሰል ፍም በአናቶቻቸው ላይ እንዲወድቅ አድርግ! ሊወጡ ወደማይችሉባቸው ጥልቅ ጉድጓዶች እንዲወረወሩ አድርግ! 11 ሌሎችን የሚሳደቡ ሰዎች እንዲቀናቸው አትፍቀድ፤ ክፉ ነገሮች በበጥባጭ ሰዎች ላይ እንዲሆኑ አድርግና አጥፋቸው! 12 ያህዌ ሆይ አንተ የተጨቆኑትን እንደምትሟገትላቸውና ትክክለኛ የሆነውን ነገር እንደምታደርግ አውቃለሁ። 13 ጻድቃን ሰዎች በእርግጥ ያመሰግኑሃል፤ አንተ ባለህበትም ይኖራሉ።
Chapter 141
1 ያሕዌ፣ ወደ አንተ እጣራለሁ፥ እባክህ በፍጥነት እርዳኝ! ወደ አንተ ስጣራ ስማኝ። 2 ጸሎቴን ለአንተ እንደሚቀርብ እጣን ተቀበለው። በማታ ጊዜ ወደ አንተ እንደሚቀርብ መሥዋእት እጆቼን ወደ አንተ ስዘረጋ ተቀበለኝ። 3 ያሕዌ፣ የተሳሳቱ ነገሮችን እንድናገር አትፍቀድልኝ፣ ጠባቂ በር እንደሚጠብቅ አንደበቴን ጠብቅ። 4 የምፈልገውን ነገር ከማድረግና ክፉ ሰዎች ከሚያደርጉት ክፉ ነገር ጋር ከመተባበር ጠብቀኝ። መልካም ምግብ እንኳ ከእነርሱ ጋር እንድመገብ አትፍቀድልኝ! 5 ቅዱሳን ቢገስጹኝ፣ ቢዘልፉኝም ስለ እኔ በቅንነት በማሰብና ወደ ትክክለኛው መንገድ እንድመለስ በመፈለግ ስለሆነ ትክክል ነው። ይህንን ሲያደርጉ ራሴን በዘይት እንደቀቡኝ አቆጥራለሁ፣ ነገር ግን ክፉ ሰዎችን ስለሚያደርጉት ክፉ ሥራ እንድትቀጣቸው ሁልጊዜ እጸልያለሁ። 6 መሪዎቻቸው በዓለት ገደል ውስጥ ሲጣሉ እኔ የተናገርኩት መልካም እንደሆነ ያውቃሉ። 7 በምድር ላይ እንደተፈረካከሰ ጓል ሬሳቸው በመሬት ላይ ተበታትኖ እንደሚወድቅ አንድ ቀን ያውቃሉ። 8 ነገር ግን አምላኬ ያሕዌ፣ እንድትረዳኝ መጠየቄን እቀጥላለሁ። እንድትጠብቀኝ እጠይቅሃለሁ፣ አሁን እንድሞት አትፍቀድልኝ! 9 ሰዎች ለእኔ ወጥመድ አድርገውብኛልና፣ በወጥመዳቸው እንዳልወድቅ ጠብቀኝ። እኔን ለመያዝ ወጥመዶችን ዘርግተዋል፣ በአንዚያ ወጥመዶች ከመያዝ ጠብቀኝ። 10 ክፉ ሰዎች በወጥመድ ይውደቁ ከእነርሱ ሳመልጥ ሊይዙኝ ይሞክራሉ።
Chapter 142
1 ያህዌ፣ ወደ አንተ እጮሃለህ፣ እንድትረዳኝ እማጸናለሁ። 2 ችግሮቼን ሁሉ ወደ አንተ አመጣለሁ፣ መከራዎቼን ሁሉ እነግርሃለሁ። 3 ተስፋ በቆረጥኩኝ ጊዜ፣ ማድረግ ያለብኝን አንተ ታውቃለህ፣ የትም ቦታ ብሄድ፣ ጠላቶቼ እንድወድቅበት ወጥመድ ያዘጋጁብኛል። 4 በዙሪያ ሁሉ እመለክታለሁ ማንም አይጠብቀኝም፣ ማንም በእኔ ላይ ስላደረሰው ግድ አይሰጠውም። 5 ስለዚህ ያሕዌ፣ እንድትረዳኝ ወደ አንተ እጮሃለሁ፣ የምትጠብቀኝ አንተ ብቻ ነህ. በሕይወት ዘመኔ ሁሉ የምፈልገው አንተን ነው። 6 ለእርዳታ ወደ አንተ ስጮህ ስማኝ እጅግ ተቸግሬአለሁና፣ የሚያሰቃዩኝ በርትተውብኛልና አድነኝ፣ ከእነርሱ ማምለጥ አልቻልኩምና። 7 ከመከራዎቼ ነጻ አድርገኝ የዚያን ጊዜ ላመሰግንህ እችላለሁና። ይህን ብታደርግ፣ በጽድቅ ከሚመላለሱ ጋር ሆኜ፣ ለእኔ መልካም ስለሆንክ አመሰግንሃለሁ።
Chapter 143
1 ያህዌ ሆይ ወደ አንተ ስጸልይ ስማኝ! አንተ ጻድቅ ስለሆንክና ቃል የገባህበትን ነገር በታማኝነት ስለምታደርግ እንድታደርግልኝ የምማጸንህን ነገር ስማ። 2 እኔ አንተን የማመልክ ነኝ፤ አትፍረድብኝ። ምክንያቱም አንተ ማንም ሰው ሙሉ በሙሉ ከበደል ነጻ እንደሆነ አትቆጥርም። 3 ጠላቶቼ ከኋላዬ ተከታትለውኛል፤ ሙሉ በሙሉ ድል ነሥተውኛል። ተስፋ የማደርገው ምንም መልካም ነገር በሌለበት በጨለማ እስር ቤት ውስጥ እንዳስቀመጡኝ ያህል ነው፤ 4 ስለዚህ በውስጣዊ ማንነቴ እጅግ ተስፋ ቆርጫለሁ፤ እጅግ ተጨንቄአለሁ። 5 ቀደም ሲል ምን እንደሆነ አስታውሳለሁ፤ ያደረግኻቸውን ነገሮች ሁሉ አሰላስላለሁ፤ የሠራኻቸውን ታላላቅ ድርጊቶች ሁሉ አመናለሁ። 6 ስጸልይ እጆቼን ወደ አንተ አነሳለሁ፤ በአውላላ ምድረ በዳ ውስጥ ውሃ እንደተጠማሁ ያህል ከአንተ ጋር መሆን እጅግ በጣም እፈልጋለሁ። 7 ያህዌ ሆይ እጅግ ተስፋ ቆርጫለሁ፤ ስለዚህ እባክህን አሁኑኑ መልስ ስጠኝ! ክእኔ አትራቅ፤ ምክንያቱም ያንን ካደረግህ ወዲያውኑ ሙታን ስዎች ወዳሉበት ስፍራ ከሚወርዱት መካከል እሆናለሁ። 8 በአንተ ስለምታመን በታማኝነት እንደምትወደኝ በየማለዳው እንዳስታውስ አድርገኝ። ወደ አንተ እጸልያለሁ፤ ላደርጋቸው የሚገቡኝን ነገሮች አሳየኝ። 9 ያህዌ ሆይ እንድትከልለኝ ወደ አንተ መጥቻለሁ፤ ስለዚህ ከጠላቶቼ ታደገኝ። 10 አንተ አምላኬ ነህ፤ እኔ እንዳደርግ የምተፈልገውን እንዳደርግ አስተምረኝ። መልካሙ መንፈስህ መደረግ ያለባቸውን ትክክለኛ ነገሮች እንዲያሳየኝ እፈልጋለሁ። 11 ያህዌ ሆይ እንደምታደርገው ቃል እንደገባኸው ለመሞት በምቀርብበት ጊዜ አድሰኝ፤ ምክንያቱም አንተ ጻድቃ ነህ! 12 እኔ አንተን የማገለግል ነኝ፤ እንደምታደርገው ቃል እንደገባኸው ስለዚህ በታማኝነት ስለምትወደኝ ጠላቶቼን ግደል፤ የሚጨቁኑኝንም ሁሉ አስወግዳቸው።
Chapter 144
1 ከአደጋ እንደምጠበቅበት ግዙፍ ዓለት የሆነውን ያህዌን እወድሳለሁ! ጦርነቶችን ለመዋጋት ልጠቀምባቸው እንድችል እጆቼን ያሰለጥናቸዋል፤ በውጊያ ውስጥ ቀስት መተኮስ እንድችል ጣቶቼን ያሰለጥናቸዋል። 2 ቃል እንደገባው የሚከልለኝ እርሱ ነው፤ እርሱ ከአደጋ እንደምጠበቅበት ምሽግ ነው፤ ጋሻዎች ወታደሮችን እንደሚከልሉ ይከልለኛል፤ መሸሸጊያ ቦታም ይሰጠኛል። ሌሎች ሕዝቦችን አሸንፎ ከኃይሌ ሥር ያደርጋቸዋል። 3 ያህዌ ሆይ እኛ ሰዎች ከዚህ ግቡ የማንበል ነን! ለምንድነው የምታስበን? ለሰዎች ትኩረት መስጠትህ እኔን ያስገርመኛል። 4 የምንኖርበት ጊዜ እንደ ንፋስ ሽውታ ያህል አጭር ነው፤ የሕይወት ዘመናችን እንደ ጥላ ይጠፋል። 5 ያህዌ ሆይ ሰማይን ቀድደህ ክፈትና ውረድ! ጭስ ከውስጣቸው እንዲወጣ ተራራዎችን ንካቸው! 6 ጠላቶችህ እንዲሸሹ መብረቅ ብልጭታ እንዲሰጥ አድርግ! ቀስትህን ወንጭፍባቸውና እንዲሸሹ አድርግ። 7 ጠላቶቼ በዙሪያዬ እንደ ጎርፍ የሆኑ ያህል ነው፤ እጅህን ከሰማይ ወደ ታች ዘርጋና ከእነርሱ ታደገኝ። የሌሎች አገራት ሰዎች ናቸው። 8 ዘወትር ሐሰትን የሚናገሩ በፍርድ ቤት እንኳን እውነትን ለመናገር ከማሉ በኋላ ውሸት ይናገራሉ። 9 እግዚአብሔር ሆይ ላንተ አዲስ መዝሙር እዘምርልሃለሁ። ስዘምርልህም አስር ክር ያለውን በገናዬን እጫወታለሁ። 10 ነገሥታት ጠላቶቻቸውን እንዲያሸንፉ ታስችላቸዋለህ፤ እኔ እንደማደርገው የሚያገለግሉንም ትታደጋለህ። 11 እነዚያ ክፉ ሰዎች በሚይዟቸው ሰይፎች ከመገደል እንድታድነኝ እጠይቅሃለሁ። ዘወትር ውሸትን ከሚናገሩና እውነቱን እንደሚናገሩ በከበደ ሁኔታ ሲያስታውቁ በፍርድ ቤት ውስጥ ቀኝ እጆቻቸውን ከሚያነሱ ከእነዚያ የውጭ እንግዳ ሰዎች ኃይል ታደገኝ። 12 ወንድ ልጆቻችን ሙ ሰው ወደ መሆን እንዲያድጉ እመኛለሁ ሴቶች ልጆቻችን ደግሞ በቤተ መንግሥት ማዕዘኖች እንድሚቆሙ ምሰሶዎች ቀጥ ያሉና ረጃጅም ሆነው እንዲያድጉ እመኛለሁ። 13 መጋዘኖቻችን በበርካታ የተለያዩ ሰብሎች እንዲሞሉ እመኛለሁ። በመስካችን ያሉ በጎች አእላፋት ጠቦቶችን እንዲወልዱ እመኛለሁ። 14 ላሞቻችን አንዳችም ጭንገፋ ሳያጋጥማቸው ወይም ሲወለዱ ሞት ሳያጋጥማቸው በርካታ ጥጃዎችን እንዲወልዱ እመኛለሁ። በውጪ ሠራዊቶች ወረራ በጎዳናዎቻችን ላይ ሰዎች በጭንቀት የሚጮኹበት ምንም ጊዜ እንዳይኖር እመኛለሁ። 15 እንደዚያ ዓይነት መልካም ነገሮች ለአንድ ሕዝብ ከሆኑለት ሕዝቡ እጅግ ደስተኛ ይሆናሉ። አምላካቸው ያህዌ የሆነላቸው ሕዝብ ደስተኛ የሚሆኑ ናቸው!
Chapter 145
1 አምላኬና ንጉሤ አንተ እጅግ ታላቅ መሆንህን አውጃለሁ። አሁንና ለዘለዓለምም እወድስሃለሁ። 2 በየዕለቱ እወድስሃለሁ፤ አዎን ለዘለዓለም እወድስሃለሁ። 3 ያህዌ ሆይ አንተ ታላቅ ነህ፤ እጅግ በጣምም ልትወደስ ይገባሃል። ምን ያህል ታላቅ መሆንህን ሙሉ በሙሉ መገንዘብ አንችልም። 4 ወላጆች ለልጆቻቸው አንተ ያደረግሃቸውን ነገሮች ይነግራሉ፤ ስለ ታላላቅ ሥራዎችህ ለልጆቻቸው ይነግራሉ። 5 እጅግ የከበርክና ግርማዊ መሆንን አስባለሁ፤ አስደናቂ ሥራዎችህን ሁሉ አሰላስላለሁ። 6 ሰዎች ስለ ታላቅና አስፈሪ ሥራዎችህ ይናገራሉ፤ እኔም እጅግ ታላቅ መሆንን አውጃለሁ። 7 አንተ ለእኛ እጅግ መልካም መሆንህን ሰዎች ያስታውሳሉ፤ ይናገራሉም። ዘወትር ትክክለኛውን ነገር ማድረግህንም በደስታ ይዘምራሉ። 8 ያህዌ ሆይ ለእኛ የቸርነትንና ምሕረትን ሥራ ሠርተሃል፤ ፈጥነህም አትቆጣም። እንደምታደርገው ቃል እንደገባኸው በታማኝነት እጅግ በጣም ትወደናለህ። 9 ያህዌ ሆይ አንተ ለሰው ሁሉ መልካም ነህ፤ ለሠራኸው ነገር በሙሉ የምሕረትን ሥራ ትሠራለህ። 10 ያህዌ ሆይ የፈጠርካቸው ፍጥረታት በሙሉ ያመሰግኑሃል፤ ሕዝብህም ሁሉ ይወድሱሃል። 11 እንደ ንጉሥ አገዛዝህ እጅግ የከበረ መሆኑን ለሌሎች ይነግራሉ፤ እጅግ ኃይለኛ መሆንህንም ይነግራሉ። 12 ያንን የሚያደርጉት ሰው ሁሉ ስለ ኃይለኛ ሥራዎችህና በእኛ ላይ በክብር የምትገዛ መሆንህን ሰዎ ች ሁሉ እንዲያውቁ ነው። 13 ንጉሥ መሆንህ ከቶም አይቀርም፤ አገዛዝህም ከመጀመሪያ እስከ መጨረሻ በትውልዶች ሁሉ ላይ ነው። 14 ያህዌ ሆይ ተስፋ የቆረጡትን ሁሉ ትረዳለህ፤ የተደነቃቀፉትንና የወደቁትን ሁሉ ታነሳቸዋለህ። 15 የፈጠርካቸው ፍጥረታት በሙሉ ምግባቸውን እንደምታዘጋጅላቸው ይጠባበቃሉ፤ አንተም በሚያስፈልጋቸው ጊዜ ምግብን ትሰጣቸዋለህ። 16 ለሕያዋን ፍጥረታት በሙሉ በልግስና ምግብ ትሰጣለህ፤ እንዲረኩም ታደርጋቸዋለህ። 17 ያህዌ የሚያደርገው ማንኛውንም ነገር በትክክል ያደርገዋል። የሚሠራውንም ነገር ሁሉ በምሕረት ይሠራዋል። 18 ያህዌ እርሱን የሚጠሩትን ሰዎች ሁሉ በእውንት በልብ ቅንነት የሚጠሩትን ሁሉ ይቀርባቸዋል። 19 ለእርሱ ከፍተኛ አክብሮቶ ላላቸው ሁሉ የሚያስፈልጋቸውን ይሰጣቸዋል። ሲጠሩትም ሰምቶ ያድናቸዋል። 20 ያህዌ የሚያወዱትን ሁሉ ይከልላቸዋል። ክፉ ሰዎችን ሁሉ ግን ያስወግዳቸዋል። 21 ዘወትር ያህዌን አወድሳለሁ፤ ሁሉን ነገር ፍጹም አድርጎ ስለሚሠራ በሁሉም ሥፍራ ያሉ ሰዎች ሁሉ ለዘላለም እንዲያወድሱት እመኛለሁ።
Chapter 146
1 ያሕዌ ይመስገን፣ ያሕዌን ከልቤ አመሰግናለሁ። 2 በሕይወቴ ዘመን ሁሉ ያሕዌን አመሰግናለሁ፣ በቀረልኝ ዘመን ሁሉ ለአምላኬ እዘምራለሁ። 3 እናንተ ሰዎች፣ በመሪዎቻችሁ አትታመኑ፣ በሰዎች አትታመኑ ሊያድኑአችሁ አይችሉምና። 4 በሞቱ ጊዜ ሬሳቸው ይበሰብሳል፣ ተመልሰውም አፈር ይሆናሉ። ከሞቱ በኋላ፣ ሊያደርጉት ያቀዱትን ማድረግ አይችሉም። 5 እግዚአብሔር የረዳቸው ያያዕቆብን አምላክ እግዚአብሔርን የሚያመልኩ እንዴት የታደሉ ናቸው? እነዚህ ሰዎች ያሕዌን አምላካቸውን እንዲያድናቸው በመተማመን የሚጠባበቁ ናቸው። 6 እርሱ ሰማይንና ምድን ፈጥሮአል፣ ውቅያኖስን እና በውስጡም ያሉትን ፍጥረታት ፈጥሮአል። እርሱ ቃል የገባውን ሁልጊዜ ይፈጽማል። 7 ለተበደሉት በቅንነት ይፈርዳል፣ ለተራቡትም ምግባቸውን ይሰጣቸዋል። በእስር ቤት ያሉትንም ነፃ ያወጣቸዋል። 8 ዐይነ ስውሮችንም እንዲያዩ ያደርጋቸዋል። የወደቁትን ያነሳቸዋል። ቅዱሳንን ይወድዳል። 9 ያሕዌ በምድራችን የሚኖሩትን የሌሎች አገሮች ሰዎችን ይጠብቃል፣ መበለቶችንና ወላጅ አልባዎችን ይረዳል። ኃጢአተኞችን ግን የሚያደርጉትን ክፉ ሥራ ያጠፋል። 10 ያሕዌ ለዘላለም ንጉሣችን ነው፣ እናንተ የእስራኤል ሕዝቦች አምላካችሁ ለዘላለም ይገዛል! ያሕዌ ይመስገን።
Chapter 147
1 ያሕዌ ይመስገን! ለአምላካችን የምስጋና መዝሙር መዘመር መልካም ነው። የሚያስደስትና ትክክለኛም ነገር ነው። 2 ኢየሩሳሌም ጠፍታ ነበር፣ ነገር ግን ያሕዌ ኢየሩሳሌምን እንደገን ኣእንድንገነባት አስቻለን። ወደ ሌላ ምድር ተወስደው የነበሩትን ሕዝብ መልሶ አምጣቸው። 3 ተስፋ የቆርጡትን እንደገና በተስፋ እንዲሞሉ እበረታታቸው፣ ይኽም ቆስለው የነበሩ እንደታከሙ ያህል ነው። 4 እርሱ የከዋክብቶችን ቁጥር ያውቃል ለሁሉም ስም ይሰጣቸዋል። 5 ያሕዌ ታላቅ ነው እጅግም ብርቱ ነው፣ የእርሱን ማስተዋል የሚያውቀው አንድም የለም። 6 ያሕዌ የተጨቆኑትን ያነሣቸዋል፣ ኃጢአተኞችን ወደ ምድር ይጥላቸዋል። 7 ያሕዌን በዝማሬ አመስግኑት፣ በመሰንቆም አመስግኑት፣ በዜማ አምላካችንን አመስግኑ። 8 ሰማይን በደመና ጋረደው፣ ዝናብንም ወደ ምድር ላከ፣ ሣርንም በተራሮች ላይ አበቀለ። 9 ለአራዊትም የሚፈልጉትን ምግብ ይሰጣቸዋል፣ የቁራዎች ጫጩቶች ተርበው ሲጮኹ እርሱ ምግባቸውን ይሰጣቸዋል። 10 በፈረሶች ኃይል አይገረምም፣ በሰዎችም ፈጣን ሩጫ አይደሰትም። 11 እርሱ የሚደሰተው ለእርሱ አክብሮት ባላቸው ሰዎች ነው፣ እርሱን በመተማመን የሚጠባበቁ እርሱ በገባላቸው ተስፋ መሰረት ይወድዳቸዋል። 12 እናንተ የኢየሩሳሌም ሕዝቦች ያሕዌን አመስግኑ! አምላካችሁን አመስግኑ! 13 ከተማችሁን ጠብቆአልና በሮቿንም ጠንካሮች አድርጎአል፣ በውስጧም የሚኖሩትን ሕዝቦች ይባርካል። 14 ሕዝባችሁን ጤናማ ያደርጋል። የተትረፈረፈና መልካም የሆነ ስንዴን ይሰጣችኋል። 15 ነገሮች ሁሉ በምድር ላይ ይሆኑ ዘንድ ያዝዛል፣ ቃሎቹ ወደሚልካችው ሥፍራዎች በፍጥነት ይደርሳሉ። 16 ምድርን እንደ ነጭ ጥጥ ይሸፍኑ ዘንድ ብናኝ በረዶን ያወርዳል፥ ነፋስ አምድን እንደሚበትን ጎመን በምድር ላይ ይበትነዋል። 17 በረዶውን እንደ ፍርፋሪ ያወርዳል፣ ከበረዶውም ቅዝቃዜ የተነሣ ማንም ጸንቶ መቆም አይቻለውም። 18 ነገር ግን ነፋስን አንዲነፍስ ያዝዛል፣ እርሱም ይነፍሳል፣ በረዶውም የቀልጣል፣ የውሃ ፈሳሽ ሆኖ በመፍሰሻው ይፈስሳል። 19 መልእክቱን ለያዕቆብ ዘሮች ይልካል፣ ለእስራኤል ሕዝቦች ያወጀውንና የወሰነውን ይነግራቸዋል። 20 ይህንን ለማንም ሌላ ሕዝብ አልተናገረም፣ ሌሎች ሕዝቦች የእርሱን ሕጎች አያውቁም። ያሕዌ ይመስገን!
Chapter 148
1 ያሕዌን አመስግኑ! በሰማይት ያላችሁ እናንተ መላእክት፣ አመስግኑት! በላይ በሰማይ ያላችሁ መላእክት አመስግኑት! 2 የእርሱ የሆናችሁ መላእክቱ ሁላችሁ፣ አመስግኑት! የያሕዌ ሠራዊት በሙሉእ አመስግኑት! 3 ፀሐንያ ጨረቃ፣ እናተም ልታመስግኑት ይገባል! እናንት የምታብረቀርቁ ከዋክብት፣ አምስግኑት! 4 ሰማየ ሰማያት አምስግኑት፣ ከሰማይ በላይ ያለ ውሃ፣ አመስግኑት። 5 እነዚይ ሁሉ እንዲያመሰግኑት እፈልጋለሁ፣ ምክንያቱም በእርሱ ትእዛዝ ይኖራሉና፣ ተፈጥረዋልምና። 6 እርሱ በወሰነላቸው ሥፍራ ተቀምጠዋል፣ በዚያ ለዘላለም እንዲሆኑ አዝዞአቸዋል፥ የእነርሱን ትእዛዛ እምቢ ሊሉ አይችሉም። 7 በምድር የሚኖሩ ሁሉ ያሕዌን ያመስግኑ! እናንተ ታላላቅ ፍጥረታት በጥልቅ ውቅያኖስም የምትገኙ ፍጥረታት ሁሉ፣ 8 እሳትና በረዶ፣ አመዳይና ውርጭእርሱን የሚታዘዙ አውሎ ነፋሳት፣ ያሕዌን እንድታመሰግኑ እናገራችኋለሁ! 9 ተራሮች ኮረብቶች፣ የፍሬ ዛፎችና ዝግባም ሁሉ፣ 10 የዱር አራዊትና ተንቀሳቃሾችና የሚበርሩ ወፎች፣ በምድር ላይ የሚሳቡ ሁሉ፣ እናንተ ሁሉ ያሕዌን እንድታመሰግኑ እናገራችኋለሁ! 11 የምድር ነገሥታትና የምትገዙአቸው ሕዝቦች በሙሉ፣ እናንተ መስፍንቶችና ገዢዎች በሙሉ፣ 12 ጎልማሶችና ቆነጃጅት፣ ሽማግሌዎችና ልጆችን ሁላችሁ ያሕዌን አመስግኑ! 13 እርሱ ከሁሉ በላት ታላቅ ነውን እነዚህ ሁሉ እርሱን እንዲያመሰግኑ እፈልጋለሁ። ኃይሉ በምድርና በሰማይ ያሉትን ሁሉ ይቆጣጠራል። 14 የእርሱ ሕዝብ አድርጎናል፣ እኛ እስራኤላውያን የእርሱ ውድ ሕዝቦች እርሱን ማመስገን አለብን፣ ስለሆነም ያሕዌን እናመስግን!
Chapter 149
1 ያሕዌን አመስግኑ! ለያሕዌ አዲስ ዝማሬን ዘምሩ፣ ለእርሱ ታማኝ የሆኑ ሰዎ ች በተሰበሰቡ ጊዜ ሁሉ ያመስኑት። 2 እናንተ የእስራኤል ሕዝቦች፣ የፈጠራችሁ እግዚአብሔር ለእናንተ ስላደረጋቸው ነገር ሁሉ ደስ ይበላችሁ! እናንተ የኢየሩሳሌም ሕዝቦች፣ ንጉሣችሁ እግዚአብሔር ስላደረገላችሁ ነገር ሁሉ ሐሴት አድርጉ! 3 ያሕዌን በከበሮና በሽብሸባ በበገናም አመስግኑት! 4 ያሕዌ በሕዝቡ ደስ ተሰኝቷል፣ ጠላቶቻቸውን እንዲያሽዐንፉ በመርዳት ያከብራቸዋል። 5 ሕዝቡ በጦርነት አሸንፈዋልና፣ የእግዚአብሔር ሕዝብ ደስ ይላቸዋል ሌሊቱን ሙሉ በደስታ ይዘምራሉ። 6 እግዚአብሔርን በታላቁ ድምፅ ያመሰግናሉ፣ ነገር ግን የተሳሉሰይፎቻቸውን በእጆቻቸው መያዝ አለባቸው። 7 እግዚአብሔርን የሚያመልኩትን መንግሥታት ወታደሮችን ለማጥቃት ሕዝቦቻቸውንም ለማሸነፍ እንዲዘጋጁ ይጠቀሙባቸዋል። 8 የአሕዛብን ነገሥታት በሰንሰለት ሌሎች አለቆቻቸውን በእግር ብረት ያስሩአችዋል። 9 የእነዚያን መንግሥታት ሕዝቦች እግዚአብሔር እንዲጻፍ ባደረገው ፍርድ መሰረት ይፈርዱባቸዋል እያንዳንዱም የእግዚአብሔርን ሕዝብ ያከብራል! ያሕዌ ይመስገን!
Chapter 150
1 ያሕዌን አመስግኑ! እግዚአብሔርን በመቅደሱ አመስግኑ! በሰማይ በኃያል ምሽት አመስግኑት! 2 ስለ ሠራው ኃያል ሥራው አመስግኑት፣ እርሱ ታላቅ ነውና አመስግኑት። 3 መለከትን በታላቅ ድምፅ በመንፋት አመስግኑት፣ በበገና እና አነስተኛ አውታር ባላቸው የሙዚቃ መሣሪያዎች አመስግኑት! 4 በከበሮ እና በሽብሸባ አመስግኑት። አውታር ባላቸው የሙዚቃ መሣሪያዎችና በዋሽንት አመስግኑት! 5 ድምፁ መልካም በሆነ ጸናጽል አመስግኑት፣ ድምፁ ከፍ ባለ ጸናጽል አመስግኑት! 6 ሕያዋን ፍጥረታት ሁሉ ያሕዌን እንዲያመሰግኑ እፈልጋለሁ! ያሕዌ ይመስገን! front